ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Відкрити в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Показати більше3 222
Підписники
+2224 години
+2707 днів
+65730 днів
Архів дописів
በመካነሰላም ግንባር ከ300 በላይ የጠላት ኃይል በምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር አሃዶች ከጥቅም ውጭ ተደረገ!
የአፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር አሃዶች ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈፅመዋል!
ባለፉት 24 ሰዓታት በመካነሰላም ግንባር በተካሄደ ውጊያ የጠላት ኃይል ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል:: ኮሎኔል ተስፋዬ እና ኮሎኔል ዘላለም እየመሩት ወደ ግዳጅ የገባው ኃይል አፈር ደቼ በልቷል::
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ከ45ኛ ክፍለ ጦር እና ከ47ኛ ክፍለ ጦር ከተውጣጡ ሻለቃዎች ጋር በመቀናጀት በተወሰደ እርምጃ የ11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር ወታደሮችን እና የአድማ ብተና 21ኛ ሻለቃ በርካታ ኃይልን መደምሰስ፣ ማቁሰል እና መበተን ተችሏል:: የመካነሰላሙ 29ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ከወግድው 45ተኛ ክፍለ ጦር 1ኛ እና 4ተኛ ሻለቃ እንድሁም ከ47ኛ ክፍለ ጦር አትሮንስ ሻለቃ ተቀንሰው ለግዳጅ የመጡ የመሀል ሳይንት አናብስት በሰሩት ኦፕሬሽን ከ300 በላይ የጠላት ኃይል ከጥቅም ውጭ ሲደረግ ጠላት ቆጥሮ የቀበረው ብቻ 170 መሆኑን የውስጥ አርበኞች ያረጋገጡ ሲሆን 27 የሚሆኑት ደግሞ በየስርቻው ወድቀው ተገኝተው ማህበረሰቡ ለቢርመዱው ብሎ እንድቀብር ተደርጓል:: የሻለቃ አዛዥን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችም ተደምስሰዋል::
ከዚህ በተጨማሪ እስካሁን አስከሬናቸው ያልተገኘም እንዳሉ እየተነገረ ሲሆን የቆሰሉ ወታደሮች በየቁጥቋጤው ስር ተገኝተው በ29ኛ ክፍለ ጦር ሀኪሞች ትብብር ተገቢው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው:: ጠላት በበርካታ ተሽከርካሪ ጭኖ የወሰዳቸው ከ100 ያላነሱ ቁስለኞች እንዳሉም የታወቀ ሲሆን በአንድ ዙር ብቻ 4 አምቡላንስ ቁስለኛ ወደ ሆስፒታል መግባቱ ተረጋግጧል:: ከከባድ ቁስለኞች በኦፕሬሽኑ 17 የጠላት ኃይል የተማረከ ሲሆን 1 ቲም የሚሆኑት ደግሞ ከድተው ወደ ፋኖ ተቀላቅለዋል::
የምዕራብ ወሎ አናብስት በፈፀሙት ጀብዱ በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ከጠላት ተማርኳል:: አንድ የጠላት ድሽቃ አፈሙዝ ተጎምዷል:: አንድ ስናይፕርም ከጥቅም ውጭ ተደርጓል:: ከ627 ተተኳሽ ጋር በወገን ኃይል የተማረከ 1 ብሬን ወደ ፋኖ ኦርድናንስ ክፍል ገቢ ሆኗል:: 694 የድሽቃ ተተኳሽ፣ 40 የክላሽ ካዝና፣ 10 የእጅ ቦንብ ተማርኳል:: 1 ፓትሮል ሙሉ በሙሉ ተቃጥላለች::
በምዕራብ ወሎ ቀጠና ከሚገኙት 11 ወረዳወች መካከል ከአብዛኛዎቹ ተውጣጥቶ ወደ መካነሰላም በማቅናት ፋኖን አፀዳለሁ ብሎ ወደ ግዳጅ የገባው የ11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር ሰራዊት እና የአድማ ብተና 21ኛ ሻለቃ ኃይል ስምጥ ይግባ ስርጥ ሳይታወቅ እንደጨው መሟሟቱ አገዛዙን ክፉኛ አስደንግጧል::
የምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር አሃዶችን ብርቱ ታጋድሎ መቋቋም ያቃተው የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎችን በግፍ ጨፍጭፏል:: በዚህም ደመቁ ታመነ የተባሉ የ60 አመት እናት ልዩ ስሙ ሰኞ ገበያ የተባለ ቦታ እና ተመስገን አንበሴ የተባለ የ10 አመት ታዳጊ ልዩ ስሙ በታ የተባለ ቦታ ላይ በግፍ ገድሏል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዝያ 11 ቀን 2018 ዓ.ም
የጠላት እንቅስቃሴ‼️
ሁለት ኦራል እና አንድ ፒካፕ ከደ/ማርቆስ ወደ አማኑኤል መስመር ተንቀሳቅሷል ለወገን ይዳረስ‼️
ሰበር ዜና
ሚያዝያ 09/2018 ዓ.ም
አርማጭሆ #ደለሳ ጠላት ተደሰሰ።
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ ዕዝ
305 ኮር በማከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ደለሳ ቀበሌ #እባዳይት ጎጥ ሰፍሮ የሚገኘዉ 54ተኛ ክፍለ ጦር ሬጅመንት-1 የብልፅግና አገር አፍራሽ ሰራዊት በጀግናዉ ሰራዊታችን ተደመሰሰ።
305ኛ ኮር በመረጃና ደህንነት ክፍሉ በተደረገ ጥናት የጠላትን የሃይል አሰላለፋ የያዘዉን የጦር መሳሪያ እና ቦታዉን በማንበብ ይህን የፋሽስት ተልዕኮ አስፈፃሚ ሰራዊት ተኝቶ ሲያንኮራፋ ንጋት አካባቢ የተመረጡ ሬጅመንቶችና የኮሩ ልዩ ተልዕኮ በሌሊት ተጉዘው ዶግ አመድ አድርገዉታል።
በነበረዉ አውደ-ዉጊያ በጠላት ላይ የደረሰ ጉዳት
መከላከያ የሞተ = 87
አድማ ብተና የሞተ= 4
ሰላም አስከባሪ=2
@ 2 የሬጅመንቱ ዘመቻ አመራር እና 2 ሻንበል መሪዎች ተደምስሰዋል።
@ የቆሰለ 35 በሁለት ኦራል እና 2 ፒካፕ መኪና ተጭኖ ወደ ሶረቃ እና ሁመራ ተልኳል።
የተማረከ
10 ክላሽ
እጅ የሰጠ= 3
1ብሬን እና 1 ስናይፐር በከባድ መሳሪያ ከጥቅም ዉጭ ተደርጓል።
ደለሳ ቀበሌ እንባ ዳይት ጎጥ ሰፍሮ የሚገኘዉን ጥርቅም በአናብስቶች ሲለበለብ አትርፉን እያሉ ሲያለቃቅሱ በ3 አቅጣጫ:- በበደዊ፣ በጃንሱማ እና በኪሻ በኩል እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን በጃንሱማ በኩል 53ኛ ክፋለ ጦር 2 ሬጅመንቶች ጠላት አሰልፎ የነበር ቢሆንም ሽመል በር ላይ ተመቶ ወደ ኃላ ተመልሷል ።
የፋኖን ጀግንነት በቦታዉ የነበረ የብልፅግና የሬጅመንት አመራር በደለሳ ከተማ የሰጠዉ ምስክርነት
አመራሮቹ እና አባሉ ያለቀበት አንድ የተረፈ የብልፅግና እድሜ አራዛሚ አንድ የሬጅመንት አመራር በዚህ ትግል 31 ዓመት አገልግያለሁ። እንዲህ አይነት ዉጊያ ገጥሞኝ አያዉቅም ልጆቸን አማራ ጨረሳቸዉ በማለት በሻይ ቡና ደላሳ ላይ በስሜት ገለፀ እንዲሁም ፊት ለፊት ዘለዉ ምሽግ ላይ የሚገቡ የማይፈሩ ሁለተኛ ነብስ ያላቸዉ የሚመስሉ እነዚህ ሰዉ አይመስሉኝም ሌላ አለም የመጡ የሚመስሉ ከምሽግ ዉስጥ ያለን መንጥቆ የሚጥል በማለትም መስክሯል።
የአርማጭሆ ጀግና አናብስቶች ባደረሱበት ጉዳት ማመን ያቃተዉ ይህ የተጨነቀ ቅዥት ዉስጥ የገባ መሪ ሀሽሽ ሳይጠቀሙ አልቀሩም በማለት ጀግንነታቸዉን ለመሸፈን በሾክ ዉስጥ በመሆን ጭንቀቱን በከተማዉ እየተዟዟረ ሲያለቃቅስ ዉሏል።
አሁንም ፋኖ አስፈላጊዉን እርምጃ ለመዉሰድ በዝግጅት ላይ ይገኛል። ከፋኖ መብረቃዊ ምትሃት ለማምለጥ አማራጩ በየ አካባቢዉ ላሉ ፋኖዎች እጅ በመስጠት ህይወታችሁን አትርፋችሁ በጉጉት ለሚጠብቋችሁ ቤተሰቦቻችሁ እንድትበቁ ጥሪ እናስተላልፋለን።
ይህን ስምሪት በብቃት የመሩት የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች ሊመሰገኑ ይገባል
1/ ወታደራዊ አዛዥ
2/ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
3/ መገናኛ መምሪያ እና የልዩ ተልዕኮ መምሪያ ኃላፊ
4/ ሌሎች የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች ስትታገሉ እና ስታስተባብሩ የዋላችሁ ምስጋና ይገባቹሀል።
5/ ይህን ግዳጅ የፈፀሙ አመራሮችና አባላት ትልቁን ሚና ተጫዉተዋል!
6/ በማስተባባበር በቀጠናዉ ያላችሁ የአንድነትና የዕዝ አመራሮች ትልቁን ሚና ተጫዉታችኃል!
ግርማ እና ሞገስ ለነገይቱ የአማራ የነፃነት ቀን ስትሉ ዛሬ ላይ በዱር በገደሉ እየተዋደቃችሁ ላላችሁ ጀግኖቻችን
ህልውናችንን በተባበረ ክንዳችን እናረጋግጣለን
አርበኛ ባንዴራዉ ግርማይ __ የ305ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ
ሚያዝያ 10/2018 ዓ .ም
Update!
ተጨማሪ እና የተስተካከለ መረጃ!
ሚያዝያ 9/2018
በአማራነታቸው የተነሳ በአባ ሳሙኤል ከፍተኛ ጥበቃ ማ/ቤት በግፍ እስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞችን በተመለከተ
ለሚመለከተው ሁሉ!
ለቀይ መስቀል ድርጅት
ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማትና ባለሙያዎች
ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች
ለጠያቂ ቤተሰቦች
የግፍ እስረኞች ጉዳይ ለሚያሳስባችሁ
ሁሉ
የምትችሉ ሂዳችሁ ጎብኟቸው!
ድምፅ ሁናቸው!
መጋቢት 24 እና 26/2018 ፣ ሚያዝያ 8/2018 እንዲሁም በተለያዩ ጊዜያት ከቂሊንጦ ማ/ቤት ወደ አባ ሳሙኤል ከፍተኛ ጥበቃ ማ/ቤት የተወሰዱ ~ ከሕንጻ ያለፈ የተሟላ ነገር የለውም በሚል በብዙዎች ዘንድ ተከታታይ ቅሬታ እየቀረበበት ባለው ማ/ቤት ውስጥ የሚገኙ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ስም ዝርዝር፦
1. ቢልሸት ይርጋ ፣
2.እዮብ ታምሩ ፣
3.ገብረማሪያም ሰጠኝ ፣
4. ስንታየው ንጋቱ፣
5. መሰረት ወርቁ ፣
6. ወርቁ ገብሬ፣
7. ምስክር ደምስ፣
8. አንዷለም ሉሌ ፣
9. ታደሰ መለሰ ፣
10. ቸርነት እሸቱ ፣
11. መሪጌታ በላይ አዳሙ፣
12. ሸጋው ምሀባው ፣
13. ሻንበል አድማሱ አለሙ ፣
14. ሄኖክ ዋለ፣
15. ቴዎድሮስ ጣምራይ፣
16. ሞላልኝ ሲሳይ፣
17. ቸርነት ዘመን፣
18. መላይክት አማረ፣
19. አማኑኤል ሳህልየ፣
20. ሁሴን ሰይድ ፣
21. ወንድ ወሰን አሰፋ፣
22. ሀብታሙ አንዳርጌ ፣
23. አሳምነው ታደሰ ፣
24. አሮን ትርፌ ፣
25. ልዑል እማዩ ፣
26. ቴዎድሮስ ተሾመ፣
27. ፍትህአለው አድማሱ ፣
28. ቢኒያም ተረፈ፣
29. እንዳለ ገዜ፣
30. በረከት ወርቁ ፣
31. ታዴ በቀለ ፣
32. አንደበት ተሻገር፣
33. ጌትነት አማረ፣
34. ሙሉጌታ አገዘው፣
35. በላይ ሲሳይ ፣
36. ታደሰ ወዳይነው፣
37. ሲሳይ መልካሙ ፣
38. ፋሲል ጌታቸው፣
39. አወል አብዱል ቃድር፣
40. ሀሰን አብዱል ቃድር፣
41. ወንድም በርሄ፣
42. ማረው ስለሽ፣
43. ደርበው አዲሱ፣
44. ሀብታሙ ዳኜ፣
45. እንደሰው ጌጡ ፣
46. ሙሉቀን ተስፋዬ ፣
47. አማረ መለሰ አከለ ፣
48. መልኩ ተስፌ ፣
49. ይላቅ ገዳሙ ፣
50. ታደሰ አባቡ ፣
51. ላቀው ሀብቴ ፣
52. ሀብታሙ ፈንታው ፣
53. ቢኒያም አስቻለው ፣
54. መልካሙ ውባንተ ፣
55. አስናቀ በቀለ ፣
56. ወተቱ ደሳለኝ ፣
57. ማናዬ አየለ ፣
58.በላይ ወንዴ ፣
59.ሳምሶን ማሞ ፣
60.መኳንንት አድማሱ ፣
61.ቢሆነኝ ጤናው ፣
62.ውብሸት ተፈራ ፣
63.ምስጋናው አባትነህ ፣
64. ሰለሞን ተፈሪ ፣
65. ታደሰ ደርቤ ፣
66. እያሱ ገላግል ፣
67. በፈቃዱ ጅንን ፣
68. ተሾመ አለምነህ ፣
69. በላይ አቤ ፣
70. ችሎት ይስማው ፣
71. ገደፋዬ አበባው፣
72. ላቀው ሞገስ ፣
73. ዳንኤል ደመቀ ፣
74. ተስፋዬ ከበደ ፣
75. አጥናፉ አድማሱ ፣
76. አየነው አስማረ ፣
77. ዘነበ ሽታ ፣
78. ሀብታሙ ፍቃዱ ፣
79. ሳሙኤል ያለው ፣
80. ተወልደ ብርሃን ዘውዱ ፣
81. አስማማው አረጋ ፣
82. አባትነህ ከፌ ፣
83. እንቻለው ውዱ ፣
84. አዶናይ ብሩ ፣
85. የሻው አደፍርስ፣
86. ድረስ ጌታቸው፣
87. ንብረት ሕብስት ፣
88.ሰለሞን ጎሳ ፣
89.ታምራት ምስጋናው ፣
90.ክንዳለም ፈረደ ፣
91.ወርቁ ፣
92.ዲያቆን ገ/ሚካኤል አባይ ፣
93.እንዳሰኘው ክበብ እና
94.ሰጠኝ በይኖ ናቸው።
....
(አውሎግሶን አንድነት ፣ ሚያዝያ 9/2018)
🔥#ሰበር_ዜና‼️
ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ አማያ ለመግባት ያሰፈሰፈውን የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ ወታደር በመልሶ ማጥቃት አካባቢውን አስከብሯል።
የአማራ ፋኖ ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር አማያን፣ባይባዋንና ጀመዶን ለመያዝ አሰፍስፎ የመጣውን ጥላት በመልሶ ማጥቃት መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በራያ ቆቦ ዙሪያ ያሉ ቀበሌዎችን ቀጠናውን በማስፋት ተቆጣጥሮ ውሏል።
በተጨማሪም የ102ኛ ኮር እስከ ጮቢ በር ዘልቆ በመግባት 65 የመከላከያ ሰራዊት አባል በተከታታይ የሞርተር ጥቃት በመግደልና የጌታቸው ረዳን 29 ሐራ መሬት የሰራዊት አባል ደምስሷል።
በዚህ ዘመቻ የነበሩት የ102ኛ ኮር ወታደራዊ አዛዦችና ወታደራ ዘመቻ መሪዎች በሚገርም መናበብና ጦርነቱን በተሻለ ብቃት ስብጥር የሞርተር ተኩስ በጥላት ላይ በመክፈት የመሩት መሆኑን የ102ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት ገልጿል።
ጠላት ከጧት ጀምሮ በድሮን፣ በቢ-ኤም፣በዙ-23፣ በመድፍና በታንክ የተጠናከረ ማጥቃት ቢያደርግም የ102ኛ ኮር አይበገሬዎቹን ማቆም ተስኖት ውሏል።
በጧት የጀመረው ዘመቻ በጥላት ላይ ወታደራዊና ፖለቲካዊ የስበት ማዕከሉን በመለየት የ102ኛ ኮር በጮቢ በር የጥላትን ድሽቃ በወገን ሞርተር ሙሉ በሙሉ ዛሬም እንደትናንቱ በማውደም የሀይል የበላይነትን በመውሰድ ከላይ የተጠቀሱትን የገጠር ቀበሌዎችንና ከተሞች በቁጥጥር ስር አውሏል።
በመጨረሻም የ102ኛ ኮርን #የሞርተርና_የድሽቃ ጥቃት መቋቋም ያቃተው የአብይ አህመድ ጨፍጫፊው አገዛዝ 05 አድስ ቅኝ ቀበሌ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያንን ሆን ብሎ በመድፍ በመምታት የ8 አመት ህፃን በመግደልና ሌሎች የቤተ-ክርስቲያን የሰንበት ተማሪዎች አቁስሏል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 10/2018ዓ/ም
+1
አራት የአድማ ብተና አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ!
አራት የአድማ ብተና አባላት ከፋሽስቱ አገዛዝ ጋር ሆነን ህዝባችንን አንወጋም አገራችንን አናፈርስም በማለት አፋብን ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: የኮሩና የክፍለ ጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::
©ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
ጥቆማ‼️
በአርማጭሆ ግንባር እየተካሄደ በሚገኘው ተጋድሎ እስካሁን ባለው ከ90 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች መደምሰሳቸው ታወቀ!
በተጨማሪም፡ አገዛዝ ስርአቱ ተጨማሪ ህዝብ የሚጨፈጭፍበት ጊዜን ለማገኘት የሚያጭበረብርበት የምርጫ ካርድና ኮሮጆም እንዲበታተንና እንዲቃጠል ተደርጓል።
በተያያዘም፡ ከጃንሱማ ወደ ጋብላ ለእገዛ በተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ላይ ልዩ ስሙ ሽመል በር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ከባድ የቆረጣ ጥቃት ተፈፅሞበት ከባድ ኪሳራን መከናነቡ ታውቋል።
+9
ሰበር የድል ዜና !
የአፋብን ወሎ ቤተአማራ ሚኒሊክ ዕ ዝ 105'ኛ ኮ ር( የቀድሞው ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር) በምዕራባዊ ቤተአማራ ቀጠና በመካነሰላም ግንባር ጠላትን በዚህ መልኩ ደም*ስሶ አዝረክ*ርኮታል!!
ጀብደኛው ሚኒሊክ ዕዝ ይችላል✊
የአባቶቹ ልጅ ፋኖ በቅርቡ ዘር ጨፍጫፊውን የብልፅግና አገዛዝ አስወግዶ የህዝባችንን ህልውና አስጠብቆ የተረገጠውን ባንዲራችንን ከፍ አድርጎ በክብር ያውለበልባል።
እየመጣን ብቻ ሳይሆን እየደረስን ነው💪
የዚህ ታሪካዊ ትግል አካል ይሁኑ!!!
ፍቅርን ብየ እንጂ ተግቼ ለሰላም እኔስ መታገሴ፣
መች ከሀገር ይበልጣል እኔስ አንድ ነፍሴ።
ወይድ አንተ አትንገረኝ ማንነቷን፣
ምጥ አታስተምር ልጅ እናቷን።
ወይድ አታስቆጥረኝ ማንነቴን፣
እኔ አውቀው የለም ወይ ደም አጥንቴን።
ወይድ አንተ ላንሳበት ባንዲራየን፣
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማየን።
💚💛❤
መንጋው ተንጫጫ! ወገን መልካም ቀን🙏Ayinades Walelgnelgne
የአባት አርበኞች ጦር ተደራጅቷል !!!
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ጀኔራል ኃይሌ ዘ ውባንተ ክፍለ ጦር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና በክፍለ ጦሩ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ሻንበል ማርዬ አስራት እና በክፍለ ጦሩ ህዝባዊ አስተዳደር ኃላፊ አርበኛ ዋሴ ታደሰ ጋር ውይይትና ምክክር በማድረግ የአባት አርበኞችን ጦር በማደራጀት ላይ ነው።
ስርዓቱ ከምንጊዜውም በላይ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ኢ - ሰባዊ እልቆ መሳፍርት የሌለው በደልና ግፍ እየፈጸመ በመሆኑ ራስንን በማደራጀትና መሰልጠን ተገቢ መሆኑን በመረዳት በስማዳ ወረዳ ጎሽሜዳ ቀበሌ :-
1ኛ .ግራዝማች ለውጤ ====ሻንበል
2ኛ .ግራዝማች ይሁኔ======= ሻንበል
3 ኛ.ግራዝማች አወቀ ======ሻንበል
4 ኛ.ግራዝማች መብራቱ====== ሻበል
በሚል ሲደራጂ መታሰቢያነቱ በጀኔራል ኃይሌ ዘ ውባንተ ክፍለ ጦር ስር ሲታገል በተሰዋው አርበኛ ግዛቸው ምትኩ ሬጂመንት ተብሎ የተሰየመ ሲሆን ለየትኛውም ወታደራዊ ግዳጂ ዝግጁ በማድረግ በቀጠናው ህግ የማስከበር ስራ የሚሰራ ሁኖ ተደራጂቷል ።
ድል ለአማራ ፋኖ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፉያለው ደሴ ኮር ቃል አቀባይ ክፍል!!
ቴዲ አፍሮን [ለሆነ] ሕዝብ (አካባቢ) ብቻ አጥበው ለመስጠት ያልተሞከሩት ነገር የለም። ቴዲን በምኒልክ በኩል"አማራ ነው" ሲሉት፤ በሐብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ በኩል ጉራጌ ይሆንባቸዋል። የተወሰነ ዘር ቆጥረው ጉራጌ ሲያደርጉት በጀግናው ጎበና ዳጨ በኩል ኦሮሞ ይሆናል። አክራሪ ክርስቲያን ነው ሲሉት በጀግናው የሶማሌ ተወላጅና ሙስሊም ኡመር ሰመተር በኩል ሶማሌ ይሆናል። አክራሪ ነው ሲሉት፦
"አንችም በሃይማኖትሽ፣ እኔም በሃይማኖቴ፣
መኖር እንችላለን፣ አይጠበኝም ቤቴ።" እያለ ይዘፍናል።
ምናልባት የቴዲ "አንዲት ኢትዮጵያ" ሕልም ላይስማማህ ይችላል። የሚከተሉትን ብዙሐኖች ግን አክብር። ለምን ተከተሉት ማለት ውርደት ነው። ቴዲ በራሱ መንገድ ስለተባበረችው ጠንካራ ኢትዮጵያ ዘመረ እንጅ የትኛውንም ኃይል አልገፋም። ቴዲን ይኼዱበታል እንጅ አይመጣባቸውም። በምናቡ የሚስላትን ሐገር በእውነተኛው የጥበብ ዓለም መዝፈን መብቱ ነው። "የድሮ ሥርዓት ናፋቂ ነው" እንዳትል፥ ጎበና፣ ምኒልክ፣ ኡመር፣ አሉላ፣ ባልቻ....የተችዎቹ የጎሳ ብሔርተኞች የትናንት ታሪካቸው እንጅ የቴዲ ብቻ አይደሉም😃
አንዳንድ "የአማራ ብሔርተኛ ነን" ባይ ደንቆሮዎችስ ስንቴ ዘመቱበት😃 ስንት ጊዜ ሰደቡት😃 በቃ ቴዲ "ቴዲ" ብቻ ነው። ትከተለዋለህ እንጅ አይከተልህም። ነገር ግን፥ ሳትወድ በግድ ታደንቀዋለህ።
በቃ ቴዲ "ኢትዮጵያዊ" እንጅ ኦሮሞ ወይም አማራ አልያም ትግሬ አይደለም።
ኧረ ነገ የሚመጣው መቼ ነው🙄#Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር
