ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 622 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 362,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 204 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 622 名订阅者。

根据 08 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 67,过去 24 小时变化为 14,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 8.25%。内容发布后 24 小时内通常能获得 4.62% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 1 288 次浏览,首日通常累积 721 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 12。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

凭借高频更新(最新数据采集于 09 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

15 622
订阅者
+1424 小时
+867 天
+6730 天
帖子存档
እንኳን ለቅድሱ ጊዮርጊስ ስባረ ዓፅሙ (ዝርወተ አጽሙ ) በሰላም አደረሳቹሁ ፠ ዐላውያን ነገሥታት በደብረ ይድራስ ተራራ ላይ የሊቀ ሰማዕቱን ሥጋውንና አጥንቱ በመንኰራኵር ፈጭተው በነፋስ ለበተኑበት፤ ነገር ግን ለአምላካችን የታመነ ሰማዕት በመሆኑ ያረፈበት መሬትና ዕፅዋት ጊዮርጊስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር እያሉ ያመሰገኑበት ነው፡፡ ------------ ....ነገሥታቱም ጊዮርጊስን ሙታኖችን ብታስነሳ በአምላክህ እናምናለን አሉ ፤በጸሎቱ ሙታኖችም አስነሳላቸው በጌታቸንም ስም አምነው በእርሱ ስም አስተማሩ ጥምቀትንም ተቀበሉ ፡፡የቀሩት ነገሥታት ግን ሰይጣናትን ነው ያሳየኸን ብለው ተከራከሩ ፡፡ ※ ከአንዲት እምበለት ቤት ተቀምጦ ምግብ ልትፈልግለት ሄዳ በተመለሰች ጊዜ ቤቷ ላይ ተአምር አየች ፤ የክርስቲያኖች አምላክ በሰው ተመስሎ እኔ ጋር መጣ ብትል ቅዱስ ጊየርጊስም #_እኔ_አምላክ_አይደለሁም_የአምላክ_ባርያ_ነኝ እነጂ አላት፡፡ የአምላክ አገልጋይ ከሆንክ ቸርነትህ እንድትደርሰኝ እለምናለሁ አለችው ልጇንም በመስቀል ምልክት አማትቦበት ከዕውርነት አድኖታል ፡ ※ ንጉሡም ተአምር ማድረጉን በሰማ ጊዜ በመንኰራኵርም ፈጨው ከከተማ ውጪ ወስደው ጣሉት ከሞትም ተነሣ ተመለሶም ወደ ነገሥታቱ ሄደ ፡፡ንጉሡም አድንቆ ይለምንው ጀመር በመንግሥቱ ላይ ሁለተኛ ያደርገው ዘንድ ቃል ገባለት ቅዱስ ጊዮርጊስ እየዘበት ነገ ጠዋት ለአማልክቶች እሰዋለሁ ብሎት አደረ ፡፡ በሚጸልይበትም ጊዜ የንጉሡ ሚስት ሰምታ ጠየቀችው እርሱም ስለ ጌታችን አስተምራት አመነች ፡፡ በማግሥቱም ንጉሡ ሰውን ሰብስቦ እንደሚጠብቀውና እውነት መስሎ በታያት ጊዜ አዘነች ፡፡እርሱም ልጅሽን በምድር ላይ አኑሪው አላት ከዚያም ወደ አጵሎን (ጣዖቱ) ሂድ ወደ እኔም እንዲመጣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እዘዘው አለው ፡፡ ልጁም ድኖ ቅዱሱ እንዳለው ሄዶ አዘዘው ፡፡ በጣዖቱም የነበረው እርኩስ መንፈስ ወጥቶ እኔ ሰውን የማስት እንጅ አምላክ አይደለሁም አለው ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ምድር ትውጠው ዘንድ አዘዛት ወዲያውኑ ዋጠችው ጣዖቱንም ከአገልጋዮቻቸው ጋር አጠፋቸውን ንጉሡም ከወገኖቹ ጋር አፈረ፡፡ ሙሉውን ታሪክ እዚህ ያንብቡ ----> https://t.me/medihanaelem/6273 ፠ እንደ ጎንደር አበራ ጊዮርጊስ ባሉት ክብረ በዓሉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርዶና አድሮ ነው በዓሉ የሚከበረው፡፡ በጎንደር በጥር ወር የሚከበሩ በዓላት ወደ ጥምቀተ ባሕር በመውጣት የሚከበሩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ጥር 18 አበራ ጊዮርጊስ፤ ጥር 21 ሎዛ ማርያም፣ ጥር 22 ቅዱስ ዑራኤል (በዓታ ያለው)፤ ጥር 25 ቅዱስ መርቆሬዎስ (በተለይ በገጠሩ አካባቢ፡፡) እርሱ እንደ ንብ አውራ ፈረሱ እንደ አሞራ፤ ጊዮርጊስ፥ ጊዮርጊስ፥ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያን አደራ፡፡ ሰአል ለነ ጊዮርጊስ፤ ሰማዕተ ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ ዘሐረፀከ ዱድያኖስ፤ ወወገረከ ደብረ ይድራስ፤ ዘዘረወከ በነፋስ፡፡

ዛሬ ከምሽት ጀምሮ ! በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዙሪያ የተመደቡት የመንግሥት ጥበቃዎች ተነሥተዋል። [ ትእዛዙ የማን እንደሆነ ባልታወቀ ሁኔታ ዛሬ ምሽት ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዙሪያ ጥበቃ ሲያደርጉ የቆዩ የመንግሥት የጥበቃ አካላት እንዲነሱ መደረጋቸውን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ገልጸዋል።

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የ"አባ" ሳዊሮስ ፣ የ"አባ" ኤዎስጣቴዎስን እና የ"አባ" ዜና ማርቆስን ማረፊያ ቤት አሸገ ! የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የ"አባ" ሳዊሮስ ፣ የ"አባ" ኤዎስጣቴዎስን እና የ"አባ" ዜና ማርቆስን ማረፊያ ቤት አሽጓል። በትናንትናው ዕለት 3ቱ አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለመናድ እና ሲኖዶሳዊ አንድነትን ለመከፋፈል በማቀድ 26 መነኮሳትን ሾመናል በማለት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል። ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ጉባኤ ከለባቶቹ #የተመደቡበት_ሀገረ_ስብከት_እና_ስማቸው 1.አባ ገ/ማርያም ነጋሳ - አባ ገብርኤል - ምዕራብ ወለጋ 2.አባ ተ/ሃይማኖት ወልዱ - አባ ባስልዮስ - ድሬዳዋ 3.አባ ገብርኤል ወ/ዮሐንስ - አባ ጢሞቴዎስ -ጉራጌ ሶዶ 4.አባ ገ/እግዚአብሔር ታደለ - አባ ጳውሎስ - ምዕራብ አርሲ 5.አባ ሚካኤል ገ/ማርያም - አባ ኤልሳዕ - ከምባታ 6.አባ ኃይሉ እንዳለ - አባ ገሪማ - ምሥራቅ ሐረርጌ 7.አባ ተ/ማርያም ስሜ - አባ ተ/ሃይማኖት - ጉጂ ሊበን 8.አባ ኃ/ኢየሱስ መንግስቱ - አባ ዕዝራ - ከፋ 9.አባ ወ/ኢየሱስ ኢፋ - አባ ኢያሱ - ቄለም ወለጋ 10.አባ ጳውሎስ ከበደ - አባ ዳንኤል - ሀዲያ 11.አባ ኃ/ኢየሱስ ተስፋዬ - አባ በርሱማ - ምሥራቅ ወለጋ 12.አባ ገ/ኢየሱስ ገለታ - አባ ሚናስ - ሆሮ ጉዱሩ 13.አባ ጸጋዘአብ አዱኛ - አባ ኤጲፋንዮስ - ምሁር ገዳም የበላይ ኃላፊ 14.አባ ኃ/ማርያም ጌታቸው - አባ አቤል - ምዕራብ ሐረርጌ 15.አባ ወ/ጊዮርጊስ ኃ/ሚካኤል - በርተሎሚዎስ - ከሚሴ 16.አባ እስጢፋኖስ ገብሬ - አባ ራጉኤል - ባሌ ረዳት ጳጳስ 17.አባ ገ/መድኅን ገ/ማርያም - አባ ዑራኤል - ጎፋ ባስኬቶ 18.አባ ኃ/ሚካኤል ንጉሤ - አባ አኖሬዎስ - ጊኒር 19.አባ አብርሃም መስቀሌ - አባ ኒቆዲሞስ - ዳውሮ,ኮንታ 20.አባ ንዋየ ሥላሴ አክሊሉ - አባ ሀ/ማርያም - ምዕራብ ጉጂ 21.አባ ኪ/ማርያም ቶሎሳ - አባ ተ/ሃዋርያት - ጅማና የም 22.አባ ወ/ማርያም ጸጋ - አባ አብሳዲ - ቦረና 23.አባ አምደሚካኤል ኃይሌ - አባ መርቆሬዎስ - አሩሲ 24.አባ መርሐጽድቅ ኃ/ማርያም - አባ ደቅስዮስ - ጌዴኦ,ቡርጁ,አማሮ 25.አባ ሞገስ ኃ/ማርያም - አባ ኤፍሬም - መናገሻ.ጋራ መ/ዓለምና ,ደ/ፀሐይ ቅ ጊዮርጊስ የበላይ ኃላፊ 26.አባ ገ/ኢየሱስ ንጉሤ - አባ አልዓዛር - ቡኖ በደሌ

#ጥር_15_በ2ት_ዓመት_ከ9ኝ #ወሩ_ሰማዕትነትን_የተቀበለው_ቅዱስ_ቂርቆስ_በ3_ዓመት_ከ1_ወር_ከ3#ቀኑ_አንገቱን_በሰይፍ_ተቆርጦ_ሰማዕትነትን_የተቀበለበት_በዓለ_ዕረፍቱ_ነው፡፡ #በነገታው_በጥር_16ም #እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ_በክብር_ያረፈችበት_ነው #ስምህ_በተጠራበት_ቤተ_መቅደስህ_በታነጸበት_ስዕልህ_ባለበት_ቦታ_ሁሉ_የሕፃናት_እልቂት_የከብት_በሽታ_የእህል_እጦት_ረሀብ_ቸነፈር_አይደርስም የሚል ቃልኪዳንም ጌታችን ገብቶለታል፡፡ #በገባለት ቃል ኪዳንም መሠረት በመዲናችን #በአዲስ_አበባ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን የሰው እልቂት የከበት በሽታ ገብቶ በነበረበት ወቅት የቂርቆስ ደብር #መካነ_ሰማዕት ሲተከል የሰውም በሽታ ርቋል፥ የከብት እልቂትም አቁሟል፡፡ #በጎንደር_ደብረ_መንክራት_ቅዱስ_ቂርቆስ_ቤክ_ደግሞ_#ጽዋ_ማስደፋት_ የሚል ሥርዐት አለ በዚህ ሥርዐትም የሰረቀውን ሰው ቅዱስ ቂርቆስ የሚያጋልጥበትና አሁንም ድረስ የሚታይ አስደናቂ ተዓምር ነው፡፡ ፠ የሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ሲባሉ፤ የተወለደው በዘመነ ሰማዕታት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በኅዳር 15 ቀን ነው፡፡ የትውልድ ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ አንጌቤን ይባላል፡፡ ፠ አንጌቤናይት ብጽዕት ኢየሉጣም ባሏ በሕይወት ባለ መኖሩ በመበለትነት ትኖር ነበር፤ በዘመኑ የነበረው መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን ‹‹ለጣዖቴ ስገጂ›› ብሎ አስገደዳት፡፡ እርሷም ‹‹ሕፃኑ ልጄ መጥቶ ይመስክር›› ብላ ስትናገር ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ‹‹ለጣዖት አንሰግድም፣ ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደው›› ብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፡፡ ፠ ንጉሡም እጅግ ተቆጥቶ 40 ጋን ውኃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ 40 ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ ዘይት፣ ዝፍጥና ሌላም በእጅጉ የሚጎዱ ነገሮችን (ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል) በውስጡ አስጨመረ፤ የእሳቱ ድምፅ እንደ ነጎድጓድ እስኪሰማ፥ ወላፈኑም እንደ ፀሐይ እስኪያንጸባርቅ ድረስ ሆነ፡፡ የፍላቱም ኃይል 14 ክንድ ያህል እየዘለለ ወጣ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ወደዚያ እቶኑ እሳት እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡ በዚያን ጊዜም 11,004 እስረኞች ከእስር ወጥተው እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም ይህን ባወቀ ጊዜ "እናቴ ሆይ ከብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ፤ ድንጋፄም አይደርብሽ" እያለ ከብሉይና ከሐዲስ እየጠቀሰ እንድትጸና አስተማራት፡፡ ፠ እናቴ ሆይ አናንያ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳናቸው እግዚአብሔር እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ውስጥ ሊያድነን ይችላል፡፡ እናት ሆይ ከሚያልፈው ከዚህ ዓለም ጭንቅ ልታመልጭ በሚያልፈው በዘለዓለም እሳት ልትቀጭ ትሻለች፡፡ እናት ሆይ ይህን አትፈልጊ፤ ይቅርብሽ አሁን እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡... እያለ አብዝቶ መከራት፡፡ ነገርግን በዚህም ምክር እናቱን መመለስና ለሰማዕትነት ማዘጋjት አልቻለም፡፡ ከዚህ በኋላ ቂርቆስ ዓይኖቹን ወደሰማይ አቅንቶ መጸለይ ጀመረ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ ይህች ባርያህ ከምትክድ ከሕይወት መጽሐፍ እኔን ፋቀኝ...›› ብሎ ጸለየ፡፡ በዚያን ጊዜ ዲያብሎስ ከእርሷ ሸሽቶ ሄደ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ እንዲህ አለች፤ በመንግሥተ ሰማያት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታህ ኃይል ሰጠኝ፡፡ የሚጠብቀንን ገድላችንን እንፈጽምና ድል እንነሣ›› አለችው፡፡ የብረት ጋኑን ሲነድ ሳየው በምንጭ ላይ በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አየዋለሁና፡፡ እያለች እየነገረችው ሳለ አንሠተው ከብረት ጋኑ ውስጥ ጨመሯቸው፡፡ በውስጡም አንገትን የሚቆለምም ልብን የሚያጣምም ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርንም የሚበጥስ መሣሪያ ነበረበት፡፡ ወዲያውም የራማው ልዑል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ከሰማይ ወረደና የብረት ጋኑን እሳት ፈጽሞ አበረደው፡፡ ከቅዱሳንም አንዱን እንኳን ሳይነካው የብረት ጋን ማቃጠሉና መፍላቱ ፀጥ አለ፡፡ እንደ ውኃም ሆነ፡፡ ፠ ንጉሡም እሳቱ እንዳልጎዳቸው ሲያውቅ ከዚያ አውጥቶ፤ * በአፍና አፍንጫቸው መርዝ ከተተበት፣ ነገር ግን መርዙ ምንም አልጎዳቸውም እንዳውም ምግብ ሆነላቸው፡፡ * ጨውና በርበሬ በዐይናቸው አነደደበት፡፡ አሁንም ምንም አልነካቸውም፡፡ * ዐሥራ አራት የተሳሉና የጋሉ ብረቶች፤ ሰባቱን በእናቱ በኢየሉጣ አካል፥ ሰባቱን በቂርቆስ አካል ውስጥ (ከነዚሁም ሁለቱን በጆሮዎቹ፥ ሁለቱን በዓይኖቹ፥ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ፥ አንዱን በልቡ) ተከሉ፤ አሁንም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ፈወሳቸው፡፡ * በ4 ችንካሮች ላይ አስቀመጧቸው፤ መልአኩ ፈወሳቸው * የራስ ጠጕራቸውን ከቆዳቸው ጋር ገፈው በእሳት ውስጥ ጨመሩት፤ ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጥቶ ፈወሳቸው፡፡ * በመቃን ውስጥ ጨመረው በገመድ ሰቀሏቸው፤ መልአኩ አዳናቸው፡፡ (ሐምሌ 19 ቀን የምናከብረው ክብረ በዓል ከላይ ያሉትን ሁሉ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ለቅዱስ ቂርቆስና ኢየሉጣ የተራዳበትን በማሰብ ነው፡፡) ፠ ንጉሡም በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በብዙ ጭንቅና ሥቃይ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ለ3 ዓመታት አሠቃያቸው፡፡ እነርሱም መከራን እየተቀበሉ በከሀዲው ንጉሥ ፊት የአምላካቸውን ስም እየጠሩ መሰከሩ፡፡ ፠ በመጨረሻም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጋድሎውን ፈጽሞ ጥር 15 ቀን በ3 ዓመት ከ1 ወር ከ3 ቀኑ አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ሰማዕትነትን ተቀበለ፡፡ ሲሰየፍም ከአንገቱም ደም፣ ውኃና ወተት የወጣ ሲሆን ሦስት አክሊላትም ወርደውለታል፡፡ ፠ ሕፃኑም በምድር ላይ አልተቀበረም ይልቁንም ጌታችን በኤልያስ ሰረገላ ሥጋውን አሳርጎለታል፤ ሄሮድስ ላስፈጃቸው 144,000 የቤቴልሔም ሕፃናትም አለቃቸው ነው፡፡ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣም በጥር 16 ቀን ሰማዕትቷን በክብር ፈጽማለች፡፡ በዚሁ ዕለት የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበርተኞች የሆኑ 11,004 ሰዎች የጌታችንን ክብር እየመሰከሩ በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ ፠ #በነገታው_በጥር_16ም #እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ_በክብር_ያረፈችበት_ነው (ምንጭ፤ የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰሌዳ መጽሔት፣ ከገድላት አንደበትና ዝክረ ቅዱሳን) ሥርዐተ ማኅለሌቱን ከዋይዜማው ጀምሮ አዘጋጅተንላችኋል፡፡ ወረቦቹን፣ እስመ ለዓለም፣ አቡንና ሰላሙን በድምፅ ከፈለጋችሁ በቴሌግራም ገጻችን ያገኛሉ፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ቅዱሳን #Saints #ክብረ_በዓላት #Feasts https://youtu.be/3o4wj7Qqcaw...

ስብስብ ስም ዝርዝር የውሸት የተሾሙት ዝርዝር 1. አባ ተክለ ሃይማኖት ።።።።።።። የቀድሞ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ 2. አባ ገብረ እግዚአብሔር ።።።።።። የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረ
+4
ስብስብ ስም ዝርዝር የውሸት የተሾሙት ዝርዝር 1. አባ ተክለ ሃይማኖት ።።።።።።። የቀድሞ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ 2. አባ ገብረ እግዚአብሔር ።።።።።። የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት አስተዳዳሪ 3. አባ ሽኖዳ ።።።።።።።።። አለም ገና ኢየሱስ አስተዳዳሪ 4. አባ ወልደ ጊዮርጊስ ።።።።።።። ወለቴ ዮሐንስ አስተዳዳሪ 5. አባ ገብረ ኢየሱስ ።።።።።። አለም ገና ሚካኤል አስተዳዳሪ 6. አባ ገብረማርያም ነጋሳ ።።።።። የኦሮምያ ቤተ ክህነት መስራች 7. አባ ጳውሎስ ከበደ ።።።።። የሐረር ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የነበረና በተሐድሶነት የተባረረ 8. አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ።።።።።።። የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መጽሐፍ መምህር ይቀጥላል. .....

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ ተሰጠ ። (ኢኦተቤ ቴቪ ጥር ፩፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ) መግለጫውን የሠጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት; ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ : በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው። ቅዱስነታቸው ዛሬ ማለዳ በተሰማው ሕገ ወጥ "ሢመተ ጳጳሳት" ጉዳይ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ በሕገወጥነት የተከናወነ መሆኑን በመግለጽ :- 1. በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል። 2. መንግሥት ክስተቱ በሀገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ ሕጋዊ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል። 3. ምዕመናን ቤተክርስቲያንን ከመቸውም ጊዜ በላይ በንቃት እንዲጠብቁ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።