الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
前往频道在 Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
显示更多未指定国家未指定类别
2 157
订阅者
-224 小时
+367 天
+41730 天
帖子存档
📣 የሶላተል ኢስቲስቃዕ በደሴ ከተማ 📣
⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞
በሃገሪቱና በሌሎች ከተሞች ላይ ዝናብ በመጥፋቱ ምክንያት እሁድ በሆጤ እስታዲየም በጧት 03፡00 ሰአት ላይ የሶላት አልኢስቲስቃዕ ይሰገዳል ‼
ሁሉም ሰው እንዲገኝ በኡለማዎች ታዟል አላህ የሚጠቅምና በረካ ያለው ዝናብን እንዲለግሰንና ወንጀላችንንም ይቅር እንዲለን: እንዲታረቀን ዱአ እናደርጋለን እንድትገኙ አደራ።
ይህ ሱና በሌሎች ከተሞችም ቢደረግ ኸይር ነው እንላለን።
★ https://t.me/alruqyehsheriyeh ★《اللَّهُمَّ صَلِّ علَى مُحَمَّدٍ وعلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كما صَلَّيْتَ علَى إبْرَاهِيمَ، وعلَى آلِ إبْرَاهِيمَ، إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ علَى مُحَمَّدٍ وعلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كما بَارَكْتَ علَى إبْرَاهِيمَ، وعلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ.》
ጌታዬ ሆይ! እውቀትን ጨምርልኝ በል አላህ ሁላችንንም ጠቃሚ እውቀት ሰጥቶ በተማርነው የምንሰራ እና ለሌሎችም የምናካፍል ያድርገን።
የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል "ከቀኖቻችሁ ሁሉ በላጩ ቀን የጁሙዓ ቀን ነው። በእሱ ላይ በእኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ ሰለዋታችሁ እኔ ዘንድ ይቀርባልና።" (አቡ ዳውድ)
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ (አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ዓላ ነቢዪና ሙሐመድ በዚህ በተባረከ የጁሙዓ ቀን ዱዓችን ተቀባይነት የሚያገኝባትን ሰዓት የምናገኝባት ወንጀሎቻችን የሚማሩባት እና በረከት በቤታችን የሚሞላበት እንዲሆንልን እንመኛለን
Repost from 🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
ዐጅብ ....
ንጉስ ሹማምንቱም
ፌደራል ፖሊሱም፣
አዛውንት ወጣቱ
ደሀው ባለ ሀብቱ ፣
አንዱ አንዱን ያፍራል
አንገቱን ይሰብራል፣
ወንጀል ለመፈፀም አንዱ ከሌላው ፊት
ሰአት ይጠብቃል ዞር እስኪባልለት ፣
ይህ ሁሉ ፍርሀት ለሰው ብቻ ሆነ
አይን ማፈር ተወች ልብም ደነደነ
አሏህን ፍራቻ አፍ ላይ ብቻ ሆነ፣
ፍፁም ተራራቀ ቃላችን ከተግባር
ድብልቅልቁ በዛ ሴቱ ከወንዱ ጋር
መሆኑ ተረስቷል ኻሊቁ ከኛ ጋር ፤
...........................................
✍ Sonu (جميلة)
በጣም ነው ያመረባት እ ውበቱን ደፍቶባታል👌👌👌
በጣም ነው ያመረቺኝ ለመፖሰት ራሱ እየሳሳኋት ነበር 🤔
ኢቶ ላሉት ሰወች የሳኡድ ምድር እደዚህ ነው የሚመስላቸው ✅✅
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
➲➢ ትላልቅ ኢስላማዊ
የቴሌግራም ቻነሎች መግዛት ይፈልጋሉ ?
አስቾካይ 2 ቻናል ብቻ ነዉ ያለን
🏷 9.3k subscribers
🏷 7.6k subscribers
👆በርካሽ መግዛት የፈለግ ብቻ ያናግረኝ
✍ ወረባ አገሬ 💫
አገሯ አረንጓዴ የእሸቱ ዘለላ
ከዚህ ውበት በላይ ምን አለና ሌላ?
በአረንጓዴው ማሳ በወርቃማው ሰብል
ማሺላና ጤፉ ልብን የሚያማልል
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🔴 ቀጥታ ስርጭት | ልዩ የሴቶች ሙሐደራ!
ሸይኽ አቡ ሀማም አሽ-ሺህሪ (ሀፊዘሁላህ)
👇👇
https://t.me/AbuSufiyan_Albenan?livestream=70a0becbab4da51f80
ኡሚ 🦋 አቡይየናፈቀው አይኔ አይኖቻችሁን ሲያይ የዘመናት ናፍቆት ሲወገድ ከኔላይ። እንዳልኩት አልሆነም ተስፋዬ ረዘመ በሰው ሀገር አፈር አመት ተራዘመ አባቴ በስተርጅና አይኑን አደከመው እናቴ ናፍቆቷ ልቧን አሳመመው የወጣሁበት ስደት እንደ ሰንሰለት አስሮኝ የምወዳቸውን እናትና አባቴን ከቅፋቸው ነጥቆኝ። ኢንሻአላህ ያረብ ተስፋዬን አትቁረጠው ሞት ሳይቀድመኝ ሄጄ እቅፋቸውን ላግኘው አባቴ በስተርጅና በስስት አይኑ ሲጠብቀኝ እናቴ በዱዓ በደስታዋ እያሰበችኝ እኔም በስደቱ አገር በናፍቆት አለሁኝ ኢንሻአላህ እሄዳለሁ አባቴንና እናቴን ለመሳም ያ የረጅም ዘመን ናፍቆት ይለወጥና በሰላም አሏህ ሆይ እድሜ ሰተህ ሞት ሳይቀድመን በእርጅናቸው ዘመን እንድንተያይ አድርገን አባቴ ያ ያረጀው እጁ ጉልበቱ እየደከመ ሲጠብቀኝ እኔ እዚህ ሩቅ ሆኜ ናፍቆታቸው ነው የሚሳምመኝ ኢላሂ አንተ ጠብቅልኝ ስመጣ እደሸኙኝ ስመለስም ተቀባይ አድርግልኝ💧
Repost from ነበእ የቂርአት ሴንተር
ለዐረብ ሀገር ወንድምና እህቶች
~
① ከሁሉም በፊት ለዲናችሁ ቅድሚያ ስጡ። ከተውሒድ ጀምራችሁ ግንዛቤያችሁን በተለያዩ መንገዶች አስፉ። ለአላህ ምስጋና ይግባውና በዚህ በኩል ብዙ ወንድሞችና እህቶች ዘንድ ጥሩ ተነሳሽነት ይታያል።
② ለአሰሪዎቻችሁ ታማኞች ሁኑ። የሰው ሀላፊነት እስከተቀበላችሁ ድረስ አላህን ፈርታችሁ ሀላፊነታችሁን ባግባቡ ተወጡ። በሰዐትም፣ በስራም፣ በገንዘብም፣ በክብርም፣ በልጆችም የምትታመኑ ሁኑ። አማናን መወጣት ትልቅ ሃላፊነት ነው።
③ በተቻላችሁ ከአላስፈላጊ የወንድና የሴት ቅልቅል ተጠንቀቁ። በጋራ የኪራይ ቤቶች ሊፈፀሙ ከሚችሉ አደጋዎች እራሳችሁን ጠብቁ።
④ እርስ በርስ ተዛዘኑ። ስራ ለሌለው ስራ በመፈለግ፣ ለተቸገረው በብድር ወይም እራስን በማይጎዳ መዋጮ ተጋገዙ።
⑤ ከወንጀለኞች ራቁ። ዐረብ ሀገር በርካታ ኢትዮጵያውያን በወንጀል ስራ ላይ መሰማራታቸው የሚታወቅ ነው። በነሱ ሳቢያ ኢትዮጵያውያን ባጠቃላይ በተደጋጋሚ ስማቸው ይጠፋል። የሚገርመው ብዙ ለነዚህ ወንጀለኞች ሽፋን የሚሰጡ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ነው። በነሱ ጥፋት አብራችሁ እንዳትጎዱ ተጠንቀቁ። እንዲያውም ለሌላ የሚተርፍ የተረጋገጠ ወንጀል ካያችሁ ለሚመለከተው አካል ጠቁሙ። ይሄ ለዲናችሁም ለገፅታችሁም ዋጋ አለው።
⑥ ቤተሰቦቻችሁን አትርሱ። ወላጅ ወላጅ ስለሆነ ብቻ ከባድ ሐቅ እንዳለው እሙን ነው። ከዚያም ባለፈ ስንት ፍዳቸውን አይተው አሳድገዋል። ዐረብ ሀገር ትሄዱ ዘንድ የተቸገሩላችሁም ብዙ ናቸው። እነዚህን ታሳቢ በማድረግ ወላጆቻችሁን አትርሱ። በዚያ ላይ አንዳንዶቻችሁ ወደ ወላጆቻችሁ ልጅ የላካችሁ ትኖራላችሁ። በዚህን ጊዜ ሐቁ ድርብርብ ነውና ኣኺራችሁን እንዳታጨልሙ ተጠንቀቁ።
⑦ እራሳችሁን አትርሱ። የወጣችሁት እንጀራ ፍለጋ ነው። ከፋም ደላ የሰው ሀገር የሰው ነው። ህልማችሁ ቋጥሮ ወደ ሀገር ለመመለስ እንጂ በልቶ ለመውዛት፣ ለብሶ ለመድመቅ አይደለም። ለዚህ ደግሞ ብልጥ መሆን ያስፈልጋል። መስራቱን ቻሉበት። መያዙንም ቻሉበት። ወጭ ቀንሱ። ለቤተሰብ ስትልኩም አቅማችሁንም፣ ኑሯቸውንም፣ ሁኔታቸውንም እያገናዘባችሁ ይሁን። ለጎረምሳ ጫት መቃሚያና መንሸራሸሪያ አትላኩ። በዚህ ወንድሞቻችሁን ታበላሻላችሁ እንጂ አትጠቅሟቸውም። ገንዘባችሁንም አጥታችሁ ወንጀለኛም ትሆናላችሁ። ባጭሩ የምትሰሩትን ገንዘብ ቁም ነገር ላይ ለማዋል ተጣጣሩ። ባዶ እጃችሁን ላለመግባት በተቻላችሁ ተጠንቀቁ። ችግር መጥፎ ነው። ቤተሰብ እንኳን እንዲገፋችሁ ያደርጋል። አገራችን ለባዶ እጅ ቀርቶ ለያዘም እየከበደ ነው።
⑧ እቅድ ይኑራችሁ። ለቆይታችሁ ገደብ አስቀምጡለት። በግምት አትኑሩ። ሁለት አመት ሰራርቼ አገሬ እገባለሁ ብለው ሃያ አመት የኖሩ አሉ። ከአላማ ካልተወጣ ክፋት አልነበረውም። እየባከኑ ሲሆን ግን ያሳዝናል። "ምን ይዤ ልግባ?" እያሉ እየተብከነከኑ መኖር ይጎዳል። ስለዚህ ገደብ ያለው እቅድ ይኑራችሁ። ለእቅዳችሁም በትጋት አስቡ፣ በትጋት ስሩ። መገናኘታችሁ እቅዳችሁን የሚያሰናክል፣ ለትርጉም የለሽ ወጭ የሚዳርግ ከሆነ ተራራቁ።
⑨ ሴቶች ሆይ! መንገደኛ አታግቡ። እስኪ አሁን ሂንዲ፣ ፓኪስታኒ፣ ባንጋሊ ማግባት ምን ይባላል? እንዲህ አይነቱ ትዳር ዘላቂ የመሆን እድሉ እጅግ የጠበበ ነው። ልጅ ከመጣም ከነ ጭራሹ አባቱ ጋር አይኖርም። ስለዚህ ለራስም ለልጅም ፈተና ነው።
(10) ለኸይር ስራ እጃችሁን ስትዘረጉ ጥንቁቅ ሁኑ። ኸይር አትስሩ አይባልም። ግን በትክክል ለታለመለት ግብ የሚደርስ መሆኑን ቢያንስ ሚዛን የሚደፋ ግምት ያዙ።
(11) ለትዳር ክብር ይኑራችሁ። ትዳርን መስፈርት በማያሟላ በተጨመላለቀ መልኩ ሳይሆን በሥርዓት ፈፅሙ። አትበዳደሉ። ኣኺራችሁን በማይጎዳ መልኩ በስርኣት ኑሩ። ለጋብቻ የተጋነነ ወጭ አታውጡ። ከሰሞንኛ ሆይሆይታ ይልቅ ለዘላቂው ትዳራችሁ ቅድሚያ ስጡ። መለያየት ግድ ካለም ባግባቡ ይሁን።
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/yehak_mnged
https://t.me/yehak_mnged
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #አራት_⓸ ፣
✍ #ፀሀፊ_☞ #አቡ_ኹዘይማ
.................. #እራቢያ ................
#ባለቤቱ_የሌለው_ስደት"
የባቲ በረሃና የጥላ ስር ዕንቁ
ታሪኩ ቀጠለ... ከኮቻ ተነስተን ባቲ ስንደርስ የድካም ካባ ደርበን ነበር። ቤተሰብ እንዳይፈልገኝ፣ ስልኬን የናፍቆት እስረኛ አድርጌ ዘጋሁት። ባቲ ላይ ዋልን ቀን አልፎ፣ ሌሊቱ የጭንቀት መጋረጃውን ሲዘረጋ፣ "የሰው ነጋዴዎች" (ደላላዎች) መጡ። በባጃጅ አውጥተው ጫካ ውስጥ ወደቆመ "ሀይሩፍ" መኪና ወሰዱን።
እዚያ መኪና ውስጥ የሰውን ክብር የሚገፈፍ ትዕይንት አየሁ። እኛ አምስት ነበርን፤ ነገር ግን መኪናው ውስጥ ሌሎች አሥራ ዘጠኝ ነፍሶች እንደ ካርቶን ተደራርበው ይጠብቁን ነበር። ደላላው "ሰው በሰው ላይ" እየጫነን፣ እንደ እቃ አፍኖን ጉዞው ተጀመረ። ሹፌሩ የባቲ ልጅ ነበር፤ በሳውዲ አረቢያ አሥራ ሁለት ዓመት እንደኖረና ፣ብዙ ገጠመኞቹን አጫወተን፣ አለንም "አብሽሩ ትገባላችሁ" እያለ በትዝታው የሚያጽናናን። ነገር ነገረን !! ታዳ የባቲ ተፍትሽ ጥበቃ አስቆመን አኛ ድምፅ አጥፉ ተባልንና መተፈስ እስከማንችል ፀጥ፣ አልን ከብዙ የደለላ ጥረት ቡኋላ ገንዘብ ከፍለው አለፍን ከዛ ሌሎችን ተፍትሽ እንጀራ 'ጭኜ ነው ብህ እለፍ' ብሎ ነገረው፦ ይሄም የሆነበት' ምክኒታት' ከባቲ ከተማ!! ወደ አፋር ክልል" የአንጀራ_ ንግድ ይደረጋል ብዙ እንዳትገረሙ ለማለትነው።
እንቀጥል
ግና የሌሊቱ ብርድ አጥንት ይሰረስር ነበር። እንዲህ አልኩ፦
"ሰው በሰው ላይ ሆኖ የነፍስ ጥሪ ሲሰማ፣
በረሃው ተከፍቷል የሞት ግጥም ሊሰማ፤
ብርዱ እንደ ጅራፍ ገላን ሲገረር፣
የሰው ልጅ ተስፋው በአላህ ነው ሚታሰር።"
ፈጅር ሊቃረብ ሲል፣ አፋር ክልል ውስጥ ባለ ጫካ አወረዱን። በዚያ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የፈጅርን ሶላት ሰገድን። ሶላቱን ጨርሼ ቀና ስል ግን፣ አንዲት ልጅ እኔን እኔን ትመለከት ነበር!። ቆንጅዬ ልጅ፣ እኔ ሶላት ከሰገድኩበት ሰዓት ጀምሮ እንደ ጥላዬ ትከተለኛለች።
ጀመር ታዳ ከተንሽ ቆይታ ቡኋላ የአፋር ደላላ መጣ አስለፈንና ወደሆነ ሸለወንዝ ጫካ ይዞን ሄደ ፣፣ ያች ልጅ ታዳ
ወደ ሸለቆው ስንወርድ አጠገቤ ትቀመጣለች፣ ስነሳ ትነሳለች።ፈጣን ደፋር ነገር ነች ስምህ ማነው አለችኝ ቀልጠፍ ባለው ድምፃ እኔም ነገርካት እሷም —"እራቢያ" እባለለሁ አለችኝ። አገርህ የት ነው አለችኝ ፣ እኔ የሀርቡና የከሚሴ ልጅ እንደሆኩ ነገርካት እሷም።ከከሚሴ ብዙ እረቀት የለላት ቱቼ የምትባል ትንሽዬ መንደር .እንደሆነች ነገረችኝ።
"ቅልብ ልብ ቢጤ" ነች ወረኛም; ነች በወሬ ጀመረችኝ፦
የስደቱን ስቃይ እስከምረሳው ድረስ በወሬዋ ታዝናናኝ ጀመር። "አይናፋር ነህ" እያለች በልጅነት ጨዋታዋ የልቤን ስጋት ገፈፈችልኝ። እሷ ለኔ በዚያ በረሃ ውስጥ የበቀለች አበባ ነበረች።
ቀኑ መሽቶ ማታ አፋሩ መጣና ለሀያ አምስት ሰው ሁለት ባጃጅ አመጣ። አስቡት! ባጃጅ ውስጥ ሰውን እንደ እቃ "መጋዘን" አስመስለው ደረደሩን። "ወይኔ እናቴ ጉድሽን አላየሽ!" አልኩ በውስጤ።ሰው በሰው ላይ ተደራርቦ ነበርና የሚጫነው።
እራቢያ ፈጣን ነገር ነችና "እኔ ላይ ይቀመጥ" አለች። ደላላውም ትእዛዝ ሰጠ።
ከእራቢያ ታፋ ላይ ቁጭ ስል፣ እንደ እናት እቅፍ አደረገችኝ። "አብሽር አትፍራ" አለችኝ። ያኔ... በውስጤ ትልቅ ማዕበል ተነሳ። "የአዋቂ አጥፊ" ስሜት ቢወርረኝም፣ ቅንነቷና ውበቷ ግን ያስደንቅ ነበር። በዚያች ጠባብ ባጃጅ ውስጥ ታቅፌ፣ ለሁለት ሰዓታት ተጉዘን "ሚሌ" ከተማ ገባን። እዚያም ሰው በማይመጣበት አሮጌ ቤት ውስጥ እንደ እስረኛ አጎሩን። ደላላ ከአንዱ ወደ አንዱ እየተቀባበለን፣ የስደትን ገሃነም ያሳዩን ጀመር። ረሃቡ አንጀታችንን ሲበላው፣ እራቢያ በዚያች ቅልብልብ ማንነቷ ለሁላችንም መፍትሔ ፍለጋ ተነሳች..
""ደላላው "ምግብ ላምጣላችሁ፣ ብር አውጡ" ብሎ የረሃባችንን ሰዓት ሲያውጅ፣ እራቢያ ልክ እንደ ታጋይ ብድግ አለች። በዚያ የፍርሃት ድባብ በነገሰበት አሮጌ ቤት ውስጥ፣ የእሷ ድፍረት እንደ ንጋት ፀሐይ ፈነጠቀ። ወደ እኔ ዞር ብላ በአዛዥነት መንፈስ እንዲህ አለችኝ፦ "ምግብ እኔ ነኝ የማዘው! አንተ አርፈህ ተቀመጥ። የምትጠጣውም በኔ ምርጫ ነው፤ እኔ የበላሁትን ትበላለህ፣ እኔ የጠጣሁትን ትጠጣለህ!" አለችኝ በቅልብልብ ምላሷ!!
አቤት ያኔ የተሰማኝ ስሜት! በባዕድ ምድር፣ በሞት ጥላ ስር ሆኜ እንዲህ ዓይነት እንክብካቤ ማግኘት ለኔ "ከሰማይ የወረደ መና" ነበር። ምግቡ መጣ። እኔና እሷ ለብቻችን ሆነን፣ የረሃባችንን አንጀት አራሳን። እንዲህ አልኩ፦
"በረሃው ሲያቃጥል ልብን በሰቀቀን፣
አላህ መላከላት - እራቢያን እንደ ምስጋና ለኛ ቀን፤
ደላላው ብር ቢቆጥር - ነፍስን ሊያገበያ፣
እሷ ግን ሆነችኝ - የሕይወት መጠለያ።"
ደላላው ስልኩን ጥሎልን "እስከ ነገ ማታ እረፉ" ብሎን ወጣ። በዚያ ሰፊ ግቢ ውስጥ ከእራቢያ ጋር ማውራት፣ መጫወትና መሳሳቅ ጀመርን።
የሚገርመው ነገር፣ የእሷ ማንነት ከእኔ ጋር ተገመደ። ስነሳ ትነሳለች፣ ስተኛ ትተኛለች፤ ልክ እንደ ጥላዬ ሆነች። አብረውን ያሉ ስደተኞች ሁሉ "እነዚህ ሰዎች መቼ ተላመዱ?" በሚል ግርምትና ቅናት ዓይናቸውን ይጥሉብን ጀመር። እኔ ግን ያንን ሁሉ "የአዋቂ አጥፊ" ስሜት በውስጤ አጭቄ፣ የስደቱን ድካም በጨዋታዋ እያከምኩ ቀኑ ነግቶ መሸ።
ነገር ግን... የመለያያና የፈተናው ሰዓት ደረሰ። ደላላው መጣና "ተዘጋጁ!" ብሎ በተርታ አሰለፈን። እኔ ሳላስበው ከፊት ተሰለፍኩ። እራቢያ ከኋላዬ መቅረቷን ስታይ፣ በዚያ ጭር ባለ ጫካና ሰፊ ግቢ ውስጥ የሚሰቀጥጥ ጩኸት አሰማች። ስመ ጥር ለቅሶዋን አወረደችው። የልቧ ትርታ "አትተወኝ" የሚል ይመስል ነበር።
ያኔ ገባኝ... የሰው ልጅ በጭንቅ ቀን የሚገናኘው ነፍስ፣ በሺህ ዘመን ከሚታወቅ ወዳጅ በላይ እንደሚጠነክር። እሷ ለእኔ የነበራት ጥልቅ ትስስር፣ በዚያች ሰከንድ በለቅሶዋ ውስጥ ሲፈስ፣ ልቤ በሐዘንና በግርምት ተከፈለ።
[ቀጣዩ ክፍል ⓹➘]
እራቢያ ለምን ጮኸች? ያ የደላላው ተርታ ወዴት ነው የሚመራን? ከፊት የተሰለፍኩት እኔና ከኋላ የቀረችው እራቢያ፣ በዚያ የሌሊት ጉዞ ላይ ምን ገጠመን? የስደቱ እውነተኛ መከራ የሚጀምረው ከዚህ በኋላ ነው...
የጨለማው ጉዞና የነፍስ ውጊያ.
ይቀጥላል.!!!!
⤵️
