ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 134
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+4247 أيام
+1 14930 أيام
أرشيف المشاركات
አሁን አንድነት ተመሰርቷል የቀደሞው አጋዚዎች ብኋላም የአማራ ልዩ ሃይል ኮማንዶ ዩኒቶች አሁን ለመቀላቀል ምክንያት አያስፈገውም ኑ ተቀላቀሉ።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን ) ለሃገራዊ ፀረ ብልፅግና ኃይሎች ላቀረበው ጥሪ የጋምቤላ ታጣቂ ኃይሎች ጥምረት ጥያቄውን ተቀብሎ አብሮ እንደሚሠራ አሳውቋል።
ይሄ ታጣቂ ኃይል ጋምቤላ ክልል ከማጃንግ እና ጋምቤላ ከተማ ውጭ ያሉ 3 ዞኖችን ተቆጣጥሮ የሚገኝ ኃይል ነው።
በመላው ሐገሪቱ የሚገኙ አካባቢዎች እና ህዝቦች ፀረ ብልፅግና ትግል ለማድረግ ለጀግናው የአማራ ፋኖ ጥያቄ እያቀረቡ ሲሆን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን ) ጥያቄያቸውን ተቀብሎ አብሮ ለመስራት ተዘጋጅቷል ።
አዲሱ ትውልድ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ፀረ አማራ የሆኑ የትርክት ፣ የሐይል ፣ የፖለቲካ አቋሞችን በመቀየር ሁሉም ሐይሎች ፣ ሁሉም የፖለቲካ ትግሎች ፣ ሁሉም ትርክቶች ፀረ ብልፅግና እንዲሆኑ አድርጓል ።
ገና የደረሰብንን ውድመት በበቂ ሳናስረዳ ፣ ገና ያለንን ሰፊ መልካአምድር ሳንጠቀም ፣ ገና ያለንን የተፈጥሮ ሐብት ለትግሉ ማዋል ሳንጀምር ፣ ገና ሚሊዮን ወጣቶችን ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ሳናስታጥቃቸው ፣ ገና ዕውቀታችንን እና ጥበባችንን ፍልስፍናችንን ከተፈጥሯዊ ጀግንነታችን ጋር ሳናጣምራቸው ጠላቶቻችን የቆሙባቸውን የህልውና ምሰሶዎች አፍርሰን ፣ የገነቡትን ሁለንተናዊ ፀረ - አማራነት ደርምሰን ለድል እየበቃን ነው ።
ማሳሰቢያ :- ትግሉ አብይን ከመጣል ባሻገር ረጅም የትውልድ ቅብብሎሽ በአዳዲስ ተለዋጭ ስልቶች እየተመራ እስከ ዓለም ፍፃሜ ይቀጥላል ።
የአማራነት ቃል-ኪዳን እና የነፃነት ጉዞ እኔ ስወለድ አማራ ነኝ፤ ያለ ማንነቴ ሌላ ስም አልነበረኝም።
ታሪኬ የሚጀምረው ከጥንት የነገሥታት እና የጀግኖች መንደር ነው። ማንነቴን በታሪኬ፣ ታሪኬን በደሜ ውስጥ አትሜው ተወለድኩ። ሳድግም አማራ ነኝ፤
በክብር የመኖርን ትርጉም፣ ለሀገር መሞትን እና ለሰው ልጆች መራራትን እየተማርኩ አደግሁ።
አማራነት ለእኔ ስም ብቻ ሳይሆን፣ ፈተናዎችን በጽናት የማለፍ እና ለማንም ላለመንበርከክ ራስን የማዘጋጀት የህይወት ትምህርት ቤት ሆኖኝ አደገ።
ዛሬ ግን...የ30 ዓመት የጎልማሳነት እድሜ ላይ የደረስኩ፣ የማንነቴን ዋጋ በሚገባ የተረዳሁ የቁርጥ ቀን ልጅ ነኝ። ዛሬ የአማራነት ኩራቴ በተግባር የሚገለጥበት ወቅት ላይ እገኛለሁ።
እኔ የአማራ ፋኖ ነፃ አውጭ ልጅ ነኝ! ለክብሩ የማይደራደር፣ ለፍትህ የሚቆም እና የታሪካዊ ጠላቶቹን ሴራ የሚያከሽፍ የትውልድ አደራ ተሸካሚ ነኝ። የፋኖነት መንፈስ በደሜ ውስጥ ይፈሳል፤ ነፃነቴን በልመና ሳይሆን በጥንካሬዬ የማስከብር፣ የነገዋን ብሩህ አማራ የምገነባ የቁርጥ ቀን ተዋጊ ነኝ።
አማራነት የማይታጠፍ ማንነት፣ ፋኖነት ደግሞ የማይበገረ ነፃነት ነው!" Dawit fano
በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አማራነት የማይታጠፍ ማንነት፣ ፋኖነት ደግሞ የማይበገረ ነፃነት ነው!"

በደብረ ማርቆስ ከተማ የመሸገው የመከላከያ እና አድማ ብተና ኃይል እየተታኮሰ ይገኛል ከሁለቱም ቡድን አመራሮች የተገደሉ ሲሆን በከተማዋ ዙሪያ የእርስበርስ ውጊያው ተጧጡፏል።
©ባዬ ደስታ የ206ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
ከአርበኛ እስቲበል ዓለሙ
የውክልና ጦርነት እየተካሄደ ያለው በቤተ-መንግሥት ውስጥ ነው።
በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማያውቅ መልኩ የሀገር ዳር ድንበር የተደፈረበት፣ ሉዓላዊነት ለባዕዳን የተሸጠበት እና ዲፕሎማሲያችን ለውርደት የተዳረገበት ዘመን ቢኖር የብልጽግና አገዛዝ ዘመን ነው። ዜጎች ፍትሕን፣ እኩልነትን እና የሕግ የበላይነትን በሰላማዊ መንገድ ስለጠየቁ ብቻ በገዛ አገራቸው እንደ ባዕድ ተቆጥረዋል። አገዛዙ ሰላማዊ የትግል በሮችን በመዝጋት ወጣቱ ትውልድ ራሱን ለመከላከል ወደ ትጥቅ ትግል እንዲገባ አስገድዶታል።
አሁንም የራሱን ውድቀት ለመሸፈን ፋኖን "የባዕዳን ተላላኪ" በሚል የሐሰት ታፔላ ለመለጠፍ ይሞክራል። አገዛዙ ፋኖንና የፍትሕ ታጋዮችን "ሀገር አፍራሽ" በማለት ቢከስም፣ በተግባር ግን እውነተኛው "ባንዳ" እና "ባዳ" ራሱ አገዛዙ መሆኑን በተደጋጋሚ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታው በማታውቀው የሞራል እና የፖለቲካ ውድቀት ውስጥ ትገኛለች። እውነተኛው "ባንዳ" እና "ባዳ" ራሱ አገዛዙ መሆኑን የሚከተሉት ሀቆች ያረጋግጣሉ።
የግድቡ ምስጢራዊ ሽያጭና የዲፕሎማሲ ውድቀት ፤ አገዛዙ በአደባባይ "ግድቡን አስጨረስኩ" እያለ ቢፎክርም፣ ከጀርባ ግን የሀገሪቱን የዘመናት ተስፋ ለግብፅና ለአሜሪካ ተጽዕኖ አሳልፎ በመስጠት፤ በካይሮ የተደረገው የ"ወላሂ..ወላሂ" መሐላ እና በአሜሪካ አደራዳሪነት የግድቡን የኃይል ማመንጨት አቅም እንዲቀንስ መስማማቱ፣ አገዛዙ ለባዕዳን ፍላጎት ተንበርካኪ መሆኑን በግልጽ አረጋግጧል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ግብፅ ግድቡን ልታፈነዳው ትችላለች" ብለው ሲዝቱና ለግብጽ በወገን መንገድ እናሸማግላችሁ የሚል ደብዳቤ የጻፉት፣ አገዛዙ የሀገርን ክብር የሚያስጠብቅ ዲፕሎማሲያዊ ውድቀት ላይ መሆኑን የታየበት አጋጣሚ ነው።
የሀገርን የዳር ድንበር መደፈርና የአገዛዙ ዝምታ፤ በዚህ አገዛዝ ዘመን የሱዳን ጦር መሬታችንን በመውረር ዜጎቻችንን ሲያፈናቅል፣ አገዛዙ የሀገርን ድንበር ከማስከበር ይልቅ ዝምታን መርጧል። የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው ንጹሐንን ሲገድሉና ልጆችን አፍነው ሲወስዱ፣ እንዲሁም አልሻባብ ወደ መሃል ሀገር ዘልቆ ሽብር ሲነዛ አገዛዙ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ አቅም እንደሌለው ታይቷል። ለሳዑዲ አረቢያ ፍላጎት ሲባል ለሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) ወታደራዊ ማሰልጠኛ ቦታ በመስጠት፣ ኢትዮጵያን የባዕዳን የጦር አውድማ አድርጓታል።
አገዛዙ፤ የውስጥ ጭፍጨፋ እና የባንዳነት ተግባር፤ አገዛዙ የገዛ ህዝቡን በድሮንና በከባድ መሳሪያ እየጨፈጨፈ፣ የሀገርን ሉዓላዊነት የሚጋፉ የውጭ ኃይሎች ሲመጡ ግን የሚንበረከክ "ባዳ" ነው። የሀገርን መከላከያ ሰራዊት በስልት በማስመታት እና ዳር ድንበርን ክፍት በማድረግ ሉዓላዊነታችንን ለውጭ ኃይሎች አሳልፎ መስጠቱ የማይረሳ ታሪካዊ ክህደት ነው።
አገዛዙ የሀገርን መሬት ለባዕዳን እየገበረ፣ ለግብፅ መሪዎች እየማለና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በምስጢር እየሸጠ "ሀገር ጠባቂ ነኝ" ሊለን አይችልም። እውነተኛው የሀገር ስጋት፣ እውነተኛው ባንዳና ባዳ የገዛ ህዝቡን እየገደለ የሀገርን ጥቅም ለባዳን አሳልፎ የሚሰጠው የብልጽግና አገዛዝ ራሱ ነው። የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የሚከበረው ይህ የክህደት ሰንሰለት ሲበጠስ ብቻ ነው።
ሰላማዊ ጥያቄን በስላቅ የመለሰው አገዛዝ፤
የኢትዮጵያ ወጣቶች "የሕግ የበላይነት ይከበር፣ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ይቁም" ብለው ሲጮሁ፣ አገዛዙ "ይኽ የሥልጣን ፍለጋ ጩኽት ነው" በሚል ንቀትና ስላቅ ምላሽ ሰጥቷል። ሰላማዊ ሰልፈኞችን በጥይት በመደብደብ እና እስር ቤቶችን በንጹሐን በመሙላት ወጣቱ ዱር ቤቴ እንዲል ያስገደደው ይኽው ኦሕዴድ መራሹ የብልጽግና አገዛዙ ነው። አሁንም "ተላላኪ" የሚለው ስም ማጥፋት የደረሰበትን ሕዝባዊ ማዕበል ለመቀልበስ የሚጠቀምበት የከሰረ ፖለቲካ ነው።
ሕዝባችን እንደሚያውቀው የታሪካዊ ጠላቶች እውነተኛ ተላላኪ ራሱ አገዛዙ ነው። አገዛዙ ፋኖን በግብፅ፣ በሻቢያ እና በምዕራባውያን ተላላኪነት ሲከስ፣ እጆቹ ግን በታሪካዊ ክህደት የቆሸሹ ናቸው። ከግብፅ ጋርም በካይሮ መድረክ "ወላሂ፣ ወላሂ" ብሎ በመማል የሀገርን የልማት ሉዓላዊነት ለግብፅ ፍላጎት ያስገዛው ራሱ አገዛዙ ነው።
በድብቅ የግድቡን የኃይል ማመንጨት አቅም በመቀነስ የብሔራዊ ጥቅማችንን ሰንሰለት ለጠላት አሳልፎ የሰጠው ኦሕዴድ ብልጽግና ነው። የሀገርን መከላከያ ለባዕዳን ሰራዊት ክፍት በማድረግ፣ የሀገርን ሉዓላዊነት ለባዕዳን ያስረገጠውና ዜጎቻችን ለባዳ በደል እንዲጋለጡ ያደረገው ይኸው የብልጽግና አገዛዝ ነው።
የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለባዕዳን አሳልፎ የሰጠ አገዛዝ፤ የብልጽግና አገዛዝ የIMF እና የዓለም ባንክን (World Bank) አውዳሚ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ምክረ-ሐሳቦችን ያለምንም ጥንቃቄ በመቀበል፣ የሀገሪቱን የገንዘብ አቅም አዳክሞ የኑሮ ውድነትን በሕዝቡ ላይ ጭኗል። ይህ የሀገርን የኢኮኖሚ ቁልፍ ለውጭ ኃይሎች በእጅ አዙር አሳልፎ የመስጠት ተግባር፣ አገዛዙ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይሆን ለውጭ አበዳሪዎች የሚገዛ መሆኑን ያረጋግጣል።
የሀገር አንድነትን የናቀና የወደብ ቁማርተኛ፤ የመገንጠል ትረካ "ትግራይ ከፈለገች ትገንጠል" በሚል የቸልተኝነት ንግግር የሀገርን ህልውና እና የግዛት አንድነት ለድርድር የሚያቀርብ፣ ለኢትዮጵያ አንድነት ደንታ የሌለው ስብስብ ነው።
የወደብ ማታለያ፤ "እንኳን ደስ ያለን የወደብ ባለቤት ሆነናል" በሚል የውሸት ፕሮፖጋንዳ ሕዝብን በአየር ላይ ሲያደናግር ቆይቶ፣ ውጤቱ ዜሮ ሲሆን ደግሞ ዳግም "ቀይ ባሕርን አስመልሳለሁ" በሚል አዲስ የቀውስ አጀንዳ ሕዝብን እያደናገረ ይገኛል። ይህ ለሥልጣን ማራዘሚያ የሚደረግ የታሪክ ቁማር የሀገርን ዲፕሎማሲ ለውርደት ዳርጓል።
የመንግሥታን መዋቅር የስርቆትና የሙስና መፈልፈያ በማድረግ፤ ሀገሪቱ በረሃብና በጦርነት እየታመሰች፣ የአገዛዙ ባለሥልጣናት በመንግሥታዊ ስርቆትና በሙስና ሕዝብን እየበዘበዙ ነው። የሀገር ብሔራዊ ጥቅም እየተሸረሸረ ያለው በፋኖ ትግል ሳይሆን፣ በአገዛዙ የሌብነት ሰንሰለትና በባዳን ተላላኪነት ነው። በመንግሥታዊ ስርቆትና በሙስና ሕዝብን እየበዘበዙ ነው። ፋኖን "የውክልና ጦርነት ያካሂዳል" የሚለው ስም ማጥፋት፣ አገዛዙ የገዛ ሕዝቡን እየጨፈጨፈ ሥልጣኑን ለማራዘም የሚጠቀምበት የፈሪ ስልት ነው።
ሕዝባችን እንደሚያውቀው ፋኖ የኢትዮጵያዊነት ጽኑ መሠረት ነው፤ ፋኖ ከየትኛውም የውጭ ኃይል ትጥቅም ሆነ ትእዛዝ አይቀበልም። የፋኖ ትጥቅ በደል የመረረው ሕዝብ ነው፤ ስንቁ ደግሞ እውነትና ፍትሕ ነው። አገዛዙ የውጭ ኃይሎችን ስም እየጠራ የሚጮኸው፣ የራሱን የባንዳነት ታሪክ ለመሸሸግ እና ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማግኘት የሚጠቀምበት የፈሪ ስልት ነው።
እውነተኛው የውክልና ጦርነት እየተካሄደ ያለው በቤተ-መንግሥት ውስጥ ነው። ኦሕዴድ መራሹ የብልጽግና አገዛዝ ለሥልጣኑ ሲል ሀገርን ለባዕዳን እየገበረ፣ የገዛ ሕዝቡን እየጨፈጨፈ ያለ የጥፋት ኃይል ነው። ፋኖ ግን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር፣ ሉዓላዊነትና የሕዝብን ነፃነት ለማስከበር የተነሳ እውነተኛ ሕዝባዊ ኃይል ነው።አገዛዙ ለሥልጣኑ ሲል ሀገርን ቢሸጥም፣ ፋኖ ግን ሕዝቡን ለማዳን እስከመጨረሻው ይቆማል!
ትግላችን እስከ ነፃነት ይቀጥላል!
አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
✊ የአማራ ህዝብና የፋኖ አንድነት ለጠላቶቻችን የራስ ምታት ነው! ክብርና ሞገስ ለጀግናው የአማራ ህዝብና ለተከበረው የፋኖ ታጋዮቻችን!
በአሁኑ ሰዓት የአማራ ህዝብ ህልውናውን ለማስከበር በሚያደርገው ተጋድሎ፣ ጠላቶቻችን በጦር ሜዳ ሊያሸንፉን እንደማይችሉ ሲረዱ ወደ መጨረሻውና አስከፊው ስልታቸው ተሻግረዋል። ይኸውም "እርስ በእርስ ማባላት" ነው።
የአብይ አህመድ አስተዳደር በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎችና በከፈላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊቶች አማካኝነት የታቀደ የከፋፋይነት ድራማ እየተሰራብን ይገኛል።
ልንነቃባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦
የመከፋፈል አጀንዳ፦ በፋኖ አመራሮች መካከል ልዩነት እንዳለ በማስመሰል፣ "ይህኛው ፋኖ የተሻለ ነው፣ ያኛው ግን አክራሪ ነው" የሚል የሀሰት ትረካ በመርጨት በመካከላችን የጥርጣሬ መርዝ እየረጩ ነው።
የሚዲያ ዘመቻ፦ በአገዛዙ ሚዲያዎች የሚለቀቁ የተቆራረጡ ምስሎችና የፈጠራ ወሬዎች አላማቸው አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም ህዝቡ በልጆቹ (በፋኖ) ላይ ያለው እምነት እንዲሸረሸር ማድረግ ነው።
ክልላዊ ክፍፍልን መቀስቀስ፦ "የዚህ አካባቢ ፋኖ" እና "የዚያ አካባቢ ፋኖ" በማለት በታኝ ስሞችን በመስጠት፣ የአማራን ብሄራዊ አንድነት ለማላላት ሌት ተቀን እየሰሩ ነው።
ምን ማድረግ ይኖርብናል?
በአይነ ቁራኛ መጠበቅ፦ እያንዳንዱን ከሚዲያ የሚወጡ መረጃዎች በንቃት መመርመር። ጠላት የሚነዛው ወሬ እኛን ለማዳከም መሆኑን መገንዘብ።
አንድነትን ማጥበቅ፦ አሁን ካለንበት ሰዓት በላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለአንድነታችን ዋጋ መስጠት አለብን። በትንንሽ ልዩነቶች ላይ ከማተኮር ይልቅ በትልቁ የህልውና ግባችን ላይ መፅናት።
የጠላትን ፕሮፓጋንዳ ማምከን፦ ጠላት በሚዲያ የሚለቀውን የሀሰት ወሬ በጎንዮሽ ከማሰራጨት ይልቅ፣ እውነተኛውን የትግል መስመርና የፋኖን ጀግንነት ለዓለም ማሳወቅ።
"የአማራ ህዝብ አንድነት የጠላቶቻችን ውድቀት ነው!"
ወንድሞቻችንና እህቶቻችን! ጠላት የሚፈልገው እርስ በእርሳችን እንድንጋጭና ጉልበታችንን በከንቱ እንድንጨርስ ነው። እኛ ግን የነቃን ነን! በአንድነት ቆመን፣ በልጆቻችን ክንድ ታጅበን ይህን የጥፋት ዘመን በድል እንሻገራለን። Dawit fano
ድል ለአማራ ህዝብ!
ድል ለፋኖ!

+2
አፋብን 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር የሁለት ወር የስራ አፈጻጸም ግምገማ ባካሄደበትና የአመራር ሪፎርም ባደረገበት ማግስት የ77ኛ ክ/ጦር አመራሮች በቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት ተደረጓል።
ከዘህ በፊት የነበረውን የፋይናንስ አሰራር ሂደት የገመገመ ሲሆን ቀጣይ መሰራት ያለበትን ስራ ታቅዶ ወደስራ እንዲገባ አቅጣጫ ተሰጧል፡፡ እንዲሁም የንብረት እና ሰነድ ርክክብ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም ከወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች ጋር ህዝብን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ፣ የኋላ ደጀን ሰራዊትን በመጠርነፍ፣ ፋትህ አሰጣጥ በተመለከተ እና በቀጣይ ተልኮዎች ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል። አጠቃላይ በቀጣይ የክፍለጦሩ ውስጥ የሚከወኑ የስራ አቅጣጫዎች ላይ በክፍለጦሩ ሰብሳቢ በአርበኛ ሀብቴ ሁነኛው ሰፋ ያለ ማብራሪያ የተሰጠ ተሰጦ የአንድ ወር የስራ አቅጣጫወችን በማስቀመጥ የዕለቱን ፕሮግራም በስኬት አጠናቀናል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
አፋብን ቴውድሮስ ዕዝ፣ 109ኛ ኮር፣ 77ኛ ክ/ጦር
ጥር 13-05-2018 ዓ.ም
የ206ኛ ኮር ህግና ስነ-ስርዓት ክፍል ለ14ኛ ክ/ጦር አመራሮችና ለሰራዊት አባላት ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ማጠናቀቁን አስታወቀ
ጥር 13/2018 ዓ.ም
===================================
የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የህግና ስነ-ስርዓት ክፍል በተሻሻለው የድርጅቱ ህግና ደንብ መሰረት የፀደቀውን የህግና ስነ-ስርዓት መመሪያ ሰነድ ለሰራዊቱና ለዓመራሩ በማቅረብ ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል።
ኮሩ በሚመራቸው ክ/ጦሮች ባሉ ሻለቃዎች የሚገኙ የሰራዊት አባላትን ተሳታፊ በማድረግ እየተሰጠ ባለው ስልጠና ወንጀልን ቀድሞ ለመከላከልና ወንጀለኛን ተጠያቂ በሚያደርጉ የህግና ስነ -ስርዓት ጉባኤ ወንጀለኛ መቅጫ ድንጋጌዎች ዙሪያ ለሰራዊቱ በተፈጠረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአመራሩ እና በሰራዊቱ መካከል የነበሩ የአሰራር ግልፀኝነትን እንደሚቀርፍ ታውቋል።
ትግሉን ወጥ በሆነ ድርጅታዊ የህግ ድንጋጌ መምራትና ማስተዳደር ሊፈጠሩ የሚችሉ ተግዳሮቶችን በህግ አግባብ መቆጣጠር ከማስቻሉም ባሻገር የሚሰጡ ስልጠናዎች ሰራዊቱን በግብረ ገብነትና ዲስፒሊን ለማነጽ እንደሚረዳ ተገልጿል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ፋኖ ከስርዓቱ ታጣቂዎች የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ማርኮ ቢታጠቅም ብልፅግና ግን ኤርትራ ፋኖን እያስታጠቀች ነው ስትል ከሳለች:: ትልቁ ጥያቄ ብልፅግና ከቱርክና ከተለያዩ ዐረብ ሃገራት ድሮን ሳይቀር ታጥቆ ንፁሃን ዜጎችን ሲጨፈጭፍ የፅድቅ ያደረገው ማነው? የሚለው ነው... ከኤርትራ ቀርቶ ለምን ከአሜሪካ አይሰጠነም😀😀አብይ አህመድ ከዱባይ ይቀበላል እኛ እንማርካለን።
ከጋሸና ወደ ፍላቂት ሲንቀሳቀስ በነበረ እራሱን አድማ ብተና እያለ በሚጠራ ሰራዊት ላይ አንሻ ክፍለ ጦር ከባድ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ድል አስመዘገቡ::
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር በአንሻ ክፍለ ጦር ቃኝ ሻለቃዎች! በጥላት ሰራዊት ላይ በተጠና የደፈጣ ኦፕሬሽን በርካቶች ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል!
የአማራን ህዝብ ክዶ በሆዱ እየተገዛ ባለው እራሱን አድማ ብተና እያለ በሚጠራው የአረጋ ከበደ ሰራዊት ላይ ጥር 13/2018 ዓ/ም በመቄት ወረዳ ወቄታ ላይ በተወሰደ እርምጃ ዘጠኙ ሲደመሰሱ ሰባት ከባድ ቁስለኛ ተደርገዋል።
ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት በዘለቀ ውጊያ የፋሽስቱ ወበር አስጠባቂ ሰራዊት አካል የሆነው አድማበትን ሙት ጓዱን ሳያነሳ ወደ ፍላቂት ከተማ ፈርጥጧል።የአማራን ህዝብ በባንዳነት ባህሪው ከፋሽስቱ የአብይ ሀይል ጋር አብሮ ሲወጋና ሲያስወጋ በነበረ አካል ላይ ተጠናክሮ እየተወሰደ ባለ ኦፕሬሽን በወቄጣ ዳግም ተደግሟል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብን) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል
ጥር 13/2018 ዓ.ም
የቴዎድሮስ ዕዝ ወታደራዊ የዘመቻ መምሪያ ዋና አዛዥ መቶ አለቃ አበበ ሰውመሆን ከዳተኞችን እና የውስጥ አስከጅዎችን በተመለከተ ጠንከር ያለ መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን ለሀቀኛ ታጋዮች ካስተላለፈው መካከል ፦
“...ከምን ተነስተን የት እንደደረስን እናውቀዋለን እኛ ከጅምሩ ገብቶን መንግስትን አፍርሰን የመጣን እንጅ ድንገት ሳናስበው መንግስት ፈርሶብን ወደ ትግል የወጣን አደለንም። .... ከሃዲዎችን ለፍርድ ለማቅረብ እና ውጥናችንን ለማሳካት ከእውነተኛ ታጋዮች የሚጠበቀው እልህ፣ ቁጭት፣ ጀግንነት፣ የአላማ ፅናት እና አሸናፊነት ነው።..”
በማለት መቶ አለቃ ትዕዛዝ አስተላልፏል ።
The #Amhara #Fano #National #Movement Polite-Committee held its first meeting.
On January 12, 2018 E.C, the Polite-Committee of the #AFNM discussed various #agendas and made #decisions. According to Patriot #Asres #Mare #Damte, Head of the #PR Department of the organization, on his social media page,
The discussion, which began with complete #trust and #camaraderie, broadly discussed the remaining leadership structure of the organization, the organizational request submitted by #Bizzamo #Command, the naming of zones and commands, the integration of #armies and the preparation of military and political roadmaps, and provided operational guidelines.
Just move forward!
Anteneh Dires
ፅናት ክፍለ ጦር ከአማራ ፋኖ አንድነት ማግስት በርካታ የብርሀኑ ጁላን ሰራዊት በመደምሰስ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለ ጦር በጥላት ሰራዊት ላይ ከባድ እርምጃ በመውሰድና ሰብዓዊ ጉዳት በማድረስ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
ጥር 12/2018 ዓ/ም በደላንታ ወረዳ እንጥጉና ቀበሌ ላይ ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:30 በዘለቀ አውደ ውጊያ በብርሀኑ ጁላ የሚመራው የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ከ29 በላይ የተደመሰሰ ሲሆን ከ47 በላይ ቁስለኛ ተደርገዋል።
ከጉባላፍቶ ወረዳ ኩረታ፣ከተንታ ወረዳና ከደላንታ ወረዳ በገፍ አሰባስቦ በሶስት አቅጣጫ የመጣን የፋሽስቱን ሰራዊት መቀበሪያው የእንጥጉና ተራራዎች ሲሆኑ በህይዎት የተረፈው ወደየመጣበት ተመልሷል::
በምርኮኛና በጥቅመኛ የሚመራው የፋሽስቱ ሰራዊትን የፅናት ክፍለጦር ክንደ ብርቱ ፋኖዎች ከበባ ውስጥ በማስገባት ለጅብ እራት አድርገዋቸዋል። ከፋኖዎቹ የደረሰበትን የተጠናከረና ረዝም ሰዓት የፈጀ ድብደባ መቋቋም የተሳነው የፋሽስቱ ሰራዊት አዳሩን አመራሮቹ ራስህን አውጣ የሚል ትዛዝ አውርደውለት ወደየመጣበት ፈርጥጦል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብን) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል
ጥር 13/2018 ዓ.ም