ar
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
3 222
المشتركون
+2224 ساعات
+2707 أيام
+65730 أيام
أرشيف المشاركات
ብሬን ተኳሿ...ፋኖ መሠረት! "የአዲስ አበባ ነዋሪ ነበርኩ። በከተማዋ"ህገ ወጥ" በሚል ስም የአማራ ተወላጆች ቤት እየተመረጠ ሲፈርስና በዚህም በርካታ የአማራ ተወላጆች ጎዳና ላይ ሲወድቁ ቆሜ ማየት
+1
ብሬን ተኳሿ...ፋኖ መሠረት! "የአዲስ አበባ ነዋሪ ነበርኩ። በከተማዋ"ህገ ወጥ" በሚል ስም የአማራ ተወላጆች ቤት እየተመረጠ ሲፈርስና በዚህም በርካታ የአማራ ተወላጆች ጎዳና ላይ ሲወድቁ ቆሜ ማየት አልቻልኩም። ይሄንን ፀረ አማራ ስዓት ለመገርሰስ ከሁለት ዓመት በፊት ፋኖን ተቀላቀልኩኝ። በአሁን ሰዓት በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር 21ኛ ክፍለጦር ብሬን ምድብተኛ ሆኜ እየታገልኩ ነው) "...አርቀህ አታሳደው፡ የተመለሰ እንደው መከራው ላንተ ነው" እንዲሉ አበው፡ አዲስ አበባ ላይ አትኖሩም ተብለው ተገፍተው በረሃ የወረዱት እነዛ ጀግኖች፣ ዛሬ በጦር ግንባር ላይ ጠላትን የሚያርበደብዱት እነሱው ናቸው።  ገፊው አካል ገፍቶ መጨረሻው ላይ ስላደረሳቸው፡ ዛሬ ተመልሰው እየመጡ ነው። የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት #የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ብሬን ተኳሿ...ፋኖ መሠረት! "የአዲስ አበባ ነዋሪ ነበርኩ። በከተማዋ"ህገ ወጥ" በሚል ስም የአማራ ተወላጆች ቤት እየተመረጠ ሲፈርስና በዚህም በርካታ የአማራ ተወላጆች ጎዳና ላይ ሲወድቁ ቆሜ ማየት
+1
ብሬን ተኳሿ...ፋኖ መሠረት! "የአዲስ አበባ ነዋሪ ነበርኩ። በከተማዋ"ህገ ወጥ" በሚል ስም የአማራ ተወላጆች ቤት እየተመረጠ ሲፈርስና በዚህም በርካታ የአማራ ተወላጆች ጎዳና ላይ ሲወድቁ ቆሜ ማየት አልቻልኩም። ይሄንን ፀረ አማራ ስዓት ለመገርሰስ ከሁለት ዓመት በፊት ፋኖን ተቀላቀልኩኝ። በአሁን ሰዓት በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር 21ኛ ክፍለጦር ብሬን ምድብተኛ ሆኜ እየታገልኩ ነው) "...አርቀህ አታሳደው፡ የተመለሰ እንደው መከራው ላንተ ነው" እንዲሉ አበው፡ አዲስ አበባ ላይ አትኖሩም ተብለው ተገፍተው በረሃ የወረዱት እነዛ ጀግኖች፣ ዛሬ በጦር ግንባር ላይ ጠላትን የሚያርበደብዱት እነሱው ናቸው። ገፊው አካል ገፍቶ መጨረሻው ላይ ስላደረሳቸው፡ ዛሬ ተመልሰው እየመጡ ነው።

አሳዛኝ የአፈና ዜና መርሻ ትባላለች የደ/ብርሃንከተማ ልጅ ነች።በደቂቀ-ዘርዓያዕቆብ ማህበር ብዙ መንፈሳዊ ተግባራትን ስታስተባብር ብዙዎች ያውቋታል። በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ለማንነቷ ከአማራ ልዩ ሀይል
አሳዛኝ የአፈና ዜና መርሻ ትባላለች የደ/ብርሃንከተማ ልጅ ነች።በደቂቀ-ዘርዓያዕቆብ ማህበር ብዙ መንፈሳዊ ተግባራትን ስታስተባብር ብዙዎች ያውቋታል። በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ለማንነቷ ከአማራ ልዩ ሀይል እስከ ፋኖ ከነፍስ ወከፍ እስከ ቡድን መሳሪያ ጭምር በመያዝ ከጠላት ጋር ግንባር ለግንባር የምትፋለም የሸዋረገድ ገድሌ መንፈስ ወራሽ ሴት አርበኛ ነበረች። ታድያ ከቅርብ ግዜ ወድህ ከትግል እርቃ ትዳር መስርታ የግል ህይወቷን እየመራች ብትገኝም በደቂቀ-ዘርዓያዕቆብ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዋና በደ/ብርሃን የከተማ ሰላማዊ ትግል ወቅት ከፍተኛ ጫና አሳድራብናለች በሚል ቂምና በቀልተኝነት የቀድሞው ጓዶቿን መሰዋት ተከትሎ ሀዘንሽን በሚዳ ገልጸሻል በሚል የሰ/ሸዋ ዞንና ደ/ብርሃን ከተማ የኦዴድ ብልፅግና አሽከሮች እህታችንን ከሰወሯት ሰንብተዋል።ይገርማል ሀዘን እንኳ መግለጽ የማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ነው አማራ የሚገኘው። pls ሁላችንም ለእህታችን ድምጽ እንሁናት!!!

ሰበር የድል ዜና !! ቀን 12/8/2018ዓ.ም 🔸208ኛ ኮር በሰሜን ጎንደር በአዲያርቃይ ወረዳ በዛሪማ ግንባር ከ60በላይ ጠላት በመደ*ም*ሰስ ድል አደረገ! የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ
ሰበር የድል ዜና !!          ቀን 12/8/2018ዓ.ም 🔸208ኛ ኮር በሰሜን ጎንደር በአዲያርቃይ ወረዳ  በዛሪማ ግንባር ከ60በላይ ጠላት በመደ*ም*ሰስ ድል አደረገ! የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ ዕዝ 208ኛ ኮር  ከድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለጦር እና ከጭና ክፍለጦር የተወጣጡ አህዶች በጥምረት ጠላት ከዛሪማ ወደ ብስኒት  እና ወደ ጥራዒና ቀበሌዎች ቀጠና በማምራት የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ በማቀድ  በሁለት አቅጣጫ  የተንቀሳቀሰውን ጠላት ተከላክሎ መልሶ በማጥቃት  ድባቅ በመም*ታት አቅዱን ከሽፎበት ሙት እና ቁስ*ለኛውን ተሸክሞ ወደ መጣበት ቢመለስም ማምለጥ ያልቻለ ሀይል ተራራ ተሰቅሎ በጀግናው ሰራዊታችን  ተከቦ ይገኛል። በዚህ አውደውጊያ  በስም ያላረጋገጥነው አንድ ኮለኔልን እንዲሁም የሻለቃ አዛዦችን ጨምሮ በርካታ ሰራዊቱን አስ*ደምስሶ ሙት እና ቁስለኛውን እያዝረከረከ  እያፈገፈገ ወደመጣበት ለማምለጥ እየተፍጨረ*ጨረ ይገኛል። በአውደ ውጊያው የተገኙ ድሎች :- ✅ ከ40በላይ የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ የመከላከያ ሰራዊት መግ*Deደል ተችሏል! ✅ከ20በላይ የሰላም አስከባሪ እና የሚኒሻ ሰራዊት መግ*Deል  ተችሏል! ✅ አንድ የአዲርቃይ ወረዳ የምርጫ አስተባባሪ አመራር ተገድ*ሏል! ✅ሁለት ኦራል እና አንድ አይሱዚ ቁስ*ለኛ ወደ ደባርቅ እና አዲያርቃይ  ሆስፒታል ገብቷል! ✅ከ38በላይ የነብስ ወከፍ ክላሽ እንዲሁም ያልተቆጠረ በርካታ ልዩ ልዩ ተተኳሽ ተማ**ርኳል! ውጊያው እንደተጠናቀቀ ሙሉ መረጃዎችን ይዘን የምንመለስ ይሆናል! ህልውናችን በተባባረ ክንዳችን ! የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ የ208ኛ ኮር ወታደራዊ ቃል አቀባይ አርበኛ ሳሙኤል አበራ ! ድል ለአማራ ፋኖ

🔥ከተድባበ ማርያም ገዳም በቅርብ ርቀት በሚገኝ በአንድ ቤተክርስቲያን ላይ የተፈፀመ የመድፍ ድብደባ‼️ ይህ የምታዩት የመድፍ ቅምቡላ ያለፈው መጋቢት ወር መጨረሻዎቹ ቀናት ላይ በአማራ ሳይንት ወረዳ 015 ደብተራ ቀበሌ በሚገኘው አድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ላይ የአገዛዙ ወታደሮች ያስወነጨፉት ቅምቡላ ነው። አድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ገዳም በቅርብ ርቀት የሚገኝ ቤተክርስቲያን ነው። የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ተላላኪ መከላከያ ሰራዊቱ በአጅባር ከተማ ባጠመደው መድፍ ነው መጋቢት 27/ 2018 ዓ/ም የአድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንን ኢላማ በማድረግ ጥቃት የፈፀመበት። ጥቃቱ በቤተክርስቲያኑ ላይ ለጊዜው ከባድ ጉዳት ባያደርስም፡ ነገር ግን የአገዛዙ ወታደሮች በአከባቢው የሚፈፅሙት ድብደባ ተባብሶ መቀጠሉን የመረብ ሚዲያ የቀጠናው ዘጋቢ ለማረጋገጥ ተችሏል። 12/ዐ8/2018 ዓ.ም

አርበኛ ዘመነ ካሤ 2013 ላይ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ንግግር ሊያደርግ በተጋበዘበት ወቅት የተነሳት ምስል🫶🫰 "ወይድ አንተ አትንገረኝ ማንነቷን፣ ምጥ አታስተምርም ልጅ እናቷን። ወይድ አንተ
አርበኛ ዘመነ ካሤ 2013 ላይ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ንግግር ሊያደርግ በተጋበዘበት ወቅት የተነሳት ምስል🫶🫰 "ወይድ አንተ አትንገረኝ ማንነቷን፣ ምጥ አታስተምርም ልጅ እናቷን። ወይድ አንተ ላንሳበት ባንድራዬን፣ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ አርማዬን።"

የፌደራል ፖሊስ በፖለቲካ እና ሕሊና እስረኞች ላይ እየፈፀመ ያለው ግፍ በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው እና በአባሪዎቻቸው ላይ ለተፈፀመው የሰብአዊ መብት ጥሰትን አጣራ የተባለው የፌደራል ፖሊስ ብዙዎችን ያሳዘነ እና ያስቆጣ ምላሽ ሰጥቷል ፤ ~ ገብቼ እንዳላጣራ ማ/ቤቱ የፍ/ቤት ትዕዛዝ ካላመጣህ በሚል ከልክሎኛል በማለት በግፍ እስረኞች ቁስል ላይ ተሳልቋል። ከሕግ ውጭ የቂሊንጦ ማ/ቤት አስተዳደር ሳይፈቅድ ዘሎ በመግባት በፀረ አማራው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ለከት የለሽ ጥላቻ ምክንያት ለዓመታት በግፍ እስር ላይ በሚገኙ የፖለቲካ እና ሕሊና እስረኞች ላይ አፈና ፣ ብርበራ ፣ ማንነት ተኮር ስድብ እና ዛቻ እየፈፀመ ያለውን ፌደራል ፖሊስ ወክለው ሚያዝያ 8/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሕገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት የተገኙት ረዳት ኢንስፔክተር አሳዬ ዋለ ናቸው ወደ ቂሊንጦ ገብቶ ለመመርመር የፍ/ቤት ትዕዛዝ የጠየቁት። ይህን አሳዛኝ እና አስቂኝ ድራማ የተናገሩት ኢንስፔክተሩ የላካቸው ፌደራል ፖሊስ ከሰኔ 2017 ጀምሮ የቂሊንጦ ማ/ቤት ግቢን ተቆጣጥሮ ከሕግ ውጭ አሁንም ድረስ የማ/ቤቱን የጥበቃ ሚና በመሻማት እና በመናቅ ጭምር በቡድን መሳሪያ እየታገዘ እስረኞችን እየጠበቀ ፣ እየፈተሸ ፣ እየበረበረ ፣ እያጀበ እና ጫናም እያደረሰ መሆኑን አንደበታቸው ባይናገረው ልባቸው ያውቃል። በዋስትና የሚፈቱና ነጻ የሚባሉ በተለይም በሽብር የተከሰሱ አማራዎችን በር ድረስ በመምጣት አፍኖ ሲወስድ እና ተጨማሪ ግፍ እና በደል ሲፈፅም ማ/ቤቱን አስፈቅዶ የማያውቀው ፌደራል ፖሊስ ነው እንግዲህ የእስረኞች ክስ እና አቤቱታ ሲሆን ማ/ቤቱ ገብቼ ምርመራ እንዳላደርግ ከለከለኝ የሚለው። የአገዛዝ የጥላቻ አስፈጻሚ እየሆነ የመጣው ፌደራል ፖሊስ ገለልተኛ ባለመሆኑ እና በእስረኞች ላይ በምርመራ ስም በሚፈፅመው ጥቃት የተገደሉ ፣ አካላቸውን ያጡ እና ለአዕምሮ ሕመም የተዳረጉ ብዙዎች ናቸው። ከሕግ ውጭ የግፍ እስረኞችን ዐይን የሚመታው ፣ ጆሮ የሚያደነቁረው ፣ ጥርስ የሚያወልቀው ፣ ወፌ ላላ ሰቅሎ የሚገርፈው ፌደራል ፖሊስ ለእስረኛ የሚጠቅም ጉዳይ መስሎ ከታየው ምክንያት መፍጠሩ የተለመደ ነው። በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ ተከሳሾች ላይ በአፋር ክልል ሰመራ እና አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካንብ እንዲሁም በአዲስ አበባ ሜክሲኮ በጨለማ ክፍል ለወራት አግቶ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀመው ፌደራል ፖሊስ በጥቃት አድራሾች ላይ የኢሰመኮን ሪፖርት መሰረት አድርጎ የወንጀል ፍሬ ነገሩን እንዲያጣራ ከታዘዘ ከ2 ዓመት በላይ ተቆጥሯል። ይህ አካል ነው እንግዲህ አዲስ የምርመራ አጣሪ ቡድን አቋቁሜ ለመስራት አስቤያለሁ ሲል በተከሳሾች ቁስል ላይ የሚሳለቀው። ይህ ቡድን ነው እንግዲህ ጊዜ የማያልፍ መስሎት ራሱን ከሕግ በላይ በማድረግ ስቃይ እየፈፀመ ያለ ከሕዝብ ይልቅ የጨፍጫፊ ስርዓት አገልጋይ የሆነ አካል ነው ከአገዛዝ ጋር ተጣብቆ ሰዎችን በማንነት መፈረጁ እና ማጥቃቱ ሳያንሰው በግፍ እስረኞች ቁስል ላይ ጨንገር እየሰደደ የሚሳለቀው። ፌደራል ፖሊስ እነ ኢ/ር ድሪባ ሰንበታ በአማራ እና በፖለቲካ እና ሕሊና እስረኞችና ቤተሰቦቻቸው ላይ ፈፀሙት በሚል ከወራት በፊት እንዲያጣራ በሚል የተሰጠውን የፍ/ቤት ትዕዛዝ እስካሁን ባለመፈፀም ፍትህን አርቆ እየቀበራት መሆኑ ግልፅ ነው። መረጃው የአውሎግሶን አንድነት ነው። ልዩ የቴሌግራም ቻናል ጥቆማ‼️ ለፈጣንና ወቅታዊ  ተዓማኒ የግንባር ዉሎ  መረጃዎችን  ለማግኘት የተራራው ሚድያ የቴሌግራም  ቻናላችንን https://t.me/fanoiswinnerlogo21 ይቀላቀሉ👇👇👇 እናመሰግናለን

ከጠላት ካምፕ ሁለት ክላሽ በመያዝ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀለ!! ቡሬ ከተማ ልዩ ስሙ አልካን ካምፕ ከመሸገው የጠላት ሀይል ጋር በመሆን አምባገነኑን የብልፅግና ስርዓት ሲያገ
ከጠላት ካምፕ ሁለት ክላሽ በመያዝ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀለ!! ቡሬ ከተማ ልዩ ስሙ አልካን ካምፕ ከመሸገው የጠላት ሀይል ጋር በመሆን አምባገነኑን የብልፅግና ስርዓት ሲያገለግል የቆየው ፍቃድ አስራት የራሱንና እንዲሁም ባንዳው ልመንህን በቦክስ በመዘረር ሁለት ክላሽ በመያዝ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅሏል፡፡ አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 10/2018

በአምባሰል ተራራዎችና በወረባቦ ግንባር የጠላት ኃይል ድባቅ ተመታ፤ የምኒልክ ዕዝ አሃዶች አንጸባራቂ ድል አስመዘገቡ! በአምባሰል ተራራዎችና በወረባቦ ግንባር የምኒልክ ዕዝ አሃዶች ከፋሽስቱ አገዛዝ ሠራዊትና ተላላኪ ካድሬዎች ጋር ባደረጉት ብርቱ ተጋድሎ፣ በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ ኪሳራ በማድረስ አንጸባራቂ ድል ማስመዝገባቸውን የአፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 104ኛ ኮር የሕዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ። ዛሬ ሚያዝያ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ንጋት 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ በአምባሰል ወረዳ አበት ሰንሰለታማ ተራራዎች ላይ በተደረገው መጠነ ሰፊ አውደ ውጊያ፣ የምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር የ35ኛ ክፍለ ጦር እና የ104ኛ ኮር የ24ኛ ክፍለ ጦር በጥምረት ባከናወኑት ኦፕሬሽን በውል ቁጥሩ ያልታወቀ የአገዛዙ ሠራዊት እርምጃ ተወስዶበታል። የዕዙ አሃዶች በወሰዱት የተቀናጀ የማጥቃት እርምጃ፣ ስትራቴጂካዊ በሆኑት የአበት ተራራዎች ላይ የመሸገው የጠላት ኃይል መፈራረሱ ተገልጿል። በተመሳሳይ መልኩ በወረባቦ ወረዳ በሂጀርሳ ሎሌና ግርድና ግንባር፣ የ101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ ባካሄደው ሌላ አውደ ውጊያ፣ የአገዛዙ ምንጣፍ ጎታች የሆነው የብአዴን ሚሊሻ በሽርጥ ለባሾቹ የፋኖ ኮማንዶዎች አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል። በዚህ ግንባር ከአንድ ቲም በላይ የጠላት ኃይል ሲደመሰስ፣ ከስምንት በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል። ጠላት የቆሰሉ ወታደሮቹን በአምቡላንስ ሰብስቦ ወደ ኃይቅ ከተማ መውሰዱን የአይን እማኞች አረጋግጠዋል። ምኒልክ ዕዝ "መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የሕዝባችን የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል" ሲል ለትግሉ ያለውን ጽኑ አቋም የገለጸ ሲሆን፣ በተባበረ ክንድ የሚመዘገቡት እነዚህ ድሎች የአማራ ሕዝብን ነፃነት እንደሚያፋጥኑ አጽንኦት ሰጥቷል።

የአማራን የህልውና ትግል ከድተው የፋሽሽቱ ብልፅግናን ጎራ የተቀላቀሉት ፍቅሩ እና ፀዳሉ እንደ ቃየል በጎዳናዎች ላይ ሲቅበዘበዙ በካሜራ እይታ ውስጥ እንዲህ ገብተዋል ጥንቃቄ ለመላው የአማራ ህዝብ

በሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በማጀቴ ዙሪያ የአርሶ አደሩ ሰብል በብልፅግና ወሮበላ ኃይሎች የማህበረሰቡ ሰብል እንዲቃጠል ተደረገ!! ​በማጀቴና አካባቢው የሚገኝ አርሶ አደር ለወራት ደክሞና ለፍቶ የሰበሰበው የጤፍ ክምር፣ በገዥው ብልፅግና ሥርዓት ታጣቂዎችና በኦሮሞ ሚሊሻዎች አማካኝነት ሆን ተብሎ እንዲቃጠል ተደረገ። ​ ጥቃቱ የተፈጸመው በመከላከያ ሠራዊት የከባድ መሣሪያ ድጋፍ በሚደረግላቸው የኦሮሞ ሚሊሻዎች ነው። አርሶ አደሩ አርሶ፣ ዘርቶ፣ አርሞና አጭዶ የከመረው ይህ ምርት፤ በሽብርተኝነትና በንብረት ማውደም ዘመቻው እንዲወድም ተደርገ!! ​ የብልፅግና መራሹ ጦርና የኦሮሞ ሚሊሻዎች አማራን ለማጥፋት ግዛታችን ከገቡ ቀን ጀምር የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅታቸው፣ ቂማቸውን በአርሶ አደሩና በሰብሉ ላይ እየተወጡ መሆኑን የሚታወቅ ኃቅ ነው ሆኖም በማጀቴ አካባቢ የሚገኙ በርካታ የጤፍ ክምሮች በእሳት እንዲጋዩ የተደረገ ሲሆን፣ ይህም በአካባቢው ላይ ከፍተኛ የምግብ ዋስትና ችግርና ረሃብ ለመፍጠር የታለመ ሴራ ነው። በተጨማሪም ከኦሮሞ ብሄረሰብ አዋሳኝ ያለው የማጀቴ አርሶ አደር ምሉ ለሙሉ በኦሮሞ የከብት መንጋ እንዲበላ እና እንዲወድም ተደርጓል። አርሶ አደሩ የዓመት ልፋቴ በዓይኔ ፊት ወደመ" በማለት ከፍተኛ ሐዘንና ቁጣቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።​ይህ "የኦሮሙማ አገዛዝ" የዐቢይ አህመድ አስተዳደር፣ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው ስልታዊ የኢኮኖሚ አሻጥርና የንብረት ውድመት ዓለም አቀፍ ሰብአዊ መርሆዎችን የጣሰ መሆኑን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ ሚያዝያ 11/08/2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት #የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

እውነት ለመነጋገር ፋኖ ላመነው ሰጤና ፋኖ በላይ ሽቴ እንደ ግለሰብም ሆነ እንደሚመሩት ሰራዊት ‘ተቋምና መሪያቸውን’ ለመጠበቅ የከፈሉትን ዋጋ ማንም አልከፈለውም። እስከሞት ድረስ የሚታመኑ እንቁዎች
እውነት ለመነጋገር ፋኖ ላመነው ሰጤና ፋኖ በላይ ሽቴ እንደ ግለሰብም ሆነ እንደሚመሩት ሰራዊት ‘ተቋምና መሪያቸውን’ ለመጠበቅ የከፈሉትን ዋጋ ማንም አልከፈለውም። እስከሞት ድረስ የሚታመኑ እንቁዎች ናቸው። ውጊያን እንደ ፊልም የህንድ አክተር ለመሆን በሚሻ ልቡና አያውቁትም። ግን የጁላ ሰራዊትን አፈር ድሜ አስልሰውና አብልተው፣ ማርከውትና ታጥቀው፣ ደምስሰውና ድል ሰርተውበት ያውቁታል። እነዚህን መሰል እንቁ ልጆች እንዳይባክኑ ማድረግና ከስህተት መጠበቅ መቻል፣ ሰራዊታችንን ከብክነት ማቀብ፣ ለተቋማዊነት የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ በማድረግ የአማራ ህዝብ ትግል ‘የድል ቀን ብስራት’ ርዝማኔ ላይ ቢቻል ወራትን ባይቻል ሰከንዶችን ቀንሶ የህዝባችን ድል እንዲያበስሩ ማስቻል የመሪነት ግዴታችን ነው። ፤ የተደረጉ ፈርጣማ ውይይቶችና የተሰጣጠናቸው ድርጅታዊና ግለሰባዊ ሂሶች ሁሉ ውጤት ተኮር እንዲሆኑ እንረባረባለን። አይዞን!

⚠️ የፖለቲካ “ኑዛዜ” ወይስ የሽንፈት ሰቀቀን? ሰሞኑን የምስጋናው አንዷለምን ጽሁፍ ስናነብ የታዘብነው ትልቁ እውነት “ድል ሲርቅ ሰበብ ይበዛል” የሚለውን ነው። “ብሔርተኝነትን ፈጠርሁት፣ አሁን ደግሞ አፈረስሁት” የሚለው ትረካ፣ ፖለቲካዊ ትዕቢት ብቻ ሳይሆን የታሪክ መሳለቂያም ነው። 1. ብሔርተኝነት የላቦራቶሪ ውጤት አይደለም! ብሔርተኝነት እንደ ንግድ ድርጅት በባለሀብት የሚቆም፣ እንደ ሸቀጥም በፈቃድ የሚመለስ አይደለም። የአማራ ብሔርተኝነት ከምቾት የተወለደ ሳይሆን፣ ላለፉት ስድሳ ዓመታት በሕዝባችን ላይ ሲወርድ የቆየው ግፍ፣ መፈናቀልና የህልውና አደጋ የወለደው Organic ንቅናቄ ነው። ግለሰቡ “እኔ ፈጠርኩት” ማለቱ “ፀሐይን የፈጠርኳት እኔ ነኝ” እንደማለት ያለ ድንቁርና ነው። የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች እንዲሉ፣ ትልቅ የታሪክ አደራ ተሸክሞ ሲያበቃ፣ ትግሉ ከቁጥጥሩ በላይ ሲሆን "አይጠቅምም" ብሎ መደምደም የፖለቲካ ብስጭት እንጂ የዕውቀት ውጤት አይደለም። 2. ርዕዮተ-ዓለማዊ መዋዠቅ ወይስ የሜዳ ላይ ሽንፈት? ምስጋናው በፖለቲካው የቼዝ ጨዋታ ተበልጦ ሲወጣና የትግሉ ሞገድ ከአቅሙ በላይ ሲሆን፣ ርዕዮተ-ዓለሙን ማውገዝ መረጠ። ትላንት በብሔርተኝነት ስም ሕዝብን ሲያደራጅ የነበረ ሰው፣ ዛሬ አሰላለፉ ሲቀየር "ርዕዮተ-ዓለሙ ጎጂ ነው" ማለቱ የሞራል ዝቅጠት ነው። የሕዝብን መስዋዕትነትና ደም እንደ ግል ካፖርት ዛሬ አጥልቆ ነገ ማውለቅ አይቻልም። 3. የአማራ ብሔርተኝነት የማንም ግል ርስት አይደለም! ፖለቲከኞች ቢመጡና ቢሄዱ፣ ቢንበረከኩና ቢጸጸቱ፣ የአማራ ብሔርተኝነት ግን በፋኖ አውደ-ውጊያና በተራራው ላይ በፈሰሰው ደም እየለመለመ ይቀጥላል። “ውሻ ባለየው ሁሉ ይጮኻል” እንደሚባለው፣ ግለሰቦች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ቢጮኹም፣ የሕዝቡ የህልውና ማዕበል ግን ወደኋላ አይመለስም። እናም የአማራ ብሔርተኝነት ትላንት የህልውና ጋሻ ነበር፤ ዛሬ የትግል ሞተር ነው፤ ነገ ደግሞ ጠንካራ መሠረት ያላት ኢትዮጵያን የመገንቢያ ኃይል ሆኖ ይቀጥላል። ግለሰቦች ቢከዱም፣ ትግሉ ግን የራሱ ባለቤትና የራሱ መንገድ አለው። የአማራ ብሔርተኝነት አብቦ ይቀጥላል!!

ለአፋብን ቴዎድሮስ እዝ 102ኛ ኮር  ወረብ ላይ የሚሰራውን ስራ እያወቃችሁ፣ አይታችሁ እንዳላያችሁ የሆናችሁበት ምክንያት ምንድን ነው? ወረብን የሚሊሻ መዋያ ከሆነ ሰንበትበት ብሏል። ባጃጅ ላይ እያስወረዱ በግድ የምርጫ ካርድ እያስወሰዱ እንደሆነ ከእኛ በላይ መረጃው ከሚሊሻ አባሉ እንደደረሳችሁ ሰምተናል። ሌላው የወረብን ህዝብ ለማፈናቀል ሙሉ መሬቱን ለመከላከያ ምልስ፣ ለአድማ በታኝ፣ ለፖሊስ እና ለሚሊሻ ምሬት ለመስጠት ሙሉ ወረብን የመሬት ወረራ እያደረገ ያለውን መንግስት ደግፈው ህዝብን እያስጨነቁ የሚገኙት ባንዳዎች አስተማሪ እርምጃ መውሰድ ያልተቻለው ለምንድን ነው????? የወረብን መሬት ለአብይ አህመድ እየሸጡ ያሉት ተላላኪ ባንዳዎች! 1. ጥጋቡ በለጠ--------------የወረብ ቀበሌ ሊቀመንበር 2. አበባው መኳንንት ---- የወረብ ቀበሌ ፅ/ቤት ሀላፊ 3. አማረ ደሴ-----------------ቀበሌው ውስጥ የሚሰራ 4. ደባሱ አያሌው------------ 200ሺህ ብር ክፈሉና የልጅ ልጃችሁን ልጃችሁ አድርገን እናፅድቅላችሁ ካልሆነ ትልቅ ልጃችሁንም እናስወጣለን 5. ሸጋ ጌትነት---------------ከጥጋቡ ጋር መጠጥ ቤት የምትዞር የውስጥ አርበኞቻችን እንደነገሩን ዛሬ በዲያስፖራ ውለው አብረው ሲመጡ ታይየዋል( አልጋውን በቀጣይ የምናጋራ ይሆናል) 6. ስማቸው በዛ------------- ሚሊሻ የነበረ የፕላን ቦታ ትቀበላለህ ተብሎ አብሮ የሚዞር 6. ሙላት ተሾመ--------------ተላላኪ ሚሊሻ 6. ምክሩ ባዬ----------------->>>>>>>>>> . . . . . ቀሪውን በቀጣይ እናጋልጣለን!!!!ትኩረታችሁ ከዚህ ላይ ይሁን!!!! ከታዛቢዎች የተላከ

የአገዛዙ ኃይሎች ፋኖን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል ​ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ፣ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር እንደገለጸው፤ በአልዩ አምባ ከተማ እና በሸዋሮቢት አ
+1
የአገዛዙ  ኃይሎች ፋኖን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል ​ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ፣ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር እንደገለጸው፤ በአልዩ አምባ ከተማ እና በሸዋሮቢት አካባቢ የነበሩ የአገዛዙ ሀይል አባላት ትጥቃቸውን ይዘው በሰላም ኮሩን ተቀላቅለዋል። ​የተቀላቀሉ ግለሰቦች ዝርዝር፦ እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦርን (ከአልዩ አምባ ከተማ) -ጌትነት ጨቅሌ፦ ከ29ኛ ሻለቃ፣ 2ኛ ሻንበል፣ የጋንታ 1 የቲም 3 ዋና አዛዥ። -ዘመኑ ሙላቱ፦ ከ29ኛ ሻለቃ፣ 1ኛ ሻንበል (አድማ ብተና)። እነዚህ ግለሰቦች ሁለት የነፍስ ወከፍ መሣሪያ (ክላሽንኮቭ) ከነሙሉ ትጥቃቸው ይዘው የተቀላቀሉ ሲሆን፤ "የአማራ ህዝብ ትግል የህልውና ጉዳይ መሆኑ ገብቶናል፤ ከህዝባችን ጎን ለመቆም ወስነናል" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። - ​ከሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር፦ -መሐመድ መብሬ ይመር፦ የሚሊሻ አባል የነበረ  በአገዛዙ በኩል በአስገዳጅ ሁኔታ (በአፈሳ) ወደ ግዳጅ ቢሰማራም፣ የተሰጠውን መሣሪያ ይዞ የደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክፍለ ጦርን በሰላም ተቀላቅሏል። ወደ ፋኖ የተቀላቀሉት አባላት ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ አሁንም በአገዛዙ መዋቅር ውስጥ የሚገኙ የሚሊሻ እና አድማ ብተና ጓዶቻቸው የወገን ጥሪን ሰምተው ከህዝባቸው ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።      '' ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ​"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!                                  ​የመረጃ ምንጭ፦ አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ አሳምነው ዕዝ፣ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን።      አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ