ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

ምክር ለወጣቶች

ምክር ለወጣቶች

前往频道在 Telegram

"አላማችን ወጣቱ ያለበትን የዲን ክፍተት እንዲስተካከል ማድረግ ነው"

显示更多
未指定国家未指定类别
7 388
订阅者
+924 小时
+1057 天
+76230 天
帖子存档
🌙 ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ! ✍️ነገ ሐሙስ ነው። የሐሙስን ሱና ጾም እንዳንረሳ። ለአላህ ብለን የምንጾመው አንድ ቀን ምናልባት የወንጀላችን ምክንያት ሆኖ የሚሰጠንን ምሕረት ያስገኝልን ይሆናል። ዛሬ
🌙 ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ! ✍️ነገ ሐሙስ ነው። የሐሙስን ሱና ጾም እንዳንረሳ። ለአላህ ብለን የምንጾመው አንድ ቀን ምናልባት የወንጀላችን ምክንያት ሆኖ የሚሰጠንን ምሕረት ያስገኝልን ይሆናል። ዛሬ ኒያችንን እናስተካክል፣ ነገ ደግሞ ሱናን በማክበር እንጹም።✍️ ✍️አላህ ጾማችንን ይቀበለን፣ በሱና ላይ ያጽናን፣ ከተቀባይ ባሮቹም ያድርገን። አሚን። 🤲

አጅነቢይ የሆነን አካል"ለአላህ ብዬ እውድሃለው/ሻለው " ማለት የፊትናን በር ይከፍታል። ተአደቡ!! https://t.me/NasihaLishebab

አሚን በሉ🤲
አሚን በሉ🤲

~ ስለ ሰይድ ቁጥብ ምን ያውቃሉ? ክፍል 1 ሰይድ ቁጥብ እና ፅሁፎቹ በሀምሳዎቹ መጨረሻ እና በስልሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ብቅ በማለት (በኢኽዋን አል ሙስሊሚን) በተበላሸው የሐሰት አስተሳሰባቸው ውስጥ ከተዘራ እና ከተተከለ ጊዜ ጀምሮ ለሙስሊም ለወጣቶች ውድመት ዋና ምክንያት ሆኖዋል ። ሰይድ ቁጥብ ሲባል ሸይኽ አይደለም እውቀትንም ፈልጎ አያውቅም። ይልቁንም እንደ ማርክስ እና ሌኒን ሌሎችም ያሉ ፈላስፎች ሀሳቡን (ፊክራውን) በፈልሰፋ የሞላ የፊደል ትመህርትን የተማረ ሰው ነው ። የእውቀት ባለቤት ባለመሆኑ እና አውቀትንም ከኡለሞች የተማረ ባለመሆኑ ምክንያት የእስልምና መሰረቶች ላይ ብዙ ትችቶችን ሰንዝሮዋል እና የአላህ መልእክተኛ እና ነቢይ የሆነውን ሙሳን ዐለይሂ ሰላም ተችቶዋል ትልልቅ የሆኑትን የነቢያችንን ባልደረቦች ሶሓቦችን ከባባድ በሆኑ በመስደብ እና በማነወር ታውቆዋል ከዚህም ማጥቃት አልፎ ተርፎም ሙስሊሞችን ሙሉ በሙሉ ካፊር ናቸው በአለም ሙስሊም የለም እስከማለት ደርሰዋል እስልምና አሁን በምድር ላይ የለም ብሎ ስላመነ በመስጂድ መስገድን አቁሟል ጁሙዓ ጀመዓ እስከማይሰግድ ድረስ መስጂዶችም የድንቁርና  ወይም معابد جاهلية (የጃሂሊያ) አምልኮ ቦታዎች ናቸው በማለት መስጂድን እርቆዋል። ይሄን ያነሳሁት ከብዙ ጥመቱ ለናሙና ያክል ነው !! የተናገራቸውን ንግግሮቹን እና ፁሁፎቹን በአሏህ ፍቃድ በሚቀጥለው አስቀምጣለው ።      ይህ ሁሉ ግልጽ የሆነ ስህተት እንዳለ ሆኖ በሚያሳዝን ሁኔታ እርሱን የሚያወድሱ አምሳያ ያሌለው ብቸኛ አሊም አስመስለው የሚያቀርቡት  እንደ ኸዋሪጅች ፣ ሂዝቢዮች ፣ ኢኽዋን እና ተክፊሮች መኖራቸው ነው። ይህም በመሆኑ ምክኒያት ወጣቱ ሃሳቡን (ፊክራውን) እዲቀባል የሱን ገፅታ ማሳመር  መሰረታዊ ምክንያት ሆነዋል እና ይህም ስራቸው ወጣቱ ወደ ተክፊ ቡድኖች እንዲቀላቀሉ አድርጓቸዋል።    …ውድ ወንድሜ፣ እህቴ፣ እውነትን የምትፈልግ እና የመዳንን መንገድ የምትፈልግ ከሆነ ፣ ከቢድዓ እና ከወገንተኝነት ከሂዝቢያ ለመዳን የምትፈልግ ከሆንክ ፣ከዚህ ተንኮል የተሞላበት የፊክራ ወረራ  ውስጥ ከመውደቅህ ተጠንቀቅ እንደ “ሰይድ ቁጥብ” ያሉ የእስልምና አስተሳሰብ አራማጆች በመባል የሚታወቁትን ወይም (المفكرين الإسلاميين) የሚባሉ “የኢኽዋን አልሙስሊሚን” ቡድን አባል በሙሉ መራቅ የግድ ነው ኢኽዋን ስውር መርዘኛ ነው ። join #telegram ቻናል https://t.me/abuabdurahmen https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/Abu_Umer1

ከኡስታዝ ምክሮች ✍ያ ኡኽቲ ለልጆችሽ ልሰጫቸው ምችይው ትልቁ ስጦታ ምን መሰለሽ ቁርዐንን ማስቀራት ነው ለዛ ደሞ አሁን አንቺ መቅራት አለብሽ ልጆች በሰሙት ሳይሆን ባዩት ነገር ላይ ስለሚቀረጹ፣ እና
ከኡስታዝ ምክሮች ✍ያ ኡኽቲ ለልጆችሽ ልሰጫቸው ምችይው ትልቁ ስጦታ ምን መሰለሽ  ቁርዐንን ማስቀራት ነው ለዛ ደሞ አሁን አንቺ መቅራት አለብሽ ልጆች በሰሙት ሳይሆን ባዩት ነገር ላይ ስለሚቀረጹ፣ እናት እራሷ ስትቀራና ለቁርአን ትልቅ ቦታ ስትሰጥ ሲያዩ እነሱም የመቅራት ፍቅራቸው ይጨምራል። ላንተም ነው አኺ🤌 https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/Abu_Umer1

ኢላህዬ...ሁለት...አንተን ፈረተው ክልከላህን..ላለመዳፈር ሸሽተው ለተራራቁ ሁለት ተስፈኞችክ.. ኢላህዬ..በሀላልህ..."አስተሳስራቸው" ኢላህዬ.."በኩን" ቃልህ አዋህዳቸው..🫰🏻 https://t
ኢላህዬ...ሁለት...አንተን ፈረተው ክልከላህን..ላለመዳፈር ሸሽተው ለተራራቁ ሁለት ተስፈኞችክ..
ኢላህዬ..በሀላልህ..."አስተሳስራቸው" ኢላህዬ.."በኩን" ቃልህ አዋህዳቸው..🫰🏻
https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/Abu_Umer1

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦ ነፍሴ በእጅ በሆነችው ጌታ እምላለሁ ጀነትን አትገቡም እስከምታምኑ ድረስ አታምኑምም እስከ ምትዋደዱ ድረስ በአንዳች ነገር አላመላክታቹህም በሰራቹህት ጊዜ የምትዋደ
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦ ነፍሴ በእጅ በሆነችው ጌታ እምላለሁ ጀነትን አትገቡም እስከምታምኑ ድረስ አታምኑምም እስከ ምትዋደዱ ድረስ በአንዳች ነገር አላመላክታቹህም በሰራቹህት ጊዜ የምትዋደዱበትን ነገር ሰላምታ በመሀከላቹህ ተለዋወጡ።
📚 ሙስሊም
https://t.me/NasihaLishebab https://t.me/NasihaLishebab

ረሱል (ﷺ) ይህን ዱዓእ ያደርጉ ነበር:- ﴿اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْأَرْبَعِ : مِنْ عِلْمٍ لَا يَنْفَعُ، وَمِنْ قَلْبٍ لَا يَخ
ረሱል (ﷺ) ይህን ዱዓእ ያደርጉ ነበር:-
﴿اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْأَرْبَعِ : مِنْ عِلْمٍ لَا يَنْفَعُ، وَمِنْ قَلْبٍ لَا يَخْشَعُ، وَمِنْ نَفْسٍ لَا تَشْبَعُ، وَمِنْ دُعَاءٍ لَا يُسْمَعُ﴾ “አላህ ሆይ! ከአራት ነገሮች በአንተ እጠበቃለሁ። ከማይጠቅም ዕወቀት፣ ከማይፈራ ልብ፣ ከማትጠግብ ነፍስና፣ ተቀባይነት ከሌለው ዱዓእ።” 📚 አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል፡ 1548 https://t.me/NasihaLishebab https://t.me/NasihaLishebab

✅   ወርቃማ ምክር ለሰለፍዮች ከሸይኽ ሑሰይን ።    ሸይኻችን ሸይኽ ሑሰይን በዚህች አጭር ደቂቃ በጣም የሚገርም ምክር ለሰለፍዮች አስተላልፏል ። ለመሻኢኾች ፣ ለጡላቦች ፣ ለዱዓቶች ፣ ለቻናልና ግሩፕ ባልተቤቶች ባጠቃላይ ጠቃሚና ገሳጭ ምክር ነው እንጠቀምበት ። በሁሉም ነገር መግባትና ነገር ማዋሰድ የሰለፎች ባህሪ አይደለም ይልቁንም የተወገዘ ነው ። በሰለፍዮች ላይ መዝመትና ሰለፍዮችን መከፋፈል አላህ ያወገዘው ተግባር ነው ። ትላልቅ የሰለፍ ዑለሞች ካላቸው ትልቅ ቦታ ጋር በሁሉ ነገር በመግባታቸው የተወገዙ መኖራቸውን ጠቅሷል ።     ሰለፍዮች እርስ በርሳቸው መደጋገፍ መከባበር እንጂ መነቋቆር መለያየት እንደሌለባቸው በፍፁም በሰለፍዮች መካከል ወሬ ማዋሰድ እንደማያስፈልግ አበክሮ መክሯል ። በሙኻሊፎች ላይ እንጂ በሰለፍዮች ላይ መዝመት ዲንን መናድ መሆኑን አስጠንቅቋል ።    ማንን ፈልጎበት ነው ከማለት ወጥተን በምክሩ እንደ መስታወት ራሳችንን አይተን እናስተካክልበት ። ቁርኣንም ፣ ሐዲስም ፣ የሰለፎች ንግግርም ለተበሩክ ሳይሆን እኛን ለማከምና ለማስተካከል ነውና የመጡት እንጠቀምባቸው ! አላህ ይወፍቀን ።     በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ምክሩን ያዳምጡ :– 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/7389 http://t.me/bahruteka

ለምንድነው ደዩስ ዲን የሌለው ሰው የምታገቡት? ምክር አሰሙ ነገ ይሻሻላል ብላቹ ዲን የሌለው ሰው ለፍቅር ለብር ወይም ለቤተሰብ ብላቹ ታገባላቹ ከዛን ደግሞ ወይ ከዲን ወይ ከዱኒያ ሳትሆኑ ዘጊ ህይወ
ለምንድነው ደዩስ ዲን የሌለው ሰው የምታገቡት? ምክር አሰሙ ነገ ይሻሻላል ብላቹ ዲን የሌለው ሰው ለፍቅር ለብር ወይም ለቤተሰብ ብላቹ ታገባላቹ ከዛን ደግሞ ወይ ከዲን ወይ ከዱኒያ ሳትሆኑ ዘጊ ህይወትን እንደ ባሪያ ሆናቹ ትኖራላቹህ።የእናንተ ስህተት ደግሞ ከእናንተ አልፎ ልጆቻቹን ዋጋ ያስከፍላል።እንደውም ደዩሷ እንደዚች አይነት ሴት ነች የእውነት ዲናን ብቶድ ኖሮ ሱናን የማይከተል ደዩስ ወንድ አታገባም ነበር https://t.me/NasihaLishebab

ግን ልጁ ቅስሙ ክሽ ብሎ ተሰብሮ ይሁን😁 እንደዚህ አይነት የመልስ ምት በዘርህም አይድረስ

ልክ ነች ከአንድ በኩል ምክንያቱም ማስተዳደር ካልቻለ በፍቅር ነው የቤት ኪራይ ሚከፍለው የምግብ ወጪ ሚችለው?
ልክ ነች ከአንድ በኩል ምክንያቱም ማስተዳደር ካልቻለ በፍቅር ነው የቤት ኪራይ ሚከፍለው የምግብ ወጪ ሚችለው?

ትላንት መካሪዬ ኪታብ አስሞጣዬ ነበር ነገር ግን ወደ ሙመይአዎች ከሄደ በኃላ ፍሪክ ሆነ። ወላሂ ጓደኛዬ ስለነበረ ሰው ነው ምነግራቹህ ፎቶውን ፌድ ተቆርጦ ሲፖስት ሳይ ደነገጥኩ አላህ ይምራው እኛንም ያፅናን🤲 https://t.me/NasihaLishebab

🚫  ለእህቶች ባጠቃላይ ዐረብ አገር የምትኖሩ በተለይ ህይወታችሁ እንዳይበላሽ ተጠንቀቁ ‼      የኢስላም ሸሪዓ ለሴት ልጅ ትልቅ ክብርና እውቅናን የሰጠ በምድር ላይ በሴት ልጅ መብት ወደር የማይገኝለት መለኮታዊ ሸሪዓ ነው ። በተደጋጋሚ ለመግለፅ እንደሞከርኩት የምእራቡ አለም ሴት ልጅ ከሰው ትመደባለች ወይስ አትመደብም እያለ ጉባኤ ይጠራ በነበረበትና የዐረቡ አለም ሴት ልጅ ዘር የምታዋርድ አድርጎ በሚያይበት የሰው ልጅ የአእምሮ ዝቅጠት ላይ በነበረበት ጊዜ ነው ኢስላም የሴትን ልጅ መብት ያወጀው ።       ሴት ልጅ በተለያዩ መለኮታዊ መመሪያዎች ከወንድ እኩል ቦታ ሰጥቶ ለዓለም ክብሯን ያሳየው ። በእናትነት ፣ በሚስትነት ፣ በእህትነትና በልጅነት ማእረግ ላይ አስቀምጦ አንገቷን ቀና እንድታደርግ ፈር ቀዷል ። ከዚህ ጎን ለጎን በስሜት ፈረስ ለሚጋልቡ ዐቅለ ደካሞች ክብሯን እንዳታስደፍር ገደብ በማስቀመጥ የህይወት መስመር ዘርግቶላታል ። በየአንዳንዱ ህግጋቱ ሴትን አስመልክቶ እንከን የለሽና ምክንያታዊ የሆኑ ብይኖችን አስፍሯል ።        ምእራባዊያኖች ሴትን ልጅ ሸቀጥ ለማድረግና የፈለጓትን እንደ ሸንኮራ አኝከው ስሜታቸውን አርክተው ለመጣል እንዲመቻቸው ለማድረግ እንዳይችሉ የኢስላሙ ሸሪዓ ስለከለከላቸው ሴትን ጨቁኗል እያሉ ያላዝናሉ ። ለሴት ልጅ ከወርቅ በላይ ቦታ የሰጠው የኢምን ሸሪዓ ይተቻሉ ። ከወርቅ በላይ የተባለው አንድ ሰው ወርቅን ሸፍኖ ከሚያስቀምጠው በላይ ኢስላም ሴትን ልጅ ራስዋን ሸፍና ገላዋንና ክብራን እንድትጠብቅ ስላደረገ ለደመነፍሳዊ ፍላጎታቸው አልመች ስላለ ነው ። በዚህም ራቁቷን ሆና እንድትወጣና ዝንብ እንደሚወረው ቆሻሻ ልትሆን ይፈልጋሉ ።      በመሆኑም ሴቶች የጌታቸውን መመሪያ ባለመጠበቅ እንሰሳዊ ስሜታቸውንና የነዋይ አፍቃሪነት ጥማቸውን ለማርካት በሚሯሯጡ ወንዶች ለሚደርስባቸው በደል በምንም መልኩ ኢስላምን ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም ። ለመግቢያ ያክል ይህን ካልኩኝ ወደ ርእሴ ልመለስ ።      ዐረብ አገር የሚኖሩ እህቶች ችግር ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ቢሆንም ለዛሬ ከትዳር ጋር የሚገናኘውን ጎን ለማይት እሞክራለሁ ። እንከን የለሹ የኢስላም ሸሪዓ ሴት ልጅ የትዳር አጓር ስታስብ ምንን መስፈርት ማድረግ እንዳለባት አስቀምጧል ።    በዚህም ሴት ልጅ ማየት ያለባት ሁለት ነገር ነው ። እሱም : – አንደኛ – ዲን              ዲን ሲባል መስገድ ማለት ብቻ አይደለም ። አላህን የሚፈራ ፣ በተውሒድና ሱና ላይ ቀጥ ያለ ፣ ሶላቱን በጀማዓ የሚሰግድ ፣ ትዳርን ለመጠቀሚያነት ሳይሆን ራሱን ለመጠበቅና የነብዩን ኡማ ለማብዛት ንያ አድርጎ የሚፈልግ ፣ አማናውን የሚጠብቅ ፣ ሴትን የማይበድል ፣ የማይዋሽ ፣ የማይከዳ ፣ የማያታልል ፣ ከሰዎች ጋር ያለው ግብረገብነት የተስተካከለና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል ። ታዲያ አንድ ሰው በእነዚህ ባህሪያት ላይ ያለውን ቦታ ማወቅ የሚቻለው በቅርበት ከሚያውቁት ከሚኖርበት አካባቢ ጀማዓ ባለትዳር ሆኖ ለሁለተኛ ከሆነ በማይታወቅ መልኩ ከመጀመሪያ ሚስቱ ቤተሰቦች በኩል የራስ ሰው ልኮ የትዳሩን ሁኔታ በጥንቃቄ እንዲያጣራ በማድረግ እንጂ ሚዲያ ላይ በሚፅፈውና በሚያናገረው ወይም በውስጥ መስመር በሚፃፃፉትና በሚያወሩት ወይም በኔት ወርክ ትስስር ባላቸው ጓደኞቹ በኩል አይደለም ። ሁለተኛ – ስነምግባር            ስነምግባር ሲባል በጣም ትልቁን የዲን ክፍል ይይዛል ። ስበምግባ ( መልካም ፀባይ ) አስመልክቶ የመጡ መረጃዎች በጣም በረካታ ናቸው ። ነገር ግን አብዛው ሰው ቤት ውስጥ ሬት  ይሆንና ውጪ ማር ነው ። ጥቂቱ በተቃራኒው ሊሆን ይችላል ። በመሆኑም ከላይኛው መስፈርት ባልተናነሰ መልክ ቱክረት ተሰጥቶት ሊጠና ይገባል ።       ወደ ትዳር የሚገቡ እህቶች እነዚህን መስፈርቶች በተባለው መልኩ ማጣራት ይኖርባቸዋል ። ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ በአጭር ጊዜ በሚዲያ ተዋውቀው ወንዱ መላኢካ መስሎ ቀርቦ ልቧን ካገኘ በኋላ ወደ ኒካሕ ይገባል ። በተለይ ዐረብ ሀገር የምትኖር ከሆነ መጀመሪያ አካባቢ እጇ ላይ ያለውን እስኪረከብ ድረስ በጣም አሳቢ ለሷ ህይወት የሚጨነቅ በመምሰል ቀርቦ ያለመው ሲሳካ ሁኔታዎች መቀየር ይጀምራሉ ። ይህ በርግጥ የሁሉም ነው ባይባልም ጥቂት አላህን የሚፈሩ ሊኖሩ ይችላሉ ። የአብዛኛዎች ታሪክ ግን ከላይ የተገለፀው ነው ።      ሴቶቹ ከኒካሑ በኋላና ዐረብ ሀገር የተቃጠሉበትን ሳንቲም ከእጃቸው ወጥቶ ሁኔታዎች ሲቀያየሩ ስለሱ ማስጠናት ይጀምራሉ ‼። የዚህን ጊዜ ጫት ቃሚ ፣ ሶላት የማይሰግድ ፣ ሺሻ ቤት የሚውል ፣ ደርስ የሚባል የማያውቅ ወይም ሱፍይ ሆኖ ይገኛል ።     ምን ያደርጋል አሳዛኝ ህይወት ፍታኝ ሲሉት ይህን ያክል ካልከፈልሽ ማለት ይጀምራል ። በጣም የሚያሳዝነው በአብዛኛ አካባቢ የሸሪዓ ፍርድ ቤት ዳኛ የሚባሉት ጫት ቃሚና ሱሰኞች ይሆናሉ ። ሴቶቹ ፍቺ ሲጠይቁ ምንድነው ችግሩ ብለው ይጠይቁና ሱሰኛ ነው ዐቂዳው የተበላሸ ነው ሲባል ዐቂዳው  ……… ህህህ እያሉ ያላግጣሉ ። ሴቶቹ ቅስማቸው ተሰብሮ ሞራላቸው ወድቆ ለታክሲና ለካርድ እንኳን የሚሆን ሳንቲም አጥተው ለሁለተኛ ጊዜ ለግርድና ወደ ዐረብ ሀገር ይሄዳሉ ። ይህ የብዙ ዐረብ ሀገር የሚኖሩ እህቶች ታሪክ ነው ።      የሚገርመው እባካችሁን ኡስታዝም ይሁን የቻናል ባለቤት ወይም ግሩፕ ላይ የሚሳተፍ በውስጥ መስመር አተገናኙ ሲባሉ ትልቅ ስኬት የተከለከሉ የሚመስላቸው ቀላል አይደሉም ።  የህይወታቸው መበላሸት የሚጀምረው በውስጥ መስመር መገናኘት የጀመሩለት ነው ።      ለማንኛውም ኒካሕ አሰራችሁ ሳይሆን ቀርቶ ኒካሕ አናወርድም ተብላችሁ የምትሰቃዩ እህቶች ነገሩ የተበላሸው መጀመሪያ ነውና ሶብር አድርጋችሁ በሽማግሌ በማስጠየቅ ነገሩን አስተካክላችሁ ኒካሓችሁ እንዲወርድላችሁ አድርጉ በምንም መልኩ የመጀመሪያው ኒካሕ ሳይወርድ ሌላ ኒካሕ እንዳታስሩ ተጠንቀቁ ።    ሌላው ወንዶችም ሴቶችም እባካችሁን አላህን ፍሩ, ባዳ ወንድና ባዳ ሴት በውስጥ መስመር መገናኘት ሐራም ነው ። የዲን ጉዳይ ለመጠየቅ ከሆነ ዑለሞች አሉ እነርሱን ጠይቁ, በየግሩፑ ሴቶችን ሰብስበው እናስቀራለን የሚሉ ሙፍቲ ወጠምሾችን ራቁ ! በጣም የሚገርመው ከሱ ውጪ የሆነን ሸይኽ ፈትዋ ከጠየቀች የኔ ፈትዋ አንሶሽ ነው እዴ ብሎ ከግሩፑ እንድትወጣ የሚያደርግ ጉደኛ መኖሩ ነው ።    ተመልከቱ ከኔ ውጪ ፈትዋ እንዳትጠይቂ ከጠየቅሽ ትባረሪያለሽ የሚል ወጠምሻ ሙፍቲ የሆነበት ዘመን ላይ ነው ያለነው ። ብቁ ሆኖ ቢሆን መልካም ነበር የሚገርመው አንዳንዱ እንኳን ሙፍቲ ሊሆን የዑለሞችን ንግግር እንኳን በቅጡ መረዳት የማይችል ነው ። በሴቶቹ በኩል ደግሞ  ዑለሞችን ከመጠየቅ ከዚህ አይነቱ መፃፃፍ ነው የሚቀናቸው ። ይህ ነው ወደ ህይወታቸው መበላሽት የሚያደርሳቸው ። በመሆኑም እንደቂል ብታዩንም አሁንም አላህን ፍሩ ከአጅ ነብይ ( ባዳ) ወንድና ሴት ጋር ያለችሁን መረን የለቀቀ ግንኙነት አቁሙ ። ትዳት ስትፈልጉ ዘሎ ከመግባት መጀመሪያ በደንብ አጣሩ ።       አላህ ይርዳችሁ ። http://t.me/bahruteka

አይ ኒቃብ ወደቀ መሬት¿ ማስክም ኒቃብም ፊትን የሚሸፍኑ ሆነው ሳለ ኒቃባቸውን አስወልቀው በማስክ አስገቧቸው። እንዳሉት ለደህንነት ጉዳይ ቢሆን ኖሮ ማስኩም ፊትን ስለሚሸፍን መለበስ አልነበረበትም።
አይ ኒቃብ ወደቀ መሬት¿ ማስክም ኒቃብም ፊትን የሚሸፍኑ ሆነው ሳለ ኒቃባቸውን አስወልቀው በማስክ አስገቧቸው። እንዳሉት ለደህንነት ጉዳይ ቢሆን ኖሮ ማስኩም ፊትን ስለሚሸፍን መለበስ አልነበረበትም። ሆኖም ግን ምክንያታቸው ሙስሊም ጠልነት ስለሆነ ፍላጎታቸው ኒቃቡን በማስወለቅ ማዋረድ፣ መጨቆን፣ ከእምነቷ ማራቅ ነው፤ አደረጉትም።   መብቷን ማስጠበቅ የነበረበት መጅሊስም ከቦታው ተገኝቶ ማስክ ገዝቶ ሰጣት። https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/Abu_Umer1

የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ 🌙 ሰባኹል ኸይር / ሰባኹል ኑር 🎧 ቁርዓን🫀 https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/Abu_Umer1

የላጤ ምኞት
የላጤ ምኞት

የመስጂዱችን አድራሻ የማታውቁ @Mujahid_Selefi አናግሩኝ

የዘንድሮዉ ክረምት ላይ አዳማ ኢብኑ ተይሚያ መስጂድ የሚጠሰው የኪታብ ኮርስ ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው ! ①· በአቂዳ (المختصر في أصول الأعتقاد)ሊሰእዲይ ②በሲራ (ኹላሰቱ ኑሩል,
የዘንድሮዉ ክረምት ላይ አዳማ ኢብኑ ተይሚያ መስጂድ የሚጠሰው የኪታብ ኮርስ ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው ! ①· በአቂዳ (المختصر في أصول الأعتقاد)ሊሰእዲይ ②በሲራ (ኹላሰቱ ኑሩል,የቂን) ③·በቀዋኢድ (አል ቀዋኢዱል ፊቅሂያ) ሊሰእዲይ ④ በአዳብ (መንዙመቱ ታኢየህ ሊልአልቢሪይ) 5 " (ሙተሚመቱል ኣጁሩሚየህ) 6 "አቂደቱ አሰለፍ አስሓቢል ሐዲስ አሳቡኒይ ደርሱ የሚሰጥበት ሰዓት ከ8:00 እስከ 10:00 እና 3:00-4:00 ነው ደርሱ የሚጀምረው በአሏህ ፍቃድ የዛሬ ሳምንት ሰኞ ሰኔ 29/ 2018 ነው ቦታ አዳማ ኢብኑ ተይሚያ መስጂድ join⬇️⬇️teegram ቻናል https://t.me/ibnuu_teymiyah https://t.me/ibnuu_teymiyah