ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 134
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+4247 أيام
+1 14930 أيام
أرشيف المشاركات
የሀይማኖት ክሀድያን ሀይማኖቱ እንዳይቀጥል አያደርጉትም‼️
የሀይማኖት ክሀድያን የነበሩበትን የሀይማኖት ተቋም ከህደው በመውጣት የወጡበትን ሀይማኖት ተቋም ስም በመጥራት ፣የተቀደሠውን ቃልና ቦታ ማንቆሸሽና ማራከስ እንደክብርና እንደጽድቅ ይቆጡሩታል።
ክሀድያኑ የወጡበትን ሀይማኖት እንዳይመለክ፣እንዲጠፋ አላደረጉትም፣ ሁሉም የሀይማኖቱ ተከታዮች ተሠልፈው እነሡ ወደገቡበት ሀይማኖት እንዲገቡም አላደረጉትም፣ይልቁንም የሀይማኖት ተከታዮች እንዲበረቱና ሀይማኖታቸውም ደግሞ የበለጠ እንዲጠነክር ያደርጉታል።
የፋኖን ተቋም ክደው የሚወጡ ክሀዲ ባንዳዎችም ፣ቁልጭ ያለ መነሻና መዳረሻ ያለውን የአማራን የህልውና ትግል ክደው በመውጣት፣ውድ የአማራ ልጆች የረገፉበትን የህልውና ተጋድሎ ቆሻሻ ስም በመቀባትና በማራከስ አንድ ጋት ወደኋላ አይመልሱትም።
ይልቁንም የበለጠ እንዲጠነክርና እንዲበረታ ያደርጉታል እንጂ። ፋኖነት አሸናፊነት ነው።ፋኖነት የተበርካኪነትና እጂን ዘርግቶ መሳሪያ ለጠላቶቹ የሚሠጥ ሳይሆን የመጨረሻዋን አንድ ጥይት ወደራሱ የሚተኩስ የጀግንነትና የአርበኝነት ጥግ ነው።
ክብር ለአማራነታቸው ሲሉ ስቀው ለተሠው ሰማዕታት‼️
ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር መርሳ ከተማ አቅራቢያ የአገዛዙ ሰራዊት ላይ የአር ፒ ጂ ጥቃት በመፈፀም ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚሊኒክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት አደረሰ።
ዛሬ ጥር 14/2018 ዓ.ም ከጧቱ 12:00 ላይ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ መርሳ ከተማ አቅራቢያ ሊብሶ ኤላ እየተባለ በሚጠራ ቦታ ላይ የስርዓቱን ወንበር ጠባቂ ሰራዊት በአንድ ተሳቢ፣አንድ ሲኖትራክ እና አንድ ፖትሮ ከመርሳ ወደ ደሴ ሲጓጓዝ በባለሽርጡ ክፍለጦር ቃኝ በተያዘ ደፈጣ ሙሉ ለሙሉ በመደምሰስና በማውደም ታላቅ ድል ተጎናፀፈዋል።
በዚህ 100% ኢላማውን በጠበቀ የአርፒጅ /RPG/ ጥቃት ከመርሳ ወደ ደሴ በአንድ ተሳቢ ፣በሲኖ ትራክ እና በአንድ ፖትሮል ተጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ጨፍጫፊ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ከነ ተሽከርካሪው ማውደምና መደምሰስ ሲቻል፣ ስርዐቱ ሙትና ቁስለኛውን በአስር አንቡላንስ ወደ መርሳ ሆስፒታል ሲያመላልስ አርፍዷል። በዚህ አውደ ውጊያ ከተደመሰሱት የስርዓቱ ሀይሎች መካከል ለጊዜዉ ስማቸዉ ያልታወቀ ከፍተኛ አመራሮችም ይገኙበታል።
በፋኖ ምት የተበሳጨዉ የጠላት ብልፅግና ሰራዊት ንፁሃን ወገኖቻችን ኢላማ በማድረግ የአርሶ አደሮችን ህይወት ሲቀጥፍና በመንገድ እያስቆመ በመደብደብና ንብረትም ሲያወድም ውሏል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚሊኒክ ዕዝ
ጥር 14/2018 ዓ.ም
#የጠላት_እንቅስቃሴ‼️
ብዛት ያለው የአድማ ብተና እና መከላከያ ጥምር ኃይል ከቀኑ 7:00 አካባቢ ከባህርዳር ከተማ ወደ ጎንደር መውጫ በር እየተጓዘ ነው መረጃው ለወገን ሀይል ይድረስ‼️
14/ዐ5/2018 ዓ.ም
+3
የወለጋ ክፍለ ሀገር ፋኖ እዝ (ቢዛሞ) የድርጅቱ መዋቅር አካል የሚሆኑበትን ሁኔታ ላይ ውሳኔ ተላልፏል። እዙ በድርጅቱ ውስጥ የጠቅላላ ጉባኤ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የስራ አስፈፃሚ እንዲሁም ሌሎች መዋቅሮች ውስጥ ተመጣጣኝ እና አስፈላጊ ውክልና እንዲኖረው ወስኗል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ ዞን የምንገኝ የአማራ ብሔር ተወላጆች፣ብሔርን መሰረት ያደረገ ግፍ እና በደል እየደረሰብን እና እየተፈፀብን እንገኛለን።አማራ ብሔር በመሆናችን ብቻ ፍትህ የማገኘት መብታችን እንደተጠማን ቆየን።የአማራ ብሄር በመሆናችን ብቻ ከመንግስት መስራያ ቤቶች የማፈናቀል ስራ ተሰርቶብናል።የአካባቢ ብሄር ተወላጅ ሹማምንቶች የአማር ብሄር ቢሮ እንዳይሰራ በማስወጉድ የተማረውን አማራ በአደባባይ እያባረሩት ይገኛሉ።እነዚህ የአካባቢ ተሻሚዎች አላማቸው የተማረውን የአማራ ብሔር በውስጥ የማጥፋት ዘመቻ ይዘው እየሰሩት ይገኛል ፣የሶሻል ሚዲያ ሽፋን እንድትሰጥልን እንጠይቃለን ፣
#የጥንቃቄ_መልዕክት‼️
አሁን ከጥዋቱ ጀምሮ በመላው ሽዋ ደብር በርሃን ዙራያ በቀጠናና አካባቢው በስፋት የድሮን ቅኝት እየተደረገ ስለሆነ ጥንቃቄ አይለየን‼️
ጥር 14/ዐ5/2018 ዓ.ም
በአምስቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች ከግንባር ሁነን እየሰራን 24 ስዓት እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
''በአማራ ክልል በተፈጸሙ ከ70 በላይ የድሮን ጥቃቶች ቢያንስ 669 ሰዎች መገደላቸውተሰማ!'' የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት
የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል ቁጥራቸው 40 የሚደርስ የራሳቸው ወገን የሆኑ ሚሊሽያዎችን በድሮን ጥቃት መግደላቸውን አንድ ነርስ እና አንድ የአካባቢውን ባለሥልጣን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ።
በየጊዜው በክልሉ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት እንደሚፈጽም የሚነገርለት ጦሩ፣ ባለፈው ጥር 15 ቀን 2018 ዓም በዋግህምራ አካባቢ በተፈፀመው ጥቃት የመንግስት ደጋፊዎች የሚገኙበትን ካምፕ መትቷል ሲሉ ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የአካባቢው ባለስልጣን ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት በስልክ ተናግረዋል።
ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት ምንም እንኳን ድሮኑ በካምፑ ላይ ቢያንዣብብም ጦሩ በማግስቱ የተፈጸመው ጥቃት "ስህተት" መሆኑን ለአካባቢው ባለሥልጣናት እንደገለጸ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት ኃላፊ ጨምረው ገልጸዋል።
"ወዲያውኑ ጭስ እና እሳት አየሁ ፤ ወደ ስፍራውም ሮጬ ሄድኩ፤ የሞቱ ሰዎች አካላት እንዲሁም የቆሰሉ ሰዎች በህምመ ሲሰቃዩ ተመለከትኩ" በማለት ባለሥልጣኑ አስረድተዋል። ባለሥልጣኑ 36 ሰዎች ወዲያውኑ መገደላቸውን እንዲሁም ሁለት ተጨማሪ ሰዎችም ሆስፒታል ውስጥ መሞታቸውንም ተናግረዋል።
አበባው ዝናቡ የተባሉ የሕክምና ባለሞያ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር "ከ40 በላይ" እንደሆነ መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ባለሥልጣኑ"ላለፉት ስድስት ዓመታት መንግስትን ከጥቃት ለመከላከል ከቤተሰቦቻቸው እና ከሚወዷቸው ርቀው በበረሃና በዱር ሸንተረሩ ሲዋጉ የቆዩ የሚሊሽያ አባላት መኖሪያ መሆኑ የሚታወቅ ካምፕ በኛ ኃይሎች እንዴት ጥቃት ደርስበት?" ሲሉ ይጠይቃሉ።
አንድ የጦሩ ቃል አቀባይ ስለደረሰው ጥቃት ምንም መረጃ እንዳልደረሳቸው ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። በአማራ ክልል የመንግሥት የፀጥታ አስከባሪዎች እና የፋኖ ታጣቂዎች ከሚያዚያ 2015 ዓ.ም. አንስቶ ውጊያ ውስጥ ቆይተዋል።
በዓለም ዙሪያ የሚካሔዱ ግጭቶችን የሚመዘግበው አክሌድ (ACLED) የተሰኘ ገለልተኛ ተቋም ከጎርጎሮሳዊው 2023 ዓ.ም አንስቶ በአማራ ክልል በተፈጸሙ ከ70 በላይ የድሮን ጥቃቶች ቢያንስ 669 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል።
የፋኖን አንድነት በጉጉት ሲጠብቁ የነበሩት የአገዛዙ ወታደሮችም ጭምር ናቸው።
ፋኖ አንድ ወጥ ድርጅት መስርቶ አንድነቱን ባወጀ ማግስት የአገዛዙ ጦር በገፍ እየተናደ ፋኖን እየተቀላቀለ መሆኑ ታውቋል።
የፋኖን አንድ መሆን በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው በመከራ ውስጥ የሚገኘው የአማራ ሕዝብና ሌሎች የዚህ ፀረ ሕዝብ ኦህዴድ መር ብልፅግና አገዛዝ ተጠቂ የሆኑ ብሔር ብሔረሰቦች ብቻ ሳይሆኑ አገዛዙን እያገለገሉ የሚገኙ ወታደሮችና ወታደራዊ አዛዦችም ጭምር ናቸው።
የአገዛዙ ወታደሮች በጉጉትና በተስፋ ሲጠብቁት የነበረው የፋኖ አንድነት የብስራት ዜና መሰማቱን ተከትሎ፡ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ከስምሪት ቀጠናቸው በመጥፋት በገፍ ፋኖን እየተቀላቀሉ መሆኑን ፍኖተ አማራ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
ሙሉ ዘገባውን አድምጡት👉h
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የፖሊት ቢሮ ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛው ድርጅታዊ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳወች ላይ ውይይት አድርጎ ውሳኔወችን አሳልፏል። በዚህም መሠረት:-
፩) የድርጅቱ ስራ አመራር አባላት በተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ፖሊት ቢሮው አርበኛ እስክንድር ነጋ ያቀረበውን ማመልከቻ መርምሯል። በዚህም አርበኛ እስክንድር በግለሰባዊ ችግር ምክንያት ድርጅቱ በመደበበት የኃላፊነት ቦታ ላይ መቀጠል እንደማይችል ይልቁንም በድርጅት አባልነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመቀጠል ዝግጁ መሆኑን እና የሚጠበቅበትን ሀላፊነቶችና ግዴታዎች በሙሉ እንደሚፈፅም ጠቅሶ ያቀረበው ጥያቄ በነፃ ፈቃዱ እና ፍላጎቱ የቀረበ መሆኑን ፖሊት ቢሮው አረጋግጧል።
ሆኖም ግን ማመልከቻው ለፖሊት ቢሮው በደረሰበት ቅፅበት ለሚዲያ የወጣበት መንገድ የድርጅቱን አሰራር የሚጥስ እና ያልተገባ ትኩረት ለማግኘት የተደረገ መሆኑን ፖሊት ቢሮው ገምግሟል። ግለሰቡም ማመልከቻው ከአሰራር ውጭ በሚዲያ በኩል ይፋ መደረጉ ስህተት መሆኑን ላነጋገሩት የፖሊት ቢሮ አባላት አሳውቋል። እንዲሁም የድርጅታችን ምስረታ ይፋ በሆነ ማግስት እጅግ አንገብጋቢ ጉዳዮች እያሉ ይህ ጥያቄ መቅረቡ ግዜውን የጠበቀ አለመሆኑን አምኖበት በቃል ይቅርታ ጠይቋል።
በመሆኑም አሳማኝ ምክንያቶች ካሉም እንኳን ትክክለኛውን ጊዜ መጠበቅ ሲገባው ከሌሎች አስቸኳይ የህልውና አጀንዳ በላይ ይህ ጉዳይ የድርጅቱ የመጀመሪያ አጀንዳ ሆኖ መቅረቡ ፖሊት ቢሮውን ያሳዘነው ቢሆንም ግለሰቡ በአባልነት ብቻ ለመቀጠል ያቀረበውን ማመልከቻ ፖሊት ቢሮው ተቀብሎታል። ፖሊት ቢሮዉ ለአርበኛ እስክንድር ተሰጥቶ በነበረው የኃላፊነት ቦታ ላይ ሌላ ሰው የሚተካ ይሆናል።
፪) የወለጋ ክፍለ ሀገር ፋኖ እዝ (ቢዛሞ) የድርጅቱ መዋቅር አካል የሚሆኑበትን ሁኔታ ላይ ውሳኔ ተላልፏል። እዙ በድርጅቱ ውስጥ የጠቅላላ ጉባኤ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የስራ አስፈፃሚ እንዲሁም ሌሎች መዋቅሮች ውስጥ ተመጣጣኝ እና አስፈላጊ ውክልና እንዲኖረው ወስኗል።
፫) በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ በተጠቀሰው መሠረት የአባት አርበኞች ምክር ቤት መዋቅር እንዲቋቋም ውሳኔ ተላልፏል። ዝርዝር ጉዳዩን በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
+2
ለአንድ ግለሰብ ስልጣን ሲል ታዳጊው ህይወቱን ገበረ
ይህ የምትመለከቱት ሩጦ ያልጠገበ ታዳጊ ልጅ ለአብይ አህመድ ስልጣን ሲል ህይወቱን ገብሯል። ለወደፊቱ በተለይ ደቡብ ወንድ ልጅ ብርቅ የሚሆንበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል። በውድም በግድም እየታፈሱ ታዲጊዎች ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ይጋዛሉ። ለብለብ ስልጠና ይሰጣቸውና ወደ ጦር ሜዳ ይላካሉ። ታዳጊዎች ናቸው እና ጦርነት ሲጀመር ይደናበራሉ። ከዚያ ይገደላሉ።
አሁን አንድነት ተመሰርቷል የቀደሞው አጋዚዎች ብኋላም የአማራ ልዩ ሃይል ኮማንዶ ዩኒቶች አሁን ለመቀላቀል ምክንያት አያስፈገውም ኑ ተቀላቀሉ።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን ) ለሃገራዊ ፀረ ብልፅግና ኃይሎች ላቀረበው ጥሪ የጋምቤላ ታጣቂ ኃይሎች ጥምረት ጥያቄውን ተቀብሎ አብሮ እንደሚሠራ አሳውቋል።
ይሄ ታጣቂ ኃይል ጋምቤላ ክልል ከማጃንግ እና ጋምቤላ ከተማ ውጭ ያሉ 3 ዞኖችን ተቆጣጥሮ የሚገኝ ኃይል ነው።
በመላው ሐገሪቱ የሚገኙ አካባቢዎች እና ህዝቦች ፀረ ብልፅግና ትግል ለማድረግ ለጀግናው የአማራ ፋኖ ጥያቄ እያቀረቡ ሲሆን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን ) ጥያቄያቸውን ተቀብሎ አብሮ ለመስራት ተዘጋጅቷል ።
አዲሱ ትውልድ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ፀረ አማራ የሆኑ የትርክት ፣ የሐይል ፣ የፖለቲካ አቋሞችን በመቀየር ሁሉም ሐይሎች ፣ ሁሉም የፖለቲካ ትግሎች ፣ ሁሉም ትርክቶች ፀረ ብልፅግና እንዲሆኑ አድርጓል ።
ገና የደረሰብንን ውድመት በበቂ ሳናስረዳ ፣ ገና ያለንን ሰፊ መልካአምድር ሳንጠቀም ፣ ገና ያለንን የተፈጥሮ ሐብት ለትግሉ ማዋል ሳንጀምር ፣ ገና ሚሊዮን ወጣቶችን ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ሳናስታጥቃቸው ፣ ገና ዕውቀታችንን እና ጥበባችንን ፍልስፍናችንን ከተፈጥሯዊ ጀግንነታችን ጋር ሳናጣምራቸው ጠላቶቻችን የቆሙባቸውን የህልውና ምሰሶዎች አፍርሰን ፣ የገነቡትን ሁለንተናዊ ፀረ - አማራነት ደርምሰን ለድል እየበቃን ነው ።
ማሳሰቢያ :- ትግሉ አብይን ከመጣል ባሻገር ረጅም የትውልድ ቅብብሎሽ በአዳዲስ ተለዋጭ ስልቶች እየተመራ እስከ ዓለም ፍፃሜ ይቀጥላል ።
የአማራነት ቃል-ኪዳን እና የነፃነት ጉዞ እኔ ስወለድ አማራ ነኝ፤ ያለ ማንነቴ ሌላ ስም አልነበረኝም።
ታሪኬ የሚጀምረው ከጥንት የነገሥታት እና የጀግኖች መንደር ነው። ማንነቴን በታሪኬ፣ ታሪኬን በደሜ ውስጥ አትሜው ተወለድኩ። ሳድግም አማራ ነኝ፤
በክብር የመኖርን ትርጉም፣ ለሀገር መሞትን እና ለሰው ልጆች መራራትን እየተማርኩ አደግሁ።
አማራነት ለእኔ ስም ብቻ ሳይሆን፣ ፈተናዎችን በጽናት የማለፍ እና ለማንም ላለመንበርከክ ራስን የማዘጋጀት የህይወት ትምህርት ቤት ሆኖኝ አደገ።
ዛሬ ግን...የ30 ዓመት የጎልማሳነት እድሜ ላይ የደረስኩ፣ የማንነቴን ዋጋ በሚገባ የተረዳሁ የቁርጥ ቀን ልጅ ነኝ። ዛሬ የአማራነት ኩራቴ በተግባር የሚገለጥበት ወቅት ላይ እገኛለሁ።
እኔ የአማራ ፋኖ ነፃ አውጭ ልጅ ነኝ! ለክብሩ የማይደራደር፣ ለፍትህ የሚቆም እና የታሪካዊ ጠላቶቹን ሴራ የሚያከሽፍ የትውልድ አደራ ተሸካሚ ነኝ። የፋኖነት መንፈስ በደሜ ውስጥ ይፈሳል፤ ነፃነቴን በልመና ሳይሆን በጥንካሬዬ የማስከብር፣ የነገዋን ብሩህ አማራ የምገነባ የቁርጥ ቀን ተዋጊ ነኝ።
አማራነት የማይታጠፍ ማንነት፣ ፋኖነት ደግሞ የማይበገረ ነፃነት ነው!" Dawit fano
በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአማራነት ቃል-ኪዳን እና የነፃነት ጉዞ እኔ ስወለድ አማራ ነኝ፤ ያለ ማንነቴ ሌላ ስም አልነበረኝም።
ታሪኬ የሚጀምረው ከጥንት የነገሥታት እና የጀግኖች መንደር ነው። ማንነቴን በታሪኬ፣ ታሪኬን በደሜ ውስጥ አትሜው ተወለድኩ። ሳድግም አማራ ነኝ፤
በክብር የመኖርን ትርጉም፣ ለሀገር መሞትን እና ለሰው ልጆች መራራትን እየተማርኩ አደግሁ።
አማራነት ለእኔ ስም ብቻ ሳይሆን፣ ፈተናዎችን በጽናት የማለፍ እና ለማንም ላለመንበርከክ ራስን የማዘጋጀት የህይወት ትምህርት ቤት ሆኖኝ አደገ።
ዛሬ ግን...የ30 ዓመት የጎልማሳነት እድሜ ላይ የደረስኩ፣ የማንነቴን ዋጋ በሚገባ የተረዳሁ የቁርጥ ቀን ልጅ ነኝ። ዛሬ የአማራነት ኩራቴ በተግባር የሚገለጥበት ወቅት ላይ እገኛለሁ።
እኔ የአማራ ፋኖ ነፃ አውጭ ልጅ ነኝ! ለክብሩ የማይደራደር፣ ለፍትህ የሚቆም እና የታሪካዊ ጠላቶቹን ሴራ የሚያከሽፍ የትውልድ አደራ ተሸካሚ ነኝ። የፋኖነት መንፈስ በደሜ ውስጥ ይፈሳል፤ ነፃነቴን በልመና ሳይሆን በጥንካሬዬ የማስከብር፣ የነገዋን ብሩህ አማራ የምገነባ የቁርጥ ቀን ተዋጊ ነኝ።
አማራነት የማይታጠፍ ማንነት፣ ፋኖነት ደግሞ የማይበገረ ነፃነት ነው!"
በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአማራነት ቃል-ኪዳን እና የነፃነት ጉዞ እኔ ስወለድ አማራ ነኝ፤ ያለ ማንነቴ ሌላ ስም አልነበረኝም።
ታሪኬ የሚጀምረው ከጥንት የነገሥታት እና የጀግኖች መንደር ነው። ማንነቴን በታሪኬ፣ ታሪኬን በደሜ ውስጥ አትሜው ተወለድኩ። ሳድግም አማራ ነኝ፤
በክብር የመኖርን ትርጉም፣ ለሀገር መሞትን እና ለሰው ልጆች መራራትን እየተማርኩ አደግሁ።
አማራነት ለእኔ ስም ብቻ ሳይሆን፣ ፈተናዎችን በጽናት የማለፍ እና ለማንም ላለመንበርከክ ራስን የማዘጋጀት የህይወት ትምህርት ቤት ሆኖኝ አደገ።
ዛሬ ግን...የ30 ዓመት የጎልማሳነት እድሜ ላይ የደረስኩ፣ የማንነቴን ዋጋ በሚገባ የተረዳሁ የቁርጥ ቀን ልጅ ነኝ። ዛሬ የአማራነት ኩራቴ በተግባር የሚገለጥበት ወቅት ላይ እገኛለሁ።
እኔ የአማራ ፋኖ ነፃ አውጭ ልጅ ነኝ! ለክብሩ የማይደራደር፣ ለፍትህ የሚቆም እና የታሪካዊ ጠላቶቹን ሴራ የሚያከሽፍ የትውልድ አደራ ተሸካሚ ነኝ። የፋኖነት መንፈስ በደሜ ውስጥ ይፈሳል፤ ነፃነቴን በልመና ሳይሆን በጥንካሬዬ የማስከብር፣ የነገዋን ብሩህ አማራ የምገነባ የቁርጥ ቀን ተዋጊ ነኝ።
አማራነት የማይታጠፍ ማንነት፣ ፋኖነት ደግሞ የማይበገረ ነፃነት ነው!"
በደብረ ማርቆስ ከተማ የመሸገው የመከላከያ እና አድማ ብተና ኃይል እየተታኮሰ ይገኛል ከሁለቱም ቡድን አመራሮች የተገደሉ ሲሆን በከተማዋ ዙሪያ የእርስበርስ ውጊያው ተጧጡፏል።
©ባዬ ደስታ የ206ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
ከአርበኛ እስቲበል ዓለሙ
የውክልና ጦርነት እየተካሄደ ያለው በቤተ-መንግሥት ውስጥ ነው።
በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማያውቅ መልኩ የሀገር ዳር ድንበር የተደፈረበት፣ ሉዓላዊነት ለባዕዳን የተሸጠበት እና ዲፕሎማሲያችን ለውርደት የተዳረገበት ዘመን ቢኖር የብልጽግና አገዛዝ ዘመን ነው። ዜጎች ፍትሕን፣ እኩልነትን እና የሕግ የበላይነትን በሰላማዊ መንገድ ስለጠየቁ ብቻ በገዛ አገራቸው እንደ ባዕድ ተቆጥረዋል። አገዛዙ ሰላማዊ የትግል በሮችን በመዝጋት ወጣቱ ትውልድ ራሱን ለመከላከል ወደ ትጥቅ ትግል እንዲገባ አስገድዶታል።
አሁንም የራሱን ውድቀት ለመሸፈን ፋኖን "የባዕዳን ተላላኪ" በሚል የሐሰት ታፔላ ለመለጠፍ ይሞክራል። አገዛዙ ፋኖንና የፍትሕ ታጋዮችን "ሀገር አፍራሽ" በማለት ቢከስም፣ በተግባር ግን እውነተኛው "ባንዳ" እና "ባዳ" ራሱ አገዛዙ መሆኑን በተደጋጋሚ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታው በማታውቀው የሞራል እና የፖለቲካ ውድቀት ውስጥ ትገኛለች። እውነተኛው "ባንዳ" እና "ባዳ" ራሱ አገዛዙ መሆኑን የሚከተሉት ሀቆች ያረጋግጣሉ።
የግድቡ ምስጢራዊ ሽያጭና የዲፕሎማሲ ውድቀት ፤ አገዛዙ በአደባባይ "ግድቡን አስጨረስኩ" እያለ ቢፎክርም፣ ከጀርባ ግን የሀገሪቱን የዘመናት ተስፋ ለግብፅና ለአሜሪካ ተጽዕኖ አሳልፎ በመስጠት፤ በካይሮ የተደረገው የ"ወላሂ..ወላሂ" መሐላ እና በአሜሪካ አደራዳሪነት የግድቡን የኃይል ማመንጨት አቅም እንዲቀንስ መስማማቱ፣ አገዛዙ ለባዕዳን ፍላጎት ተንበርካኪ መሆኑን በግልጽ አረጋግጧል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ግብፅ ግድቡን ልታፈነዳው ትችላለች" ብለው ሲዝቱና ለግብጽ በወገን መንገድ እናሸማግላችሁ የሚል ደብዳቤ የጻፉት፣ አገዛዙ የሀገርን ክብር የሚያስጠብቅ ዲፕሎማሲያዊ ውድቀት ላይ መሆኑን የታየበት አጋጣሚ ነው።
የሀገርን የዳር ድንበር መደፈርና የአገዛዙ ዝምታ፤ በዚህ አገዛዝ ዘመን የሱዳን ጦር መሬታችንን በመውረር ዜጎቻችንን ሲያፈናቅል፣ አገዛዙ የሀገርን ድንበር ከማስከበር ይልቅ ዝምታን መርጧል። የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው ንጹሐንን ሲገድሉና ልጆችን አፍነው ሲወስዱ፣ እንዲሁም አልሻባብ ወደ መሃል ሀገር ዘልቆ ሽብር ሲነዛ አገዛዙ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ አቅም እንደሌለው ታይቷል። ለሳዑዲ አረቢያ ፍላጎት ሲባል ለሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) ወታደራዊ ማሰልጠኛ ቦታ በመስጠት፣ ኢትዮጵያን የባዕዳን የጦር አውድማ አድርጓታል።
አገዛዙ፤ የውስጥ ጭፍጨፋ እና የባንዳነት ተግባር፤ አገዛዙ የገዛ ህዝቡን በድሮንና በከባድ መሳሪያ እየጨፈጨፈ፣ የሀገርን ሉዓላዊነት የሚጋፉ የውጭ ኃይሎች ሲመጡ ግን የሚንበረከክ "ባዳ" ነው። የሀገርን መከላከያ ሰራዊት በስልት በማስመታት እና ዳር ድንበርን ክፍት በማድረግ ሉዓላዊነታችንን ለውጭ ኃይሎች አሳልፎ መስጠቱ የማይረሳ ታሪካዊ ክህደት ነው።
አገዛዙ የሀገርን መሬት ለባዕዳን እየገበረ፣ ለግብፅ መሪዎች እየማለና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በምስጢር እየሸጠ "ሀገር ጠባቂ ነኝ" ሊለን አይችልም። እውነተኛው የሀገር ስጋት፣ እውነተኛው ባንዳና ባዳ የገዛ ህዝቡን እየገደለ የሀገርን ጥቅም ለባዳን አሳልፎ የሚሰጠው የብልጽግና አገዛዝ ራሱ ነው። የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የሚከበረው ይህ የክህደት ሰንሰለት ሲበጠስ ብቻ ነው።
ሰላማዊ ጥያቄን በስላቅ የመለሰው አገዛዝ፤
የኢትዮጵያ ወጣቶች "የሕግ የበላይነት ይከበር፣ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ይቁም" ብለው ሲጮሁ፣ አገዛዙ "ይኽ የሥልጣን ፍለጋ ጩኽት ነው" በሚል ንቀትና ስላቅ ምላሽ ሰጥቷል። ሰላማዊ ሰልፈኞችን በጥይት በመደብደብ እና እስር ቤቶችን በንጹሐን በመሙላት ወጣቱ ዱር ቤቴ እንዲል ያስገደደው ይኽው ኦሕዴድ መራሹ የብልጽግና አገዛዙ ነው። አሁንም "ተላላኪ" የሚለው ስም ማጥፋት የደረሰበትን ሕዝባዊ ማዕበል ለመቀልበስ የሚጠቀምበት የከሰረ ፖለቲካ ነው።
ሕዝባችን እንደሚያውቀው የታሪካዊ ጠላቶች እውነተኛ ተላላኪ ራሱ አገዛዙ ነው። አገዛዙ ፋኖን በግብፅ፣ በሻቢያ እና በምዕራባውያን ተላላኪነት ሲከስ፣ እጆቹ ግን በታሪካዊ ክህደት የቆሸሹ ናቸው። ከግብፅ ጋርም በካይሮ መድረክ "ወላሂ፣ ወላሂ" ብሎ በመማል የሀገርን የልማት ሉዓላዊነት ለግብፅ ፍላጎት ያስገዛው ራሱ አገዛዙ ነው።
በድብቅ የግድቡን የኃይል ማመንጨት አቅም በመቀነስ የብሔራዊ ጥቅማችንን ሰንሰለት ለጠላት አሳልፎ የሰጠው ኦሕዴድ ብልጽግና ነው። የሀገርን መከላከያ ለባዕዳን ሰራዊት ክፍት በማድረግ፣ የሀገርን ሉዓላዊነት ለባዕዳን ያስረገጠውና ዜጎቻችን ለባዳ በደል እንዲጋለጡ ያደረገው ይኸው የብልጽግና አገዛዝ ነው።
የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለባዕዳን አሳልፎ የሰጠ አገዛዝ፤ የብልጽግና አገዛዝ የIMF እና የዓለም ባንክን (World Bank) አውዳሚ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ምክረ-ሐሳቦችን ያለምንም ጥንቃቄ በመቀበል፣ የሀገሪቱን የገንዘብ አቅም አዳክሞ የኑሮ ውድነትን በሕዝቡ ላይ ጭኗል። ይህ የሀገርን የኢኮኖሚ ቁልፍ ለውጭ ኃይሎች በእጅ አዙር አሳልፎ የመስጠት ተግባር፣ አገዛዙ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይሆን ለውጭ አበዳሪዎች የሚገዛ መሆኑን ያረጋግጣል።
የሀገር አንድነትን የናቀና የወደብ ቁማርተኛ፤ የመገንጠል ትረካ "ትግራይ ከፈለገች ትገንጠል" በሚል የቸልተኝነት ንግግር የሀገርን ህልውና እና የግዛት አንድነት ለድርድር የሚያቀርብ፣ ለኢትዮጵያ አንድነት ደንታ የሌለው ስብስብ ነው።
የወደብ ማታለያ፤ "እንኳን ደስ ያለን የወደብ ባለቤት ሆነናል" በሚል የውሸት ፕሮፖጋንዳ ሕዝብን በአየር ላይ ሲያደናግር ቆይቶ፣ ውጤቱ ዜሮ ሲሆን ደግሞ ዳግም "ቀይ ባሕርን አስመልሳለሁ" በሚል አዲስ የቀውስ አጀንዳ ሕዝብን እያደናገረ ይገኛል። ይህ ለሥልጣን ማራዘሚያ የሚደረግ የታሪክ ቁማር የሀገርን ዲፕሎማሲ ለውርደት ዳርጓል።
የመንግሥታን መዋቅር የስርቆትና የሙስና መፈልፈያ በማድረግ፤ ሀገሪቱ በረሃብና በጦርነት እየታመሰች፣ የአገዛዙ ባለሥልጣናት በመንግሥታዊ ስርቆትና በሙስና ሕዝብን እየበዘበዙ ነው። የሀገር ብሔራዊ ጥቅም እየተሸረሸረ ያለው በፋኖ ትግል ሳይሆን፣ በአገዛዙ የሌብነት ሰንሰለትና በባዳን ተላላኪነት ነው። በመንግሥታዊ ስርቆትና በሙስና ሕዝብን እየበዘበዙ ነው። ፋኖን "የውክልና ጦርነት ያካሂዳል" የሚለው ስም ማጥፋት፣ አገዛዙ የገዛ ሕዝቡን እየጨፈጨፈ ሥልጣኑን ለማራዘም የሚጠቀምበት የፈሪ ስልት ነው።
ሕዝባችን እንደሚያውቀው ፋኖ የኢትዮጵያዊነት ጽኑ መሠረት ነው፤ ፋኖ ከየትኛውም የውጭ ኃይል ትጥቅም ሆነ ትእዛዝ አይቀበልም። የፋኖ ትጥቅ በደል የመረረው ሕዝብ ነው፤ ስንቁ ደግሞ እውነትና ፍትሕ ነው። አገዛዙ የውጭ ኃይሎችን ስም እየጠራ የሚጮኸው፣ የራሱን የባንዳነት ታሪክ ለመሸሸግ እና ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማግኘት የሚጠቀምበት የፈሪ ስልት ነው።
እውነተኛው የውክልና ጦርነት እየተካሄደ ያለው በቤተ-መንግሥት ውስጥ ነው። ኦሕዴድ መራሹ የብልጽግና አገዛዝ ለሥልጣኑ ሲል ሀገርን ለባዕዳን እየገበረ፣ የገዛ ሕዝቡን እየጨፈጨፈ ያለ የጥፋት ኃይል ነው። ፋኖ ግን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር፣ ሉዓላዊነትና የሕዝብን ነፃነት ለማስከበር የተነሳ እውነተኛ ሕዝባዊ ኃይል ነው።አገዛዙ ለሥልጣኑ ሲል ሀገርን ቢሸጥም፣ ፋኖ ግን ሕዝቡን ለማዳን እስከመጨረሻው ይቆማል!
ትግላችን እስከ ነፃነት ይቀጥላል!
አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
