የቀጠናው ተመልካች
الذهاب إلى القناة على Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 294
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-137 أيام
-8030 أيام
أرشيف المشاركات
4 300
🇺🇸🇮🇱️ — AIPAC (በአሜሪካ የአይሁድ ለጋሾች ማህበር) እና ሌሎች የእስራኤል ደጋፊ ቡድኖች ኮንግረስማን ቶማስ ማሴን በኬንተኪ በመጪው የሪፐብሊካን ምርጫ ለማሸነፍ ከ9 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርገዋል፣ ይህም በውድድሩ አጠቃላይ ወጪን ከ32 ሚሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ እጅግ ውድ የሆነው የኮንግረስ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ሂደት እንዲሆን አድርጎታል፣ እንደ POLITICO ዘገባ።
ከታዋቂ የእስራኤል ሪፐብሊካን ለጋሾች የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ፣ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ የእስራኤልን ረጅም እጅ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፣ ከዚህ በፊት በድብቅና በሹክሹክታ ይደረግ የነበረው የድጋፍ ተሳትፎአቸው፣ አሁን ላይ በአደባባይ ወጥቶ መነጋገሪያ እንዲሆን ሆኗል። ይህ ከመሆኑ ጋር በተያያዘም፣ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ፀረ- አይሁድ እንቅስቃሴ በስፋት እየተስተዋለ ይገኛል። ተመሳሳይ ስሜት በሕዝቡ ዘንድም ተፈጥሯል።
በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ የእስራኤልን ጣልቃ ገብነት ከሚቃወሙ ድምፆች መካከል ደግሞ የሪፐፕሊካኑ የኮንግረስ ዕጩ ቶማስ ማሲ ዋነኛውና ትልቁ ሆኖ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወጥቷል።
ማሴ፣ ከአብዛኛው ለእስራኤል ከሚሰግዱት የኮንግረስ አባላት አፈንግጦ የቆየ ሲሆን፣ በቅርቡም AIPAC እንደ ባዕድ ሀገር ወኪል እንዲመዘገብ የሚያስገድድ የሕግ አንቀጽ በመቅረፅ፣ በኮንግረስ ፊት ለምርጫ አቅርቧል።
4 300
🇺🇸⚡ሁለት የአሜሪካ F-18 ወታደራዊ ተዋጊ ጄቶች፣ በ Idaho የአየር ትርዒት እያሳዩ ባሉበት ተጋጭተው ፈንድተዋል።
የጀቶቹ ፖይለቶች ተርፈዋል።
4 300
🇺🇦🇷🇺 ዩክሬን ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ሞስኮ ከተማ ላይ በወሰደችው መጠነ -ሠፊ ጥቃት በርካታ ዒላማዎች መምታቷን አስታውቃለች።
ከዩክሬን የተነሱ የተባሉ ድሮኖች በሞስኮ ከተማ ጠልቀው በመግባት ዒላማዎችን መምታት የቻሉ ሲሆን፣ ጉዳዩ ብዛት ያላቸውን የሩሲያ ተንታኞችን አስደንግጧል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሩሲያ የዩክሬን ጥቃት እያየለ የመጣ ሲሆን፣ አጠቃላይ የጦርነቱን አቅጣጫና መልክ በመቀየር ላይ ነው።
በዚህ የዩክሬን ጥቃት መባባስ አውሮፓዊያን መንግሥታት በርግጥም ሩሲያ ልትሸነፍ ካልሆነም ልትሽመደመድ ትችላለች የሚል አስተሳሰብ እንዲያዳብሩና ዩክሬንን ግፊ በማለት እርዳታቸው እንዲጨምሩ እያደረጋቸው ይገኛል።
4 300
🇸🇦🤝🇦🇪-ሳዑዲ አረቢያ በአልዳፍራ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባራካህ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ የተፈፀመውን የድሮን ጥቃት "የአካባቢውን ደህንነት እና መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥል" በማለት በጽኑ አውግዛለች።
4 300
!!️🇺🇸🇮🇷 ዩ ኤስ ኢራን ድርድሩን መቋጨት የምትችለው እነዚህን አምስት ቅድመ ሁኔታዎችን ስታሟላ ነው ብላለች - ፋርስ።
️የዋሽንግተን ቅድመ- ሁኔታዎች:
➖ US ምንም አይነት ካሳ ወይም ጉዳት ለመክፈል ፈቃደኛ አትሆንም።
➖400 ኪሎ ግራም ዩራኒየም ከኢራን ወደ አሜሪካ መላክ እና ማስተላለፍ ያስፈልጋል።
➖በኢራን ውስጥ የአንድ የኑክሌር ተቋም ብቻ ሥራ እንዲሠራ ይፈቀዳል። የቀሩት ሁሉ መዘጋት ይኖርባቸዋል።
➖የታገዱ የኢራን ንብረቶችን 25% እንኳን ለመመለስ ፈቃደኞች አንሆንሞ።
➖በሁሉም ግንባሮች ጦርነት ማቆም የሚቻለው ድርድሩ ከተጀመረ በኋላ ብቻ ነው።
**
ኢራን እነዚህን ሁኔታዎች ብታሟላ እንኳ፣ የአሜሪካ እና የእስራኤል የጥቃት ስጋት ይቀንሳል ተብሎ አይገመትም። በዛ በኩል ዋስትና ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም።
የኢራን አቋም የዚህ ግልባጭ ነው። በዋነኝነት በአራት ሁኔታዎች ዙሪያ ያተኩራል። ኢራን፡ አሜሪካ ከአካባቢው ሙሉ ለሙሉ ለቅቃ እንድትወጣ ትፈልጋለች፣ የታገዱባት ንብረቶች በሙሉ እንዲመለስላት ትሻለች፣ አሜሪካና እስራኤል ዳግመኛ እጃቸውን ኢራን ላይ ላለ ማንሳት እንዲፈርሙ እና እስራኤል ከሊባኖስ ለቅቃ እንድትወጣ በዋነኝነት የሚጠይቋቸው ናቸው።
ኢራን የሚሰማት ጦርነቱን በበላይነት እንደተወጣችው ነው፣ በመሆኑም የምታቀርባቸው ቅድመ ሁኔታዎቿ ያንን የሚያሳዩ ናቸው። (እነ አሜሪካ White Flag እንዲያውለበልቡ ትፈልጋለች)።
የትራምፕ መንግሥት ኢራን ይሄን አቋማን እንድታንፀባርቅ ክፍተት የከፈተ መሆኑ በሀገር ቤት ብዙ ትችቶች እንዲነሱበት፣ በእርግጥም ኢራን በበላይነት ጦርነቱን ተወጥታለች እንዲባል ሆኗል።
እናም ይህ አዲሱ የአሜሪካ ቅድመ ሁኔታ ያንን ትችት ለማዳፈን የታሰበ ነው።
4 300
🇺🇸🇮🇷⚡️ — ፕሬዝዳንት ትራምፕ በTruth Social በኩል፦
ለኢራን፣ ሰዓቱ እየጠበበ ነው፣ እናም በፍጥነት ቢንቀሳቀሱ ይሻላቸዋል። ያ ካልሆነ፣ ከእነሱ ምንም ነገር እንዳይቀር ይሆናል።
ጊዜ ወሳኝ ነው!
4 300
🇮🇱⚡- የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ወታደራዊ አመራሮች የተካተቱበት ዝግ የካቢኔ ስብሰባ መምራት ጀምሯል።
4 300
🇺🇸🇮🇱⚡️- ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ዛሬ ማታ ንግግር ለማድረግ ቀጠሮ አላቸው።
4 300
🇮🇷⚡️🇺🇸 ጋዜጠኛ፡ 'ስለዚህ በኢራን የኃይል መሠረተ ልማት ላይ ጥቃት እንዲደረግ እየጠየቁ ነው?'
ሊንድሲ ግራሃም፦ 'አዎ፣ ይህንን አገዛዝ ለመጉዳት ጥሪ እያቀረብኩ ነው።'
'በበቂ ሁኔታ በደንብ ከጎዳችኋቸው ምናልባት ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ።'
4 300
—❗🇨🇺/🇮🇷/🇺🇸 ይህ አሜሪካውያን ሦስተኛ ዙር የኢራን ጦርነትን ለአሜሪካ ህዝብ ለመሸጥ እየሞከሩ ሊሆን ይችላል።
ከመጨረሻው የረመዳን ጦርነት ከጥቂት ቀናት በፊት፣ AXIOS እንዲሁ ኢራን አሜሪካ ሊደርሱ የሚችሉ አህጉራዊ ባሊስቲክ ሚሳይሎችን እየሠራች መሆኑን ዘግቦ ነበር።
በነገራችን ላይ፣ የአይሁዶች የሻቩኦት በዓል ከአራት ቀናት በኋላ ነው።
4 300
❗️❗️🇺🇸❗️ትራምፕ ዛሬ ይገኝባቸዋል ተብለው የሚጠበቁትን ሁሉንም ይፋዊ ዝግጅቶችን መሰረዙ የታወቀ ሲሆን፣ በምትኩ፣ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በኢራን ላይ በሚደረግ የደህንነት ስብሰባ ላይ ይሳተፋል።
4 300
—❗🇨🇺/🇮🇷/🇺🇸 ትኩስ፦ ኩባ ከ300 በላይ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን ተቀብላለች፣ ምናልባትም ከኢራን እና ከሩሲያ የተገኙ ሊሆኑ ይችላሉ፣ እናም በደሴቲቱ ላይ የአሜሪካ ጥቃት ቢደርስ፣ በጓንታናሞ ቤይ የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ማዕከልን ጨምሮ፣ በአሜሪካ ወታደራዊ መርከቦች እና በፍሎሪዳ የባህር ዳርቻ ላይ ለመጠቀም እየተዘጋጀች ነው – Axios
4 300
🇦🇪 | የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ 3 ድሮኖች “ከምዕራብ” ወደ ግዛቷ መግባታቸውን እና አንድ ድሮን በአል ዳፍራ ክልል ውስጥ ከሚገኘው የባራካ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ውጫዊ ወሰን ውስጥ የኤሌክትሪክ ጄነሬተሬ መምታቱን ተናግራለች።
ጠዋት በዚሁ አካባቢ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ ተከስቶ የነበር ሲሆን እስከ አሁን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አደጋውን ለመቆጣጠር እየጣሩ ናቸው።
የ"ምዕራብ ክልል" ማለት ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራቅ ወይም የመን ሊሆን ይችላል።
4 300
🇮🇷⚡️የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር፣ ዛሬ፣ እስራኤልን "በሽብር የምትኖር ሽብርተኛ ሀገር" ብሎ በጠራበት ደብዳቤው፣ የሐማስን መሪ ግድያ በጽኑ አውግዟል።
4 300
🇮🇷🇺🇸🇮🇱 (ኢራን) The Wall Street Journal፦ በኢራን ላይ የተካሄደው ጦርነት በዓለም ላይ የድንጋይ ከሰል ፍላጎትን ጨምሯል።
🔹የሆርሙዝ መተላለፊያ ወሽመጥ መዘጋት ጋር የኃይል አማራጭ ምንጮችን ሲፈልጉ የነበሩ ሀገራት፣ አሁን ፊታቸውን ወደ ድንጋይ ከሰል አዙረዋል፣ በዚህም ፍላጎቱ ጨምሯል።
የአሜሪካ የድንጋይ ከሰል አውጪ ኩባንያዎች፣ የገበያው ፍላጎት አጨናንቋቸው ይገኛል፣ ከሀገር አቅርቦት ውጭ፣ የሚልኩት እጥፍ ዕድገት አሳይቷል ተብሏል።
በአሜሪካ ከተፈጥሮ ጋር ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ የድንጋይ ከሰል እንደሆነ ይታወቃል።
4 300
🇮🇷⚡️🇺🇸 በኢራን ወገን በኩል ያሉ ተንታኞች እና የቀጠናው ባለሙያዎች፣ በኢራን ላይ ጦርነቱ ዳግም ሊተረኮስ አንድ ሐሙስ እንደቀረው ነው እያወሩ ያሉት።
"እንመታ ይሆናል፣ እንሞት እንጠፋም ይሆናል፣ ነገር ግን ቀጠናውን ይዘን አብረን ለመጥፋት ነው የምንሞክረው"፣ በማለት ላይ ናቸው። ማንም ሞቱ ማንም አይቀራትም ፖሊሲ ላይ ደርሰዋል።
**
"በቴህራን፣ ግጭት የማይቀር እና በጣም ቅርብ መሆኑን የሚያሳይ የመጨረሻ እምነት የተደረሰበት ይመስላል።
"በዚህ መሠረት፣ አዲስ የዒላማ ክምችት ተዘጋጅቷል። በዋነኝነት በ UAE ፣ ኩዌት ፣ ባህሬን እና ከዚያ ባሻገር፣ ከፓኪስታን እና ከኩርድስታን ጎን ለጎን ለድንበር ዛቻዎች ዝግጅቶች፣ እንዲሁም ካርግ እና አቡ ሙሳ ደሴት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን ጨምሮ ከብዙ ድንበሮች ጦርነት የመፈጠር እድል ላይ ያተኮረ ነው ።
"ይህ በኢራን ላይ የሚደረግ የመጨረሻው የጥቃት ደረጃ ሊሆን የሚችልበት እድል እየጨመረ ነው፣ ይህም በሚያሳዝን ሁኔታ ከፍተኛ የአመራር ደረጃዎችን ጨምሮ የዋና ዋና ግለሰቦችን ሰማዕትነት ሊያካትት ይችላል።
"ነገር ግን፣ ግምቶች እንደሚያመለክቱት ኢራን ለማስፈራሪያዎች ወይም ለጥቃቶች አትሸነፍም። ከባድ ኪሳራዎች ቢደርሱባትም፣ አሸናፊ ለመሆን ትሞክራለች፣ ይህም ደግሞ የሚያስከትለው ውድመት በባህረ ሰላጤው ሀገራት ውስጥ በእኩል ወይም ከዚያም በበለጠ ከባድ ሊሆን ይችላል።"
