ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك 👈

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
4 039
المشتركون
+6824 ساعات
+3957 أيام
+1 39230 أيام
أرشيف المشاركات
'' እርምጃ ውሰዱበት ተብለናል" የአገዛዙ ፖሊሶች! "ከተቃጣብኝ የግድያ ሙከራ ለጊዜው ብተርፍም ፣ መላው ቤተሰቤ ግን አሁንም አደጋ ላይ ነው" ዘሪሁን ገሠሠ! የቀድሞው የአብን ፓርቲ መስራች አባልና አመራር የነበረው፡ በኋላም የሕዝቤን ጥያቄ በምስር ወጥ አለውጥም በሚል በአቋሙ በመፅናቱ ከእስራት ጀምሮ አያሌ ግፍና መከራ የተፈፀመበት ፖለቲከኛው ዘሪሁን ገሠሠ "ህዝብ_ይወቅልኝ" በሚል ትናንት ጥር 25/2018 ዓ/ም የተፈፀመበትን ግፍ በሚከተለው መልኩ ገልጿል። ህዝብ_ይወቅልኝ! በዛሬው እለት ማለዳ ለስራ ከወጣሁበት ስልክ ተደወለልኝ። ''አባቴ ቤታችንን ሊያፈርሱብን ነው!'' የሚል የልጆቼ ድምፅ ነበር። የዛሬ ሁለት አመት በመከላከያ (ኮማንድ ፖስት) ተይዥ ወደአዋሽ አርባ ከመሄዴ በፊት '' አባቴ ኪራይ ቤቱን በ3 ቀን ለቃችሁ ውጡ ተባልን!'' ብለው በገለፁልኝ የለቅሶ ድምፅ ነበር። ከነበርኩበት በፍጥነት ደረስኩ። ስደርስ ግን ''ሀሰን'' በሚባል አየር ማረፊያ አካባቢ በሚኖር የኮምቦልቻ ከተማ #ሚሊሻ የሚመራ የታጣቂ ቡድን ግሬደር አስገብቶ ማፍረስ ጀምሯል። ወጉ አይቀርምና ''በህግ አምላክ!'' ብዬ ለማስቆም ሞከርኩ። '' መላ ቤተሰቤን ገድላችሁ ካልሆነ ፣ በአመታት ጥረት በይዞታዬ ላይ የሰራሁትን ቤት ከህግ አግባብ ውጪና ተገቢውን ካሳ ሳትከፍሉ አታፈርሱም!'' በማለትም ለማስረዳት ጣርኩ። ሀሰን የሚባለው የቡድኑ መሪ ግን '' እርምጃ ውሰዱበት ተብለናል። አይተኩሱም ብለህ እንዳታስብ!'' በማለት አፈሙዝ ወደደረቴ አነጣጠረ። መላው የአካባቢው ማህበረሰብ ሁኔታውን በለቅሶ ታጅቦ ይከታተል ነበር። ''እሺ አፍርሱ'' ብዬ ሂደቱን በካሜራዬ ለመቅረፅ ስጀምር ሁሉም የታጠቁ ሀይሎች በህብረት እላዬ ላይ ሰፈሩ። ባለቤቴን ጨምሮ የስድስት ወር ህፃን ልጄ ተፈነከተች። ግፍን ተሸክሜ ከምኖር መሞትንም በደስታ ስለምቀበለው ፣ በእኔ ላይ የደረሰውን ልተወውና መላው ቤተሰቤ ግን እጅጉን ተጎድቷል። ግብግቡ ከቀጠለ በኃላ በበርካታ ታጣቂዎች ታግቼ ውያለሁ። ሂደቱ የቤቱን አጥር በማፍረስ ለጊዜው የቆመ ቢሆንም ፣ ''በቀጣይ ቀናት እናፈርሰዋለን!'' የሚል ዛቻ ተነግሮኛል። ለዚህ ሁሉ መነሻ የሆነው በአካባቢው የሚሰራው የአስፋልት መንገድ ሲሆን የመንግስት አመራሮች '' ካሳ የምንከፍለው ገንዘብ የለንም። ገንዘብ ስናገኝ እንከፍላለን። መንገዱ ግን እስከምርጫው ማለቅ ስላለበት ፣ እናንተ በ15 ቀን ውስጥ ቤታችሁን አፍርሳችሁ ጎዳና ውደቁ!'' የሚል ውሳኔ ይዘው መምጣታቸውን ተከትሎ ሲሆን ፣ ሌሎች አርሶደሮችና ባለይዞታዎች በተባለው አግባብ ፈርተው ያለአንድ ብር ካሳ ሲያፈርሱ ፣ የኔ ልጆችና ቤተሰቦቼ ግን የምንወድቅበት ሌላ አማራጭ ስለሌለን '' በህግ አግባብ በተቀመጠው መልኩ ይፈፀም። አለበለዚያ እኛን ገድላችሁ ቤቱን በላያችን ላይ አፍርሱት'' የሚል ውሳኔ በመወሰናችን ነው! ምንም እንኳ መጠነኛ ጉዳት ባስተናግድም ከታጣቂዎቹ እገታ ለጊዜው ነፃ ወጥቻለሁ። መላው ቤተሰቤ ግን በዚህ ጨለማ '' ምን ቤት አለንና ...'' ብለው ፤ በረንዳ ላይ እየተላቀሱ በስጋት ላይ መሆናቸውን ደውዬ አረጋግጫለሁ። ይህ ዛሬ የግድያ ሙከራ ያደረገ ቡድን ነገ ምን እንደሚያደርጋቸው አላውቅም! ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ ብቻ - አግተው ከስራ አሰናበቱኝ ፣ ቤተሰቤን ከተከራየንበት ቤት እንዲወጡ በማድረግ ጎዳና በትነው የበቀል ጥማታቸውን ተወጡ ፣ ከአስር ወራት የአዋሽ አርባ ቆይታ በኃላ ከእስር ብወጣም ፣ '' የፌደራል ኮማንድ ፖስት ቢለቅህ እኛ እንፈልግሀለን'' ተብዬ በጊዜው የተያዙብኝ ስልኮችና ሌሎች ንብረቶችን ጨምሮ እስካሁን አልተለቀቁልኝም። የባንክ አካውንቴ ከታገደ ሁለት አመት አለፈው። ''ልቀቁልኝ'' ብዬ ስሄድ '' ስናፈላልግህ ነበር'' ተብዬ ታሰርኩ ፣ መልሼ ተፈታሁ። በመጨረሻም አካባቢውን ለቅቄ መሄድን መረጥኩ። አሁን ደግሞ ልጆቼን በገዛ ይዞታቸው ላይ ቤት ሰርቼ ''ከኪራይ ቤት ወጡ'' ስል ሞልቶ አልፈስ ያላቸውን የግፍ ቁና ሊሰፍሩ መጥተው ፣ ይህ ኢ-ሰብአዊና አረመኔያዊ ወንጀል ተፈፅሟል። ይህን ከመቻል በላይ የሆነውንና አደባባይ ለማውጣት የተገደድኩበትን ግፍ ስለፍትህ የቆመ ሁሉ እንዲያውቅልኝ እፈልጋለሁ! ምናልባትም በእኔም ሆነ በቤተሰቤ ላይ ከዚህም የከፋ ነገር ቢከሰት ተጠያቂዎቹና ይህን የፈፀሙትን አካላትም ከወዲሁ ለማሳወቅ እወዳለሁ!

photo content
+2

በመጀመሪያ ደረጃ፣ አብይ አህመድ ሊገነዘበው የሚገባው ነገር ቢኖር ስለ ዳግማዊ ምኒልክ ታሪክ ለማውራት የሚያስችል የሞራል ብቃት የሌለው መሆኑን ነው። አብይ ለሀገርና ለታሪክ ካላቸው ትልቅ ቦታ አንጻ
በመጀመሪያ ደረጃ፣ አብይ አህመድ ሊገነዘበው የሚገባው ነገር ቢኖር ስለ ዳግማዊ ምኒልክ ታሪክ ለማውራት የሚያስችል የሞራል ብቃት የሌለው መሆኑን ነው። አብይ ለሀገርና ለታሪክ ካላቸው ትልቅ ቦታ አንጻር ሲታይ፣ የእሳቸውን የእግር ጥፍር ያህል እንኳን ሊመጥን የማይችል ፍጡር ነው። ​በመቀጠልም፣ ‘ባንዳ’ የሚለውን ቃል በተመለከተ፤ አማራን እንደ ከብት እያሳረድክ ያለኸው አንተ ራስህ ሆነህ ሳለ፣ ሌላውን ባንዳ ብለህ ለመፈረጅ እንዴት ትደፍራለህ? እውነተኛው የባንዳነት ባለቤት አንተ ራስህ መሆንህን ለምን ረሳኸው? ይህ የታሪክና የህዝብ ተጠያቂነት በቅርቡ የሚያገኝህ ይሆናል።

አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት ለመላው የፋኖ አመራሮች!" ​"ከብልፅግና የደህንነት መሥሪያ ቤት (ከቁጥር 604) ለፋኖ አመራሮች ስልክ እየተደወለ ይገኛል። በመሆኑም ማንኛውም የአመራር አካል ከዚህ ቁጥር የሚመጣን ጥሪ በፍጹም እንዳያነሳ እና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን። ይህ መረጃ ለሁሉም አመራሮች እንዲደርስ በከፍተኛ ፍጥነት 'ሼር' (Share) በማድረግ ተባበሩ።" ​ ​ይህ መልዕክት ለምን አስፈላጊ እንደሆነና ሊከተሉ የሚችሉ አደጋዎችን በሦስት ዋና ነጥቦች ማየት ይቻላል፡ ​1. የደህንነትና የመረጃ ጥበቃ ​የደህንነት መሥሪያ ቤቶች አጭር ቁጥሮችን (እንደ 604) ተጠቅመው የሚደውሉት መረጃ ለመሰብሰብ ወይም የአንድን ግለሰብ ማንነት ለማረጋገጥ ሊሆን ይችላል። ስልኩ በሚነሳበት ጊዜ ተደዋዩ ያለበትን ትክክለኛ ቦታ (Location) በቴክኖሎጂ ለመለየት ስለሚያመች፣ ጥሪውን አለማንሳት ለደህንነት ሲባል ተመራጭ ነው። ​2. የስነ-ልቦና ጫና (Psychological Tactics) ​እንዲህ ያሉ ጥሪዎች በአመራሮች መካከል ጥርጣሬን ለመፍጠር፣ ግራ ለማጋባት ወይም "ድርድር እንጀምር" በሚል ሽፋን መረጃ ለማውጣት ሊደረጉ ይችላሉ። ጥሪውን ባለመቀበል የጠላትን የመረጃ ምንጭ መዝጋት ይቻላል። ​3. የመረጃው ተደራሽነት (Urgency) ​"ሼር አድርጉ" የሚለው ጥሪ መልዕክቱ በፍጥነት ካልተሰራጨ፣ አንድ ወይም ሁለት አመራሮች ባለማወቅ ጥሪውን አንስተው ለአደጋ ሊጋለጡ ስለሚችሉ ነው። በመሆኑም መረጃውን በየደረጃው ላሉ የአደረጃጀት መዋቅሮች ማድረስ አስፈላጊ ነው። ​በተጨማሪም ለጥንቃቄ ያህል፦ አመራሮች የዲጂታል ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ስልካቸውን በየጊዜው "Airplane Mode" ላይ ማድረግ ወይም ኢንተርኔት በማይጠቀሙበት ሰዓት መዝጋት ይመከራል።

photo content
+1

photo content

መንግስት አፈንግጠው ከሚወጡ ጋር ከሚደራደር በርካታ የጦር ሠራዊት ካላቸው ታጣቂዎች ጋር እውነተኛ ድርድር የማያደርገው ለምንድነው የሚል ጥያቄ በፓርላማ ተነሳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2018 በጀት አመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላቱ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ መስጠት የጀመሩ ሲሆን ከእርሳቸው አስቀድሞ ግን የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተውላቸዋል፡፡ በዋናነት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ የባህር በር፣ ሰላምና ጸጥታ፣ የተፈናቃዮች ሁኔታ፣ ህወሓት፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ የፓርላማ አባሉ አበባው ደሳለው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባነሱት ጥያቄ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ችግር ከሚያባብሱ ጉዳዮች መካከል ዋነኛው በሀገሪቱ  ያለው የሰላም እና የፀጥታ  ችግር አለመቀረፍ ነው ብለዋል። ይህንን ለመቅረፍም የምክር ቤት አባላቱ ለ3 ዓመታት ውትወታ ሲያደርግ እንደነበር ቢከርምም ምንም ዓይነት ለውጥ አለመምጣቱ እንዲሁም  መንግስት ከተለያዩ የታጠቁ አካላት ጋር ድርድር እያደረግኩ ነው ቢልም ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ በተጨማሪ መንግስት አፈንግጠው ከሚወጡ ታጣቂዎች ጋር ከመደራደር ይልቅ በርካታ የጦር ሠራዊት ካላቸው ታጣቂዎች ጋር እውነተኛ ድርድር የማያደርገው ለምንድነው? ሲሉም አክለዋል፡፡ የባህር  በር ፣ የልማት፣ ሀገራዊ ምክክር እና ምርጫን በተመለከተ መንግስት ያለሠላም እንዴት ለማሳካት አሰበ የሙሉ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሠንዝረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በመስጠት ምላሽ ጀምረዋል፡፡ ❤Dawit fano አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

photo content

መንግስት አፈንግጠው ከሚወጡ ጋር ከሚደራደር በርካታ የጦር ሠራዊት ካላቸው ታጣቂዎች ጋር እውነተኛ ድርድር የማያደርገው ለምንድነው የሚል ጥያቄ በፓርላማ ተነሳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ተኛ ዓመት
መንግስት አፈንግጠው ከሚወጡ ጋር ከሚደራደር በርካታ የጦር ሠራዊት ካላቸው ታጣቂዎች ጋር እውነተኛ ድርድር የማያደርገው ለምንድነው የሚል ጥያቄ በፓርላማ ተነሳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2018 በጀት አመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላቱ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ መስጠት የጀመሩ ሲሆን ከእርሳቸው አስቀድሞ ግን የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተውላቸዋል፡፡ በዋናነት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ የባህር በር፣ ሰላምና ጸጥታ፣ የተፈናቃዮች ሁኔታ፣ ህወሓት፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ የፓርላማ አባሉ አበባው ደሳለው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባነሱት ጥያቄ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ችግር ከሚያባብሱ ጉዳዮች መካከል ዋነኛው በሀገሪቱ  ያለው የሰላም እና የፀጥታ  ችግር አለመቀረፍ ነው ብለዋል። ይህንን ለመቅረፍም የምክር ቤት አባላቱ ለ3 ዓመታት ውትወታ ሲያደርግ እንደነበር ቢከርምም ምንም ዓይነት ለውጥ አለመምጣቱ እንዲሁም  መንግስት ከተለያዩ የታጠቁ አካላት ጋር ድርድር እያደረግኩ ነው ቢልም ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ በተጨማሪ መንግስት አፈንግጠው ከሚወጡ ታጣቂዎች ጋር ከመደራደር ይልቅ በርካታ የጦር ሠራዊት ካላቸው ታጣቂዎች ጋር እውነተኛ ድርድር የማያደርገው ለምንድነው? ሲሉም አክለዋል፡፡ የባህር  በር ፣ የልማት፣ ሀገራዊ ምክክር እና ምርጫን በተመለከተ መንግስት ያለሠላም እንዴት ለማሳካት አሰበ የሙሉ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሠንዝረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በመስጠት ምላሽ ጀምረዋል፡፡

#የመንግስት_ሽንፈት እና #የመከላከያ_ሠራዊት_የምርኮ ሁኔታ_አሳሳቢ_ደረጃ_ላይ_መድረስ‼‼‼ The defeat of the government and the captivity situation of the def
#የመንግስት_ሽንፈት እና #የመከላከያ_ሠራዊት_የምርኮ ሁኔታ_አሳሳቢ_ደረጃ_ላይ_መድረስ‼‼‼ The defeat of the government and the captivity situation of the defense forces and worrying level. የመንግስት ሀይሎች የመዋጋት አቅም የሚፈጠረው የሞራል ብቃት እና ዝግጅት እንድሁም የሰለጠነ የሰው ሀይል እና የታጠቀው መሳሪያ ወሳኝነት አለው። የብልጽግና መንግስት መከላከያ ሀይል የመዋጋት አቅምም ሆነ ብቃት አለያም የሰለጠነ የሰው ሀይሉ ተሟጦ በማለቁ በአጭር ጊዜ በመክዳት ፋኖን በመቀላቀል እና በጦርነት እጅ በመስጠት ሊበተን ይችላል የሚል የውጭ የፖለቲካ ተንታኞች እየተናገሩ ነው። ለዚህም እንደቅርብ ምሳሌ የሚቀርበው #የአፍጋኒስታን_መንግስት በነሐሴ 2021 በማስወገድ ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ ከሀገር እንድሸሹ ያደረጋቸው የአፍጋኒስታን ብሔራዊ የመከላከያ እና የደህንነት ኃይሎች ለታሊባን በፍጥነት እጅ በመስጠታቸው ነው። #የብልጽግና_መንግስት በአጭር ጊዜ እንደዚህ አይነት እጣ ፈንታ ሊገጥመው ይችላል የሚል ግምገማ ተወስዷል።

ሰበር የድል ዜና‼️‼️ አርበኞች ክፍለ ጦር ድርጅቱ በተመሰረተ ማግስት በጠላት ላይ መብ*ረቃዊ ጥ*ቃት አደረሰ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ በላይ ዕዝ 4ኛ ደጃዝማች ኮር አርበኞች ክፍለ ጦር ከብርጌዶ
+2
ሰበር የድል ዜና‼️‼️ አርበኞች ክፍለ ጦር ድርጅቱ በተመሰረተ ማግስት በጠላት ላይ መብ*ረቃዊ ጥ*ቃት አደረሰ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ በላይ ዕዝ 4ኛ ደጃዝማች ኮር አርበኞች ክፍለ ጦር ከብርጌዶች የተዉጣጣ ሃይል በቀን 25/5/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በሰቲት ሁመራ ዞን በጠገዴ ወረዳ እንባጋላይ ቀበሌ ላይ ዘር መርጦ ገዳ*ይ የብልፅግና ሰራዊት በመሸገበት ፍኖ መብረ*ቃዊ ጥ*ቃት በማድረሱ እስካሁን ባለዉ:- ✅ የሞ*ተ =ከ25 በላይ ✅ የተማረ*ከ = 14 ✅የቆ*ሰለ =5 ሲሆን ✅ 1 ብሬን ✅ ከ20 በላይ ነፍስ ወከፍ ክላሽ ልዩ ለዬ ተተኳሾች ተማር*ኳል። በጠያይሞቹ አንገት በጣ*ሽ ተኳ*ሾቹ ዉ*ጊያ እንደቀጠ ሲሆን ሙሉ መረጃዉን በየሰዓቱ እንገልፃለን። አርበኛ ባንዴራዉ ግርማይ የ4ኛ ደጃዝማች ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ

ሰበር ዜና‼️ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ፋኖን ተቀላቀሉ !   የብልፅግና መራሹ መንግስት አራት የሰራዊት አባላት ከአርሲ ዞን ቦሰት ወረዳ ቦሌ ከሚባል አከባቢ በመነሳት ሶስት ቀን የፈጀ የጫካ ጉዞ በማድረግ፤ በሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ወራዳ በመግባት አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ ኮር የነበልባል ክ/ጦር'ን ከነ'ሙሉ ትጥቃቸው መቀላቀላቸው ተገለፀ ። ዕድሚያቸው ለአቅመ-ውትድርና ያልደረሱ በብልፅግናው አገዛዝ በግዳጅ ታፍሰው መከላከያ ሰራዊት የነበሩ፤ በአሁኑ ሰዓት የአማራ ፋኖ ወደ አንድ መምጣቱን ተከትሎ እነሱም የነበሩበትን ስርዓት በመቃወም እና ለነፃነቱ የሚታገለው ፋኖ ጋር አብረው ለመታገል እና ይህን ጦርነት-ጠማቂ መንግስት ለማስወገድ በማሰብ ከኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ቦሰት ወረዳ  ቦሌ ከሚባል አከባቢ በመነሳት ለሶስት ቀን የእግር ጉዞ በማድረግ ነበልባል ክ/ጦር'ን እንደተቀላቀሉ ታውቋል ። የአገዛዙ ሰራዊት አባላት የነበልባል ክ/ጦርን ሲቀላቀሉ፤ የተሰማቸውን ደስታ እና ምድር ላይ ያለውን ሀቅ በተለይም አገዛዙ ያስተማራቸውን የሀሰት ትርክት ሲናገሩ፤ "እኛ ዕድሚያችን ለውትድርና ሳይደርስ ነው ታፍሰን ወደ መከላከያ የተቀላቀልንው፤ በአገዛዙ ቤት ቆይታችን ስለ ፋኖ የሚነገረንና አሁን ምድር ላይ መጥተን የተመለከትንው ፍፁም ልዩነት አለው ፥ ፋኖ ጀግና የአማራ ህዝብ አለኝታ መሆኑን በተለያዩ ነገሮች አስመስክሯል ። እናንተን ስለተቀላቀልን እጅግ ደስተኞች ነን ። መንግሥት ስለ እናንተ የነገረን ሀሳት መሆኑን መጥተን ከጎናችሁ ሆነን አረጋግጠናል ። እዚህ ከመጣን ብዛት ያላቸው የቡድን መሳሪዎች፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪዎች እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰራዊት አባላትን ተመልክተናል ። አሁን የቀሩትን ጓዶቻችን መጥተው ወንድሞቻቸውን (ፋኖን) እንዲቀላቀሉ እናደርጋለን ሲሉ ተደምጠዋል ። አክለውም፤ ለአማራ ህዝብ ብሎም ለሀገራችን እኛም ከዛሬ ጀምሮ ፋኖ ወንድሞቻችንን ተቀላቅለን በቆራጥነት እንታገላለን" በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ። አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ ኮር ሪፖርተር አርበኛ ጋዜጠኛ አበባየሁ ሰይፈ

photo content

​በታሪክ ማህደር ውስጥ ስማቸው በወርቅ ቀለም የሚጻፍ ጥቂት ጀግኖች አሉ። እነዚህ ጀግኖች ሞትን እንደ ሰርግ የሚቆጥሩ፣ ስለ ህዝባቸው ክብር ሲሉ ህይወታቸውን በቆራጥነት የሰጡ የጄነራል አሳምነው ጽጌ
​በታሪክ ማህደር ውስጥ ስማቸው በወርቅ ቀለም የሚጻፍ ጥቂት ጀግኖች አሉ። እነዚህ ጀግኖች ሞትን እንደ ሰርግ የሚቆጥሩ፣ ስለ ህዝባቸው ክብር ሲሉ ህይወታቸውን በቆራጥነት የሰጡ የጄነራል አሳምነው ጽጌ የርዕዮተ-ዓለም ልጆች ናቸው። "የአሳምነው ፋኖዎች" ሲባሉ ዝም ብሎ ስም አይደለም፤ የፅናት፣ የቁርጠኝነት እና የአልበገሬነት ትርጉም እንጂ። ሁሌም ስራ ላይ" ጀግኖች እንቅልፍ የላቸውም። ለጥቁር አስፓልቱ ባዕድ አይደሉም፤ ይልቁንም አስፓልቱ በነሱ የጀግንነት እርምጃ ይርገበገባል። "ሁሌም ስራ ላይ" መሆናቸው ​የማያቋርጥ ዝግጁነት፡ ጠላት ባልጠበቀበት ሰዓትና ቦታ ተገኝተው የህዝባቸውን ደህንነት የማስጠበቅ ብቃታቸውን። ​ለዓላማ መኖር፡ የግል ምቾታቸውን ትተው፣ ቀዝቃዛውን ሌሊትና ትኩሱን ፀሐይ ተቋቁመው ለታላቁ ዓላማ መሰለፋቸውን። በወሬ ሳይሆን በሚያሳዩት ተጨባጭ ድልና ስራ ማንነታቸውን መግለፃቸው ብቻ በቂ ነው።

የፋኖ ሰራዊት በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል። የማጥቃት መስመሮቹም.... ወልደያ ..ደሴ..ደብረብርሀን..አዲስ አበባ ***" ባህር ዳር ወረታ ደብረማርቆስ ደጀን አዲስ አበባ ***" ወለጋ ለቀምቴ አምቦ ቡ
የፋኖ ሰራዊት በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል። የማጥቃት መስመሮቹም.... ወልደያ ..ደሴ..ደብረብርሀን..አዲስ አበባ ***" ባህር ዳር ወረታ ደብረማርቆስ ደጀን አዲስ አበባ ***" ወለጋ ለቀምቴ አምቦ ቡራዩ አዲስ አበባ * መተማ ቋራ ጭልጋ ቆላድባ ጎንደር ወረታ ባህርዳር አዲስ አ. ** በለሳ ጎህላ እብናት ጋይት ደበረታቦር ባህርዳር አዲስ አበባ **

ሰላም እንደምን አላችሁ ውድ የቻናላችን ቤተሰብ ይህን ለሶስት ቀን መረጃዎች የአላጋራናችሁ ለግዳጅ ወጣ ብለን ስለነበር  ከልብ ይቅርታ እየጠየቅን ቀጣዩን 24 ስዓት እንደተለመደው እውነታውንና ትክክለኛውን የፋኖ መርጃዎች እዚሁ ከግንባር ሁነን የምናደርሳችሁ መሆኑን ከልብ እንገልፃለን ታዲያ ከእናንተ ጆይንና ሸር በማድረሰግ መወዳጀት ብቻ ነው ውድ አማራዊያን!!

አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ ፖለቲካ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ!! በዚህ ወቅት ወልቃይትም ሆነ ራያ፣ መተከልም ሆነ ደራ፣ ደብረዘይትም ሆነ በረራ፣ ደብረብርሃንም ሆነ ባህርዳር፣ ደሴም ሆ
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ ፖለቲካ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ!! በዚህ ወቅት ወልቃይትም ሆነ ራያ፣ መተከልም ሆነ ደራ፣ ደብረዘይትም ሆነ በረራ፣ ደብረብርሃንም ሆነ ባህርዳር፣ ደሴም ሆነ ጎንደር... ጥያቄዎቻችን ናቸው። የሁሉም ጥያቄዎቻችን መልስ ያለው 'አራት ኪሎ' ነው። የትናንቱ ጥገኛ ብአዴን ወልቃይትና ራያን፣ መተከልና ደራን አሳልፍ እንደሰጠው ሁሉ የዛሬው ተረኛ ተለ*ጣፊ የአማራ ብልፅግና ደብረብርሃንና ባህርዳርን፣ ደሴ እና ጎንደርን ለኦህዴድ ወረራ አሳልፎ መስጠቱን ማንም ቢሆን መዘንጋት የለበትም። እየታገልን ያለነው ትናንትም ዛሬም አሳልፎ በመስጠት አማራን ለሁለንተናዊ ህልውና አደጋ የዳረገዉን 'ጥገኛ እና ተለጣፊ ቡድን' እስከነአስተሳሰቡ ለመቅበር ነው። በአጭሩ የአማራ ህልዉና በዘላቂነት የሚረጋገጠው የባህርዳሩ ተላላኪ የክልል መንግስት ከሥሩ ሲነቀል፣ የአዲስ አበባዉ ፀረ አማራ አገዛዝ ፈፅሞ ሲወገድ፣ የአማራ ህዝብ በአዲሱ አማራዊ ድርጅት 'የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ' ተመርቶ ለስልጣን ሲበቃ ብቻ ነው። የወቅቱ ትኩረታችን 2015 ዓ.ም የጀመርነውን ጦርነት ማሸነፍ ብቻ ነው። አማራነት ይለምልም!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር በጠላት ላይ የደፈጣ ጥቃት ፈፀመ። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ➯ በቀን 25,05,
+2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር በጠላት ላይ የደፈጣ ጥቃት ፈፀመ። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ➯ በቀን 25,05,2018ዓ.ም መነሻውን ባህርዳር አድርጎ ከፍተኛ የመከላከያ አመራርን በሰባት ፓትሮልና ተጨማሪ መኪናዎች አጅቦ ጭንባ ደርሶ በሚመለስበት ሰሀት 102ኛ ኮር የ22ኛ ክፍለጦር ተናዳፊ ተርቦች ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ባህርዳር አፍንጫ ስር ይጎዲ ቀበሌ አቅራቢያ እሪ በከንቱ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ ጠላት አገር አማን ነው ብሎ በሚመለስበት ጊዜ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ድንገተኛ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በጠላት ላይ ሰባዊና ቁሳዊ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን፤ግሪሳው የብርሀኑ ጁላ ጦር ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ድንብርብሮ እየወጣ ወደ ባህርዳር ከተማ ገብቷል። ፋኖ አማረ ጌታቸው ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር የ22ኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት:: ጥር 25,2018ዓ.ም ክፋት ለማንም!በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተሰፋ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር በጠላት ላይ የደፈጣ ጥቃት ፈፀመ። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ➯ በቀን 25,05,2018ዓ.ም መነሻውን ባህርዳር አድርጎ ከፍተኛ የመከላከያ አመራርን በሰባት ፓትሮልና ተጨማሪ መኪናዎች አጅቦ ጭንባ ደርሶ በሚመለስበት ሰሀት 102ኛ ኮር የ22ኛ ክፍለጦር ተናዳፊ ተርቦች ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ባህርዳር አፍንጫ ስር ይጎዲ ቀበሌ አቅራቢያ እሪ በከንቱ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ ጠላት አገር አማን ነው ብሎ በሚመለስበት ጊዜ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ድንገተኛ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በጠላት ላይ ሰባዊና ቁሳዊ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን፤ግሪሳው የብርሀኑ ጁላ ጦር ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ድንብርብሮ እየወጣ ወደ ባህርዳር ከተማ ገብቷል። ፋኖ አማረ ጌታቸው ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር የ22ኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት::   ጥር 25,2018ዓ.ም ክፋት ለማንም!በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተሰፋ! ❤Dawit fano አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ሰበር ዜና! በአፋብን የተለያዩ አሃዶች ጥምረት መቄት ወረዳ ላይ ዲሽቃ እና ብሬን ተኳሾችን ጨምሮ በርካታ የፋሽስቱ ሰራዊቶች ተደመሰሱ:: አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር
ሰበር ዜና! በአፋብን የተለያዩ አሃዶች ጥምረት መቄት ወረዳ ላይ ዲሽቃ እና ብሬን ተኳሾችን ጨምሮ በርካታ የፋሽስቱ ሰራዊቶች ተደመሰሱ:: አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር፤ጎንደር ጠ/ግ/ዕዝ ጨጭሆ ብርጌድ እንዲሁም እራስ አንችም ክፍለጦር በጋራ በመሆን በጥላት ላይ በተሰራ ኦፕሬሽን በርካታ የፋሽስቱ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል! ጥር 25/2018 ዓ/ም በተደረገ የተጠና ኦፕሬሽን የፋሽስቱ ድሽቃ ተኳሽና ብሬን ተኳሾች እድሁም 39 እግረኞች ጭምር ተደምስሰዋል። ዘጠኙ ሚሊሻ 13 አድማ ብተና እድሁም 17 የመከላከያ ሰራዊት ሲሆኑ የአድማ ብተና የድሽቃ ተኳሽና የመቄት ወረዳ ሚኒሻ ብሬን ተኳሽም የተደመሰሱ ሲሆን በርካታ የብሬንና የነፍሰኮፍ ተተኳሾች በሶስቱም የአፋብን አሃዶች ተማርኳል። የጥላት ሰራዊት በበኩሉ የተለመደ የዘወትር ተግባሩን ማለትም አስከሬንና ቁስለኛውን በመኪና ጭኖ ወደ ፍላቂት ከተማ የፈረጠጠ ቢሆንም በመቄት ከተማ ከፍተኛ አለመረጋጋትና ፍርሃት በፋሽስቱ ሰራዊት ላይ ነግሷል። የብአዴን የመንፈስ ልጅ የሆኑት በሰባት ሽህ ብርና በሰባ ውሸት ተደልለው የአማራን ህዝብ የሚወጉ አድማ ብተናና ሚኒሻ ከብልፅግና ስብስብ የሚከፈላቸው ገንዘብም ሆነ የውሸት ፕሮፖጋንዳ ከውሻ ሞት ሊታደጋቸው ፈፅሞ ባለመቻሉ ወደማይቀረው ተሸኝተዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል ጥር 25/2018 ዓ.ም