ሪፖርተር ET
前往频道在 Telegram
🔖 ይህ የሪፖርተር ET የቴሌግራም ገፅ ነው ®️ ☆ በቻናሉ 📌 ፈጣን 📌 ትኩስ 📌 ወቅታዊ እና 📌 ወሳኝ መረጃዎችን እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል ! 🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
显示更多📈 Telegram 频道 ሪፖርተር ET 的分析概览
频道 ሪፖርተር ET (@reportereth) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 18 724 名订阅者,在 新闻与媒体 类别中位列第 12 108,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 913 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 18 724 名订阅者。
根据 19 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -330,过去 24 小时变化为 -7,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 15.58%。内容发布后 24 小时内通常能获得 10.26% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 2 919 次浏览,首日通常累积 1 923 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 6。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“🔖 ይህ የሪፖርተር ET የቴሌግራም ገፅ ነው ®️
☆ በቻናሉ
📌 ፈጣን
📌 ትኩስ
📌 ወቅታዊ እና
📌 ወሳኝ መረጃዎችን እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !
🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !”
凭借高频更新(最新数据采集于 20 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 新闻与媒体 类别中的关键影响点。
18 724
订阅者
-724 小时
-787 天
-33030 天
帖子存档
18 724
ደንበኞች የቆጣሪ ንባባቸውን በቴሌግራም ቻትቦት የሚያሳውቁበት አዲስ አሰራር ወደ ሥራ ገባ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች ወርሃዊ የቆጣሪ ንባባቸውን በራሳቸው ማሳወቅ እንዲችሉ የቴሌግራም ቻትቦት አበልጽጎ ወደ ሥራ አስገብቷል።
አዲሱ አሰራር በመደበኛው የቆጣሪ ንባብ ወቅት ንባባቸው ያልተወሰደላቸው ደንበኞች ትክክለኛውን የቆጣሪ ንባብ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ፣ ማለትም ከመደበኛው የንባብ ወቅት ማብቂያ በኋላ ባሉት አራት ተከታታይ ቀናት ውስጥ፣ በቀጥታ እንዲያስገቡ ያስችላል።
አገልግሎቱ በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ ነጠላ ፌዝ ቆጣሪ ያላቸው የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች ብቻ የተዘጋጀ ነው።
ደንበኞች በቴሌግራም ላይ @Eeuchatbot ብለው በመፈለግ ወይም በተቋሙ ይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ የቻትቦቱን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።
በአዲስ አበባ፣ በጅማ እና በአጋሮ ከተሞች መደበኛው የቆጣሪ ንባብ ወር በገባ ከ13ኛው እስከ 26ኛው ቀን ይካሄዳል። በዚህ ወቅት ቆጣሪያቸው ያልተነበበላቸው ደንበኞች ከ27ኛው እስከ 30ኛው ቀን ድረስ በቻትቦቱ አማካኝነት ንባባቸውን ማስገባት ይችላሉ።
ከእነዚህ ከተሞች ውጭ ለሚገኙ ደንበኞች የማስገቢያ ጊዜው በየንባብ ቡድናቸው መሠረት እንደሚከተለው ይሆናል፦
👉 ቡድን 1፦ ከወሩ 21ኛው እስከ 24ኛው ቀን
👉 ቡድን 2፦ ከወሩ 28ኛው ቀን እስከ ቀጣዩ ወር 1ኛው ቀን
👉 ቡድን 3፦ ከወሩ 5ኛው እስከ 8ኛው ቀን
👉 ቡድን 4፦ ከወሩ 12ኛው እስከ 15ኛው ቀን
ደንበኞች የቆጣሪ ንባባቸውን ለማስገባት የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይችላሉ፦
✅ በቴሌግራም ላይ @Eeuchatbot ብለው በመፈለግ ቻትቦቱን ያግኙ።
✅ ቻትቦቱን ካስጀመሩ በኋላ “Send Meter Reading” የሚለውን አማራጭ ይምረጡ።
✅ ባለ 12 ዲጂት የደንበኛ መለያ ቁጥርዎን (Contract Account Number) ያስገቡ።
✅ ትክክለኛውን የቆጣሪ ንባብ በማስገባት ይላኩ።
ደንበኞች ንባባቸውን ማስገባት የሚችሉት በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ውስጥ ብቻ ነው። ከተፈቀደው ጊዜ በፊት ወይም ከገደቡ በኋላ ንባብ እንዲሁም የተሳሳተ ንባብ ማስገባት አይቻልም። ስለሆነም ደንበኞች ትክክለኛውን የቆጣሪ ንባብ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ማስገባታቸው አስፈላጊ ነው።
ይህ አዲስ አሰራር በቆጣሪ ንባብ አለመወሰድ ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ የፍጆታ ሂሳብ አዘገጃጀት ችግሮችንና የክፍያ መዘግየት ቅሬታዎችን ለመቀነስ የታለመ ሲሆን፣ ደንበኞች በቀላሉና በተመቻቸ መንገድ የቆጣሪ ንባባቸውን እንዲያሳውቁ ዕድል ይፈጥራል።
18 724
ደንበኞች የቆጣሪ ንባባቸውን በቴሌግራም ቻትቦት የሚያሳውቁበት አዲስ አሰራር ወደ ሥራ ገባ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች ወርሃዊ የቆጣሪ ንባባቸውን በራሳቸው ማሳወቅ እንዲችሉ የቴሌግራም ቻትቦት አበልጽጎ ወደ ሥራ አስገብቷል።
አዲሱ አሰራር በመደበኛው የቆጣሪ ንባብ ወቅት ንባባቸው ያልተወሰደላቸው ደንበኞች ትክክለኛውን የቆጣሪ ንባብ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ፣ ማለትም ከመደበኛው የንባብ ወቅት ማብቂያ በኋላ ባሉት አራት ተከታታይ ቀናት ውስጥ፣ በቀጥታ እንዲያስገቡ ያስችላል።
አገልግሎቱ በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ ነጠላ ፌዝ ቆጣሪ ያላቸው የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች ብቻ የተዘጋጀ ነው።
ደንበኞች በቴሌግራም ላይ @Eeuchatbot ብለው በመፈለግ ወይም በተቋሙ ይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ የቻትቦቱን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።
በአዲስ አበባ፣ በጅማ እና በአጋሮ ከተሞች መደበኛው የቆጣሪ ንባብ ወር በገባ ከ13ኛው እስከ 26ኛው ቀን ይካሄዳል። በዚህ ወቅት ቆጣሪያቸው ያልተነበበላቸው ደንበኞች ከ27ኛው እስከ 30ኛው ቀን ድረስ በቻትቦቱ አማካኝነት ንባባቸውን ማስገባት ይችላሉ።
ከእነዚህ ከተሞች ውጭ ለሚገኙ ደንበኞች የማስገቢያ ጊዜው በየንባብ ቡድናቸው መሠረት እንደሚከተለው ይሆናል፦
👉 ቡድን 1፦ ከወሩ 21ኛው እስከ 24ኛው ቀን
👉 ቡድን 2፦ ከወሩ 28ኛው ቀን እስከ ቀጣዩ ወር 1ኛው ቀን
👉 ቡድን 3፦ ከወሩ 5ኛው እስከ 8ኛው ቀን
👉 ቡድን 4፦ ከወሩ 12ኛው እስከ 15ኛው ቀን
ደንበኞች የቆጣሪ ንባባቸውን ለማስገባት የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይችላሉ፦
✅ በቴሌግራም ላይ @Eeuchatbot ብለው በመፈለግ ቻትቦቱን ያግኙ።
✅ ቻትቦቱን ካስጀመሩ በኋላ “Send Meter Reading” የሚለውን አማራጭ ይምረጡ።
✅ ባለ 12 ዲጂት የደንበኛ መለያ ቁጥርዎን (Contract Account Number) ያስገቡ።
✅ ትክክለኛውን የቆጣሪ ንባብ በማስገባት ይላኩ።
ደንበኞች ንባባቸውን ማስገባት የሚችሉት በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ውስጥ ብቻ ነው። ከተፈቀደው ጊዜ በፊት ወይም ከገደቡ በኋላ ንባብ እንዲሁም የተሳሳተ ንባብ ማስገባት አይቻልም። ስለሆነም ደንበኞች ትክክለኛውን የቆጣሪ ንባብ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ማስገባታቸው አስፈላጊ ነው።
ይህ አዲስ አሰራር በቆጣሪ ንባብ አለመወሰድ ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ የፍጆታ ሂሳብ አዘገጃጀት ችግሮችንና የክፍያ መዘግየት ቅሬታዎችን ለመቀነስ የታለመ ሲሆን፣ ደንበኞች በቀላሉና በተመቻቸ መንገድ የቆጣሪ ንባባቸውን እንዲያሳውቁ ዕድል ይፈጥራል።
========================
ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃ ቻናላችንን join አድርጉ፣ለትክክኛ መረጃ ፈላጊዎች ጋብዙ👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
18 724
ተሿሚዎች ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ገቡ‼️
በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተሾሙ አዳዲስ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና ለመውሰድ ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ መወሰዳቸው ተሰማ። ይህ ያልተለመደ እርምጃ የመጀመሪያው ዙር ሲሆን በቀጣይም ሌሎች ባለስልጣናት በተከታታይ ተመሳሳይ ወታደራዊ ስልጠና እንደሚወስዱ ታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም በፓርላማ እና በተለያዩ መድረኮች ላይ፣ የመንግስት ሹመኞች "ቦርጭ ማውጣት እና ከመጠን በላይ መወፈር እንደሌለባቸው" በማንሳት፣ ጂም በመግባት እና ስፖርት በመስራት ንቁና ቀልጣፋ መሆን እንዳለባቸው በሳቅ የታጀበ ማሳሰቢያ ሲሰጡ ተሰምተው ነበር።
Via:- ዘሐበሻ
18 724
"ገጥመን ከማሸነፍ ውጪ አማራጭ የለንም" ሻብያ
በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ የሉአላዊነት ወረራ የፈጸመው ሻብያ ኢትዮጵያን ለመውጋት መዘጋጀቱን ይፋ አደረገ። በአፍሪካ ቀንድ ቀውሶችን በማቀጣጠል የሚታወቀው ሻብያ፤ ባሁኑ ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን አዲስ ግጭት ተንተርሶ ወረራ መፈጸሙ ይታወቃል።
ቡድኑ በዛሬው እለት በማስታወቂያ ሚኒስትሩ ድህረ ገጽ ባሰራጨው መግለጫ፣ "ኢትዮጵያን ገጥሞ ከማሸነፍ ውጪ አማራጭ የለኝም" ሲል አውጇል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሕዝብ የመረጠውን መንግሥት ባጭር ጊዜ ለማስወገድ እንደሚሰራ በመግለጫው አረጋግጧል።
18 724
ሰበር ዜና‼️
በትግራይ ክልል የሚገኙት ሦስት ከተሞች፣ አክሱም፣ ሽራሮ እና ዛላንበሳ በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስራ ገብተዋል!
18 724
ተመድ ዛሬ በኢትዮጵያ ጉዳይ በዝግ ሊመክር ነው‼
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና በአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ላይ ዛሬ በዝግ ለመምከር ቀጠሮ ያዘ።
ይህንን ስብሰባ አሜሪካ የጠየቀችው በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ውጊያ መባባሱን ተከትሎ እንደሆነ ተሰምቷል።
የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በትግራይ፣ በአፋርና በአማራ ክልሎች ያለው ግጭት ቀጠናውን ወደ ብስጭትና አለመረጋጋት እንዳይመራ በማስጠንቀቅ፣ የተኩስ አቁም እንዲደረግና የሰላም ንግግር እንዲጀምር ጥሪ ማቅረባቸውን ጠቅሶ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።
18 724
+1
እጃቸውን ሰጡ‼️
የጄኔራል ጆን ሜዲድ አጃቢዎችና ሹፌር ጄኔራሉን ከመኪናቸው ጋር በእንትጮ በረሃ ትተው ለመከላከያ ሰራዊት እጅ ሰጥተዋል።
አዚህ በተጨማሪ ኮሎኔል ብርሃኔ ገብረአናንያ (የቀድሞ የትግራይ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር አሁን የአርሚ 72 ምክትል አዛዥ) ከቡድናቸው ጋር እጅ ሰጥተዋል።
አዩዘሀበሻ
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
========================
ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃ ቻናላችንን join አድርጉ፣ለትክክኛ መረጃ ፈላጊዎች ጋብዙ👇👇👇👇??👇👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
18 724
እገላ ገርሁ - የተፈፀመ የድሮን ጥቃት‼
በእገላ ገርሁ ስርናይ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ሰፍረው የነበሩ የሎጂስቲክስ ቁሳቁሶችን የጫኑ የኤርትራ ጦር ተሽከርካሪዎች ትናንት በድሮን ጥቃት መመታታቸው ተገለጸ።
እንደ መረጃዎች ገለጻ፣ ጥቃቱ የተፈጸመው የጦር ሰራዊቱ ትምህርት ቤቱን ለመጠለያነት እና ለሎጂስቲክስ ማከማቻነት ሲጠቀምበት በነበረበት ወቅት ነው ተብሏል።
18 724
+5
በሽሬ ከተማ የህወሓት መሣሪያ ማከማቻዎች በሀገር መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር ዋለ
በሽሬ ከተማ ለረጅም ጊዜ ተደብቀው የቆዩ የህወሓት ቡድን መሣሪያ ማከማቻዎች በሀገር መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ምንጮች አስታውቀዋል። በማከማቻዎቹ ውስጥ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች፣ ተተኳሾች፣ የመሣሪያ መለዋወጫዎችና ወታደራዊ ትጥቆች እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ ያሳያል።
በሠራዊቱ ቁጥጥር ሥር ከዋሉት ቁሳቁሶች መካከል የ120 ሚሊሜትር ሞርተር፣ የቢኤም እና የኤግላ መሣሪያዎች፣ የእስትሬላ፣ ዙ-23፣ ክላሽ፣ ድሽቃ፣ መትረየስና የታንክ ተተኳሾች እንዲሁም የእጅ ቦንቦች እንደሚገኙበት ተገልጿል። የተገኙት የመሣሪያ መለዋወጫዎችና ወታደራዊ ትጥቆችም በሠራዊቱ ቁጥጥር ሥር ውለዋል።
በተያያዘ ዜና፣ በሽሬና በአካባቢው የሕወሓት አባላት እንደሆኑ የተገለጹ ወጣቶች የትጥቅ ትግሉን ትተው እጃቸውን እየሰጡ ነው።
@Seledadotio
@Seledadotio
18 724
+3
የመከላከያ ሠራዊቱ አዲግራት ከተማን ተቆጣጥሯል። አዲግራት ከተማን ሲቆጣጠር የከተማው ነዋሪዎችና የአካባቢው ህብረተሰብ ለሠራዊቱ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሽብር ጠማቂው ሻዕብያ እየተመራ የዕውር ድንብር ሽሽቱን የቀጠለው ህወሀት በሠራዊቱ ብርቱ ክንድ እየደረሰበት ባለው ብርቱ ጥቃት አዲግራትንና አካባቢውን ለቆ ፈርጥጧል።
የአዲግራት ከተማ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያደረጉት አቀባበል በፎቶ።(ናትናኤል መኮነን)
@Addis_News
@Addis_News
18 724
ወደ መቀሌ በረራ‼️
ወደ መቐለ ተቋርጦ የነበረው የመደበኛ የበረራ አገልግሎት ጥቅምት 1 ይጀመራል!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት አቋርጦት የነበረውን ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ የአየር በረራ አገልግሎት ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚጀመር ታውቋል።።
18 724
ዛላንበሳ‼️
በኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ከባድ የድሮን ጥቃት መፈፀሙ ታወቀ።
በዛሬው ዕለት መስከረም 29/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4:20 አካባቢ በኤርትራ ድንበር ዛላንበሳ አካባቢ በኦራል ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ታጣቂዎች ላይ የድሮን ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን የደረሰው ጉዳት ለጊዜው አልታወቀም።
18 724
ኢትዮጵያ ብዙ አይነት ድሮን እያመረተች መሆኑ ተዘገበ።
አለም አቀፍ ተነባቢ የሆነው Defense Express ጋዜጣ ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት በማሰባሰብ ስለታጠቀቻቸው እና በምታመርታቸው ድሮኖች ዙሪያ በሰጠው ማብራሪያ በአሁኑ ወቅት
- የቱርክ (Akinci እና Bayraktar TB2)
-የኢራን (Mohajer-6)፣ እና የቻይና (Wing Loong I) የሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖችን) በታጠቁ ኃይሎቿ ውስጥ በማካተት ሰፊ ስብስብ መገንባቷን ገልጿል።
በቅርቡ "ኢትዮጵያ የሩሲያ ስሪት የሆነው ‘Orion-E’ የተባለውን ዘመናዊ ሰው አልባ ድሮን መግዛቷ በተለያዩ አለም አቀፍ ሚድያዎች ሲዘዋወር የታየ ቢሆንም መረጃው የሀሰት መሆኑን እና ድሮኑ በኢትዮጵያ ባለሞያዎች በሀገር ውስጥ የተመረተ መለያ ስሙም " ነጋሽ" እንደሚባል ዘገባው ጠቅሷል።
18 724
በመንግስትና በፋኖ ኃይሎች መካከል የተካሄደ ከባድ ግጭት
በአማራ ክልል በመንግሥት ወታደሮችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ አካባቢዎች (መሀል ሜዳ፣ ዘመሮ እና ሞላሌ) በመንግስትና በፋኖ ኃይሎች መካከል በተካሄደ ከባድ ግጭት የሰዎች ህይወት ማለፉንና በንፁሃን ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼቨለ ገለጹ።
ደቡብ ወሎ መካነ ሰላም ከተማ ትናንት ከተሰማ የከባድ መሳሪያ ተኩስ በኋላ ዛሬ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖሩ ተጠቅሷል።
18 724
ባልና ሚስት በካቢኔ — ከአንድ ቤት ሁለት ሚኒስትሮች!
ከአንድ ማዕድ እስከ ሀገር መሪነት — የዶ/ር ጌዲዮን እና የወ/ሮ ሃና ታሪካዊ የካቢኔ ስየማ
አዲስ አበባ — በኢትዮጵያ ዘመናዊ የመንግሥት አስተዳደር ታሪክ ውስጥ አልፎ አልፎ የሚከሰት፣ የላቀ የሙያ ስኬት እና የጋራ ራዕይ መገለጫ የሆነ አዲስ ምዕራፍ ተመዝግቧል።
ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የሀገሪቱን የዲፕሎማሲ ማዕከል የሚመራውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በኃላፊነት እንዲረከቡ ሲሰየሙ፣ ባለቤታቸው ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ ደግሞ የህግና የፍትህ የበላይነትን የማስከበር ትልቅ ሀገራዊ አደራ ያለበትን የፍትህ ሚኒስቴርን በባለቤትነት እንዲመሩ ተሾመዋል።
ይህ አጋጣሚ የሁለት ከፍተኛ የህግ ባለሙያዎችን የእውቀት እና የልምድ ጥምረት የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ፣ ከአንድ ማዕድ የተነሱ ሁለት መሪዎች በሀገሪቱ የካቢኔ ማዕድ ላይ ጎን ለጎን ተሰልፈው ሀገርን የሚያገለግሉበትን ልዩ ታሪካዊ አጋጣሚ ፈጥሯል።
ሁለቱም ተሿሚዎች በህግ እና በመንግሥት አስተዳደር ዘርፍ የካበተ ልምድ ያላቸው፣ ቀደም ሲል በነበሯቸው የኃላፊነት ቦታዎች ውጤታማነታቸውን ያረጋገጡ ከፍተኛ የሙያ ባለቤቶች ናቸው።
በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ሁለት የካቢኔ ሚኒስትሮች ተሰይመው የሀገሪቱን ታላላቅ መዋቅሮች በጋራ ሲመሩ ማየት በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ሆኖ ተመዝግቧል።
የሀገሪቱን የውጭ ግንኙነት እና የፍትህ ስርዓት በግንባር ቀደምትነት የመምራት ታላቅ ሀገራዊ አደራ የወደቀባቸው እነዚህ ሁለቱ መሪዎች፣ የላቀ የመንግሥት ስራ ውጤታማነት ያሳያሉ ተብሎ ትልቅ እምነት ተጥሎባቸዋል።
ይህ ያልተለመደ የሙያ እና የህይወት ጉዞ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን ያተረፈ ሲሆን፣ ለሁለቱም አመራሮች በያዙት ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነት ስኬታማ እና ፍሬያማ የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞት እንገልፃለን።
@Seledadotio
@Seledadotio
18 724
ሰበር! "ራሴን ከመከላከል ውጪ አማራጭ የለኝም" ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በመግለጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በደብዳቤ አሳወቀች።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት በጻፉት ደብዳቤ የኤርትራ ሠራዊት ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን ገልጸዋል።
18 724
" መከላከያ ሠራዊትና የትግራይ የሰላም ኃይል መላውን ክልል ሙሉ በሙሉ በእጃቸው ለማስገባት ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የሚገኙ ሦስት ከተሞች ብቻ ነው የቀሯቸው"
" እነሱም፦ አክሱም፣ ዓድዋ እና ዓዲግራት ናቸው። የህወሃትና የኤርትራ ኃይሎች በድንበር አካባቢ ኃይላቸውን መልሰው ለማደራጀት ወደኃላ እያፈገፈጉ ነው።"
"ከዚህ በኋላ ያለው ሂደት የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ውሳኔ የሚጠይቅ ይሆናል። ጄነራሎቹና ወታደሮቻቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ በስኬት ለማጠናቀቅ በቂ ዝግጅት እንዳላቸው በተግባር አሳይተዋል።”
ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ
18 724
Update❗
ሽሬ❗️
ከማይፀብሪ-አዲ ገብሩ-እንዳ ባጉና-ሽሬ-አክሱም መስመር ላለፉት ሁለት ሳምንታት ከፍተኛ ውጊያ ሲስተናገድበት የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት መስከረም 28 የህወሓት ተዋጊዎች ከእንዳባጉና እና ሽሬ ለቀው የወጡ ሲሆን መከላከያ ሠራዊት ዛሬ አመሻሽ ላይ ሽሬ መግባቱን የአካባቢው ምንጮች ከምስል ጋር አጋርተውናል።
