ch
Feedback
መንፈሳዊ ግጥም ብቻ

መንፈሳዊ ግጥም ብቻ

前往频道在 Telegram

በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ @Solasc12 @Solasc13 @Mgetem_group ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ @Ortho_quotes

显示更多

📈 Telegram 频道 መንፈሳዊ ግጥም ብቻ 的分析概览

频道 መንፈሳዊ ግጥም ብቻ (@mgetem) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 27 276 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 2 689,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 219

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 27 276 名订阅者。

根据 28 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -287,过去 24 小时变化为 0,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 19.38%。内容发布后 24 小时内通常能获得 5.43% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 286 次浏览,首日通常累积 1 481 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 25

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ @Solasc12 @Solasc13 @Mgetem_group ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ @Ortho_quotes

凭借高频更新(最新数据采集于 29 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

27 276
订阅者
无数据24 小时
-457
-28730
帖子存档
ጠፍቼ ሳለው... (ሳሙኤል አለሙ) @Mgetem ° ° በለመለመው መስክ ላይ እኛ በጎቹ ፥ ነበርን አንድ-ላይ ስንግጥ ባንድ ላይ ስንጠጣ ባንድ ላይ የማይነጥፈው ሳለ ፥ ሳለ ተንዠርግጎ ለወዲያ ማዶ ፥
ጠፍቼ ሳለው... (ሳሙኤል አለሙ) @Mgetem ° ° በለመለመው መስክ ላይ እኛ በጎቹ ፥ ነበርን አንድ-ላይ ስንግጥ ባንድ ላይ ስንጠጣ ባንድ ላይ የማይነጥፈው ሳለ ፥ ሳለ ተንዠርግጎ ለወዲያ ማዶ ፥ አንገቴ አስግጎ አረሙ ናፍቆኝ ፥ ካንተ አመለጥኩኝ። ° ° አረሙ ናፍቆኝ መግደሉ ናፍቆኝ ዝሙቱ ናፍቆኝ ስርቆቱ ናፍቆኝ ይኸው ጠገብኩኝ ፥ ካይነት ካይነቱ ጣዕሙ አልሆነኝ ፥ እንደ ትላንቱ። ° ° ጣዕሙ አልሆነኝ አንገዳገደኝ እንዴት ልመለስ... አስሬ እያነሳ ፥ አስሬ እየጣለኝ ወደ በጎችህ... የማት[ቀላቅለኝ] ፥ እየመሰለኝ ከደጅህ እመለሳለሁ። በኩነኔ አፍሬያለሁ። ° ° ከደጅህ እመለሳለሁ። በምን አይኔ አይሃለሁ። ውቅያኖስ ያህል ፥ ሀጥያት ነበረኝ ባንዲት ዕንባዬ ፥ ሞገዱ ሲጠራኝ ወደ ኩሬ ስትቀይረኝ... አቤት ማለት ፥ አፌ አስፈራኝ። ° ° ወደ ኩሬ ስትቀይረኝ መጣኽና አጠለልከኝ። አንተ ጠባቂዬ አንተ ከለላዬ አንተ እረኛዬ አቅፈኸ ነው ፥ የሳምከኝ ከበጎችህ ፥ የ--ቀላቀል--ከኝ። @Mgetem @Mgetem @Mgetem_group

የውድቀቴን መንገድ ሸርሽራ በመውደድ ያቀናችኝ ንግስት ... የሰጠችኝ ክብር አቤት አቤት ሲያምር {ልክ እንዳንቺ ማርያም} መኖር እንድጠላ መንፈሴን አድክሞ ማጣት አንቆኝ ሲዞር ክንዱን አፈርጥሞ የምሆነው ጠፍቶኝ ተንበርክኬ ሳዝን ሳትለኝ ደካማ ቀና አረገችኝ ቀንበሬን ተሸክማ! እምቅ የእንባ ጠል ጉንጬን ሲንጠለጠል ኅዘን በደቆሰው ልስልስ ስስ አንጀቷ ዕንባዬን ያበሰው አቤት ሲያምር ጣቷ {ልክ እንዳንቺ ማርያም} እኔነት እስካጣ ፍቅር ሸሽቶኝ በሮ ብቸኝነት ሚስማር ሲያደማኝ ቸንክሮ የማረገው ጠፍቶኝ ሞቴን እየናፈቅኩ ሳዘጋጅ መስቀሌን ትንፋሽ ለገሰችኝ ዳብሳ ሰንበር ቁስሌን የጅራፍ ሹል ትርትራት የልቤ ስውር ስብራት አድቅቆ ሲጥለኝ ... እንዲሆን ለነፍሷ ስሞ ሳቅ ያሳየኝ አቤት ሲያምር ጥርሷ {ልክ እንዳንቺ ማርያም} ስትችልበት ማዘን ስታውቅበት ማቀፍ ብሶት አስዘርግፎ በሰላም ማሳረፍ {ልክ እንዳንቺ ማርያም} ስትችልበት ጸሎት ስታውቅበት ማውራት ጨለማን ገርስሶ በፈገግታ ማብራት {ልክ እንዳንቺ ማርያም} ስትችልበት ማከም ስታውቅበት ማዳን ፍቅር በልብ ሰጥቶ መለገስ ማር ኪዳን #ኤልዳን http://t.me/Mgetem http://t.me/Mgetem http://t.me/Mgetem

የሰኔ ማርያም ❤🙏 የሰኔ ጎልጎታ 🙏❤ እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን፣ አደረሳችሁ። በዚህች ቀን ሰኔ ፳፩ እመቤታችን ልጇን ወዳጇን ስለኃጥአን
የሰኔ ማርያም ❤🙏 የሰኔ ጎልጎታ 🙏❤ እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን፣ አደረሳችሁ። በዚህች ቀን ሰኔ ፳፩ እመቤታችን ልጇን ወዳጇን ስለኃጥአን ጎሎጎታ ላይ ምሕረትን ለምናዋለች። ጌታችንም "ስምሽን የጠራውን፣ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ" ሲል ቃል ኪዳን ሰጥቷታል። ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት በሁላችን ላይ ይደርብን ፤ አሜን። 🙏🙏🙏 @Mgetem @Mgetem

ሚካኤል ደግ ነው 🖥 ሚካኤል ደግ ነው ብዬ እዘምራለሁ ያደረገልኝን እኔ ብዙ አውቃለሁ ሚካኤል አምሳለ ኮከብ ልብህ የዋሕ የፍቅር መዝገብ ገና ከልጅነት እኔን ተንከባክቦ ከተዋበ ደጁ በረከት መግቦ በመንገዴ መርቶኝ አለሁ እስከዛሬ ክብሩን እያሰበ ይቀኛል ከንፈሬ ከአምላክ አገናኘኝ በፍቅር ቃል ጠርቶ ግብጽን እንዳልሰማ ጆሮዎቼን ቃኝቶ አሁን በሕይወት ነኝ ገብቼ ከርስቴ በፍጹም ሳይርቀኝ ሚካኤል አባቴ ከኋላ ያጠረኝ ከፊት የቀደመ ደመናን ዘርግቶ ጠላቴን ያስቆመ ከእግዚአብሔር ተልኮ ፈጥኖ የደረሰ የዋሕ ነው ሚካኤል እንባዬን ያበሰ በእኩለ ሌሊት በእሥራት ሳለሁ ከእንቅልፌ ቀስቅሶ ብርሃን አይቻለሁ ሰንሰለቴ ወድቋል ከክብር የተነሳ ውለታው ብዙ ነው ከቶ የማይረሳ 🖥🖥🖥 በድምጽ 👇👇 https://youtu.be/Kt4MDFvRsLc https://youtu.be/Kt4MDFvRsLc

☦️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን/፫☦️ 📌መንፈሳዊ ጥሪ🔊 ይህን የበረከት ጥሪ መቅረት አይደለም ማርፈድ ያስቆጫል❕❕ የ❹ኛ ዓመት የምስረታ በዓል 🌹 እንኳን አደረሳችሁ🌹
☦️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን/፫☦️ 📌መንፈሳዊ ጥሪ🔊 ይህን የበረከት ጥሪ መቅረት አይደለም ማርፈድ ያስቆጫል የ❹ኛ ዓመት የምስረታ በዓል 🌹 እንኳን አደረሳችሁ🌹                 " ናቢኦት " "በለመንኩት ጊዜ እግዚአብሔር ቅርቤ ነው " " መኑ ከመ አምላክ  " (ሚካኤል ፦ ማን እንደ አምላክ ) 📖ከሚካኤ በቀር ማንም የሚያፀናኝ የለም ትንቢተ ዳንኤል 📖10፥22📖 📌በሚል መሪ ቃል ከሰኔ 12፣13፣14 ጀምሮ ታላቅ መርሃ ግብር በማህበራችን ውስጥ ተዘጋጅቷል። 🛐🛐 🛐🛐ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ (መዝ 122÷1)* 🌟በዕለቱ ምን ይጠብቅዎታል❔ ​አስተማሪ መንፈሳዊ ትምህርቶች (ከታላላቅ መምህራን) ​ልዩ የመዝሙር ግብዣዎች (ከሚወዷቸው ዘማሪያን) ​የኪነ-ጥበብ ስራዎች እና ሌሎች አዳዲስ ዝግጅቶች❕ ​በዚህ በረከት በተሞላበት የምስረታ በዓል ላይ በመገኘት፣ በሊቃውንት ትምህርት እና በዘማሪያን መንፈሳዊ ዝማሬዎች ለመንፈስዎ ምግብ ይሁኑ። 💡በሰኔ 12~ 14የምስረታ በዓል ልዩ ጉባኤ ተዘጋጅቷል መቅረት አይታሰብም!! 💡ሰኔ 12 ፤ 13 ፤14 በቴሌግራም ግሩፓችን ውስጥ ከምሽቱ 2:00ሰዓት ጀምሮ 💎💎💎🌹💎💎💎💎💎 🛐🛐 🛐🛐✞ቤተ_ቅዱስ_ሚካኤል_በጎ አድርጎት መንፈሳዊ ማህበር 🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷 የማኅበሩ ሊንክ Join ያድርጉ 📎👇👇👇 https://t.me/Bete_kidus_Michael_12 https://t.me/Bete_kidus_Michael_12 https://t.me/Bete_kidus_Michael_12

ሚካኤል ደግ ነው 🖥 ሚካኤል ደግ ነው ብዬ እዘምራለሁ ያደረገልኝን እኔ ብዙ አውቃለሁ ሚካኤል አምሳለ ኮከብ ልብህ የዋሕ የፍቅር መዝገብ ገና ከልጅነት እኔን ተንከባክቦ ከተዋበ ደጁ በረከት መግቦ በመንገዴ መርቶኝ አለሁ እስከዛሬ ክብሩን እያሰበ ይቀኛል ከንፈሬ ከአምላክ አገናኘኝ በፍቅር ቃል ጠርቶ ግብጽን እንዳልሰማ ጆሮዎቼን ቃኝቶ አሁን በሕይወት ነኝ ገብቼ ከርስቴ በፍጹም ሳይርቀኝ ሚካኤል አባቴ ከኋላ ያጠረኝ ከፊት የቀደመ ደመናን ዘርግቶ ጠላቴን ያስቆመ ከእግዚአብሔር ተልኮ ፈጥኖ የደረሰ የዋሕ ነው ሚካኤል እንባዬን ያበሰ በእኩለ ሌሊት በእሥራት ሳለሁ ከእንቅልፌ ቀስቅሶ ብርሃን አይቻለሁ ሰንሰለቴ ወድቋል ከክብር የተነሳ ውለታው ብዙ ነው ከቶ የማይረሳ 🖥🖥🖥 በድምጽ 👇👇 https://youtu.be/Kt4MDFvRsLc https://youtu.be/Kt4MDFvRsLc

Merry Begena አስደሳች ዜና ለወላጆች እና በገና ለመማር አስባችሁ ሁኔታዎች ላልተመቻቸላቹ በonline እና በአካል እያስተማርን እንገኛለን ። አድራሻችን ቦሌ ቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ ለበለጠ መ
Merry Begena አስደሳች ዜና ለወላጆች እና በገና ለመማር አስባችሁ ሁኔታዎች ላልተመቻቸላቹ በonline እና በአካል እያስተማርን እንገኛለን ። አድራሻችን ቦሌ ቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ ለበለጠ መረጃ በ0936290305 ላይ ይደውሉ ። በቴሌግራም @buchula36 ላይ ይፃፋልን።

እንኳን አደረሳችሁ 🥰🥰 https://youtu.be/7zQwggBA_Bs

አንዱ ሐሙስ እግሩን አጥቦት ፣ ቀምሶ ማያውቀውን ምርጥ ዕራት መግቦት ፤ በዛው ሊክድ ሲሄድ እግሩን ያቆሸሸ ፣ ከሰው ዓይን እንጂ ከራሱ መች ሸሸ ​ሌላው ፣ ሐሙስ እግሩን አጥቦት ፣ ቀምሶ ማያውቀውን ምርጥ እራት መግቦት ፤ እግሩ ቢቆሽሽም ቢከተል በርቀት ፣ ከብርድ አመለጠ በንስሐ ሙቀት ​መቼም በመራመድ ብዛት እግር ይቆሽሻል ፤ ታድያ ከህይወት ውሃ ሰው እንዴት ይሸሻል ? አዬ ጴጥሮስ ብልጡ  አዬ ይሁዳ ሞኙ አብረው በልተው ፣ ክደው ፤ አንዱ ከጌታው ስር ፣ አንዱ ከዛፉ ስር ተኝተው ተገኙ እና ከሞላህ በፀፀት የኃጢአትህ ብዛት ፣ ዲያቢሎስ በክፋት ልብህን ከያዛት ፤ ወደ ጌታህ እንጂ ፣ አትሂድ ወደ ሌላ ፤ ከፈጠረህ ውጪ ፣ የነፍስህን ጉድለት ከቶ ማን ሊሞላ ? ። @Mgetem 🖥 በድምጽ ለማዳመጥ እና ሌሎችም ዝማሬዎችን ለማግኘት 👇👇👇👇👇 https://youtu.be/Qd9Ry7Xkef4 https://youtu.be/Qd9Ry7Xkef4

🔴 በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል | ሰባቱ መንጦላዕት | ዲ/ን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ https://youtu.be/Qd9Ry7Xkef4 https://youtu.be/Qd9Ry7Xkef4

sticker.webp0.26 KB

🔴 በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል | ሰባቱ መንጦላዕት | ዲ/ን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ https://youtu.be/Qd9Ry7Xkef4 https://youtu.be/Qd9Ry7Xkef4

ጨረስኩ ሳልጀምረው 🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤 ከፊደላት ተራ ከሆህያት ገብቼ ክብርሽን ለመግለጽ አሙልቼ አስፍቼ አበው ሲናገሩ ስላንቺ ሰምቼ ቃላትን ከቃላት መርጬ አሳክቼ። <ሀ>ብዬ ጀመርኩኝ ልናገር ጸጋሽን መጽሐፍ ከሚለው በልቢም ያለውን አባቶች ቅዱሳት ያስተላለፉትን በሕይወት ከነሱ የተቀበልኩትን። ከነ<ሀ> ነጎርቤት ከነ <ለ> አዝማዳት በሰባት በሰባት ከተከፋፈሉት ከላይ እስከታች የተደረደሩት እስከነ <ፐ >ድረስ ከተሰበሰቡት። ያንንም ሳወጣው ይንንም ስመዘው ጥንት የመረጥኩትን መልሼ ስተወው ፊት ያስገባሁትን ኃላ ስመልሰው አንዱን አስገብቼ ሌላውን ሳወጣው ፈጽሜአለሁ ብዬ የፃፍኩትን ሳየው ድንግል ውዳሴሽን ጨረስኩ ሳልጀምረው። _____________________________ 🔤🔤🔤🔤 🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤 http://t.me/Mgetem http://t.me/Mgetem http://t.me/Mgetem

ለወላጆች አስደሳች ዜና 🙏 ለህፃናት የሚሆን ልዩ የበገና ትምህርት አዘጋጅተን እየጠበቅንዎ ነው። አድራሻችን ቦሌ ቡልቡላ ሲሆን ቅዳሜ እና እሁድ ከጠዋቱ 4 ሰአት ጀምሮ ልናስተምራቸው ዝግጅታችንን አጠናቀን በይፋ ልጆችዎን እየተቀበልን ነው። በአካል ለሚርቃችሁ በonline ስላልን በ 0936290305 ላይ በመደወል አልያም በ ቴሌግራም @buchula36 ላይ ያነጋግሩን።

ለወላጆች አስደሳች ዜና 🙏 ለህፃናት የሚሆን ልዩ የበገና ትምህርት አዘጋጅተን እየጠበቅንዎ ነው። አድራሻችን ቦሌ ቡልቡላ ሲሆን ቅዳሜ እና እሁድ ከጠዋቱ 4 ሰአት ጀምሮ ልናስተምራቸው ዝግጅታችንን አጠናቀን በይፋ ልጆችዎን እየተቀበልን ነው። በአካል ለሚርቃችሁ በonline ስላልን በ 0936290305 ላይ በመደወል አልያም በ ቴሌግራም @buchula36 ላይ ያነጋግሩን።

ሦስተኛ ዙር የበገና ስልጠና ትምህርት ምዝገባ እንደጀመርን ስናበስርዎ በደስታ ነው ። ለመመዝግብ በ0936290305 ላይ ይደውሉ እንዲሁም በቴሌግራም @buchula36 ላይ ፈጥነው ይመዝገቡ ።