ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

前往频道在 Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

显示更多
未指定国家未指定类别
916
订阅者
无数据24 小时
-67 天
+5630 天
帖子存档
◾️ቅመው የተቃሙ‼️ ➖➖➖➖➖➖➖ ጫትን መውደዳቸው ይገርማል ይደንቃል ሰው እንዴት ጠላቱን ልቡ ላይ ያትማል ካልገደልከኝ ብሎ ደጃፋን ይጠናል ስንት ወንዶች አይተናል ቅመው የተቃሙ መንገድ ለቀው ጠፍተው ጠመው የጠመሙ። 🔘ጫት፦ ብክነት ድህነትን መከራን ያወርሳል አመንምኖ አድርቆ ውበትን ያረግፋል አእምሮን በማወክ ማስተዋል ያግዳል እንቅልፍም ያሳጣል እረፍትን ይነሳል ከአላማ አሰነካሎ ቦዘኔ ያደርጋል 🔘ጫት፦ ጎጂ ለመሆኑ አያጠራጥርም አኮላሽ መኾኑም አያከራክርም በሽታ መሆኑን ዘንግተው ስተው ስንቶቹ ተመገቡት መድሀኒት ነው ብለው። ድብርት ያስወግዳል ብለው የሚሉት ዘላቂ አይደለም ይጠፋል በቅፅበት ድብርት የለቀቀ ቢመስል ለጊዜው ምርቃናው ሲጠፋ ጭንቀት ነው ሚወረው ወዳጄ ልምከርህ ስማኝ አድምጠኝ ጫት መቃምን ራቅ ጎጂ ነው እመነኝ ከኪሳራ ውጪ ምንም ትርፍ አታገኝ የሕመም መድሐኒት መጠኑ ልኬቱ እንደ በሽታው አይነት ይለያል ብርታቱ ጉንጩን ሞልቶ የሚቅም የጫት ሱሰኛ ቀንም እረፍት የለው ለሊትም አይተኛ የቂማ መዘዙ ቢያወጉት አያልቅም ጉዳቱን ጥፋቱን ቃሚውም አይክድም የጫትን ጉዳት የሚቃወም ካለ ወይ በሽተኛ ነው ወይ የተታለለ ይህ በእንዲህ እያለ… ሱናን ለመከተል አሻፍርኝ ያለው በሺርክ በቢድዓ የሚጨማለቀው ልብሱን በማስረዘም መንገድ የሚጠርገው ፂሙን እየላጨ ሴት ልጅ የመሰለው የሼሆቹ ሙሪድ ያ የጫት ምርኮኛው ሸሊላ እያለ ድቤ የሚወግረው በሀቅ ላይ መፅናት ልቡ እቢ ያለው ለሸሪአ እውቀት ምንም ግድ የሌለው ሰላቱ መስጅድ ላይ ሄዶ የማይሰግደው… ተዉሂድን ያዝ ሲሉት ሰበብ ሲደርድር ምስኪን ሲለምነው ብር የለኝ የሚል ኑሮ ተወደደ ብሎ የሚያማርር ለጫት ግን ያወጣል በቀን መቶ ሀምሳ ብር ደግሞም ብሎ ይላል ጌታየ ምን ነካህ ሀብት እፍልጋለሀ ተው ስጠኝ እባክህ ከሰው በታች ሆኘ እዳልቀር ከምድርህ ብሎ ይፍክራል ጫቴን እየበላሁ አንተን እንድዛህ ጫት የቃመ ጊዜ ምድሩ የሚጠበው አለምን በሙሉ የያዘ እሚመስለው ፎቁን ሱቁን ሁሉ የተቆጣጠርው ውሰዱ እያለ የሚያከፋፍለው በቅዠት ሲዋልል ውሎ የሚያመሸው ስካሩ ሲለቅ ግን ያ ሁሉ ባዶ ነው። ✍️ ቢንት አሕመድ

ሁለት የተዋደዱ ሰዎች ሁሉ በመጨረሻ ይለያያሉ። ከመለያየት በስተቀር ያለው ሁሉ ቀላል ነው።የምንወዳቸውን ሰዎች አንድ በአንድ ማጣታችን፣ ምንም ቅርበት ለዘላለም እንደማይቆይ ያስተምረናል። አንዳንድ ሰዎች ከአጠገባችን ቢለዩም፣ ትዝታቸው ከልባችን አይለይም። መለያየት የሕይወት ክፍል ቢሆንም፣ መቀበሉ ግን ሁሌም ቀላል አይሆንም። ለገጠመን ሐዘን አላህ የሚወደውን ነገር እንጂ ሌላን አንልም። #ትዝብት

ዛሬም እንደ ትናንት ሽርክን ይዋጋሉ፡ ተውሒድን ሱና ጋር ሁሌ ይሰብካሉ፡ ማነው ኢትዮጲያ ውስጥ ኢኽዋንን የወቃው⁉️ አህባሽ የረገጠ እስኪከፈት ላንቃው⁉️ ማነው በሀበሻ ወጣቱን ያነቃው⁉️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

ስለ መርዛማ ነሽዳ እና መንዙማ   የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች  ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇 የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት  ማዳመጥ ይችላሉ ❶ ነሽዳ በኢስላም እይታ ❷ ጦለዕል አለይና በድሩ ➌ ረመዳን እና ነሽዳ ➍ስንኩን አንሱት ነብዩ ➎ነብዩ ባትመጡማ ➏ሙሀመድ አወል ሀምዛ ➐ዞር በልልኝ የሀድራው ጠላት ➑ ያቀመር መካ ልቤ በእርሶ ➒ሶለዋት አለ ነቢ ➓በማንሲንቆ መንዙማ ❶❶ይቅርብኝ ጀነት ❶➋በቁረአን ሙዚቃ ❶➌አብሬት ክፍል ❶ ❶➍አብሬት ክፍል ➋ ❶➎ቃጥባሪ ነሽዳ ❶➏መገን ነቢ የሁሉ ቀላቢ ❶➐ መንዙማ ድብቅ መርዝ ❶➑ሁው ሁው ሁው ሁው ❶➒መንዙማ ➋0የሽርክ መንዙማ ➋❶መንዙማ እና EBC ➋➋መንዙማ ጉድ ➋➌ ጫት እና መንዙማ ➋➍መንዙማ ➋➎ ሙዚቃ እና ነሽዳ ➋➏ነብዩ ኢሳ እና አብሬት ➋➐የሱፉዮች መንዙማ እጅ ከፍንጅ በሚል ርዕስ በተከታታይ ክፍል መርዛማ መንዙማ በድምፅ የታገዘ ነው በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁሏህ ክፍል ❶                 ክፍል ➋➊ ክፍል ❷                 ከፍል ➋➋ ክፍል ➌                 ክፍል ➋➌ ክፍል ➍                 ክፍል ❷➍ ክፍል➎                  ክፍል❷➎ ክፍል ➏                ክፍል ❷➏ ክፍል➐                 ክፍል ❷➐ ክፍል➑                 ክፍል❷➑ ክፍል ➒                 ክፍል➋➒ ክፍል ➓                 ክፍል➌0 ክፍል ❶➊             ክፍል ➌➊ ክፍል ❶❷              ክፍል➌➋ ክፍል ➊➌              ክፍል➌➌ ክፍል ❶➍              ክፍል➌➍ ክፍል ➊➎             ክፍል ➌➎ ክፍል ❶➏             ክፍል ➌➏ ክፍል ➊➐             ክፍል ➌➐ ክፍል ❶➑             ክፍል ➌➑ ክፍል ➊➒ ክፍል ➋0 የአህባሾች መንዙማ በሚል ርዕስ በተከታታይ ክፍል መርዛማ መንዙማ በድምፅ የታገዘ ነው በኡስታዝ አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን ሀፊዘሁሏህ ክፍል➊              ክፍል ➐ ክፍል➋               ክፍል➑ ክፍል➌               ክፍል ➒ ክፍል➍               ክፍል ➓ ክፍል➎                ክፍል ❶❶ ክፍል➏                 ክፍል ❶❷ ጥናተ መንዙማ በሚል ርዕስ በተከታታይ ክፍል መርዛማ መንዙማ በድምፅ የታገዘ ነው በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁሏህ ክፍል➊              ክፍል➋               ክፍል➌               ክፍል➍               ክፍል➎                ክፍል➏ ክፍል ➐ ክፍል ➑ ክፍል ➒  የሙሐመድ አወል የሺርክ መንዙማዎች በሚል ርዕስ በተከታታይ ክፍል መርዛማ መንዙማ በድምፅ የታገዘ ነው በኡስታዝ አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን ሀፊዘሁሏህ ከክፍል ❶--➋0 ታገኝላችሁ ተጫኑኝ              ይደመጥይደመጥበጣምአስፈላጊወሳኝነው የሽርክ ስንኝ  በሚል ርዕስ በተከታታይ ክፍል መርዛማ መንዙማ በድምፅ የታገዘ ነው በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁሏህ ከክፍል ❶--❶➏ታገኝላችሁ ተጫኑኝ

➡️ ተመልከቱ በቃ እነዚህ ሰዎች ለየላቸው ጭራሽ ID'ካርድ ማዘጋጀት ጀመራችሁ نعوذ بالله من الغلو والخذلان ሚዛናዊነት የጎደለው በእልህ የተሞላ የغሉው ውጤት ማሳያ ፍርድ ነው!! ከ
➡️ ተመልከቱ በቃ እነዚህ ሰዎች ለየላቸው ጭራሽ ID'ካርድ ማዘጋጀት ጀመራችሁ نعوذ بالله من الغلو والخذلان ሚዛናዊነት የጎደለው በእልህ የተሞላ የغሉው ውጤት ማሳያ ፍርድ ነው!! ከንደዚህ አይነት እውር ድንበር አላፊነት አላህ ይጠብቀን። https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1

👆 ተመልከት ይህን በምርቃና እንደመጣለት የሚያወራ ሰውየ!! ⚠️ እርሱን ያልመሰሉ ሰዎችን የመጥላት ስሜቱ እዚህ ደረጃ አድርሶታል! መካሪ ያጣ ሽማግሌ! 👇 የሚናገረውን ስማ እስቲ !! 👉ነቢያቸው የመን!! 👉 አምላካቸው የመን!! 👉 ኢማማቸው የመን!! ነው እያሌ ጋሼ!! نعوذ بالله من الغلو والخذلان 👆 ሚዛናዊነት የጎደለው በእልህ የተሞላ የغሉው ውጤት ማሳያ ፍርድ ነው!! ከንደዚህ አይነት እውር ድንበር አላፊነት አላህ ይጠብቀን። وعين الرضا عن كل عيب كليلة كما أن عين السخط تبدي المساوي ሰውየው ከጩኸት ውጪ በመረጃ መናገር የማይችል ተራ ለፍላፊ መሆኑን በግልፅ እያሳወቀን ነው።

Repost from N/a
ተዘጋበት ጊዜ ውስጥ መደረጉ ነው፡፡ ከነዚህ መስፈርቶች አንዱን ያጓደለ ተውበቱ ትክክለኛ አይደለም፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግ ሃሜት ላይ በወደቅን ቁጥር እውነተኛ የሆነን ተውበት ብናደርግ በቀጣይ ተመሳሳይ ጣጣ ውስጥ ላለመግባት እንጠነቀቃለን፡፡ ⑨ ከወንድም ክብር ላይ መከላከል ያለውን ፋይዳ ማሰብ፡- ወንድምህ ሲታማ ከሱ መከላከልህ ላንተ ትልቅ ሽልማት አለው፡፡ ነብዩ ﷺ “ከወንድሙ ክብር ላይ የተከላከለ አላህ በቂያማ ቀን ከፊቱ እሳትን ያርቅለታል” ይላሉ፡፡ ስለዚህ ይሄ ሽልማት እንዳያመልጥህ ከወንድምህ ተከላከል፡፡ አንድ ሽልማት፡፡ ይሄ ተግባርህ ሃሜት ላይ የሚወድቅ ወንድምህንም ከጥፋት ስለሚያቅበው ሌላም ሽልማት አለህ፡፡ ያለበለዚያ ግን ከአፍታ በኋላ እራስህን የሃሜቱ አካል ሆነህ ልታገኘው ትችላለህ፡፡ ①∅ ሆደ ሰፊ መሆን፡- ለሃሜት ከሚገፉን ነገሮች አንዱ በሌሎች ላይ የሚኖረን ቅሬታ ነው፡፡ ታጋሽና ይቅር ባይ ብንሆን ግን ስለሰዎች ክፉ እንዳናስብና በክፉ እንዳናነሳቸው ይረዳናል፡፡ ①① ሃሜት የሚፈቀድባቸውን ሁኔታዎች ጠንቅቆ መለየት፡- የሰዎችን ድክመት ወይም ጥፋት መናገር የሚፈቀድባቸው ወይም ግዴታ የሚሆንባቸው ውስን ሁኔታዎች እንዳሉ የሚታወቅ ነው፡፡ እነዚያ ሁኔታዎች ለአስገዳጅ ምክንያት ብቻ የሚፈቀዱ ስለሆነ ያለ አግባብ እየመነዘርናቸው እንዳይሆን መጠንቀቅ አንዱ ከሃሜት መራቂያ ስልት ነው፡፡ አንዳንዱ በሸሪዐዊ ምክንያቶች አስታኮ የግል ቂሙን የሚያወራርድ፣ ተያያዥነት በሌላቸው ግለሰባዊ ጉዳዮች ውስጥ ዘልቆ የሚገባ፣ አልፎም አካላዊቅርፅን ሳይቀር እያነሳ የሚያንቋሽሽ ያጋጥማል፡፡ ለዚህ አይነቱ ጥፋት እራስን መሸወድ ካልሆነ በስተቀር ሃሜት የሚፈቀድባቸውን ሁኔታዎች ማጣቀስ አያዋጣም፡፡ የአላህ ሶላትና ሰላም በነብያችን ላይ ይሁን።      @IbnuMunewor

Repost from N/a
ከሃሜት ለመራቅ የሚያግዙ #11 ነጥቦች፦ 👉 አላህ ያደለው በጣም ጥቂት ሰው ካልሆነ በስተቀር ከሃሜት ወንጀል የሚተርፍ የለም፡፡ እንዲያውም “እነ እከሌ ሃሜተኞች ናቸው” እያሉ ሌሎችን የሚወነጅሉ ሰዎች እራሱ በአብዛሀኛው እራሳቸውም ሃሜተኞች ናቸው፡፡ ልዩነቱ ለሃሜት የሚገፋው ምክንያትና የሚታማው አካል መለያየት ብቻ ነው፡፡ #ስለዚህ ይሄ ችግር አብዛሀኞቻችን የተዘፈቅንበት ነው፡፡ በዚህ ረገድ አጋዥ የመሰሉኝን ጥቂት ነጥቦች እንደሚከተለው አሰፍራለሁ፡፡ ① የሃሜትን ምንነት መረዳት፡-   ብዙ ሰዎች ሰዎችን እያሙ ነገር ግን “ይሄ እውነት ነው፤ ሃሜት አይደለም” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ይሄ ስለሃሜት ያላቸውን የግንዛቤ ክፍተት የሚያሳይ ነው፡፡ ሃሜት ማለት ነብዩ ﷺ እንደገለፁት “ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው፡፡” “የማነሳው ነገር ከወንድሜ ዘንድ ካለስ?” ተብለው ሲጠየቁ “የምትለው ነገር ከወንድምህ ዘንድ ከኖረ በርግጥም አምተኸዋል፡፡ የምትለው ነገር ከሌለበት ግን በእርግጥም ቀጥፈህበታል” አሉ፡፡ [ሙስሊም የዘገቡት] አንዳንዱ ወንድሙን እያማ “ይሄ ከፊቱም የምናገረው ነው” ይላል፡፡ ይሄ ግን ሐቂቃውን አይቀይረውም፡፡ እንዲያውም ከፊቱ እየተናገረ ቅስሙን ሲሰብር ወይ ተጨማሪ ወንጀል ይደርባል፡፡ አለያ ደግሞ ተጣልቶ ፊትና ያቀጣጥላል፡፡ እንዲያውም አንዳንዱ “ይሄ ከፊቱም የምናገረው ነው” የሚለው ሃሜተኛ እንዳይባል ለአድማጮቹ የሚሰጠው ጉቦ ነው እንጂ ውሸቱን ነው የሚያወራው፡፡ ጉዳዩን ከሚታማው ሰው ዘንድ ቢያወራ እንኳን በሌለበት በሚያወራው መልኩ አይሆንም፡፡ ② የሃሜትን አስከፊነት መገንዘብ፡- አብዛሃኞቻችን ሃሜት ምን ያክል #አስከፊ እንደሆነ በሚገባ አናውቅም፡፡ አንድ ሁለት ምሳሌ ብቻ ብንመለከት የጉዳዩን አስፈሪነት ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል፡፡ ምሳሌ አንድ፡- የመጀመሪያው ሃሜት ልክ የሞተ ወንድምን ስጋ እንደመብላት ነው የሚለው ቁርዓናዊ መልእክት ነው፡፡ ትኩረት ብንሰጠው ይሄ እጅግ ቀፋፊ ነገር ነው፡፡ እስኪ አስቡት አንድ ጨካኝ ገዢ “ሰዎችን በሃይል እየደበደበ የሞቱ ሰዎችን ስጋ እንዲበሉ አደረጋቸው” የሚል ዜና ከምስል ጋር ብንመለከት ምን ይሰማናል?! ሰቅጫጭ ነው አይደል?! የሆኑ ሰዎች የሰው ስጋ እየመተሩ፣ እየዘለዘሉ ሲበሉ ብንመለከትስ ምን ይሰማናል?! በቃ ጌታችንም ሃሜት ማለት የሞተ ወንድምን ስጋ እንመብላት ነው አለን፡፡ ሰው ባማን ቁጥር በአይነ ህሊናችን ጥርሳችን የተቦጫጨቀ የሰው ስጋ እንደያዘ ወይም እያኘከ እንደሆነ ብንስለው ዘግናኝ ምስል ይታየናል፡፡ ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “አላህ ይህን ምሳሌ የሰጠው የሞተን መመገብ አፀያፊ የሆነ ሐራም ስለሆነ ነው፡፡ ሃሜትም እንዲሁ በሃይማኖት የተወገዘ፣ ከነፍስ ዘንድ የሚያፀይፍ ነው፡፡” ምሳሌ ሁለት፡- ነብዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸው ነው፡፡ “በእርግጥም አንድ ሰው ደንታ ሳይሰጠው በተናገረው ንግግር ሰባ አመት ወደ ጀሀነም ይምዘገዘጋል!!” አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡ ምሳሌ ሶስት፡- ነብዩ ﷺ በሁለት ቀብሮች ዘንድ አለፉ፡፡ ሰዎቹ በቀብራቸው ውስጥ የሚቀጡ ናቸው፡፡ “አንዱ ሰዎችን ያማ የነበረ ነው” አሉ፡፡ [ሶሒሑል ኣደብ አልሙፍረድ፡ 275] እነዚህ ምሳሌ ብቻ ናቸው፡፡ ሌሎችም አስፈሪ መረጃዎችን አልፎ አልፎ ብንመልከትና ደዕዋዎችን ብናዳምጥ ጠቃሚ ነው፡፡ ③ ለሃሜት የሚያጋልጡን መንገዶችን መለየት፡- በአብዛሀኛው ለሃሜት የሚያጋልጡን መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡- ስራ መፍታት፡- ስራ ፈቶች በብዛት ሃሜተኞች ናቸው፡፡ እራሳችንን በስራ መጥመድ አንድ ከሃሜት መራቂያ ብልሃት ነው፡፡ ስለሆነም አእምሯችንን ስለሰዎች ከማሰብ ዞር በሚያደርጉን ስራዎች ላይ መጥመድ ፋይዳው ድርብርብ ነው፡፡ በተጨማሪም ቁርኣን በመቅራት፣ ዚክር በማድረግ፣ ጠቃሚ ፅሁፎችን በማንበብ፣ ሙሓዶራዎችን ወይም ደዕዋዎችን በማዳመጥ ትርፍ ጊዜያችን ከሃሜት በመራቅ በጠቃሚ ነገር ላይ ማሳለፍ እንችላለን፡፡ ዑለማዎቻችን እንደሚሉት ምላስ በጥሩ ነገር ካልጠመድናት ያለ ጥርጥር በመጥፎ ነገር መጠመዷ አይቀርም፡፡ ወሬ ማብዛት፡- ወሬው የበዛ ሰው ያለ ጥርጥር ለጥፋት የቀረበ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “ዝም ያለ ተረፈ” ይላሉ፡፡ ስለዚህ በዝምታ ውስጥ ያሉ ፋይዳዎችን ልናስተነትን ይገባል፡፡ ባጭሩ ወሬ መቀነሳችን ለሃሜት ከምንጋለጥባቸው መንገዶች ዋናውን መቀነስ ነው፡፡ የጓደኛ ጣጣ፡- መቼም ሃሜት የጋራ ወንጀል ነው፡፡ ሃሜት የሰማ ሰው በመቃወሙ የሚከተል አደጋ ካልኖረ በስተቀር መቃወም ግዴታው ነው፡፡ ይህን ያልቻለ ቢያንስ በልቡ ሊጠላ ይገባዋል፡፡ ያለበለዚያ አድማጩም እንደተናጋሪው ተጠያቂ ነው፡፡ መቼም እራሳችንም ሆንን ጓደኛችን በቀላሉ ነገሮችን ወደ ሃሜት የሚለውጥ አይጠፋም፡፡ ይህን ችግር አሰተውሎ ለህክምናው መታገል ብልሃት ነው፡፡ ችግሩ ከኛ ከሆነ ተቅዋን መላበስ ሁነኛ መፍተሄ ነው፡፡ ከጓደኞቻችንም ለዚህ ጥፋት የሚያጋልጡንን ከቻልን ግልፅ መመካከር ኖሮ ተያይዞ ከጥፋት በመራቅ ወደ ኸይር መጓዝ፡፡ ካልሆነ ግን በመራቅም ቢሆን ቢያንስ እራስን ከጥፋት ማትረፍ ትልቅ ብልሃት ነው፡፡ ይሄ ውሳኔ ለአንዳንዶቻችን ትልቅ መስዋእትነት ሊጠይቅ ቢችልም የሚከተለውን መዘዝ ማሰባችን ጉዳዩን ያቀለዋል፡፡ የልብ መድረቅ፡- እንዲያውም ቁልፉ እዚህ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ተቅዋችን ይጨምር ዘንድ ልንታገል ይገባል፡፡ ④ ሙራቀባ፦ (በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ላይ ዘወትር አላህን ማሰብ)፡- “ከሱ ዘንድ ረቂብና ዐቲድ ቢኖሩ እንጂ አንድም ንግግር አይናገርም” የሚለውን አስፈሪ ቁርኣናዊ መልእክት ማሰብ ጥሩ ነው፡፡ ⑤ ነፍስን መቆጣርና መተሳሰብ፡- ህይወትን በግምት መግፋት አይገባም፡፡ ለራሳችን ከሐራም ነገሮች ያለንን ርቀት፣ ከግዴታ ነገሮች ያለንን መዘነጋት የምንገመግምበት ፋታ ልንሰጥ ይገባል፡፡ ካልሆነ ግን እራሳችንን ሳናስተውለው በቀላሉ ከማንመለስበት ርቀት ላይ ልናገኘው እንችላለን፡፡ ⑥ የመልካም ቀደምቶችን አርአያ መከተል፡- ሌላው ከሃሜት መራቂያ ብልሃት ነው፡፡ በዚህ ረገድ የሰለፎች አቋም ምን ይመስል እንደነበር ተግባራዊ ተሞክሮዎችን ማጥናት ጠቃሚ ዘዴ ነው፡፡ ምን ያክል ሃሜትን ይፀየፉ እንደነበር፣ ለሃሜተኛ ምን አይነት መልስ ይሰጡ እንደነበር መመልከት፡፡ ይሄ ለሚያስተውል ሁሉ በራሱ ማንነት እንዲሸማቀቅ በማድረግ በተጨባጭ የሚታይ ውጤት የሚያስከትል ስለሆነ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ዘዴ ነው፡፡ ⑦ ዱዓ፡- አላህ ምላሳችንን ከሃሜት እንዲጠብቅልን መማፀን አንዱ ከሃሜት መራቂያ መንገድ ነው፡፡ ⑧ እውነተኛ ተውበት፡- ለምንፈፅመው የሃሜት ጥፋት እንዲሁ የዋዛ ፈዛዛ “አስተግፊሩላህ” ሳይሆን መስፈርት የሚያሟላ እውነተኛ ተውበት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሰው ያለ አግባብ የወሰደው የሰው ሐቅ ካለ በዚህ ጥፋቱ ከአላህ ፊት እንዳይጠየቅ የሚያስፈልጉ የተውበት መስፈርቶች አሉ፡፡ እነሱም አንደኛ፡- አላህን ብቻ በማሰብ መመለስ- ኢኽላስ፡፡ አላህን አስቦ እስካልተመለሰ ድረስ ከጥፋቱ መራቁ ብቻውን ቀድሞ ከተፈፀመው ጥፋት ከመጠየቅ አያተርፈውም፡፡ ሁለተኛ፡- ስለፈፀመው ጥፋት መፀፀት (ጉዳዩን አቅልሎ ሊያይ አይገባምና) ሶስተኛ፡- ከጥፋቱ ሙሉ ለሙሉ መራቅ (የሰው ሐቅ ካበት መመለስ) አራተኛ፡- ዳግም ወደዚያ ጥፋት ላይመለስ ቁርጠኛ ውሳኔ ማድረግ አምስተኛ፡- ተውበቱ የተውበት በር ባል

ኢብኑ ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸዉ እና እንድህ ይላሉ "أنه إذا كثرت الأحزاب في الأمة فلا تنتم إلى حزب، فقد ظهرت طوائف من قديم الزمان مثل الخوارج والمعتزلة والجهمية والرافضة، ثم ظهرت أخيرًا إخوانيون وسلفيون وتبليغيون وما أشبه ذلك، فكل هذه الفرق اجعلها على اليسار وعليك بالأمام وهو ما أرشد إليه النبي في قوله: فَعَلَيْكُمْ بِسْنِي وَسُنَّةِ الْخُلَفَاءِ الرَّاشِدِينَ . የሙስሊም  ቡድኖች ከበዙ ወደ ማንም ቡድን አትቀላቀል፤ ከጥንት ጀምሮ እንደ ኸዋሪጅ፣ ሙዕተዚላ፣ ጀህሚያ እና ራፊዷ የመሳሰሉ ክፍሎች(ጀመዓወች) ታይተዋል፤ ከዚያም በኋላ የኢኽዋኖች፣ ሰለፍዮች፣ ተብሊጊዎች እና የመሳሰሉት ታይተዋል፤ ስለዚህ እነዚህን ቡድኖች ሁሉ በግራ በኩል ተዉዋቸው እና አንተ ወደፊት (ቀጥተኛው መንገድ) ላይ ፅና፤ ይህም ነቢዩ (ሱ.ዐ.ወ) ያመላከቱት ነው፡- «የኔን ሱና እና በቅን መንገድ የተመሩ ምትኮችን ሱና ያዙ» በማለት። ولا شك أن الواجب على جميع المسلمين أن يكون مذهبهم مذهب السلف لا الانتماء إلى حزب معين يسمى السلفيين، فهناك طريق السلف وهناكحزب يسمى السلفيون والمطلوب اتباع السلف، إلا أن الإخوة السلفيين هم أقرب الفرق إلى الصواب ولكن مشكلتهم كغيرهم أن بعض هذه الفرق يضلل بعضًا ويبدعه ويفسقه، ونحن لا ننكر هذا إذا كانوا مستحقين، لكننا ننكر معالجة هذه البدع بهذه الطريقة، والواجب أن يجتمع رؤساء هذه الفرق، ويقولون بيننا كتاب الله عز وجل وسنة رسوله فلنتحاكم إليها لا إلى الأهواء والآراء، ولا إلى فلان أو فلان، فكل يخطئ ويصيب مهما بلغ من العلم والعبادة ولكن العصمة في دين الإسلام.. ያለምንም ጥርጥር በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ግደታዉ ፣አካሄዳቸዉ የቀደምቶች አካሄድ እንጂ 'ሰለፊዎች' የሚባል የተወሰነ ፓርቲ (ወይም ቡድን) አባል መሆን አይደለም። በመሆኑም የሰልፍ መንገድ አለ፣ 'ሰለፊዎች' የሚባል ፓርቲም አለ፤ የሚፈለገው ግን የሰልፍን መንገድ መከተል ነው። ነገር ግን ሰለፊ ወንድሞች ከቡድኖች ሁሉ ወደ እውነት የቀረቡ ናቸው፤ ችግራቸው ግን እንደ ሌሎች ሁሉ ከእነዚህ ቡድኖች መካከል አንዳንዶቹ ሌሎችን ስተዋል፣ ሙብተድዕ ፣ ወይም ፋሲቅ ማለታቸው ነው። እኛም ይህ የሚገባቸው ከሆነ እንሱን አንቃወምም፣ ነገር ግን እነዚህን ፈጠራዎች (ቢድዓዎች) በዚህ መንገድ ማከቸውን(ማስተካከላቸዉን) እንቃወማለን። የነዚህ ቡድን መሪዎች  መሰብሰብ እና 'በእኛ መካከል የአላህ መጽሐፍ እና የነቢዩ ሱና አለ፤ ወደ እነርሱ እንጂ ወደ ፍላጎቶችና ሐሳቦች፣ ወይም ወደ እገሌ እና እገሌ ፍላን ( አመለካከት)አንመለስም' ማለት ይገባቸዋል፤ ምክንያቱም የቱንም ያህል በእውቀትና በአምልኮ የገፋ ቢሆንም እያንዳንዱ ሰው ይሳሳታል፣ ትክክልም ይሆናል፤ ጥበቃ (ዒስማ) ግን በእስልምና ሃይማኖት ውስጥ ብቻ ነው የሚገኘው።" شرح أربعين النووية በወንድም አቡበከር ሰዒድ https://t.me/wdumuslimstu https://t.me/wdumuslimstu https://t.me/wdumuslimstu

Repost from N/a
ሀብት ለጊዜው ዓይንን ያደምቃል ዲንና አኽላቅ ግን ለዘላቂ ሕይወት ብርሃን ይሆናሉ። በትዳር መንገድ ላይ ቁሳቁስና ገንዘብ አካፋይ እንጂ የመሠረት ያህል ጥንካሬ የላቸውም። ትዳር ማለት የሁለት ነፍሶች ውህደት እና የሁለት ልቦች ሰላም ወደ አላህ የሚያደርስ መንፈሳዊ ጉዞ ነው። ​አላህ በታላቁ ቃሉ ውስጥ ትዳርን ሲገልጽ በገንዘብና በቁሳቁስ መለኪያ ሳይሆን በሰላምና በመረጋጋት ነው የገለፀው ለዚህም(لتسكنوا) የሚለውን ቃል ተጠቀመ ይህም ማለት ልብ ከውጭ ዓለም ውዥንብር አርፋ የምትታደስበት ነፍስ የምትረጋጋበት ማለት ነው። ገንዘብ አልጋ ይገዛል እንጂ እውነተኛ እንቅልፍና መረጋጋትን አይገዛም። ቁሳቁስ ትልልቅ ቪላዎችን ይገነባል የልብ ሰላምን ግን የሚገነቡት መወዳህ እና ረሕማ ናቸው። እነዚህ ደግሞ የሚመነጩት ከአላህ ዲን እና ከመልካም አኽላቅ ብቻ ነው። ​ነብዩ ﷺ የትዳር መሠረት ምን መሆን እንዳለበት ሲያስተምሩ ከቁሳቁስ ባሻገር ያለው እውነተኛ ሀብት ዲን መሆኑን በግልጽ አስምረውበታል። ሴት ልጅ ለአራት ነገሮች ስትባል ትገባለች ለሀብቷ ለዘሯ ለውበቷ እና ለዲኗ የዲን ባለቤት የሆነችውን ያዝ ያ ካልሆነ እጆችህ ይክሰሩ:: ቡኻሪና ሙስሊም በሌላም ሀዲስ ነብዩ ﷺ ልጆቻችንን ለምን አይነት ሰው መዳር እንዳለብን ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል:- ዲኑንና አኽላቁን የምትወዱት ሰው ለእጮኛነት ከመጣችሁ አግቡት ይህንን ካላደረጋችሁ በምድር ላይ ትልቅ ፈተናና ታላቅ ብልሹነት ይከሰታል። ቲርሚዚ ​ነቢዩ ﷺ ሀብቱ ስንት ነው? በሉ አልሉም «ዲኑና አኽላቁ እንዴት ነው በሉ» አሉ እንጂ። ምክንያቱም ገንዘብ በሌሊት መጥቶ በጠዋት ሊጠፋ የሚችል አላፊ ነገር ነው። ዲን ያለው ሰው ግን በሀብት ጊዜ አላህን ያመሰግናል በችግር ጊዜ ይታገሳል። ሚስቱን ቢወዳት ያከብራታል ባይወዳት እንኳ አላህን ስለሚፈራ አይበድላትም አያዋርዳትም ሀቋን ይጠብቃል በቀጥተኛው መንገድ ላይ ያግዛታል:: ​የቀደምት መልካም ሰለፎች ለትዳር አጋር መረጣ የነበራቸው ሚዛን ቁሳቁሳዊ ሳይሆን ዲናዊ ነበር። ​አንድ ሰው ወደ ታላቁ ዓሊም ሐሰን አል-በስሪ መጥቶ፦ ሴት ልጅ አለችኝ ብዙ ሰዎች ለእጮኛነት ጠይቀዋታል፤ ለማን ልዳራት? ብሎ ጠየቃቸው እሳቸውም እንዲህ አሉት:- ​አላህን የሚፈራን ሰው አጋባት ምክንያቱም ቢወዳት ያከብራታል ቢጠላት እንኳ አላህን ስለሚፈራ አይበድላትም። ከእዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ድንቅ ታሪክን ማውሳት እንችላለን:: ​የዐብዱላህ ኢብኑ ሙባረክ አባት ሙባረክ በአንድ ባለሀብት የአትክልት ስፍራ ውስጥ ተቀጣሪ ዘበኛ ነበር። የቦታው ባለቤት አንድ ቀን መጥቶ ጣፋጭ ሮማን እንዲያመጣለት ጠየቀው። ሙባረክ ያመጣለት ሮማን ግን መራራ ሆነ። ባለቤቱም ተናዶ እዚህ ሁሉት አመት እየሰራህ ጣፋጩንና መራራውን አታውቅም እንዴ አለው። ሙባረክም ጌታዬ ሆይ አንተ እንድጠብቅ እንጂ እንድቀምስ አልፈቀድክልኝም ስለዚህ አንድም ፍሬ ቀምሼ አላውቅም አለው። ​ባለቤቱ በሙባረክ አላህን ፈሪነትና ታማኝነት እጅግ ተደነቀ። ባለቤቱ አንዲት ውብና ሀብታም ልጅ ነበረችው። ከየአቅጣጫው ያሉ ሀብታሞችና ባለስልጣናት ለትዳር ይጠይቋት ነበር። ባለቤቱ ሙባረክን ልጄን ለማን ብድራት ይሻላል ብሎ ጠየቀው። ​ሙባረክም እንዲህ አለው፦ ​የጃሂልያ ሰዎች ለትዳር ዘርን ይመረጡ ነበር አይሁዶች ሀብትን ይመረጣሉ ነሷራዎች ውበትን ይመረጣሉ የዚህ ኡመት ሙስሊሞች ግን ዲንና አኽላቅን ይመረጣሉ። ስለዚህ የምትከተለውን ምረጥ:: ​ባለቤቱ የሙባረክን ጥበብና አላህ ፈሪነት አይቶ ውድ ልጁን ለደሃው ዘበኛ ለሙባረክ ዳረለት። አላህም ከዚህ ትዳር ለኡመቱ ታላቅ ብርሃን የሆኑትን ዐብዱላህ ኢብኑ ሙባረክን ሰጣቸው:: ምን ግዜም ቢሆን አላህን ከሚፈራ ሰው የሚወጣው ዘር ከአላህ እገዛ ጋር የተባረከ እና በኸይር ላይ ያለ ነው:: ​ሀብት ውበት የትዳርን በር ያደምቃሉ የቤቱን ምሰሶ ግን አያቆሙም። የቤቱን ምሰሶ አጽንተው የሚያቆሙት ማዕበል ሲነሳ መርከቧን የሚያጸኗት የባል እና የሚስት ሶብር እና መልካም አኽላቅ ብቻ ናቸው። ይህ ደሞ የሚገኘው ትዳር መጀመሪያ ላይ አላህን በመፍራት እና በአኽላቅ ላይ ከተመሰረተ ነው:: ​ገንዘብ ተለዋዋጭ ነው ዛሬ ያለ ነገ ሊጠፋ ይችላል። ውበት አላፊ ነው በዕድሜና በጊዜ ሂደት ይረግፋል። ዲንና አኽላቅ ግን ዘላቂ ሀብቶች ናቸው! ​ዲን ያለው/ላት አጋር ወደ ጀነት የሚያቀናን መንገድ ይመራል በኢባዳ በመልካም ስራ ያግዛል በችግር ጊዜ እንደ አለት ይቆማል። ​አኽላቅ ያለው/ላት ድካም ይረዳል ስህተት በጥበብ በሶብር ያልፋል ቤትን በፈገግታና በሰላም ይሞላል። ​ስለዚህ ለትዳር ዋነኛው መሰረት ልናረግ የሚገባን ዲን እና አኽላቅ ነው:: በእዚህ ግዜ እየተስተዋለ ያለው ግን በወርቅና በብር ትዳር እየተመዘነ ዲን እና አኽላቅ እየተዘነጋ ነው:: ​ትዳርን በወርቅና በብር ሚዛን ሳይሆን በዲን በአኽላቅ ሚዛን መመዘን በሰላም በሙሀባ የተሞላ ሕይወት ለመኖር ዋና ቁልፍ ነው። ​አኽላቅ የሌለውን በሀብቱ ማግባት ወይም በውበቷ ተማርኮ ብቻ ማግባት መርዛም እባብን በወርቅ ሰንሰለት አጋይጦ እንደመያዝ ነው። ወርቁ ያምራል መርዙ ግን ገዳይ ነው። ዲን እና አኽላቅ መሰረታችን ይሁን!!! كتبه الفقير إلى عفو ربه ابو عبدالله https://t.me/Abbu_Abdillah

እውን ሰይድ ቁጥብ ሙስሊሞችን አያከፍርምን⁉️ 🎤በኡስታዝ ሙሀመድ ሢራጂ ሀፊዘሁሏህ !! 🍃👉https://t.me/abujemila25

👉ለወቅታዊ የሀገራችንን ሰላም መታወክ የሻይኽ አብዱረዛቅ ብኑ አብደል ሙህሲን ሪሳላ ልጠቁማችሁ ተጠቀሙ በት። أَمْنُ البِلادِ: أَهميَّتُه وَوَسائِلُ تَحقيقِه وحِفظِه የሃገር ደህንነት: አሳሳቢነቱና የማረጋገጫ መንገዶቹ || አምኑል_ቢላድ 📝 ዝግጅት፡ ዐብዱረዛቅ ብኑ ዐብዲል ሙሕሲን አልበድር 🇸🇦 ቋንቋ: ዐረብኛ 📄 ገፆች፡ 43 🗂 የፋይል መጠን: 526.64 KB 📂 የፋይል አይነት፡ PDF = 🍃👉https://t.me/abujemila25 🍃👉https://t.me/abujemila25

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አድስ ፍሬሸማን ተማሪዎች የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት እናንተን ተቀብሎ ማንኛውንም ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን በሚከተለው መልኩ ገልጿል። የም
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አድስ ፍሬሸማን ተማሪዎች የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት እናንተን ተቀብሎ ማንኛውንም ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን በሚከተለው መልኩ ገልጿል። የምታውቁት ጓደኛ ወይም ቤተሰብ ካለ መልዕክቱን Share በማድረግ ወንድማዊ ትብብራችሁን አሳዩአቸው።
መልዕክታቸው እንደወረደ👇 ​ምንም ሓሳብ አይግባችሁ! 🔗 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ እያልን፤ ወደ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ። 👉 ​ስለ ግቢው ሁኔታም ሆነ ስለ መስጂድ እና ጀመዓ ምንም ሳትጨነቁ በነዚህ ስልኮች በመደወል መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በታላቅ ደስታ እንገልፃለን። ​ 1, ​Abdurehim 📞 0925622332 2, ​Arebu      📞 0901700111 3, ​Abdellah 📞 0908704005 4, ​Faruq        📞 0985883937 5, Nesredin Afanoromo 0915486276 ​መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ እንመኛለን! (Mizan Tepi University Muslim Student JEMEA) 🔗 Join & Share our channel: 👇          👇 http://t.me/eqrai_jemea

በተለያዩ ማዕረጎች ለተላበሱ ዳኢዎች /ኡስታዞች/ለነ ዶክተር እከሌም አሁን ላይ ያለው የዶክትሬት እና ሌሎችም ማዕረጎች እውነት ትክክለኛ ትምህርቱን ተከታትለው ከሚታወቁ ዩኒቨርስቲዎች የተሰጠ ነው ወይስ እንደት ነው አሁን ላይ ምንም ሳይቀሩ የሆነ ጃሚዓ ላይ ይቆዩና እኔ በድግሪ፣በድፕሎም በሌሎችም ተመረቅን የሚሉ ሰዎችን እያየን ነው፣እውነት የሚታወቅ ጃሚዓዎች፣የሚታወቁ የሱና ኡለሞች ይሄን ማዕረግ ሰተዉህ ከሆነ ማሻአላህ፣ አሁን ላይ ያለው ነገር ግን በዶላር ወይም በብዙ ብሮች የሚገዛ ሁኗል። እከሌ ኡስታዝ ድግሪውን ያዘ ተብሎ ይወራል፣ነገር ግን ይሄን ማዕረግ የያዘው ከአመት የተወሰኑ ቀናቶችን ሄዶ ለተወሰኑ ሰአቶች ትምህርት የሚሰጥበት ቦታ ይቀመጥና መጨረሻ ላይ ይሄን ማዕረግ ይሰጠዋል አላሁ ሙስተዓን። እዉነታው ሲታይ ግን ከትምህርት ዘርፎች አንዱንም በትክክል የሚረዳ ላይሆን ይችላል። ይሄን ማዕረግ ከተላበሰ ቡሃላ የተለያዩ ነገሮች ሊታዩበት ይችላሉ ከእነዛ መካከል 1) መማር አይፈልግም፣ ምክንያቱም የእውቀት መጨረሻ ደረሻለሁ ብሎ ስለሚያስብ። 2) እኔ ማዕረግ አለኝ ህዝቡ እኔን ይከተለኝ የማለት። 👌በኦንላይን ተምረው የተለያዩ ማዕረግ የያዙ አካሎች አሁን ላይ በዝተዋል፣ ራሳቸውንም ሙፍቲ፣የሃድስ ሙዓሊል፣ሀድስን ተስሂህ እና ተድዒፍ ማድረግ እንችላለን የሚሉ   ያሱብሃን አላህ። ወንድሜ እንደዚህ አይደለም ጉዳዩ መጀመሪያ በደንብ አድርገህ ተማር ትልልቅ አሊሞች ጋር ማዕረጉም ቢቀርብህ አትጎዳም። እስኪ ጥያቄ ልጠይቅህ በኦንላይን ኪታብ እያየህ የሰራኸው ፈተና የድግሪ ማዕረግ ቢሰጥህ አይቀፍህም በአላህ እውቀት ሳይኖርህ❓ እውቀት ሳይኖረው ማዕረግን ለተላበሰ አካል እንድህ የሚል አባባል አለ፡ كَشَخْصٍ يَضَعُ سَمَّاعَةَ طَبِيبٍ فِي أُذُنِهِ، وَيَقُولُ: أَنَا أَكْبَرُ الْأَطِبَّاءِ. የዶክተሮችን ማዳመጫ ጆሮው ላይ እንደሚያረግ ነው ከዛ ምን  እንደሚል ነው እኔ ማለት ከዶክተሮች ሁሉ በላጭ ዶክተር ነኝ። ይሄ የዶክተሮችን ማዳመጫ ጆሮው ላይ አድርጎ ከዶክተሮች ሁሉ በላጭ ነኝ እያለ የሚጎረረው እንኳን ዶክተር ሊሆን ተራ የሆነ ሰው ነው። ➻ ስታስቡት  አንድ ተራ ሰው የዶክተሮችን ማዳመጫ ጆሮው ላይ ስላደረገ፣የዶክተሮችን ልብስ ስለለበሰ ዶክተር ነው ማለት ይቻላል❓ አሁንም ላይ ያለው ነገር ከዚህ ጋር የተቀራረበ ነው በምንም በማይለይ መልኩ አላሁ ሙስተዓን። 👌 አንዳንዶችማ ከተለያዬ ምንነታቸውም ከማይታወቅ የኦላይን ትምህርቶች ተምረው ማዕረግን የያዙ አሉ፣ከዚህ ቦታ ድግሬዬን ያዝኩ ብለው ለማዉራት ከሚሸማቀቁበት ያ አላህ። በዱንያ ላይ ይሄ ማዕረግ የተለያዬ የዱንያ ጥቅም፣ስምህ እንድታወቅ ሊያደርግህ ይችላል ግን አላህ ዘንድ ትጎዳለህ። ምክንያቱም ራስህን በማይታወቁ ማዕረጎች ክበህ ድን ልታበላሽ ትችላለህና።

💫 بشائر انتصار السعودية على الرافضة والمكر الإسرائيلي الغربي 💫 ▶️ يوتيوب - مرئيا - : [https://youtu.be/qrsyFvbdg1w] 🔗 الموقع - صوتيا - : [https://www.islamancient.com/?p=41785] 🎙د. عبدالعزيز بن ريس الريس.

Repost from N/a
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ هل صوت المرأة عورة؟ للشيخ محمد آدم الإتيوبي حفظه الله https://t.me/nuruya76

🔖እርግጠኛ ሆኜ ለኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር የምመሰክርለት አንድ ነገር ቢኖር፣ የትኛውንም ርዕስ ወይም ጉዳይ ካነሳ፣ በዚያ ጉዳይ በቂ የሆነ እውቀትና ጥልቅ ግንዛቤ አለው። የሆነ ኪታብ አስተምራለሁ ካለ
🔖እርግጠኛ ሆኜ ለኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር የምመሰክርለት አንድ ነገር ቢኖር፣ የትኛውንም ርዕስ ወይም ጉዳይ ካነሳ፣ በዚያ ጉዳይ በቂ የሆነ እውቀትና ጥልቅ ግንዛቤ አለው። የሆነ ኪታብ አስተምራለሁ ካለህ፣ እመነኝ! ያንን ኪታብ አጥንቶ፣ አብስሎና አድቅቆ በልቶታል። ስለዚህ ወንድሜ፣ እሺ ብለህ ከእሱ ዝቅ ብለህ ተማር እያልኩህ ነው! ከእውቀት ሰዎች መማር እንጂ ከእነሱ ጋር በእኩልነት ለመከራከር መቸኮል አይገባም። እውቀት ትሕትናን ይፈልጋል። ~ https://t.me/Asselefya2

" እውነተኛ እስረኛ ማለት ልቡ ከአላህ የታሰረበት ሰው ነው፤ እውነተኛ ተሸናፊም በስሜቱ የተሸነፈ ሰው ነው።" . " ኢብኑ ተይሚያህ "