ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد2 952
المشتركون
+424 ساعات
+147 أيام
+38830 أيام
أرشيف المشاركات
+4
ግንቦት 17/2018 ዓ.ም
የ6ኛ ዕዝ 117 ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲ አባል የሆኑት
- ስመኘው አለሙ
- ለሜ አብዱቃድር
- ኑረዲን ሀሳነ 206ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል።
የአረመኔው ሰራዊት በጀነራል ብርሃኑ ጥላሁን ከሚመራው 6ኛ ዕዝ ምርጫን ለማስፈፀም በማህበረሰቡ ላይ አሰቃቂ ድርጊት እንዲፈፀምና ህዝቡ እንዲሸማቀቅ የሚያደርግ ማንኛውንም ትዕዛዝ የተሰጠው በመሆኑ ሰሞኑን በጎዛምን እና ስናን ወረዳዎች ብቻ 6 (ስድስት) ሴቶች መደፈራቸውን አረጋግጠዋል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
🚨 ለማመን የሚከብድ እውነታ!
የአብይ አህመድን መንበር ለማስጠበቅ የተከፈለው ታላቅ መስዋዕትነት!
ያ የአማራ ልጅ...የፖለቲካውን ሚዛን ለመጠበቅና ስልጣንን ለማፅናት ሲባል ብቻ ለማመን የሚከብድ ውድ መስዋዕትነትን ከፍሏል። ታሪክ የማይረሳው፣ ልብ የሚነካ ዋጋ ተከፍሏል። ነገር ግን ታሪኩ እዚህ ላይ አያበቃም! 🔥
ዛሬ የለውጥ ነፋስ እየነፈሰ ነው። የቁስልና የለቅሶው ምዕራፍ አክትሞ፣ የፋኖ ታጋዮች የማንነትና የነፃነት ሰንደቅ አብርሃቸውን ወደፊት መገስገስ ጀምረዋል።
📌 መልዕክቱ ግልፅ ነው፦
«ጉዞው ገና አሁን ተጀመረ እንጂ ፈፅሞ አላለቀም! ወደፊት ብቻ!»
ይህ የፅናት፣ የክብር እና የማንነት ድምፅ ነው። ድምፃችን ጎልቶ እንዲሰማ፣ ታሪካችን ለዓለም እንዲደርስ የአንተ/አንቺ ድርሻ ያስፈልጋል።
🔴 አማራ ከሆንክ፦
👉 SHARE / ሸር ሸር ሸር!
👉 ቻናሉን ጆይን በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ፣ ይተባበሩ! Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር ቀጥታ ከግንባር #አማራ #ፋኖ #Amhara #Fano #ኢትዮጵያ #Ethiopia #Share
በዝርዝር ልመጣበት ነው ቤተሰብ ሸር ሸር ሸር ይለያል ነው የምላችሁን ዛሬ ሊገልህ ቤትህ ድርስ አይደል የመጣው ሸር ሸር ሸር ብቻ
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ ጦር ድርብ የደስታ ቀን ነው።
========================
በቀን 18/09/2018 ዓ.ም
የሙስሊም ወንድሞቻችን 1447ኛ ዓመት የአረፋ በዓል የደስታ ቀን በሆነበት አፋህድ ጎጃም ጠቅላይ ግዛት ዕዝ እና የ74ኛ ክ/ጦር አባላት በጋራ ውህደት ፈጥረው የወንድሞቻችን ህይወት የተሰዋበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ውህደት ፈጥረን የህዝባችን አንገት ቀና ያለበት እና ጠላት አንገቱን ያስደፋንበት ዕለት ነው
ድርጅታችን አፋብን ከተመሰረተ ከጥር 09/2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የአማራ ግዛቶች ውስጥ የሚገኙ የአፋህድ እና አፋብኃ አመራር እና አባለት ውህደት በመፍጠር አንድ ወጥ የሆነ መሪ እና ድርጅት መፍጠሩ ይታወቃል ስለሆነም በዛሬው ዕለት የአፋህድ ጎጃም ጠቅላይ ግዛት ዕዝ እና የቴ/ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር አመራር እና አባላ በጋራ አንድ ላይ እጅ ለእጅ ተያይዘው ውህደት የፈጠሩ ሲሆን ይህ የተቀደሰ ስራ ተጀምሮ እስከሚያልቅ ድረስ ትልቁን የአመራርነት ጥበብ እና ሚና የተወጡት የአፋብን ቴ /ዕዝ ህግ እና ስነ ስርዓት ዘርፍ ም/ኃላፊ ጠበቃ ምንያምር አዲስ እና የዕዙ ኢንዶክትሪኔሽን ኃላፊ መቶ አለቃ ግዮን ጀምበሬን ከልብ እናመሰግናለን።
"ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም"
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተላለፈ የጥንቃቄ መመሪያ
የብልፅግና አገዛዝ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል ነባራዊ ሁኔታ በሌለበት አውድ ውስጥ በተለይም በአማራ ክልል እና በሌሎች አካባቢወች የመከላከያ ጀነራል መኮንኖችን ጨምሮ የበርካቶችን ህይወት የሚቀጥፍ የተፋፋመ ጦርነት እያለ በመጭው ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የምርጫ ድግስ ማዘጋጀቱ ይታወቃል።
አገዛዙ "ምርጫዉን" ህዝቡን ባሳተፈ መንገድ እንደማያከናውን እና የምርጫ ሂደትን ለማሳካት የሚያበቃ አንዳችም ቅድመ ሁኔታ ያልተሟላ መሆኑን ቢያውቅም ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን እና ሌላውን ኢትዮጵያዊ ጭምር ለማታለል በአንዳንድ ከተሞች ይዞታውን ለማስፋት አዳዲስ የውጊያ ግንባሮችን በመክፈት ላይ ይገኛል።
ይህንን ተከትሎም ከአገዛዙ ሰራዊት ጋር የሚደረጉ ውጊያወች በበርካታ አካባቢወች ከሌላው ጊዜ በባሰ ሁኔታ ተጠናክረው ቀጥለዋል። የጠላት ኃይል ሲቪሊያንን መጨፍጨፍ እንደ ውጊያ ስልት ከመጠቀሙ ባሻገር ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያወችን በዘፈቀደ በማስወንጨፍ የሚያደርሰው ጉዳት በመቀጠሉ የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ይህንን የጥንቃቄ መመሪያ ማስተላለፍ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በመሆኑም ከአርብ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት ከአንቡላንሶች በስተቀር ሁሉም መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ መደረጋቸውን እያሳወቅን በእነኝህ ቀናት ውስጥ ህዝቡ መደበኛ እንቅስቃሴውን በመገደብም ጭምር ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
81ኛ ክፍለ ጦር በአፓርታይዱ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ላይ ድል ተቀዳጀ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር 81ኛ ክፍለጦር የጨረባ ምርጫ አስፈፅማለሁ ብሎ በቀን ቅዠት ውስጥ በሚደናበረው የአፓርታይዱ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ላይ በሰሜን ወሎ ዞን ገረገራ ግንባር በተጠና ኦፕሬሽን መብረቃዊ ጥቃት ሲፈፀምበት ወደ አግሪት የተንቀሳቀሰው ደመነፍሳዊ ኃይል እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ ተመለደው የአይጥ ጎድጓዱ ገብቷል።
ግንቦት 19/2018 ዓ/ም ረፋዱን በተሰራው ኦፕሬሽን 12 ሲደመሰስ 17 ቁስለኛ ሁኗል። በጦር ጠበብቶቹ የ81ኛ ክፍለጦር አመራሮች የተመራዊ ኦፕሬሽን በኃይል የምርጫ ድጋፍ ውጡ እያለ ንፁሃንን ሲያሰቃይ የነበረውን የብልፅግና ስርዓት አቀንቃኞች ቅስም የሰበረ እንደነበር ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃውን አድርሷል!
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 19/ 2018 ዓ.ም
+5
ዘረ ፈጁ የአብይ አህመድ ሰራዊት በእናርጅ እናውጋ ወረዳ እና ጎንቻ ሲሶ አነሴ ወረዳ ንጹኃንን ጨፈጨፈ ።
∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞
......ግንቦት 19/2018ዓ.ም
ፀረ ህዝብ እና አገር አፍራሽ የሆነው የአብይ አህመድ አገዛዝ የፋኖን ፈርጣማ ክንድ መቋቋም ሲያቅተው በአካባቢው ያሉትን አርሶ አደሮችን ቤት ለቤት በመሔድ በጥይት በመግደል ፣ ሩቅ ቦታ ያሉትን ደግሞ ጀነራል መድፍ በመተኮስ 2 ንጹኃንን የገደለ ሲሆን 4 ሰዎችን ከባድ ቁስለኛ አድርጓል።
ግንቦት18/09/2018 ዓ.ም እናርጅ እናውጋ ወረዳ ቤታቸው ውስጥ በጥይት ተደብድበው የተገደሉ ፦
1. መኳንንት አስረስ መጣያ ቀበሌ ስራ ነጋዴ
2. ካሳሁን አንዳለም ቀበሌ መጣያ ስራ አርሶ አደር
ከባድ ቁስለኛ
1. ጌትነት አስማማው የጢጣር ባድማ ቀበሌ አቦ ጎጥ
2.ጌታየ የኔዓለም ባድማ ቀበሌ ።
~በ18/09/2018 ዓም ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በመድፍ ተመተው ከባድ ቁስለኛ የሆኑ ንጹኃን አርሶ አደሮች፦
1. ዝምነው አይተነው ቀበሌ ወይራ
2.ልጃለም ይግረም ቀበሌ ወይራ ናቸው
"ነጻነታችን በተባበረ ክንዳችን እናረጋግጣለን "
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+1
የጠላት የቡድን መሳሪያዎች በገፍ ወደፋኖ እየገቡ ነው‼️
አያልሰው ይብለጥ የ 6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር ቃኝና መሐንዲስ አባል የነበረ ከአነደድ ከተማ በመውጣት ጥቁር ስናይፐር ይዞ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል።
በ4 ቀናት ውስጥ ብቻ ከ10 በላይ የጠላት ኃይል 206ኛ ኮርን የተቀላቀሉ ሲሆን ትጥቅ ይዘው ለሚቀላቀሉት ልዩ ድጋፍ እየተሰጣቸው ይገኛል ሲል የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ገልጿልደ
ይቀጥላል..............‼️
ግንቦት 19/2018 ዓ/ም
፻ አለቃ አበበ ደርሶ 8 የአገዛዙን ሰራዊት በመደምሰስ መስዋዕትነትን ተቀብሏል።
(206ኛ ኮር) ግንቦት 19/2018 ዓ.ም
=======================================
፻ አለቃ አበበ ደርሶ በአነደድ ወረዳ ዝንቅር ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን ባለትዳር እና የልጆች አባት ነው። በ1991-92 ዓ.ም በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ከሽራሮ እስከ ባድሜ በነበሩ ግምባሮች በመሰለፍ ጀብድ የፈፀመ ቆራጥ ወታደር ነበር።
ከውትድርና ህይወት በክብር የተሰናበተው ፻ አለቃ አበበ ወደ ትውልድ መንደሩ ዝንቅር ቀበሌ በመመለስ ትዳር መስርቶ መኖር ከጀመረ ሀለት አስርት አመታት ያለፉት ሲሆን የአረመኔው ሰራዊት ለሀገር የዋለውን ውለታ ከቁብ ሳይቆጥር ግንቦት 18/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ቤቱን በመክበብ በቁጥጥር ስር ለማዋል አነጋጉ ላይ እጅ እንዲሰጥ የጠላት ኃይል ሁለት ሻምበል ሰራዊት አዝምቶበታል።
በጠላት ከበባ ውስጥ የነበረው ፻ አለቃ አበበ ደርሶ የግል ትጥቅ የሆነችውን ክላሹን አንስቶ እየተኮሰ ቤቱን ከፍቶ ሲወጣ በሩ ላይ የነበረውን ፶ አለቃ ቢሻው የተባለውን ብሬን ተኳሽ ፖሊስ ግንባሩ መቶ ከበባውን ጥሶ ወጣ። የጠላት ኃይል ፻ አለቃ አበበ ደርሶ ተከትሎ ለማጥቃት በተንቀሳቀሰበት ቅፅበት ደግሞ እጅግ የተባለውን ሚኒሻ ከሁለት አድማ ብተናዎች ጋር አነጥፎ ሶስት ክላሽ በመማረክ እራሱን እየተከላከለ ባለበት የ34ኛ ክ/ጦር ተድላ ጓሉ ሻለቃና የመብረቁ ሻለቃ በፍጥነት ሽፋን እየሰጡ ውጊያውን ከጎኑ ሁነው አግዘውታል።
መቶ አለቃ አበበን ከጠላት ከበባ ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት ሁለቱ ሻለቆች የጠላትን ቅስም በመስበር እስከ 11:00 ሰዓት ከፍተኛ ውጊያ የከፈቱ ሲሆን ፻ አለቃ አበበ ደርሶ ከበባውን ጥሶ ከጀግኖች ጎን ተሰልፎ እየተዋጋ ባለበት ተጨማሪ 4 የጠላት ኃይል በመምታት ከቀኑ 9:00 ሰዓት ገደማ በድምሩ 8 የጠላትን ሰራዊት ደምስሶ መሰዋትነትን ተቀብሏል።
አነጋጉ ላይ የጀመረው ትንቅንቅ እስከ ቀን 11:00 ቀጥሎ ጠላት 15 አስክሬን ተሸክሞ ሲመለስ 7 አድማ ብተና አባላት ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል። ጠላት በአልጠበቀው መልኩ የደረሰበትን ኪሳራ ለመበቀል ፻ አለቃ አበበ ደርሶን ቤት ያቃጠለ ሲሆን በሰራዊታችን ትንቅንቅና በህዝባችን እርብርብ በአካባቢው ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ተደርጓል።
ክብር በጀግንነት ለተሰው ጓዶች!!
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+1
#ሰበር_ዜና_ባንዳ_ከሞቱ_አሟሟቱ‼️
#100% #የተረጋገጠ_መረጃ_በመከላከያ_አመራሩ_ተገደለ❗️
በደብረብርሃን ከተማ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ ፲ አለቃ ተ/አረጋይ ጌታቸው በአገዛዙ ተገደለ።
በደብረብርሃን ከተማ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ ፲ አለቃ ተ/አረጋይ ጌታቸው ግንቦት 18/2018ዓ.ም ከለሊቱ 6:00 ሰዓት ላይ በስምሪት ላይ እንዳለ በአገዛዙ መከላከያ አመራሮች መገደሉ ተረጋግጧል❗️
#ባንዳ_ከሞቱ_አሟሟቱ‼️
የአፋብን ሽዋ ጠቅላ ግዛት አሳምነው ዕዝና ወሎ ቤተ አማራ ሚኒልክ ዕዝ በሸዋ ደራ ወረዳ በተካሄደ የተቀናጀ የ"መብረቅ" ጥቃት በብልፅግና መራሹ ኃይሎች ላይ ከባድና የማያገግም ሽንፈት አደረሱ!!!
ግንቦት 19/09/2018 ዓ.ም
በሸዋ ጠቅላ ግዛት ደራ ወረዳ ስልታዊና የተቀናጀ ወታደራዊ እርምጃ የወሰዱት የአፋብን ወሎ ቤተ አማራ ሚኒልክ ዕዝ መብረቅ ክፍለ ጦር እና የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር በጋራ በመሆን በአብይ አህመድ አረመኒያዊ ኃይሎች ላይ ከባድና የማያገግም ሽንፈት በማሳረፋ ድልን ተቀናጁ።
በዚህ በላቀ ስልታዊ ዘመቻ፣ 20 የሚሆኑ የጠላት ጥምር ብሎ የሚጠራተው ታጣቂዎች ሙሉ በሙሉ የተደምሰሱ ሲሆን፣ የሚኒልክ እና የአሳምነው የፋኖ አናብስቶች በሚሊሻው ላይ ብቻ ሳይሆን በራሱ በብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ላይ ጭምር ፍጹም የበላይነትን በመቀዳጀት ደማቅ ድልን አስመዝግበዋል። ከጠላት ኃይል ማለትም ከመከላከያና ከሚሊሻው ኃይሎች የተፈቱ በርካታ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሣሪያዎች፣ የእጅ ቦምቦችና ሙሉ ወታደራዊ አልባሳት፣ እንዲሁም በቁጥጥር ስር የዋሉና የፋኖን ብርቱ ክንድ በዓይናቸው ያዩ በርካታ የሚሊሻ አባላት ተማርከዋል።
ይህ ዘመቻ ከተማ ለመቆጣጠር ሳይሆን፣ የጠላትን ኃይል የመምታትና ትጥቅ የመፍታት ቀጥተኛ ግብ የነበረው ሲሆን፣ የተነደፈው ዓላማም መቶ በመቶ ተሳክቷል። የብልፅግና ስርዓት በብዙሃን መገናኛዎቹ አማካኝነት የሐሰት ወሬዎችንና የፕሮፓጋንዳ ጭሶችን ቢነዛም፣ መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን በማስርጃና በምስል የተደገፈ የጦር መሣሪያ ምርኮ መሆኑ ያረጋግጣል። ጀግኖቹ የነጻነት ጉዟቸውን በድል አድራጊነት ወደፊት እየገፉበት ይገኛሉ።
✊ ክብር ለተሰው ሰማዕታት!
✌️ ድል ለአማራ ሕዝብ!
የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዓፄ ዘርዓያዕቆ ፩ኛ ኮር ህዝብ ግኑኝነት መምሪያ
ከድርጅታችን አፋብን የሚሰጠንን ተልዕኮ ለመፈፀም ዝግጁነታችንን አጠናቀናል ሲሉ የደባይ ጥላት ግን ወረዳ አባት አርበኞች (የኋላ ደጀን) አባላት ገለፁ
ግንቦት 19/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር
በአፋብን ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር የደባይ ጥላት ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት በዛሬው ዕለት ግንቦት 19/2018 ዓ.ም ከኋላ ደጀን ጦር (አባት ፋኖ) አባላት ጋራ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይይ ተደረገ።
የኋላ ደጀን ጦር (አባት ፋኖ) አባላት በአሁኑ ወቅት አገዛዙ ለዳግም አምሰት(5) አመት አረመኒያዊ ተግባሩን በአማራ ህዝብ ላይ ለመፈፀም በምርጫ ሰም እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።የሰሞኑንም ምርጫን አሰመልክቶ የጮቄ ተራራማ ሰፍራን ለመያዝ ወረራ ጀምሯልነገር ግን እኛ እያለን አይደለም ጮቄን ሊይዝ ይቅርና ከቁይ ከተማ ወጥቶ ወደ አንዲት ቀበሌም የማናቀሳቅሰው መሆኑን እናረጋግጣለን ብለዋል።
ከዛሬ ጀምሮ ለሚሰጠን ማነኛውም ግዳጅ ከደባይ ጮቄ ሻለቃ ጋራ በመሆን የአረመኒያዊ አገዛዙን ዙፋን አሰጠባቂ ሰራዊት ከመከላከልም ባለፈ ወደ ሙሉ ማጥቃት የትግል ጉዞ ለማድረግ ሙሉ ዝግጁ ነን አሁን የሚሰጠንን ግዳጅ ለመወጣት መሳሪያችን ወልውለን ለግዳጅ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን ብለዋል።
አዲስ ትውልድ አዲስ ተስፋ አዲስ አስተሳሰብ
አፋብን 24ኛ ክ/ጦር የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ጊዚያዊ መንግሰት አስተዳደር ሚዲያ ክፍል
1447ኛውን የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል አስመልክቶ ከአፋብን የተሰጠ መግለጫ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በተለይም በዓሉን በየግንባሩና በየጦር ሜዳው ለምታከብሩ የድርጅታችን ሙስሊም አመራር እና አባላት እንኳን ለ1ሺህ 447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።
ይህ በዓል ትዕግስትና መስዋዕትነት በመጨረሻ ወደ ክብርና ድል የሚያደርሱ መሆናቸውን የምናስታውስበት ታላቅ ቀን ነው። ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) በፈተና ውስጥ ሆነው ያሳዩት የማይናወጥ እምነትና ፅናት ዛሬም እውነትን ለያዙና ለሕልውናቸው ለሚታገሉ ወገኖቻችን ትልቅ ትምህርት ነው።
የአረፋ በዓልን ስናከብር፡ ሙስሊም ክርስቲያኑ አጠቃላይ የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በአብሮነት፣ በመከባበርና በአንድነት ለጋራ ዓላማ መቆም ወቅታዊ ችግሮችንና ጫናዎችን በጋራ ለመቋቋም የሃይማኖት ልዩነት ሳይበግረው እጅ ለእጅ ተያይዞ ሊቆም እንደሚገባ በማስታወስ ጭምር መሆን ይገባዋል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የአረፋ በዓልን የሚያከብሩ ሁሉ፡ በአገዛዙ የተፈናቀሉ ወገኖችን በማሰብ፣ በዚህ የዘር ማጥፋት ጦርነት እና በተለያዩ ምክንያቶች አደጋ ላይ የወደቁ እና በችግር ላይ ያሉ ወገኖችን ማሰብ እና መርዳት እንደሚገባ ጥሪ ያቀርባል።
በድጋሚ መልካም የአረፋ በዓል!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ!
