ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
4 039
订阅者
+22224 小时
+3937 天
+1 35930 天
帖子存档
እንኳን ለ 86ኛው የአገው ፈረሰኞች ማህበር ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ!! 86ንቲ አዊው ፊርስትኒ ባልስ እንኳ ዴክስ ታምፁናስ! እኛ ማለት ታሪካችን፥ባህላችንና እሴቶቻችንን ነን። የዚህ ሁሉ ትው
እንኳን ለ 86ኛው የአገው ፈረሰኞች ማህበር ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ!! 86ንቲ አዊው ፊርስትኒ ባልስ እንኳ ዴክስ ታምፁናስ! እኛ ማለት ታሪካችን፥ባህላችንና እሴቶቻችንን ነን። የዚህ ሁሉ ትውስታ ደግሞ በትክክል ቆሞ ለመሄድ የሚያስፈልገን ደማችን ነው።የጋራ ማህበረሰባዊ ትውስታ/ትዝታ ጭቆናን ለመከላከል፥ማህበረሰባዊ መስተጋብርን ለማጠናከርና የጋራ ማንነትን ለማጉላት እጅግ ወሳኝ መሳሪያ ነው። "አንድን ህዝብ በተሳካ መንገድ ለማጥፋት ታሪኩን እንዳይረዳ ማድረግና ለራሱ ታሪክ ያለውን እይታ ማዛባት ወይንም መጋረድ ነው። " ወይም/እና "ትናንትን የተቆጣጠረ ነገን ይቆጣጠራል፥ ዛሬን የተቆጣጠረ ትናንትን ይቆጣጠራል " እንዲል ኦርዌል ታሪካችን በቅጡ ለማወቅ፥ ለመዘከር፥ለመቆጣጠርና ለመጠበቅ የምናደርገው ጥረት የህልውና ትግላችን አንዱ ወሳኝ አካል ነው። በድጋሚ እንኳን አደረሰን! አንድ አማራ! እስከ ምፃት አማራ! ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ፥ አዲስ አስተሳሰብ፥ አዲስ ተስፋ! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ጥር 23/2018 ዓ.ም አርበኛ ዘመነ ካሴ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር

ሰበር ዜና የአገዛዙ ጥምር ሀይል በወርቅ ደቦ ከተማ በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ተደመሰሰ። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቀረ (አፋብን ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ
ሰበር ዜና የአገዛዙ ጥምር ሀይል በወርቅ ደቦ ከተማ በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ተደመሰሰ። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቀረ (አፋብን ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አሀድ የሆነው አጥናፋ ብርጌድ አባላት ወርቅ ደቦ ከተማ ጥር 22/2018 ዓ/ም ከቀኑ አስር ሰዓት ዘልቀው በመግባት እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ባካሄዱት አውደ ውጊያ የአገዛዙን ጥምር ሀይል ሲያረግፋት አምሽተዋል። የአጥናፋ ብርጌድ ጀግኖች በአውደ ውጊያው ፋኖን እናጠፋለን እያሉ ሲፎክሩ የነበሩ አጥቤ አይለብሴ መዥገር የሆኑ የሚኒሻ አባላትን ጨምሮ ከ8 በላይ የአገዛዙን ጥምር ሀይል በሞት ሲሸኙት 7 ደግሞ በማቁሰል እዳሩን ሲያንጫጩት አድረዋል ።ከሟቾቹ መካከል በቀጠናው መንገድ እየመራ የፋኖ ቤተሰቦችን ሀብትና ንብረት ሲያዘርፍ የነበረው ቻሌ ገብሬ የተባለው ቀንደኛ ሚኒሻ ይገኝበታል ። ህልውናችንን በተባበረ ክንዳችን !!!! አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ ጥር 23 /2018 ዓ/ም

በዛሬዋ ቀን አባቶቻችን በአድዋ ጦርነት ፈረስና ፈረሰኞች ተቀናጅተው የሰሩትን ፀረ ወረራ፣ የተቀዳጁትን አለም አቀፋዊ ኩራትና ያወረሱንን ነፃነት ለማስታወስ ለሚከበረው የ86ኛው የአገው ፈረሰኞች በአል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ለማለት እወዳለሁ። ጥልያን በጥበብ ኢትዮጵያን ልትገዛ የትርጓሜ ተዛምዶ የሌለውን ውል አዘጋጅታ አስፈረመች። ድፍን ኢትዮጵያ የሀገሩ መወረር አንገብግቦት በአማራዊ መንፈስ ዘላኑ ግመልና ፈረሱን አስሮ፣ ገበሬው ሞፈርና ቀንበሩን ሰቅሎ ጦርና ጋሻውን አነገበ። ፈረሰኞችም የጦር ፈረሳቸውን አሰገሩ።ሀገሬው ለጠላት መትረየስ ደረቱን ሰጥቶ ወደፊት ገሰገሰ። ከጠላት መትረየሶች ይልቅ የህብረብሔራዊነት በሰፊው የታየበት የአርበኞች ፉከራና ሽለላ የአድዋ ተራራን አራደው። እስከ ጉልበቱ ድረስ ቦት አጥልቆ ከመጣው ጣልያን ይልቅ ስንቅ እንኳን በቅጡ ያልቋጠረው የሃገር አርበኛው የባዶ እግር ኮቴ ምድሪቷን አንቀጠቀጠ። ወጣት አርበኞች በግንባራቸው እሳት እየነደደ በደረታቸው ውሀ እየፈሰሰ ተራራው ወደ ሚፈርስበት ሰማይ ከምድር ወደ ተደበላለቀበት አድዋ ምድር ደረሱ። መጠቃት ያስቆጣቸው የጦር ፈረሶችም  ሽምጥ እየጋለቡ ድንገት የጣልያንን ጦር መሐል ለመሐል ሰንጥቀውት ገቡ።ዘራፍ የምኒልክ አሽከር፣ የቴዎድሮስ ልጅ፣ የአሉላ ቀኝ እጅ፣ የነ እገሌ ዘር እያሉ ዘመናዊ የጦር መሣረያ የታጠቀውን የጣልያን ጦር ይጎራርዱት ጀመር። ይሄንን ለነፃነት የተከፈለ ዋጋን ለማሰብ የተሰባሰባችሁ የአገው ፈረስና ፈረሰኞች የከበረ ሠላምታየን አቀርባለሁ። ለክብርና ለነፃነታችን ለተከሰከሰው አፅም ለፈሰሰው ደም፣ ለተቀላው አንገት ለተበሳው ደረት ሁሉ የከበረ ሰላምታየን አቀርባለሁ። መሬትና ህዝበችንን ለመጠበቅ ያሳዩት የአባቶቻችን ቁርጠኝነትነ የማይነወጥ ድፍረት ታጋያችንን ያነሳሳዋል። በተጨማሪም በዛሬው ዕለት በአሉን የምታከብሩ ፈረሰኞች በሒሊኮፍተር ተጭነው በታንክ ታጅበው የሚታደሙ እጃቸው በደም የጨቀዩ ፖለቲከኞች በአሉን ላልተገባ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማነሳሻ እንዳያደርጉት መጠበቅ ያስፈልጋል። አገውነትና አማራነት ውህድ የባህል፣ የታሪክና የማንነት ውጤቶች ናቸው። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! ከሰላምታ ጋር           ጥር 23/2018      መቶ አለቃ ማርቆስ አሞኘ

"ጦርነትር በቃኝ!ሰላም ይሻለኛል!" ብለህ እጅ ከሰጠህ በኋላ ፦"አዲስ ጦርነት ስለተቀሰቀሰ ትዘምታላችሁ!" ስትባል...
"ጦርነትር በቃኝ!ሰላም ይሻለኛል!" ብለህ እጅ ከሰጠህ በኋላ ፦"አዲስ ጦርነት ስለተቀሰቀሰ ትዘምታላችሁ!" ስትባል...

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንልክ እዝ እና የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የስልጠና መምሪያ በጋራ በመሆን የአማራ ህዝብ ለተከታታይ ዓመታት እየታገለ ያለውን የህልውና ትግል ግለቱን ጠብቆ እንዲሄድ አዲስ ምልምል ሰራዊት ለማሰልጠን ድርጅታችን አፋብን በስልጠና መምሪያው በኩል ዕቅድ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል እንደሚታወቀው በአሁኑ ስዓት የአማራ ፋኖ በአራቱም ዕዞች የተሻለ ሰራዊት ማደራጀት ተችሏል አሁን እያደረግን ላለነው የቀጠና ትሥስር እና የትግል ጉዞ አዲስ ሰልጣኝ ማሰልጠን ስለምንፈልግ ይህን ታሪካዊ ስልጠና ለማሰልጠን በርካታ ልምድ ያላቸው አሰልጣኞች ተቋሙ ስለሚፈልግ መስፈርቱን የምታሟሉ የኮማንዶ የአየር ወለድ እና የልዩ ሃይል አባለት በሽዋ እና በወሎ ማለትም ሁለቱ ዕዞች በተቆጣጠሯቸው ቀጠና በአካል በመሄድ ከ23/05/2018---30/05/2018 ድረስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ። 1ኛ ብሄር አማራ የሆነ 2ኛ ከማንኛውም ደባል ሱስ ነፃ የሆነ 3ኛ የኮማንዶ ሰርትፊኬት ማቅረብ የሚችል 4ኛ የማሰልጠን ልምድ ያለው 5ኛ በሚኖርበት አካባቢ በማህበረሰቡ ሊታውቅ የሚችል 6ኛ የማራ ህዝብን የህልውና ትግል የተረዳ 7ኛ እስከ መጨረሻው ለመታገል ፈቃደኛ የሆነ 8ኛ በሚኖርበት አካባቢ የቀበሌ መታወቂያ ማቅረብ የሚችል 9ኛ ዕድሜው እስከ 55 አመት ድረስ የሆነ ወደ ትግላችን ተቀላቅላችሁ የበኩላችሁን ሙያዊ ክህሎት እንድታበረክቱ እንዲሁም የዚህ ትውልድ የታሪክ ተካፋይ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። NB ኮማንዶ የሆነ በሙሉ ወደ ቀጠናው ሄዶ በመመዝገብ የትግላችን አጋር መሆን ይቻላል ! የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የስልጠና መምሪያ ሃላፊ መቶ አለቃ ዮሴፍ አስማረ(ጆሲ)

ወጣቱ የጦር ጠበብት ጀግና ማሸነፍ ሁሌም በግንባሩ ላይ የሜነበበው አርበኛ የአስራት ወልደየስ ልጅ ኢሳያስ ደመቀ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል መሪ የአሳምነው
ወጣቱ የጦር ጠበብት ጀግና ማሸነፍ ሁሌም በግንባሩ ላይ የሜነበበው አርበኛ የአስራት ወልደየስ ልጅ ኢሳያስ ደመቀ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል መሪ የአሳምነው ልጅ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ተስፋ ባለ ምጥቁ የጦር ጠበብት የሽዋው ለአመነበት የሚሞት ንስር

ሁሉም አማራ ማሰብ ያለበት አብይን ከ 4 ኪሎ ማስወጣት ላይ ነው ። ሌሎቹ አጀንዳዎች ከአብይ ዙፋን መውረድ በኋላ የምናሳካቸው ናቸው ። የአብይን ዙፋን ለማስጠበቅ የፋኖን ስም ከሌላ ፀረ-ብልፅግና ኢ
ሁሉም አማራ ማሰብ ያለበት አብይን ከ 4 ኪሎ ማስወጣት ላይ ነው ። ሌሎቹ አጀንዳዎች ከአብይ ዙፋን መውረድ በኋላ የምናሳካቸው ናቸው ። የአብይን ዙፋን ለማስጠበቅ የፋኖን ስም ከሌላ ፀረ-ብልፅግና ኢትዮጵያዊ ኃይል ጋር ማያያዝ ለፋኖ ሀገር አቀፍ የትብብር ትግል እውቅና የመስጠት ያክል ነው ። ቤተ መንግስቱ ላይ ቁጭ ብሎ በመድፍ እና በድሮን የአማራን ህዝብ እያጠፋ ያለ ኃይል በርታ ደግ አደረግህ እያሉ ላለመሞት የሚታጋለውን ፋኖን ለማነወር መሞከር ተክለ ብአዴንነት ስለሆነ ከብልፅግና እኩል እንታገለዋለን ። ብአዴን ጠላት ስለሆነ በሁሉም የአማራ ግዛቶች እኩል ማውገዝ እና እኩል ማጥቃት እንጅ እንደ ተወለድንበት አካባቢ ጠይም ትህትና ማሳየት በራሱ ጠላትነት ነው ። Girum Misalie ግሩም ምሳሌ

ሰበር ዜና! ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር ተንታ እና መቅደላ ወረዳ በመቶ የሚቆጠር የብልፅግና ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ሁለት የቡድን መሳሪያ እና ከ37 በላይ ክላሽ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: በመድፍ፣ በቢ ኤም 107፣ ዙ23 እና ሞርተሮች ታግዞ ከባድ ውጊያ የከፈተው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ዛሬ ጥር 22/2018 ዓ.ም ደቡብ ወሎ ዞን ተንታ እና መቅደላ ወረዳ እንዲሁም ማሻ ከተማ ዙሪያ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ያስተናገደ ሲሆን ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር የንጉስ ሚካኤል ኮር አሃድ ከሆነው ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ጋር በመጣመር በመቶ የሚቆጠር የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም በርካታ ጦር መሳሪያና ተተኳሽ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር በተጋድሎው ማሻ ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት በርካታ ጥምር ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ከመደምሰስ ባሻገር አንድ ስናይፐር፣ አንድ ብሬን፣ 21 ክላሽ፣ እና የእጅ ቦምቦች እንዲሁም 3000 የክላሽ ተተኳሽ ማርከዋል:: በተጨማሪም ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ማሻ ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት ባንዳን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣትና በመማረክ ጭምር ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል:: ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር ለሌላ ተጨማሪ ጦርነት እየተዘጋጀ ላለው ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ራስ ምታት የሆነ ታላቅ ድል ማሻ ከተማ ላይ ያስመዘገቡ ሲሆን በርካታ እግረኛ ሰራዊቱ የተመታበት ብሎም የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እንዲሁም ተተኳሽ የተማረከው አገዛዙ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብቷል::  ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ያስተናገደውና የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የብልፅግና ሰራዊት የበቀል አፈሙዙን ወደ ንፁሃን ጦር መሳርያ ያልታጠቁ አማራዎች በማዞር ተንታ አካባቢ አንዲት እናት በሞርተር የገደለ ሲሆን በዙ23 ዘጠኝ መኖሪያ ቤቶችን አቃጥሏል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 22/2018 ዓ.ም

ወዶገቦቹ የገቡበት አጣብቂኝና የተሰሙ አዳዲስ መረጃዎች! በቅርቡ አገዛዙ ካስፈረማቸው ወዶገብ የFaኖ አመራሮች መካከል ፣ በአዲስአበባ እየተንከራተቱ የሚገኙት ማስረሻ ሰጤና  ፈንታው ሙሀቤ  '' በሆቴል ቤት እየተሰቃየን ነው። ተረጋግተን ህይወት የምንጀምርበት መኖሪያ ቤት ስጡን!'' ሲሉ መማፀናቸው የተገለፀ ሲሆን ከአገዛዙ ሰዎች በኩል '' ይህን ለመሸፈን የሚያስችል የበጀት አቅም  ስለሌለን ባለሀብቶችን አስተባብረን እንዲገዛላችሁ ለማድረግ እንሞክራለን!'' የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸውም ለማወቅ ተችሏል! ፈንታሁን ሙሀቤ ከሁሉም በባሰ ሁኔታ በከፍተኛ የመገለልና የመረሳት ስነልቦናዊ ስብራት ውስጥ እንደሚገኝ የገለፁት ምንጮች  '' ምነው እዚያው ሞቼ ቀርቼ በነበር!'' ሲል መደመጡም ታውቋል! ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተለይ በጎንደር አካባቢ በርካቶች ተመልሰው ወደጫካ እየገቡ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በቅርቡ ከአገዛዙ '' በህግ የሚጠየቁት በህግ ይጠየቃሉ። የተቀሩት ተሀድሶ ተደርጎላቸው ለግዳጅ ዝግጁ ይሆናሉ'' የሚለው መረጃ መውጣቱን ተከትሎ ፣ እንዳሰቡትና እንደጠበቁት አልህንላቸው ብሎ ለችግር የተዳረጉት ወዶገብ ታጣቂዎች በቡድን በቡድን እየሆኑ ወደጫካ መግባትን ምርጫ እንዳደረጉ ተገልጿል። ይህን ተከትሎ አንድ አስተያየት ሰጪ '' እኚህ ተመልሰው ወደጫካ የሚገቡ ታጣቂዎች ከአደረጃጀት ውጪ የሚንቀሳቀሱ በመሆኑ በዘረፋና ውንብድና ላይ ተሰማርተው የአፋብንን ስም ጥላሸት እንዳይቀቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል'' ሲሉ አሳስበዋል። ከዚሁ ጋር በተያዪዘ በቅርቡ ወደአገዛዙ ገብቶ የነበረውና  የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ጉና ክፍለ ጦር እስቴ ዴንሳ ብርጌድ የፋኖ አባል የነበረው ሻንበል ውበቴ (ገደፋየ) የሚባል ወዶገብ ''ለFaኖ መረጃ ታቀብላለህ'' በሚል በመከላከያ መረሸኑ ተሰምቷል። የልጁን መገደል ያልካዱት ለአገዛዙ ቅርበት ያላቸው አክቲቪስቶች '' የተገደለው ደም ስላለበት ነው'' የሚል ማስተባበያ ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ እኚሁ ለአገዛዙ ቅርበት ያላቸው አክቲቪስቶች ፣ እነሱ ''የሰላም ጥሪ ተቀብለው ገቡ'' የሚሏቸውን ወዶገቦች ''ገሚሶቹ ከተወሰኑ የክልሉ አመራሮች ጋር  ተልእኮ ወስደው ለመፈፀም የገቡ 'ቀኜ' የተሰኘ የፋኖ አደረጃጀት ክንፍ በመሆናቸው አስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል'' ሲሉም ይደመጣሉ። ©ዘር ይሁን ገሠሠ

ሻለቃ መሪው እስከ አጃቢው ተቀንድሿል !! ጥር 22/05/2018ዓም የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለጦር ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ልጆች በዛሬው እለት ጎሽየ
ሻለቃ መሪው እስከ አጃቢው ተቀንድሿል !! ጥር 22/05/2018ዓም የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለጦር ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ልጆች በዛሬው እለት ጎሽየ ቀበሌ ላይ ታሪክ ሰርተዋል አንድ የሻለቃዋ አባል ከተማ ውስጥ ሰርጎ በመግባት ስምሪት በመስጠት ላይ የነበረውን ሻለቃ መሪ እሰከ አጃቢው እስከወዲያኛው በመሸኘት ሁለት ክላሽ ማርኳል ። የአብይ ተላላኪ ሰራዊት ሻለቃ መሪው ሲመታበት ተደነባብሮ ፈርጥጦ አዴት ገብቷል ። ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ልጆች ( የምድር ድሮኖች ) ወደቀደመ ዝናቸው እና አስፈሪነታቸው እየተመለሱ ነው ። ቀጠናው ላይ ለጠላት የእግር እሳት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እና አነቃቂ የተሳካ ሚሽን ፈፅመዋል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም !! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አጼ ዘረያቆብ ፩ኛ ኮር!! ባለነፍጡ ነፍጠኛ✊ ድል ለነፍጠኛ!!

ሰበር የድል ዜና: መቅደላ ላይ የአገዛዙን ጦር ወደ መግደያ ቀጠና ስቦ በማስገባት ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደረሰበት፦ አፋብን ምስራቅ አማራ ምኒልክ ዕዝ፣ የልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለጦር እና ራ
ሰበር የድል ዜና: መቅደላ ላይ የአገዛዙን ጦር ወደ መግደያ ቀጠና ስቦ በማስገባት ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደረሰበት፦ አፋብን ምስራቅ አማራ ምኒልክ ዕዝ፣ የልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለጦር እና ራስ አሊ ንጉስ ሚካኤል ኮር ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ፣ የተውጣጡ ሸ/አለቆች ታልቅ ጀብድ ፈጽመዋል! የአገዛዙ ጦር ከማሻ ከተማ ዙ-23 እና ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአገዛዙን ሰራዊት በመያዝ ወደ ባዙራ አነስተኛ ከተማ ቢገባም 23ኛ ክፍለጦር ... ጣመሬ እና ሴዳ ወደ ተባሉ ቦታቦዎች ስቦ በማስገባት እና ተመልሶ በመክበብ 1 ብሬን 1 ስናይፐር እና በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ሲማረክ፣ ጣመሬ ላይ ብቻ ባለ ቀይ ቦኔት ከ15 በላይ አስከሬን አሁን ህዝቡ አንስቷል፣ በርካታ አስከሬኑ ደግሞ በየጢሻው ሲዎድቅ፣ በርካታ ቁስለኛውን መቅደላ ሆስፒታል ማስገባት ተስኖት ወደ ተንታ ወስዷል። "እነሱ ገጠር ሲሄዱ እኛ ከተማ እንገባለን" በሚለው መርህ የንጉስ ሚካኤል ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር አካል የሆነችው ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ወደ ማሻ ከተማ በመግባት የአገዛዙ ጦር ላይ ጥቃት በመፈጸም፣ የጥላት ሀይልም በከፍተኛ መደናገጥ ባዙራ ላይ የነበረውን አስከሬን እና ቁስለኛ ሳያነሳ ተመልሷል። ይሄ ብቻ አይደለም፣ በርካታ ሀይሉ በማሻ ዙሪያ ተራሮች ተመቶበታል! ቁጥርን በውል ያላወቅነው የአገዛዙ ጦር ቁስለኛ ሆኖ መቅደላ(ማሻ) ሆስፒታል ሳይታከም ወደ ተንታ ተጉዟል🙏 ዝርዝር መረጃውን በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ይዘን እንመለሳለን....

"የዘሩትን ፍሬ ለመብላት" በእያንዳንዱ የፋኖ ቀጠና ውስጥ አስተዋይ፣ አርቆ አሳቢ፣ ከጠላትነት መንፈስ የፀዳ ስራዊት መገንባት ያስፈልጋል። እያንዳንዱን የፋኖ ስራዊት ውስጥ የፋኖነትን ጥንተ ተክለ ቁመና የተረዳ ያወቀ የአስተሳሰብ መከወን ያስፈልጋል፡፡ በእያንዳንዱ የፋኖ ቀጠና ውስጥ በሽርፍራፊ ጥቅም በመታለል፤ በሰሞኔ ሳንቲም በመደለል፤ በመርፌ ቀዳዳ ያህል የግንዛቤ መንገድ በመጓዝ የልዩነት የእርስ በእርስ የጥፋት አንጃ ለመፍጠር ከሚሯሯጡ ተግባራት የፀዳ ስራዊት ማዋቀር ይገባል። በእያንዳንዱ የፋኖ ስራዊት "፩" አማራ ብሎ የትግሉን የኪዳን አቋቋም፤ ለነፃነት ማማ አገዛዙን ለመጣል የትግሉን የቅድስና መስመር ያዘለ የስነልቦና በሳል አመለካከት ያለው አደረጃጀት መፍጠር የሚችል ስራዊት መመስረት ያስፈልጋል፡፡ በእያንዳንዱ የፋኖ ሰራዊት የብልጽግና የጥፋት ስልታዊ እቅድን ወደጎን በመተው ለህዝብና ለህልውና ትግል መውጣቱን ያረጋገጠ አመለካከት የተከተለ መስመር ማሳየት ይገባል፡፡ ስርቆትን በመከናነብ፣ ባንዳነትን በፋኖ ዩኒፎርም በመለባበስ የፋኖነትን ሥነ-ተፈጥሮ ለማጥፋት መሯሯጡ ለሰኞ ጠቃሚ አጀንዳ ቢመስልም ለማክሰኞ ምላሽ ግን የመከራው ዕዳ መብዛቱ"አይቀርምና እያንዳንዳችን እራሳችንን መመርመር ይጠበቅብናል፡፡ ከዚህ ውጭ ፋኖነት የትርፍ ክፍፍል የፖለቲካ ሽፋን የአብይ አህመድ የፕሮፓጋንዳ የሚዲያ አጀንዳ ፎቶሾው አይደለምና ሁሉም ራሱን መጠየቅና በእውነተኛ የትግል መስመር ተሰልፎ በተጠንቀቅ መቆም ይገባል እንላለን፡፡ 👌ማሳሰቢያ፦ መረጃው የ64ኛ ክፍለ ጦር የውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን ነው፡፡ አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! ጥር 22/2018 ዓ.ም #የበላይ_ትንፋሾች #አባ_ኮስትሮች የምስራቅ አፍሪካ የውሀ ማማ ጮቄ ተራራ ላይ 💪💪💪

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ  ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ምስራቅ አማራ  ኮር1 ባለሽርጡ ክፍለጦር! ፋኖ በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች ህዝባዊ መድረኮች እንደቀጠሉ ናቸው!        ጥር 22/2018 ዓ.ም በአፋብን  ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ  ኮር1, ባለሽርጡ  ክፍለ ጦር እና የልጂ እያሱ ኮር አመራሮች  በተቆጣጠሯቸው  የተውለደሬ  ወረዳ ቀበሌዎች መካከል ከሀይቅ በቅርብ እርቀት የምትገኘውን  017 ቀበሌ  /ሰግለን/    ህዝቦች ጋር የክፍለ ጦርና የኮር አመራሮች  ጥር  22/2018 ዓ.ም ጥልቅ ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ የተካሄደው የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥና የምስራቅ አማራ ኮር 1 ዘመቻ  አርበኛ ፋኖ እንድሪስ ጉደሌ እና  ሌሎች የኮር አንድ እና የልጂ እያሱ ኮር  አመራሮች በተገኙበት ሲሆን ህዝቡም ሃሳቡን በነፃነት የገለፀበት ከአመራሮቹም በቂ ምላሽ የተሰጠበት መሆኑን ከህዝቡ በተገኙ አስተያየቶች ተረጋግጧል። ህዝቡም ፋኖ ከመምጣቱ በፊት ሰብላችን ይበላና ይወድም ነበር፣የከብቶቻችን መዋያ ጥብቅ ስፍራዎች በህገወጥ በነፍስ ወከፍ ደኖች እየተጨፈጨፉ ለእርሻ ስራ ይውሉ ነበር ።በአገዛዙ ተልኮ የተሰጣቸው ሌቦች፣ ወንበዴዎች በዝተው ነበር፣ህዝቡ በነፃነት ማሳ ውሎ አይመጣም ነበር፣በአጠቃላይ ህዝቡ በስጋትና በፍራቻ ቆፈን ውስጥ ይኖር ነበር ነገር ግን ፋኖ ከመጣ ወዲህ ነፃነታችንን አግኝተናል።     ማህበረሰቡ አያይዞም  ትግሉን እኛም እንደግፈዋለን ከጎናችሁ ነን በማለት ህዝቡ ለፋኖ ድጋፉን ችሮታል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምስራቅ አማራ ኮር1 የባለሽርጡ ክፍለጦር   ቃል አቀባይ ፋኖ ደምሌ  መኮነን  መረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ   ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ      ጥር 22/ 2018 ዓ.ም]