Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና
前往频道在 Telegram
- እውነተኛ የህይወት ታሪኮች - ኢስላማዊ የስነልቦና ምክሮች ፣ ጥያቄዎች እና አገልግሎቶችን ያገኛሉ። - ስለ ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ ይማራሉ። - ሳምንታዊ ሽልማቶች ለሁሉም በማጋራት የሙስሊሙ ኡማ የአይምሮ ጤና የሚጠበቅበትን ይህን ቻናል እናሳድግ ጥያቄ ለማቅረብ እና አገልግሎት ለማግኘት @usmanoman ላይ ያናግሩን።
显示更多未指定国家未指定类别
802
订阅者
+3124 小时
+1807 天
+39230 天
帖子存档
አሰላሙአለይኩም ኢስላማዊ የስነልቦና ድጋፍ እና የምክክር አገልግሎት እንዲሁም ፅሁፎችን ለብዙዎች ተደራሸ የማድረግ ስራ ከጀመርን ከራረምን
የላወቁ እንዲያውቁ ወደ እዚህ ግሩፕ አድ በማድረግ ተጠቃሚዎችን ያብዙ። እናመሠግናለን
ወደ እዚህ ሊንክ በመግባት አድ ያድርጉ።
https://t.me/+XYW03GmihQM3Yzhk
+2
የእህታችን ልብ የሚነካ ታሪክ! እንደዚህ አጋርታናለች።ካነበባችሁ በኋላ ሃሳባችሁን ከታች የምናያይዘው poll/መምርጫው ላይ አስፍሩ።
ፈጅር ተነስተን 'ከምድር ከራሷ እና በውስጧ ካለው በላይ የሚልቀውን'' ቀብሊያ/የቅድሚያ ሱና መሰገድ የላቀ የሆነው የአዱኒያ እና የአኼራ የመልካም ስራ በር ለማስከፈት ታላቅ እድል ይሰጣል።
መልካም ፈጅር
ጥያቄ ሁለት
አሰላሙአለይኩም እኔ የ 27 አመት ወጣት ወንድ ነኝ።በአንድ አሳሳቢ ነገር ተለክፍያለው።
እሱም ፖርን (የወሲብ ፊልም) የማየት ሱስ ነው። መች እንደ ጀመርኩ በቅጡ ባላስታውሰውም ትምህርት ቤት ውስጥ ጓደኞቼ ሞባይል ስልካቸው ላይ ሲመለከቱ ማየት ግን የተለመደ ነገር ነበር።
ጠንካራ ኢስላማዊ መሠረት ያለው አሰተዳደግ ውስጥ ስላለፍኩኝ በጊዜው በጣም የምፀየፈው ነገር የነበረ ብቻ ሳይሆን እኩዮቼንም መመልከት እንዲያቆሙ እመክራቸው ነበር።
አሁን ብቻዬን ነው የምኖረው። በሚያሳዝን ሁኔታ ከብዙ አመታት በኋላ እኔም እዚህ ውስጥ ተዘፍቄ መገኘቴ በጣም የሚያስገርመኝ እና የሚያሳስበኝ ጉዳይ ነው።
ይህን ተከትሎም ሶላት ላይ መሳነፍ የስራ ተነሳሽነት ማጣት ህይወትን መጥላት እና ተስፋ መቁረጥ ይሰማኛል።
ካደረግኩት በኋላ ብዙ ሀፍረት እና ፀፀት ውስጥ እወድቃለሁ።ዳግም ላልመለስ አልቅሼ ተውበት ባደርግም ዳግም ራሴን እዛው ላይ አገኘዋለሁ።
ወደዚህ እይታ የሚመራኝ ተፈጥሯዊ ወሲባዊ ስሜቴ ሲሆን። ያማከርኳቸው ሰዎች እንዳገባ ይመክሩኛል ግን ይህን የማድረግ የሞራል እና የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ አልደረስኩም።
ከዚህ ለከት ከሌለው ስሜቴ እና ሱሴ እንዴት ልላቀቅ እባክህ ምክርህን ብትለግሰኝ።
[ጥያቄው በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተዋቀረ (case study) ነው።]
(የጥያቄውን ምላሽ ቻናላችን ላይ ይጠብቁ ኢንሻአላህ!)
#ኡስማኒክ_ኢስላማዊ_ስነልቦና
ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን።
ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ/ኢልመ- ነፍስ
ክፍል 1
-ፊጥራ
-ነፍስ
-ሩህ/spirit
-አቅል/አይምሮ
-ቀልብ/ልብ
-ተዝኪየቱ ነፍስ/ራስን ከወንጀል ማፅዳት
ለዛሬ ፊጥራን በአጭሩ እናያለን ኢንሸአላህ!
ፊጥራ ምንድነው?
ፊጥራ-: ተፈጥሮ ማለት ሲሆን የአንድ ነገር የመጀመሪያ ያልተነካካ ምንነት ነው። ሁሉም የሰው ልጅ አላህ ውስጡ ባስቀመጠው አካላዊ መንፈሳዊ እና ባህሪያዊ የማንነት አይነት እና ቅርፅ ውስጥ ሆኖ ይወለዳል። ይህም ፊጥራ ይባላል።
በኢስላሚክ ሳይኮሎጂ ውስጥ የፊጥራ ጥናት
የሰው ልጅ ዝንባሌ ተሰጥኦ እና ራእይን አላህ ሲሰራው ከሰጠው ተፈጥሮአዊ አቅም ላይ ተመርኩዞ እንዲወጣ አለም ላይም አስተዋጽኦዎን አሳርፎ መሄድ የሚችል ምርታማ እና ደስተኛ ሰው ለማፍራት የተለያዩ ስነ ዘዴዎችን የሚጠቀም ሰው አገዝ አንድ የኢስላሚክ ስነልቦና ዘርፍ ነው።
(✍️
ከኢስላሚክ ሳይኮሎጂ መፅሀፍ የተወሰደ
አዘጋጅ እና ፀሀፊ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂስት ኡስማን ሙስጠፋ)
ኢንሻአላህ ይቀጥላል ....ፈጅር ተነስታችሁ በመስገድ የአይምሮ ጤናችሁን ጠብቁ።
አብዛኛው የጭንቀት የድባቴ እና የአይምሮ መታወክ መንስኤ ከፈጣሪያችን ጋር ያለን ግንኙነት በመበላሸቱ ነው።
እሱ ሀኪም ነው ያክመናል። እሱ የተበቃቃ ነው ይሰጠናል። እሱ አዛኝ ነው ያነሳናል።
አይዞን!!
በኢስላም አስተምህሮ መሠረት ጭንቀትን ለመቀነስ የሚረዳው የኢባዳ/አምልኮአዊ ተግባር የቱ ነው?
ኢስላማዊ የስነልቦና አገልግሎት ለምትፈልጉ በሙሉ
የትዳር የቤተሰብ እና የስራ ጉዳይ ድብርት ወይም ጭንቀት ውስጥ ካላችሁ ወይም ለሌላ ማንኛውም ጉዳይ @usmanoman ላይ አዋሩኝ (ሁሉም በሚስጥር የሚጠበቅ ነው)
ወይም 0912027023/ 0921390122 ደውሉ
ከታች የተያያዘውን ሊንክ በመንካት ፎርም መሙላት አይርሱ ሲጨርሱ ከላይ በሰፈሩት አድራሻዎች ያሳውቁን። 👇👇👇
____
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdl5ehGATYpwQpFCLs66NcS26Laedz36GRjQze0Gxyw1SzzBA/viewform?usp=header 🔗📝
__
መልስ .1
መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአለም አቀፍ ደረጃ የሴቶች የጋብቻ እድሜ ድሮ ከነበረበት በብዙ እጥፍ ከፍ ብሏል።
ቀጥለን በምንጠቃቅሳቸው ምክንያቶች አለም ላይ ብዙ ሴቶች ዘግይቶ በማግባት ፣ ፍፁም ባለማግባት ወይም ባልተሳካ ትዳር ቀውስ ምክንያት ጥልቅ ጭንቀት ውስጥ እያለፉ ይገኛሉ።
ከምክንያቶቹም-: የሴቶች በትምህርት ለአመታት የመቆየት ባህል መስፋፋት ፣ የተዛባ የጋብቻ እሳቤ ፣ የወንዶች በጊዜ ማግባት ያለመፈለግ ፣የኑሮ ጫና ፣ የሴቶች ትዳርን የነፃነት ፀር አድርጎ በመቁጠር ሳያገቡ የመቆየት ፍላጎት ፣ የወንዶች በጣም በእድሜ የምታንሳቸውን ሴት የመምረጥ ልምድ፣
የፍቺ መስፋፋት ፣ አለም ላይ የተነዛው የምእራብያውያን ሴራ የወለደው የሴቶች ንቅናቄ ግልፅ እና ስውር ተፅእኖ ፣ በግል የትዳር አጋርን የመምረጥ መብትን ተከትሎ የተፈጠረው ገደብ የሌለው መስፈርት የማብዛት አባዜ ....ወዘተ....ይጠቀሳሉ። (የብዙ ሴቶች አለማግባት ከቂያማ/የምፅአት ቀን መቃረብ ምልክቶችም ጭምር መሆኑን ሊቃውንቱ ይገልፃሉ)
ይህ ጉዳይ (የሴቶች ቶሎ አለማግባት) የሩቅ ሀገር ተረት ሳይሆን የሁላችንንም በር ያንኳኳ ማህበረሰቡ አፍኖት እየኖረ ያለው ጭንቀት እና የራስ ምታት ነው።
የእህቶች በጊዜ አለማግባት ወይም በፍቺ ምክንያት በላጤነት የመኖር ወረርሽኝ መስፋፋት ማህበረሰባችን ቤተሰብ መመስረት ላይ እየደረሰበት ያለውን ሁለንተናዊ ቀውስ ግልጽ ማሳያ ነው።
እህቴም አገባቸዋለው ብላ ያሰበቻቸው ወንዶች የውሀ ሽታ እየሆኑ መጥፋት እና እስካሁን አለማግባቷ የራስ ምታት እንደሆነባት በአፅንኦት ትገልፃለች።
እህታችን ሆይ! በጊዜ ለማግባት ከነበረሽ እቅድ አንፃር 31 አመት ድረስ መቆየትሽ ጭንቀት ሊፈጥርብሽ እንደሚችል የሚጠበቅ ቢሆንም ብዙ ሴቶች ከዚህም ከፍ ባለ እድሜ አግብተው ደስተኛ ህይወት መመስረት እና አይናቸውንም ባይናቸው ማየት ችለዋል።
ግን ሁሌም ህይወት መልከ ብዙ እና ፈታኝ እንደመሆኗ መጠን ለምንፈልገው ብቻ ሳይሆን አላህ እኛ ላይ ስለወሰነው ነገርም ጭምር ዝግጁ መሆን መቻል አለብን።
ትዳርን እንደ ማንኛውም እርዚቅ ወይም ሲሳይ የአላህን ፍቃድ የሚጠይቅ እና በእኛ እጅ የሌለ ነገር ግን ለማግኘት ሁሉን ሰበብ የምናደርስለት ጉዳይ መሆኑን አስታውሰሽ በመልካም ትእግስት እና በዱአ ውስጥ የጌታሽን ውሳኔ ያለ ቀቢፀ ተስፋ የመምረጥ ሚዛንሽን ሳታዛንፊ ግን ደግሞ በጣም ሳትለጥጪ አላህ የሚልክልሽን ሰው በትእግስት መጠበቅሽን ቀጥይ።
በመታገስሽ የምታገኚው ገደብ የሌለው ምንዳ እና የአላህን ውዴታ እያስታወስሽ ሀብቱ ብዙ ከሆነው ጌታ ደጅ ሳትሰልቺ የልብሽን ሰው ጠይቂ ከዛ ውሳኔውን ለአላህ አሳልፈሽ ስጪው።
ይህ ካልሆነም የአማኝ ሀገሩ አዱኒያ ብቻ አይደለም እና በዚህ ከንቱ አለም ያጣሽውን ደስታ በቀጣዩ አለም በእጥፍ አባዝቶ እንደሚለግስሽ አምነሽ የጌታሽን ውሳኔ በደስታ መቀበል የሚያስችል ኢማን አዳብሪ።
አላህ መልካም ትዳርን ለእህቶቻችን በሙሉ ይስጣቸው!!
[ጥያቄው በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተዋቀረ (case study) ነው።]
✍️ ኡስማን ሙስጠፋ ከኡስማኒክ ሳይኮሎጂ።
ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን።ምስጢራዊነቱ የተጠበቀ ነው
ጥያቄ .1
አሰላሙአለይኩም እኔ (ስሜ ለጊዜው ይቆይ) ሙስሊም የ 31 አመት ሴት ስሆን እስካሁን የትዳርን ወግ አላየሁም።በ 24 አመቴ የማግባት እቅድ ስለነበረኝ ያለ ትዳር የማሳልፋት እያንዳንዷ ቀን ለኔ ከባድ ጫና አላት።
አለማግባቴ ቁሞ ቀር የመሆንን ስሜት እያሳደረብኝ ነው።
አንዳንዴም የተረገምኩና ምንም ጥቅም የሌለኝ ሰው የሆንኩ እየመሰለኝ መኖር ያስጠላኛል።
ያገቡኛል ብዬ ሰፍ ብዬ የጠበኳቸው ወንዶች ሳላስበው ድንገት የውሀ ሽታ ሆነው ይሰወራሉ።
ድሮ ወንድን ለትዳር የምመርጥበት ትላልቅ መስፈርቶች የነበሩኝ ቢሆንም አሁን ሁሉም ተሸርሽረው በጣም ጥቂቶቹ ቀርተዋል።
በዚህ ከቀጠልኩኝ 'ወንድ ይሁን ብቻ እንጂ አገባለው' ወደሚል ቀቢፀ ተስፋ (ተስፋ መቁረጥ) ውስጥ እንዳልገባ እፈራለሁ እባክህ ሀሳብህን አካፍለኝ።
(የጥያቄውን ምላሽ በ 24 ሰአት ውስጥ ቻናላችን ላይ ይጠብቁ ኢንሻአላህ!)
#ኡስማኒክ_ኢስላማዊ_ስነልቦና
ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን።
የሰው ልጅን በአካል እና አይምሮ ብቻ።
የአይምሮ ህመሞች እና የማንነት ቀውሶች እጅግ የበዙበት መዛግብትን አገላብጠን የማንጨርሰው (disorders )የህሊና መዛባት አይነቶች የበረከቱበት አሳዛኝ የኑሮ ተጨባጭ ላይ ደርሰናል።
ወደ ሩቃ/መንፈሳዊ ሀኪም ቤት ሳይካትሪስት እና ሳይኮሎጂስቶችን ደጅ መጥናት መደበኛ የእለት ተእለት ኑሯችን እስኪከሆን ድረስ መላቅጡ የጠፋውን የህይወታችንን ሰንኮፍ ታቅፈነው እየኖር ነው።
የህክምናው ሳይንስ እና የአይምሮው ጥናት እውቀት የሰው ልጅን አካል እና አይምሮ (mind and body) ብቻ ብሎ ለሁለት ከፍሎ የሩህን እና የልቦናን የህይወት መሠረታዊያንን (essence) ነቅሎ ጥሎ የሚታየውን ብቻ ለማከም ይታገላል።
የብዙ ሰዎች ችግር ከረቂቁ ማንነታቸው የመነጨ የነፍስ እና የቀልብ መታመም ተፈጥሯችን ከምትራበው እና የአለም ስርአት ቆርጦ ካስወገደው መለኮታዊ ምግብ የሆነው የመልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮ እና የጌታዋ ቃል ቁርአን ረሀብ የወለደው መታወክ ነው።
ስለዚህ ሁሉም ዲሲፕሊኖች ውስጥ ይህን ሰማያዊ መድሀኒት በመጨመር ብዙዎችን መታደግ ይቻላል። ኢንሻአላህ!!
🖊️ usman mus
#ስለ_ሰው_ልቡና
