የቀጠናው ተመልካች
前往频道在 Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
显示更多未指定国家未指定类别
4 292
订阅者
+524 小时
-137 天
-8430 天
帖子存档
4 295
⚡️🇺🇸🇮🇱 The Economist፦ "በነዳጅ ታሪክ ውስጥ ትልቁ የአቅርቦት እጥረት አደጋ በፍጥነት እየሰፋ ነው። በሆርሙዝ መተላለፊያ መዘጋት ምክንያት ወደ 2 ቢሊዮን በርሜሎች ወይም ከዓለም ዓመታዊ የነዳጅ አቅርቦት 5% ያህል ጠፍቷል።"
4 295
🇳🇬🇺🇸⚡️- "ዛሬ ማታ፣ በእኔ መመሪያ፣ ጀግኖች የአሜሪካ ኃይሎች እና የናይጄሪያ ጦር ሃይሎች በዓለም ላይ በጣም ትልቅ የሆነውን አሸባሪ ከጦር ሜዳ ለማስወገድ በጥንቃቄ የታቀደ እና በጣም ውስብስብ ተልዕኮን ያለምንም እንከን አከናውነዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የISIS ሁለተኛ አዛዥ የሆነው አቡ-ቢላል አል-ሚኑኪ በአፍሪካ መደበቅ እንደሚችል አስቦ ነበር፣ ነገር ግን ምን እየሰራ እንዳለ መረጃ የሚሰጡን ምንጮች እንዳሉን አላወቀም።
ከአሁን በኋላ፣ የአፍሪካን ህዝብ አያሸብርም፣ ወይም አሜሪካውያንን ዒላማ የማድረግ ተግባራትን ለማቀድ አይረዳም።
እሱ በመወገዱ፣ የISIS ዓለም አቀፍ ተግባር በእጅጉ ቀንሷል።
በዚህ ተግባር ላደረጉት የአጋርነት ሥራ የናይጄሪያን መንግስት አመሰግናለሁ።
እግዚአብሔር አሜሪካን ይባርክ! ፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ. ትራምፕ"
4 295
🇺🇸🇨🇳 የኋይት ሃውስ የግንኙነት ዳይሬክተር ስቲቨን ቼንግ፣ በቻይና ቤጂንግ በሚገኘው በታላቁ የሕዝብ እልፍኝ አዳራሽ፣ በቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ እና በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መካከል በተደረገው የሁለትዮሽ ስብሰባ ላይ ተገኝቶ ይታያል፣ May 14፣ 2026 እ.ኤ.አ። ሮይተርስ።
4 295
Repost from ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…✍
ሚስቱ እና ልጁን በግፍ ያጣው አባወራ ሌሎችንም ራሱንም እንዳይጎዳ ቤት ውስጥ ታስሮ ይገኛል ጭካኔ የተሞላበትን ድርጊት ፈፅመው ህይወትን ነጥቀው ቀሪ ቤተሰብንም ለከፋ ሀዘን እና ህመም ዳርገዋል።
ጎበዝ በአሽከርካሪ ረዳት እና ተሳፋሪ ላይ የሚደርስን አፈና ግድያ ልንቃወም ልናወግዝ ፍትህን ልንጠይቅ ይገባል።
BBC News Amharic እናመሰግናለን
4 295
🇮🇳 በBloomberg መረጃ መሠረት፣ ሕንድ በእሷ ባንዲራ ሥር ያለ የንግድ መርከብ ረቡዕ ዕለት በኦማን የባህር ዳርቻ ላይ ጥቃት ደርሶበት መስጠሙን ገልጻለች።
የመርከቡን ሠራተኞች ያለ ምንም ጉዳት ከመርከቡ ላይ ማዳን ተችሏል።
ኒው ዴሊ ክስተቱን አውግዛ፣ ነገር ግን መርከቡን ማን እንዳጠቃው አልገለጸችም።
4 295
🇺🇸🇰🇪 Microsoft፣ በኬንያ ዋና የዳታ ማዕከል ለመገንባት ያለውን እቅድ ትቶታል፣ ምክንያቱም ሀገሪቱ ዳታ ሴንተሩን ለመደገፍ የሚያስችል በቂ ኤሌክትሪክ የላትም።
ኬንያ ለታቀደው የዳታ ማዕከል የኤሌትሪክ ኃይል ማቅረብ ቢኖርባት ኖሮ፣ በግምት ግማሽ የሚሆነው የሀገሪቱ ክፍል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ያጣ ነበር።
***
Blessing In Disguise ማለት ይሄ ነው። እንኳን የቀረባችሁ!
4 295
🇺🇸⚡️🇮🇷 ትራምፕ ከቻይና መልስ፣ በኢራን ጦርነት ላይ ከፊቱ ውሳኔ ተጋርጧል።
የኢራን ጦርነት ከሚቀጥለው ሳምንት ቀደም ብሎ ሊቀጥል ይችላል — NYT
ድርድሩ ከመክሸፉ ጋር በተያያዘ፣ የፕሬዝዳንቱ ከፍተኛ አማካሪዎች የውጊያ ፕላን አዘጋጅተዋል።
በአሁኑ ሰዐት፣ አሜሪካ እና እስራኤል ለግጭት መባባስ 'በከፍተኛ ሁኔታ' እየተዘጋጁ ይገኛሉ።
አማራጮች፣ የኑክሌር ቁሳቁሶችን ለመያዝ በኢራን መሬት ላይ የአሜሪካ ልዩ ኦፕሬሽኖችንን የሚያክትት ሊሆን ይችላል።
4 295
+4
🇮🇱❌🇵🇸 — ትኩስ ዜና፦ የእስራኤል አየር ኃይል በጋዛ ከተማ ሪማል ሰፈር በሚገኝ የመኖሪያ ሕንፃ ላይ የዓል-ቃሲም ቡድን አዛዥ እና በጋዛ ሠርጥ የሃማስ መሪ የሆነውን ዒዘዲን አል-ሃዳድን ዒላማ በማድረግ የአየር ጥቃት ፈጽሟል።
አንድ ከፍተኛ የእስራኤል የደህንነት ባለሥልጣን ለ The Times of Israel እንደተናገረው፣ አል-ሃዳድ በመኖሪያ ሕንፃው ላይ በተደረገው ጥቃት መገደሉን የሚያሳዩ “የመጀመሪያ ምልክቶች” አሉ።
አል ሃዳድ፣ የሀማስ መሪ የነበረው ያህያ ሲንዋር ህልፈትን ተከትሎ፣ የቡድኑ መሪ የሆነ ቁልፍ በጋዛ ሰው ነበር።
4 295
🇺🇸🇨🇺⚡️— የCIA ዳይሬክተር ጆን ራትክሊፍ ወደ ሃቫና ኩባ ባደረጉት ጉብኝት፣ አሜሪካ ከኩባ ጋር በኢኮኖሚ እና በደህንነት ጉዳዮች ላይ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን በመግለጽ፣ ኩባ፣ ከግዛቷ የሩሲያ እና የቻይና በአሜሪካ መንግሥት ላይ ያቋቋሟቸውን የስለላ ማዳመጫ ማማዎችን መዝጋትን ጨምሮ፣ "መሠረታዊ ለውጦችን" ካደረጉ ብቻ ግንኙነታቸው እንደሚሻሻል አሳውቋል።
➡️ የራትክሊፍ ጉዞ በኩባ መንግሥት ላይ ጫናን ለመጨመር እና የመንግስት ለውጥ ለማምጣት እንዲሁም የትራምፕን ጥረት ለማራመድ የተዘጋጀ ሰፊ ዘመቻ አካል ነበር።
4 295
— 🇮🇱/🇮🇷 የእስራኤል ሚዲያ፦ 'ጠቅላይ መሪው ሙጀተባ ካምኔይ ከአባቱ የበለጠ አክራሪ ብቻ ሳይሆን፣ በማንኛውም ቁልፍ የድርድሩ ነጥቦች አንዲት ኢንች ፈቀቅ ለማለት ፈቃደኛ አይደለም። ድርድሩንም የጎተተው እና ያፈረሰው በዚህ አቋሙ ነው።'
4 295
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለማንኛውም የኢራን ስጋት ወይም ጠላታዊ ድርጊት ምላሽ ለመስጠት ሙሉ ሉዓላዊ፣ ሕጋዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ መብቶች እንዳላት አስታወቀች።
4 295
— 🇺🇸/🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ፦ 'በኢራን ውስጥ ያሉትን ድልድሎች እና የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ማቆየት እንችላለን፣ ወይም ሁሉንም በሁለት ቀናት ውስጥ ማጥፋት እንችላለን።'
4 295
— 🇦🇪/🇸🇦/🇰🇼/🇧🇭/🇶🇦/🇮🇷 ትኩስ ዜና፡ በቅርቡ በተካሄደው ጦርነት ወቅት፣ የዩኤኢ መሪ ሙሐመድ ቢን ዛይድ የባህሬን፣ የኩዌት፣ የኳታር እና የሳውዲ አረቢያ መሪዎችን በግል ደውሎ ኢራንን የሚቃወም የአረብ ጥምረት እንዲፈጠር ሀሳብ አቅር ነበር። ነገር ግን እያንዳንዱ ሀገር እምቢ ብለውታል – Bloomberg
4 295
— 🇮🇱/🇦🇪 አዲስ፦ እስራኤል የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን ለሁለተኛ ጊዜ ከጀርባዋ ወግታታለች።
አሁን ኔታንያሁ አቡ ዳቢን መጎብኘቱን ብቻ ሳይሆን ይፋ ያወጣችው፣ የIDF የጦር ሰራዊት አዛዥ፣ የሞሳድ ኃላፊ እና የሺን ቤት ኃላፊም እንደጎበኙ ገልፃለች
የኤሜሬትስ ባለስልጣናት በአዲሱ የእስራኤል መግለጫ 'በጣም ተቆጥተዋል' ተብሏል።
4 295
+2
— 🇺🇸/🇨🇺 50 ዓመት በአሜሪካ ያልተንበረከከችው ኩባ፣ በስተመጨረሻ፣ ፀሐይ እየጠለቀችባት ይመስላል።
ኩባ ሳይተኮስባት እጅ እየሰጠች ነው።
ከወራት ጫና፣ ከነዳጅና ምግብ እገዳ፣ እና ከዩናይትድ ስቴትስ የአገዛዝ ለውጥ ማስፈራሪያዎች በኋላ፣ የCIA ዳይሬክተር ከኩባ ባለስልጣናት ጋር ለቀጥታ ውይይት ወደ ሃቫና ተጋብዟል።
መልዕክቱ የሚሆነው አንድና አንድ ነው፣ ለአሜሪካ አጎንብሱ ነው።
4 295
+1
— 🇮🇱/🇱🇧፦ IDF በደቡብ ሊባኖስ እና በሰሜን እስራኤል ባሉት ሁሉም የጦር ካምፖች ላይ፣ ፀረ-ድሮን ዓሣ ማስገሪያ መረብ የመወጠር ግዙፍ ፕሮጀክት ጀምሯል።
4 295
— 🇺🇸/🇨🇳/🇮🇷 ሪፖርተር፦ 'ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር በተያያዘ ፕሬዝዳንት ሺን በትክክል ምን ጠየቁት?'
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፦ 'ምንም ነገር አልጠየቀውም።
የቻይናን እርዳታ እየጠየቅን አይደለም፣ እርዳታቸው አያስፈልገንም።
ኢራን የኑክሌር መሳሪያ ሊኖራት እንደማይችል ግልጽ አድርገናል።'
4 295
🇮🇱 የእስራኤል መከላከያ ሚንስቴር፡ “በኢራን ያለን ተልእኮ አላለቀም፣ በቅርቡ እርምጃ ልንወስድ ስለምንችል ለዚያ ዝግጁ ነን።”
**
እስራኤል ከኢራን ጋር ለሌላ ዙር ጦርነት ቋምጣለች፣ በአሜሪካ ትከሻ ላይ ተንተርሳ። አሜሪካ ደግሞ፣ በምንም ተዓምር ጦርነቱን ማስቀጠል አትፈልግም። አሁን ላይ የምትፈልገው በማንኛውም መንገድ አቁማ መውጣት ነው። ኢራን ከጠበቀችው በላይ ዋጋ አስከፍላታለች።
ወደ ጦርነት የምትመለስ ከሆነ፣ የምትመለሰው የእስራኤል ንዝነዛ አሸንፏት ነው።
'ንዝነዛ' በዚህ አገባብ ፍቺው፣ ጥምዘዛ እና ማስገደድ ነው።
4 295
🇮🇷 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፦ “የኢራን ገጽታ በዓለም ዓይን ተለውጧል።
ዓለምን ገለባብጠው ለማየት ቢፈልጉ፣ ይህን ማድረግ የሚችሉ ሰዎችን እየገጠሙ መሆኑን ተገንዝበዋል።”
4 295
—❗🇮🇱/🇺🇸/🇮🇷 "ነገ ትራምፕ የቻይና ጉብኝቱን ጨርሶ ሲመለስ፣ የእስራኤል ጦር ሠራዊት በከፍተኛ የተጠንቀቅ ደረጃ ውስጥ ይገባል" J POST
