ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

前往频道在 Telegram

ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

显示更多
未指定国家未指定类别
319
订阅者
+124 小时
-47 天
+5530 天
帖子存档
መውሊድ እና ተየያዥ ነጥቦች.mp312.04 MB

ሸይኽ_አወል_አልከሚሴ_ሺርክ_እና_መውሊድ.m4a46.51 MB

መውሊድ_እንደ_ማይፈቀድ_የሚያሳዩ_መረጃዎች.mp35.24 MB

መውሊድ የሙስሊሞች በአል አይደለም.mp34.06 MB

መውሊድ ውስጥ የሚፈፀሙ ስህተቶች.mp33.74 MB

ሸይኽ ሆይ! ኡስታዝ ሆይ! አላህ በቁርአንና በሐዲሥ ዒልም ካከበረህ በኋላ ለፖለቲከኛ ጆሮህን ሰጥተህ፣ አፍህን ከፍተህ አትከታተል። ደጋሚ ናቸው፣ ቀልብህን ያበላሹታል። ምንም ያላደረጉህን ምስኪኖች በዘራቸው ልዩነት እንድትጠላ ያደርጉሃል። የራሱን የዘረኝነት ቆሻ ^ሻ አሸክሞ መስጂድና መጅሊስ ይዘህ እንድትገባ በማድረግ ያረክስሃል። እሱ የቅንጦት ህይወት እየኖረ አንተን ግን አኺራህን ብቻ ሳይሆን ዱንያህንም ያሳጣሀል። በተለይ የሃገራችን ፖለቲከኛ የደም ነጋዴ እንደሆነ በተደጋጋሚ አይተነዋል። በቅንጦት ቤቱ ያለው ቀርቶ ጫካ ውስጥ ያለው ሳይቀር አላማው አዱኛ እንደሆነ እያየን ነው። በቅርቡ የአንድ "ታጋይ" ቪዲዮ እያየሁ ነበር። እጁ ላይ ያሰረው ውድ ሰዓት ነው። በመቶ ሺዎች የሚገመት ዋጋ ያለው ሞባይል ይዟል። የሁለቱም እጆቹ ጣቶች በወርቅ ተንቆጥቁጠዋል። ይሄ ያየነው ነው። ያልታየውስ? በዚህ ዘመን "ትግል" ቢዝነስ ሆኗል። እየዘረፈ፣ እያገተ በተለያዩ ከተማዎች ውስጥ ቤቶችን፣ መሬቶችን፣ ፎቆችን የገዙት ቀላል አይደሉም። እንደዚህ ጨው የቀመሱ አካላት በቀላል ያርፋሉ ተብሎ አይጠበቅም። በሕዝብ ስም የሚምለው ሁላ የገዛ ወገኑን አላላውስ አላንቀሳቅስ ብሎ ደም እንባ ሲያስለቅስ እያየን ነው። ሸይኽ ሆይ! ኡስታዝ ሆይ! "ሰዎች ይሰሙ ይሆን?" ብለህ ሳትጨነቅ የዘረኝነትን አደጋ አስተምር። ወጣቱ የምላሰ ጮሌ ፖለቲከኞች ባሪያ ከመሆን ወጥቶ ለራሱም፣ ለቤተሰቡም በሚጠቅም መስመር ላይ እንዲሰለፍ ደጋግመህ ተጣራ። በዘር ጥላቻ ተሞልቶ ሌሎችን ማጥቃት ከአኺራ በፊት ዱንያን ሲያበላሽ እያየን ነው። በዚህ ዘመን የግፍ ክፍያ እጅ በጅ ሆኗል። ደካሞችን የፈጁ ሁሉ ዘግናኝ አወዳደቅ ወድቀዋል። በጅምላ የፈጁ በጅምላ ረግፈዋል። በጥላቻ ያፈናቀሉ፣ በቀያቸው መረጋጋት አቅቷቸዋል። ከቅጣት ብትር የተረፉትም አዙሪቱ አይለቃቸውም። ከአኺራ በፊት ብድር በምድር ሲሆን እያየን ነው። ነገ ደግሞ የከፋ ነው። ዱዓቶች ሆይ! ለማስተማር፣ ለወገን ለመድረስ ጀግኖችና ቆራጦች ሁኑ። በፈሳድ መብዛት ተስፋ አትቁረጡ። የተጠራቀሙ ድምፆች ብዙ ርቀት ያስተጋባሉ። አላህ ያለላቸውን ልቦች ያነቃሉ። በቅድሚያ ግን ራስን መለወጥ ያስፈልጋል። እኛ ሳንለወጥ ለሌሎች መድረሱ ሩቅ ነው። የሌለው አይሰጥም። ምስሉ ላይ ያለው ፅሁፍ፦ | "የኔ ውድ የሶባሕ እናት! የቤቱን ቁልፍ እዚያ ላይ አስቀምጬልሻለሁ። በኸይር እንገናኝ" ይላታል፣ ሊገድላት እያጠመደ። የመልእክቱ ባለቤት ከፊርማው አጠገብ "የሶባሕ አባት ነኝ" ይላል። ወዳጅ መሳይ ጊ Nጥ! የአብዛኛው ፖለቲከኛ ምክር እንደዚህ ነው። በገዛ ወገኑ ላይ ቂም ያረገዘ እስከሚመስል መሞቻውን ነው የሚያዘጋጅለት። ደጋግሞ ሞቱን ጉዳቱን እያየ እንኳን አይደነግጥም። አላህ ይገላግለንና። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ከፊሉ ልጅ የለኝም ብሎ ያለቅሳል። ሌላውን ልጁ ያስለቅሰዋል። ከፊሉ እህት ወንድም የለኝም ብሎ ይከፋዋል። ሌላው በእህት በወንድሞቹ ውስጡ ቆስሏል። ዱንያ አጃዒቧ አያልቅም። ግማሹ በመከራ፣ ሌላው በጥ
ከፊሉ ልጅ የለኝም ብሎ ያለቅሳል። ሌላውን ልጁ ያስለቅሰዋል። ከፊሉ እህት ወንድም የለኝም ብሎ ይከፋዋል። ሌላው በእህት በወንድሞቹ ውስጡ ቆስሏል። ዱንያ አጃዒቧ አያልቅም። ግማሹ በመከራ፣ ሌላው በጥጋብ ያለቅሳል። "እናቱ የሞተችበትና፣ ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል" በሚለው አገርኛ ብሂል ውስጥ ህመም አለ። መከራ ሁሉ አንድ አይደለም። ከባሰም በላይ ብዙ የባሰ እንዳለ በማስተዋል "አልሐምዱ ሊላህ" እንበል። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

በዚህ ዘመን በየ አቅጣጫው ተከፋፍሎ  የሚላተመው አካል ትልቁ ችግሩ የተቅዋ መቅለል ያመጣው የኢንሷፍ ችግር ነው።እራሱ ጋር ያለ ችግር ይደብቃል ሌላውን ያጠቃል ! 🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሓፊዘሁላህ        ~ t.me/Darutewhide

👂👂👂👂👂👂👂 👂👂👂👂👂👂👂

ሙስሊም ወንድሞቼ ፣ ጊዜው ሳያልፍ እንንቃ! ያ አላህ! ጉዳዩ እየከበደና እያሳሰበ መጥቷል። ሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ለተለያዩ ፊርቆችና አስተሳሰቦች እየተጋለጠች ነው። አንዳንድ ቡድኖችና እንቅስቃሴዎችም በሕዝቡ መካከል እየተስፋፉ ሲሆን፣ በተለይም ወጣቶችንና ሕፃናትን ማነጣጠራቸው እየጨመረ ነው። በቅርብ ጊዜም ከአህሉስ-ሱና ወልጀማዓ አስተምህሮ ፍፁም የሚለያዩ ቡድኖች፣ ከእነሱም መካከል ሺዓ፣ አሕመዲያ እና ሌሎችም በአንዳንድ አካባቢዎች እየተስፋፉ እንደሚገኙ እናስተውላለን። በተለይም በባቲና በአካባቢዋ የተለያዩ የትምህርትና የዳዕዋ እንቅስቃሴዎች እየተካሄዱ መሆናቸው ትኩረታችንን ይሻል። በተለይ ልንጠነቀቅ የሚገባን ሕፃናትና ወጣቶች ላይ የሚደረገው ትኩረት ነው። አንዳንድ ወገኖች ትምህርት ቤቶችን፣ ማዕከላትንና የትምህርት ተቋማትን በመክፈት ሕፃናትን ገና ከልጅነታቸው ከ kg ጀምሮ ለማስተማር እየሰሩ ነው። እንግዲህ ራሳችንን መጠየቅ ይገባናል፦ ልጆቻችን እና ወጣቶች ምን እየተማሩ ነው? ምን ዓይነት እምነትና አስተሳሰብ እየተቀበሉ ነው? ትምህርታቸውን የሚከታተልና አቅጣጫ የሚሰጣቸው ማን ነው? ወንድሞቼና የተከበራችሁ ወገኖቼ ሆይ! ከሀገራችን ጫፍ እስከ ሌላኛው ጫፍ ድረስ፣ የአህሉስ-ሱና ወልጀማዓ ተከታዮች ሆይ፣ የአካባቢያችን ሰዎች ሆይ፣ በተለይም የባቲ ነዋሪዎች ሆይ! የልጆቻችን የወጣቶችን የራሳችንንእምነት መጠበቅና የአላህን መጽሐፍ እና የነቢዩን ﷺ ሱና ማስተማር ታላቅ ኃላፊነት ነው። ይህንንም በዘፈቀደ ግጭት፣ በስድብ ወይም ሌሎችን በማዋረድ ሳይሆን፣ በዕውቀት፣ በጥበብ፣ በትክክለኛ ትምህርት፣ በግንዛቤ ማስጨበጥ እና ማህበረሰባችንን በቁርአን፣ በሱናና በትክክለኛ የእስልምና እምነት ማጠናከር ነው። ማህበረሰባችንን በቅርብ ልንከታተል፣ ምን እንደሚማሩም ልናውቅ ይገባል። በራሳችን ትምህርት ቤቶችና የእስልምና ማዕከላት ውስጥም ጠንካራና ጠቃሚ ትምህርት እንዲያገኙ ልንጥር ይገባል። ይህም ቁርአንን፣ ትክክለኛ የአቂዳ ትምህርትን፣ ፊቅህን፣ መልካም ሥነ-ምግባርንና የዓረብኛ ቋንቋን ያካተተ መሆን አለበት። ሌሎች ሰዎች ቦታውን እንዲይዙ ከፈቀድን በኋላ፣ ሐሳቦቻቸው ስለተስፋፉ ብቻ ማማረር መፍትሔ አይሆንም። ስለዚህ ኃላፊነታችንን እንወጣ። ማህበረሰባችን ከሌሎች ዘንድ ከመማራቸው በፊት እኛ እናስተምራቸው። የተሳሳቱ አስተሳሰቦችንም በዕውቀት፣ በማስረጃና በጥበብ እንመልስ። ኢንሻአላህ፣ እነዚህ ቡድኖች ምን እንደሆኑ፣ መሠረታዊ ሐሳቦቻቸውና እምነቶቻቸው ምን እንደሆኑም በማስረጃና በታማኝ ምንጮች ላይ በመመስረት አብራራለሁ፤ ዓላማዬም ሙስሊሙ ስለ ዲኑ በቂ ዕውቀት እንዲኖረውና በጉዳዮች ላይ በግልጽ እውቀት እንዲቆም ነው። አላህ ሆይ! ሀገራችንንና ማህበረሰባችንን ጠብቅ። እኛንና እነርሱን በቁርአንና በሱና ላይ አጽና። ዑለማዎቻችንን፣ ዳዒዎቻችንንና መምህራኖቻችንን ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ እርዳቸው። ከቀናው መንገድ የራቁትንም ወደ እውነት ምራቸው። አላህ ሆይ! የሙስሊሞችን ልጆች ጠብቅ፣ እምነታቸውን ጠብቅ፣ ወደ እውነትና መልካም ሥራ የሚጠሩ ዳዒዎች አድርጋቸው። አሚን! = አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

🔖 ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸዉ እንዲህ ይላሉ፦   يَقُول ابْن القَيّم "رحمه الله   " ‏إذا مَنع الله عَنك شَيئاً تُريده و تُحبه ، فتَح لَك بِحكمته ورَحمته أبوَاباً أخرَى هِي أنفَع لَك ! فَلا تَحزن و لا تَيأس وَكًن مُوقِناً لحكمَة الله وَ عَدله وَ رحمَتِه. «አላህ ከምትፈልገው እና ​​ከምትወደው ነገር ቢከለክልህ በጥበቡ እና በእዝነቱ ሌሎች የሚጠቅሙህን በሮች ይከፍትልሃል! ስለዚህ አትዘን ወይም ተስፋ አትቁረጥ የአላህን ጥበብ፣ ፍትሀዊነት እና እዝነት እርግጠኛ ሁን።