ar
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
3 222
المشتركون
+2224 ساعات
+2707 أيام
+65730 أيام
أرشيف المشاركات
ባህርዳር 06 ቀበሌ ምንድን ነው የተፈጠረው ? አንድት እህታችን ባህርዳር 06 ቀበሌ መኳንንት ስለሽ ሆቴል ትሰራ ነበር ። ትናንት ጉልበተኛ አስገድዶ በመድፈር ገd ሏታል ተብሏል ። ቀብሯም እንደተፈ
+1
ባህርዳር 06 ቀበሌ ምንድን ነው የተፈጠረው ? አንድት እህታችን ባህርዳር 06 ቀበሌ መኳንንት ስለሽ ሆቴል ትሰራ ነበር ። ትናንት ጉልበተኛ አስገድዶ በመድፈር ገd ሏታል ተብሏል ። ቀብሯም እንደተፈፀመ ነው መረጃ የደረሰኝ ። ይህ እየሆነ ያለው ባህርዳር 06 ቀበሌ ነው ። ደፍሮ ገdላት የሟች ፎቶ ግራፍ አብሬ አስቀምጫለሁ ። ግለሰቡ የአማራ አድማ ብተና አመራር ሲሆን ስሙም ያምራል ይባላል !! ይህ ከሰባዊነት ያፈነገጠ ተግባር የተፈፀመው በቁኑ 8:00 ላይ ነው ብለዋል ።

ድምፃዊ ዳኜ ዋለ ነኝ :- "ቴዲ አፍሮ የሁላችንም የዩኒቨርስቲ መምህር ነው። ድምፃዊ ዳኜ ዋለ ነኝ፤ እንግዲህ ሁላችንም ነገ ስምንት ሰዓትን በጉጉት እየጠበቅን ነው። ክቡር ዶክተር ቴድሮስ ካሳሁን (
ድምፃዊ ዳኜ ዋለ ነኝ :- "ቴዲ አፍሮ የሁላችንም የዩኒቨርስቲ መምህር ነው። ድምፃዊ ዳኜ ዋለ ነኝ፤ እንግዲህ ሁላችንም ነገ ስምንት ሰዓትን በጉጉት እየጠበቅን ነው። ክቡር ዶክተር ቴድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እንደ አጋጣሚ ሆኖ አዲስ ከሚመጣው ስራው ላይ የተወሰኑ ትራኮችን የመስማት ዕድል አጋጥሞኝ ነበር። በተለይ አንዷን ዘፈን 'ደግመህ ስማት' እያለኝ ሶስት አራት ጊዜ አድምጫታለሁ። ስሜቴን ነክታው እምባዬ እስኪመጣ ድረስ ነው ያደመጥኳት። ወንድማችን ቴዲም 'አብሽር! አብሽር!' ብሎኝ ወደ ጭዋታችን ቀጠልን ። እውነት ለመናገር እጅግ ድንቅ ስራ ነው ይዞ እየመጣ ያለው፤ ደግሞም ቴዲ ምን ዓይነት ጥበብ እንደሚሰራ ሁላችንም እናውቃለን። ቴዲ አፍሮ ለሁላችንም የዩኒቨርሲቲ መምህራችን ነው። * እንወድሃለን፣ * እናከብርሃለን! መልካም ዕድል ለነገው ዕለት፤ ሁላችንም ስምንት ሰዓትን በጉጉት እየጠበቅን ነው።" ©️ድምፃዊ ዳኜ ዋለ ነገን ጓጓሁ እኔም ጎበዝ

ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር የትንሳኤ በአልን በማስመልከት ተሃድሶ በማድረግ በትግሉ ሁኔታ ላይ ምክክር አደረገ:: ሚያዚያ 6/2018 የትንሳኤን በአልን በማስመልከት በደማቅ ሁኔታ ተሃድ
ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር የትንሳኤ በአልን በማስመልከት ተሃድሶ በማድረግ በትግሉ ሁኔታ ላይ ምክክር አደረገ:: ሚያዚያ 6/2018 የትንሳኤን በአልን በማስመልከት በደማቅ ሁኔታ ተሃድሶዉን ሲያደርግ በጃማ ቀጠና አካባቢ ያሉ የአገር ሽማግሌዎች፣የሀይማኖት አባቶችና የአባት አርበኞችን ጨምሮ ነው።በዚሁ ተሃድሶ ኘሮግራም ላይ ያሉ የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ፀረ አማራ አገዛዙ አማራ ህዝብ  ላይ እያደረሰዉ ያለዉን የንፁኋን ሞት እና ንብረት ላይ በፁኑ አዉግዘዋል። የክፍለ ጦሩ አመራሮች በተሃድሶው የአማራን ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ ብርቱ ተጋድሎ ላይና በድል ዋዜማ እንገኛለን በቀጣይም በቁርጠኝነት ታግለን ለድል እንበቃለን በሚል ከህዝባችን ጋር ተግባብተናል ብለዋል::  መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 07/2018 ዓ.ም ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን አውደ ውጊያዎችን ስናደርሳችሁ እጅጉን ኩራት ይሰማናል ይወዳጁን ቤተሰብ ሁኑ!!

።።የጨነቀለት።።_ ደብረ-ወርቅ የጥምር ጦሩ ሻንበል አዛዥ እና የኦፕሬሽናል መምሪያ ሀላፊው ፋኖን ተቀላቀለ ። ___ሚያዝያ 07 / 2018 አ.ም የእናርጅ እናውጋ ወረዳ አስተዳዳሪ የአቶ ሙሉ ጌቴ አ
።።የጨነቀለት።።_ ደብረ-ወርቅ የጥምር ጦሩ ሻንበል አዛዥ እና የኦፕሬሽናል መምሪያ ሀላፊው ፋኖን ተቀላቀለ ። ___ሚያዝያ 07 / 2018 አ.ም  የእናርጅ እናውጋ ወረዳ አስተዳዳሪ የአቶ ሙሉ ጌቴ አጃቢ የነበረው እና ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የወረዳው ጥምር-ጦር ሻንበል አዛዥ ምክትል ሳጅን ምንአይቶ አብራራው የጥምር ጦሩን  መረጃ እና ደህንነት የሆነውን ሀብቴ ዋለን በመምታት  ሁለት ክላሽ በመያዝ የአፋብን ቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ /ጦር 4ኛ ሬጅመንትን ተቀላቅሏል። _ይቀጥላል __

ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር የትንሳኤ በአልን በማስመልከት ተሃድሶ በማድረግ በትግሉ ሁኔታ ላይ ምክክር አደረገ:: ሚያዚያ 6/2018 የትንሳኤን በአልን በማስመልከት በደማቅ ሁኔታ ተሃድ
+1
ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር የትንሳኤ በአልን በማስመልከት ተሃድሶ በማድረግ በትግሉ ሁኔታ ላይ ምክክር አደረገ:: ሚያዚያ 6/2018 የትንሳኤን በአልን በማስመልከት በደማቅ ሁኔታ ተሃድሶዉን ሲያደርግ በጃማ ቀጠና አካባቢ ያሉ የአገር ሽማግሌዎች፣የሀይማኖት አባቶችና የአባት አርበኞችን ጨምሮ ነው።በዚሁ ተሃድሶ ኘሮግራም ላይ ያሉ የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ፀረ አማራ አገዛዙ አማራ ህዝብ  ላይ እያደረሰዉ ያለዉን የንፁኋን ሞት እና ንብረት ላይ በፁኑ አዉግዘዋል። የክፍለ ጦሩ አመራሮች በተሃድሶው የአማራን ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ ብርቱ ተጋድሎ ላይና በድል ዋዜማ እንገኛለን በቀጣይም በቁርጠኝነት ታግለን ለድል እንበቃለን በሚል ከህዝባችን ጋር ተግባብተናል ብለዋል::  መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 07/2018 ዓ.ም

የፋኖን ብትር መቋቋም ያቀተው የብልፅግና ሰራዊት ንፁሀንን በይፋ ከቤት አውጥቶ ረሽኗል። ........................................... ሚያዚያ 07/2018 ዓ.ም በቀጥታ መዋጋት ያልቻለው የብልፅግና ሰራዊት እና የሰርአቱ አሽከሮች የበቀል ጥሙን የንፁሀንን ህይወት ከቤት በማውጣት እየቀጠፈ ይገኛል አገር ሰላም ነው ብለው ከቤታቸው ተቀምጠው የነበሩ ባል እና ሚስት እንዲሁም ልጃቸውን አንድ ቤት ውስጥ የነበሩትን አርሶአደሮች በአደባባይ የገደለ ሲሆን፦ 1.ታዴ ቢነጋ......ዕድሜ... 51....አባወራ 2.አንችኔ ዘለቀ....ዕድሜ .48..ሚስት 3.ምንታምር ታዴ .ዕድሜ ..22.ልጅ ሲሆኑ በሞጣ ሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ደብር ሚካኤል ቀበሌ ሚያዚያ 03/2018 ዓ.ም ጥቃቱ የተፈፀማቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪወች አስክሬናቸውን በማንሳት ስርአተ ቀብር እንዲፈፀም ተደርጎል። ስርአቱ አማራ ጠል ነው የምንለው በምክኒያት ነው ዛሬም አረመኔነቱን በይፋ አሳይቷል። የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ሰበር ዜና! ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ከተማን በከፊል በቁጥጥር ስር በማዋል ታላቅ ድል አስመዘገበ:: ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር በጥላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በራያ ቆቦ ዙሪያ ያሉ ቀበሌዎችንና የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና መቀመጫን ቆቦ ከተማን በከፊል ተቆጣጥሮ ውሏል። በተጨማሪም የ102ኛ ኮር እስከ ቆቦ ከተማ ዘልቆ በመግባት 105 የፌደራል ፖሊስና ከ250 በላይ የመከላከያ ሰራዊት ደምስሷል። ተወርዋሪዋ ልዩ ዘመቻ በቀይ አፈር በነበረው ተጋድሎ 89 የመከላከያ ሰራዊት ደምስሳለች። ጠላት ከጧት ጀምሮ በድሮን፣ በቢ-ኤም፣በዙ-23፣ በመድፍና በታንክ የተጠናከረ ማጥቃት ቢያደርግም አይበገሬዎቹን ማቆም ተስኖት ውሏል። የወገን ሀይል የ102ኛ ኮር እንድሁም ተወርዋሪ የሆነችው ልዩ ዘመቻ በጥምረት ባደረጉት ማጥቃት በሰሜን ወሎ ቆቦ ከተማን በከፊል በመቆጣጠር የአብይ አህመድን ስልጣን አስጠባቂ የፌደራል ፖለስና የመከላከያ ሰራዊት በከፍተኛ ደረጃ ተመትቶ ሙትና ቁስለኛውን በአንፑላን ወደ ቆቦ ሆስፒታል ሲያመላልስ ውሏል። በጧት የጀመረው ተጋድሎ በጥላት ላይ ወታደራዊና  ፖለቲካዊ የስበት ማዕከሉን በመለየት የ102ኛ ኮር በጮቢ በር የጥላትን ድሽቃ በወገን ሞርተር ሙሉ በሙሉ በማውደም፣ በካራይላና በጠዘጠዛ ካምፕ  በከፍተኛ ደረጃ እርምጃ የተወሰደበት ሲሆን በተወርዋሪዋ ልዩ ዘመቻ በቀይ አፈርና አባሆይ ጋሪያ በተመሳሳይ የወገን ጦር የሀይል የበላይነትን በመውሰድ ከላይ የተጠቀሱትን የገጠር ቀበሌዎችንና ከተሞች በቁጥጥር ስር አውሏል። በመጨረሻም የወገንን ሀይል መቋቋም ያቃተው የአብይ አህመድ ጨፍጫፊው አገዛዝ 01 ቆቦ ዙሪያ የቀመሌ ተክለሀይማኖት ቤተ-ክርስቲያንን ሆን ብሎ በመድፍ በመምታት እንድሁም የንፁህ አማራዎችን ቤት ታርጌት በማድረግ ፋኖን ለማስለቀቅ በሚል ስሌት የበርካታ ሲቪሊያንን ህይወት በከባድ መሳሪያ ቀጥፏል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 7/2018 ዓ/ም

ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ራያ ቆቦ እና ጊዳን ወረዳ አቅራቢያ ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ:: የጊዳን ወረዳ መቀመጫ ከሆነችው ሙጃ ከተማ እና ከወንዳች በርካታ እግረኛ ሃይል እና ቢ ኤም 107 እና ዙ23 መካናይዝድ እንዲሁም በአየር ሃይል በሁለት ድሮኖች ታጅቦ ውጊያ የከፈተውን የፋሽስቱ ሰራዊት በሚገባ በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ በርካታ የጠላት ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::  የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ በቀይ አፈር በነበረው ተጋድሎ 89 በላይ የሚሆን የ61ኛ ክፍለ ጦር የመከላከያ ሰራዊት ደምስሳለች። ጠላት ከጧት ጀምሮ በድሮን፣ በቢኤም፣በዙ23፣ እንዲሁም በመድፍ የተጠናከረ ማጥቃት ቢያደርግም አይበገሬዎቹን ማቆም ተስኖት ውሏል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 7/2018 ዓ/ም

የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አካል የሆነው የአፄ አምደ ፅዮን ኮር አሃዶች በአይዞሽ አሞራ ተራራማዎች ላይ ባደረጉት የተቀናጀ ውጊያ በርካታ የአገዛዙ አየር ወለድ ክፍለጦር አባላት ሙትና ቁስለኛ ማድረጋቸውን ኮሩ በግንባር መረጃው ገለፀ። ሚያዚያ 07/2018ዓ.ም የአፄ አምደ ፅዮን ኮር አካል የሆኑት ከራንቦ ክፍለጦርና ከ7ለ70 ክፍለጦር በተወጣጡ ውስን ሻለቆች በተደረገ የቅንጅት የጨበጣ ውጊያ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ የአገዛዙ ሰራዊት ከጥቅም ውጭ ማድረጉን ኮሩ አረጋግጧል። ጠላት መነሻውን ከደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር፣ ከጉዶበረት እና ከቀይት ከተማ በማድረግ በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ስር በሚገኘው ወደ ባሶና ወረና ወረዳ ልዩ ቦታው አይዞሽ አሞራ በተባለ አካባቢ በሞርተርና ዙ-23 ታጅቦ በድሮን እየጨፈጨፈው የሚገኘውን የአማራ ህዝብ በሀይል የምርጫ ካርድ ለማሰራጨት ከንጋቱ 12:00 ላይ በማቅናት ላይ እያለ በጀግናው ሰራዊታችን በተፈፀመበት ጥቃት በርካታ የብልፅግናው ሰራዊት ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በደፈጣ ጥቃት የተጀመረው ውጊያ ወደ ጨበጣ ውጊያ ተቀይሮ ጀግናው የአማራ ፋኖ በአገዛዙ የቀይ ቦኔት ለባሽ ላይ በተጎናፀፈው ድል በሁለት (2) አንቡላንሶች የጠላትን አስክሬንና ቁስለኛውን ወደ ደብረብርሀን ከተማ ሲያመላልስ ውሏል። ይሕ ዜና እስከተጠናቀረበት እኩለ ቀን ድረስ በአይዞሽ አማራና አካባቢው አድማሱን ያሰፋው ውጊያ ተጠናክሮ መቀጠሉን ኮሩ የገለፀ ሲሆን ጠላት በደረሰበት ከፍተኛ ምት በመደናገጥ በዘፈቀደ የሞርተር ቅንቡላ ወደ ማህበረሰቡ እየወረወረ ይገኛል። በተመሳሳይ ዜና በትላንትናው ዕለት የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአጼ ዘር ዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ነጎድጓድ ክፍለጦር ከደብረብረሀን ከተማ ቅርብ ርቀት ላይ ከኩኬለሽ እስከ በዞ ድርሰ በነበረው አውደ ውጊያ ክፉኛ የተመታው የጠላት ሀይል እስከ አሁኗ ሰአት ድረስ ሙት እና ቁስለኛውን እየሰበሰበ ሲሆን በተያያዘ ዜና ናደው ክፍለጦር በመራቤቴ ቀጠና ባደረገው መጠነ ሰፊ የማጥቃት ዘመቻ ክፉኛ የተመታው ጠላት የበቀል እርምጃውን ዛሬም በ107 እና ሞርታር ተራራዎችን እየደበደበ ይገኛል ሲል የአፄ ዘር ዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር አስታውቋል።        ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''     ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ      ሚያዚያ 07/2018ዓ.ም

ሰበር ዜና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ዐፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ስር የሚገኘው ብርቱው ነጎድጓድ ክፍለ ጦር፣ ከማለዳው የፀሐይ መውጣት ጀምሮ የብልፅግናን ጦር አይቀጡ ቅጣት እየቀጣው ይገኛል። ​​ለ
+2
ሰበር ዜና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ዐፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ስር የሚገኘው ብርቱው ነጎድጓድ ክፍለ ጦር፣ ከማለዳው የፀሐይ መውጣት ጀምሮ የብልፅግናን ጦር አይቀጡ ቅጣት እየቀጣው ይገኛል። ​​ለመውደቅ "አንድ ሐሙስ" ብቻ እንደቀረው የሚነገረው የብልፅግና አገዛዝ፣ በዛሬው ዕለት የመጨረሻ ያለውን ኃይል አስተባብሮ ወጥቷል። በሻለቃ እሬና የሚመራውና ከደብረ ብርሃን ከተማ "አለኝ" የሚለውን ኃይል የኮማንዶ ክፍለ ጦርን፣ የአድማ ብተናንና ሚሊሻን አጣምሮ የያዘው ይህ ጦር በፋኖ ብርቱ ክንድ እየተገረፈ የሚገኝ ሲሆን ​የውጊያው ድባብና ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ለመያዝ ያሰበ የአገዛዙ ሰራዊት ሽንፈትን እያስተናገደ ይገኛል። ይህ አውደ ​ውጊያ ትላንት ማለዳ በ2:30 ላይ የጀመረ ሲሆን፣ እንደ እሳተ ገሞራ እየተፋፋመ እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ ቀጥሏል። ውጊያው የተደረገባቸው ቀጠናዎች ከኩኬለሽ እስከ ዘንዶጉር የተዘረጉ ሲሆን፣ የጠላት ጦር ዋና ፍላጎት "በዞ" የተባለውን ቀበሌ በቁጥጥሩ ስር ለማዋል ነበር። ሆኖም ግን የነጎድጓድ ክፍለ ጦር ተዋጊዎች የቀጠና ድንበር የጠላት መቃብር በማድረግ አድማሱን እያስከበሩ ይገኛሉ። ይህ አራዊት ሰራዊት በጀግኖቹ የዐፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ብርቱ ክንድ እየተደቆሰ ፊት መቆም አቅቶት በመፈራረስ ላይ ከመሆኑም በላይ የሸዋ ምድር በጀግኖች ድምፅ እየተናወጠች የአማራ የመኖር ነፃነት ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ ሚያዝያ 07/08/2018 ዓ.ም

የጥንቃቄ መረጃ‼️ የሜጀር ጀኔራል ውባንተ 1ኛ ኮር ቀጠና ጠላት ከወረዳ ከተማዎች እየወጣ አፈና ከበባ ለመፈጸም እያቀደ ይገኛል።በመጀመሪያ እቅዱ ጉና ክፍለጦር ጠንካራዋ እስቴ ዴንሳ ብርጌድን ለመክበብ ማቀዱ ታውቋል። የወትሮ ዝግጁነት አይለያቹህ‼️                  ድል ለአማራ ፋኖ!

ከአባ ሳሙኤል ማረሚያ ቤት የተሰማ የፖለቲካ እስረኞች የድረሱልን ጥሪ፡ "ምግብና ውሃ ተከልክለናል" መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቂሊንጦ ወደ አባ ሳሙኤል ማረሚያ ቤት የተዛወሩ የአማራ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች፣ በማረሚያ ቤቱ እየተፈጸመባቸው ያለውን "ኢ-ሰብአዊ አያያዝ" በመቃወም ዛሬ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ። እስረኞቹ በችሎት ፊት ባሰሙት አቤቱታ፣ መሠረታዊ የሆኑት የምግብ፣ የንጹህ ውሃ እና የሕክምና አገልግሎቶች በመከልከላቸው ለከፍተኛ ስቃይ መዳረጋቸውን ገልጸዋል። በተለይም ማረሚያ ቤቱ የሚሰጠው ምግብ ለፍርደኞች (ቅጣት ለተወሰነባቸው) ብቻ ተብሎ የተዘጋጀ መሆኑንና እስረኞች በራሳቸው ወጪ እንኳን ምግብ ገዝተው እንዳይመገቡ መታገዳቸውን አስረድተዋል። ቤተሰብ እንደ በሶ ያሉ ምግቦችንና አልባሳትን እንዳያስገባላቸው መከልከሉ ለከፍተኛ ረሃብና ለጤና መታወክ እንደዳረጋቸው በአጽንኦት ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የታሰሩበት "ዞን አራት" ቀደም ሲል ለከፍተኛ የዲስፕሊን ቅጣት ተብሎ የተለየ ክፍል መሆኑን የጠቀሱት እስረኞቹ፣ የውሃ አቅርቦት በቀን ለ15 ደቂቃ ብቻ በመገደቡ የግልና የአካባቢ ንጽህናን ለመጠበቅ እንዳልተቻለ ገልጸዋል። የመጸዳጃ ቤቶች መሙላትና የፍሳሽ ቆሻሻ በየክፍሉ ወለል ላይ መፍሰስ በፈጠረው ጠረን ለተላላፊ በሽታዎች እየተጋለጡ መሆኑንና በማረሚያ ቤቱ ያለው የሕክምና አገልግሎትም እጅግ ደካማ እንደሆነ አመልክተዋል። በተጨማሪም ክፍሉ ምንም ዓይነት የቤተ-መጻሕፍትም ሆነ የቴሌቪዥን አገልግሎት እንደሌለው ተገልጿል። የሕግ ባለሙያዎች እንደሚገልጹት፣ ገና ጥፋተኝነታቸው ባልተረጋገጠ "የቀጠሮ እስረኞች" እና ፍርድ ባረፈባቸው "ታራሚዎች" መካከል ግልጽ የሆነ የቦታና የአያያዝ ልዩነት ሊኖር ይገባል። ሆኖም በአባ ሳሙኤል የሚገኙት እነዚህ የአማራ የሕሊና እስረኞች፣ ከባድ ወንጀል ፈጽመው የረጅም ጊዜ እስራት ከተፈረደባቸው ግለሰቦች ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጋቸው ለደህንነታቸው ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው ለችሎቱ አስታውቀዋል።

የሙጎጉቱ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በአገዛዙ ሠራዊት በመድፍ ተመታ! (ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም - ኢትዮ 251 ሚዲያ) ከመካነሰላም ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኘውና በቅርቡ የተመሰረተው የሙጎጉቱ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም፣ በአገዛዙ 11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 87ኛ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድ ምድብተኞች በተተኮሰ መድፍ መመታቱን የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ አስታወቀ። በመካነሰላም ከተማ "አሜጃ" በተባለ ስፍራ ላይ መድፍ አጥምዶ ወደ ገዳሙ በተደጋጋሚ ሲተኩስ የዋለው የጠላት ኃይል፣ በፈጸመው ጥቃት የገዳሙ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ጣራ በመድፉ ፍንጣሪ እንዲበሳሳ አድርጓል። ይህ አረመኔያዊ ጥቃት በሃይማኖት ተቋሙ ላይ ካደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በንጹሐን ዜጎች ላይም ከባድ ሰብዓዊ ጥፋት አስከትሏል። እንደ ዕዙ መረጃ ከሆነ፣ በመድፍ ጥቃቱ ሳቢያ ሁለት ንጹሐን ሰዎች ክፉኛ የቆሰሉ ሲሆን፣ ከቆሰሉት መካከል አንዱ በደረሰበት ከባድ ጉዳት ምክንያት የመትረፍ ዕድሉ አነስተኛ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ገልጸዋል። የገዳሙ አካባቢ ነዋሪዎች በበኩላቸው የአገዛዙ ሠራዊት የሃይማኖት ተቋማትን እንደፈለገ ለወታደራዊ ምሽግነት እንደሚጠቀም፣ ካልሆነም ደግሞ ታርጌት አድርጎ በመምታት ሕንፃዎችን እንደሚያፈርስ በመጥቀስ ድርጊቱን በጽኑ አውግዘዋል። ምኒሊክ ዕዝ የአገዛዙ ሠራዊት በንጹሐንና በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚፈጽመው ይህ ዓይነቱ ጥቃት የሽንፈቱ ማሳያ መሆኑን ገልጾ፣ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ሕዝብ የህልውና ተጋድሎ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

+3
በአንዱ የባንክ አካውንቱ ውስጥ ብቻ 17 ሚሊዮን ብር አለ። ስራው #አምቦ ከተማ ውስጥ እየዞረ በጉልበት ገንዘብ መሰብሰብ ነው። የአምቦ ከንቲባ የቅርብ ጓደኛ ነው። በጋራ ነው የሚሰሩትን ገንዘብ የሚካፈሉት። ዛሬ አብረው እንደነበሩ መረጃ አለ። ይህ ጨካኝ ማፊያ ከዚህ በፊት አንድ ሴት ልጅ አስገ ድዶ ከደፈረ በኃላ በጩቤ ወግቶ ገድ ሏ ታል። በፖሊስ ተይዞ ምንም ሳይጠየቅ ነው የተለቀቀው። ከዚህም የባሱ ዘንግናኝ ወንጀል የፈፀመ ነው። የተጠናከረ ማስረጃ በተከታታይ ይቀርባል። #ብልፄ ሀገሪቷን የማፊያዎች ፣ የወንጀለኞች ፣ ያሻቸውን በሚፈፅሙ ቡድኖች አዋቅሯታል። በመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች የተደራጁ ለብልፄ ሽፋን የሚሰጡ ፣ በባለስልጣናት የሚደገፉ ፣ የዘረፋ ስኳዶች አሉ። የሁሉም በዝርዝር ይቀርባል። ህዝቡ ከዚህ በኃላ ይህንን የግፍ አገዛዝ #እምቢ ማለት አለበት። ከዚህ በላይ ምንም የሚመጣ ግፍና ጭካኔ የለም። በባለስልጣናትም በሰፈር ጋንግስተሮችም እጅ መስጠት ይብቃ ሸር ሸር

ከሌሊቱ 5:45 በደብረ ማርቆስ ከተማ እነማይ ሆቴል ፊት ለፊት የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በፈፀመው የቦምብ ጥቃት 5 አድማ ብተና አባላት ህይወታቸውን አጠዋል። ሚያዚያ 6 2018 ዓ.ም ======================================= የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት ከሌሊቱ 5:45 ከተማዋን በም/ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ፓትሮል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 9 የአድማ ብተና አባላት የጥቃቱ ሰለባ ሲሆኑ 5 ( አምስት) የሚሆኑት ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ ቀሪ 4 (አራት) የሚሆኑት ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል። የሰሌዳ ቁጥር 04251 (4) ንብረትነቷ የምስራቅ ጎጃም ፖሊስ መምሪያ በሆነች ፓትሮል ተጭነው ሲንቀሳቀሱ ጥቃት የተፈፀመባቸው የአድማ ብተና አባላት የምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ዙሪያ ጥበቃ የሚያደርጉ መሆናቸውም ታውቋል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት