የጥበብ ማዕድ
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 የጥበብ ማዕድ 的分析概览
频道 የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 974 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 411,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 116 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 974 名订阅者。
根据 25 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 604,过去 24 小时变化为 -23,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 2.64%。内容发布后 24 小时内通常能获得 2.10% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 419 次浏览,首日通常累积 334 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!”
凭借高频更新(最新数据采集于 26 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 974
订阅者
-2324 小时
+1447 天
+60430 天
帖子存档
15 968
፡፡፤፤፡፡ ጥያቄ ? ፡፡''''',,???,, '''
በአለማችን "ከሰው ልጅ ቀድመው ተፈጠሩ " የተባሉ ብዙ ፍጥረታት አሉ። ለእነዚህም ለሁሉም በሚባል ደረጃ ሰው በራሱ ፈቃድ የህይወት መስመር ወይም ቀመር አውጥቶላቸዋል። ማንኛውም ተመሳሳይ ዝርያ ይህን የወጣለትን ህግ ተከትሎ ጉዞውን ያጠናቅቃል። ታዲያ ግን ለቀማሪው "ሰው" ይህ መስመር አልተገኘለትም። ጉዞውን ይጀምራል ፣ ኋላም ያጠናቅቃል ከማለት በስተቀር። ለምን ይሆን ? እኔ~ በእንስሳት አንድ ዝርያ እንደምንለው ሁሉ በሰውም አንድ ዝርያ ማለት አንድ ሰው ነው። ለምን ቢሉ ሰው በራሱ ህግ የሚሄድ ፍጡር ስለሆነ። ይሁን እንጂ ይህንም ሰው ጉዞውን ከፈፀመ (ሞት) በኋላ ነው ይህን ቀመር የምናውቀው። ይህ ቀመር ፣ እንደ እንስሳት ለሰውም ከመወለዱ እስከ ፍፃሜው ሲተነበይ ፣ አንድ ድምዳሜ ላይ መድረስ ይቻላል። ድምዳሜው ምስጢር ነው። ማወቅ ግን ይቻላል። ህግ አፍራሽ ፍጡር,..... ለዚህም ነው ፣ እኛ የሁለንታን ህግ ስለምናፈርስ ከእንስሳት ልዩ ነን የምንለው። እነርሱ ስለማያፈርሱ። ✍ Tewodros D.
15 968
ከክላስ እንደወጣን ቀጥታ ወደ ተለመደው መቀመጫችን ግቢያችን ውስጥ ካለው ካፌ ሰብሰብ ብለን እያወራን ነው ።
እኔ ፣ ደጉ ፣ ፍቃዱ ና አስቴር ቁጭ ብለን እንዱ ቅሌታሙን classmateችንን እየበላን (እያማን ) ነው ።
አስቴር የሃብታም ልጅ ስለሆነች ገንዘብ አይጨንቃትም ። እናንተ ይሄ ዝኔ ግን ምንድነው እንደዚ ሚያረገው ? ብላ ትጠይቀናለች
ፍቃዱ ት/ት አይወድም ኑሮን ቀለል አርጎ መኖሩን ያውቅበታል ። እንዲያውም የሆነ ሰዓት ቤተሰቦቹ ገንዘብ ሲልኩለት ወዲያው ነው ልብስና ጫማ የገዛበት ። ሲገዛም እርካሽ ነገር አይወድም ።
"ብር ገብቶልኛል እንሂድ ሱቅ አለኝ "
ስንት ብር ገብቶልህ ነው ሱቅ እንሂድ ምትለው ? አልኩት
አስር ሺ ብር
ያ ከሆነ እንሂድ አልኩትና ሃብታሙ ፋሽን ልብስና ጫማ መሸጫ ቡቲክ ገባን ።
እንደገባን " አባቱ የአሜሪካ ሱሪ አለሽ " አለው ባለ ቡቲኩን
"አዎ አለኝ" ብሎ በስነ ስርዓት የተጣጠፉትን ሱሪዎች በየ ከለሩ አመጣለት
ቡላ ከለሩን ከመረጠ በኋላ " ስንት ነው " ? አለው
6000 ብር ነው ባባ
ልቤ ከቦታው ተንሸራቶ ኪሴ ውስጥ ገባ
"ቀንስ እንጂ ትክክለኛ ገዢ ነኝ" አለ ጓደኛዬ
አባቱ የአሜሪካ ሱሪዎች እንደዚ ናቸው ሚቀንስ ከፈለክ ጋርመንቶች አሉልህ አለው
አይ! ጋርመንት አልፈልግም ይህኛው ይሁንልኝ አስታየት አርግልኝና ልውሰደው
አይይ ! አስታየት የለውም ብሎ ቁርጥ ያለ መልስ ሰጠው ።
እኔም ጓደኛዬ ተስፋ ቆርጧል ብዬ " እ ? እንውጣ በቃ ሌላ ቦታ ሚቀንስ እንፈልግ አልኩት ።
አይይ አልወጣም ይህን ከለር ሌላ ቦታ አላገኝም ልገዛ ነው አለና ስልኩን አወጣ
አንተ ፍቃዱ ስማኝ አንተ'ኮ ተማሪ ነህ ሁሉ ነገር የሚያምርህ ከሆነ ውስጥህ ላይ የሆነ ችግር አለ ። ፈላጎቶችህን መግራት አለብህ የሀብታም ልጆች የሚለብሱትን ሁሉ እለብሳለሁ አትበል ቤተሰቦችህ ይህን ገንዘብ ከየት እንዳመጡ አስተውል እስኪ ራስህን ግዛ ራስህን ተመልከት ። አሁን ይህን አስር ሺ ብር ዛሬ ጨርሰህ ነገስ ? አንተ እያወቅክ ባጠፋሀው ማነው ሚጠየቅ ? እኛ ጓደኞችህ ? ቤተሰቦችህ ? ፈጣሪ ? ማነው ሚጠየቅ ? ነገ ገንዘብ አጥተህ ማንን ነው ምታማረው ዛሬ እንደፈለክ በትነህ ። እኔ የጓደኝነት ምክሬን ሰጥቸሃለሁ አይሆንም ካልክ እንደ ፈለክ ብዬ ወደ ጊቢ ተመለስኩ ።
✍ Henok
15 968
☦️እግዚያብሄር ለኛ መልካም የሚያደርግልን
በጎ ነው ብለን በምናስበው ነገር ብቻ አደለም
እጅግም ክፉና አስቸጋሪ መስለው ከሚታዩን
ሁኔታዎችም ለእኛ ለልጆቹ እጅግ የሚደንቅና
በጎ ነገርን ማድረግ ይችልበታል::🙏🏻😇
ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ
GM y'all 🫶🥰
15 968
ያለፍናቸው ችግሮች ለምን እንደሆነ ባላውቅም እንደ ትናንት አልፎ አናየውም ነገም ፊታችን ላይ ተደቅኖ እናየዋለን ። ሚቀየረው ቀኑ እንጂ ችግሩ ባለበት ይጠብቀናል ። ቀናች እስከሚመጣ ድረስ እስኪ እንጋፈጠው 💪💪💪
15 968
እኛ የስርቻ ሰዎች በወጉ ተጠፍረን መያዝ እንዳለብን ተረድቻለሁ ። የኔ አይነቱ ሰዉ አንዲት ቃል ሳይተነፍስ ለአርባ አመታት ጉድባው ውስጥ ተወትፎ ይኖርና አንድ ቀን ወጣ ብሎ አፉን ከከፈተ ማቆሚያ የለውም ።
🗣 ፊዮዶር ዲዮስቲዮቨስኪ
15 968
??? ወዴት እየሄድን ነው ??
ቤተሰቦቹ ወደ ጎረቤታቸው ልከውት ነገር ግን ከጎረቤቶቹ ልጆች ጋር ሲጫወት እና ሲቀልድ መልዕክቱን እና ቤተሰቦቹን የረሳውን ልዑክ ህፃን ልጅ ሳስብ፤ መሬት ላይ የሚኖረውን"ሰው - ፍጡር" ያስታውሰኛል።
አብዛኛው ሰው የሚጋራው አንድ እውነታ አለ ፤ ይኸውም ወደ ምድር የመጣንበትን ዓላማ ነው።
ጭራሽ እኮ አላማ ሊሆን የሚገባውን ነገር ፣ ፈፅሞ አግልለነው የመጨረሻ ምርጫችን አድርገነዋል። ኧረ ከነካቴው ረስተነዋል።
እውነት ግን ወዴት እየሄድን ነው ፣ እንዴ ሲጀመር መንገዳችን እኮ ግልባጩን ነው።
የጨዋታውን ፣ የቀልዱን መማረክ ደግሞ የመጣንበትን ዓላማ ለማስታወስ የሚሞክሩ አካሎችን ማግለላችን ያሳብቃል።
ዓላማ አለኝ ምናምን እያልን በራሳችን ላይ የምንቀልደው ነገርስ.....
ይገርመኛል ብቻ🤔 .........
✍ Tewodros D.
15 968
Repost from ዘምናኒት 🌬️
ትዕቢት ወይስ ራስን መቅጣት?
ባልሳሳት ይሄን አመል ብዙዎቻችን እየተላመድነው ነው ጭልም ባለ ክፍል ውስጥ መቀመጥ፤ሰበብ እዬፈለጉ ማለቃቀስ፤የምናቅደው ሌላ የሚሆነው ሌላ፤ስድስተኛ ስሜታችንን መፍራት፤ከማንም በላይ ለስልካችን ትኩረት መስጠት ፤ማንም ጋር ያለማውራት ፍላጎት ፤ እንቅልፍ ማጣት ፤ራስን የማጥፍት ሃሳብ፤በሰዎች ዘንድ ተፈላጊነት ማጣት፤ ስደት ስደት የሚል mindset አሁን ላይ እንደቀልድ ባህርያችን እስኪመስል ድረስ ተጋብቶብን እዬኖር ነው ግን ደግሞ ማንም ሰው ቢሆን በዚህ ስሜት ውስጥ እንዳለን አይረዳንም ኧረ አንች ምን አለብሽ ፤ ከኛ ስልኩ በልጦብሽ (እነሱን የማወራበት energy እንደሌለኝ አልገባቸውም፡፡ አንዳንዴ ሲያዩን አእምሮ ሚባል ነገር ያለን አይመስላቻውም እናም ይህ አመል ለነሱ ትዕቢት ነው ለኛ ደግሞ መደበቂያ 🥺 በዚች እድሜ ስንት pain እንደተሸከምን ማን በነገራቸው 💔 እንደ ጓደኞችሽ የምትባለዋን ቃል መስማት ምን ያህል እንደሚያቆስል በምን ባሳዬናቸው 😔 ስሜቴ ቢሰማቸው እና ብንቀያዬር ሁኔታዬን እኔን ሆነው ቢያዩት ምኞቴ ነበር ግን ደግሞ ይሄን ስቃይ ለsecond እንኳን ማንም እንዲሰማው አልፈልግም አይገርምም እዬገደሉኝም አዝንላቸዋለው🥺
ሰናይ ቀን ✨🫶🏻
✍🏻 ᵏᵘʳᵘሴት
15 968
በአንድ ወቅት መለስ ዜናዊ ለጉብኝት ወደ Belgium ሄዶ እዚያ ባደረገው ስብሰባ ከተጋበዙት ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዷ ሃሳብ ለመስጠት ተነሳች፡፡
ወጣቷ፦ “የርስዎ መንግሥት በጣም አስጠሊታ ነው። ስርዓታችሁ አስጠሊታ፣ አካሄዳችሁ አስጠሊታ፣ ባለስልጣኖቻችሁ አስጠሊታ፣ ሁለመናችሁ አስጠሊታ ነው”።
መለስ_ዜናዊ፦ “ጥሩ ነው:። አስጠሊታ ልንሆን እንችላለን። አሁን እዚህ የመጣነው ግን ለቁንጅና ውድድር አይደለም”
15 968
እስከመች ይህ መልፈስፈስ
እስከመች በሁለት ልብ ማንከስ
እስከመች ይህ መባከን
በማባበል የት ለመድረስ
እስከምን ድረስ ለመዛለቅ
መተው ነው እንጂ ሲሄዱ መልቀቅ
እየተገፋ ካላለ ፎቀቅ
መተው ነው እንጂ እየፈለጉ
ምርጫ ሲኖረው
መቼ ያስጠጋል የሰው ኣመሉ
ይነዋወጣል በየመሃሉ
እንደሞገድ ነው እንደ መኣበል
እንደ ነድ እሳት እንደ ነበልባል
የቀረበውን የሚያቀጣጥል
meron
15 968
፡፡፤፤፡፡የእኔነት ቀመር ፡፡፤፡፡
ሁሉም ሰው በማማለል ለማሸነፍ የሚፈልገው የሆነ አካል አለ። ያ አካል ግን ለመሸነፍ የተለያየ መስፈርት ይጠይቃል።ታዲያ ለምን ይህ ሁሉ ሰው በተለያየ መንገድ ይኳትናል ?ያንን አካል ለመማረክ የሚያስፈልገው መስፈርት የተለያየ ስለሆነ። ✍ Tewodros D.
15 968
ትናንትን መርሳት የተዋለለትን መዘንጋት የደካማ ባሕሪ ነው !! ደካማነት ምቹ ስፍራ ሲያገኝ እና ጊዜ ሲደላደልለት የሚያብብ ደዌ ነው ።
📕 አዎ እሱጋ ያመኛል
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
