መጽሐፉ ይናገር | Official
الذهاب إلى القناة على Telegram
መጽሐፉ ይናገር ክርስቲያናዊ አገልግሎት በወንጌላዊያን አማኞች የነገረ መለኮት ተማሪዎችና የቃሉ አገልጋዮች በ2013 ዓ.ም የተመሠረተ ተቋም ሲሆን አሁናዊ መስኮቹ፦ 🔘 የመጋቢያንና መሪዎች ስልጠና 🔘 የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ (Gateway) 🔘 የቲቪ ፕ/ም በተስፋ TV ቅዳሜ 9-10 🔘 መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኅብረቶች ሊንክ፦ @metsihafuyinager በውስጥ፦ @adfontess ☎️ +251947424046
إظهار المزيد353
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+17 أيام
+1430 أيام
جاري تحميل البيانات...
القنوات المماثلة
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
سحابة العلامات
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
الإشارات الواردة والصادرة
---
---
---
---
---
---
جذب المشتركين
أكتوبر '26أكتوبر '26
أكتوبر '260
في 0 قنوات
سبتمبر '26
+23
في 1 قنوات
Get PRO
أغسطس '26
+25
في 1 قنوات
Get PRO
يوليو '26
+327
في 1 قنوات
| التاريخ | نمو المشتركين | الإشارات | القنوات | |
| 01 أكتوبر | 0 |
منشورات القناة
ትዝታዬ! 📖
ሕግህን እጽፈዋለሁ በልቦናዬ፣
እንዲሆን የሞገስ ዘውዴ የአንገት ድርዬ፣
ሁሌ ቃልህ ነውና ለእግሬ መብራት፣
መንገዴን የሚያቀናልኝ በአንተው ስርዓት።
አቤቱ እንዳልበድልህ 😥
ትዝታዬ ቃልህ ይሁን! 📖
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess
| 2 | ሌላ ማነው?
"የነፍሴ መድኃኒት ሆይ...
የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ...
በመስቀል ላይ ያማጥክልኝ...
ለብቻህን አይደል ወይ...?"
ሌላ ማነው ከአንተ በስተቀር!
በእኔ ሕይወት ምህረቱ 'ሚዘከር!
(አዜብ ኃይሉ)
አንተ ብቻ ካተረፍኸኝ ዘንዳ
እኔም ላንተ ብቻ ልኑር!!!!!!
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 58 |
| 3 | ዛሬ በነበረን ውይይት ጊዜ ትኩረታችን ቆላ 1:3-5 ባሉት እውነታዎች (እምነት፣ ተስፋና ፍቅር) ሲሆን በጥናት ክፍሉ ዐውድ አንዱ ሌላውን የሚያስከትልበትን መንገድ ተመልክተናል።
የቆላስይስ አማኞች በሰማይ የተዘጋጀላቸው ተስፋ በክርስቶስ ላላቸው እምነትና ለቅዱሳን ላላቸው ፍቅር መሠረት እንደሆነ በጥንቃቄ ለማየት ሞክረናል። ከዚህም ተነስተን እምነታችን ተስፋችንን እንደሚያህል ለቅዱሳን የሚኖረን ልብ ሰማይን ከተረዳንበት መጠን እንደማያልፍ ተገንዝበናል። የወንጌሉ ተስፋ በግልጥ ባልተብራራበት የወንጌሉ ፍሬ የለም።
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 117 |
| 4 | በዚህ የቴሌግራም Group ላለፉት 5 አመታት የተጠኑ መጻሕፍት!
2013 ዓ.ም -- የኤፌሶንን መልእክት
2014 ዓ.ም -- የያዕቆብን መልእክት
2015 ዓ.ም -- የዮሐንስ መልእክት (1ኛ)
2016 ዓ.ም -- የዕብራውያን መልእክት
2017 ዓ.ም -- የገላትያ መልእክት
አንዳንዶቹን መጻሕፍት (በተለይም ገላቲያንና 1ኛ ዮሐ) አጠናቅቀን ባናጠናም ግን ላለፉት አምስት አመታት በየአመቱ አንድ መጽሐፍ መቃኘታችን ይታወቃል። | 39 |
| 5 | Voice Chat ተከፍቷል። ወደ ውይይት ክፍሉ ተቀላቀሉ። በቴሌግራም Voice Chat እንግዳ የሆናችሁ ከስክሪናችሁ ግራ በኩል "join" የሚለውን Icon ተጭናችሁ ወደ ክፍሉ መግባት ትችላላችሁ። | 130 |
| 6 | ከ30 ደቂቃዎች በኋላ (3:00) Voice Chat ይከፈታል። በቆላስይስ መልእክት ምዕ 1:6-7 Discussion ይኖረናል። ሰምታችኋል አይደል? | 132 |
| 7 | ዛሬ ምሽት ONLINE እንገናኛለን!
በቆላስይስ መልእክት ጥናታችን ከምዕ 1-3-8 ያለውን ክፍል እየመረመርን እንደሆነ ይታወቃል። ዛሬ ምሽት በሚኖረን ጊዜ ቁ6-7 ባሉት ወንጌሉን በሚመለከት በቀረቡ እውነቶች እንነጋገራለን። በርግጥ ይህን በባለው ጥናታችን አንስተነው የነበረ ቢሆንም መቋጫ የሰጠን ባለመሆኑ ዛሬ እዚሁ ከOnline Community ጭምር አብረን እናጠናለን።
"...ይህም ወደ እናንተ ደርሶአል። ይህንም ወንጌል ከሰማችሁበትና የእግዚአብሔርን ጸጋ በእውነት ከተረዳችሁበት ቀን ጀምሮ በዓለም ዙሪያ እየሠራ እንዳለ ሁሉ በእናንተም ዘንድ ፍሬ እያፈራና እያደገ ነው።" (ቈላ 1:6-7 አ.መ.ት.)
➘ የወንጌሉ ባሕርይ (Nature)
➘ የወንጌሉ ይዘት (Content)
➘ የወንጌሉ ሥራ (The act)
➘ የወንጌሉ አድማስ (Sphere)
ባለፉት የጥናት ጊዜያት አብራችሁን የነበራችሁ ያለፉትን ውይይቶች ዐውድ በማገናዘብ በዛሬውም ውይይት ክፍል በንቃት እንድትሳተፉ እናሳስባለን።
--------
⏰ ከምሽቱ 3:00-4:30
እዚሁ Online እንገናኛለን።
--------
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 145 |
| 8 | እግዚአብሔር አለ!
ክፋት እያየለ፣ አመጽ እየገነነ፣ ኃጥአን ከትላንት ይልቅ ዛሬ እየበረቱ፣ ጻዲቁ በጭንቅ እየማቀቀ ብታዩ "ይህ ለምን ይሆናል?" አትበሉ። ይህ የሚሆነው ነገሮች ወደ ፍጻሜ እንዲቸኩሉና የእግዚአብሔር (የፍርድ) ቀን በቶሎ ይመጣ ዘንድ እንደሆነ መጽሐፉ ነግሮናልና። በግዞት ጨለማ የተጣልንና ፈጽሞ የተተውን ሲመስለን ያን ጊዜ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አለ።
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 131 |
| 9 | "ቁም ነገረኛ ሁን፤ ነገር ግን ኮስታራ አትሁን!"
( ከአጥባቂ ደቀ መዝሙር የተወሰደ፣ ጆን ስቶት)
1️⃣ ዘወትር ኹልጊዜ እግዚአብሔርን አመስግን… በቋሚነት ስለተሰጡህ በረከቶች በትኲረት እና በአድናቆት እግዚአብሔርን አመስግን… ምስጋና፣ ኲራት በቀላሉ የማይበቅልበት ዐፈር ነው።
2️⃣ የኀጢአትህን ኑዛዜ በትኲረት አድርግ። በእግዚአብሔር ፊት ራስኽን መተቸትህን ርግጠኛ ሁን፤ ይህ ራስኽን መመርመርሕ ነው። ራስኽን በመለኮታዊ ትችት ሥር አድርግ፤ ያ የኀጢአትህ ኑዛኔ ነው…
3️⃣ ውርደት ለመቀበል ዝግጁ ሁን። በከፍተኛ ኹኔታ ሊጐዳህ ይችላል፤ ነገር ግን ትሑት እንድትኾን ይረዳሃል። ጥቃቅን ውርደት ሊኖር ይችላል፤ ተቀበለው። ትልቅ ውርደት ሊኾን ይችላል ... እነዚህ ኹሉ ወደ ትሑቱ እና ስቁሉ ጌታ የሚያቀርቡን ዕድሎች ሊኾኑ ይችላሉ።
4️⃣ ስለ ክብር(ቦታ) አትጨነቅ... ጌታችን እንዲያሳስበን የጋበዘን አንድ ኹኔታ ብቻ ነው፤ ርሱም ለራሱ ቅርብ የመኾናችን ኹኔታ ነው ...
5️⃣ ሣቅህን ተጠቀም። በነገሮች ላይ ሣቅ፤ በሕይወት ከንቱነት ላይ ሣቅ፤ በራስኽ ላይ ሣቅ፤ እና በራስኽ ከንቱነት ላይ ሣቅ። በእግዚአብሔር መላ፟ለም ፣ እኛ ኹላችንም ኢምንትና አስቂኝ ፍጥረታት ነን። ቁም ነገረኛ ሁን፤ ነገር ግን ኮስታራ አትሁን፤ ምክንያቱም ስለ ኹሉም ነገር ኮስታራ ከሆንክ ፤ ይህም በራስኽ ላይ እንደዚያው ወደ መኾን ያደርሳሃል።
ወንድማችን አቤኔዘር ጤቻ እንዳቀረበው
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 146 |
| 10 | ደቀ መዝሙር
(ከሀብታሙ ፍሬው)
"ደቀ መዝሙር" ማለት በኢየሱስ የሚያምን፣ ቤተክርቲያን የማይቀር (አቴንድ የሚያደርግ) ወይም የክርስቲያን ስም የያዘ ሰው ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንስ ደቀ መዝሙር ማለት ለኢየሱስ ሕይወቱን የሰጠ፣ የእርሱ (የክርስቶስ) ዓለማ ዓላማው የሆነ፣ እርሱን እየተከተለ የሚኖርና ወደ እርሱ እየተለወጠ የሚሄድ ሰው ነው።
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 130 |
| 11 | የቁልቁለቱ ጉዞ!
"የክርስቲያን መሪ የጉዞ አቅጣጫ ይህች ዓለም እንደምትራኮትበት ሽቅብ ወደ ላይ ሳይሆን፣ መዳረሻው ወደ መስቀሉ የኾነ የቍልቍለት ጉዞ ነው። ይህ ጨለምተኛና ተስፋ አስቈራጭ ሊመስል ይችላል፤ የእግዚአብሔርን የመጀመሪያ ፍቅር ሰምተው ምላሽ ለሰጡ ኹሉ ግን የኢየሱስ የቍልቍለት ጉዞ፣ ከዚህ ዓለም ወዳልሆነው ወደ እግዚአብሔር ደስታና ሰላም የሚያደርስ መንገድ ነው።"
ፋኑኤል ብርሃነ (ከ"ሄንሪ ኖዌን" ሥራ ንባቡ)
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 168 |
| 12 | ዛሬ በአያት አካባቢ ኅብረት ጥቂት ሆነን በተስፉ ሆቴል ካፍቴሪያ ጥሩ ጊዜ አሳልፈናል። ያለፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቆይታችንን መገምገም፣ ስለወደፊቱ የኅብረታችን እጣ ፈንታ መወያየትና አንዳችን የሌላችንን ሸክም ለመካፈል እድል ያገኘንበት ጥሩ አጋጣሚ ነበር።
በዚህ ቤተሰብ ውስጥ እግዚአብሔር ስለሰጠን ሕያው እምነት ስሙን እናከብራለን። በእርሱ (በክርስቶስ) ማመናችን ከትላንት ይልቅ እንዲበዛና ለወንድሞችም ያለን ፍቅር እያደር እንዲጨምር ቃሉን መሠረት ባደረጉ እውነቶች እግዚአብሔር እያነጸን ነውና በዚህ እድለኞች ነን።
በአያት፣ ሰሚት፣ ፊጋ፣ ፍየል ቤት፣ Cmc፣ አራብሳ፣ ጣፎ፣ አርባ ዘጠኝ፣ ሰባ ሁለትና አካባቢው ላይ ያላችሁ ኑና በዚህ አካባቢ የተጀመረውን ሥራ አብረን እንሥራ። የክርስትናችንን መሠረት መፈተሹንና ጤናማውን አስተምህሮ አጥብቆ በመያዙና በያላችሁበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ውስጥ ሆናችሁ አብራችሁን ትተጋላችሁ። | 193 |
| 13 | ዛሬ በአያት ሴንተር!
ቆላስይስ 1:3-8 ሲጠና መቆየቱ ይታወሳል። ዛሬ በሚኖረን ጊዜ "ለቅዱሳን ያላችሁ ፍቅር" በሚለው የወንጌሉ ፍሬ (አስከትሎት) የመስክ ሥራ ይኖረናል። ይኸውም የጋራ የኅብረት ጊዜ (Coffee fellowship time) 🤎 ነው። ስለዚህም 11:30 ላይ አያት አደባባይ ያኔት ሆስፒታል ፊት ለፊት እንድንገናኝ ተወስኗል።
------------
⏰11:30-1:30
☎️ 0947424046
------------
Join & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
በውስጥ፦ @adfontess | 181 |
| 14 | ፍቅር እንዲህ ነው!
"አሳ ትወዳለህ?" ሲባል አብዛኛው ሰው "አዎ! በጣም ነው የምወደው" ይላል ነገር ግን አሳውን ሳይሆን ሰውየው ራሱን ነው የሚወደው! "ለምን?" ካላችሁ አሳውንማ ብትወዱት ከምቹ መኖሪያው፣ ነፍሱ ከምትቀጥልበት ስፍራና ከሚወዳቸው ወዳጆቹ አትለዩትም (አትነጥሉትም) ነበር።
ብትወዱትማ አታልላችሁ ባላጠመዳችሁትና ጠብሳችሁ ባልበላችሁት...እና አሁንም አሳውን ነው የምወደው ትላላችሁ? ወድጃለሁ የሚል ሰው ነፍስ ሲቀማ ለወደደው ሰው ነፍሱን የሰጠ ክርስቶስ ነው። ለዚህ ነው መጽሐፉም "ፍቅር እንደዚህ ነው" የሚለን።🥰
ጽዮናዊት መልካሙ
(ከVladimir Savchuk ንባቧ)
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 171 |
| 15 | እኛ የምንሠራው ቤተ ክርስቲያን በሕልውናዋ እንድትቀጥል አይደለም። እርሷ የሰው ማኅበር አይደለችምና ህልውናዋን የሚያጠፋ ኃይል በምድር የለምና። ነገር ግን ለማንነቷና ለተልዕኮዋ የማትታመን ሆና በሕልውናዋ መቀጠል ትችላለች።
ይህ ከባድ ፈተና ነው። የህልውናዋ አደጋም ጭምር ነው። የቤተ ክርስቲያን ትክክለኛ መልኳ የማይበገር መዋቅር ያላትና በሕዝብ ብዛቷ ምድርን የሞላች መሆኗ ላይ አይደለም። መኖሯ (ተፅዕኖዋም) የሚለካው ለተልዕኮዋ በምታሳየው ታማኝነት ነው።
አልበርት ሞህለርም እንዳሉት ሁሉ “የዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን ሐሰተኞች አስተማሪዎችን በዝምታ የምታልፍ ከሆነ፣ እንዲሁም ትምህርቶቻቸውን ሳታርምና ሳትጋፈጥ ከተወቻቸው ታማኝ ሆና መኖሯን መቀጠል አትችልም” ስለዚህ የእኛ አገልግሎት ከፍሬያማነት ታማኝነትን ያስቀድማል።
እናንተስ በግላችሁ ለክርስቲያናዊ ተልዕኳችሁ ታማኞች ናችሁ? የየእለት ምልልሳችሁ ያንን መሲሕ የሚወክል (portray የሚያደርግ) ነው? ለእርሱ (ለማንነቱ) እና ለሥራው መታመናችሁ (ሕይወታችሁ ከዚያ አንጻር የተቃኘ መሆኑ) ብቻ ክርስቲያን መሆናችሁን ይጠቁመናል።
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 240 |
| 16 | መጽሐፉና በረከት
(ከኃ/የሱስ ደ.)
አንድ ነገር እርግጠኛ ሆኜ አውቃለሁ። "መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር እንደሚባርክህ መረጃ የሚያደርስህ ጋዜጣ አይደለም።"
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 170 |
| 17 | ወንጌሉ ነጠላ ዜና ብቻ!?
የክርስቶስ ወንጌል እውነተኛ ማንነታችንና ክርስቲያናዊ ተልዕኳችን Define የሚያደርግ ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ምክር እንጂ "በስርጭት" መልክ ወደ ሰዎች የምናደርሰው ነጠላ ዜና (just a simple news) ብቻ አይደለም።
አማኝ በወንጌሉ ዜና በኩል ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይፈልሳል። ወንጌሉ መሠረቱ ወደሆነው መሲሓዊ ማኅበረሰብ ይቀላቀላል፤ በወንጌሉ እውነቶች በውስጥ ሰውነቱ ያድጋል። በወንጌሉ ጌታ ስር እየሰደደ ይጠነክራል። ከወንጌሉ በሚወጣው ማስቻል (ብቃት) ለወንጌሉ ኖሮ ለወንጌሉ ይሞታል።
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 210 |
| 18 | ዛሬ የኅብረት ጊዜ አይኖረንም!
እለቱ የበዓሉ ዋዜማ እንደመሆኑ ከተማው ላይ ከሚኖሩ መዋከቦችና የትራንስፖርት እጦት እንግልት የተነሳ ዛሬ በአያት ሴንተር የቆላስይስ መጽሐፍ ጥናት አይኖረንም።
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 237 |
| 19 | ወንጌሉ ወደ ውስጥም!
የክረስቶስ ወንጌል ወደ ውጪ ብቻ ሳይሆን ወደ ውስጥም (ለአማኙም) ጭምር ነው። አቀራረቡ ደግሞ ሥነ መለኮታዊ ተፈጥሮውን የጠበቀ፣ ይዘቱን ያላሳሳ (የወንጌል ንጽሕናን የማያሳድፍ)፣ ዘመኑን ያስተዋለ (ዐውዳዊ)፣ ተገቢ ስልቶችን የሚጠቀም (ስልታዊ)፣ በቂ ዝግጅት የተደረገበት (ስንዱ የኾነ)፣ ወንጌል ተኰር ማኅበረ ሰብ መፍጠር እና እግዚአብሔርን ማክበርን ያለመ መኾን ይጠበቅበታል።
(በርናባስ ዘመነ)
------------
Join Us & Share!!!
@metsihafuyinager
------------
ወደ ውስጥ፦ @adfontess | 263 |
| 20 | Voice Chat መግባት የምትችሉ ተቀላቀሉና ለጥቂት ደቂቃዎች እንወያይ! | 14 |
