Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 16 049 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 274,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 238 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 16 049 名订阅者。
根据 30 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 511,过去 24 小时变化为 3,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 23.32%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.33% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 742 次浏览,首日通常累积 1 658 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 29。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 31 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
16 049
订阅者
+324 小时
+1077 天
+51130 天
帖子存档
ሆሣዕና
የሰሞነ ሕማማት የመጀመሪያው ቀን ሆሣዕና ይባላል፤ ትርጉሙም ‹‹እባክህ አሁን አድን አንድም መድኃኒት›› ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት ጌታችን የማዳን ሥራውን ወደሚፈጽምባት ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ ቤተ ፋጌ ሲደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ ‹‹ያስፈልጉኛልና የታሠሩትን አህያና ውርንጫ ይዛችሁልኝ ኑ፡፡›› ብሎ ላካቸው፡፡ በምስጢሩም የአዳምን ልጆች ከዲያብሎስ ቁራኝነት ሊፈታ እንደ መጣ ለማጠየቅ ነው፡፡ እነርሱም እንደታዘዙት መጡ፤ ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ሲሆን 14ቱን በእግሩ፣ 2ቱን በአህያ ሄዶ፣ ቤተ መቅደሱን 3 ጊዜ በውርንጫላዋ ከዞረ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፡፡
ቀድሞ በነቢያት ዘመን ጸብዕ (ጥል) በሆነ ጊዜ በፈረስ ተቀምጠው የጦር ዕቃ ይዘው ይታዩ ነበር፤ ዘመነ ሰላም በሆነ ጊዜ ደግሞ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታያሉ፤ እርሱም ‹‹ዘመነ ሰላም ይዤላችሁ›› መጣሁ ሲል በአህያ ተቀምጦ መጣ፡፡ (ስለ ሰላምሽ የሚሆነውን አንቺስ ብታውቂ … /ሉቃ. 19፥24/) ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስም በትንቢቱ በአህያ እንደሚመጣ ተናግሮ ነበር /ዘካ. 9፥9/፡፡
በግራና በቀኝ የነበሩትም ‹‹እንኳን አንተ የተቀመጥክባትም አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም›› እያሉ ግማሹ ልብሱን ግማሹ የዘንባባ ዝንጣፊ አነጠፉለት፡፡ አብርሃም ይስሐቅን፣ ይስሐቅ ደግሞ ያዕቆብን በወለዱ ጊዜ፣ እስራኤል ከግብጽ በወጡ ጊዜ፣ ዮዲት ሆሎፎርኒስን በገደለች ጊዜ ዘንባባ ይዘው አመስግነው ነበር፤ በዚያ ልማድ ጌታችንንም ዘንባባ ይዘው ‹‹ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ሆሣዕና በአርያም›› እያሉ አመሰገኑት፡፡
ከዚህ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በዚያ ይሸጡ ይለውጡ የነበሩትን ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት›› ብሎ በመቆጣት የለዋጮችን ገበታ እየገለበጠ አስወጣቸው፡፡ አይሁድም ሕፃናት ሲያመሰግኑ ሰምተው በቅንአት በታወረ ልቦናቸው ‹‹ዝም አስብላቸው እንጂ›› አሉት፡፡ ጌታችንም ‹‹ከሕፃናትና ከሚጠቡ አፍ ምስጋና ለራስህ አዘጋጀህ›› /መዝ. 8፥2/ የሚለውን የመጽሐፍ ቃል ጠቅሶ አሳፍሯቸዋል፡፡ በሌላም አንቀጽ እነሱ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ሲያመሰግኑ አይተው አፍረዋል፡፡ይህ በዓል ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዓበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው፡፡
ልዩ ማስታወሻ፤ የማኅሌቱን ሥርዐት በበዓታ(በታች ቤት)ና በዐቢየ እግዚእ(በላይ ቤት) አብነት የምትቆሙ አድባራት እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትቆሙበት ዘንድ፤ የሚለያዩባቸውን ዘበዐታና ዘዐቢየ እግዚእ በሚል አስቀምጠንላችኋል፡፡
+*" ሰማዕታተ ኢትዮጵያ "*+ (በዛሬዋ በሚያዝያ 11 ቀን የኢትዮጵያ ሰማዕታት በሊብያ አረፉ፤ ይህም የሆነው በሚያዝያ 11 2007 ዓ.ም. ሲሆን፤ አይሲስ በተባሉ ተንባላት ኢትዮጵያውያኖቹ ክርስትናቸውን እንዲክዱ፤ ማዕተባቸውን እንዲበጥሱ ቢጠይቋቸውም እምቢ በማለታቸው፤ ሓሳባቸውን ለማስቀየር በግፍና በመከራ፤ በውኃ ጥምና በረሃብ ቢቀጧቸውም ልባቸውን ለአምላካቸው ያጸኑ መኾናቸውን ሲረዱ አንገታቸውን በሰይፍ መቷቸው፡፡)
አመ ዐሡሩ ወአሚሩ ለሚያዝያ በዛቲ ዕለት አዕረፉ ሰማዕታተ ኢትዮጵያ:: በረከቶሙ የሃሉ ምስሌነ ለዐለመ ዐለም አሜን፡፡
ከመዝ ኮነ በውስተ ሀገረ ሊብያ በዕሥራ ምዕት ወሰብዐቱ ዐመተ ምሕረት፡፡ በአሜሃ ዘመን ተንሥኡ ተንባላት እለ ስሞሙ አይሲስ በውስተ ሀገረ ኢራቅ ወሶርያ ወሊብያ ወየመን፡፡ አሐዙ ይቅትሉ ሰብአ ዘረከቡ ወፈድፋደሰ እለ ኮኑ ክርስቲያነ በእምነቶሙ፡፡
ብዙሓን ክርስቲያን ተመትሩ አርእስቲሆሙ በአይሲስ ወተወክፉ አክሊለ ስምዕ እምእላ ሀገራት፡፡ በዝ ዘመን ውእቱ ዘረከቦሙ አይሲስ ለሰብአ ኢትዮጵያ በውስተ ሀገረ ሊብያ እንዘ የሐውሩ ኀበ ሀገረ ኢጣልያ በእንተ መፍቅደ ልቦሙ፡፡ እሉ ከሀድያን ውሉደ ሰይጣን ወአራዊተ ገዳም አሐዝዎሙ ወአዘዝዎሙ ወአፍርሕዎሙ ከመ ይክሀዱ ስሞ ለኢሱስ ክርስቶስ፡፡
ወእምዝ ዘበጥዎሙ በዘዚአሁ ዝብጠታተ በእንተ ዘኮኑ ክርስቲያነ ርእዮሙ ማዕተበ ክሣዶሙ፡፡ ውእቶሙሰ አበዩ ይእዜኒ ክሂደ ሃይማኖቶሙ እመኒ አመከርዎሙ በረሐብ ወጽምዕ ወበካልኣን ኵነኔያት፡፡ ሶበ አበዩ ክሂደ ወሰድዎሙ ኀበ ምድረ በድው ኀበ አልቦ እክል ወማይ ከመ ይእመኑ እምጽንዐ ረሐብ ወጽምዕ፡፡
ወእምዝ ጠየቅዎሙ ከመ ይብትኩ ማዕተበ ክሣዶሙ ወይክሀዱ ስሞ ለእግዚአብሔር አምላኮሙ፡፡ እሉሰ ሰማዕታት ይእዜኒ አበዩ ክሂደ ስሞ ለፈጣሪሆሙ፡፡ አዲ ይቤልዎ ለአይሲስ "ኦ አይሲስ ለእመ ክህልከ ቀቲሎታ ለሥጋነ ኢትክል ቀቲሎታ ለነፍስነ፡፡ ኢንፈርሕሂ ወኢንደነግጽ እምብልሐ ሰይፍከ እስመ አቅዲሙ ነገረነ አምላክነ እንዘ ይብል ኢትፍርሕዎሙ ለእለ ይቀትሉ ሥጋክሙ ወለነፍስክሙሰ ኢይክሉ ቀቲሎታ፡፡"
አዲ ይቤለነ በውስተ ወንጌሉ ቅዱስ እስመ ኵሉ ዘከቀተለክሙ ይመስሎ ከመ ዘመሥዋዕተ ያበውእ፡፡ ይእዜኒ አንተ ላእኩ ለዲያብሎስ ፈጽም በላዕሌነ መልእክተከ ሰይጣናዌ ወአብእ መሥዋዕተከ ርኩሰ ለእምላክከ ሰይጣናዊ፡፡ ንህነኒ ናበውእ ክሣደነ ንጹሐ ለእምላክነ ዘፈጠረነ እስመ ነአምር ዘከመ ያነሥአነ በትንሣኤሁ ቅድስት አመ ዳግም ምጽአቱ፡፡
አሲስኒ አላዊ መተሮሙ አርእስቲሆሙ በሰይፍ ወኮኑ ሰማዕተ በከመ ዛቲ ዕለት፡፡ ወእምዝ ተሀውከት ኵላ ኢትዮጵያ ወኵላ ዐለም እስመ ትርእየ ትእይንተ ጥብሐቶሙ ለሰማዕታት በመስኮተ ትእይንት፡፡ ኵሎሙ ሰብአ ኢትዮጵያ አስቆቀዉ ወበከዩ ብካየ መሪረ እንዘ ይገብሩ ሰላማዌ ትእይንተ በበአዕዋዲሁ ወበበፍኖቱ፡፡
ወይብሉ በበቃሎሙ "አይሲስ አይሲስ እንተ ትቀትሎሙ ለሰማዕታት: ወታውሕዝ ደመ ንጹሓን በበፍናዊሁ ከመ ደመ አክልብት: ይደልወከ ትቁም ውስተ ዐውደ ፍትሕ ሰማያዊ፡፡"
በዝንቱ ዘመን ቈስለ ልቡ ለህዝብ በሐዘነ ሥጋ እስከነ ይብል "ፍትሐ ጽድቅ ዘዐርገት ውስተ ሰማይ ከመ ትንበር ምስለ ዘፈጠራ እግዚአብሔር እስመ ኢረከበት ውስተ ዛቲ ምድር ኀበ ትነብር ወኀበሂ ታጸልል፡፡ ናሁ ይጸርሕ ደሞሙ ለሰማዕታት ቅድመ ገጹ ለኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይረድ ፍትሐ ርትዕ ዲበ ምድር ወይሠረው አሲስ እምውስተ ገጻ ለምድር፡፡"
በረከቶሙ: ወጽንዐ ገድሎሙ ለእሉ ሰማዕታት ይሕድር ላዕሌነ ለዐለመ ዐለም አሜን፡፡
**ሰላም ለክሙ በቃለ ማሕሌት ወእንዚራ፡፡
ምስለ ሰማዕታት ዘግብጽ መከራቲክሙ ዘሐብራ፡፡
ቅዱሳን ሰማዕታት ዘኦርቶዶሳዊት ሐራ፡፡
እፎ ክህልክሙ ተዐግሦ ጽኑዕ መከራ፡፡
እስከ ክሳውዲክሙ በአሲስ ተመትራ፡፡
(በአንድ ስሙን ባልጠቀሰ /ባልታወቀ/ ጸሓፊ የተጻፈ)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ሰማዕታት ከኾኑት መካከል የቂርቆስ ልጆች አብዛኛው ስላሉበት የሚከተለው ግጥም ተገጥሞላቸዋል፡፡
#የቂርቆስ ልጆች
የቂርቆስ ልጆች መች ልብ አላቸው፤
ሁሌም ሁከት ነው የለት ሥራቸው፤
ይኸው ዛሬ ደግሞ እንደለመዱት፤
የኢትዮጵያን አንጀት በኀዘን ጎመዱት፡፡
የቂርቆስ ልጆች ያውቃሉ አድማ፤
ሌላው አይሸሽም አንዱ ሲደማ፤
ይኸው ባደባባይ ጎን ለጎን ቆመው፤
ሀገር አሳመሙ እነሱ ታመው፡፡
ድሮም አልወደው እኔ ያንን ሰፈር፤
ሰው እንዴት ይሠራል የሕፃን ነገር፡፡
ሕፃኑን ቂርቆስ እያዩ አድገው፤
አይቅርብን አሉ እሱ ያደረገው፡፡
ይኸው እንደ ቂርቆስ እንደ ኢየሉጣ፤
እነሱም አሉ የመጣው ይምጣ፡፡
አይ የቂርቆስ ልጆች፤
ሕፃኑን ሰምታችሁ እናንተም ትሔዱ?
እሱ እንደሆነ ይህ ነው ልማዱ፡፡
እናቱን እንኳን እየጎተተ፤
እንሙት ያለ የወተወተ፤
የሱን ምክር ቃል ስትሰሙ አድጋችሁ፤
ይኼው ይህ ሆነ መጨረሻችሁ፡፡
ሌላ ምን እላለሁ፤!?
እግዜር ይይላችሁ፡፡
የፊጥኝ ታስራችሁ መነዳታችሁን፤
ስለ ክርስቶስ ስም መመስከራችሁን፤
በባሕር ዳርቻ መንበርከካችሁን፤
እንደ በግ በስለት መቈረጣችሁን፤
በጥይት እሩምታ መደብደባችሁን፤
እግዜር ይይላችሁ!፡፡
የሕፃኑ መንገድ ያዋጣል ካላችሁ፤
ወደ እኛ እንዳትመጡ ቤት አለን ብላችሁ፤
ሕፃኑ ካለበት ማረፊያ ይስጣችሁ!፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ፤ ሚያዝያ 13 2007 ዓ.ም.፡፡
እንዲሁም፤
የቂርቆስ ልጆች እነ ሞት አይፈሬ፤
እርግፍ እርግፍ ያሉት እንደ ሾላ ፍሬ፡፡
ስንናፍቀው የነበረው የአንድነት ጕባኤ፤ እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ #በዕለተ_ሆሣዕና_ሚያዝያ_13/2011 ዓ.ም.፤ #ከቀኑ 8-11 ሰዐት፤ #በመናገሻ_ገነተ_ጽጌ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
#የመርሐ ግብሩ አዘጋጆች፤ (የ5ቱ የሰ/ት/ቤቶች የጋራ ጕባኤ)
፠የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤ/ክ ኆኅተ ሰማያት ሰ/ት/ቤት፤
፠የምስካየ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰ/ት/ቤት፤
፠የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት፤
፠የደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ፍቊረ እግዚእ ሰ/ት/ቤት፤
፠የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት፡፡
#የመርሐ ግብሩ አስተባባሪዎች፤ የአራዳና የጉለሌ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት፡፡
/በ5ቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀድሞ አገልጋይ የነበራችሁና የተማራችሁ፤ እንዲሁም አሁን በመማርና በማገልገል ላይ የምትገኙ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡/
#ላልሰሙት_ያሰሙ፡፡#ላልሰሙት_ያሰሙ፡፡
*ወንድሞች በጋራ ቢቀመጡ እነሆ ያማረ ነው፤ እነሆ መልካም ነው፡፡
#ምክረ_አበው_ወዝክረ_ቅዱስ_ያሬድ
(በቅዱስ ቊርባን ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች በአበው መምህራን ምላሽ ይሰጥባቸዋል፡፡)፤
#ዐርብ_ሚያዝያ_11_ከምሽቱ_11፡30-2፡00 ሰዐት፡፡
በታላላቅ ገዳማት የሚጸለየው #የመሐረነ_አብ ጸሎት ይደርሳል፥ የቅዱስ ያሬድ ተዓምር ከጥንታዊ ገድሉ ላይ ይነበባል፡፡
እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ በመርሐ ገብሩ ላይ የደብራችን አስተዳዳሪ ይገኛሉ፤ ካህናት በማዕጠንታቸው ያጥናሉ፤ /የዕጣኑ ሽታ ... የናፈቃችሁ ሁሉ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን/፡፡
#አስቸኳይ_አስቸኳይ_SHAREEEEEEEE_ሼርርርርር_ማድረጋችሁን_እንዳትዘነጉ_!!!!!!
በኢሉባቡር ሀገረ ስብከት ቡኖ በደሌ ዞን በገቺ ወረዳ ሴቀቻ በምትባል ቀበሌ ውስጥ ከሌሊት ፲፩ ሰዓት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የሰማዕቱ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ ደረሰበት፡፡
/ፎቶው ላይ የምታዩዋቸው ምዕመናን፤ ከቃጠሎው በኋላ በዕንባ ጭምር የምሕላ ጸሎት ሲያደርሱ ነው፡፡/
የቤተክርስቲያኑ ተራዳኢ በሆነው ወንድም ላይም ያለጥፋቱ ፖሊስ ድብደባ አካሂዷል፡፡
ይግባኝ ለክርስቶስ ፬፡፡ /መድኀኔ ዓለም ሆይ፤ የዛሬውን የኢሉባቡር ሐዘንና መከራ፤ የቤተ ክርስቲያናችን የኀዘንና የመከራ ማብቃያ (ተፍጻሜት) አድርግልን/
#በጅጅጋ፥ በኤጄሬ፥ በከሚሴና በአጣዬ በኢሉባቡር ያለች ጽዮን ቤተ ክርስቲያንን ባሰብናት፥ ድምጿን በሰማናትና ገጿን ባየናት ጊዜ አለቀስን፤
ቤተ ክርስቲያን ሆይ! ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ፤ ባላስብሽ አንደበቴ ከጕሮሮዬ ጋር ይጣበቅ፡፡
ቤተ ክርስቲያንን እስከ መሠረቷ ድረስ ፈጽሞ አፍርሱ የሚሉትን ጎስቋሎችን የሚበቀላቸው አምላካችን ብፁዕ ነው፡፡ /መዝ. 136/
#መዝሙረ ዳዊት 73፤ ‹‹#መቅደስህንም_በእሳት_አቃጠሉ፤ … #አቤቱ_ተነስ_በቀሌንም_ተበቀል፡፡››
‹‹በመንጋዎችህ በጎች ላይ መቈጣትን ተቈጣህ፤
መቅደስህንም በእሳት አቃጠሉ፤
አንተ ፀሐይንና ጨረቃን ፈጠርህ፤
ጠላት እግዚአብሔርን ተገዳደረው፤
ሰነፍ ሕዝብም ስሙን አስቈጣው፤
ዘወትርም የድኾችን ነፍስ አትርሳ፤
አቤቱ ተነስ በቀሌንም ተበቀል፤
ሰነፎች ሁልጊዜ የተገዳደሩህን አስብ፤
የአገልጋዮችህን ቃል አትርሳ፡፡››
ጽዋው ሞልቶ ተትረፈረፈ፤ 4ት ጊዜ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥሉ፡፡
#በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ፤
ምንም በመከራ መካከል ብሄድ አንተ ታድነኛለህ፤
በአሕዛብ ቊጣ ላይ እጆቼን ዘረጋህ፤
ቀኝህም አዳነኝ፤ እግዚአብሔር ይበቀልልኛል፤
አቤቱ ይቅርታህ ለዘለዓለም ነው፡፡ /መዝ. 137/
#ኢይትአጸው አናቅጽኪ፤
ክቡራት ዕንቊ መሠረትኪ፥
ሠናይት ሰላማዊት እንተ ናፈቅራ በጽድቅ፤
መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል፡፡ /ዚቅ ዘሰኔ 21/
(#በተከበሩ_ዕንቊ_የተመሠረትሽ_ቤተ_ክርስቲያን_ሆይ_ደጆችሽ_አይዘጉ፡፡)
##መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ሆይ፤ አሕዛብ አምላካቸው ማን ነው? ወዴትስ አለ? ቢኖር ኖሮ ለምን ዝም አላቸው? እንዳይሉ ስለ አባቶቻችን ብለህ ተለመንን፤ ኀይልና ብርታቱን፥ ፍቅርና አንድነቱን፥ ጥበብና ማስተዋሉን፥ እውነቱንና ፍርዱን አንተ ስጠን፤ አንተ ተበቀልልን፨
#ነቢያተ ፳ኤል ጸሐፉ በመጽሐፎሙ እሙነ፤
ነገረ ሰቈቃው ወላህ በዘመኖሙ ዘኮነ፡፡
ለኢትዮጵያ ውስተ አድያሚሃ አመ በኀጢአት ነበርነ፤
ውስተ ኲሃቲሃ እንዚራቲነ ሰቀልነ፤
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን እምነ፡፡/ነግሥ ዘኅዳር 21/
#በሐ በልዋ ተሳለምዋ፤ ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ፤
ደዩ ልበክሙ ውስተ ኃይላ፤
እንተ ተሐንፀት በስሙ፤ ወተቀደሰት በደሙ፤
ወተአትበት በዕፀ መስቀሉ፤ ጊሡ ኀቤሃ፤
እስመ ኃይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ።
ቤተ ክርስቲያንን ሰላም በሏት፤¬
ቤተ ክርስቲያን ጽዮንን ክበቧት
በመድኀኔ ዓለም በስሙ የታነጸችና የተቀደሰች ናትና፡፡ /ዚቅ ዘሰኔ 21/
#*በአስኬማ ቆብ የተቀዳጃችሁ፤ በፈርጂያ ሰፊ ልብስ የተንቦረቀቃችሁ፤ የመከራ መስቀሉን ምልክት የጨበጣችሁ፤ ….. ለመንግሥትና ለፖለቲካ፤ ለተለያዩ አካላትና ለግለሰቦች ሳይቀር አድር ባይ የሆናችሁ፤ ቤተ ክርስቲያናችንን ያስጎዳችሁ፤ ስትጎዳም እያያችሁ ዝም ያላችሁ፤ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አንስቶ እስከ አናጎንስጢስ መዐርግ ድረስ ያላችሁ፤
*የቤተ ክርስቲያናችንን ከመዐርና ከሱካር የጣፈጠውን፥ ከወተትና ከበረዶ የነጻውን ትምህርቷን ግታችሁ የተማራችሁ ሊቃውንትና መምህራን፤ እናት ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚሸረበውን ሴራና ደባ፤ የሚደርሰውን ጥፋትና ውድመት እያያችሁና እየሰማችሁ ባልሰማና ባላየ ያለፋችሁ፤ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለመንግሥት አካላትና ለምዕመናን ትክክለኛውንና እውነተኛውን ትምህርት ያላስተማራችሁና ያልገሰጻችሁ፤
*እምየ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስመ ክርስትና ሰጥታ በአገልግሎቷ ተሳታፊ ያደረገቻችሁ ምዕመናን፤ ነገር ግን ጉዳቷን ሰምተን ለሥጋዊ ሕይወታችን ብቻ እየሮጥን ጉዳቷን እንዳልሰማ ዝም ብለን የከረምን፤
*ቤተ ክርስቲያን ልጆቼ ብላ በሰንበት ትምህርት ቤት ያዋቀረችን ሰንበት ትምህርት ቤቶች፤ የእናት ቤተ ክርስቲያንን ጉዳት የኛ ጉዳት መሆኑ ሁሉ እስኪዘነጋን ድረስ በአብዛኛው ዘመነኛ ሆነው በመጡ መዝሙር የደነዘዝን፤ የሰ/ት/ቤት ዋና ተልእኮ መዘመር ብቻ የመሰለን፤ ………. ፡፡
*በአንድ ላይ ቢደራጁ ራሳቸው ተጠቅመው ይጠቅሙኛል ብላ ያደራጀችን ማኅበራት /ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ/፤ የቤተ ክርስቲያንን ጥፋት ከመታደግ ይልቅ በጠበልና ጠዲቅ ብቻ የተወሰንን፤ የቲሸርት ልብስ መልበስን ትልቁ ግልጋሎት ያደረግን ……
አብዛኞቻችን ዝም አይነቅዝም ያልነው፤ አምላክ ያያል ይፈርድማልና ይህን አትዘንጉ፤ ታሪክም የዘመኑንና የዕለቱን ታሪክ ይቈጥራልና ይህን አትርሱ፤ ዝምታው ይሰበር፤ ሕግ ከቤተ ክርስቲያን ይወጣልና፤ አጥፊዎችን መንግሥት አልቀጣምና በሕጋችን መሠረት አጥፊዎችን እንገሥጻቸው፥ እንቅጣቸው፡፡
#የመንግሥት አካላትም ሥራችሁ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ቀድማችሁ መጠበቅ፥ መከላከልና መቆጣጠር፤ ችግሮች ሲከሰቱም ባስቸኳይ መፍታት እንጂ፤ …… እንደ ሌላ ሀገር መሪ፤ ችግሩ ከተከሰተ በኋላ፥ ሰው ከሞተ በኋላ፥ አብያተ ክርስቲያናት ከተቃጠሉ በኋላ፤ ሮጦ ዜናና ዲስኩር መልቀቅ፤ መግለጫ ማውጣት፤ እንዲሁም ለይስሙላ ያህል ድርጊቱን አጥብቀን እናወግዛለን በማለት ምዕምናንንና ሕዝቡን መሸበብና መደለል ሥራችሁ አይደለም፤ ካልቻላችሁ አልችልም ብሎ ቦታውን መልቀቅ አዋቂነት ነው!!፡፡
#የመንግሥት አካላት፤ ከጠቅላይ ሚንስትር እስከ ቀበሌ ሹም፤ ከመከላከያ እስከ ፌደራል፤ ከክልል ልዩ ኀይል እስከ ፖሊስ፤ ከሚሊሻ እስከ አካባቢ ጠባቂ፤ ….. ቤተ ክርስቲያናችን ስትቃጠል ካልደረሰ፤ ሕዝባችን ሲሞት ካልታደገ፤ ችግርን ካልቀረፈ፤ ጉዳትን ካላከመ፤ የራሱን ልብስ ለብሰው አደጋ ጣዮችን ካልገሰጸና ፈልጎ ካልቀጣ፤ ምን ሊሠራ፥ ምንስ ሊያደርግ፥ ስሙስ ለምን መንግሥት ይባላልን!!!!!????
**በጅጅጋ 13 አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ፤ ካህናትና ምዕመናን በጭካኔ ተገደሉ ዝም አልን
በኤጄሬ 2ት አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ፣ ካህናት ተደበደቡ ዝም አልን፣
በአጣዬ ካራቆሬና ማጀቴ ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለ፡፤ …….…
ዛሬ ደግሞ በኢሉባኑር ቤተ ክርስቲያን፡፡
ከእንግዲህ ወዲያ ግን ዝም አንልም!!!፡፡
ከእንግዲህ ወዲያ ስለ ሃይማኖታችንም ሆነ ስለ ሃገራችን ኢትዮጵያ ዝም አንልም!!!፡፡
አንተ የምትተኛ ንቃ!
#ምን_እናድርግ_የሚለውን_መፍትሔም_አስቀምጡ_አንብባችሁ_ከንፈር_ብቻ_መምጣት_እንዳይሆን፡፡
#SHAREEEEEEEE_ሼርርርርር_ማድረጋችሁን_እንዳትዘነጉ_!!!!!!
*ኦ እግዚኦ አእርፍ ለነፍሳቲሆሙ አኀው ወአኀት እለ አእረፉ በባሕረ ኤርትራ (ቀይ ባሕር)፡፡
**ቀይ ባሕርን አቋርጠው ወደ ሳውዲ ዓረቢያና የመን በጀልባ ቅዳሜ መጋቢት 28 ሌሊት በመጓዝ ላይ የነበሩ 70 ገደማ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የመገልበጥ አደጋ ደርሶባቸው ዐርፈዋል፡፡
***አምላከ አበው መድኀኔ ዓለም ነፍሳቸውን በገነት ከቅዱሳን ጋር ይደምርልን፡፡
ምክረ አበው፤ የዐርብ ጕባኤና ዝክረ ቅዱስ ያሬድ በአንድ ላይ የሚደረጉበት ጕባኤ፤ በምሥጢረ ቊርባን ዙሪያ የሚነሡ ጥያቄዎች የሚመለሱበት፡፡
7 ኒቆዲሞስ.jpg0.55 KB
