🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
前往频道在 Telegram
显示更多
未指定国家未指定类别
1 373
订阅者
+22724 小时
+3587 天
+63430 天
帖子存档
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት
☎️ የመጀመሪያው ፕሮግራም
🎙በወንድም አቡ አመቲ ረህማን
📚 የቁረአን ሰዎች እንሁን
ተ
ጀ
መ
ረ
ገባ ገባ በሉ ሊንኩን ሸር ሸር አድርጉት
https://t.me/Ye_ewqet_Seleda_link
https://t.me/Ye_ewqet_Seleda_link
Repost from []سَكِينَةُ الْقُلُوبِ ሰኪነቱል-ቁሉብ[]
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ እህቶች በሴት ኡስታዛ ቁርአንን በተጅዊድ ልቅም አድርጋችሁ መቅራት ምትፈልጉ ... ተአሉ ይሄ እድል ሳያመልጣችሁ 🎀
@Bint_Aliy54 በዚህ ኑ ልውሰዳችሁ
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የደርስ ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት
«نُورُ التَّوْحِيدِ وَظُلُمَاتُ الشِّرْكِ»
ኑሩ ተውሂዲ ወዙሉማቱ ሽርኪ)
🎙ወንድም አቡ ኢምራን መራድ(ሀፊዘሁሏህ)
ተ
ጀ
መ
ረ
ገባ ገባ በሉ ሸር ሸር አድ አድርጉ
https://t.me/sobabilelmesjide?videochat=c14fc8baf86aeb1060
🌷ሴት ልጅ ከወንድ ምን ትፈልጋለች?
ሴት ከወንድ የምትፈልገው ብዙ ነገር የሚመስል ቢሆንም፣ የልቧን ሰላም የሚገነባው በአብዛኛው ከወንድ ልጅ የምትፈልገው እውነተኛ ፍቅር፣ እንክብካቤ እና ክብር ነው።
🌹 ① ሴትነቷን የሚወድላት ፍቅር የሚሰጣት ወንድ ትፈልጋለች፦
ሴት ባሏ ሴትነቷን እንዲወድ፣ እንደ ሚስቱ ብቻ ሳይሆን እንደ ተወደደች ሴት እንዲያሳያት ትፈልጋለች።እንደሚወዳት እንዲነግራት፣ በቃሉ እንዲያረጋጋት፣ በአመለካከቱም “አንቺ ለእኔ ልዩ ነሽ” የሚል ስሜት እንዲሰጣት ትፈልጋለች።
እሷ ፍቅርን ስታገኝ የባሏን ወንድነት ታረጋግጣለች፤ እሷም በራሷ ሴትነት ውስጥ በሰላም ትኖራለች ስለዚ ወንድሜ በደንብ ፍቅር ስጣት።
🌿 ② እዝነት እርህራሄና እንክብካቤ ትፈልጋለች፦
ሴት ባሏ የምትወጣውን ድካም እንዲያይላት ትፈልጋለች። ቤትን መጠበቅ፣ ልጆችን ማሳደግ፣ ባሏን መንከባከብ ብዙ ጊዜ ሳይታይ የሚከናወን ትልቅ ሥራ ነው።
አንዳንድ ጊዜ “ደክሞሻል?” ብሎ መጠየቅና፣
●“እኔ አለሁልሽ”አብሽሪ ማለት፣
●በርህራሄ መመልከት፣
●እና በችግሯ ጊዜ ከጎኗ መቆም…
እነዚህ ትንንሽ የሚመስሉ ነገሮች በሴት ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታ ይይዛሉ።
ርህራሄውን ስታገኝ የመልካም ባህሪውን ውበት ትሰማለች፤ እሷም በተቻላት መጠን ባሏን፣ ልጆቿንና ቤቷን በፍቅር ትንከባከባለች።
👑 ③ አንተን እንዲታከብርህ እንደምትፈልገው እሷም ካንተ ክብር ትፈልጋለች፦
ሴት በቤቷ ውስጥ ክብር እንዲሰጣት ትፈልጋለች። ባሏ በሰዎች ፊት እንዳያዋርዳት፣ ስህተቷን በማዋረድ እንዳያስተካክል፣ ስሜቷንም እንዳይንቅ ትፈልጋለች። ክብር ማለት ሴትን ሁልጊዜ ትክክል ናት ማለት አይደለም፤ ስትሳሳት እንኳን ክብሯን ሳታስነካ ማስተካከል ነው።
እሷ በባሏ ዘንድ ክብር ስታገኝ፣ እሷም በልቧ ታከብረዋለች። እሱን የቤቷ መሪ እንደሆነ ታውቃለች፣ ነገር ግን መሪነትን ከጭካኔ ጋር አታያይዘውም።
🌹 ጀግናው ወንድሜ አስታውስ…
ሴት ሁልጊዜ ውድ ስጦታ ወይም ብዙ ገንዘብ ብቻ አትፈልግም። አንዳንዴ የምትፈልገው ከባሏ አጠገብ ተቀምጣ “እኔ የምወደው ሰው አለኝ፣ የሚያከብረኝም ሰው አለኝ፣ በችግሬም የሚያግዘኝ ሰው አለኝ” ብላ በልቧ ሰላም ማግኘት ነው።
ያን ጊዜ.....
●ፍቅር ልቧን ያሞቀዋል፤
●ርህራሄ ልቧን ያሳርፈዋል፤
●ክብር ደግሞ በቤቷ ውስጥ ደህንነት ይሰጣታል።እና ባልም ሚስቱን ሲወድ፣ ሲያዝንላት፣ ሲያከብራትና ሲንከባከባት፣ ቤታቸው የግድግዳና የእቃ ቤት ብቻ አይሆንም፤ የፍቅር፣ የሰላምና የርህራሄ መኖሪያ ይሆናል። 🌷🏡
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
የፍቺ ጉዳይ
~
በኢስላም የፍቺ ጉዳይ ልቅና ገደብ የለሽ አይደለም። ሶስት ፍቺ የፈፀመ ሰው ዳግም ሚስቱን ለመመለስ ነገሩ ከባድ ነው። ባጭሩ ሸርጡን ባሟላ ኒካሕ ሌላ ሰው አግብታ የተፈታች ከሆነ ነው የመጀመሪያው መመለስ የሚችለው። አንድ ሰው ለመጀመሪያው ባል ሐላል ለማድረግ አስቦ ቢያገባት ራሱ ድርጊቱ ከባድ ወንጀል ከመሆኑም ጋር ለመጀመሪያውም ባል ሐላል ማድረግ አይችልም፡፡
እንዲህ አይነት ጣጣ እንዳይገጥም ፍቺ ውስጥ ከመግባት በፊት ቀድሞ ደግሞ ደጋግሞ ማሰብ ይገባል። እለታዊ ግጭቶች ያልፋሉ። ነገሮች ሲበርዱ ቁጭት ሊከተል ይችላል። ፍቺ ቀላል ነገር አይደለም። የሚከተሉት ውሳኔዎች ይኖራሉ። በተለይ ልጆች ሲኖሩ ተፅእኖው ከባድ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ፍቺን እለታዊ ግጭትን ሰበብ በማድረግ ሳይሆን በጥልቀት ካሰቡ በኋላ መፈፀም ይሻላል። በችኮላ ኒካሕ አውርደው ከዚያ መውጫ ቀዳዳ ፍለጋ የሚባዝኑ፣ ተጨንቀው የሚያስጨንቁ ብዙ ሰዎች አሉ። "ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ፣ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ" ይሆናል ነገሩ።
በነገራችን ላይ ፍቺን ዑለማኦች ለሁለት ይከፍሉታል፣ ሱናዊ የሆነ እና ቢድዐዊ በመሆኑ የተወገዘ ብለው። እውነታው ይህ ከሆነ ሱናውን የጠበቀ የፍቺ ስርዓትን መለየት ያስፈልጋል ማለት ነው። ይህም ሴቷ ከወር አበባ ንፁህ በሆነችበት ወቅት ላይ፣ ግንኙነት ሳይፈፀም በፊት የሚፈፀም ፍቺ ነው። ሁለት መስፈርቶች አሉት ማለት ነው።
1ኛ:- ሚስት ከወር አበባ ንፁህ መሆን አለባት። በወር አበባ ወቅት ላይ ፍቺ መፈፀም ጥፋት ነው።
2ኛ፦ በንፅህናዋ ወቅትም ቢሆን ግንኙነት ሳይፈፀም በፊት መሆን አለበት። በዚህ የንፅና ወቅት ላይ ግንኙነት ተፈጽሞ ከሆነ፣ ፍቺ ቢያስብ የወር አበባ እስከሚመጣ መጠበቅ ይኖርበታል። ከዚያ ከወር አበባዋ ንፁህ ስትሆን የፍቺ ውሳኔው እንዳለ ከሆነ ግንኙነት ሳይፈፅም በፊት ፍቺውን መፈፀም ይችላል።
ይሄ ሂደት የፍቺውን ውሳኔ በወቅታዊ ግጭት በደመነፍስ እንዳይፈፀም ማሰቢያ ጊዜ ይሰጣል። ይሄ ሂደት ቢጠበቅ ስንት ትዳር በወቅታዊ ግጭት ሰበብ ከመፍረስ እንደሚድን አስቡት።
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 10/2018)
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
🌸اذكار الصباح🌸
▪️አዝካሩ ሰባህ
➱➱➱➱➱➱➱
➲የጧት ዚክርوَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ፡
#ብልህ ሴት
የአላህ መልዕክተኛ { ﷺ } እንዲህ ብለዋል፦
«መልካም ሴት #ባለቤቷ ወደ እሷ ሲመለከታት #የምታስደስተው ናት!»ብለዋል።
ዛሬ አብዛኛዎቹ ሴቶች የሚዋቡት ለሠርግ አሊያም ለፕሮግራም ጭራሽ ደግሞ አንዳንዶች መንገድ ላይ እንዲሁም በየሱቁ ላሉ ወንዶች ለመታየት ይዋባሉ።
እንዲህ አይነቶቹ ደግሞ ለባሎቻቸው መዋብን በቤት ውስጥ ፍፁም የዘነጉ ናቸው ።
ሷሊህ የሆነች ሴት የትና መቼ መዋብ እንዳለበት ታውቃለች።
= t.me/FKR_ESKE_JENET
ሞት
☞ ዛሬ ለሞቱት አልቃሽ ነገ በተራው ይለቀስበታል።
☞ የዛሬ ሬሳ ባይ በተራው ጀናዛ ይባላል።
☞ የዛሬ ሟች አጣቢ ተራው ሙቶ ይታጠባል።
☞በሬሳ ላይ ሰጋጅ በተራው ይሰገድበታል።
☞የዛሬ ቀብር ቆፋሪ በሌላ ጊዜ ለራሱ ይቆፈርለታል።
☞የዛሬ ቀባሪ በተራው ይቀበራል።
ወደድንም ጠላን የሚሆነው ይህ ነው። እድለኛ ማለት ከዱንያው በላይ ለአሄራው የሚለፋና ሞት እንዳለበት አውቆ ሁሌም በተጠንቀቅ የሚዘጋጅ ነው።
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የደርስ ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት
በኡስታዝ አበል ሁበይብ
መንሀጅ ፊርቀቱል ነጂያ ደርስ
ተ
ጀ
መ
ረ
ገባ ገባ በሉ ሸር ሸር አድ
t.me/sobabilelmesjide?videochat=c42e18a35fffc2daf4
ኢማን በልብ ነው… ወይስ በተግባር?
ብዙ ጊዜ ሀቅንና መመሪያን ስናስታውስ የምንሰማው የተለመደ ምላሽ አለ እሱም «ኢማን በልብ ነው የሚል»
እህቴ ሆይ፦ ሂጃብሽን አስተካክይ አላህና ረሱል ﷺ ባዘዙት መልኩ ልበሺ ስትባይ፣ «ኢማን በልብ ነው» ትያለሽ።
ወንድሜ ሆይ፦ አለባበስህን አስተካክል፣ ሱሪህንም ከቁርጭምጭሚትህ በላይ አሳጥር ፀጉርክንም አስተካክለክ ተቆረጥ ወ.ዘ.ተ ስትባል፣ አንተም «ኢማን በልብ ነው» ትላለክ።
እውነት እንነጋገር ከተባለ ግን…
በልባችን ያለው ኢማን ወደ ውጪ በተግባር መታየት አይገባውምን?
እውነተኛ ኢማን በልብ ብቻ ታስሮ የሚቀር አይደለም፤ በንግግርና በተግባርም መገለጥ አለበት።
እስቲ ራሳችንን እንመርምር፦
የምንሰጠው “ኢማን በልብ ነው” የሚለው መልስ እውነትን ለመከተል ነው? ወይስ ከሚከብደን ትእዛዝ ለመሸሽ?
መልሱን ለራሳችን እንተወው።
አላህዬ ይዘንልን፣ ኢማናችንንም በቃልና በተግባር የሚገለጥ ያድርግልን
https://t.me/Sekinetul_Qulub_Channel
https://t.me/Sekinetul_Qulub_Channel
Repost from []سَكِينَةُ الْقُلُوبِ ሰኪነቱል-ቁሉብ[]
ኢማን በልብ ነው… ወይስ በተግባር?
ብዙ ጊዜ ሀቅንና መመሪያን ስናስታውስ የምንሰማው የተለመደ ምላሽ አለ እሱም «ኢማን በልብ ነው የሚል»
እህቴ ሆይ፦ ሂጃብሽን አስተካክይ አላህና ረሱል ﷺ ባዘዙት መልኩ ልበሺ ስትባይ፣ «ኢማን በልብ ነው» ትያለሽ።
ወንድሜ ሆይ፦ አለባበስህን አስተካክል፣ ሱሪህንም ከቁርጭምጭሚትህ በላይ አሳጥር ፀጉርክንም አስተካክለክ ተቆረጥ ወ.ዘ.ተ ስትባል፣ አንተም «ኢማን በልብ ነው» ትላለክ።
እውነት እንነጋገር ከተባለ ግን…
በልባችን ያለው ኢማን ወደ ውጪ በተግባር መታየት አይገባውምን?
እውነተኛ ኢማን በልብ ብቻ ታስሮ የሚቀር አይደለም፤ በንግግርና በተግባርም መገለጥ አለበት።
እስቲ ራሳችንን እንመርምር፦
የምንሰጠው “ኢማን በልብ ነው” የሚለው መልስ እውነትን ለመከተል ነው? ወይስ ከሚከብደን ትእዛዝ ለመሸሽ?
መልሱን ለራሳችን እንተወው።
አላህዬ ይዘንልን፣ ኢማናችንንም በቃልና በተግባር የሚገለጥ ያድርግልን
https://t.me/Sekinetul_Qulub_Channel
https://t.me/Sekinetul_Qulub_Channel
🌿 حِكْمَةُ امْرَأَةٍ ذَكِيَّةٍ (የአንዲት ብልህ ሴት ጥበብ)
رَأَى رَجُلٌ امْرَأَةً فِي الطَّرِيقِ فَقَالَ لَهَا: مَا رَأَيْتُ فِي حَيَاتِي أَجْمَلَ مِنْكِ
አንድ ወንድ መንገድ ላይ አንዲት ሴት አይቶ "በሕይወቴ ካንቺ የበለጠ ቆንጆ አይቼ አላውቅም" በማለት አድናቆቱን ገለጸላት
فَقَالَتْ: لَوْ رَأَيْتَ أُخْتِي، فَهِيَ قَادِمَةٌ خَلْفِي، وَهِيَ أَجْمَلُ مِنِّي
እርሷም ብልህ ነበረችና የልቡን እውነተኝነት ለመፈተን "ከኋላዬ የምትመጣውን እህቴን ብታያትስ? እርሷ ከእኔ እጅግ ትበልጣለች (ትቆነጃለች)" በማለት መለሰችለት
فَالْتَفَتَ، فَلَمْ يَرَ أَحَدًا
እርሱም እናንተ እንደምትገምቱት ከኋላው የተሻለች ቆንጆ ፍለጋ ዞር ብሎ ሲመለከት ግን ማንንም አላገኘም
فَقَالَتْ: أَيُّهَا الْكَاذِبُ فِي دَعْوَاهُ، لَوْ صَدَقْتَ فِيمَا قُلْتَ مَا الْتَفَتَّ
በዚህ ጊዜ ሴቲቱ እንዲህ ባለ ጥልቅ ጥበብ መከረችው፦ "አንተ በንግግርህ ውሸታም የሆንክ ሰው ሆይ! በተናገርከው ቃል እውነትህን ብትሆንና 'ካንቺ በላይ ቆንጆ የለም' ብለህ በእውነት አምነህ ቢሆን ኖሮ፤ የተሻለ ፍለጋ በፍጹም ዞር ብለህ አትመለከትም ነበር" በማለት የፍቅሩን ግብዝነት አጋለጠችው
እኛም ከዚህ የምንረዳው እውነተኛ ውዴታ ባገኘው ነገር የሚረካ እንጂ ሁሌም "የተሻለ" ፍለጋ ዓይኑን የሚያንከራትት አለመሆኑን ነው
ብዙ ወንዶች ይከተሉሻል ማለት ቆንጆ ነሽ ማለት አይደለም ለተራበ ሰው ሽሮም ክትፎ ነው
አስቸኳይ ድጋፍ ለወዳጆቼ! ✨
ከታች ያለውን ሊንክ ተጠቅማችሁ ቻናሉን Join በማድረግ ብቻ የ100 Telegram Stars አሸናፊ እንድሆን ልትረዱኝ ትችላላችሁ!
የእናንተ አንዲት ሰከንድ ለእኔ ትልቅ ዕድል ናት፤ ሊንኩን ተጭናችሁ ተቀላቀሉልኝ:
👉 https://t.me/+z82bjSmByxszN2M0
ስለ ትብብራችሁ ከልብ አመሰግናለሁ! ⭐️
ኡሙ ሓቲም
