ch
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

前往频道在 Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

显示更多
未指定国家未指定类别
4 292
订阅者
+524 小时
-137 天
-8430 天
帖子存档
🇮🇷⚡️🇺🇸 ጋዜጠኛ፡ 'ስለዚህ በኢራን የኃይል መሠረተ ልማት ላይ ጥቃት እንዲደረግ እየጠየቁ ነው?' ሊንድሲ ግራሃም፦ 'አዎ፣ ይህንን አገዛዝ ለመጉዳት ጥሪ እያቀረብኩ ነው።' 'በበቂ ሁኔታ በደንብ ከጎዳችኋቸው ምናልባት ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ።'

🇸🇦ሳዑዲ ድሮኑን ብታየውም እንኳ፣ ወደ ኤሜሬት የሚያልፍ እስከሆነ ድረስ የምትነካው አይመስለኝም።
🇸🇦ሳዑዲ ድሮኑን ብታየውም እንኳ፣ ወደ ኤሜሬት የሚያልፍ እስከሆነ ድረስ የምትነካው አይመስለኝም።

—❗🇨🇺/🇮🇷/🇺🇸 ይህ አሜሪካውያን ሦስተኛ ዙር የኢራን ጦርነትን ለአሜሪካ ህዝብ ለመሸጥ እየሞከሩ ሊሆን ይችላል። ከመጨረሻው የረመዳን ጦርነት ከጥቂት ቀናት በፊት፣ AXIOS እንዲሁ ኢራን አሜሪካ ሊደርሱ የሚችሉ አህጉራዊ ባሊስቲክ ሚሳይሎችን እየሠራች መሆኑን ዘግቦ ነበር። በነገራችን ላይ፣ የአይሁዶች የሻቩኦት በዓል ከአራት ቀናት በኋላ ነው።

❗️❗️🇺🇸❗️ትራምፕ ዛሬ ይገኝባቸዋል ተብለው የሚጠበቁትን ሁሉንም ይፋዊ ዝግጅቶችን መሰረዙ የታወቀ ሲሆን፣ በምትኩ፣ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በኢራን ላይ በሚደረግ የደህንነት ስብሰባ ላይ ይሳተፋል።

—❗🇨🇺/🇮🇷/🇺🇸 ትኩስ፦ ኩባ ከ300 በላይ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን ተቀብላለች፣ ምናልባትም ከኢራን እና ከሩሲያ የተገኙ ሊሆኑ ይችላሉ፣ እናም በደሴቲቱ ላይ የአሜሪካ ጥቃት ቢደርስ፣ በጓንታናሞ ቤይ የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ማዕከልን ጨምሮ፣ በአሜሪካ ወታደራዊ መርከቦች እና በፍሎሪዳ የባህር ዳርቻ ላይ ለመጠቀም እየተዘጋጀች ነው – Axios

🇦🇪 | የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ 3 ድሮኖች “ከምዕራብ” ወደ ግዛቷ መግባታቸውን እና አንድ ድሮን በአል ዳፍራ ክልል ውስጥ ከሚገኘው የባራካ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ውጫዊ ወሰን ውስጥ የኤሌክትሪ
🇦🇪 | የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ 3 ድሮኖች “ከምዕራብ” ወደ ግዛቷ መግባታቸውን እና አንድ ድሮን በአል ዳፍራ ክልል ውስጥ ከሚገኘው የባራካ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ውጫዊ ወሰን ውስጥ የኤሌክትሪክ ጄነሬተሬ መምታቱን ተናግራለች። ጠዋት በዚሁ አካባቢ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ ተከስቶ የነበር ሲሆን እስከ አሁን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አደጋውን ለመቆጣጠር እየጣሩ ናቸው። የ"ምዕራብ ክልል" ማለት ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራቅ ወይም የመን ሊሆን ይችላል።

🇮🇷⚡️የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር፣ ዛሬ፣ እስራኤልን "በሽብር የምትኖር ሽብርተኛ ሀገር" ብሎ በጠራበት ደብዳቤው፣ የሐማስን መሪ ግድያ በጽኑ አውግዟል።
🇮🇷⚡️የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር፣ ዛሬ፣ እስራኤልን "በሽብር የምትኖር ሽብርተኛ ሀገር" ብሎ በጠራበት ደብዳቤው፣ የሐማስን መሪ ግድያ በጽኑ አውግዟል።

🇮🇷🇺🇸🇮🇱 (ኢራን) The Wall Street Journal፦ በኢራን ላይ የተካሄደው ጦርነት በዓለም ላይ የድንጋይ ከሰል ፍላጎትን ጨምሯል። 🔹የሆርሙዝ መተላለፊያ ወሽመጥ መዘጋት ጋር የኃይ
🇮🇷🇺🇸🇮🇱 (ኢራን) The Wall Street Journal፦ በኢራን ላይ የተካሄደው ጦርነት በዓለም ላይ የድንጋይ ከሰል ፍላጎትን ጨምሯል። 🔹የሆርሙዝ መተላለፊያ ወሽመጥ መዘጋት ጋር የኃይል አማራጭ ምንጮችን ሲፈልጉ የነበሩ ሀገራት፣ አሁን ፊታቸውን ወደ ድንጋይ ከሰል አዙረዋል፣ በዚህም ፍላጎቱ ጨምሯል። የአሜሪካ የድንጋይ ከሰል አውጪ ኩባንያዎች፣ የገበያው ፍላጎት አጨናንቋቸው ይገኛል፣ ከሀገር አቅርቦት ውጭ፣ የሚልኩት እጥፍ ዕድገት አሳይቷል ተብሏል። በአሜሪካ ከተፈጥሮ ጋር ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ የድንጋይ ከሰል እንደሆነ ይታወቃል።

🇮🇷⚡️🇺🇸 በኢራን ወገን በኩል ያሉ ተንታኞች እና የቀጠናው ባለሙያዎች፣ በኢራን ላይ ጦርነቱ ዳግም ሊተረኮስ አንድ ሐሙስ እንደቀረው ነው እያወሩ ያሉት። "እንመታ ይሆናል፣ እንሞት እንጠፋም ይሆናል፣ ነገር ግን ቀጠናውን ይዘን አብረን ለመጥፋት ነው የምንሞክረው"፣ በማለት ላይ ናቸው። ማንም ሞቱ ማንም አይቀራትም ፖሊሲ ላይ ደርሰዋል። ** "በቴህራን፣ ግጭት የማይቀር እና በጣም ቅርብ መሆኑን የሚያሳይ የመጨረሻ እምነት የተደረሰበት ይመስላል። "በዚህ መሠረት፣ አዲስ የዒላማ ክምችት ተዘጋጅቷል። በዋነኝነት በ UAE ፣ ኩዌት ፣ ባህሬን እና ከዚያ ባሻገር፣ ከፓኪስታን እና ከኩርድስታን ጎን ለጎን ለድንበር ዛቻዎች ዝግጅቶች፣ እንዲሁም ካርግ እና አቡ ሙሳ ደሴት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን ጨምሮ ከብዙ ድንበሮች ጦርነት የመፈጠር እድል ላይ ያተኮረ ነው ። "ይህ በኢራን ላይ የሚደረግ የመጨረሻው የጥቃት ደረጃ ሊሆን የሚችልበት እድል እየጨመረ ነው፣ ይህም በሚያሳዝን ሁኔታ ከፍተኛ የአመራር ደረጃዎችን ጨምሮ የዋና ዋና ግለሰቦችን ሰማዕትነት ሊያካትት ይችላል። "ነገር ግን፣ ግምቶች እንደሚያመለክቱት ኢራን ለማስፈራሪያዎች ወይም ለጥቃቶች አትሸነፍም።  ከባድ ኪሳራዎች ቢደርሱባትም፣ አሸናፊ ለመሆን ትሞክራለች፣ ይህም ደግሞ የሚያስከትለው ውድመት በባህረ ሰላጤው ሀገራት ውስጥ በእኩል ወይም ከዚያም በበለጠ ከባድ ሊሆን ይችላል።"

🇺🇸⚡️💰 "እስራኤል በኮንግረስ ውስጥ መቀመጫዎችን ትገዛለች፣ በፍፁም የእኔን አይደለም" ቶማስ ማሲ። ተወካዩ ቶማስ ማሲ፣ በሚሊዮኖች በሚቆጠር የዘመቻ ገንዘብ፣ እንዳይመረጥና ሥራውን ለማስተጓጎል የሚሞክሩ የፅዮናውያን ለጋሾችን ሰንሰለት አጋልጧል። 💬 “ይህ ሲጠናቀቅ፣ ምናልባት 20 ሚሊዮን ዶላር ያወጡ ይሆናል፣ ለባዶ ውጤት!” ብሏል። ✡️ ማሲ አፅንኦት ሰጥቶ እንደተናገረው፣ "ሌላ ማንኛውም የአሜሪካ አጋር በአሜሪካ ምርጫ ውስጥ በዚህ መንገድ ጣልቃ አይገባም — ነገር ግን እስራኤል ልዩ ፈቃድ ታገኛለች" ሲል ተናግሯል። ቶማስ ማሲ ኦርጅናሉ MAGA ሪፐብሊካን ቢሆንም፣ የትራምፕን መንግሥት እና እስራኤልን በብዙ አጀንዳዎቹ በመቃወሙ፣ ትራምፕ "ከMAGA አባርሬሃለሁ" ያለው የኮንግረስ አባል ነው። ባሁኑ ሰዓት ድጋሜ ለመመረጥ እየጣረ ቢሆንም፣ እስራኤል በግልፁ ለተቀናቃኙ ሚሊዮኖችን በማፍሰስ እንዳይመረጥ እየሰራች ነው ተብሏል። አሁን ማሲ፣ የቅድመ- ሕዝብ ድምፅ ምርጫን በ1% ተፎካካሪውን እየመራ ነው።

ትራምፕ፡ "ከአውሎ ነፋሱ በፊት ፀጥታ ነበር።" ወደ ጦርነት ሊመለስ የሚመስሉ ብዙ ምልክቶች አሉ። አሜሪካና እስራኤል በከፍተኛ ደረጃ ያደረጉትን እንዳጠናቀቁ ትናንት ተነግሯል። ከቻይና የትራምፕ ጉብኝ
ትራምፕ፡ "ከአውሎ ነፋሱ በፊት ፀጥታ ነበር።" ወደ ጦርነት ሊመለስ የሚመስሉ ብዙ ምልክቶች አሉ። አሜሪካና እስራኤል በከፍተኛ ደረጃ ያደረጉትን እንዳጠናቀቁ ትናንት ተነግሯል። ከቻይና የትራምፕ ጉብኝት መጠናቀቅ በኋላ፣ የሚጠብቁት ትልቅ ክስተት ለመኖሩ ምልክት እየሰጡ ነው።

+2
🇺🇸⚡️ USS Gerald R. Ford የተባለው የአሜሪካ ትልቁ የጦር መርከብ፣ ዛሬ፣ ከ 11 ወራት የባሕር ላይ ቆይታው በኋላ፣ ወደ አሜሪካ ተመልሷል። በአሜሪካ መቀመጫው በኾነው Norfolk Virginia በደረሰና መልህቁን በጣለ ጊዜ፣ የጦር ሚኒስትሩ ለመርከበኞቹ ጨምሮ ለሁሉም አቀባበል አድርጓል። መርከቡ፣ የኢራን ጦርነት በተጀመረ በጥቂት ቀናቶች ውስጥ በሚሳዬሎች ተመቶ እንደነበርና በባሕሩ ላይ መንቀሳቀስ ስላልቻለ ተጎትሎ ወደ ኋላ አፈግፍጎ እንደነበር በሰፊው ሲወራ ነበር። ይህም የአሜሪካን ወታደራዊ አካላትን ክፉኛ ያስደነገጠ ክስተት እንደነበር በጊዜው የተዘገበ ነው። አሁንም ቢሆን፣ የመርከቡ ከውጊያ ቀጠና ውጭ መሆኑ፣ ለብዙዎች የተዋጠ አይደለም።

— 🇮🇷 የኢራን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በብሔራዊ ደረጃ የውጊያ ዝግጁነትና ተነሳሽነት አካል የሆነውን የጠመንጃ አጠቃቀም ዘይቤን ለሕዝቡ ማብራራታቸውን ቀጥለዋል።
+2
— 🇮🇷 የኢራን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በብሔራዊ ደረጃ የውጊያ ዝግጁነትና ተነሳሽነት አካል የሆነውን የጠመንጃ አጠቃቀም ዘይቤን ለሕዝቡ ማብራራታቸውን ቀጥለዋል።

🇨🇳 የቻይና ትልቁ ተነባቢ ጋዜጣ፣ የትራምፕን ቻይና ጉብኝት በዚህ መልኩ ገልጾታል።
🇨🇳 የቻይና ትልቁ ተነባቢ ጋዜጣ፣ የትራምፕን ቻይና ጉብኝት በዚህ መልኩ ገልጾታል።

🇮🇷⚡️ኢራን ዛሬ የ MOSSAD ሰላይ ነበር ያለችውን ኢራናዊ ተጠርጣሪ በስቅላት ገድላለች። ከ MOSSAD ጋር በደህንነትና መረጃ ልውውጥ በመስራት ክስ በቁጥጥር ስር የዋለው እና የተፈረደበት ኢህ
+3
🇮🇷⚡️ኢራን ዛሬ የ MOSSAD ሰላይ ነበር ያለችውን ኢራናዊ ተጠርጣሪ በስቅላት ገድላለች። ከ MOSSAD ጋር በደህንነትና መረጃ ልውውጥ በመስራት ክስ በቁጥጥር ስር የዋለው እና የተፈረደበት ኢህሳን አፍሬሽታህ፣ ሙሉ የወንጀል የፍትህ ሂደቱን ካጠናቀቀ በኋላ እና በጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ውሳኔው ከተረጋገጠ እና የመጨረሻ ማጽደቅ ከተደረገ በኋላ ዛሬ ማለዳ ላይ ተገድሏል፣ ተብሏል። በሪፖርቱ መሠረት፣ በመጀመሪያ በመልእክት መተግበሪያዎች እና በኋላ በኢሜይል ከሞሳድ አለቆቹ ጋር ግንኙነት አድርጎ እንደነበር እና በታክሲ አሽከርካሪ መልክ እየሰራ ተልእኮዎችን እንደፈጸመ ተገልጿል። ከእስራኤል አገዛዝ ጋር በትብብር በሚሰራበት ጊዜ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ እና ዕብራይስጥ በደንብ መናገር እንደቻለ እና በሞሳድ ውስጥ የሚስጥር ኮድ ስሙ “ጄምስ” እንደነበር ተገልጿል። ከድምጽ ግንኙነቶች በተጨማሪ በየወሩ ከአራት እስከ አምስት ኢሜይሎችን እንደተለዋወጠ ይነገራል፣ በአጠቃላይ ከ300 በላይ መልዕክቶችን ከ MOSSAD ጋር ተለዋውጠዋል።

🇮🇳🇦🇪 ሕንድ በጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ የአቡ ዳቢ ጉብኝት ወቅት ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር የመከላከያ ትብብር ስምምነት ፈረመች። በልዋጩም ሕንድ $5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የኤሚሬትስ ኢንቨስትመንት ቃል ተገብቶላታል።

— 🇮🇷/🇦🇪 በኢራን ቴሌቪዥን፣ አንድ ወታደራዊ አስተማሪ በቤት ውስጥ ላሉ ሰዎች የክላሽኒኮቭ ጠመንጃ እንዴት እንደሚተኮስ እያስተማረ ይታያል። የዜናው አቅራቢም ክላሹን በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ባንዲራ ላይ በማነጣጠር ሲተኩስና፣ በስተጀርባ የዱባይ ምስል ሲቃጠል ይታያል።

— 🇮🇷/🇷🇺፦ ሩሲያ ለሶሪያ መንግሥት ተዋጊ ጀቶችን መስጠቷ እውነት ከሆነ፣ ይህ የሩሲያ ከኢራን ጋር ስላላት 'ሽርክና' ከባድ ጥርጣሬዎችን የሚፈጥር እንግዳ እርምጃ ነው። ኢራን ጀቶችን ከሩሲያ ካዘዘች ቆይታለች። ክፍያዎችን ፈጽማ አብራሪዎችን አሰልጥና ዓመታት ተቆጥረዋል። እስካሁን ግን አንድም የSu-35 አውሮፕላን ከሩሲያ አልተቀበለችም። እንደ ተተኪ ወይም ጊዜያዊ መፍትሄ አንድ የMiG-29 አውሮፕላን እንኳን አልደረሳትም። ከሶሪያ በላይ ኢራን እንደሚያስፈልጋት እየታወቀ እንኳ።

— 🇷🇺/🇸🇾 አዲስ፦ ሩሲያ ሁለት የMiG-29 ተዋጊ አውሮፕላኖችን ለአዲሱ የሶሪያ መንግሥት አየር ኃይል አስረክባለች፣ ዛሬ ወደ ክሜሚም አየር ኃይል መንደርደሪያ ደርሰዋል ሽብርተኝነትን ለመከላከል እና የአየር ክልልን ለመጠበቅ እንዲረዳ በቱርክ ጥያቄ መሰረት አቅርቦቶች ተደርገዋል። ምንም እንኳን የሶሪያ አክቲቪስቶች ቪዲዮው አርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እንደሆነ ቢገልጹም፣ ይህ በተለያዩ ዋና ዋና የዜና አውታሮች ሪፖርት እየተዘገበ ነው።

⚡️🇺🇸🇮🇱 The Economist፦ "በነዳጅ ታሪክ ውስጥ ትልቁ የአቅርቦት እጥረት አደጋ በፍጥነት እየሰፋ ነው። በሆርሙዝ መተላለፊያ መዘጋት ምክንያት ወደ 2 ቢሊዮን በርሜሎች ወይም ከዓለም ዓ
⚡️🇺🇸🇮🇱 The Economist፦ "በነዳጅ ታሪክ ውስጥ ትልቁ የአቅርቦት እጥረት አደጋ በፍጥነት እየሰፋ ነው። በሆርሙዝ መተላለፊያ መዘጋት ምክንያት ወደ 2 ቢሊዮን በርሜሎች ወይም ከዓለም ዓመታዊ የነዳጅ አቅርቦት 5% ያህል ጠፍቷል።"