ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多2 966
订阅者
+424 小时
+127 天
+38830 天
帖子存档
+3
#ዛሬም_አፋብን_ሸዋ_ጠቅላይ_ግዛት_አሳምነው_ዕዝ_ጠላትን_ስቦ_በማሥከዳት_እያፈረሱት_ይገኛሉ‼️
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አ/ዕዝ
ግንቦት 03/2018ዓ.ም
ከ450 በላይ የብሬን ተተኳሽና ከነ ሙሉ ትጥቁ የያዘ የ104ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ አባል አፄ አምደፂዎን ኮርን የተቀላቀለ ሲሆን ከ120 በላይ የክላሽ ጥይትና ከነ ሙሉ ትጥቁን ይዞ የመጣው የአድማ ብተና ፖሊሥ ደግሞ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር ጣይቱ ክፍለ ጦር ፋኖን ተቀላቅሏል። አባላቶቹም በክፍለጦሩ አመራሮች ደማቅ አቀባል ተደረገላቸው።
መነሻውን ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት መንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ በማድረግ የአፋብን ሸዋ ጠቅለይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የራንቦ ክፍለጦርን የተቀላቀለው የብልፅግናው 104ኛ ኮማንዶ ክፍለጦር አባል ለፈፀመው ጀግንነት በክፍለጦሩ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአድማ ብተና ፖሊሱም ከአንኮበር አለዩ አምባ ከ29ኛ ሻለቃ ሻምበል (2) ከጋንታ ቲም (2) ምክትል ቲም መሪ ሥሙ ተሥፋዬ ቼሬ የተባለ አድማ ብተና ሁለት እግር ክላሽ፣ ከ(3) መጋዘንና ከ120 የክላሽ ጥይት ጋር የዕዙ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ጣይቱ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
ፋኖን የተቀላቀለው የኮማንዶ አባሉ:-
✅ሁለት የደረት ትጥቅ
✅450 የብሬን ተተኳሽ
✅375 የክላሽ ተተኳሽ
✅8 ካዝና እና
✅አንድ ዘመናዊ የኮማንዶ ጥርጥር ክላሽ
በመያዝ ጀግናው የራንቦ ክፍለጦርንና ጣይቱ ክፍለ ጦርን መቀላቀላቸውን የሁለቱም ኮሮች በላኩት የግንባር መረጃ ገልፀዋል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
#ዛሬም_አፋብን_ሸዋ_ጠቅላይ_ግዛት_አሳምነው_ዕዝ_ጠላትን_ስቦ_በማሥከዳት_እያፈረሱት_ይገኛሉ‼️
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አ/ዕዝ
ግንቦት 03/2018ዓ.ም
ከ450 በላይ የብሬን ተተኳሽና ከነ ሙሉ ትጥቁ የያዘ የ104ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ አባል አፄ አምደፂዎን ኮርን የተቀላቀለ ሲሆን ከ120 በላይ የክላሽ ጥይትና ከነ ሙሉ ትጥቁን ይዞ የመጣው የአድማ ብተና ፖሊሥ ደግሞ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር ጣይቱ ክፍለ ጦር ፋኖን ተቀላቅሏል። አባላቶቹም በክፍለጦሩ አመራሮች ደማቅ አቀባል ተደረገላቸው።
መነሻውን ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት መንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ በማድረግ የአፋብን ሸዋ ጠቅለይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የራንቦ ክፍለጦርን የተቀላቀለው የብልፅግናው 104ኛ ኮማንዶ ክፍለጦር አባል ለፈፀመው ጀግንነት በክፍለጦሩ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአድማ ብተና ፖሊሱም ከአንኮበር አለዩ አምባ ከ29ኛ ሻለቃ ሻምበል (2) ከጋንታ ቲም (2) ምክትል ቲም መሪ ሥሙ ተሥፋዬ ቼሬ የተባለ አድማ ብተና ሁለት እግር ክላሽ፣ ከ(3) መጋዘንና ከ120 የክላሽ ጥይት ጋር የዕዙ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ጣይቱ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
ፋኖን የተቀላቀለው የኮማንዶ አባሉ:-
✅ሁለት የደረት ትጥቅ
✅450 የብሬን ተተኳሽ
✅375 የክላሽ ተተኳሽ
✅8 ካዝና እና
✅አንድ ዘመናዊ የኮማንዶ ጥርጥር ክላሽ
በመያዝ ጀግናው የራንቦ ክፍለጦርንና ጣይቱ ክፍለ ጦርን መቀላቀላቸውን የሁለቱም ኮሮች በላኩት የግንባር መረጃ ገልፀዋል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
የተባበሩት ኢምሬቶች አዲሷ ኢምፔሪያሊስት ሆናለች። ከግማሽ ምዕተ ዓመት የማይበልጥ እድሜ ያላት፤ የአዲስ አበባን ሩብ ያህክል የህዝብ ቁጥር የሌላት ሀገር የሺህ ዘመናት የስልጣኔ ባለቤት እና በአፍሪካ የነፃነት አባት የሆነችዋን ኢትዮጵያ ቅኝ እየገዛች ትገኛለች። ትክክለኛ ሊደር ሺፕ እና የጋራ ርዕይ የሌለው ህዝብ እንዲህ ነው ሚሆነው።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከደመወዝ እስከ ቁሳቁስ በኢምሬቶች ይሸፈናል። ስራ ላይ ካሉት ድሮኖች መካከል ከአንቴና ውጭ ሳትኮም (ሳተላይት) እንዲጠቀሙ ተደርገው የተሻሻሉት TB2 ድሮኖች እና ከ 4 እስከ 24 ሮኬት ቦንቦች መሸከም የሚችሉ ዘመናዊወቹ አኪንቺ ድሮኖች ባለንብረቶች የሆኑት ኢምሬቶች ደብረ ዘይት፣ ባህርዳር እና አሶሳ ላይ የራሳቸውን ድሮኖች ኦፕሬት እያደረጉ ከትመዋል።
AI ሲስተም የተገጠመላቸው እነዚህ እጅግ ዘመናዊ ድሮኖች ውድ ከመሆናቸው የተነሳ ኢትዮጵያ መታጠቅ ያልቻለቻቸው ናቸው። በግዜያዊነት ለስልጠና እና ክትትል የሚመጡትን ሳይጨምር ዛሬ ላይ ከ125 በላይ የአረብ ኤምሬት አየር ሃይል ስታፍ አባላት በደብረ ዘይት እና በሌሎች አየር ኃይል ግቢወች ይገኛሉ። በተለይ ከኢትዮጵያ ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚደረገው ድንበር ዘለል የድሮን ኦፕሬሽን የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በUAE ዜጎች ሲሆን የሀገር ውስጥ ሰወች ምንም አይነት ተሳትፎ የላቸዉም።
ምግብ ሳይቀር ከዱባይ የሚመጣላቸው እነኝህ የUAE ዜጎች አልፎ አልፎ የወርቅ ንግድ ቱጃሩ የሐምዳን ዳጋሎ ወንድም ከሚደግፋቸው በስተቀር የነዳጅ፣ የተተኳሽ እና የስታፍ ወጭ በሙሉ በሀገራቸው ይሸፈናል። የጀነራል ይልማ መርዳሳ ቢሮ መንደርደሪያወችን ከመፍቀድ የዘለለ ሚና የለውም።
ከፖርት ሱዳን እስከ ዳሬ ሰላም ያሉ ፖርቶችን በመቆጣጠር የወደብ ተስፋፊ (Port- imperialist) ለመሆን የምትደክመው ሀገር በሊቢያ ጀነራል ቃፍታርን፣ በሱዳን ዳጋሎን፣ በሶማሊያ ጁባ ላንድ እና ፑንት ላንድ የመሳሰሉ ራስ ገዝ ክልላዊ ኃይሎችን፣ በቻድ የመሃማት ኢድሪስ ዴቢን ሽግግር መንግስት እና ሌሎችንም ስፖንሰር በማድረግ የአፍሪካን ወርቅ በመልቀም ላይ ትገኛለች።
ኢትዮጵያ ውስጥም በሀገር ላይ ያመፀውን አብይን የምትደግፈው እና በተለይም የአማራን ህዝብ የምትወጋው ይህች ሀገር ፍላጎቷ ከእርሻ መሬት ፍለጋም አለፍ ያለ ፀረ-ኢትዮጵያዊ ፕሮጀክትንም ያካትታል።
በነገራችን ላይ ፕሮፌሰር Alex de Waal ከመለስ ዜናዊ ጋር በተለያዬ ግዜ በነበረው ውይይት የያዘዉን ማስታወሻ እ.ኤ.አ 2018 ባካተተበት "The Future of Ethiopia: Developmental State or Political Market Place" በሚለው መጣጥፉ ስር መለስን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ላይ ትልቁ ስጋትህ ምንድን ነው ሲል መጠየቁን አስፍሯል። መለስም ...ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት አንፃር የሚያስቃዠኝ ጉዳይ ቢኖር የባህረ ሰላጤው ዘውዳዊ አገዛዞች (Gulf Monarchies) የአፍሪካ ቀንድን የፉክክር ሜዳቸው ሊያደርጉ የሚችሉበት እድል መኖሩ ነው... በተለይም ታዛዥነትን (loyalty) በስልጣን ሊያከራይ የሚደፍር አመራር ከመጣ ከባድ ችግር ይከተላል የሚል ይዘት ያለው ምላሽ ሰጥቷል። ይህ ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ይከሰት ዘንድ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ስሌት ውስጥ ትልቅ ፖለቲካዊ ውስልትና በመስራት የፀረ-ኢትዮጵያዊ ኃይሎች አቅም ከልክ በላይ እንዲፈረጥም በሰራው ስትራቴጅካዊ ስህተት እርሱም ከደሙ ንፁህ ባይሆንም በበቂ ትንተና ላይ የተመሰረተው የሰውዬው የፖለቲካ ትንበያ አስገራሚ ነበር።
ያ የተሰጋው የኢትዮጵያ ናሽናል ሴኩሪቲ አደጋ በመሐመድ ቢን ዛይድ እና በአብይ አህመድ ጥምረት እውን ሆኗል። ማንም ሀገሩን ማትረፍ የሚፈልግ ቢኖር ይህንን ስትራቴጅካዊ አሰላለፍ ተከትሎ ማስላት ይጠበቅበታል።
ግብዝ ካልሆንን በስተቀር መወረር እና ቅኝ መገዛት ከዚህ በላይ መገለጫ ሊኖረው አይችልም። ደሃው የአማራ ገበሬ፣ ለነፍሱ ማይሰስተው ፋኖ እየተዋጋ ያለው የውስጥ አረመኔወችን ብቻ ሳይሆን የውጭ ቅኝ ገዥወችን ጭምር ነው።
አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ
ድልና ነፃነት ለአማራ ህዝብ
የአማራ ህዝብ ባለፉት ስምት (8)አመት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በአረመኔው ብልፅግና ስርአት ጆኖሳይድ ተፈፅሞበታል ይሄን የተፈፀመበት ብልፅግና ባዋቀራቸው ቡድኖች እና በተለምዶ ጥምር ጦርነኝ በሚለው አሽከሮቹ እና በአማራ የእግዴ ልጆች ነው ። አማራ ሲተርት ከቻልክ እደበሬ ሁን ካልቻልክ እዳህያ ከመሆን ሞትን ምረጥ ይላል ። ይህ ሲባል በሬ የጓደኘውን ደም ወይም ፈርስ ካገኘ ያጓራል የጓደኘው ደም እና ፈርስ ይከረፈዋል አማራ ከሆክ የወድሞችህ ደም በአደባባይ የተገደሉት ይከርፋህ ። ካልሆነ ግን እደአህያ አትሁን ያሲ ባል አህያ የጓደኛውን ደም እና ፈርስ ላይ ሳር ካገኘ እያሸተተ ሳሩን ይበላል እደአህያ ከመሆን ሞትን መምረጥ ጀግንነት ነው ። ለዚህ ደሞ አማራ ሆናችሁ ጥም ጦር እና ካድሬ(ካብኔ) ሆነህ የብልፅግና ስርአት ዳይበር የሆናችሁ ከቀልባችሁ ሁኑ ካልሆነ ግን ቀኑ ሊዘገይ እጂ በአማራ ህዝብ እና በአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ትጠየቃላችሁ ።የኬሚሴ ሚኒሻ ከመከላከያ ጋር የመከላከያ ልብስ ለብሰህ ማጀቴ ክላስተር ላይ የበደላችሁትን በደል በጥፍ ይከፈላል ይህ ሲባል በህዝባችን ላይ የደረሰ በደል ።
1ኛ. የአርሶ አደሩን ከብት ዘርፋል።
2ኛ. የህዝቡን አትክልትና ሰብል ዘርፍል
3ኛ.በስራ ላይ ያሉ ንፁሀን ተገድለዋል (ተረሽነዋል)
4ኛ.መስቀልበር ቀበሌ የገብረኤል ቤተክሪስታን ቁሳቁስ እና መጠበቂያውን መሳሪያ ወስደዋል
5ኛ.ነጌሶ ቀበሌ ሞላሌ ላይ አምስት ሰው ረሽነው ከብቶች ተወስደዋል
6ኛ.በመድፍ ህብረተሰቡን ያለበትን ቦታ በመደብደብ ንፁሀን ገሏል ቤት አቃጥሏል
7ኛ.ወጀድ ት/ቤትን በድሮን ደብድቦታል ተማሪዎችን አልሞ ለመምታት የታቀደ ነበረ
አገዛዙ ብልፅግና የተባለ አረመኔ ስርአት ያሰማራቸውን ጥምር ጦርን የተደራጀው የአማራ ህዝብና የአማራ ፍኖ ከላይ የተጠቀሱትን በደሎች ለመቀልበስ የተሰሩ ስራዎች ።
1ኛ.በሽምቅ የግዴ ልጆች የሆኑትን ሚኒሻ እና ፖሊስ ካራለጎማ ቀበሌ ለመግባት ሲፈልጉ አይቀጡ ቅጣት ተቀጡ
2.የማጀቴ ህዝብ መከላከያ የተባለ ገዳይን በአይናችን ማየት አንፈልግም አሏቸው በፈጠሩት ስብሰባ
3.ካራቆሪ ሚኒሻ በወጣበት ዋርድያ ሲጠብቁ እቅልፍ ወሰዷቸው በፋኖ በትር ተቅልፋቸው ሳይነቁ በዚያው አሸለቡ
4. ማጀቴን ለመቆየት አፈሩ ሁሉ እሳት ሆነባቸው በፋኖ በትር
5.ህዝብ ሰብስበው ስሐምርጫ ሲወሩ አገር እየፈረሰ ሰው እየሞተ ምን አይነት ምርጫ ነው ብለው አፋጠጧቸው
6.የመከላከያ አባል የሆኑት ሰራዊቶች እየሰረጉ ጠፉ
የአገዛዙ አሸከሮች ምን ወሰኑ
1.ማጀቴ ከቆየን በትሩም ይጠነክራል ህዝቡ ይመታናል ሰራዊታችን ጨርሶ ከድቶ ብቻችንን ነው የምቀረው ብሎ ውልቅ አለ
2.ማጀቴ ያለን ንብረት የዘረፉትን ሀብት ሳያሳቸው ከቱርክ መገድ በታች ማንም እዳይወርድ ብለው ሲያስተላልፉ የሚቀበላቸው ሲያጡ የሚመጠውን ሲረዱት ቶሎ አፈተለኩ
3.ኤፉራታና ግድም ምርጫ መረጠ አልመረጠ እኛ ቀድመን አሸንፈናል በማለት ሀዘናቸውን ገልፀው ህዝብ እደጠላቸው አረጋግጠው ሄደዋል
የፋኖ የትጥቅ ትግል ህዝባዊነቱን ያረጋግጣል
ድል ተተጨቆነው ለአማራ ህዝብ
+4
አድዋ ክፍለጦር ግዙፍ የሆነ እግረኛ የፋኖ ሰራዊት ለ11ኛ ዙር አስመረቀ‼️
በአፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ ኮር አድዋ ክ/ር ከፍተኛ አመራሮች ባሉበት ማለትም አፋብን በፓሊት ቢሮ የስልጠና መምሪያ ኃላፊ፣ የበላይ ዕዝ አመራሮች፣ የመይሳ ካሳ ኮር አመራሮችና የአድዋ ክ/ር አመራሮች በተገኙበት በደማቅ መልኩ ማክበር የተቻለ ሲሆን በአርበኛ ተመስገን ወለላው ወ/አዛዥነት የሚመራው የአድዋ ክ/ር እንደከዚህ ቀደሙ በተሻለ መንገድ የሰለጠነ የፋኖ ሰራዊት ከማፍራት አንፃር ታስቦና ታቅዶ አመርቂ በሆነ መንገድ በሁለንተናዊ ዘርፍ የሰለጠነና ብቁ የሆነ ሰራዊት እንዲሁም እዝ እና ሰንሰለትን የጠበቀ መርህን ተከታይ የሆነ ስልጡን ጠንቀቅ ያለ የአማራን ክፉ አሚካላ ስርአት በሁለንተናዊ ዘርፍ የሚጋፈጥ ግዙፍ ሰራዊት 11ኛ-ዙር በማስመረቅ የአድዋን ክ/ር አሀድ መቀላቀል ችሏዋል።
©አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ ህዝብ ግንኙነት ክፍል!
03/ዐ9/2018 ዓ.ም
በአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት የአሰምነው ዕዝ ቁጥጥር ስር በዋሉ አካባቢዎች አፋብን ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት ታሪካዊ የሆኑ የህዝብ ውይይቶች በድምቀት እየተካሄዱ ይገኛሉ።
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!” በሚል መሪ ቃል፣ በትግሉና በህዝቡ መካከል ያለውን ትስስር የሚያጠናክሩ ሰፊ መድረኮች በመርሀቤቴ አውራጃ በሦስት ቀበሌዎች ተካሂደዋል። በዚህም በመርሓቤቴ ወረዳ፦ የታች ቤት እረመሽት ወርካንባ ቀበሌ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ስለ ብሔራዊ ህልውናው መክሯል። እንዲሁም በአፈዘዝ በርቃቶ፦ የመርሓቤቴ ህዝብ ከትግሉ ጎን መቆሙንና በፖለቲካዊ ንቃት ራሱን እያደራጀ መሆኑን ዳግም ያረጋገጠበት መድረክ ተካሂዷል በለሚ እንሳሮ (በይድኖ በሬሳ ቀበሌም በተመሳሳይ ሁኔታ ህዝባዊ ውይይቱ የቀጠለ ሲሆን፣ የአማራ ህዝብን ብሔራዊ ማንነትና ጥያቄ የሚያነቁ ስራዎች ተከናውነዋል።
የፋኖን ምት መቋቋም ያልቻለውና በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኘው የአማራ ጠሉ የአብይ አህመድ "የብልፅግና" ስብስብ፣ እነዚህን ህዝባዊ ስብሰባዎች ለመበተን አስነዋሪ ሙከራዎችን አድርጓል።
በዚህም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሽዋ ጠቅላ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከማህበርሰቡ ጋር ስብሰባ እያካሄደ ባለበት ቅፅበት፣ በሌላ በኩል ደግሞ የአምባገነኑ ስርአት ሰራዊት ስብሰባውን ለማደናቀፍ በወረወረው የሞርተር ቅንቡላን፣ አንድ ንፁህ ከብት እረኛ ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ አድርሷል። ይህ ድርጊት ስርዓቱ ህዝብን ለማሸበር ያለውን ጽኑ ፍላጎት ቢያሳይም፣ በየቀበሌው የቀጠለው ህዝባዊ መነሳሳት ግን ከምንጊዜውም በላይ እየጠነከረ መሄዱን የደረሰን መረጃ ያረጋግጣል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 02/2018ዓ.ም
በጋዜጠኛ ጋሻዬ ንጉሴ ፈረደ ላይ ተጥሎ የነበረው የሥራ እገዳ ሙሉ በሙሉ ተነሳ!
(ግንቦት 02 ቀን 2018 ዓ.ም)
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብን) የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ፣ በጋዜጠኛ ጋሻው ንጉሴ ፈረደ ላይ ጥሎት የነበረውን የሥራ እገዳ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን አስታወቀ።
ዕዙ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ለጋዜጠኛ ጋሻዬ ንጉሴ በላከው ይፋዊ ደብዳቤ እንዳመለከተው፣ ቀደም ሲል በአፋብን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በጋዜጠኛው ላይ ተጥሎ የነበረው የሥራ እገዳ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ ተወስኗል።
ጋዜጠኛ ጋሻዬ ንጉሴ ፈረደ የቀድሞ የፋኖ አባል መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ እገዳው የተነሳው ዕዙ ባደረገው ግምገማ መሆኑ ተጠቁሟል።
ደብዳቤው የተፈረመው በቴዎድሮስ ዕዝ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ በማርሻት ፀሃው አማካኝነት ነው።
በምኒልክ ልጆች፣በአሳምነው ግርፎች፣ በአምባሰል ተራሮች ላይ የረገፈው የአብይ አህመድ ቅጥረኛ ዘራፊ መከላከያ ሰራዊት❌
በቅርብ ቀናት ውስጥ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች አማካኝነት በእኔና በማንነቴ ላይ የሚሰነዘሩ መሰረተ ቢስ ጥቃቶችንና ስም የማጥፋት ዘመቻዎች ስለ ማንነቴና ስለ ቆሜበት ዓላማ እኔ ጎጠኛም ሆንኩኝ የገዛ ጥቅሙን ብቻ የሚያሳድድ አስመሳይ አማራ አይደለሁም። የማንነት ኩራቴንና ለሕዝቤ ያለኝን ክብር ከግል ጥቅምና ከርካሽ ፖለቲካ ጋር አላውለውም። ሰሞኑን ያለ ምንም ስነ-ምግባርና ሃፍረት በክብሬ ላይ ዘመቻ የከፈታችሁ ግለሰቦችና ስብስቦች አደብ እንድትገዙና ከእኩይ ተግባራችሁ እንድትታቀቡ አጥብቄ አሳስባለሁ።
በተለያዩ ማዕዘናት በእኔ ስም የሚሰራጩ መረጃዎች በሙሉ እኔን የማይወክሉና ከእውነት የራቁ ናቸው። በተለይም የክቡር የሆነውን የአማራ ፋኖ ትግል ሽፋን በማድረግ፣ በሐሰተኛ አካውንቶች (Fake Accounts) ስሜን ለማጠልሸት የሚደረገው ጥረት እጅግ አረመኔያዊና የከሳሪዎች አካሄድ ነው። ይህ ድርጊት የትግሉን መንፈስ የሚጎዳና የጠላቶቻችንን ዓላማ የሚያገለግል ነው።
ከዛሬ ጀምሮ በእኔ ስም የሚጻፍ፣ የሚነገርና የሚሰራጭ ማንኛውም መረጃ እኔን እንደማይወክል በይፋ አሳውቃለሁ። እነዚህ የአረማውያንና የከፋፋዮች ሴራዎች ዓላማቸው እኔን ካነገብኩት ዓላማ ማሰናከል ቢሆንም፣ እኔ ግን ከእናንተ ሴራ በላይ መራመድ የምችል ጽኑ ሰው መሆኔን በተግባር አሳያለሁ። በእኔ ስም ከሚከፈቱ የሐሰት ገጾችና ከሚሰራጩ የፈጠራ ወሬዎች ራሱን እንዲጠብቅ እጠይቃለሁ። እውነት ሁልጊዜም ታሸንፋለች!
አለቀ!
+2
የአምባሰል ተራሮች ዛሬም እንደ ትላንቱ የብልፅግናው አገዛዝ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት መቀበሪያው ሆኖ ቀጥሏል!
ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ ከሁለት ቀናትን በላይ በፈጀ አውደ ውጊያ በርካታ የጠላት ሀይል ተደመሰሰ። የምኒልክ ዕዝ አሃድ የሆኑት104ኛ እና 101ኛ ኮር በአገዛዙ ቅጥረኛ ሰራዊት ላይ በቅንጅት በአምባሰል ሰንሰለታማ ተራሮች እጅን ከአፍ የሚያስጭን ገድል ፈፅመዋል። ግንቦት 01/2018ዓ.ም በጀመረው አውደ ውጊያ የ101ኛ ኮር 35ኛ ክ/ጦር ፣ 104ኛ ኮር 24ኛ እና 23ኛ ክፍለጦር የጠላትን ሀይል ሙት፣ ቁስለኛ እና ምርኮ በምርኮ አድርገውታል። በውጊያው የጠላት የ104ኛ ኮር 36ኛ ክፍለጦር አምስተኛ ሬጅመንት ሶስተኛ እና አራተኛ ሻምበል እንዲሁም የክፍለጦሯ ቃኝ ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል። በዚህ ታሪካዊ ተጋድሎ በርካታ የቡድን መሳሪያወች ሞርታርን ጨምሮ ተማርከዋል። ከተማረኩት መሳሪያዎች መካከል፦
☑️ አንድ ሞርተር 82 ከእነ ተተኳሹ
☑️4 ብሬን
☑️ ሁለት ስናይፐር
☑️ ከ80 በላይ ነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ
☑️ 5000የክላሽ ተተኳሽ
☑️2500 የዲሽቃ ተተኳሽ እንዲሁም አንድ መኪና ሙሉ የጠላትን ሬሸን ገቢ ማድረግ ተችሏል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 02/2018 ዓ.ም
ለተላላኪው አብይ አህመድ ስልጣን መሞት በምንም ተዓምር፣ በፍፁም ለሀገር መሞት ሊባል አይችልም።
ይህ...የአብይ አመድንና የጥፋት ቡድኑን ለመታደግ ትልቁን የአማራ ሕዝብ ሲዋጉ ያለቁ የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ናቸው።
የዕዙ አዛዥ አቶ ዘውዱ ሰጥአርጌ ምን ብሎ ሪፖርት ያቀርብ ይሆን?
የአማራ ሕዝብ ባህር ነው። ሲጠማህ ያጠጣሃል። ብትቆሽሽ በፍቅርና በይቅርታ ያጥብሀል።
ስትቶብት ውጦህ ይቀራል። በእብሪ ስትጠጋው አስጥሞ ያስቀርሃል።
ይሄንን እያወቁም ሆነ ሳያውቁ በእብሪትና በአንዳች ጥላቻ ታውረው የገቡ በምታዩት መልኩ ቀርተዋል።
የአምባሰል ተራራና ገደልም እራሱን የቻለ አንድ ክፍለጦር ነው።
የሥነ ልቦና ጦርነት ስትራቴጂዎች የሰዎችን የማስተዋል ችሎታ ለሚፈልጉት ዓላማ እንዲውል የማድረግ (Perception Manipulation) ጥበብ ነው።
አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን መረጃን፣ ክስተቶችን ወይም ሁኔታዎችን የሚያይበትንና የሚረዳበትን የማስተዋል ችሎታ ሆን ተብሎ ለመቀየር የሚደረግ ጥረት ሲሆን ግቡ እውነታን በመለወጥ ላይ ብቻ የተመሰረተ ሳይሆን ያለዉን እውነታ ለአጥቂው ግብ ስኬት በሚመች መንገድ ትርጉም እንዲኖረው ተፅዕኖ በማሳረፍ ዒላማው ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ለማድረግ የሚታቀድ ስትራቴጂ ነው፡፡
የወገንን ሞራል ለመጠበቅ ሲባል አንድን
ክስተት ወደምትፈልገው ነገር ማስተካከል (Framing)፤ ጠላት ዝርዝር ነገሮችን ደብቆ የተመረጡ መረጃዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ማድረግ (Selective Exposure)፤ ቁልፍ መልዕክቶችን መደጋገም (repetition)፤ እርስ በእርስ የሚቃረን መረጃዎችን ማቅረብ (Contradictory Information) የመሳሰሉት ታክቲኮች በዚህ ስትራቴጂ ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡
የጠጠረ ድንቁርና ያለባቸው ግለሰቦች ደግሞ ለዚህ ጥቃት የተመቹ ናቸው። በፋኖ ተጋድሎ ውስጥ የጠላት የደህንነት ተቋማት በከፊል ማሳካት ከቻሉት የጥቃት ስልት መካከል አንደኛው ይህ ዘርፍ ነዉ።
የስነ ልቦና ጦርነት ጥቃትን ለመከላከል ስሜታዊነትን እና ግብታዊነትን በማስወገድ በሰከነ እና በተጠና መንገድ ጥቃትን ለመቋቋም የሚያስችል የተቀናጀ እና የተደራጀ ስራ ይጠይቃል።
የስነ ልቦና ጦርነት እያንዳንዱ ግለሰብ ሊዋጋው የሚችል በመሆኑ ምንነቱን፣ መተላለፊያ መንገዶቹን፣ ባህሪውን፣ ጉዳቱን እና የምከታ ዘዴውን በተመለከተ አልፎ አልፎ መጣጥፎችን የማጋራ ይሆናል።
አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ
የጠላት አንድ ሬጅመንት ኃይል ሙሉ ለሙሉ ተደመሰሰ‼️
የምኒልክ ዕዝ አሃዶች አንድ ሻለቃ የጠላት ሃይል የተደመሰሰበትና በርካታ እግረኛ ሰራዊት እንዲሁም ሞርተር የቡድንና በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ የተማረከበትን ድል ተጎናፀፉ::
ምኒልክ ዕዝ 104ኛ ኮር እና 101ኛ ኮር በቅንጅት የስርዐቱን ወንበር ጠባቂ ሰራዊት በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ በ011 ቀበሌ ልዩ ቦታው ዳቃና ድብል በተባለ ስፍራ የጠላትን አንድ ሻለቃ ሀይል ሙሉ ለሙሉ በመደምሰስ ታላቅ ድል ተቀዳጂተዋል።
የአገዛዙን ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ልዩ ቦታው ዳቃና ድብሌ እየተባለ በሚጠራ ስፍራ ዛሬ ግንቦት 01/2018 ዓ.ም ከ101ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦርና ከ104ኛ ኮር 24 ክፍለጦር እና 23ኛ ክፍለ ጦር የጠላትን ሰራዊት በማቁስል ፡በመደምሰስ እና የቡድን እና ነፍሰ ወከፍ መሳሪያዎችን በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል።
በዚህ አውደ ውጊያ ከተማረኩት የቡድን መሳሪያዎች መካከል
👉አንድ ሞርተር ከእነ ተተኳሹ
👉2 ብሬን
👉አንድ ስናይር እንድሁም፣ አንድ መኪና ሙሉ የጠላትን ሬሸን የተማረከ ሲሆን ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ክላሸ እንኮፍ ገቢ ማድረግ ተችሏል። አውደ ውጊያውም በአሁኑ ስዐት እንደቀጠለ ስለሆነ ፣የተደመሰሰውን ሀይል በቁጥር፣የተማረከውን ክላሸ እንኮፍ እንዲሁም ተጨማሪ የቡድን መሣሪያ ከየክፍለጦሮቹ መረጃውን በቪዲዮ ይዘን ዝርዝሩን እንመለስበታለን።
©ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
