GLOW KG AND PRIMARY SCHOOL ADDIS ABABA ETHIOPIA.
前往频道在 Telegram
1 431
订阅者
+824 小时
+127 天
+730 天
帖子存档
> Sis:
በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!
========================
👉ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው::ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤
ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዘዴዎች፤
------------------------------------------------
☝️ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።
☝️ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡
👌ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ።
☝️ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።
☝️ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።
☝️ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።
ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤
👉 ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።
👉አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።
👉ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።
👉 በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር::
👉 ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤
👉በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።
👉ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።
👉በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ።
👉መጭው ወቅት የፈተና ወቅት ነውና ለተፈታኞች በሙሉ መልካም ጊዜ ተመኘን👏👏👏👏
📝ሰሞነኛ 📝
ልጆችና👧🧒 ዝናብ🌧
ልጆች በዝናብ እንደመጫወት በውሀ እንደመንቦራጨቅ የሚያስደስታቸው ነገር የለም አልፈንበታልና መቼም ሁላችንም እናውቀዋለን ግን ምን ያደርጋል የሚያስደስት ሁሉ መልካም አይደለም አደጋ አለው እናም ጥንቃቄዎችን ለኛም ለልጆቻችንም እናድርግ።
"አይሆንምን ትተሽ ይሆናልን ያዢ" 👵ትለኝ ነበር አያቴ ምክሩ ቀላል ይመስላል ብዙዎቻችን ምንም አይመጣም ችግር የለውም ብለን የምናልፋቸው ነገሮች ደርሰው ጎድተውናልና ቅድመጥንቃቄን መተግበር መልካም ነው ስለዚህ?ስለዚህ...
⛈ የአየሩን ሁኔታ አይቶ ለልጆች ከደንብ ልብስ (ከዮኒፎማቸው)ስር የሚሞቁ ልብሶችን ማልበስ🧥🥼
⛈ በዝናብ ውስጥ እንዳይሯሯጡ እና በውሀ እንዳይንቦራጨቁ መምከር።
⛈ በዝናብ ወቅት የተቆፈረ ወይም ያልተደፈነ ጉድጓድ በውሀ ስለሚሸፈን ልጆቻችን ከእጃችን ሳይወጡ ግልፅ ሆኖ በሚታይ መንገድ መጓዝ ይኖርብናል።
⛈ እንደሚታወቀው ዝናብ ለመኪናም አስቸጋሪ ስለሆነ ስናሽከረክርም🚗 በጥንቃቄ እግረኛም ከሆንን ልጆቻችንን እጃቸውን ይዘን እራሳችን ብንወስዳቸው ይመረጣል።
⛈ ዝናቡ አባርቶ እንኳን ከሌላ ቦታ በዘነበ ዝናብ ምክንያት ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ልጆችን በቤት ውስጥ ማቆየት
⛈ ከዚህ በፊት በምናውቀው በዝናብ ወቅት ድንገት የኤሌትሪክ መቋረጥ፣ የኤሌትሪክ ⚡️ገመድ መርገብ፣ የኤሌትሪክ እንጨት መውደቅ፣ በገመዶቹ መነካካት የሚፈጠር እሳት🔥 እና ሌሎችም አደጋዎች ስለሚኖሩ በዚህም ጉዳይ የተቻለንን ጥንቃቄ ማድረግ መልካም ነው።
የልጆቼ ወላጆች👨👩👧👦 አይሆንምን ትተን ይሆናልን እንያዝ ጨርሻለሁ።
ት/ቤትዎ
✍የ2015 ትምህርት ዘመን 2ኛው ሴሚስተር አጋማሽ ፈተና ፕሮግራም ከላይ የተያያዘ ሲሆን ልጅችዎ በፕሮግራሙ መሰረት እንዲያጠኑ እገዛ ያድርጉላቸው፡፡
# ስለሚደረገው ክትትልና ድጋፋ እናመሰግናለን!!👍👍👍👍👍
ት/ቤትዎ
የ2015 ትምህርት ዘመን 2ኛው ሴሚስተር አጋማሽ ፈተና ፕሮግራም ከላይ የተያያዘ ሲሆን ልጅችዎ በፕሮግራሙ መሰረት እንዲያጠኑ እገዛ ያድርጉላቸው፡፡
# ስለሚደረገው ክትትልና ድጋፋ እናመሰግነለን!!
ት/ቤትዎ
ሚያዚያ 19/ 2015 ዓ.ም
የተከበራችሁ የትምህርት ቤታችን
ወላጆች
# ከነጌ ሚያዚያ 20 - 21/2015 ዓ.ም በመምህራን ስልጠና ምክንያት ትምህርት የማይኖር መሆኑን እና
# ሚያዚያ ሰኞ 23/2015 ዓ.ም የላብ አደሮች ቀን ታስቦ ስለሚዉል ትምህርት አይኖርም።
# ሚያዚያ ማክሰኞ 24/2015 ዓ.ም መደበኛ ትምህርት ይቀጥላል።
ለ1444ኛዉ ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።
ግሎው ት/ቤት
Eebla 12/2015 ALH
Maatiiwwan manan barumsaa keenya hundaaf / Maraaf
Duran dursa hordoftoota Amantaa Musliimota maraaf baga ayyaana waggaa 1444ffaa IId Alfaxiriif isin gahe Jenna.
Haa ta’u malee sababa ayyaana kanaan walqabatee Eebla 13/2015 ALH manni barumsaa cufaa ta’uu isaa isin beeksifna.
Dabalataanis Sambata Eebla 14/2015 ALH sababa ayyaana kanaan barumsi gargaarsaaf/ Tutor Class/ kennamu kan hin jiraanne ta’uu isaa isin beeksifna.
Wixata Eebla 16/2015 ALH barnootni idilee guyyaa guutuu itti fufa.
Mana Barumsaa Glow
ሚያዚያ 12/ 2015 ዓ.ም
የተከበራችሁ የትምህርት ቤታችን ወላጆች
ለእስልምና እምነት ተከታዬች እንኳን ለ1444ኛዉ ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።
በኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት ነገ ዓርብ ሚያዚያ 13 /2015ዓ.ም ትምህርት ቤት ዝግ ሆኖ ይውላል፡፡
ቅዳሜ ሚያዚያ 14/2015 ዓ.ም በበዓሉ ምክንያት የማጠናከሪያ ት/ት የማይኖር መሆኑን እየገለፅን።
ሰኞ ሚያዚያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም መደበኛው ትምህርት ይቀጥላል፡፡
ግሎው ት/ቤት
ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!! አደረሰን!
መልካም ዓመት በዓል!
ግሎው ት/ ቤት
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
