መጽሐፉ ይናገር | Official
前往频道在 Telegram
መጽሐፉ ይናገር ክርስቲያናዊ አገልግሎት በወንጌላዊያን አማኞች የነገረ መለኮት ተማሪዎችና የቃሉ አገልጋዮች በ2013 ዓ.ም የተመሠረተ ተቋም ሲሆን አሁናዊ መስኮቹ፦ 🔘 የመጋቢያንና መሪዎች ስልጠና 🔘 የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ (Gateway) 🔘 የቲቪ ፕ/ም በተስፋ TV ቅዳሜ 9-10 🔘 መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኅብረቶች ሊንክ፦ @metsihafuyinager በውስጥ፦ @adfontess ☎️ +251947424046
显示更多353
订阅者
无数据24 小时
+17 天
+1430 天
吸引订阅者
十月 '2610月 '26
十月 '260
在0个频道中
九月 '26
+23
在1个频道中
Get PRO
八月 '26
+25
在1个频道中
Get PRO
七月 '26
+327
在1个频道中
| 日期 | 订阅者增长 | 提及 | 频道 | |
| 01 十月 | 0 |
频道帖子
| 2 | ተወዳጆች Voice Chat ተከፍቷል። ወደ ውይይት ክፍሉ ግቡ። ኑ... ከቃለ እግዚአብሔር እንማማር። ስለ ሰማያዊው ተስፋ እንወያይ! | 51 |
| 3 | ከአንድ ሰዓት በኋላ ማለትም ልክ ከምሽቱ 3:00 እዚሁ እንገናኛለን? አላችሁ? ዝግጁ ናችሁ? የውይይት ሃሳብ ከላይ ተለጥፏል። ወዳጆቻችሁን ጋብዙ! ኑና ስለ ሰማያዊው ተስፋ እንነጋገር።
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 57 |
| 4 | በይደር የተያዙ ጥያቄዎች!
ቆላ 1:3-8 ጸሐፊው ስለ አማኞቹ እግዚአብሔርን የሚያመሰግንበት ክፍል ሲሆን የምስጋናውም ርዕሰ ጉዳይ በወንጌሉ በኩል በአማኞች ሕይወት የታየ ፍሬ መሆኑን ተገንዝበን ፍሬዎቹም "በክርስቶስ ያላቸው ፍቅር" እና "ለቅዱሳን ያላቸው ፍቅር" መሆኑን ተረድተናል።
በክፍሉ "እምነት፣ ተስፋና ፍቅር" አንድ ላይ የቀረቡ ሲሆን ማን ማንን ይቀድማል? ማንስ ማንን ያስከትላል? የሚሉ ሃሳቦችም ተንሸራሽረው ነበር። አማኞቹ ፍሬ እንዲገኝባቸው እንደ ዋና ሰበብ (ultimate cause) ተደርጎ የቀረበው በሰማይ የተዘጋጀላቸው ተስፋ (1:3) እንደሆነ ተመልክተን ይህ ተስፋ የፍሬዎቹ መሠረት (foundation) መሆኑን አስምረንበታል።
ስለዚህ ተስፋ መሠረታዊነት ጥቂት ማብራሪያዎች ቀርበዋል። ኋላም ገለጻውን (the presentation) ከተከታተሉት ቤተሰቦቻችን ሁለት ጥያቃዎች ተሰንዝረዋል። ዛሬ ምሽት ውይይታችንን እነርሱን ጥያቄዎች በመመለስ እንጀምራለን።
1️⃣ ይህ "በሰማይ የተዘጋጀላቸው ተስፋ" ምንድነው? ይዘቱን በግልጽ ማወቅ እንችላለን?
2️⃣ አማኞቹ በምድር ኑሯቸው ፍሬ ያፈሩት በሰማይ ካላቸው ተስፋ የተነሳ ነው ስንል ተስፋውን በጣም አላራቅነውም? ተስፋው ከእኛ ነባራዊ ዓለም ለምን በዚህ መልኩ ርቆ ቆመ? እኛም በዚህ መልኩ ስናስብ ተስፋችንን ሩቅ አያደርግብንም?
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 64 |
| 5 | ከላይ Pin ያደረግነው Post ባለፈው ምሽት ከቆላስይላ 1:3-8 የጀመርነውን ውይይት የምንቀጥልበት ነው። ዛሬ ምሽት ውይይታችንን የምንጀምረው ባለፈው ከተጠየቁ ጥያቄዎች ይሆናል። | 69 |
| 6 | ትዝታዬ! 📖
ሕግህን እጽፈዋለሁ በልቦናዬ፣
እንዲሆን የሞገስ ዘውዴ የአንገት ድርዬ፣
ሁሌ ቃልህ ነውና ለእግሬ መብራት፣
መንገዴን የሚያቀናልኝ በአንተው ስርዓት።
አቤቱ እንዳልበድልህ 😥
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን! 📖
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 81 |
| 7 | ሌላ ማነው?
"የነፍሴ መድኃኒት ሆይ...
የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ...
በመስቀል ላይ ያማጥክልኝ...
ለብቻህን አይደል ወይ...?"
ሌላ ማነው ከአንተ በስተቀር!
በእኔ ሕይወት ምህረቱ 'ሚዘከር!
(አዜብ ኃይሉ)
አንተ ብቻ ካተረፍኸኝ ዘንዳ
እኔም ላንተ ብቻ ልኑር!!!!!!
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 90 |
| 8 | ዛሬ በነበረን ውይይት ጊዜ ትኩረታችን ቆላ 1:3-5 ባሉት እውነታዎች (እምነት፣ ተስፋና ፍቅር) ሲሆን በጥናት ክፍሉ ዐውድ አንዱ ሌላውን የሚያስከትልበትን መንገድ ተመልክተናል።
የቆላስይስ አማኞች በሰማይ የተዘጋጀላቸው ተስፋ በክርስቶስ ላላቸው እምነትና ለቅዱሳን ላላቸው ፍቅር መሠረት እንደሆነ በጥንቃቄ ለማየት ሞክረናል። ከዚህም ተነስተን እምነታችን ተስፋችንን እንደሚያህል ለቅዱሳን የሚኖረን ልብ ሰማይን ከተረዳንበት መጠን እንደማያልፍ ተገንዝበናል። የወንጌሉ ተስፋ በግልጥ ባልተብራራበት የወንጌሉ ፍሬ የለም።
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 140 |
| 9 | በዚህ የቴሌግራም Group ላለፉት 5 አመታት የተጠኑ መጻሕፍት!
2013 ዓ.ም -- የኤፌሶንን መልእክት
2014 ዓ.ም -- የያዕቆብን መልእክት
2015 ዓ.ም -- የዮሐንስ መልእክት (1ኛ)
2016 ዓ.ም -- የዕብራውያን መልእክት
2017 ዓ.ም -- የገላትያ መልእክት
አንዳንዶቹን መጻሕፍት (በተለይም ገላቲያንና 1ኛ ዮሐ) አጠናቅቀን ባናጠናም ግን ላለፉት አምስት አመታት በየአመቱ አንድ መጽሐፍ መቃኘታችን ይታወቃል። | 39 |
| 10 | Voice Chat ተከፍቷል። ወደ ውይይት ክፍሉ ተቀላቀሉ። በቴሌግራም Voice Chat እንግዳ የሆናችሁ ከስክሪናችሁ ግራ በኩል "join" የሚለውን Icon ተጭናችሁ ወደ ክፍሉ መግባት ትችላላችሁ። | 146 |
| 11 | ከ30 ደቂቃዎች በኋላ (3:00) Voice Chat ይከፈታል። በቆላስይስ መልእክት ምዕ 1:6-7 Discussion ይኖረናል። ሰምታችኋል አይደል? | 143 |
| 12 | ዛሬ ምሽት ONLINE እንገናኛለን!
በቆላስይስ መልእክት ጥናታችን ከምዕ 1-3-8 ያለውን ክፍል እየመረመርን እንደሆነ ይታወቃል። ዛሬ ምሽት በሚኖረን ጊዜ ቁ6-7 ባሉት ወንጌሉን በሚመለከት በቀረቡ እውነቶች እንነጋገራለን። በርግጥ ይህን በባለው ጥናታችን አንስተነው የነበረ ቢሆንም መቋጫ የሰጠን ባለመሆኑ ዛሬ እዚሁ ከOnline Community ጭምር አብረን እናጠናለን።
"...ይህም ወደ እናንተ ደርሶአል። ይህንም ወንጌል ከሰማችሁበትና የእግዚአብሔርን ጸጋ በእውነት ከተረዳችሁበት ቀን ጀምሮ በዓለም ዙሪያ እየሠራ እንዳለ ሁሉ በእናንተም ዘንድ ፍሬ እያፈራና እያደገ ነው።" (ቈላ 1:6-7 አ.መ.ት.)
➘ የወንጌሉ ባሕርይ (Nature)
➘ የወንጌሉ ይዘት (Content)
➘ የወንጌሉ ሥራ (The act)
➘ የወንጌሉ አድማስ (Sphere)
ባለፉት የጥናት ጊዜያት አብራችሁን የነበራችሁ ያለፉትን ውይይቶች ዐውድ በማገናዘብ በዛሬውም ውይይት ክፍል በንቃት እንድትሳተፉ እናሳስባለን።
--------
⏰ ከምሽቱ 3:00-4:30
እዚሁ Online እንገናኛለን።
--------
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 145 |
| 13 | እግዚአብሔር አለ!
ክፋት እያየለ፣ አመጽ እየገነነ፣ ኃጥአን ከትላንት ይልቅ ዛሬ እየበረቱ፣ ጻዲቁ በጭንቅ እየማቀቀ ብታዩ "ይህ ለምን ይሆናል?" አትበሉ። ይህ የሚሆነው ነገሮች ወደ ፍጻሜ እንዲቸኩሉና የእግዚአብሔር (የፍርድ) ቀን በቶሎ ይመጣ ዘንድ እንደሆነ መጽሐፉ ነግሮናልና። በግዞት ጨለማ የተጣልንና ፈጽሞ የተተውን ሲመስለን ያን ጊዜ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አለ።
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 131 |
| 14 | "ቁም ነገረኛ ሁን፤ ነገር ግን ኮስታራ አትሁን!"
( ከአጥባቂ ደቀ መዝሙር የተወሰደ፣ ጆን ስቶት)
1️⃣ ዘወትር ኹልጊዜ እግዚአብሔርን አመስግን… በቋሚነት ስለተሰጡህ በረከቶች በትኲረት እና በአድናቆት እግዚአብሔርን አመስግን… ምስጋና፣ ኲራት በቀላሉ የማይበቅልበት ዐፈር ነው።
2️⃣ የኀጢአትህን ኑዛዜ በትኲረት አድርግ። በእግዚአብሔር ፊት ራስኽን መተቸትህን ርግጠኛ ሁን፤ ይህ ራስኽን መመርመርሕ ነው። ራስኽን በመለኮታዊ ትችት ሥር አድርግ፤ ያ የኀጢአትህ ኑዛኔ ነው…
3️⃣ ውርደት ለመቀበል ዝግጁ ሁን። በከፍተኛ ኹኔታ ሊጐዳህ ይችላል፤ ነገር ግን ትሑት እንድትኾን ይረዳሃል። ጥቃቅን ውርደት ሊኖር ይችላል፤ ተቀበለው። ትልቅ ውርደት ሊኾን ይችላል ... እነዚህ ኹሉ ወደ ትሑቱ እና ስቁሉ ጌታ የሚያቀርቡን ዕድሎች ሊኾኑ ይችላሉ።
4️⃣ ስለ ክብር(ቦታ) አትጨነቅ... ጌታችን እንዲያሳስበን የጋበዘን አንድ ኹኔታ ብቻ ነው፤ ርሱም ለራሱ ቅርብ የመኾናችን ኹኔታ ነው ...
5️⃣ ሣቅህን ተጠቀም። በነገሮች ላይ ሣቅ፤ በሕይወት ከንቱነት ላይ ሣቅ፤ በራስኽ ላይ ሣቅ፤ እና በራስኽ ከንቱነት ላይ ሣቅ። በእግዚአብሔር መላ፟ለም ፣ እኛ ኹላችንም ኢምንትና አስቂኝ ፍጥረታት ነን። ቁም ነገረኛ ሁን፤ ነገር ግን ኮስታራ አትሁን፤ ምክንያቱም ስለ ኹሉም ነገር ኮስታራ ከሆንክ ፤ ይህም በራስኽ ላይ እንደዚያው ወደ መኾን ያደርሳሃል።
ወንድማችን አቤኔዘር ጤቻ እንዳቀረበው
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 146 |
| 15 | ደቀ መዝሙር
(ከሀብታሙ ፍሬው)
"ደቀ መዝሙር" ማለት በኢየሱስ የሚያምን፣ ቤተክርቲያን የማይቀር (አቴንድ የሚያደርግ) ወይም የክርስቲያን ስም የያዘ ሰው ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንስ ደቀ መዝሙር ማለት ለኢየሱስ ሕይወቱን የሰጠ፣ የእርሱ (የክርስቶስ) ዓለማ ዓላማው የሆነ፣ እርሱን እየተከተለ የሚኖርና ወደ እርሱ እየተለወጠ የሚሄድ ሰው ነው።
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 137 |
| 16 | የቁልቁለቱ ጉዞ!
"የክርስቲያን መሪ የጉዞ አቅጣጫ ይህች ዓለም እንደምትራኮትበት ሽቅብ ወደ ላይ ሳይሆን፣ መዳረሻው ወደ መስቀሉ የኾነ የቍልቍለት ጉዞ ነው። ይህ ጨለምተኛና ተስፋ አስቈራጭ ሊመስል ይችላል፤ የእግዚአብሔርን የመጀመሪያ ፍቅር ሰምተው ምላሽ ለሰጡ ኹሉ ግን የኢየሱስ የቍልቍለት ጉዞ፣ ከዚህ ዓለም ወዳልሆነው ወደ እግዚአብሔር ደስታና ሰላም የሚያደርስ መንገድ ነው።"
ፋኑኤል ብርሃነ (ከ"ሄንሪ ኖዌን" ሥራ ንባቡ)
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 174 |
| 17 | ዛሬ በአያት አካባቢ ኅብረት ጥቂት ሆነን በተስፉ ሆቴል ካፍቴሪያ ጥሩ ጊዜ አሳልፈናል። ያለፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቆይታችንን መገምገም፣ ስለወደፊቱ የኅብረታችን እጣ ፈንታ መወያየትና አንዳችን የሌላችንን ሸክም ለመካፈል እድል ያገኘንበት ጥሩ አጋጣሚ ነበር።
በዚህ ቤተሰብ ውስጥ እግዚአብሔር ስለሰጠን ሕያው እምነት ስሙን እናከብራለን። በእርሱ (በክርስቶስ) ማመናችን ከትላንት ይልቅ እንዲበዛና ለወንድሞችም ያለን ፍቅር እያደር እንዲጨምር ቃሉን መሠረት ባደረጉ እውነቶች እግዚአብሔር እያነጸን ነውና በዚህ እድለኞች ነን።
በአያት፣ ሰሚት፣ ፊጋ፣ ፍየል ቤት፣ Cmc፣ አራብሳ፣ ጣፎ፣ አርባ ዘጠኝ፣ ሰባ ሁለትና አካባቢው ላይ ያላችሁ ኑና በዚህ አካባቢ የተጀመረውን ሥራ አብረን እንሥራ። የክርስትናችንን መሠረት መፈተሹንና ጤናማውን አስተምህሮ አጥብቆ በመያዙና በያላችሁበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ውስጥ ሆናችሁ አብራችሁን ትተጋላችሁ። | 206 |
| 18 | ዛሬ በአያት ሴንተር!
ቆላስይስ 1:3-8 ሲጠና መቆየቱ ይታወሳል። ዛሬ በሚኖረን ጊዜ "ለቅዱሳን ያላችሁ ፍቅር" በሚለው የወንጌሉ ፍሬ (አስከትሎት) የመስክ ሥራ ይኖረናል። ይኸውም የጋራ የኅብረት ጊዜ (Coffee fellowship time) 🤎 ነው። ስለዚህም 11:30 ላይ አያት አደባባይ ያኔት ሆስፒታል ፊት ለፊት እንድንገናኝ ተወስኗል።
------------
⏰11:30-1:30
☎️ 0947424046
------------
Join & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
በውስጥ፦ @adfontess | 189 |
| 19 | ፍቅር እንዲህ ነው!
"አሳ ትወዳለህ?" ሲባል አብዛኛው ሰው "አዎ! በጣም ነው የምወደው" ይላል ነገር ግን አሳውን ሳይሆን ሰውየው ራሱን ነው የሚወደው! "ለምን?" ካላችሁ አሳውንማ ብትወዱት ከምቹ መኖሪያው፣ ነፍሱ ከምትቀጥልበት ስፍራና ከሚወዳቸው ወዳጆቹ አትለዩትም (አትነጥሉትም) ነበር።
ብትወዱትማ አታልላችሁ ባላጠመዳችሁትና ጠብሳችሁ ባልበላችሁት...እና አሁንም አሳውን ነው የምወደው ትላላችሁ? ወድጃለሁ የሚል ሰው ነፍስ ሲቀማ ለወደደው ሰው ነፍሱን የሰጠ ክርስቶስ ነው። ለዚህ ነው መጽሐፉም "ፍቅር እንደዚህ ነው" የሚለን።🥰
ጽዮናዊት መልካሙ
(ከVladimir Savchuk ንባቧ)
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 182 |
| 20 | እኛ የምንሠራው ቤተ ክርስቲያን በሕልውናዋ እንድትቀጥል አይደለም። እርሷ የሰው ማኅበር አይደለችምና ህልውናዋን የሚያጠፋ ኃይል በምድር የለምና። ነገር ግን ለማንነቷና ለተልዕኮዋ የማትታመን ሆና በሕልውናዋ መቀጠል ትችላለች።
ይህ ከባድ ፈተና ነው። የህልውናዋ አደጋም ጭምር ነው። የቤተ ክርስቲያን ትክክለኛ መልኳ የማይበገር መዋቅር ያላትና በሕዝብ ብዛቷ ምድርን የሞላች መሆኗ ላይ አይደለም። መኖሯ (ተፅዕኖዋም) የሚለካው ለተልዕኮዋ በምታሳየው ታማኝነት ነው።
አልበርት ሞህለርም እንዳሉት ሁሉ “የዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን ሐሰተኞች አስተማሪዎችን በዝምታ የምታልፍ ከሆነ፣ እንዲሁም ትምህርቶቻቸውን ሳታርምና ሳትጋፈጥ ከተወቻቸው ታማኝ ሆና መኖሯን መቀጠል አትችልም” ስለዚህ የእኛ አገልግሎት ከፍሬያማነት ታማኝነትን ያስቀድማል።
እናንተስ በግላችሁ ለክርስቲያናዊ ተልዕኳችሁ ታማኞች ናችሁ? የየእለት ምልልሳችሁ ያንን መሲሕ የሚወክል (portray የሚያደርግ) ነው? ለእርሱ (ለማንነቱ) እና ለሥራው መታመናችሁ (ሕይወታችሁ ከዚያ አንጻር የተቃኘ መሆኑ) ብቻ ክርስቲያን መሆናችሁን ይጠቁመናል።
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 250 |
