የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU 的分析概览
频道 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 14 319 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 6 154,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 360 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 14 319 名订阅者。
根据 22 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 507,过去 24 小时变化为 11,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 49.23%。内容发布后 24 小时内通常能获得 13.09% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 0 次浏览,首日通常累积 1 875 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 0。
📝 描述与内容策略
尚未提供频道描述。
凭借高频更新(最新数据采集于 23 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
14 319
订阅者
+1124 小时
+1077 天
+50730 天
帖子存档
"አየሁም፥ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥" ራዕ 5፡11
ኅዳር 13 በዚህች ቀን የቅዱሳን አዕላፍ መላእክት መታሰቢያ ነው። ከቅዱሳን መላእክት ረድኤት በረከት ያካፍለን። ሰናይ ሌሊት! መልካም በዓል!
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
“ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ።” ዳን 10፡13
👉🏻 #ሚካኤል ማለት መኑ ከመ አምላክ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው የሚል ትርጉም አለው። ይህም እንደ እግዚአብሔር ያለ በባሕርይው ቅዱስ የሆነ ፣ እንደ እግዚአብሔር ያለ ንጹሐ ባሕርይ ፣ እንደ እግዚአብሔር ያለ ፍጹም ማነው የሚል ነው። ቅድስና ፣ ንጽሕና እና ፍጹምነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ ከእግዚአብሔር በቀር የለምና።
👉🏻 ሚካኤል ፍጥረቱ በዕለተ እሑድ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘፍ 1፡3 ላይ “እግዚአብሔርም ብርሃን ይሁን አለ።” ብሎ ብርሃንን በፈጠረ ጊዜ ሕልውና መላእክት ታውቋል። እንዴት ቢሉ ሰሚ በሌለበት ተናጋሪ አይናገርምና እንዲሁ ልዑል እግዚአብሔር አስቀድሞ ሰሚአን የሆኑ መላእክትን ስለፈጠረ ብርሃንን በነቢብ (በመናገር) ፈጥሯል። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በዛሬው ዕለት ኅዳር 12 ቀን በዓለ ሲመቱ ይታሰባል። ይህ ቅዱስ መልአክ መጋቤ ብሉይ እየተባለ ይጠራል። በብሉይ ብዙ ገቢረ ተአምራትን እየሠራ በጎላ በተረዳ አበው ነቢያትን ስለተራዳና ከእግዚአብሔር ተልኮ ድንቅ ድንቅ ሥራዎችን በማድረጉ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል።
👉🏻 በዘኁ 22፡21-35 ላይ የእግዚአብሔርን ሕዝብ እሥራኤል ዘሥጋን ያለአግባብ ሊራገም የወጣውና ሀብተ መርገም የተሰጠው በልአምን የተቋቋመው እሥራኤል ዘሥጋን ከእርግማን ያዳናቸው ይህ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው።
👉🏻 ኢያ 5፡13-15 ላይ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል በጌልጌላ ለነቢዩ ኢያሱ ወልደ ነዌ ተገልጦለት ነበር። ኢያሱም የመልአኩን ማንነት ሲያረጋግጥ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን?” አለው። መልአኩም መልሶ “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ” ቢለው ኢያሱ በመልአኩ ፊት በፍርሃት ሰግዷል። “እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።” በሚለው ታላቅ የእምነት ንግግሩና ምክሩ የምናውቀው መስፍን ዝቅ ብሎ ለመልአኩ የሰገደው ስለምንድን ነው ብለን ብንጠይቅ ለቅዱሳን መላእክት የጸጋ ስግደት ስለሚገባ ነው። ቀድሞ ከሊቀ ነቢያት ሙሴ ጋር ሆኖ ሕዝቡን ሲመራ የነበረው ይህ ቅዱስ መልአክ ከኢያሱም ሳይለይ እስራኤል ዘሥጋ በጠላቶቻቸው እንዳይዋረዱ ሲረዳቸው ነበር። ዛሬም ይህ መልአክ ክርስቲያኖች በጠላት ዲያብሎስ እንዳይዋረዱ ይራዳቸዋል።
👉🏻 ዘጸ 23፡20-22 ላይ እግዚአብሔር አምላክ ለእርሱ የሚታዘዙትን ሁሉ በመንገዳቸው እየጠበቃቸውና እየተራዳቸው ወደ ርስት መንግሥተ ሰማይ መርቶ ለክብር እንዲያበቃቸው እንዲሁም አመጸኞችን ይቀጣ ዘንድ ለዚህ ቅዱስ መልአክ ክብርና ሥልጣን እንደሰጠው ይናገራል። “በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወደ አዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ መልአኬን በፊትህ እሰዳለው።” እንዲል። በዚህ ቃል መሠረት እግዚአብሔር በመልአኩ በቅዱስ ሚካኤል አማካኝነት እሥራኤል ዘሥጋን ከግብጽ ባርነት ወደ ምድረ ርስት ከንአን እንደሚያስገባቸው ተናግሯል። ታዲያ እሥራኤል ዘነፍሥ የሆንን እኛ ክርስቲያኖችን ደግሞ በግብጽ ከተመሰለች ሲኦል በምድረ ርስት ከንዐን ወደ ተመሰለች ገነት ርስት መንግሥተ ሰማይ በአማላጅነቱ በተራዳኢነቱ እንደ ምን አያገባን? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልአኩ አማላጅነትና ተራዳኢነት ፈጣን አገልግሎቱም ርስቱን እንደምንወርስ ሲናገር “ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስ አይደሉምን?” ብሏል። ዕብ 1፡14 እኛም ከቅዱሳን መናፍስት ወገን አንዱና አለቃቸው የሆነ ቅዱስ ሚካኤል መዳን መንግሥተ ሰማይን እንወርስ ዘንድ የሚላክ የሚያገለግል አይደለምን እንላለን። ወደ ቀደመው ነገራችን ስንመለስ ገጸ ንባቡ እንዲህ ብሎ ይቀጥላል “በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።” የእግዚአብሔር ስም በስሙ ላይ ላለ ለዚህ ታላቅ መልአክ የመፍረድንም ሥልጣን ከአምላካችን እንደተሰጠው ትመለከታላችሁን? ከማማለድም በላይ ኃጢአት የሚሠሩትን አመጸኞችን የመቅጣት ሥልጣንን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቸረው ደግ ሩህሩህ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው። በአንጻሩ ቃሉን የሚሰሙትን እርሱን የሚያከብሩትን ደግሞ በረድኤት በበረከት ይሞላቸዋል ፣ ምድራቸውን ከበሽታ ይፈውስላቸዋል ፣ እህሉንም ውኃውንም ይባርካል ፣ ጠላቶቻቸው የሆኑ አጋንንትን ከእግራቸው በታች ይቀጠቅጥላቸዋል።
በተጨማሪም መልአሉ ቅዱስ #ሚካኤል
👉🏻 ድኅነተ ሥጋ ወነፍስ ያሰጣል። መዝ 33፡7 ፣ ዘፍ 48፡16 ፣ ዕብ 1፡14
👉🏻 ከክፉ ሁሉ ይራዳል። ዳን 10፡13 ፣ ዳን 12፡1
👉🏻 ያማልዳል ያስታርቃል። ዘካ 1፡12-13
👉🏻 ለሰው ሁሉ በጎን የሚያደርግ መልአክ ነው። ሔኖክ 6፡1-2
👉🏻 የከበረ መልአክ ነው። ከክብሩ የተነሳም ምድር ሁሉ ትበራለች። ራእ 10፡1 ፣ ራእ 18፡1
👉🏻 የትሕትና አባት ነው። ይሁ 1፡9
👉🏻 በሰዎች ድኅነት ሀሴት ደስታን የሚያደርግ ነው። ሉቃ 15፡7
👉🏻 በተጨነቅን ጊዜ የሚያበረታን የሚያረጋጋን የሚያጽናናን መልአክ ነው። ሉቃ 22፡43 ፣ ዳን 10፡20
የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ረድኤቱ አማላጅነቱ ፈጣን ተራዳኢነቱ ዘወትር ከኛ ጋር ይሁን!!! መልካም በዓል!
ይቆየን።
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
"አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ!" መኃ 7:1
ሰላማጢስ ማለት ሰላማዊት የሰላም መገኛ ማለት ነው። እውነተኛዪቱ የሰላም መገኛ እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። በባሕርይው ሰላም የሆነ ክርስቶስ ከእርሷ ተገኝቷልና ሱላማጢስ ሰላማዊት ትባላለች። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች በላከላቸው መልእክቱ "እርሱ ሰላማችን ነው።" ብሎናል። ኤፌ 2÷14 ራሱ ጌታችንም በመዋዕለ ሥጋዌው "ሰላሜን እተውላችኋለሁ። ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም።" ዮሐ 14፡27 በማለት የሰላም ባለቤት እርሱ መሆኑን ነግሮናል። ይህ የሰላም ባለቤት የተገኘው ደግሞ ከእመቤታችን በመሆኑ እርሷም ሰላማዊት ተብላለች። "ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ነው፤ ስሙም ድንቅ መካር ኃያል የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።" እንዲል። ኢሳ 9፡6
ሱላማጢስ የተባለች እመቤታችንን አባቷ ሰለሞን በትንቢት መነጽር የስደቷን ነገር በዘመረበት መዝሙሩ "አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ተመለሺ" ብሏታል። ፈጣኒቱ ደመና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቀዳማዊቷ ሔዋንን ስደት ስደቷ አድርጋ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በግብጽ በረሀ ለ3 ዓመት ከ6 ወር ያህል ተንከራትታለች። "ልጄን ከግብጽ ጠራሁት" ሆሴ 11፡1 የሚለው የነቢዩ የሆሴ ቃል ይፈጸም ዘንድ ከቆየችበት ከባዕድ ሀገር ግብጽ ወደ ሀገሯ ወደ ገሊላ ተመልሳለች። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አስቀድሞ ለዮሴፍ ወደ ግብጽ እንዲወርድ እንደነገረው ሁሉ "የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ።" ብሎ እንዲመለስም አዝዞታል። ያን ጊዜ ሱላማጢስ እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ወደ እስራኤል መጥታ በናዝሬት ገሊላ ኖራለች።
የእመቤታችን ከግብጽ ወደ እስራኤል መመለሷ ዛሬም በኃጢአት እና በዓለም ለተሰደድን ልጆቿ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ወደ ገቢረ ጽድቅ እንድንመለስ ትልቅ ትምህርት ያስተምራል። ሰለሞን እናይሽ ዘንድ ተመለሺ እንዳላት እኛም ወደ ቅድስት እናታችን ወደ ቤተ ክርስቲያን ተመልሰን በዐይነ ልቡናችን እመቤታችንን እየተመለከትን እንድንኖር አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን።
ይቆየን!
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
