ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 132
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+4577 أيام
+1 19430 أيام
أرشيف المشاركات
የፋኖ አላማ በደም የምትታጠበውን አገር ነፃ ማውጣት ነው
=============================
Estibel Alemu Zerihun
ይህ ትግል በአሸናፊነት የሚደመደመው በመሣሪያ ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በያዝነው የሞራልና የሰብአዊነት የበላይነት ነው።
የፍቅር ጥይት፤ ለአገዛዙ ወንበር የመጣኸው ወታደር ሆይ፣ በሕዝብ እቅፍ ውስጥ መሆንህን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።
በነፃነትና በሕልውና ትግል ግንባሮች ላይ የምናየው ትዕይንት፣ ዓለምን የሚያስደንቅና የትግላችንን መንፈሳዊ ልዕልና የሚያሳይ ነው። አንተ! ወደህም ይሁን ተገደህ የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም፣ ሕዝብን በድሮንና በከባድ መሣሪያ እንድትጨፈጭፍ ታጥቀህ የመጣህ ወታደር ዙፋን ጠባቂ ወታደር ነበርህ።
ነገር ግን፤ የተማረክህ ዕለት የገጠመህ ሞት ሳይሆን ሕይወት ነው፤ በጥላቻ የታወረ አፈሙዝ ሳይሆን በፍቅር የተዘረጋ የሕዝብ እጅ ነው። አንተ! ልትገድለው፣ ቤቱን ልታፈርስና ልጆቹን ልታሳጣ የመጣኸው ይኽ "ጠላት" ያልከው ሕዝብ፤ ዛሬ የቆሰለ አካልህን በጨርቅ እየጠቀለለ ያክምሃል። ጥይት ልታጎርሰው የመጣኸው ሕዝብ፣ ካለው ጥቂት ጉርሻ አከፋፍሎ አብልቶሃል።
ይህ ተግባር ትግላችን ከወንበርና ከጥቅም በላይ መሆኑን የሚያሳይ ከፕሮፖጋንዳ ያለፈ ድንቅ ተግባር ነው። እኛ የምንዋጋው የሥርዓቱን ግፍ እንጂ የአንተን ማንነት አይደለም። ደጋግመን እንደተናገርነው፣ ትግላችን የጥላቻ ሳይሆን የነፃነት፣ የፍትሕና የእኩልነት ነው። ዓላማችን፤;እኩልነት የጠፋባትን፣ ፍትሕ የራቃትንና በንጹሐን ደም የምትታጠበውን ሀገር ነፃ ማውጣት ነው። አገዛዙ አንተን ለሥልጣኑ "መሣሪያ" አድርጎ ሲጠቀምብህ፣ እኛ ግን እንደ "ሰው" እናከብርሃለን። አንተን መግደል ሳይሆን አንተ ጋር የተሸረበውን የባርነት ሰንሰለት መበጠስ የትግላችን አካል ነው።
እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም የምናስተላልፈው መልዕክት! በየግንባሩ ያላችሁና ለአገዛዙ ጥላቻ ተሰልፋችሁ የምትገኙ ወታደሮች ሆይ፤ አስተውሉ! ጠላታችሁ ማን ነው? ጠላታችሁ የተራባችሁ ዕለት የሚያበላችሁ፣ የተጠማችሁ ዕለት ውኃ የሚያጠጣችሁ ይህ የዋህና ጀግና ሕዝብ ነውን? በገዛ ወገኑ ላይ ድሮን የሚያዘንብ አገዛዝ ወይስ የቆሰለ ምርኮኛን የሚያክም ሕዝብ የትኛው ነው ለሀገር የሚቆረቆረው?
ለአገዛዙ ሰራዊት የቀረበ የሕሊና ጥያቄ፤ ወታደር ሆይ! ይህን ፎቶ በጥልቀት ተመልከተው፤ የታጠቀው ማን ነው? አንተ የጥፋት መሣሪያ ታጥቀህ መጣህ፤ አርሶ አደሩ ግን የሕይወት መሣሪያ የሆነውን "እንጀራ" ይዞ ቀረበልህ። ጠላትህ ማን ነው? አዛዦችህ "ሽፍታና ጽንፈኛ" ብለው ሊያስገድሉህ የላኩህ ሕዝብ፣ ዛሬ በረሃብ እንዳትዝል የላብ እህሉን እያቀረበልህ ነው። ለማን ትሞታለህ? አንተ ቆስለህ ስትማረክ ጀርባውን የሰጠህ አገዛዝ ወይስ የቆሰለ አካልህን አክሞ ያበላህ ሕዝብ የትኛው ነው ለክብርህ የሚመጥነው?
ይህ ትግል በአሸናፊነት የሚደመደመው በመሣሪያ ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በያዝነው የሞራልና የሰብአዊነት የበላይነት ነው። አፈሙዝ ታጥቀህ ልትገድለው ብትመጣም፣ ሕዝባችን በፍቅርና በሰብአዊነት ይዞሃል። ይህ ፍቅር ነገ ለምትፈጠረው አዲስና ፍትሐዊት ኢትዮጵያ መሠረት ነው።
ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ማውቅ ያለበት ዋና ነገር፤ ይህ ትግል የሁለት ታጣቂዎች ሽኩቻ አይደለም። ይህ ትግል በግፈኛ አምባገነንነት እና በሰብአዊነት መካከል ያለ ግብግብ ነው። አገዛዙ በንጹሐን ላይ ድሮን ሲያዘንብ፣ የነፃነት ኃይሎችና ሕዝቡ ግን ለምርኮኞች የጄኔቫን ስምምነት (Geneva Convention) በላቀ ሁኔታ በተግባር እየተረጎሙት ይገኛሉ።
ዓለም ሊያውቀው የሚገባው ሀቅ ቢኖር፣ በኢትዮጵያ ምድር ፍትሕንና ሰላምን ሊያመጣ የሚችለው አፈሙዙን ለሰው ልጅ ክብር ዝቅ የሚያደርገው በፋኖ ኃይል እንጂ፣ ሕዝቡን እንደ ጠላት ፈርጆ የሚጨፈጭፈው አምባገነን ሥርዓት አለመሆኑን ነው።
ጥላቻን በፍቅር እናሸንፋለን!
ትግላችን ለፍትሕ፣ ለእኩልነትና ለነፃነት ነው!
ክብር ለሰብአዊነት ዘብ ለቆመው ሕዝባችን!
አዲስትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ታህሳስ 28/2018ዓ.ም
+1
#የአፋብሃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ እዝ #ተወርዋሪ_በላጎ_ሻለቃ የአባት አርበኛ ሻለቃ ጋሽ ሀሰን ቀበለ ከድሽቃ ምድብተኛዋ የመከላከያ ሻምበል #2_ጥቁር_ክላሽ_በመማረክ ታላቅ ስራ ሠርተዋል።
ታህሳስ 29/2018 ዓ.ም
ከአፋብኃ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን በሙሉ እንኳን ለጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!
በመከራና በፈተና ውስጥ ሆነህ ለነገ በተስፋ እየታገልክ ላለኸው የአማራ ህዝብ ሆይ!
ለህልውና ብሎም ለሃገርና ለህዝብ ደህንነት በተጋድሎ ላይ ያላችሁ የፋኖ ሰራዊት አባላት ሆይ!
እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በፅናት አደረሳችሁ።
ዛሬ በከባድ ፈተና መካከል ብንሆንም፣ አንድነታችንና የሰውነት ክብራችንን ጠብቀን የማይረሳ አኩሪ ተጋድሎ እያደረግን እንገኛለን።
"ገና" የሚያስታውሰንን የተስፋ ብርሃን በልባችን ይዘን የአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ ሙሉ በመሉ ተቀልብሶ፣ ነፃነቱ እስከሚረጋገጥ ድረስ እና የሃገሩ ኢትዮጵያ ባለቤት እስኪሆን ድረስ የጀመርነውን ትግል ወጥ በሆነ አማራዊ አንድነት አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እየገለፅን፣ ለአማራ ህዝብ እና ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን፣ ለፋኖ ሰራዊት በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፤ ገና የተስፋ መልእክቱ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ)

የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኋይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ እዝ አፄ ዘርያእቆብ ፩ኛ ኮር የ7ለ70 ክፍለ ጦር መሪ አረጋ ሙሉነህ የገና በአልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል
ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲሁም ፀሀዩ ሳይበግራችሁ ጨለማዉ ሳያግዳችሁ ዱሩ ቤቴ ጫካዉ ጎረቤቴ ብላችሁ ለሀገራችሁ ክብር ለማስጠበቅ ብላችሁ የወጣችሁ የአማራ ፋኖዎች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፋል ።
በአሉ የሰላም የፍቅር የአንድነት የመተሳሰብ እንዲሁም የመረዳዳት አንዲሆን መልካም ምኞቱን እየገለፀ እንሆ በአሉ ከምን ጊዜዉም በላይ ሰላማችንን በመጠበቅ ከጎናችን በሒዎት የተለዩንን የቆሰሉትን እና አቅመደካሞችን በመጠየቅ የምናከብርበት እንዲሆንልን ሲል አስተላልፏል
መልካም የገና በአል
አረጋ ሙሉነህ
የ7ለ70 ክፍለጦር ዋና አዛዥየእንኳን አደረሳችሁ መልእክት
አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኋይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ እዝ አፄ ዘርያእቆብ ፩ኛ ኮር የ7ለ70 ክፍለ ጦር አዛዥ አረጋ ሙሉነህ የገና በአልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል።
ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲሁም ፀሀዩ ሳይበግራችሁ ጨለማዉ ሳያግዳችሁ ዱሩ ቤቴ ጫካዉ ጎረቤቴ ብላችሁ ለሀገራችሁ ክብር ለማስጠበቅ ብላችሁ የወጣችሁ የአማራ ፋኖዎች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፋል ።
በአሉ የሰላም የፍቅር የአንድነት የመተሳሰብ እንዲሁም የመረዳዳት አንዲሆን መልካም ምኞቱን እየገለፀ እንሆ በአሉ ከምን ጊዜዉም በላይ ሰላማችንን በመጠበቅ ከጎናችን በሒዎት የተለዩንን የቆሰሉትን እና አቅመደካሞችን በመጠየቅ የምናከብርበት እንዲሆንልን ሲል አስተላልፏል
መልካም የገና በአል
አረጋ ሙሉነህ
የ7ለ70 ክፍለጦር ዋና መሪ
ገብርኤል, ከሰማይ, ኤልሳቤት, ከምድር ባንድ, መሰከሩ, ስለድንግል, ክብር!! ለኛ,ሲል ከሰማይ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነብሷ ነብስ ነስቶ ተወልዶ አዳነን ከባርነት ነጣ አወጣን!! እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ለየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ!!
የዳዊት አምላክ አገራችን እና ሕዝቦቿን ይባርክ ይጠብቅልን! የጀግናው የአሳምነው ዕዝ ክንደ ነበልባል የአሳምነው ልጆች አርበኛ አማረ ታዘዘና አርበኛ ሱራፊል
ሰበር የገና ስጦታ 🎄🎄🎄
4የሚሊሻ አባላት 74ኛ ክ/ጦር ጎንቻ ሲሶ እነብሴ ወረዳ ተቀላቅለዋል።
🎄🎄🎄🎄4 ክላሽ
🎄🎄🎄10ካዝና ከነ ተተኳሹ
🎄🎄🎄🎄4 የደረት ትጥቅ በመያዝ በዛሬው እለት ፋኖን ተቀላቅለዋል ።
1.ክንድ አበባው 2.ጌትነት ሙሉ
3.ሙጭየ በላቸው 4.ታዴ ይደግ ሰርዓቱ በአማራ ላይ እየፈፀመ ያለውን ግፍ ውስጥ ላይ ሆነን ማየት ስላልቻልን ቀሪ ጊዜያችን የአማራን ህዝብ ለመካስ ተዘጋጅተናል ብለዋል በአመራሮችም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ታህሳስ 29/2018 ዓ.ም
አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ
የቴወድሮስ ዕዝ 2ዐ1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+4
ዘመቻ መሪው እና ብሬን እረዳቱ አገዛዙን ሰራዊት በመታኮስ 64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቀሉ።
10 አለቃ አሰግድ አስጠራው የክፍለ ጦር ቀኝ እና ምሃንዲስ ዘመቻ መሪ እና አክሊሉ ባይነስ ብሬን እረዳት ቢቸና ከተማ ከሚገኘው 6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር 75ኛ ክፍለ ጦር ቀኝ እና መሃንዲስ ብሬን እረዳት ሲሆኑ ቢቸና ከተማ ከምሽቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ አብረውት የነበሩ ጓዶቹን ክላሽ ነጥቆ በመታኮስ በጠላት ኃይል ላይ ጉዳት በማድረስ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር #64ኛ_ክፍለ_ጦር ተቀላቅለዋለ ።
#ሚሊሻ_ደረሰ_ዋለ ሸበል በረንታ ወረዳ ሌዲና አካባቢው ቀበሌ ተወላጅ ሲሆን በሸበል በረንታ ወረዳ መርገጭ 01 ቀበሌ የሚገኘው የአገዛዙን ቅጥረኛ ሚሊሻ በካባቢው ማህበረሰቡ ላይ የሚፈፅመውን #ዝርፊ በመቃወም ታህሳስ 29/2018 ዓ.ም 64ኛ ክ/ጦር ተቀላቅሏል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስተ ተስፋ፣ አዲስ አስተሳሰብ!!
ታህሳስ 29/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
ትግላችን ትውልዱን በሙሉ አርበኛ ማድረግ ነው‼️
እንኳን ለ2018ዓ/ም ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ አደረሰን። የገናን በዓል ስናከብር እየሱስ ክርስቶስ በዕለተ አርብ በመከራ መስቀሉ ተሰቅሎ የ5500አመት የሰው ልጆችን ሁሉ የእዳ ደብዳቤ በቤዛነቱ እና በመስዕዋትነቱ ለመቅደድ በቤተ መንግስት ይወለዳል ተብሎ ሲጠበቅ በከብት ጉረኖ ተወልዶ ዓለምን እንዳስደነቀ ሁሉ የዘመናችን የዕለተ ዓርብ የመስዋዕት በጎች ለመሆን በመቁረጥና በመቁረብ ዓለም የምቾትና የድሎት ስፍራዎች ብሎ ከበየናቸው ቦታዎች ከመገኘት ይልቅ የህልውና አደጋ ለገጠመው ህዝባችን መስዋዕት ለመሆን የስቃይ፣የእንግልት እና የመከራ ቦታዎችን በመምረጥና በመጋፈጥ ሊሆን ይገባል።
አርበኛ የሚለው ቃል ጥሬ ትርጉም ዓርብ የተገኘ ሲሆን በዕለተ ዓርብም እራሱን ለሌሎች ምቾት፣ድሎት፣ፍላጎት ፣ህይወትና ህልውና አሳልፎ ለመስጠት ሲል የመከራ ቀንበርን በፈቃዱ የሚሸከም ነውና እኛም የአዲሱ ትውልድ የአማራ ህዝብ ወኪሎች የገናን በዓል ስናከብር ከቻልን ትውልዱን ሁሉ አርበኛ ለማድረግ በመስራት ሲሆን ካልቻልን ደግሞ ቢያንስ እራሳችንን አርበኛ አድርገን የማያልፍ ታሪክ ሰርተን ለማለፍ ነፍስያችንን ወትሮ ዝግጁ በማድረግ ይሁን። በመጨረሻም በአራቱም የአማራ አፅመ ርስቶች ስር የምትገኙ ለአማራ ህዝብ ህልውነት ስትሉ በዱር በገደሉ ለምትዋደቁ ታጋዩች፣ ለትግላችን ደጋፊ ኢትዮጵያውያን እና ትግላችንን በአይነ ቁራኛ ለምትከታተሉ ለሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም ደግሞ አጋር አካላት በሙሉ:-
አሁን ያለንበት ወቅት ትግላችን የመጥራት፣ የመንፃት፣የስርየት እና የመፅናት ወቅት ነውና በዚህ ወቅት በትግላችን ወንፊት በአግባቡ ተነፍቶ ፍሬው ከገለባው፣ ብስሉ ከጥሬው እና ምርቱም ከግርዱ እየተለየ ነውና የታጋይነት ካባን ደርበው ህሊናቸውንና ህዝባቸወን ሲያጭበረብሩ የቆዩ ታጋይ መሳዮች ወደቀጣሪያቸውና ወደፈጣሪያቸው ሲመለሱ አይታችሁ አትደንግጡ አትሸበሩ።ይልቁንም ደስ ይበላችሁ ።የታደለ እንደ ፊያታዊው ዜይማ እድሜውን በሙሉ ሲዘርፍና ሲያጭበረብር ኖሮ በክርስቶስ የስቅለት ዕለት ጌትነቱንና መሀሪነቱን አይቶ ማረኝ ብሎ ይማራል ያልታደለ ደግሞ ተቃራኒውን ያደርጋል።
_አዲስ ትውልድ!
_አዲስ አስተሳሰብ!
_አዲስ ተስፋ!
©አርበኛ ዳሞት አለኸኝ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድርስ ዕዝ 206ኛ ኮር ሰብሳቢ
የተከበረው የአማራ ህዝብና የትግላችን ደጋፊዎች፤ የተከበራችሁ የፋኖ ሰራዊታችንና አመራሩ እንዲሁም የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር ቢቡኝ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አስተዳደር #ጊአኮ አመራርና አባላት ክቡራትና ክቡራን ወገኖች ከሁሉም በፊት በጠላት ከብክቦ የማያልቅ የጦርነት ድግስ በመደገስ የክልላችንን ዉድቀትና ብሶት ለመቻልና ለመቋቋም ሀይል የሰጠንንና እዚህ ያደረሰንን የድንግል ማሪያም ልጅ የሆነዉን #አምላካችንን ላመሰግን እወዳለሁ።
እንዲሁም ባለፈው ሁለት ዓመት ተኩል የአደባባይ ወንጀለኛው፣ ጨፍጫፊው፣ገዳዩ፣በጅምላቀባሪው፣ አፈናቃዩ፣ዘራፊው፣ሀይማኖት የለሹ እና ሀይማኖተኞችን አሳዳጁ የብልፅግና ሥርዓት ያለምንም ጥፋትና ፍርድ በያለበት የአማራ ሕዝብ በየሀሩርና ቁሩ፣ በየጋራና ሸንተረሩ፣ በየገደሉና ዱሩ እና በየከተማዉ ለዚህ ትግል ብለዉ ቀድመዉን የተሰዉ መስዋትነትን ለተቀበሉት ሰማዕታት ወገኖቻችን በህሌና በቀጥታ ልናስታዉሳቸዉ አሳስባለሁ።
ዛሬ ውድ ክልላችን ዳብዟ ጠፍቶ ህዝቧ ምስቅልቅሏ ወቶ ስነልቦናው እየተሰለበ አይኑ እያየ ጆሮዉ እየሰማ ባህሉ እየተንቋሸሸ ታሪኩ እየተደለዘ ቅርሱ እየተመዘበረ ይገኛል።ይህ ታሪካዊ ስተት እንዲፈፀም የሚያበረታቱ የአማራ ልጆችን እያወገዝን ለዚህ የነፃነት ትግል ብላችሁ ከቤተሰብ ወጥታችሁ በየሀሩርና ቁሩ፣ በጋራና ሸንተረሩ፣ በገደሉና ዱሩ እየታዋደቃችሁ ያላችሁ ወገኖቸ እንኳን ለጌታችን ለመደሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹህ አደረሰን!
አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ።
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ
201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር የቢቡኝ ወረዳ ጊዜአዊ የመንግስት አሰተዳደር ሚዲያና ግንኙነት ሀላፊ
ኢንጅነር ያብስራ ጸጋየ
#የጥንቃቄ_መልዕክት‼️
ደጋዳሞት በተለይ ዳማ ቀጠና ያሉት መሉ ቀጠናው የድሮን ቅኝት ከጥዋቱ 11 ሰአት ጀምሮ ተደርጓል ፣እየተደረገም ይገኛል ስለሆነም ጥንቃቄ አይለየን‼️
#ማሳሰቢያ የአብይ አህመድ አገዛዝ በዛሬው ዕለት በዓሉን ምክንያት በማድረግ መዘናጋቶች ይኖራሉ በሚል ሀሳብ አጋጣሚዎችን ለመጠቀም በእግረኛና በአየር ሀይል ጥቃት መሞከሩ አይቀሬ ስለሆነ በዬትኛውም ቀጠና የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ሰራዊት በዓሉን ሲያከብር ለእግረኛ ሆነ ለድሮን በማያጋልጥ መልኩ እንዲሆን እናሳስባለን!
28/ዐ4/2018 ዓ.ም
_*አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት ለሁሉም የሰራዊት አመራርና የሰራዊት አባሎቶች መድረስ አለበት* :-_
ጠላት በዓልን ምክንያት በማድረግ የፋኖን ሰራዊትና አመራር አናጠቃለን ብለው ካቀዷቸው ዕቅዶች ውስጥ የሚከተሉት ናቸው።
1ኛ/ በዓልን ምክንያት በማድረግ ወደገጠሩና ፋኖ ወደያዛቸው ቀጠናዎች በሲቪል አስርጎ በማስገባት አመራሩን መምታት
2ኛ/ የፋኖ ሰራዊት ለበዓል ወደቤተሰብ ሊሄድ ሲለሚችል በየሰፈሩ የሰፈር ሚኒሻዎችን ለመረጃነት በመጠቀም ማፈንና መያዝ።
3ኛ/ ለበዓል ሰራዊቱ ሊዘናጋና መጠጥ ሊጠጣ ስለሚችል መረጃን ዘርግቶ ሰርጎ በመግባት ማጥቃት
4ኛ/ ሰራዊቱ ሰብሰብ ብሎ በዓል ሲያከብር መረጃዎችን አስርጎ በማስገባት በድሮን መምታት እና የመሳሰሉትን ዕቅዶች በማቀድ በዓልን እየጠበቀ መሆኑን መረጃዎች የደረሱን መሆኑን እየገለፅን
የጠላትን እቅድ ማክሸፊያ ጥንቃቄዎች
1ኛ የሰራዊትም ሆነ የአመራር የፍቃድ እንደሌለ አስጠንቅቆ መንገር
2ኛ ወደኛ ቀጠና የሚመጡ ፀጉረ ልውጥ ሰዎችን በአግባቡ መከታተልና ከተገኙም በአግባቡ ይዞ ምርመራ ማድረግ
3ኛ ለበዓል ስንሰባሰብ ከሲቪሉ ማህበረሰብ ራቅ ያሉ ጫካማ ቦታዎችን መጠቀም
4ኛ/ ቋሚ ቦታዎችን አለመጠቀም እና በተቻለ መጠን ስብስቦችን ማስወገድ
5ኛ/ ጠላት ይመጣባቸዋል ተብሎ በሚጠረጠሩ ቦታዎች ላይ የቀንና የማታ ደፈጣዎችን ማድረግ
6ኛ/ ለረጅም ጊዜ ጫዋታና ጭፈራዎችን አለማድረግ እና ጫዋታ ካስፈለገም በከፍታ ቦታዎች ላይ የድሮንን እንቅስቃሴ የሚከታተል ተመልካች ማስቀመጥ ሰራዊቱን ደህንነት መጠበቅ። በመጨረሻም ሁሉም አመራር ለሁሉም አመራር እንዲደርስ አድርጉ እስከ ሻለቃ አመራሮች እንዲደርስ ይደረግ።
ይህ ትግል በአሸናፊነት የሚደመደመው በመሣሪያ ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በያዝነው የሞራልና የሰብአዊነት የበላይነት ነው።
የፍቅር ጥይት፤ ለአገዛዙ ወንበር የመጣኸው ወታደር ሆይ፣ በሕዝብ እቅፍ ውስጥ መሆንህን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።
በነፃነትና በሕልውና ትግል ግንባሮች ላይ የምናየው ትዕይንት፣ ዓለምን የሚያስደንቅና የትግላችንን መንፈሳዊ ልዕልና የሚያሳይ ነው። አንተ! ወደህም ይሁን ተገደህ የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም፣ ሕዝብን በድሮንና በከባድ መሣሪያ እንድትጨፈጭፍ ታጥቀህ የመጣህ ወታደር ዙፋን ጠባቂ ወታደር ነበርህ።
ነገር ግን፤ የተማረክህ ዕለት የገጠመህ ሞት ሳይሆን ሕይወት ነው፤ በጥላቻ የታወረ አፈሙዝ ሳይሆን በፍቅር የተዘረጋ የሕዝብ እጅ ነው። አንተ! ልትገድለው፣ ቤቱን ልታፈርስና ልጆቹን ልታሳጣ የመጣኸው ይኽ "ጠላት" ያልከው ሕዝብ፤ ዛሬ የቆሰለ አካልህን በጨርቅ እየጠቀለለ ያክምሃል። ጥይት ልታጎርሰው የመጣኸው ሕዝብ፣ ካለው ጥቂት ጉርሻ አከፋፍሎ አብልቶሃል።
ይህ ተግባር ትግላችን ከወንበርና ከጥቅም በላይ መሆኑን የሚያሳይ ከፕሮፖጋንዳ ያለፈ ድንቅ ተግባር ነው። እኛ የምንዋጋው የሥርዓቱን ግፍ እንጂ የአንተን ማንነት አይደለም። ደጋግመን እንደተናገርነው፣ ትግላችን የጥላቻ ሳይሆን የነፃነት፣ የፍትሕና የእኩልነት ነው። ዓላማችን፤;እኩልነት የጠፋባትን፣ ፍትሕ የራቃትንና በንጹሐን ደም የምትታጠበውን ሀገር ነፃ ማውጣት ነው። አገዛዙ አንተን ለሥልጣኑ "መሣሪያ" አድርጎ ሲጠቀምብህ፣ እኛ ግን እንደ "ሰው" እናከብርሃለን። አንተን መግደል ሳይሆን አንተ ጋር የተሸረበውን የባርነት ሰንሰለት መበጠስ የትግላችን አካል ነው።
እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም የምናስተላልፈው መልዕክት! በየግንባሩ ያላችሁና ለአገዛዙ ጥላቻ ተሰልፋችሁ የምትገኙ ወታደሮች ሆይ፤ አስተውሉ! ጠላታችሁ ማን ነው? ጠላታችሁ የተራባችሁ ዕለት የሚያበላችሁ፣ የተጠማችሁ ዕለት ውኃ የሚያጠጣችሁ ይህ የዋህና ጀግና ሕዝብ ነውን? በገዛ ወገኑ ላይ ድሮን የሚያዘንብ አገዛዝ ወይስ የቆሰለ ምርኮኛን የሚያክም ሕዝብ የትኛው ነው ለሀገር የሚቆረቆረው?
ለአገዛዙ ሰራዊት የቀረበ የሕሊና ጥያቄ፤ ወታደር ሆይ! ይህን ፎቶ በጥልቀት ተመልከተው፤ የታጠቀው ማን ነው? አንተ የጥፋት መሣሪያ ታጥቀህ መጣህ፤ አርሶ አደሩ ግን የሕይወት መሣሪያ የሆነውን "እንጀራ" ይዞ ቀረበልህ። ጠላትህ ማን ነው? አዛዦችህ "ሽፍታና ጽንፈኛ" ብለው ሊያስገድሉህ የላኩህ ሕዝብ፣ ዛሬ በረሃብ እንዳትዝል የላብ እህሉን እያቀረበልህ ነው። ለማን ትሞታለህ? አንተ ቆስለህ ስትማረክ ጀርባውን የሰጠህ አገዛዝ ወይስ የቆሰለ አካልህን አክሞ ያበላህ ሕዝብ የትኛው ነው ለክብርህ የሚመጥነው?
ይህ ትግል በአሸናፊነት የሚደመደመው በመሣሪያ ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በያዝነው የሞራልና የሰብአዊነት የበላይነት ነው። አፈሙዝ ታጥቀህ ልትገድለው ብትመጣም፣ ሕዝባችን በፍቅርና በሰብአዊነት ይዞሃል። ይህ ፍቅር ነገ ለምትፈጠረው አዲስና ፍትሐዊት ኢትዮጵያ መሠረት ነው።
ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ማውቅ ያለበት ዋና ነገር፤ ይህ ትግል የሁለት ታጣቂዎች ሽኩቻ አይደለም። ይህ ትግል በግፈኛ አምባገነንነት እና በሰብአዊነት መካከል ያለ ግብግብ ነው። አገዛዙ በንጹሐን ላይ ድሮን ሲያዘንብ፣ የነፃነት ኃይሎችና ሕዝቡ ግን ለምርኮኞች የጄኔቫን ስምምነት (Geneva Convention) በላቀ ሁኔታ በተግባር እየተረጎሙት ይገኛሉ።
ዓለም ሊያውቀው የሚገባው ሀቅ ቢኖር፣ በኢትዮጵያ ምድር ፍትሕንና ሰላምን ሊያመጣ የሚችለው አፈሙዙን ለሰው ልጅ ክብር ዝቅ የሚያደርገው በፋኖ ኃይል እንጂ፣ ሕዝቡን እንደ ጠላት ፈርጆ የሚጨፈጭፈው አምባገነን ሥርዓት አለመሆኑን ነው።
ጥላቻን በፍቅር እናሸንፋለን!
ትግላችን ለፍትሕ፣ ለእኩልነትና ለነፃነት ነው!
ክብር ለሰብአዊነት ዘብ ለቆመው ሕዝባችን!
አዲስትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
Estibel Alemu Zrihun
ታህሳስ 28/2018ዓ.ም
መቶ አለቃ አበበ ሰው መሆን የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
☦የልደት በዓልን አስመልክቶ ከ አፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ ፅሕፈት ቤት የተሰጠ የእንኳን አደረሳቹህ መልዕክት‼️
ቀን፡ታህሳስ 28/2018 ዓ.ም
ላለፉት 50 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ስልጣን የሚመጡ ተረኛ ነን ባዮች ሁሉ መነሻቸውም ሆነ መድረሻቸው አማራ ጠልነት ነው፡፡ወንበር ላይ የወጣው ባለጊዜ ሁሉ አማራን ካላረድክ እና ካልጨፈጨፍክ ወንበርህ አይፀናም የተባለ እስኪመስለን ድረስ በአማራ ላይ የዘር ጭፍጨፋ ሲያካሂዱ ቆይተዋል፡፡በተለይ ላለፉት 8 ዓመታት የግብር አባቶቹን አማራን የመጨፍጨፍ ተልዕኮ ያስቀጥል ዘንድ ወደ ዙፋን የመጣው ተረኛው ባለ ጊዜ ኦህዴድ ብልፅግና የአማራ ሞት ህገ መንግሰታዊ ሽፋን የተሰጠው በማድረግ ይፋዊ የሞት አዋጅ በማወጅ የኢትዮጵያ ምድር ለአማራ ሲዖል እንድትሆን አድርጓታል፡፡የአማራ ፋኖ ይሄን የታወጀውን የሞት አዋጅ ለመሻር እንዲሁም የአማራን ህልውና በማረጋገጥ፣አማራን ወደ ነፃ ህዝብነቱ በመመለስ የአማራን ዳግም ውልደት(ልደት) ለማምጣት ከጠላት ጋር ዓመታትን ያስቆጠረ ዉጊያ እያደረገ ይገኛል፡፡ብዙ ወገናችን አልቆ፣ብዙ ወገናችን በተወለደበትና ባቀናው ሀገር ባይተዋር እና ስደተኛ ሁኖ ፤ጀንበር ወጥታ ስትገባ ማየትን ተስፋ በማድረግ በየ መጠለያ ካምቡ የሰው እጅ በመጠበቅ የመከራ ጊዜያትን እያሳለፈ ይገኛል፡፡ ይህ የመከራ ጊዜ ያጥር ዘንድ እና የአማራን ህልውና ለማረጋገጥ በዱር በገደሉ ለነፃነት እየተዋደቃችሁ ላላችሁ ለአማራ ፋኖ ታጋዮች፣በመላው ዓለም ለምትኖሩ የአማራ ፋኖ ታጋዮች እና ደጋፊዎች እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል(ገና) በሰላም አደረሳችሁ፡፡ክርስቶስ መከራው መከራችን ልደቱ ልደታችን ነውና፣ይህን የመከራ ዘመን ከፈጣሪ በታች በክንዳችን አሸንፈን የአማራን ልደት እናይ ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው፡፡
በመጨረሻም ለመላው የአማራ ፋኖ የህልውና ታጋዮች አሁን ላይ የአማራ ልደት ከአመት አንድ ጊዜ የምናከብረው ቀን አይደለም፡፡ዛሬም ነገም ምናልባት ከዓመታት በኋላም ሊሆን ይችላል፡፡የአማራ ልደት የሚጀምረው ከአንድነታችን ነው፡፡በአንድነታችን አማራ ዳግም ይወለዳል፤አንድ ካልሆን አማራ ዳግም አይወለድም፤መወለድ ከሌለ ልደት የለም፡፡ስለዚህ በሁሉም ቀጠና ያላችሁ የፋኖ አመራሮች፤ለእራት አንድ እንጀራ ሊበቃ መቶ እንጀራ ቢያግበሰብሱት ከመበላሸት ውጭ ጥቅም የለውም፤ያውም የሞተው ሙቶ በህይወት ያለው በ72 ሰዓት ውስጥ አንድ ጊዜ እንኳ የሚበላው አጥቶ ወገናችን በራብ አለንጋ እየተገረፈ ባለበት ወቅት፤ታሪክ እንሰራለን ብለን ታሪክ ተበላሽቶ ታሪክ እንዳይወቅሰን አንድ እንሁን!!!
በድጋሚ እንኳን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል(ገና) በሰላም አደረሳችሁ፡፡
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል
© አፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ ፅሕፈት ቤት
28/ዐ4/2018 ዓ.ም