ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد3 011
المشتركون
+2324 ساعات
+367 أيام
+41430 أيام
أرشيف المشاركات
"ውድቀቴን ለሚመኙ ሁሉ፣ ተስፋ መቁረጤን ለማየት የሚጓጉበትን ያህል፣ ተመልሼ ስነሳ ለማየት የሚሆን ትዕግስት ይስጣቸው።"
"አንበሳ የታመመ ሲመስላቸው የሚደሰቱ ብዙ ናቸው፤ ነገር ግን አንበሳ ሲነሳ ሁሉም ወደ ዋሻቸው ይገባሉ።"
"እኔን ለመጣል የሚወረውሩት ድንጋይ፣ እኔ የምቆምበትን መሰላል ለመስራት ያግዘኛል።"
ሰበር ዜና!
ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ ወግዲ እና ጎረንጂ ከተሞችን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ!
በምኒልክ ዕዝ ስር የሚገኘው 105ኛ ኮር 45ኛ ክፍለጦር እና 29ኛ ክፍለጦር የተውጣጡ ሻለቆች በጋራ በመሆን ባከናወኑት የተቀናጀ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ወግዲ እና ጎረንጂ ከተሞችን ከብልፅግና ፀረ-አማራ አገዛዝ ነፃ አውጥተዋል ።
ግንቦት 04/2018ዓ.ም ማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በተከፈተ መብረቃዊ ማጥቃት ሶስት(3) የሆድአደሩ መከላከያ ሰራዊት ሻለቃዎች ላይ በአንድ ጊዜ እርምጃ ተወስዷል። በውጊያውም የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ጦር ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል። የ105ኛ ኮር አናብስቶች በወሰዱት ድንገተኛ እና ኢ-ተገማች ማጥቃት በርካታ የጦር መሣሪያዎች መማረክ ችሏል፡፡ በዚህ አውደ ውጊያ ሁለት(2) ብሬን መትረየሶች ፣ ሰላሳ ሶስት(33) ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች እና በርካታ ቁጥር ያለው ተኳሾች ተማርኳል ።
በተጨማሪም በወረዳው የነበረው ማረሚያ ቤት በመስበር በርካታ የአማራ የሕሊና እስረኞች ሙሉ በሙሉ ማስለቀቅ የተቻለ ሲሆን የብልፅግና ፓርቲ አገልጋይ አመራርና ካቢኔ ወረዳውን ለቆ እግሬ አውጭኝ ብሎ ሸሽቷል።
በዚህ መብረቃዊ ጥቃት የተበሳጨው ሰወ-በላው ስርዓት የእግረኛ ጦሩ ሽንፈትን መከናነቡን ተከትሎ ከተሞቹ ላይ የድሮን ድብደባ አካሂዷል። በጥቃትም የወረዳው አስተዳደር ሕንፃና የፖሊስ ጣቢያ በድሮን ሲውድም ከ10 በላይ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል፡በርካታ የሕዝብና የመንግስት ንብረቶች መውደማቸውም ጭምር ማረጋገጥ ተችሏል።
መዳረሻውን ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ሕዝብ የሕልውና ተጋድሎ ተጠናክር ይቀጥላል!
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 04/2018ዓ.ም
በቋሪት የብልጽግና ቅጥረኞች በውርደት ተመልሰዋል!
༻༺༻༺༻༺༻༺༻
[ግንቦት 04/2018 ዓ.ም፣ ዐፋብን ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት]
የንጹሐንን ደም የሚያፈስሰው የብልጽግና አገዛዝ በቋሪት ወረዳ ወይበይኝ ቀበሌ በማክሰኝን ታዳጊ ከተማ የገለባ ፍራሽ በመሥራት ራሱንና ቤተሰቡን ያስተዳድር የነበረውን ምስኪኑን ግለሰብ #አቶ_መኩሪያው_ታፈረን በአሰቃቂ ሁኔታ በግፍ ቢገድሉትም በፋኖ ክንድ የሚገባቸውን ቅጣት አግኝተው ተመልሰዋል።
ይህ በግፍ የተገደለው ግለሰብ የፋኖ ምሕረት ጥሩነህ የቅርብ ቤተሰብ መሆኑ ታውቋል። ሰላማዊ ዜጎችን በማጥቃት ሕዝብን ለማሸበር የሚሞክረው አገዛዝ፣ የፋኖን የቆረጠ ክንድ መቋቋም አቅቶት ሙትና ቁስለኛውን ተሸክሞ ወደ መሸገበት ጉድጓድ ተመልሷል።
ስሙን መጥቀስ ያልፈለገ በአካባቢው የሚገኝ ነዋሪ በሰጠው መረጃ መሠረት፦
▶ አንድ ሚሊሻ ወዲያውኑ ሲሞት በቁጥር ያልታወቁ የሚሊሻ አባላት ቆስለዋል።
በመጨረሻም ከዘመነ-ኢሕአዴግ እስከ ዘመነ-ብልጽግና ድረስ በኮማንደርነት ሲያገለግል የነበረውን አቶ ተስፋሁን አባተን ሚሊሻዎች አግተው ወስደውታል።
ንጹሐንን መግደል የጀግንነት ሳይሆን የፍርሃትና የውድቀት ምልክት ነው። የብልጽግና ሰራዊት በውጊያ አውድማ መቆም ሲያቅተው ወደ ሰላማዊ ዜጎች መዞሩ፣ ሥርዓቱ ምን ያህል የሞራል ዝቅጠት ላይ መውደቁን ያሳያል።
ፋኖ ግን የሕዝብ ልጅ መሆኑን በተግባር እያሳየ፣ የሕዝብን ሰላም ለማስከበርና የንጹሐንን ደም ለመመለስ ትግሉን አፋፍሞ ቀጥሏል።
#ፎቶው፦
▶ ብልጽግና ላሰማራቸው አራጆች በአንድ ወቅት ያሰራጨው የእርድ መፈፀሚያ ምሳር (መጥረቢያ) ነው።
#8የአገዛዙ አባላት ያለ አንድ ተኩስ (04) መከላከያ( 04) ፓራ ኮማንዶ በስቦ ማስከዳት ስልት ጋንታ አዛዡና ቲም መሪው ፋኖን ተቀላቀሉ!!
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
....ግንቦት 04/2018 ዓ.ም
ለማህበራዊ ስራ ኃላፊነትየማይሰጧቸውን ጨቅላ ህፃናት ለጦርነት የሚማግደው የአብይ አህመድ ስርዓት ነው።
1-አዲሱ አሻግሬ ዕድሜ_16..ፓራኮማንዶ
2-ዋሲሁን ዘውዱዕድሜ_15.ፓራኮማንዶ
3-ቻላቸው ስሜ ዕድሜ_17..ፓራ ኮማንዶ ከታፈኑበት አምልጠው ወደ ቤተሰቦቻቸው ተቀላቅለዋል።
4-ማሞ ጫላ......መከላከያ ከ25ክ/ጦር
5_አብርሀም ኩማ.......መከላከያ ከ25ክ/ጦር
6.አብዲ ሙላቴ....መከላከያ ከ25ክ/ጦር
7-መለሰ አሰፋ..... ፓራኮማንዶ 74ኛ ክ/ጦር የተቀላቀለ
8-ግርማይ አበራ.....መከላከያ74ኛክ/ጦር ከፉለገ ብርሀን ከተማ ከድጎ ፅዮን ቢቡኝ ወረዳ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ጋንታ መሪው አዛዡና ቲም መሪው ወደ 201ኛ ኮር 54ኛ እና 74ኛ ክፍለ ጦር ፋኖን ተቀላቅለዋል።
የአብይ ስርአት ትምህርት ቤቶችን ዘግቶ የአማራን ህፃናት ሳይቀር ለጦርነት እያደረጋቸው ሲሆን..
በምስራቅ ጎጃም ከ25ወረዳወች 1400 ፓራ ኮማንዶ አስገድደው ማስገባታቸውን ከልጆች ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን የዳኘ ዋለ ሙዚቃ ከስልካቸው የተገኘባቸው ሰልጣኞች በአብይ ወታደሮች ደ/ማርቆስ ፓሊስ ኮሌጅ እንደተረሸኑ የአይን እማኞች አረጋግጠውልናል።
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ሰበር ዜና!
ምኒልክ ዕዝ ወግዲ እና ጎረንጂ ከተሞችን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ፤ የወንዶቹን በ"ት"ር መቋቋም ያቃተው አገዛዙ ከተማዋን በድሮን ደብ*ድቧን!
ምኒልክ ዕዝ ስር የሚገኙ የ105ኛ ኮር 45ኛ ክፍለ ጦር እና የ29ኛ ክፍለ ጦር ሻለቆች በጋራ በመሆን ባከናወኑት የተቀናጀ ወታደራዊ ኦፕሬሽን፣ ወግዲ እና ጎረንጂ ከተሞችን ከብልፅግና አገዛዝ ኃይሎች ነፃ አውጥተዋል።
ፋኖ በወሰደው በዚህ ድንገተኛ ጥቃት በርካታ የጦር መሣሪያዎችን መማረክ የቻለ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል፦
• 2 ብሬን መትረየሶች
• 33 የክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች * በርካታ ቁጥር ያላቸው ጥይቶችና ተተኳሾች ይገኙበታል።
አፋብን ወደ ፊት
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ባደረገው ልዩ የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን ድል ተቀዳጅቷል።
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አ/ዕዝ
ግንቦት 04/2018ዓ.ም
የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ዛሬ ግንቦት 04 ቀን 2018ዓ.ም ከንጋቱ 12:00 ጀምሮ በደብረ ብረሃን ከተማ ዙሪያ ልዩ ቦታው አንጨቆረር ከተማ ድረስ ዘልቆ በመግባት በወሰደው የተጠና መብረቃዊ ጥቃት በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን ኮሩ በግንባር መረጃው ገልጿል።
ክፍለጦሩ ከአራት ቀናት በፊት እራሱን እንደ ንስር አድሶ በልዩ የሞራል ልዕልና ከፍታ ላይ በፈፀመው የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የብልፅግናው ቀኝ እጅ የሻምበል አመራር በጀግናው የነጎድጓድ ክፍለጦር አናብስቶች ተማርኳል።
ሰራዊታችን በፈፀመው የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን:-
✅ አንድ ፻አለቃ ማዕረግ አመራርን ጨምሮ 3 የጠላት ኃይሎች ተገ*ድለ*ዋል።
✅ 7 ከባድ ቁስለኛ
✅ አንድ (1) ዋና ሻንበል የተማረከ
✅2 ክላሽንኮቭ
✅120 የክላሽ ጥይት
✅ 2 ሙሉ የወገብ ትጥቅ ከነ ካዝናው እንዲሁም
✅ ሙሉ የጠላት የደንብ ልብስ መማረኩን ኮሩ በግንባር መረጃው አረጋግጧል።
በተመሳሳይ የግንባር መረጃ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በመንዝ አውራጃ የዕዙ አካል የሆነው አፄ አምደ ፅዮን ኮር የምኒልክ ክፍለጦር አሃዶች ህዝብን ለመዝረፍ በተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ጥምር ጦር ወራሪ ኃይል ላይ ጉዳት ማድረሱን ኮሩ በላከው የግንባር መረጃ ገለፀ።
ጠላት በሁለት ግንባር ያቀና ሲሆም፣ ከመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ ወገሬ ከተማ ወደ ጦል ንዑስ ወረዳ በማቅናት ከምኒልክ ክፍለጦር አሃዶች ጋር ባደረገው ውጊያ 2 የመከላከያ አባላት ሲገደሉ ከ 4 በላይ የጥምር ጦሩ አባላት ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል።
በሌላኛው ግንባር ጠላት መነሻውን ከመንዝ ቀያ ወረዳ ዘመሮ ከተማ በማድረግ ወደ ክምር ድንጋይ በማቅናት ላይ እያለ በምኒሊክ ክፍለጦር ሻለቆች ክፉኛ መመታቱን ኮሩ የገለፀ ሲሆን በቀጠናው በተደረገ የተቀናጀ ውጊያ በውል የማይታወቅ የአገዛዙ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን ኮሩ አረጋግጧል።
ተደጋጋሚ ሽንፈት እያስተናገደ ያለው የአገዛዙ ዘራፊ ሰራዊት ዛሬም እንደተለመደው በመንዝ ላሎ ወረዳ የጦልና አካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ዝርፊያ የፈፀመ ሲሆን፣ የአርሶ አደር አቶ ታምሩ ወንዶሰን መኖሪያ ቤትን ሰብረው በመግባት ከ37,000ብር ጥሬ ገንዘብ በላይ ሲወስዱ ቤተሰብን ለማገዝ በሞተር ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ላይ ከእያንዳኔዳቸው ላይ ዘረፋ መፈፀሙን ኮሩ በመረጃው አረጋግጧል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 04/2018ዓ.ም
ኩራቶቻችን የምኒልክ ዕዝ ጀግኖች በቦታው የነበረውን ጠላት ደምስሰው ወታደራዊ ስትራቴጅክ ጥቅም ያላትን ወግዲን ጨብጠዋታል።
ዝርዝሩን ይዘን እንመጣለን።
አርበኛ አስረስ ጉድ አለ ሽር ሸር አድርግማ
የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት #የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ኩራቶቻችን የምኒልክ ዕዝ ጀግኖች በቦታው የነበረውን ጠላት ደምስሰው ወታደራዊ ስትራቴጅክ ጥቅም ያላትን ወግዲን ጨብጠዋታል።
ዝርዝሩን ይዘን እንመጣለን።
አርበኛ አስረስ
+5
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!
በሚል መሪ ቃል በምስ/ጎጃም አዋባል ወረዳ የአርሶአደሮች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ግንቦት 4/2018 ዓ.ም
=======================================
ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 206ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የአርሶአደሮች መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተካሒደዋል። የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ ቀርቧል።
በምስራቅ ጎጃም ጎዛምን ወረዳ የቦቅላ ቀኝ አቦ ቀጠና እንዲሁ ህዝባዊ ውይይት የተደረገ ሲሆን አርሶአደሩ ተሳታፊ ሁኗል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ጥበብ ለነጻነት፦ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ ወታደራዊ ኪነት ቡድን አባላት ስልጠና እና የተሃድሶ መርሃ-ግብር በስኬት ተጠናቀቀ!!
ግንቦት 04 ቀን 2018 ዓ.ም።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ፤ በስሩ ለሚገኙ የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ የወታደራዊ ኪነት ቡድን አባላትና አመራሮች ሲሰጥ የነበረውን የአንድ ወር ጥልቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና መሰረታዊ እውቀት ስልጠና በደመቀ ሁኔታ አጠናቋል።
የስልጠናው ዋና ትኩረት፦ ለአንድ ወር በዘለቀው በዚህ መርሃ-ግብር፣ የኪነት ቡድኑ አባላት የሚከተሉትን መሰረታዊ እውቀቶች እንዲጨብጡ ተደርጓል፦
1ኛ, ርዕዮተ-ዓለማዊ ግንባታ፦ የትግሉ ግብ፣ የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ጥያቄዎች እና የወታደራዊ ኪነት ስትራቴጂካዊ ሚና።
2ኛ, የስነ-ልቦና ዝግጁነት፡ በጦር ግንባር እና በሲቪሉ ማህበረሰብ ዘንድ የሞራል ግንባታ ስራዎችን የሚመሩበት ጥበብ።
3ኛ, የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስልት፡ ጥበብን እንደ "ለስላሳ መሳሪያ" (Soft Power) በመጠቀም የጠላትን ፕሮፓጋንዳ የማክሸፍ ስልቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ስልጠናው ተካሂዷል።
ሰልጣኞቹ የቀሰሙትን እውቀት የሚመዝን የጽሁፍ እና የተግባር ፈተና የወሰዱ ሲሆን፣ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ አባላትና አመራሮች እንደየደረጃቸው የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ይህ የምዘና ሂደት የቡድኑን ጥራትና ዝግጁነት ለማረጋገጥ የተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
ከባለድርሻ አካላት የተሰጡ አስተያየቶችን በተመለከተ፦ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ የአፋብን ከፍተኛ አመራሮች፣ የእዝ አመራሮች፣ የኮርና የክፍለ ጦር አመራሮች፣ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ባስተላለፉት መልዕክት፡-
"ፋኖ በጠመንጃው ብቻ ሳይሆን በጥበቡም ጭምር የሚታገል ሃይል ነው። ይህ የኪነት ቡድን የትግላችን ድምጽ፣ የጀግኖቻችን ታሪክ መዝጋቢ እና የህዝባችን ተስፋ ነው" በማለት የቡድኑን አስፈላጊነት አረጋግጠዋል።
የአፋብን ወታደራዊ ቃል አቀባይና የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ ባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ወታደራዊ ኪነት ቡድን የቦርድ ሰብሳቢ አርበኛ አበበ ሙላቱ በፕሮግራሙ መዝጊያ ላይ ባደረገው ንግግር፤ ይህ የተሃድሶ መርሃ-ግብር የኪነት ቡድኑን ይበልጥ በማጠናከር፣ ወደ ተለያዩ ግንባሮችና ማህበረሰቦች በማሰማራት የትግሉን መንፈስ በአዲስ ወኔ እና ተነሳሽነት እንዲያቀጣጥሉ ያስችላቸዋል በማለት ገልጿል። አያይዞም ጠመንጃ መሬትን ሲቆጣጠር፣ ጥበብ ደግሞ ልብንና አእምሮን ትቆጣጠራለች በማለት ድርጅቱም እነዚህን የኪነት ቡድኖች በበላይነት መምራቱ ደግሞ ትግሉ ተቋማዊ መልክ እንዲኖረውና ከባህል እሴቶች ጋር እንዲተሳሰር አድርጎታል በማለት የፕሮግራሙ ፍፃሜ ሆኗል።
“ጥበብ ለነጻነት፤ ኪነት ለህልውናችን!!”
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!! ድል ለአማራ!!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ ባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ወታደራዊ ኪነት ቡድን !!
ፀረ-አማራው አገዛዝ በሰሜን ወሎ ዞን አይና ቡግና ወረዳ ብርኮ 07ቀበሌ እና ብርኳኳ 011 ቀበሌ ንፁሃን ግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ኢ-ሰብዓዊ ጥቃት ፈፀመ!
የአፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር 19ኛ ክ/ጦር በምትንቀሳቀስበት ብርኮ 07 ቀበሌ ነፃ ነው የሚል የተወዛገበ መረጃ ከራሱ የአገዛዙ ሚሊሻዎች የደረሰው የአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ መከላከያ ሰራዊት መነሻውን ከአይና ቡግና ወረዳ የሃሰት ምርጫ ካርድ ለመስጠት እና የተለመደውን የውሸት ፕሮፖጋንዳ ለህዝብ ለመንዛት የተሰጠውን ተልእኮ በአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች በከበረ መስዕዋትነት እና ጥበብ ከሽፏል።
ቀድመው መረጃውን ያጠናከሩት የፋኖ አናብስቶቹ አገር አማን ብሎ እየተግተለተለ የመጣውን የብርሃኑ ጁላን ጦር ባላሰበው እና ባልጠበቀው መንገድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰውበታል።
በዚህ አውደውጊያ ሰባት(7) የጥላት ሃይል ሲደመሰስ አስረ አንድ (11) ቁስለኞችን በአምቡላስ ወደ አይና ቡግና ይዞ ተመልሷል። በዚህ መብረቃዊ ምት የተበሳጨው የብርሃኑ ጁላ ጦር የተሳሳተ መረጃ አድርሰኸናል በሚል የራሱን ተላላኪ አንድ(1) ሚሊሻ ሲረሽን ብርኳኳ 011 ቀበሌ አልጋዞ ጎጥ ላይ እህል ለማስፈጨት ወፍጮ ቤት እየሄዱ የነበሩ ንፁሃን ግለሰቦች ላይም የጭካኔ በትሩን አሳርፎባቸዋል። የ14 ዓመቱ ህፃን ወንድሙ ያረጋል የተባለ ግለሰብ በግፍ የተረሸነ ሲሆን ወጣት አወቀ ፈንቴን ጨምሮ በርካታ ንፁሃን የፋኖ ደጋፊዎች ናችሁ በሚል አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት አድርሰውባቸዋል።
በርካታ ትልልቅ አዛውንቶችም ለፋኖ የቆዬና አመታትን ያስቆጠሩ የአማራ ታሪክን ትናገራላችሁ በሚል የስድብ ዛቻና ማስጠንቀቂያ ማስፈራሪያም ጭምር እንደተሰጡ የአካባቢው ማህበረሰብ መረጃውን አድርሰውናል።
መዳረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ -አማራ ሚኒሊክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 03/2018ዓ.ም
የአሰቦት ገዳም ካህን ተገደሉ‼️
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ አንድ ካህን ተገደሉ።
ተኩሱ የተከፈተው ከገዳሙ ታችኛው የእናቶች ገዳም ሲሆን ዛሬ ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም 9:00 አካባቢ ነው።
ታጣቂዎቹ ዙሪያውን ከበው በከፈቱብን ተኩስ አንድ ካህን ተገድለዋል አስከሬንም ማንሳት አልቻልንም ያሉት መረጃ ሰጫችን እስካሁኗ ሰዓት የጸጥታ ኃይሎች አልደረሱም ብለዋል።
ገዳማውያኑ “እኛ ገዳማውያን ነን መሳሪያ የለንም፤ አባቶቻችን ለሚመለከታቸው አካላት መረጃውን በፍጥነት ያድርሱልን” በማለትም ጥሪ አቅርበዋል።
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም ተመሳሳይ ጥቃቶች እየተፈጸሙ ገዳማውያኑ እና የአካባቢው ምእመናንን እየተሰደዱ እንደሆነም ተገልጿል።
Via- Mahibere kidusan broadcasting servuce
የአሰቦት ገዳም ካህን ተገደሉ‼️
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ አንድ ካህን ተገደሉ።
ተኩሱ የተከፈተው ከገዳሙ ታችኛው የእናቶች ገዳም ሲሆን ዛሬ ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም 9:00 አካባቢ ነው።
ታጣቂዎቹ ዙሪያውን ከበው በከፈቱብን ተኩስ አንድ ካህን ተገድለዋል አስከሬንም ማንሳት አልቻልንም ያሉት መረጃ ሰጫችን እስካሁኗ ሰዓት የጸጥታ ኃይሎች አልደረሱም ብለዋል።
ገዳማውያኑ “እኛ ገዳማውያን ነን መሳሪያ የለንም፤ አባቶቻችን ለሚመለከታቸው አካላት መረጃውን በፍጥነት ያድርሱልን” በማለትም ጥሪ አቅርበዋል።
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም ተመሳሳይ ጥቃቶች እየተፈጸሙ ገዳማውያኑ እና የአካባቢው ምእመናንን እየተሰደዱ እንደሆነም ተገልጿል።
©️ማህበረ ቅዱሳን
