ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد2 952
المشتركون
+424 ساعات
+147 أيام
+38830 أيام
أرشيف المشاركات
በ4 ፓትሮል እና በ3 አይሱዙ ሰራዊት ታጅቦ #20 ተሳቢ ሎጅስቲክ የጫነ የአብይ ወራሪ ሰራዊት ከባህርዳር መኮድ ካንፕ ዛሬ 1:50 ላይ ወጥቷል።
አድራሻው ወደ ጎንደር ወይም አዴት-ሞጣ መስመር መሆን ይችላል።
አብዛኛው ጀሌ ነው።
አሁን ተጨማሪ 1 ዙ-23 እና አንድ አይሱዙ ጨፍጫፊ ተከትሎ ሄዷል።
መረጃውን አጋሩት
የደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክፍለ ጦርና አባት አርበኞች የተቀናጀ ድል አስመዘገቡ
ግንቦት 18/2018 ዓ.ም
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) አሳምነው ዕዝ፣ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ሥር የሚገኘው ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክፍለ ጦር፣ ከጀግኖቹ አባት አርበኞች ጋር በመቀናጀት በጠላት ላይ ታላቅ ድል ተቀዳጀ።
ሥርዓቱ የጨረባ ምርጫውን በግዳጅ ለማስፈጸምና በንጹኃን ላይ ጭፍጨፋ ለመፈጸም ከሸዋሮቢትና ከአጣዬ ከተሞች በጎዜ ተራራና ልዩ ዞኑን ተገን በማድረግ ወደ የለን ቀበሌ ያንቀሳቀሰው የቅጥረኛ ሠራዊት፣ በአናብስት ታጋዮቻችን መብረቃዊ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ተቀጥቶ ወደ መጣበት ተመልሷል።
ከታደለ ወርቁና መሐመድ ስንዴው ብርጌድ በተውጣጡ ተወርዋሪ ሻለቆች አማካኝነት በነጣፌና በስውር ጅረት በኩል የተቀጣው የጠላት ኃይል፣ የፋኖን ብትር መቋቋም ሲያቅተው በንጹኃን አርሶ አደሮች ላይ የጭካኔ በትሩን አሳርፏል። ጠላት ከሸዋሮቢት ከተማ በጀነራል መድፍ በመደብደብ የጎለጓዲሳ ጎጥ ነዋሪ የሆኑትን አሠፋ የተባሉ አባት ከሁለት ህጻናት ልጆቻቸው ጋር ማቁሰሉንና የአርሶ አደሩን ከብቶች መጨፍጨፉን የክፍለ ጦሩ የሕዝብ ግንኙነት አስታውቋል።
በይበልጥ በድንጋጤና በፍርሃት የተዋጠው የጠላት ሠራዊት፣ መድፍና ሞርተር እየተኮሰ ወደ ሸዋሮቢት ከተማ እግሬ አውጭኝ ብሎ መሸሹ ታውቋል።
በሌሎች ግንባሮችም ተመሳሳይ ድል ተመዝግቧል። ከአጣዬ ወደ አላላ ቀበሌ ወደ ብርቂቶ እና ሸረፋ የተንቀሳቀሰውን ተጨማሪ ኃይል፣ የአካባቢው አባት አርበኞች ቀድመው በመመከትና ከሰዓት በኋላ በመልሶ ማጥቃት ጠላትን ወደ ቀበሮ ጉድጓዱ አባረውታል። እንዲሁም ከመንዝ ማማ ሞላሌ ወረዳ ለምርጫ ቅስቀሳ ወደ መለያና ይገም ተንቀሳቅሶ የነበረው ኃይል፣ በአባት አርበኞች የጥበብ ስልት ታቅዶ የነበረው የፖለቲካ ቁማር እንዲከሽፍ ተደርጎ ተዋርዶ ወደ መጣበት መመለሱ ተረጋግጧል።
አፋብን አሳምነው ዕዝ፣ የጠላት ኃይል በየትኛውም የሸዋ አካባቢ ለወረራና ለሕዝብ ማፈናቀል በሚያደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ፣ ፋኖና አባት አርበኞች በጋራ ተቀናጅተው የአካባቢውን ሰላምና የሕዝቡን ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ እንደሚጠብቁ በድጋሚ አስታውቋል።
የአፋሐድ ጎጃም ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በመጨረሻም ከወንድሞቻቸው ጋር ተዋሕደዋል።
ይች ቀን ለእኛ ልዩ ትርጉም አላት ከአንድ ምንጭ የተቀዳ ውሃ በአንድ ብርጭቆ ጠጥተን እንዳላደግን፤ በአንድ መንደር ቦርቀን እንዳላደግን፤ በስስት የምንተያይ ወንድማማቾች በነበረን ድርጅታዊ ልዩነት መከፈል የሌለበት መሰዋትነት ከፍለን ህዝባችንን ማዕቅ ማልበሳችን ሳስብ ምናልባት ፀፀቱ የሚለቀን አይመስለኝም።
ትግሉን በአንድ ወጥ የሆነ መዋቅር እንዲመራና የፀና የጠነከረ በአማራነት ላይ የተገነባ ግዙፍ ድርጅት ይኖረን ዘንድ ተያይተን የማንጠጋገብ ወንድማማቾች የነበረን ልዩነት ተቀርፎ ዛሬ 74ኛ ክ/ጦር ጋር በመዋሐዳቸው እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል።
ከወራት በፊት የጎጃም ጠቅላይ ግዛት የሰራዊት አባታትና አመራሮችን በክብር ተቀብላችሁ በፍቅር ላስተናገዳችሁ የ74ኛ ክ/ጦር አመራሮችና አባላት እና የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ማህበረሰብ እንዲሁም ከሀገር ውጭ የምትኖሩ ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሯቹሁ ግፊት ስታደርጉ የነበራችሁ የምናከብራችሁ ታላላቆቻችን እና በሀገር ውስጥ በከፈልነው መሰዋትነት ቁጭት ገብቷችሁ በምክር በሀሳብ ለደገፋችሁን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እወዳለሁ።
አርበኛ ምንያምር አዲስ እና መቶ አለቃ ጊዮን ሒደቱን ጥንቅቅል ባለ ጥበብና የአመራርነት አቅም በስኬት ቋጭተውታል አክብሮቴ ይድረሳችሁ።
አንድ አማራ! እስከ ምጽአት አማራ!
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ አሳምነው ዕዝ፣ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር፣ ከሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር እንኳን ለ1447ኛው የአረፋ ባዕል አደረሳችሁ!!!
🌙 የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፦
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፣ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም፣ በጤና እና በህይወት አደረሳችሁ!
ይህ በዓል የመስዋዕትነት፣ የፅናትና የታማኝነት ማሳያ እንደመሆኑ መጠን፤ እኛም በዱር በገደሉ ላይ የሕዝባችንን ሰላምና ክብር ለማስጠበቅ የምንከፍለው መስዋዕትነት ከበዓሉ መንፈስ ጋር የተቆራኘ ነው። የፋኖ ጀግንነት የጦር ሜዳ ውሎ ብቻ ሳይሆን፤ የሕዝብን አንድነት መጠበቅ፣ እምነትን ማክበርና ፍቅርን መዝራት ጭምር ነው።
የዘንድሮው የአረፋ በዓል ለተጨቆኑት ሁሉ ነጻነትን፣ ለታረዱት ሰላምን፣ ለተራቡት በረከትን የሚያወርድ፤ የደስታና የድል ይሆን ዘንድ የክፍለ ጦራችን ጀግኖች ምኞታቸውን ይገልጻሉ።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የበረከት እንዲሆንላችሁ ከልብ እየተመኘን፤
✊ "ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!!!"
💪 "ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!"
ግንቦት 18/2018 ዓ.ም
አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የሰባት ለሰባ ክፈለ ጦር
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ አሳምነው ዕዝ፣ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር፣ ከሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር እንኳን ለ1447ኛው የአረፋ ባዕል አደረሳችሁ!!!
🌙 የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፦
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፣ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም፣ በጤና እና በህይወት አደረሳችሁ!
ይህ በዓል የመስዋዕትነት፣ የፅናትና የታማኝነት ማሳያ እንደመሆኑ መጠን፤ እኛም በዱር በገደሉ ላይ የሕዝባችንን ሰላምና ክብር ለማስጠበቅ የምንከፍለው መስዋዕትነት ከበዓሉ መንፈስ ጋር የተቆራኘ ነው። የፋኖ ጀግንነት የጦር ሜዳ ውሎ ብቻ ሳይሆን፤ የሕዝብን አንድነት መጠበቅ፣ እምነትን ማክበርና ፍቅርን መዝራት ጭምር ነው።
የዘንድሮው የአረፋ በዓል ለተጨቆኑት ሁሉ ነጻነትን፣ ለታረዱት ሰላምን፣ ለተራቡት በረከትን የሚያወርድ፤ የደስታና የድል ይሆን ዘንድ የክፍለ ጦራችን ጀግኖች ምኞታቸውን ይገልጻሉ።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የበረከት እንዲሆንላችሁ ከልብ እየተመኘን፤
✊ "ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!!!"
💪 "ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!"
ግንቦት 18/2018 ዓ.ም
አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የሰባት ለሰባ ክፈለ ጦር
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር እንኳን ለ1447ኛው የአረፋ ባዕል አደረሳችሁ!!!
🌙 የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፦
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፣ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም፣ በጤና እና በህይወት አደረሳችሁ!
ይህ በዓል የመስዋዕትነት፣ የፅናትና የታማኝነት ማሳያ እንደመሆኑ መጠን፤ እኛም በዱር በገደሉ ላይ የሕዝባችንን ሰላምና ክብር ለማስጠበቅ የምንከፍለው መስዋዕትነት ከበዓሉ መንፈስ ጋር የተቆራኘ ነው። የፋኖ ጀግንነት የጦር ሜዳ ውሎ ብቻ ሳይሆን፤ የሕዝብን አንድነት መጠበቅ፣ እምነትን ማክበርና ፍቅርን መዝራት ጭምር ነው።
የዘንድሮው የአረፋ በዓል ለተጨቆኑት ሁሉ ነጻነትን፣ ለታረዱት ሰላምን፣ ለተራቡት በረከትን የሚያወርድ፤ የደስታና የድል ይሆን ዘንድ የኮሩ ጦራችን ጀግኖች ምኞታቸውን ይገልጻሉ።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የበረከት እንዲሆንላችሁ ከልብ እየተመኘን፤
እናቅዳለን እንፈፅማለን
አማራነት ያሸንፋል፤ ፋኖነት ይነግሳል!!
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ከአማራ ፉኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፉብን/ የ101ኛ ኮር ምክትል ወታደራዊ አዛዥ እና የ35ኛ ክፍለጦር ዋና አዛዥ አርበኛ እንድሪስ ጉደሌ የተላለፈ የዒድ አል-አድሐ (አረፋ) በዓል
🌙 የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፦
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፣ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም፣ በጤና እና በህይወት አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የበረከት እንዲሆንላችሁ ከልብ እየተመኘሁ፡
ይህ በዓል የታሪክ ማስታወሻ ብቻ ሳይሆን በተግባር የምናሳያቸው ሦስት ታላላቅ ምሶሶዎች አሉት፦
አንድነትና እኩልነት፦ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በቅድስት ስፍራ መካ (ሐጅ) ላይ ምንም ዓይነት የዘር፣ የቋንቋና የደረጃ ልዩነት ሳይኖራቸው በአንድነት የሚቆሙበት የሰላም መገለጫ ነው።
መተሳሰብና መጋራት (ኡድሒያ)፦ በዓሉ የመሥዋዕት እንስሳትን በማረድ ሥጋውን ለቤተሰብ፣ ለጎረቤትና በተለይም አቅም ለሌላቸው ድሆችና ምስኪኖች የምናካፍልበት የበጎ አድራጎት ወቅት ነው።ይቅርታና ሰላም፦ በሰዎች መካከል ያሉ ቅያሜዎች የሚረሱበት፣ ፍቅርና ሰላም የሚነግስበት ዕለት ነው።
የዒድ አል-አድሐ በዓል መሠረቱ የታላቁ ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) እና የልጃቸው ኢስማዒል (ዐ.ሰ) ታሪክ ነው። ይህ ታሪክ የሚያስተምረን ትልቁ ቁምነገር ጽናትን ነው
የተስፋ መልዕክት፦ ነቢዩ ኢብራሂም በሕይወታቸው ትልቁን ፈተና ባስተናገዱበትና በከፍተኛ ጭንቅ ውስጥ በነበሩበት ወቅት፣ ለአምላካቸው ፍጹም ታዛዥ ሆነው በመጽናታቸው ምክንያት አላህ በግ መሥዋዕት አድርጎ በመላክ ከጭንቁ አውጥቷቸዋል። ዛሬም በግፍና በጭፍጨፋ ውስጥ ያለው ወገናችን በትዕግስቱና በጽናቱ ምክንያት ከአላህ ዘንድ ታላቅ እፎይታንና ፍትህን እንደሚያገኝ ማሳያ ነው።
የአማራ ህዝብ በደልና መከራ በበዛበት በዚህ ወቅት፣ በዓሉን በደስታ ብቻ ሳይሆን በሚከተሉት ሰብአዊና መንፈሳዊ እሴቶች ልናሳልፈው ይገባል፦
ድምፅ መሆንና ማሰብ፦ በዓሉን ስናከብር ቤታቸው በላያቸው ላይ የፈረሰባቸውን፣ በግፍ የተጨፈጨፉትን ንጹሐንና ወላጆቻቸውን ያጡ የቲሞችን በማሰብ ሊሆን ይገባል። እኛ በደስታ ስናሳልፍ እነሱ በሰቀቀን ውስጥ መሆናቸውን ፈጽሞ መዘንጋት የለብንም።
በዱዓ (በጸሎት) መረባረብ፦ የአረፋ (የሐጅ) ዕለት ዱዓ ተቀባይነት ያለው ታላቅ ቀን ነው። መላው ሙስሊም በግፍ የሚጨፈጨፉ ሕዝቦች ከዚህ አገዛዝና ጭቆና ነጻ እንዲወጡ፣ ለበዳዮች አላህ ተገቢውን ፍርድ እንዲሰጥ፣ ለተበደሉት ደግሞ ፍትህና ሰላምን እንዲያወርድ በጋራ መማጸን ይኖርበታል።
ፍትሕ መዘግየቷ አይቀሬ ቢሆንም፣ በደልና ግፍ ግን ዘላቂ አይደሉም። ፈጣሪ የተበዳዮችን እንባ ፈጽሞ አይረሳም። በግፍና በጭፍጨፋ ውስጥ የምትገኙ ወገኖቻችን በሙሉ፦ ብርታቱና ጽናቱ ይስጣችሁ፤ አላህ ከእናንተ ጋር ነው።በመጨረሻም የአማራ ህዝብ የጋረጠበትን የህልውና አደጋ ለመመከት ለምትታገሉ ለመላው የአማራ ፉኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሰራዊታችን መልካም ምኞቴን ለመገለፅ እወዳለሁ።
“ትዕግስትና ጽናት መከራን ያሸንፋል፤ ከእያንዳንዱ ጭንቅ በኋላም ብርሃን ይመጣል።”
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ/አፉብን/
18/08/2018 ዓ.ም
የፍኖተ ሰላም አደባባይ ምዕራብ ጎጃም ነሐሴ 2015 ዓ.ም ከ40 በላይ ንጹሃን በአንድ ጊዜ ረግፈዋል። በከተማዋ መሀል ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ ላይ የተፈጸመ የድሮን ጥቃት ነው።
በተለይም በመላው አማራ በስም ላልተጠቀሱ እና የመርሳ ገበያ (ሰሜን ወሎ) እና ሸዋ ሮቢት፣ ቢቸና፣ ደብረ ማርቆስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች በተለያዩ ጊዜያት። በገበያ ቀናት እና በህዝብ መንደሮች ላይ የሚወርዱ የከባድ መሳሪያ ድብደባዎች እና ከተሞች በተያዙ ማግስት የሚደረጉ የቤት ለቤት ፍተሻዎች ንጹሃንን ሰለባ አድርገዋል።
በቋሪት ወረዳ (ፈረስ ቤት ከተማ 2016 ዓ.ም)፦ በአብይ አህመድ መከላከያ ሰራዊት በተፈጸመ የከባድ መሳሪያ ድብደባ በአንድ የመኖሪያ መንደር ውስጥ ከ18 በላይ ንጹሃን እናቶችና ህጻናት በቤታቸው ውስጥ እያሉ ተገድለዋል።
በምስራቅ ጎጃም ህዳር 2016 ዓ.ም ከባድ ውጊያዎችን ተከትሎ በተደረገ የቤት ለቤት ፍተሻ ከ25 በላይ ንጹሃን ወጣቶች ያለ ምንም ፍርድ በአደባባይ ተረሽነዋል።
ዋሸራ ማርያም አዊ ዞን በቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ተጠልለው የነበሩ ከ15 በላይ አዛውንቶችና ምዕመናን በግጭቱ ሳቢያ ህይወታቸውን እንዲጠፋ ተደርጓል።
በአዲስ አበባ ከተማ (ስልታዊ ማግለል እና የጅምላ እስራት በዋና ከተማዋ የተፈጸሙት ወንጀሎች ህዝቡ ድምፅ አልባ እንዲሆን ለማድረግ ታቅደው የተከናወኑ የመዋቅር ጥቃቶች ናቸው።
መደበኛ ያልሆኑ የጦር ሰፈሮች አዋሽ ሰባት፣ ገላን፣ ኮልፌ ማሰልጠኛ)፦ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከ100,000 በላይ ታሳሪዎች የአማራ ተወላጅ የሆኑ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ የቪዲዮ ባለሙያዎችና ወጣቶች ያለ ምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታድነው በእነዚህ በረሃማ ካምፖች ውስጥ ለእንግልት ተዳርገዋል።
የአዲስ አበባ መግቢያ በሮች ሰንዳፋ፣ ሱሉልታ፣ ቡራዩ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ተጓዦች ተጎድተዋል። ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተፈናቀሉና በሰላማዊ መንገድ ወደ ዋና ከተማዋ ለመግባት የሞከሩ ዜጎች በማንነታቸው ብቻ መታወቂያቸው እየታየ ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ ተከልክለዋል።
ፖለቲካዊ እና ህሊናዊ ማጠቃለያ
ተጠያቂነትን ማድበስበስ፦ በእነዚህ ሁሉ ቦታዎች የተፈጸሙትን የጅምላ ጭፍጨፋዎች አስቀድሞ መከላከል ያልቻለው፣ ሲፈጸምም ዜጎቹን ጥሎ የሸሸው እና እስካሁንም ለተጎጂዎች ፍትህን ያልሰጠው ይኸው ስልጣን ላይ ያለው የብልፅግና መራሹ ስርዓት ነው።
ዛሬም ድረስ በአማራ ግዛቶች ከተሞችና ገጠር ቀበሌዎች የሚዘንበው የድሮን እሳት፣ በአዲስ አበባ ከተማ መግቢያ በሮች ላይ የሚፈጸመው ስልታዊ ማግለል እና የሺዎች ዜጎች የጅምላ እስራት የብልፅግና ስርዓት ቀጥተኛ ፖሊሲ ውጤቶች ናቸው።
ስለሆነም፣ ይሄንን የአማራን ህዝብ የህልውና አደጋ ወደ ጎን በመተው እና የተፈሰሰውን የንጹሃን ደም በመርሳት የብልፅግናን ስልጣን በምርጫ ለማደስ መሞከር ከተገደሉት ንጹሃን በላይ የታሪክና የህሊና ተጠያቂነትን የሚያስከትል ነው። ይህ ጉዳይ ለፖለቲካ የድጋፍ ስምምነት የሚቀርብ ሳይሆን፣ የንጹሃን ዜጎችን የመኖር መብት እና የሀገርን ህልውና የማዳን ስር ነቀል ጥያቄ ነው። #Dawit #Amhara ከንጉሶች መንደር
የማይሻረው የታሪክ ጠባሳ፦ የንጹሃን ደም እና አማራ ጠሉ የብልፅግና ስርዓት ምርጫ!!
ባለፉት ስምንት ዓመታት በአብይ አህመድ የሚመራው የብልፅግና ስርዓት ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ፣ በመላው ሀገሪቱ በማንነታቸው (በአማራነታቸው) ብቻ ተለይተው በግፍ የተጨፈጨፉት፣ የተፈናቀሉት እና የታሰሩት ውድ የሆኑ የአማራ ልጆች መከራ የታሪክ ጥቁር ማህደር ነው።
በዚህ እጅግ አሳዛኝ እና አስከፊ ሁኔታ ውስጥ፣ ዛሬ ላይ ቆሞ የአብይ አህመድ የብልፅግና ስርዓት በድጋሚ መምረጥ ማለት በማንነታቸው ምክንያት ህይወታቸውን ባጡት ውድ በሆኑት የእነዚህ ሁሉ ሚሊዮኖችን የአማራ ልጆች ደምና ሰቆቃ ላይ መቀለድ ነው።
ይህንን የታሪክ እውነታ ከዚህ ቀደም ባልተጠቀሱ ተጨማሪ ቦታዎች፣ ቀበሌዎችና አሃዞች ጭምር በሰፊው እንደሚከተለው ቀርቧል ቀሪ እና የምታውቁት እናንተ በውስጥ አድርሱኝ!!!
በኦሮሚያ ክልል የተፈጸሙ ስልታዊ የጅምላ ጭፍጨፋዎች እና ማፈናቀሎች በዚህ ክልል ውስጥ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ለትውልድ የኖሩባቸው የገጠር መንደሮች የጅምላ መቃብር ተደርገዋል። ጥቃቶቹ የተፈጸሙት የአብይ አህመድ ጸጥታ ኃይሎች አካባቢውን ጥለው በወጡ ማግስት በሚል ማግስት ሲሆን በዚህም የቶሌ ቀበሌ ፍጅት (ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ) ሰኔ 2014 ዓ.ም በይፋ ከ338 በላይ (የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንደገለጹት ደግሞ እስከ 500 የሚጠጉ) ንጹሃን።
የሽመልስ አብዲሳ ኃይል መንደሩን በመክበብ ምንም መከላከያ የሌላቸውን ህጻናት፣ እናቶችና አረጋውያንን በአንድ ቀን ጨፍጭፈው በጅምላ ቀብረዋል።
የሃዋ ገላን ወረዳ (ቂለም ወለጋ፣ ቲቾ ቀበሌ ሰኔ 2014 ዓ.ም መጨረሻ ከ200 በላይ ሰላማዊ አርሶ አደሮች ተገድለዋል። ከቶሌ ፍጅት ጥቂት ቀናት በኋላ የተፈጸመ የቤት ለቤት እረሸና ሲሆን፣ ንብረታቸው በሙሉ እንዲወድም ተደርጓል።
የኪረሙ እና ጊዳ አያና ወረዳዎች ምስራቅ ወለጋ ህዳር 2015 ዓ.ም
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሟቾች እና ከ500,000 (ግማሽ ሚሊዮን) በላይ ተፈናቃዮች። በዚህም በተደራጀ መልኩ የተከፈተ ጥቃት ሲሆን፣ በተለይ በሀሮ ቀበሌ የተፈጸመው ጭፍጨፋ አካባቢውን ሙሉ በሙሉ ከአማራ ተወላጆች የማጽዳት (Ethnic Cleansing) ስራ የተካሄደበት ነው። በአጋምሳ ከተማ እና ጮቢ መንደር ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ነሐሴ 2014 ዓ.ም ከ100 በላይ ንጹሃን አማራ ተገደዋል። ሰላማዊ አርሶ አደሮች በማሳቸው ላይ እና በቤታቸው ውስጥ እያሉ ድንገተኛ ጥቃት ተሰንዝሮባቸዋል ተገድለዋል።
የጋዋ ቃንቃ ትምህርት ቤት ጭፍጨፋ ምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጥቅምት 2013 ዓ.ም፦ ከ54 በላይ ንጹሃን አማራዊያን ተገድለዋል። በተናበበ ሲራ የአብይ አህመድ መከላከያ ሰራዊት አካባቢውን ለቆ በወጣ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የሽመልስ አብዲሳ ኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የተጠለሉ አማራዎችን ለይተው ረሽነዋል። የሰኔ 2012 ዓ.ም የከተሞች ሁከት (ሻሸመኔ፣ ባቱ/ዝዋይ፣ አሰላ፣ ሮቤ፣ አጋርፋ እና ጭሮ ከ200 በላይ ሰዎች በጭካኔ ተገድለዋል።
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ፖለቲካዊ መነሻ በማድረግ፣ በማንነታቸውና በሃይማኖታቸው በተለይ ኦርቶዶክስ የሆኑ አማራዎች ተለይተው በዱላና በሰይፍ ተጨፍጭፈዋል፤ ታሪካዊቷ የሻሸመኔ ከተማ የንግድ ተቋማት ወድመዋል።
አሙሩ ወረዳ (ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ነሐሴ 2014 ዓ.ም)፦ በዚሁ በመከላከያ እና በሸኔ በተቀናጀ ወረራ ቡድን በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ80 በላይ ንጹሃን አርሶ አደሮች የተገደሉ ሲሆን፣ ከ20,000 በላይ ዜጎች መኖሪያ ቤታቸው ተቃጥሎ ተፈናቅለዋል።
ኑኑ ኢንፓር ቀበሌ (ምስራቅ ወለጋ 2015 ዓ.ም)፦ በማንነታቸው ብቻ ተለይተው ከ35 በላይ የሚሆኑ የአማራ ተወላጆች በቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው በህይወት እያሉ የተቃጠሉበት አሰቃቂ ቀጠና ተደርጓል።
ፈንታሌ ወረዳ ምስራቅ ሸዋ መተሃራ ዙሪያ በ2014 ዓ.ም በስኳር ፋብሪካ እና በአካባቢው እርሻዎች ላይ በቀን ሰራተኝነት እና በነዋሪነት ይኖሩ የነበሩ ከ40 በላይ የአማራ ተወላጆች ተለይተው ተረሽነዋል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ማጽዳት ዘመቻ በመተከል ዞን የነበረው ጥቃት ዋነኛ ዓላማ በሰፈራ ፕሮግራም ለዘመናት የኖሩትን የአማራ አርሶ አደሮች በማስፈራራት መሬታቸውን እንዲቀሙ ተደርጓል።
የቢኩጂ ቀበሌ ጭፍጨፋ (ቡለን ወረዳ ታህሳስ 2013 ዓ.ም ከ207 በላይ ንጹሃን አማራ ተጨፍጭፈዋል።በዚህም በአንድ ሌሊት የተፈጸመ ጥቃት ሲሆን፣ ሰለባዎቹ በገጀራና በጥይት ተለይተው ተረሽነዋል።
የባቡሊስ ቀበሌ (ጉባ ወረዳ) መቃብር ፶" ተብሎ የሚጠራው ልዩ ቦታ፦ በቁጥር ያልታወቁ ነገር ግን በርካታ የአማራ ልጆች በህይወት እያሉ በቡድን ወደ እሳት ተጥለው የተቃጠሉበት እና እጅግ አሰቃቂ የቪዲዮ ምስክርነት ለዓለም የወጣበት ቦታ ነው።
የዳንጉር፣ ድባጤ እና ማንቡክ ወረዳዎች ከ2012 እስከ 2014 ዓ.ም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሟቾች ተከታታይ የቤት ማቃጠል ንብረት መዝረፍ እና የመንገድ ላይ አድብቶ መግደል ወንጀሎች የተፈጸሙባቸው ቦታዎች ናቸው። በዚህ ሳቢያ ከ100,000 (አንድ መቶ ሺህ) በላይ ተፈናቃዮች በቻግኒ ማረፊያ ካምፕ ውስጥ ተጠልለው ሲሰቃዩ ነበር
የምዛ ቀበሌ ድባጤ ወረዳ መስከረም 2013 ዓ.ም የወረዳው ባለስልጣናት ባሳዩት ቸልተኝነት ታጣቂዎች በከፈቱት ድንገተኛ ተኩስ ከ45 በላይ ንጹሃን የአማራ አርሶ አደሮች በአንድ ጀንበር ተገድለዋል።
የቻግኒ ዙሪያ እና ባንቡዋሲ ቀበሌዎች፦ ከቤኒሻንጉል ክልል ተገፍተው የወጡ በአጠቃላይ ከ120,000 በላይ የአማራ ተወላጆች ለዓመታት ያለ መጠለያና ያለ ምግብ በሜዳ ላይ ተጥለው የቆዩበት ታላቅ የሰብአዊ ቀውስ ማዕከል እንዲሆን አድርገውት ነበር።
ከሰሜኑ ጦርነት ጋር ተያይዞ የተፈጸሙ የበቀል ፍጅቶች የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ በሰላማዊ አማራዎች ላይ መጠነ-ሰፊ ጥቃቶችን ፈጽመዋል።
የማይካድራ ከተማ ጭፍጨፋ ህዳር 2013 ዓ.ም፦ ከ600 በላይ ንጹሃን አማራ በጦርነቱ መጀመሪያ ሰሞን "ሳምሪ" በተባለ ቡድንና በአካባቢው ሚሊሺያዎች አብዛኞቹ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የቀን ሰራተኞች በዱላ፣ በሰይፍና በገመድ ታንቀው የተጨፈጨፉበት እጅግ ዘግናኝ ክስተት ነው።
የጭና መንደር ፍጅት ደቡብ ጎንደር፣ ዳባት ወረዳ ነሐሴ መስከረም 2013 ዓ.ም ከ120 በላይ ንጹሃን። የሳምሪ ኃይሎች አካባቢውን ጥለው ከመውጣታቸው በፊት የሃይማኖት አባቶችን፣ አረጋውያንንና ህጻናትን በየደጃፋቸው የረሸኑበት የበቀል ጥቃት ነበር።
የቆቦ ከተማ መንዲዳ እና ፍልኪት መንደሮች ሰሜን ወሎ ነሐሴ 2013 ዓ.ም፦ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች። ወደ ከተማዋ የገቡ ኃይሎች በነዋሪው ላይ ሰፊ የጅምላ ግድያ እና የተቋማት ማውደም ወንጀል ፈጽመዋል።
[የጋሸና እና አግሪት አካባቢዎች (ዋድላ ወረዳ ጥቅምት 2014 ዓ.ም ከ80 በላይ ንጹሃን አርሶ አደሮች በጅምላ ተረሽነዋል።
የአጋምሳ እና ኡርጌሳ ቀበሌዎች ሰሜን ወሎ ጦርነቱ በተፋፋመበት ወቅት በአካባቢው በነበሩ የመኖሪያ መንደሮች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ50 በላይ ሴቶችና ህጻናት ተገድለዋል።
በአሁኑ ወቅት በአማራ ግዛትከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የአብይ አህመድ መከላከያ ሠራዊት የድሮንና የከባድ መሳሪያ ቴክኖሎጂን በከተሞች ላይ በመጠቀም ንጹሃንን እየገደለ ይገኛል።
