ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

ምክር ለወጣቶች

ምክር ለወጣቶች

前往频道在 Telegram

"አላማችን ወጣቱ ያለበትን የዲን ክፍተት እንዲስተካከል ማድረግ ነው"

显示更多
未指定国家未指定类别
7 429
订阅者
无数据24 小时
+1227 天
+80630 天
帖子存档
~ ስለ ሙስጠፋ አቡ ኒብራስ የደሴው ሙለቢስ ማስታወሻ ! 🎙 አቡ ፈውዛን ከ መካነ ሰላም https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/Abu_Umer1

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ውድና የተከበራችሁ የኢብኑ ተይሚያ መስጂድ  ደርስ ታዳሚያን በሙሉ  በኢደል አድሓ በአል ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ደርስ በአላህ ፍቃድ የፊታችን ሰኞ  ማለትም በቀን 01/10/2018 ሙሉ የመስጂዱ ደርሶች እንደሚጀመሩ እናሳውቃለን። ላልሰሙት በማዳረስ በጊዜ ለመገኘት እንሞክር። https://t.me/ibnuu_teymiyah https://t.me/ibnuu_teymiyah https://t.me/ibnuu_teymiyah

sticker.webp0.25 KB

ለጀማሪዎች ብቻ በሴት ኡስታዛ መቅራት ምፈልጉ ኑ ሳይሞላ ተመዝገቡ ለመመዝገብ ከታች ባለው ዩዘርኔም ያናግሩን👇👇👇 @Mujahid_Selefi

ሴቶችዬ,,, ሀፊዝ ሆናቹ ከዛ ባላቹ ጋር ሙራጀዐ ስታሰሙ🫰 ያ ሰላም ምነኛ ያማረ ህይወት ነው ♡ الطَّيِّبَاتُ لِلطَّيِّبِينَ وَالطَّيِّبُونَ لِلطَّيِّبَاتِ «ጥሩ
ሴቶችዬ,,, ሀፊዝ ሆናቹ ከዛ ባላቹ ጋር ሙራጀዐ ስታሰሙ🫰 ያ ሰላም ምነኛ ያማረ ህይወት ነው ♡ الطَّيِّبَاتُ لِلطَّيِّبِينَ وَالطَّيِّبُونَ لِلطَّيِّبَاتِ «ጥሩ ሴቶች ለጥሩዎች ወንዶች ፣ጥሩ ወንዶችም ለጥሩዎች ሴቶች የተገቡ ናቸው።» አላህ ይወፍቀን አሚን በሉ 🤲 የተወሰደ🙌 https://t.me/Abu_Umer1

👉 ሶላት ዒባዳ አይደለም ! ከላይ እንደ ምትመለከቱት ኡስታዝ ተብዬው ኻሊድ ክብሮም ተፍሲር ብሎ በሚዘባርቀው ፍልስፍናው ላይ የሶላት ትልቁ ሚና ዒባዳ እውን እንዲሆን የሚያግዝ መሳሪያ እንጂ ሶላት
👉 ሶላት ዒባዳ አይደለም ! ከላይ እንደ ምትመለከቱት ኡስታዝ ተብዬው ኻሊድ ክብሮም ተፍሲር ብሎ በሚዘባርቀው ፍልስፍናው ላይ የሶላት ትልቁ ሚና ዒባዳ እውን እንዲሆን የሚያግዝ መሳሪያ እንጂ ሶላት ዒባዳ አይደለም ይላል ‼ ። በጣም የሚያሳፍሩት ከሱ ስር ቁጭ ብለው ይህን የሚማሩት እንጂ እሱ አይደለም ። ምክንያቱም የሱ አላማ ሙስሊሞች ከስማቸው በላይ የሚያውቁዋቸውን የእስልምና ማእዘናቶች ላይ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ውስጣቸውን ከትክክለኛው እስልምና ባዶ ማድረግ ነውና ! እባካችሁን አላህን እንፈራለን የምትሉ ኡስታዞች ከዚህ ሰው በማስጠንቀቅ ሙስሊሞችን ታደጉ ! ። http://t.me/bahruteka https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/Abu_Umer1

በትእግስት አንብቡት👇👇👇 አሰላሙ አለይኩም ወንድም እንዴት ነህ አንድ ነገር ላማክርህ ነበር ቻናል ስላለህ ምናልባት ከብዙ ሰዎች ጋር ትተዋወቅ ከሆን ብዬ ነበር እና ምን መሰለህ  ይህንን ስልህ ምንም ያህል የሁላችንም ከጭንቅ፣ ከሀዘንና ከመከፋት አልፎ ከግራ መጋባት ብቸኛ መጠጊያና መሸሻችን አላህ ቢሆንም፤ አንዳችን ለአንዳችን ወደ ኸይር ልንጠቋቆም ስላዘዘን እኔም ግራ ሲገባኝ እንድታመላክተኝና ሰበብ እንድትሆነኝ በማሰብ ነው። በውስጤ ያለውን ከባድ ጭንቅና ያለሁበትን ሁኔታ ላካፍልህ ያሰብኩት፣ ሰለፍይ ወንማችን ስለሆንክ እናም በተለያዩ ቻናሎች ላይም ለዲን የምታደርገውን እንቅስቃሴ ስለተመለከትኩ ነው  ምን  በአሁኑ ሰዓት በተደራራቢ ፈተናዎችና ሙሲባ ውስጥ ነው ያለሁት። ምናልባት አላውቅ ይሆናል ያለብኝን ችግር መናገሬ ሰበብ ይሁነኝ አይሁነኝ ግን በአሁን ሰአት ያለኝ አማራጭ ይህ ብቻ ነው ወደ ዲን ወደ ሰለፍይነት ማለቴ ነው ከመጣሁ ገና ወእ 3፣4 ዓመት አካባቢ ነው ኒካህም ያሰርኩት በ18 ነበር ሰለፍይ ከሆንኩ ከ2 አመት በኋላ የዛኔ በጣም እያመመኝ ስለነበር ፋሚሊ ራሱ ስነግራቸው አይ ሲሉኝ እነሱ ሳያውቁ ነበር ያሰርኩት  በእጄ ላይ ምንም ሳይኖር በአላህ ላይ ካለኝ ተስፋ ውጪ ይሀው አሁን 2 አመት ሆነኝ ግን ፋሚሊ ትምህርት እንድማር ይፈልጉ ስለነበር፣ ወደ ዲን ከመጣሁ በኋላ ትምህርት በማቆሜና ኒካህ በማሰሬ ደስተኛ ስላልሆኑ ብዙም ድጋፍ አያደርጉልኝም ግን አልሀምዱሊላህ ☺️ ባሮቹ በየትኛውም ሃል ውስጥ ቢሆኑ የማይጥላቸው ጌታ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የራሴን ሪዝቅ ሰጠኝ ከዛ ኖርማል ላይፍን ባይሆንም ብዙ መሸቃ ሙሲባዎች ቢኖሩትም እንዴትም በአላህ ፈቃድ እዚ ብደርስም ኢላሂ ሊፈትነኝ ባለቤቴ ያሳደገቻት አያቷ ወደአኺራ ስትሄድ ህመሙ ባሰባት በዚው ሰአት እኔም ስራ ፈታው አጣሁኝ አልሆነልኝም አልሀምዱሊላህ እስከዛሬ ሁሉንም ሙሲባ እንድቋቋም ረድቶኝ ይሀው እየተነፈስኩ ነው ግን አሁን ላይ በቃ ስራ ካጣው በኋላ መጨነቅ ግራ መጋባት ሆኗል ህይወቴ የሷ ነገር አለ እዚ ጋር የኔ ህመም በዛላይ የሷ ሃላፍትና ግራ ገባኝ ነገራቶች ከበዱብኝ እና በቃ ለዛ ነው ምናልባት አውርቼው ከሱና ወንድሞቼ ዘንድ አላህ ሰበብ የሚሆንልኝን ነገር ካሰማኝ ብዬ ነው ታውቃለህ ለሩቃ አዳማ አትሆንም አላህን የሚፈራ ተቅዋን የተላበሰ ሰለፍይ አይደለም ከዛ መስመር ውጭ የሆኑት ወንድ እና ሴትን ባለመእባለቅ ከኢኽዋን መለስ ያሉት ሙመይዕዎች እንኳ የሉም ብቻ አሁን ሌላው ቀርቶ ሁለታችንም ለመታከም መስራት አለብኝ ግን ግራ ገባኝ ምን ልስራ? ፈለኩ ፈለኩ አሁን ላይ ችሎታህን ብቃትህን አይደለም ወረቀትህን ነው የሚያዩት በዛ ላይ ይህን ምፈልገው እንኳ ውስጤ እየተረበሸ ግራ እየተጋባ ነው ከና ልሰራ ልሞክር ስል አትችልም የሚል ድምጽ ፍርሃት ነው ሚሰማኝ ሠራው ሌላ ገና ነገ ልሰራ ሳስብ በጭንቀት እንቅልፍ አጥቼ ማድረው 😫🥹 ያ አላህ እስኪ ከቻልክ በዱዕም ብቻ አልሀምዱሊላህ  ከባዱ ህመም ምን እንደሆነ ታውቃለህ ሀቢቢ? ብዙዎቻችን ጀሰዳችን  ላይ የሚደርሰው ነው አይደል የሚመስለን? ወላሂ ተሳስተናል፣ ከባዱ የቀልብ ህመም ነው በጣም ግራ እየገባኝ ነው በቃ ያለሁበት ባለቤቴን እና ራሴን ማሳከም መታከም ይቅርና እሷን ማኖሩና የትዳር ሀላፍትናዬን ግዴታዬን መወጣቱ እጅግ በጣም ከብዶኛል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ በጣም አዛ የሆነ ላይፍ ነው እየኖርኩ ያለሁት። የነገራቶች መሸቃ ተስፋ ባያስቆርጠኝም፣ አቅም አሳጥቶ አድክሞኛል። ነገሮች በሙሉ በአንዴ ተደራርበውብኝ ማሰብ አቅቶኛል፣ በጣም ግራ ተጋብቻለሁ። በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ሆኜ ግን ልቤ ከዲኔ እንዳይርቅ፣ በመሃል የተፈጠረብኝ ክፍተት ሰፍቶ እቺ የቀረችኝ ኢማኔ እንዳትቀንስ... አረ እንዳልጠፋ በጣም ፈርቻለሁ ከአላህ መንገድ መራቅ በፍጹም አልፈልግም! አሁን ላይ ሙሉ ትኩረቴ ተበታትኖ በዱንያ መሸቃ ብቻ ግራ መጋባት ውስጥ ነኝ አቅሌ ሰላም አይደለም እናም እንድታግዘኝ የምፈልገው በምንም አይደለም፤ በቀን 1 ሰዓትም ይሁን ግማሽ ቀን እንኳ በመስራት ራሴን ቢዚ የማደርግበት፣ ከጭንቀቴ እንድርቅና ዲኔ ላይ ጫና እንዳያሳድርብኝ ስራ እንድታፈላልግልኝ ብቻ ነው። አልሀምዱሊላህ የምታውቃቸው ልጆች ምናምን ካሉ ብቻ ጠይቅልኝ እስኪ በአላህ... አሁን ላይ በቃ አቅም አንሶኛል። 🥹😭 በጣምም ግራ ገብቶኛል አለ አይደል ማወቅ አያድንም መተግበር ሰበብ አድርሶ አላህን መለመኑ እንጂ ያለሁበት ሙሲባ ምናልባት በወንጀሎቼ አልያ ኢላሂ ሊፈትነኝ ይሆናል ግን እሱን አውቄ ካልሰበርኩ ራሴን ካጣሁ ምን ጥቅም አለው 😔 አንድ ቀን ግን ሁሉም ያልፍ ይሆናል ኢንሻአላህ። እሱን አግኝታቹ መርዳት ምፈልጉ @Mujahid_Selefi  👈👈በዚህ አናግሩኝ

እኮ
እኮ

ትንሽ ኢልም በሽታ ነው🙌 እንታከመው!

ሳይሞላ ተመዝገቡ👆👆👆

አብዛኞቹን ሴቶች ይሄ ፍቅር ሚባለው ነገር የሀራም ሪሌሽን ነው እየሰበራቸው ያለው💔 አብዛኞቹን ወንዶች እርድና ነው ብሎ የጀመሩት ሱስ ነው በቁም እየገደላቸው ያለው💨 ተሳሳትኩ? https://t.me/NasihaLishebab https://t.me/NasihaLishebab

🚫  የኻሊድ ክብሮም የአክፍሮትና ሽርክ ጉዞ    ኻሊድ ክብሮም የተባለው ግለሰብ ሰልሜያለሁ ብሎ ወደ እስልምና ከገባ በኋላ የትና ማን ጋር እንደተማረና ሸይኹ ማን እንደሆነ ሳይታወቅ ወደ ዳዕዋ ሜዳ በመግባት በተለይ ሴቶችን ያለ ሒጃብ ፊት ለፊት በማስተማር ሙሪዶቹ እንዲሆኑ ካደረገ በኋላ በጣም አደገኛ አካሄድ እየሄደ ይገኛል ።     ይህ ግለሰብ እየሄደበት ያለው አካሄ በጣም መርዛማና ትክክለኛውን እስልምና የሚበርዝ ነው ። ግለሰቡ እየሄደበት ያለው አካሄድ ምእራባዊያን የሰጡት የቤት ስራ ያለ እስኪመስል እየደረሰ ነው ። ይህ ግለሰብ  በረቀቀ መልኩ የነብዩን ሐዲስ ውድቅ በሚያደርግ መልኩ ቁርኣንን ብቻ መያዝና የቁርኣንን መረጃነት ብቻ መቀበል የሚለውን የቁርኣናዊያን ቡድኖች አካሄድ እያሰረፀ ነው ። በዚህ ብቻ አላቆመም ቁርኣንን ራሱ ማንም ቢያብራራው ተቀባይነት እንደሌለውና በቀጥታ ቁርኣንን ብቻ በመገንዘብ መብቃቃት እንደሚቻል መሰረት በመጣል ላይ እየሰራ ነው ። ይህን አስተምሮ በሚቀጥለው ንግግሩ ተመልከቱት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/7251 ይህ አካሄድ ሰለፎች ቁርኣንን የፈሰሩበትን መንገድ ውድቅ ለማድረግና ሰዎች በዝንባሌያቸውና ከስሜታቸው ጋር በሚስማማ መልኩ እንዲፈስሩት በዚህም ምእራቦች የሚፈልጉት አይነት ባህላዊ እስልምና እንዲስፋፋ ለማድረግ ያለመ አካሄድ ይመስላል ።     ሌላኛው የዚሁ የፈተና ሰው ዳዕዋ ሰዎች በኢማናቸው አማካይነት የፈለጉትን የማድረግ አቅም አላቸው የሚለውን የአሕባሾች ዐቂዳን ለማስፋፋት የሚያደርገው ጥረት ነው ። ይኸው ግለሰብ የለበሱት ልብስ ለሌሎች በረከት የሚያስተላልፍ ትራፊ ውሃቸው ለሌሎች መድሃኒት የሚሆንላቸው ፍፁም የሆነ ሀይል (ፓወር) ያላቸው አሉ እያለ የሰውን ልጅ የረቂቅ ሀይል ባልተቤትና ፍፁም ነው በማለት የቀብር አምልኮና በሙታን መንፈስ ወደ መታገዝ እየተጣራ ይገኛል ። ይህንን አስተምሮ በሚቀጥለው ሊንክ ገብታቸው አዳምጡ ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️ https://drive.google.com/file/d/1nRc3dU70O311-ljNlE_JueD3-AeG6DQe/view?usp=drivesdk       ከዚህ የሚከፋውና በጣም አደገኛው ደግሞ የደጋጎችን ልብስ መልበስ የእነርሱ መንፈስ ወዳንተ እንዲተላለፍ ያደርጋል የሚለው አስተምሮ ነው !  ይሄኛውንም በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ያዳምጡ : – 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://drive.google.com/file/d/1dR8C1c5Tv4SIVCK1h4IyKFBd8dx75xFy/view?usp=drivesdk      ተመልከቱ አንድ ጃሂል ስለጠሃራ የማያውቅ የአንድን ወልይ ልብስ ቢለብስ ወልይ መሆን ይችላል ማለት ሽርክ አይደለም እያለ ነው የሚያስተምረው ። ለማንኛውም ይህ ግለሰብ ብዙ ሴቶችና ወጣቶች ዘንድ እንዲህ አይነቱን የኩፍርና የሽርክ አስተምሮ ተቀባይነት እንዲኖረው እያደረገ ያለ ግለሰብ ስለሆነ ሙስሊሞች ከግለሰቡና ከአስተምሮቱ እንዲርቁና የኢስላም ጠላቶችን ተልእኮ እያስፈፀመ መሆኑን በማስገንዘብ መታደግ ያስፈልጋል እላለሁ ። http://t.me/bahruteka

ቤተሰብ ውሎ እናንተ ጋር እዴት ነው? እኛ ጋር ጭር ብሏል No ሱቅ No ባጃጅ(አዳማ)

语音消息01:52

ከዚህ ታሪክ ምን ተማራቹ ወጣቶች? በComment ያስቀምጡ✍

አስለቅሶኛል💔

✨ማሊክ ኢብኑ ዲናር በጣም ትልቅ ኢማም ናቸው። ዛሂድ ከሚባሉት ከሰለፎች ውስጥ አንዱ ናቸው።ይህ አሊም ምን ይላሉ ህይወቴን እየሰከርኩ ነው የጀመርኩት። ህይወቴ በቃ መጠጣት መስከር ነው!   ከዛ ከእለታት አንድ ቀን ሚስት ማግባት ልጅ መውለድን ተመኘሁ ይላሉ።ማግባት ፈለኩኝ! አላህ አ'ለና ሚስት አገባሁና አንድ ሴት ልጅን ሰጠኝ አላህ✨። ስሟንም ፋጢማህ አልኳት ፋጢማ ብዬ ሰየምኳት🎀🙌   ፋጢማ እያደገች ስትመጣ ልቤ ወደ ኢማን እየቀረበ መጣ።ወንጀል መስራት እየተውኩ፤ውጪ ምጠጣውን መጠጥ 🍾 እቤት ይዤ መግባት ጀመርኩ ይላሉ።ፋጢማን እጭኔ እግሬ ላይ አስቀምጬ ነበር የምጠጣው ይላሉ።እንዲያም ሆኖ ግን ይሰግዳሉ።   አንዴ ቁጭ ብዬ እየጠጣሁ ፋጢማ ሁለት አመት አይሞላትም ይላሉ። ስትጫወት የምጠጣውን መጠጥ በእጇ ገፍታ ደፋችብኝ!ከዛ ምን አልኩኝ "አሀ!"አልኩ ይሄ የፋጢማ እጅ አይደለም የአላህ እጅ ነው አልኩኝ በሷ ሰበብ አጠጣ እያለኝ ነው ብዬ ተረዳሁ ይላሉ። ከዛ ፋጢማህ 3 አመት ሞላት።በጣም የምታምር የምታጓጓ ትንሽዬ ልጅ ነበረች።🤌 ፋጢማ 3 አመት እንደሞላት እንድ መጥፎ ክስተት ተከሰተ። ፋጢማ የምወዳት ልጄ ሞተችብኝ! አልቻልኩም ትግስት የሚባል ነገር አነበረኝም ይላሉ።ከነበርኩበት ባህሪ  የበለጠ ሆኜ ብሶብኝ ተገኘሁ! መጠጣት መስከር ጀመርኩ በንዴት💔 ከዛ እንድ ቀን ሸይጧን መጣና ምን አለኝ(ውስዋስ ውስጥ ገባሁ) "ዛሬ ሰክረኸው የማታውቀውን ስካር መስከር አለብህ መጠጣትህን አታቁም!!"  አለኝ። እኔም በቃ እሺ! አልኩት ሸይጧንን   ከዛ ስጠጣ... በጣም ጠጣሁ! ወዲያው በስካር መንፈስ ህልም አይኔ ላይ ከላይ ወደታች መዥገርገር ጀመረ። ወደኩ! ወደኩና አንድ ለተውባ የከፈተልኝን በር  በህልሜ ተመለከትኩ!✨✨✨✨   ልክ ተኝቼ እንዳለሁ ቂያማ የቆመ መሰለኝ(አላህ በህልም ነው የሚያሳያቸው) ፀሀይቱ ጠቁራለች🌚 ባህሩ ይነዳል 🔥ሰው ሁሉ አላህ ፊት ተሰብስቦዋል።እዛ ሰው ሁሉ ፊት ተጣሪ ይጣራል!🗣"እከሌ የእከሌ ልጅ ውጣ ለአላህ ፍርድ ቅረብ!"ይባላል።ልክ ያ ሰውዬ ሲጠራ ወዲያው ፊቱ ክስም ይላል   ሰዉ ሁሉ ሲጠራ ቆየና የኔ ተራ ደረሰ!! 🗣"ማሊክ ኢብኑ ዲናር ከአላህ ፊት ለመቆም ውጣ!" ተባልኩኝ ይላሉ።ያኔ ከመቅፅበት ከአካባቢዬ ሰው ሁሉ ጠፋና ከፊት ለፊቴ ትልቅ ዘንዶእባብ ያባረኝ ገባ!ይላሉ እኔ ስሮጥ  እሱ ሲከተለኝ🐉እኔ ስሮጥ  እሱ ሲከተለኝ ... በመንገዴ ላይ አንድ ሽማግሌን አገኘሁ!, ከዛ ብዬ አልኩት "እባክህ አድነኝ" አልኩ።ከዛ ትኩርር ብሎ አየኝና እኔ ሽማግሌ ነኝ እንዴት ብዬ ላድንህ እስኪ ትተርፍ እንደሆን በዚ መንገድ እሩጥ አለኝ! እሺ አልኩና መሮጥ ጀመርኩ ይላሉ። ያ እባብ ይከተለኛል ሮጬ ስደርስ ከፊት ለፊቴ እሳት ነው!🔥 ከእባብ አምልጬማ እራሴን እሳት ውስጥ??? አይሆንም!! አልኩኝና በሌላ መንገd l! በሌላ መንገድ ስሄድ ተመልሼ ያንኑ ሽማግሌ አገኘዋለሁ (ህልማቸው ላይ ነው ይሄ ሁሉ ሱብሀነላህ ጭንቀት!) ያን ሰው መጥቼ አንተ ሽማግሌ ሆይ በአላህ ይሁንብህ  አግዘኝ እርዳኝ ስለው አለቀሰ ለሁኔታዬ ከዛ ምን አለኝ "እንዴት ብዬ ላድንህ ልጄ?እኔ ደካማ እንደምታየኝ እስኪ ትድን እንደሆን ወደዛ ተራራ እሩጥ አለኝ።ወደተራራው መሮጥ ጀመርኩ።🏔    ወደ ተራራው  እየሮጥኩኝ ሳለ ህፃናት ተሰብስበው ያ ፋጢማህ ... ፋጢማ ሆይ አባትሽን እባብ ሊበላው ነው አድኝው ይላሉ። ይህንን ስሰማ ለካ በ3አመቷ የሞተችብኝ ልጅ አለችኝ ልታድነኝ ነው እያልኩ ደስ እያለኝ ወደተራራው እሮጣለሁ። ልክ ስደርስ ልጄ እኔን በቀኝ እጇ ያዘችኝ እና በግራ እጇ ወዲህ አድርጋ ጣለችው ይላሉ።   ከዛ ዱንያ ላይ አደርጋት እንደነበረው ጉልበቴ ላይ አስቀምጬ አወራታለሁ። "እንዴት ነህ አባቴ?" አለችኝ።  እሱ ይቆይ ልጄ ሆይ እስኪ ንገሪኝ ያ እባብ ምን ነበር ሊበላኝ የነበረ?  አልኳት።   📍 አባቴ ያ እኮ በዱንያ ስትሰራው የነበረው መጥፎ ስራህ ነው።አንተ ነህ እንዲ ያወፈርከው ያተለከው። እሺ ሽማግሌውስ?አልኳት   📍ሽማግሌው ደግሞ ጥሩ ስራህ ነው ደካማ ነው ሊያድንህ አልቻለም አንተ አደከምከው። ከዛ አንድ ቁርዐን ቀራችልኝ ምን የሚል ፦                 "ለእነዛ ምዕመናን ለአላህ ግሳፄ የሚፈሩበት                  ጊዜ አልደረሰም ወይ??" የሚለውን ኣያ አነበበችልኝ   ✨ልክ እኔም ከእንቅልፌ እየጮኽኩ ተነሳሁ።አዎ ጊዜው ደርሶዋል ጌታዬ እያልኩ እያለቀስኩ ተነሳሁ ይላሉ። ከዛ ተነሳሁ እና ሻወር ወስጄ ኡዱ አደረኩና ወደ መስጂድ መሄድ ጀመርኩኝ። መስጂድ ደርሼ ሱብሂ ስሰግድ ኢማሙ የመስጂዱ ኢማም ልጄ በህልሜ የቀራችልኝን አያ እየቀራ ነበር። አላህ ለዛ ነው ከዛ ቡሀላ ትልቅ አሊም ሆነው የወጡት!✨ከዛ ሁሌም መስጂድ በር ላይ ሁሉም ሰግዶ ሲወጣ ይቆሙና...   🗣"አንተ አላህን ያመፅክ ባሪያ ሆይ ወደ አላህ ተመለስ!!"እያሉ ይናገሩ ነበር። አህህ ማሊክ ኢብኑ ዲናር! የተወሰደ🙌 https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/NasihaLishebab https://t.me/NasihaLishebab

✅اسلام عليكم وراحمة الله و بركاته✅ ቁርአን ከቃኢዳ ጀምሮ መቅራት  ምፈልጉ ብቻ  በዚህ አናግሩኝ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @Mujahid_Selefi  የምንቀበለው ተማሪ ብዛት ቃኢዳ 5  ነዘር 5 ሂፍዝ 5  ተማሪ ብቻ ነው

የመዳም ቅመሞች አንብቡት በዛውም ሼር አድርጉት በተረፈ አሏህ ይጠብቃቹህ ከFB ያገኘሁት ነው https://t.me/Abu_Umer1
የመዳም ቅመሞች አንብቡት በዛውም ሼር አድርጉት በተረፈ አሏህ ይጠብቃቹህ ከFB ያገኘሁት ነው https://t.me/Abu_Umer1

ወላጆችሽ ጫት ሲቅሙ አትኻድሚያቸው ቡና በማፍላት ይሁን ውሃ በማቅረብ🙌 https://t.me/NasihaLishebab