የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU 的分析概览
频道 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 14 376 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 6 129,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 349 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 14 376 名订阅者。
根据 24 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 522,过去 24 小时变化为 23,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 27.03%。内容发布后 24 小时内通常能获得 N/A% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 880 次浏览,首日通常累积 0 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 33。
📝 描述与内容策略
尚未提供频道描述。
凭借高频更新(最新数据采集于 25 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
14 376
订阅者
+2324 小时
+1087 天
+52230 天
帖子存档
“ተቀጸል ጽጌ” (አበባን ተቀዳጅ) በዓል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመከበር ላይ ይገኛል።
በዐፄ ዳዊት ዘመን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ግማደ መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ የገባበት “ተቀጸል ጽጌ” (አበባን ተቀዳጅ) በዓል መስከረም ፲ ቀን በየዓመቱ ይከበራል፡፡ በዘንድሮው ዓመትም በዓሉ ሲከበር ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፤ የባሕር ዳር እና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነትና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ካህናት ምእመናን የሰንበት ትምሕርት ቤት ዘማርያን ተገኝተዋል።
በክብረ በዓሉ ያሬዳዊ ዜማ በአጫብር በሊቃውንት ቀርቧል። የየረር ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያንም የአጫብር ወረብ አቅርበዋል። “ተቀጸል ጽጌ” (አበባን ተቀዳጀ) የሚለውን መዝሙር የዜማን የቅኔ መሥራች የሆነው ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ ነው። የተመሠረተውም በ፮ኛው መ/ክ/ዘ መጀመሪያ በዐፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት ነው። በዚሁ መሠረት የክረምቱና የልምላሜው ጊዜ አልፎ የአበባውና የፍሬው ጊዜ በሚተካበት በመስከረም ፳፭ ቀን ቅዱስ ያሬደ ውደ ንጉሡ ዙፋን ቀረቦ “ተቀጸል ጽጌ ገብረ መስቀል ዐጼጌ” በማለት ዘምሯል፡፡ ዐፄ ገብረ መስቀል ክረምቱ አልፎልሃልና አበባን ተቀዳጅ፣ አበባን ተላበስ እያለ ያወድሰው የነበረው በዓላዊ ትውፊት እየተቀባበለ እስከ ፲፭ኛው ምዕት ዓመት ደርሶ ነበር፡፡ በኋላም ዐፄ ዳዊት የጌታችን ግማደ መስቀል ከኢየሩሳሌም አስመጥቶ መስከረም ፲ ቀን ወደ ኢትዮጵያ በመድረሱ ግማዱም በንጉሡ ምክንያት በመምጣቱ “ዐፄ መስቀል” እየተባለ መከበር ሲጀምር፣ የ፳፭ኛው ቀን የአበባው በዓልም በ፲፭ ቀን ወደ ኋላ በማፈግፈግ በአንድነት የዐፄ መስቀልና ተቀጸል ጽጌ እንዲከበር ተወስኖ እስካሁን ድረስ በታላቅ ሥነ ሥርዐት በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
©eotc tv
በዚህች ቀን ከእመቤታችን ስዕል ተአምር ተገለጠ!
ጼደንያ ማርያም! እንኳን አደረሳችሁ!
https://www.tiktok.com/@eotc_gssu/video/7416622754000063775
+4
የተማሪዎች የምረቃ መርሐግብር በማዕከላዊ ጎንደር
(የሰ/ት/ቤቶች አንድነት) መስከረም 06/01/2017 ዓ.ም
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በደብረ ሣኅል ቅዱስ ሩፋኤል ወአቡነ ሐራ ድንግል ቤ/ክ ውሰጥ የሚገኘው የውሉደ ያሬድ ሰ/ት/ቤት በ2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ሥርዓተ ት/ት መሰረት የ1ኛ እና የ2ኛ ክፍል ትምህርት የተማሩ ልጆችን አስመረቀ።
በመርሐ ግብሩ ከማዕከላዊ ወደ ትልቆች ክፍል ያለፉ ልጆችን የምስክር ወረቀት የመስጠት መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን በጉባኤው የማዕ/ጎ/ዞ/ሃ/ስ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍል ሐላፊ ሊቀ አዕላፍ ብርሃኑ ፍትሕአምላክ: የማዕ/ጎ/ዞ/ሃ/ስ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ተቀዳሚ ም/ሰብሳቢ ዲያቆን አንዳርጋቸው እንዳለው :የደብሩ ሰ/ጉ/አባላትና ካህናት አገልጋዮች እንዲሁም የአካባቢው ምዕመናን በተገኙበት በቀን 05/01/2017 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ተከናውኗል::
በዚሁም ዕለት በዓለማዊ ት/ት ደረጃ ለያዙ: የ12ኛ ክፍል መግቢያ ፈተና ላለፉ እንዲሁም ሰ/ት/ቤቱን በሐሳብ እና በገንዘብ ላገዙ ባለ ድርሻ አካላት ሰንበት ት/ቤቱ እውቅና ሰጥቷል::
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ይከታተሉ።
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
+4
በድሬደዋ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሥርዓተ ትምህርት ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተከናወነ።
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) መስከረም 05/01/2017 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድሬደዋ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የ2016 ዓ.ም የሥርዓተ ትምህርት ማጠቃለያ መርሐ ግብር የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ መልአከ ኃይል አባ ተስፋዬ እማምሰው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ዋና ክፍል ኀላፊ መጋቤ ኅሩያን ቀሲስ ሐዲስ ኪዳነ ማርያም በትምህርታቸው የደረጃ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በኆኅተ ሰማይ ቅድስት ማርያም ካቴድራል ሁለገብ አዳራሽ ተከናውኗል።
በዕለቱም ከየአጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተማሪዎች የካርድ እና የምስክር ወረቀት የመስጠት መርሐ ግብር እንደ አጠቃላይ ደረጃ ለወጡት ተማሪዎች እና በንቃት ሲያገለግሉ ለነበሩ አገልጋዮች ደግሞ ሽልማት እና እውቅና የመስጠት መርሐ ግብር እንደተከናወነም ተገልጿል።
በመጨረሻም የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ መልአከ ኃይል አባ ተስፋዬ ከ1ኛ-4ኛ ክፍል የታተሙ መጻሕፍትን ለሰ/ት/ቤቶች ያስረከቡ ሲሆን የሥርዓተ ትምህርቱን አተገባበር በማድነቅ በቀጣይ ለሚሰራውም ትውልድን የመቅረጽ ስራ ሀገረ ስብከቱ የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ በመግለጽ መርሐ ግብሩን በፀሎት ዘግተዋል።
መረጃው የአንድነቱ ትምህርት ክፍል ነው።
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
+4
በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ ከተማ የሥርዓተ ትምህርት የግንዛቤ መስጫ መርሐ ግብር ተከናወነ።
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት (መስከረም 5/2017 ዓ.ም)
በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ ከተማ መንበረ ጵጵስና እየተከናወነ የሚገኘው ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የተዘጋጀውንና በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ ትግበራ ላይ በሚገኘውን ሥርዓተ ትምህርት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
በሥልጠናው የሀገረ ስብከቱ ማደራጃ መምሪያ መ/ሰ አክሊሉ የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤት አንድነት ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ መምህር መኮንን የአድባራት አስተዳዳሪዋች የሰበካ ጉባዬ አባላት የሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮችና የተለያዩ ማኅበራት የተሳተፉበት ነው።
ሥልጠናው የተሰጠው በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አዘጋጅነት በ2016 ዓ.ም በክረምት ሥልጠና ሀገረ ስብከቱን ወክለው በተሳተፉ መምህራን ሲሆን የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዓመት እንዲረዳ የመማርያ መጻሕፍት ግዥ በመፈፀም በሥርጭት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
+3
በደሴ ከተማ ለሚገኙ ከሁሉም አድባራት ለተወጣጡ የሰ/ት/ቤት መምህራን እንዲሁም የስብከተ ወንጌል ሐላፊዎች እና የመጻሕፍት መምህራን አዲሱን የሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርትን በተመለከተ በጠቅላይ ቤተክህነት ለ20ቀናት ሥልጠና በወሰዱ መምህራን ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሥልጠና በደሴ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት አማካኝነት በደሴ ቅዱስ ገብርኤል ካቴደራል ሰ/ት/ቤት አዳራሽ መስጠት ተጀምሯል።
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) መስከረም 04/01/2017 ዓ.ም
በሥልጠናው የተገኙ የወረዳው የሰ/ት/ቤቶች ክፍል ሐላፊ ፣ የስብከተ ወንጌል ሐላፊዎች እና የመጻሕፍት መምህራን ፣ የሰ/ት/ቤት መምህራን እና የሰ/ት/ቤቶች አንድነት አመራሮች ተገኝተዋል። በመጀመሪያ ቀን የግማሽ ቀን ውሎ በሥርዓተ ትምህርቱ ትግበራ ዙሪያ እንዲሁም በስልጠናው ለተገኙ አካላቶች መልእክት በዲ/ን ሀብታሙ ለማ የደቡብ ወሎ ሃ/ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ ተሰጥቶ በወ/ም ሚኪያስ አወቀ ለሰልጣኞች የአራት ቀን ውሎ አጠቃላይ ገለጻ ተሰጥቶ በወ/ም መስፍን አበባው እና በወ/ም ኢዩኤል ሞገስ አጠቃላይ የሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ሥልጠና ተሰጥቷል። ከሻይ እረፍት በኋላ በወ/ም ሚኪያስ ዘነበ እና በእህት ቃልኪዳን ሰይድ የመሠረተ ሃይማኖት(ዶግማ) ክፍለ ትምህርት ለሰልጣኞች ተሰጥቶ የግማሽ ቀን ሥልጠናው ተጠናቋል። ሥልጠናው ለ 4 ቀን የሚቆይ ይሆናል።
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
+3
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወሰብዓቱ ዓመተ ምሕረት የእንኳን አደረስዎ መርሐ ግብር በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተከናወነ።
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
