የጥበብ ማዕድ
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 የጥበብ ማዕድ 的分析概览
频道 የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 974 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 411,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 116 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 974 名订阅者。
根据 25 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 604,过去 24 小时变化为 -23,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 2.64%。内容发布后 24 小时内通常能获得 2.10% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 419 次浏览,首日通常累积 334 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 10。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!”
凭借高频更新(最新数据采集于 26 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 974
订阅者
-2324 小时
+1447 天
+60430 天
帖子存档
15 974
..
ግራ ዘመም ነፍሱ
ወይ ያይደለ መልካም ወይ ያይደለ ክፉ
ሹልክልክ ኣመል ነው መች ይያዛል ጫፉ
ኣንዳንዴ መልኣክ ያስንቃል
ኣንዳንዴ ከሰይጣን ይከፋል
ኣንዳንዴ ካለሱ ሰው የለም
ኣንዳንዴ እሱው ነው ገሃነም
እሳት ነው በራድ ነው
ኣይሞቅም ትኩስ ነው
ሲቀረብ ያነዳል ሲራቅ ይናፍቃል
ተትቶ እንዳይተው ደግሞኮ ያሳሳል
ምን ኣቃለው በየት በኩል እንዳገኘኝ
ባከንኩ እኔስ የማስበው እስኪጠፋኝ
መች ያውቅና በሱ ምክንያት እንደከፋኝ
መች ያውቅና በሱ ግራስ እንደገባኝ
ጥግ ሳሊዝ ወይ ከጥሉ ወይ ከመውደድ
ታይቶትእኮ ኣያቅም
ይህን ያህል ግዜ ለብቻዬ... ስነድ
.meron
15 974
፡፡፡፡ የጥንቃቄ መልዕክት ፡፡፡፡፡፡
ተማሪ ለነበራችሁ፣ ለሆናችሁ እንዲሁም ለምትሆኑ ሁሉ፤
ለካስ ከአስር እና አስራ አምስት ዓመታት በላይ ተምረን የምንሰጠው ጥሬ ነገር ወይም ተጨባጭ ነገር (ለምሳሌ ገንዘብ) አይደለም። ረቂቅ የሆነ ነገር ሁኖ የሚገልፀውም እያንዳንዱን ስዓታችን ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀማችንን ብቻ ነው በፅሑፍ የምንቀበል። አይገርምም!!😱 እና ምን እንጠብቃለን ,,,,, ወረቀቱን(cirtificate) የሚሰጥህ ብቻ አይደለም ፤ የሚቀበልህም እንዲሁ ካንተ የሚፈልገው በተሰጡህ ስዓቶች ያጠራቀምከውን ክህሎት ነው። ተማርክ ማለት ችግሮችህን አሸነፍክ ማለት አይደለም። ይልቁንስ ለማሸነፍ አስፈላጊውን ትጥቅ ትቀበላለህ ይህም እንዳንተ ተነሳሽነት ይወሰናል። መልካም ትጥቅን ተመኘሁላችሁ 💐💐💐
15 974
ለህይወትና ለስኬት የሚረዱ ነገሮች
🧠 1. አእምሮን አበርክት
መማር አታቁም፤ መጽሐፍ አንብብ፣ አዲስ ነገር ሞክር
ስህተትን እንደ ትምህርት ተቀበል
⏰ 2. ጊዜን አስተዳድር
ቀንህን አቅድ
አስፈላጊ ነገሮችን ቅድሚያ ስጥ
💪 3. ጤና ቀዳሚ ነው
መደበኛ እንቅስቃሴ (exercise) አድርግ
ጤናማ ምግብ ብላ
በቂ እንቅልፍ አድርግ
💬 4. አነጋገርህን አሻሽል
ሰዎችን አድምጥ
አስተያየትህን በግልፅ አቀርብ
🎯 5. ግብ አውጣ
አጭር እና ረጅም ጊዜ ግቦች አውጣ
ቀስ በቀስ እንዲደርስ ስራ ጀምር
🤝 6. ግንኙነት ገንባ
ከሌሎች ተማር
መልካም ጓደኞች አግኝ
💡 7. አዎንታዊ አስተሳሰብ ይኑርህ
ራስህን እምነት አድርግ
ምንም ነገር እንደምታደርገውና እንደምታሳካው እመን
አስቸጋሪ ጊዜ እንኳን እድል እንደሆነ እይ
ከነዚህ ውስጥ በየቀኑ ትንሽ ብቻ ቢሆንም ተግባራዊ ብታደርግ ትልቅ ለውጥ ታያለህ 👍
✍ Henok
15 974
፡
እኔ እኮ አረ'ጋም፡
በምን ነገር ሳብሽኝ፣
ልቤ ማያቅ መውደድ፡
ገፍተው የሰብሩት፡
በምን ቃል አሸ'ሽኝ
እንጃ!
እኔማ
ልመነዝር ነገ የከረመ በቀል፣
ሲያከብዱኝ፡ ስከብድ፡
የገፉኝ'ለት…ስቀል፣
እኔ ለኔ ሳልኖር፡
ደስታን አስቀምጬ፡
ከተበሳ ወንፊት፡
በድፍረት የማልቆም
ከድንግዝግዝ ሀሴት
ከሰዎች ፊት ለፊት
ሳለው ረብ የለሽ
የተመለከትኩኝ
ክፋትን ገልቤ
ካንቺ ምን አፀናኝ
እንዴት ተጣመሩ ልብ'ሽና ልቤ
ግን እንዴት ቻልሽበት…?
Abu(Alazar Tewodros)
15 974
በህይወት ዘመኔ አንድ ሰው ብቻ ነው አቅፎ የሳመኝ እሷም እናቴ።
አሁን ከሞትኩ በኋላ ነው ብዙ ሰው እንደሚወደኝ ያወኩት ። ሞት ጋ በድንገት ነበረ የተገናኘነው ። ስራ አግኝቸ የትምህርት ማስረጃዬን እየወሰድኩ ነበረ ። ብቻዋን ለፍታ ያስተማረችኝን እናቴን ለመጦር ነበረ ደረስኩ እያልኩ እያሰብኩ ሳለ የተሳፈርኩት መኪና ከጭነት መኪና ጋ ተጋጭቶ ሞትን ጨበጥኩት ። በአንዴ እችን ዓለም እና እናቴን ትቸ ወደ ሌላ ዓለም ከሞት ጋር ሄድኩ ።
ከመኪናው ውስጥ ከነበርነው አስራ አምስት ሰዎች መካከል የሞትነው ጋቤና ውስጥ ያለነው እኔና ሹፌሩ ብቻ ነበርን ። ሬሳችንን ለመመርመር ሆስፒታል ወሰዱን ። ሰው ከሞተ በኋላ ጥሎት የሄደውን ዓለም ያያል እንዴ ? እኔ ግን ሰማይ ሆኜ እያየሁ ነበረ ።
ሞቴ ለሁሉም እንደ ሰበር ዜና ተሰማ ። መሞቴ viral ወጣ ። ጓደኞቼ በየ ፌስቡክ ፣ በቴሌግራም ፣ በኢንታግራም ፣ በቲክታክ ፣ በቫይበር ፣ በታንጎ ፣ በዋትሳፕ ፣ በኢሞ ፣ በምንንትስ እንዳለ እንደምረጡኝ ቅስቀሳ በፎቶዬ RIP እያሉ ፖሳሰቱኝ ። ያቺ ከይሲ ኤልሳም ( ኣክ ቱ !! ስሟን ዓለም ላይ ያሉ ቄሶች ይጥሯትና ) እየሳቅኩ የተነሳሁትን ፎቶ profile አረጋዋለች ።
አረ ! አረ ! አረ! ማነው ይሄ ሰውዬ ? ስሜን አቆላምጦ ሚጠራኝ ። ዕርስቱ የነበረውን ስሜን ወደ " የኔ ዕርስት ዕርሰቱዬ ዕርስቱዋ " ቀይሮ ይቀውጠዋል በቀብሬ ቀን ። እናቴን አየኋት መቆም መቀመጥ አልቻለችም እስከመቼ ይሁን ቀኑ ባይታወቅም ለቀብሬ ቀን ሰው ደግፏታል ።
ዕርስቱዬ ብቸኛው የእህቴ ልጅ ( አረ ጉድ ነው ! አክስትም አለኝ ለካ!! በህይወት እያለሁ የሌለች አክስት ስሞት እንደ አረም በቀለች እንዴ ??)
የኔ ከርታታ የኔ ወርቅ የኔ አሳቢ የኔ ቆንጆ ትላለች።
እንዴ !! ኤልሳ ናት ሌላ ሰው ነው ? አረ ጉድ !! አንተ ዘረ ቢስ ያለችኝ የኔ ፍቅረኛ ተብዬዋ ናት እኮ አሁን እየቀወጠች ለያዥ ለገናዥ ምታስቸግር ። ፓፓፓፓ ! አረ ቀወጠችው ኡኡታው ቀለጠ እንዴ ! አጨናነቀችው እኮ ።
በለው ሌላ ጀማ ደሞ መጣ ። አረ ጉድ ነው የዞናችን አስተዳዳሪ እኮ ነው ታጅቦ ሚመጣው ። ( እኔን ያውቀኛል እንዴ ? ) ዕርስቱዬ የኔ ሽሙንሙን ይሄ ነው ዎይ ወግ ማዕረግህ ? ይሄ ነው ወይ ለኔና ለእናትህ ሚገባው ?( ጆሮዬ ነው ? በሰይፋጥራው !! በህይወት እያለሁ ማያውቀኝ ሰውዬ አሁን ስሞት አባት ነኝ ብሎ መጣ !! ጉድ ነው !!ጉድ ነው !! )
ሬሳዬ በሚያብለጨልጩ ሳጥንና የሳጥን መልበሻ ደምቀዋሉ ። ወደ ቤተክርስቲያን ሊቀብሩኝ እየወሰዱኝ ሳለ ..... ጥቁር የለበሰው ሰዉዬ ነጎድጓድ በሚያስንቅ ድምፅ አንተ ! ብሎ ጠራኝ ..
እኔም የብርሃንን ፍጥነት በሚያስንቅ ቅልጥፍና ከተኛሁበት ዓልጋ ብዲግ አልኩና
በስመ አብ ወልድ በስመ አብ ወልድ በስመ አብ ወልድ ሶስቴ አማትቤ ተነሳሁ ።
ህልም እልም !!!!✍ Henok
15 974
ካለ ግዛት ንግስና የለም እሱን ሁሌ አስቀድም!
ምናልባት በሰው ግዛት በአንጋሽ አለሁልህ ከዜሮ ተነስተህ ልትነግስ ትችላለህ! ያ ግን አንተ እንደፈለከው የተሰራ መንግስት አይደለም!!!
15 974
Unw ብዙ የሚያስጨንቅ የሚያስደነግጥ ነገር በህይወት ውስጥ happen ያደርጋ or ደግሞ ሊያደርግ ይችላል ግን ዋናው ነገር ለምን ተፈተንኩኝ ብሎ ከማማረር እንዴት ፈተነኝ ብሎ ማመስገን is the best ጌታን እስኪ አስቡት እግዚአብሔር በኔ ትክሻ ምን ያህል ቢተማመን ነው ይሄን የሚያህል ትልቅ ፈተና ያሸከመኝ? የምር እሱ በጥንካሬ ተማምኖ እዬፈተነኝ why እኔ የሱን እምነት የማጎድልበት ስለምን እየኮራብኝ ላሳፍረው ik ከባድ ነው በጣም ማለት ብዙ የሚያስጨንቅ ነገር እያለ እንደገና ሌላ ተጨማሪ ፈተና ሲመጣ ሆድ ያስብሳል ግን ደግሞ ራስን ለእግዚአብሔር አደራ መስጠት አንተው ፈጠርከኝ,አንተው እያኖርከኝ እንደገና አንተው እኔን ልታበረታ ፈተንከኝ አባት ሆይ እኔ እኮ ያላንተ ደካማ ነኝ ሸክሜን እንደ እድሜዬ ያለፈ አድርግልኝ በሉት ከዛ ሁሉም ቀላል ነው ። እግዚአብሔር የሰጠንን ፈተና ማለፍያ ጥበብ ያድለን 🤲🏿🥹
ደና አደራችሁ♥️✨
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
