🛑 ፍሪጅ ደረጃውን ያልጠበቀ (Substandard) መሆኑን የሚያጋልጡ 9 ምልክቶች❗️
======
👉ገበያ ላይ በውጫዊ ውበታቸው እና በዝቅተኛ ዋጋቸው አታለው ከገዛናቸው በኋላ የራስ ምታት የሚሆኑብን ፍሪጆች አሉ።
👉 ፍሪጅ ለመግዛት ይዳችሁ እነዚህን 9 አሳዛኝ ጉድለቶች ካያችሁ አምልጡ አሁን ላይ ውጫዊ ውበታቸውን አስምረው በዝቅተኛ ዋጋ የሚሸጡ አብዛኞቹ ፍሪጆች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ችግሮች አሉባቸው❗️ብዙዎቹ በማስታወቂያ ሀይል ብቻ እየተሸጡ ያሉ ነገር ግን ብዙ ሳይቆዩ ለጥገና እንኳን ስለማይመቹ የሚጣሉ ናቸው❗️
1⃣
. ከአልሙኒየም የተሰራ የውስጥ ቱቦ (Aluminum Coil)
👉ጥራት የሌላቸው ፍሪጆች የውስጥ ቅዝቃዜ ማስተላለፊያ ኮንደንሰር (Condenser) ከመዳብ (Copper) ይልቅ ከአልሙኒየም የተሰራ ነው። አልሙኒየም ቶሎ ዝገት ይበላዋል፣ ይበሳል፣ ጋዝ ያስወጣል። አንዴ ከተበሳም ለመበየድ (ለመጠገን) እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ ፍሪጁን ከጥቅም ውጪ ያደርገዋል።
2⃣
. የቮልቴጅ መዋዠቅን ፈፅሞ አለመቋቋም (Needs External Stabilizer)
👉ዘመናዊ ፍሪጆች ቮልቴጅ ከፍና ዝቅ ሲል ራሳቸውን ተቋቁመው ሲሰሩ፣ ጥራት የሌላቸው ፍሪጆች ግን ትንሽ መብራት ሲዋዥቅ የውስጥ ቦርዳቸው እና ኮምፕሬሰራቸው በቀላሉ ይቃጠላል። ግዴታ ውድ የሆነ ተጨማሪ ስታብላይዘር እንድንገዛ ያስገድዱናል ወይም በየጊዜው የፍሪጁ ራስ የሆነውን ኮምፕረሰር ስንቀይር እንኖራለን።
3⃣
. ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ፍጆታ እና ጩኸት (Non-Inverter)
👉ዘመናዊው 'ኢንቨርተር' (Inverter) ሞተር የሌላቸው ናቸው። እነዚህ ፍሪጆች ሲሰሩ ትልቅ የድምፅ ጩኸት እና ንዝረት ያሰማሉ፤ የኤሌክትሪክ ፍጆታቸው ከፍተኛ ስለሆነ የወሩን የመብራት ቢል ያንራሉ። (በበሩ ላይ ባለው የኤሌክትሪክ ቆጣቢነት መለኪያ 1 ወይም 2 ኮከብ ብቻ ያላቸው ናቸው)።
4⃣
. ተራራ የሚያህል በረዶ ማከማቸት (Direct Cool)
👉'No-Frost' (በረዶ የማያከማች) ሲስተም የላቸውም። በዚህም ምክንያት በፍሪዘሩ ውስጥ ከፍተኛ በረዶ ስለሚሰሩ፣ በየሳምንቱ ፍሪጅ ማጥፋት እና በረዶ ማቅለጥ ግዴታዎ ይሆናል።
5⃣
. ለሀገራችን አየር ንብረት ያልተሰሩ (Wrong Climate Class)
👉በአውሮፓ ቀዝቃዛ አየር ንብረት ታስበው የተሰሩ (Climate Class N ወይም SN) ፍሪጆች ናቸው። እነዚህ ፍሪጆች ሃገራችን ውስጥ በተለይ በበጋ ወቅት ክፍሉ ሲሞቅ ማቀዝቀዝ ያቅታቸዋል፤ ኮምፕሬሰራቸውም ሙቀቱን መቋቋም አቅቶት ቶሎ ይቃጠላል። (ትክክለኛው 'T' ወይም Tropical መሆን አለበት)።
6⃣
. ደካማ ማግኔት እና ስስ መደርደሪያ (Poor Build Quality)
👉የበራቸው ላስቲክ/ማግኔት (Gasket) ደካማ በመሆኑ አየር በቀላሉ ወደ ውጭ ያስወጣሉ፤ ይህም ኮምፕሬሰሩ ያለ እረፍት እንዲሰራ ያደርገዋል። ይህ ደግሞ ያለረፍት መስራቱ ብቻ ሳይሆን ምግብ በአግባቡ አያቀዘቅዝም። የውስጥ
👉መደርደሪያዎቻቸውም ከማይሰበር መስታወት (Tempered Glass) ይልቅ በቀላሉ በሚሰበር ስስ ፕላስቲክ የተሰሩ ናቸው።
7⃣
. የተስተካከለ አየር የሌላቸው (Poor Air Circulation)
👉የተስተካከለ የአየር መውጫ ቀዳዳዎች (Multi-Air Flow) ስለሌላቸው፣ ከላይ ያለው ምግብ በረዶ ሲሆን ታችኛው ክፍል ደግሞ በቂ ቅዝቃዜ ሳያገኝ ምግቡ ይበላሻል።
8⃣
. የውሸት ብራንድ እና የመለዋወጫ እጦት (Fake Brands)
👉ስማቸው ያልታወቁትን ስመ ጥር በሆኑ የታወቁ ብራንዶችን ስም አመሳስለው (Fake/Counterfeit) በህገ-ወጥ መንገድ የተሰሩ ናቸው።
👉እነዚህ ፍሪጆች ሲበላሹ ማዘርቦርድም ሆነ ሌላ የውስጥ መለዋወጫ ሀገር ውስጥ ስለማይገኝላቸው በቀጥታ ወደ ቆሻሻ መጣያ ነው የሚሄዱት።
👉ይህ ብቻ አይደለም ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንደ ፍሪጅ፣ ቲቪ እና የመሳሰሉት ምንም ልዩነት የሌላቸውን አንድ አይነት ምርቶች ሆነው እያለ ስማቸው ብቻ ነው የሚቀየረው❗️
9⃣
. አጭር ወይም ዋስትና አልባ (No Warranty)
👉አምራች ኩባንያው በእቃው ጥራት ስለማይተማመን፣ ለኮምፕሬሰሩ (ሞተሩ) የሚሰጠው የዋስትና ጊዜ ከ1 ወይም 2 ዓመት አይበልጥም (ጥራት ያላቸው ብራንዶች 10 ዓመት ነው የሚሰጡት)። ምናልባት 10 ዓመት ቢሰጥ እንኳን የውሸት ነው!
👉ውድ
ተከታዮቻችን... ቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመድዎ የለፋበትን ገንዘብ በከንቱ እንዳያባክን ይህንን ወሳኝ መረጃ #Share በማድረግ ያካፍሏቸው!❗️💬
👉ከዚህ በፊት ያጋጠማችሁ ካለ ሌሎች እንዲማሩበት #አስተያየት መስጨው ላይ ፃፉልን❗️
👉እውቀት ነፃ ያወጣል እንደሚባለው
የፍሪጅ ሞተር አይነቶችን፣ የውስጥ ጋዝ ሙሌትን እና ሙሉ ጥገናን 100% በተግባር አውቀው በዘርፉ አትራፊ ባለሙያ መሆን ከፈለጉ ወይም ካላስፈላጊ ወጪ ለመዳን በአሜን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
የቤት ውስጥ እቃዎች ጥገና (Home Appliance Repair)--ፍሪጅ፣ ቲቪ፣ ልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ ኦቨን ወዘተ ስልጠናን ወስደው የዘመኑ ተፈላጊ የቴክኒክ ባለሙያ ይሁኑ❗️ አዲሱ ዙር ምዝገባ ተጀምሯል፤ አሁኑኑ ቦታዎን ያስይዙ❗️
⏺
የምዝገባ እና የስልጠና ቦታዎች፦
👉
የምዝገባ ቦታ ፦ ቦሌ ሚካኤል፣ የቅዱስ ሚካኤል ህንፃ 2ኛ ፎቅ
📞
ለበለጠ መረጃና ቦታ ለማስያዝ አሁኑኑ ይደውሉ፦
👉 0991 15 69 69
👉 0939 55 55 10
🔗
ማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይከተሉ፦
👉
Telegram:https://shorturl.at/zKTN2
👉
TikTok:https://shorturl.at/VQN6I
👉
Facebook:https://www.facebook.com/ameninstitutetechnology
"ወጣትነት በክህሎት ካልታጀበ፤ እርጅና በቁጭት ያልፋል❗️"
አሜን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት — በእጅዎ የሚጨበጥ የነገ ብሩህ ተስፋ❗️