ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد3 279
المشتركون
+3924 ساعات
+3057 أيام
+69830 أيام
أرشيف المشاركات
✝️ ቢዛሞ/ወለጋ የዘመኑ ጎልጎታ❗️፤የአማራ ፋኖ ደግሞ የማይቀረው የትንሳኤ መብረቅ❗️
==============================
በቢዛሞ/ወለጋ ምድር የፈሰሰው የአማራ ደም፣ ዝም ብሎ ፈሳሽ አይደለም፤ እንደ አቤል ደም ከምድር ወደ ሰማይ የሚጮህ፣ ፍትህን የሚጠይቅ የሰማዕታት ህያው ቃል ነው!
ልክ እንደ ቀራኒዮ፣ በቢዛሞ/ወለጋ ያለው ህዝባችን የማንነቱን "የሾህ አክሊል" ተጭኖበት፣ በግፈኞች "ለዋጠው" እና "ለአራጁ" ተላልፎ ተሰጥቷል። የስቅለተ ዓርብ ጨለማ በዛ ምድር ላይ ለዘመናት ነግሷል። ነገር ግን፣ መከራው እና ስቅለቱ የጭካኔያቸው ጥግ ቢሆንም፣ የእኛ ግን የፅናታችን እና የታሪካችን አዲስ ምዕራፍ ማብሰሪያ ነው።
ምክንያቱም እውነት ይሰቀላል እንጂ አይሞትም! መቃብርም እውነትን ለዘላለም ይዞ ማቆየት አይችልም!
ስቅለት ባለበት ትንሳኤ አይቀሬ ነው! ዛሬ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የዛ የታፈነች እውነት ትንሳኤ፣ የመቃብሩን ድንጋይ ፈንቅሎ የወጣው የህዝባችን የክብር ብርሃን ነው! ፋኖ በቢዛሞ/ወለጋ ለደረሰው ግፍ የተሰጠ የመለኮት ምላሽ፣ የሞትን ደጃፍ የሰበረ የነፃነት መዶሻ ነው።
እንደ አንድ የዚህ ቅዱስ ትግል አባል፣ በመከራው እቶን ውስጥ ላለፈው ህዝቤ ቃል እገባለሁ፦
የተሸከምነውን የመከራ መስቀል አስቀምጠን፣ የጠላቶቻችንን የጭቆና በትረ-መንግስት ሰብረን፣ የድሉን እና የነፃነቱን አክሊል በጋራ እንቀዳጃለን! የቢዛሞ/ወለጋ አማራ ከገባበት የመከራ መቃብር በክብር፣ በኃይል እና በግርማ መነሳቱ የማይታጠፍ የታሪክ ሀቅ ነው።
የአርብ ጨለማ በትንሳኤ እሁድ ብርሃን እንደሚገፈፍ፣ የቢዛሞ/ወለጋ ግፍም በፋኖ የድል መብረቅ ይበተናል!
ትንሳኤያችን በክንዳችን፣ ነፃነታችን በደማችን ይረጋገጣል!
ድል ለተገፋው፣ ነገር ግን ለማይሸነፈው የአማራ ህዝብ!
Nigusie Walelgn
©️ንጉሴ ዋለልኝ አማረ
በአፋብን የቢዛሞ ቀጠና አይሻ ሰይድ እዝ ሰብሳቢ
ለመላው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሰራዊት አባላትና ለጽኑ ደጋፊዎቻችን፦ እንኳን ለ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከሰማያት ሰማይ ወርዶ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ፣ በሞቱ ሞትን ድል አድርጎ ዓለምን ያዳነበት ፍቅሩ እጅግ ይደንቃል! ይላሉ አበው!!
ዛሬም እኛ አማራዎች፣ በመስቀል ላይ ካለው መከራ በኋላ የሚመጣውን ትንሳኤ በተስፋ የምንጠብቅ ሕዝቦች ነን።
ይህ ታላቅ ሕዝብ በገዛ ምድሩ ላይ የሰላም አየር እንዳይተነፍስ የአብይ አህመድ አምባገነን አገዛዝ ሌት ተቀን ክፉውን ይዶልታል። ሰማዩን በባዕድ ሀገር (ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ) ድሮኖች አጨልሞታል፤ ምድሩን ደግሞ በወንበር ጠባቂ መከላከያ ሰራዊትና "ዳይፐር" በታጠቁ የብአዴን ሚሊሻዎች፣ የአድማ መከላከልና የሕዝብ ፖሊስ ጋር በፈጠረው "የአላቻ ጋብቻ" ደም እንዲነባ አድርጓል።
ያ የዋህና ሰፊ ሕዝብ፣ አማርኛ በመናገሩ ብቻ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ሊጠፋ ከታደነ እነሆ ስምንት ክፉ ዓመታት አልፈዋል።
ነገር ግን ሞትን የማይፈራው የተራራዎች ንጉሥ የአማራ ልጅ ፋኖ ይህንን አረመኔያዊ ሥርዓት ከምድረ ገጽ ለማጥፋትና የሕዝቡን ክብር ለመመለስ በየሸንተረሩ እየተዋደቀ ይገኛል።
ውድ ሰራዊታችንና ጽኑ ሕዝባችን ሆይ! የፋሲካን በዓል ስታከብሩ፣ ይህ "ሰው በላ" ሥርዓት በጭንቀትና በሽንፈት ውስጥ ስላለ፣ በበዓል አጋጣሚ ጥቃት እንዳይሰነዝር ከወዲሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ፍኖተ አማራ ሚዲያ ከጦር ግንባር መልእክቱን ያስተላልፋል።
ድል ለአማራ ሕዝብ!
የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ለመላው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሰራዊት አባላትና ለጽኑ ደጋፊዎቻችን፦ እንኳን ለ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከሰማያት ሰማይ ወርዶ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ፣ በሞቱ ሞትን ድል አድርጎ ዓለምን ያዳነበት ፍቅሩ እጅግ ይደንቃል! ይላሉ አበው!!
ዛሬም እኛ አማራዎች፣ በመስቀል ላይ ካለው መከራ በኋላ የሚመጣውን ትንሳኤ በተስፋ የምንጠብቅ ሕዝቦች ነን።
ይህ ታላቅ ሕዝብ በገዛ ምድሩ ላይ የሰላም አየር እንዳይተነፍስ የአብይ አህመድ አምባገነን አገዛዝ ሌት ተቀን ክፉውን ይዶልታል። ሰማዩን በባዕድ ሀገር (ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ) ድሮኖች አጨልሞታል፤ ምድሩን ደግሞ በወንበር ጠባቂ መከላከያ ሰራዊትና "ዳይፐር" በታጠቁ የብአዴን ሚሊሻዎች፣ የአድማ መከላከልና የሕዝብ ፖሊስ ጋር በፈጠረው "የአላቻ ጋብቻ" ደም እንዲነባ አድርጓል።
ያ የዋህና ሰፊ ሕዝብ፣ አማርኛ በመናገሩ ብቻ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ሊጠፋ ከታደነ እነሆ ስምንት ክፉ ዓመታት አልፈዋል።
ነገር ግን ሞትን የማይፈራው የተራራዎች ንጉሥ የአማራ ልጅ ፋኖ ይህንን አረመኔያዊ ሥርዓት ከምድረ ገጽ ለማጥፋትና የሕዝቡን ክብር ለመመለስ በየሸንተረሩ እየተዋደቀ ይገኛል።
ውድ ሰራዊታችንና ጽኑ ሕዝባችን ሆይ! የፋሲካን በዓል ስታከብሩ፣ ይህ "ሰው በላ" ሥርዓት በጭንቀትና በሽንፈት ውስጥ ስላለ፣ በበዓል አጋጣሚ ጥቃት እንዳይሰነዝር ከወዲሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ፍኖተ አማራ ሚዲያ ከጦር ግንባር መልእክቱን ያስተላልፋል።
ድል ለአማራ ሕዝብ!
መነሻውን ከደብረ ማርቆስ አድርጎ ወደ ስናን ረቡዕ ገበያ ሎጅስቲክ ለማድረስ የተንቀሳቀሰው የአረመኔው ሰራዊት በአደረሰው የመድፍ ጥቃት ንፁሃን ተገደሉ።
ሚያዚያ 2/2018 ዓ.ም
=======================================
አብነት አልማው እድሜ 18 አመት ሲሆን ትውልዱ በምስራቅ ጎጃም ስንን ወረዳ ነው። በቤተሰቦቹ ድጋፍ በደብረ ማርቆስ ከተማ በአብነት ት/ቤት በሊቃውንት አባቶች የሚሰጠውን የቅስና ትምህርት እየተከታተለም ነበር።
የትንሳኤን በዓል ለማክበር ወደ ቤተሰቦቹ እየሔደ ባለበት መነሻውን ደብረ ማርቆስ ከተማ አድርጎ ወደ ስናን ረቡዕ ገበያ ሎጀስቲክ ለማቀበል የሚሔደው ጠላት በስጋት ወደ ደብረዘይት በወረወረው መድፍ ይህ የ18 አመት ወጣት ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ተገድሏል።
በደብረ ማርቆስ እና በረቡዕ ገበያ ተደጋጋሚ ጥቃት ተከፍቶበት ከባድ ኪሳራ የደረሰበት የጠላት ኃይል ሎጀስቲክ ለማቀበል እንኳ በመድፍና በድሮን መታገዝ ከተገደደ ቆይቷል።
በዚህ ፍርሀት የተዋጠው የአረመኔው ሰራዊት ከእነራታ ቀበሌ ወደ ደብረዘይት መድፍ በመወርወር በዓለ ትንሳኤን ለማክበር ወደ ቤተሰቦቹ እየሔደ የነበረው አብነት አልማውን ገድሏል።
በክርስትና እምነት ተከታዮች የሚከበረውን የትንሳኤ በዓል ተከትሎ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ቢሆንም የአረመኔው ሰራዊት በግዴለሽነት የሚያደርገው የመድፍና የድሮን ጥቃት በርካታ ንፁሃን እየተገደሉ ይገኛሉ ።
በዚህ መሰረት በዓሉን ለማክበር ከቦታ ቦታ የምትንቀሳቀሱ ወገኖቻችን ማንኛውንም ጥንቃቄ እንድታደርጉ እያሳሰብን የህዝባችንን ደህንነት ለማስጠበቅ ከጠላት የሚደረጉ ወራዎችን ለመመከት አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቃችንን ማረጋገጥ እንወዳለን።
አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ህዝብ ግንኙነት
ሰበር ዜና‼️
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክ/ጦር በጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ አደረሰ ።
ሚያዝያ 01/08/2018 ዓ.ም፡ የነበልባል ክፍለ ጦር ሻለቃዎችን ለመክበብ በለሊት የተንቀሳቀሰው የሪፐፕሊካን ጥበቃ 5ኛ ክፍለ ጦር የስርዓቱ ወንበር ጠባቂ ሰራዊት ያላሰበው ከበባ ውስጥ ገብቶ ተቀጥቅጦ መመለሱ ተገለፀ ።
መነሻውን ከአረርቲ ያደረገው የስርዓቱ ገረድ ሰራዊት የነበልባል ክፍለ ጦር ሻለቃዎችን ለመክበብ በጥቁር አማራዎች ጠቋሚነት የሌሊት ጉዞ በማድረግ ከአጉጭ ከተባለ ቦታ እስከ ብሩድሬ አስፍቶ ለመክብብ ቢንቀሳቀስም #በራስ በሀይሉ ሻለቃ #ብሩድሬ በኩል የተንቀሳቀሰው በደፈጣ መተውት የወጡ ሲሆን እነሱን ተከትሎ የመጣውን የጠላት ሀይል #ምነበላ በተባለ ቦታ ላይ ስቦ በማስገባት #ራስ በሀይሉ ሻለቃ ሁለተኛ ዙር በያዙት ደፈጣ በድጋሜ የተመታ ሲሆን ከዚህ ከበባ ለሽፋን በሌላ አቅጣጫ የተንቀሳቀሰውን የጠላት ሀይል #መብረቁ ሻለቃ #ወርቄአገር በተባለ ቦታ በመጠበቅ በከፍተኛ ሁኔታ መመታቱ ታውቋል ።
በደፈጣና በስቦ ማስገባት በሁለቱ ሻለቃዎች ቅብብሎሽ ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ የገባው ተቀጣሪው ሰራዊት እራሱን ለማዳን የተሰዋበትንና ቁስለኛውን ከብሩድሬ እስከ ምነበላ ያሉትን ሲቪሊያን ማህበረሰብ በማስያዝ ወደ መደበኛ ካምቡ ለመመለስ ተገዷል ።
እከባለሁ ብሎ በእውር መሪ የገባው የጠፋት ሀይል #በራስ በሀይሉ ሻለቃና #በመብረቁ ሻለቃ በደረሰበት ምት ወደ ኋላ ለመመለስ በሞከረበት ሰዓት #የራስ በሀይሉ ሻለቃ ቃኚዎችና የክፍለ ጦሩ ቃኚ #ነብሮ ሻለቃ በጥምረት ኮርማ ቀበሌ #መዞሪያ አካባቢ ባደረጉት ደፈጣ ምት ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ አድርሰውበታል ።
በእዚህ አወደ ውጊያ ከ50 በላይ ቁስለኛና የተሰዋ ሰራዊት ይዞ እንደወጣ በግዳጅ የተሰዋበትንና ቁስለኛ እንዲያወጡ ከተገደዱት ሲቪሊያን የውስጥ አርበኞቻችን መረጃውን አድርሰውናል ።
ከዚሁጋ ተያይዞ በሽንኮራ በኩል ያሉት የነበልባል ክፍለ ጦር ሻለቃዎች ከፍተኛ የሆነ በጠላት ላይ የማደናገሪያ ስልት በመጠቀም ጠላት ተረጋግቶ የሀይል ሚዛኑን በአንድ በኩል እንዳይጠቀም አድርገውታል፤ በማለት የነበልባል ክ/ጦር ሪፖርተራችን መረጃውን አድርሶናል ።
''ክብር ለሰውት';
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የመረጃ ምንጪ-አፋብን ሸ/ጠ/ግ/አ/ዕ ከሰም ፪ኛ ኮር ሚዲያ ክፍል ኃላፊ እና ህ/ግንኙነት መምሪያ
+1
ብሬን ይዞ ፋኖን ተቀላቅሏል
ብልሆች ነብሳቸውን እያተረፉ ነው ፋኖንም እየተቀላቀሉ ነው። ባለማወቅ የስርዓቱ አገልጋይ የነበሩ የደቡብ ዕዝ 104ኛ ኮር 39ኛ ክ/ጦር አራተኛ ሻለቃ
1️⃣ ብሬን ተኳሹ ከነ ብሬኑ
2️⃣ የሻለቃዋ የስው ሀይል እና ሌሎች ነብስ ወከፍ መሳሪያወችን በመያዝ አፋብን ጎጠግ በላይ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ግዙፉ እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር ተቀላቅለዋል።
©️አፋብን አስቻለው ደሴ 204ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
የብልፅግና ሰራዊት መፍረስ ቀጥሏል፦ "ፋኖ የሀገር ተስፋና የስርዓቱ ማብቂያ ነው"
02/08/2018 ዓ.ም
በምርጫ ስም ዕድሜውን ለማራዘም የሚጣጣረው የብልፅግና አስተዳደር፣ መተማመኛ አድርጎ ያሰለጠነው ሰራዊት በየቀኑ እየፈረሰ ወደ ፋኖ ካምፖች መቀላቀሉን ቀጥሏል። የሥርዓቱ መሠረት እየተናደ መሆኑን የሚያሳዩ ተጨማሪ አባላት በዛሬው ዕለት የቴዎድሮስ እዝ 102ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል።
ካምፑን የተቀላቀሉ የሰራዊቱ አባላት ዝርዝር፦
1. ዘሪሁን ባረንጋ፦ የ99ኛ ክፍለ ጦር፣ 2ኛ ሬጅመንት አባልና ረዳት ብሬን ተኳሽ፤
2. አበበ ውዴ፦ ሙሉ ትጥቅና መሳሪያ (አብራራው) ይዞ፤
3. ታዘብ ያረጋል፦ ባለ ሁለት እግር ማይካ ክላሽንኮፍ ይዞ፤
4. አንተነህ ውበቱ፦ የ16 ዓመት ብላቴና ሲሆን፣ "አሞኘ አባተ" የተባለውን የሚሊሻ አባል አዲስ ክላሽንኮፍ በማስፈታትና በመቀማት 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦርን በጀግንነት ተቀላቅሏል።
እነዚህ ወጣቶች በሰጡት አስተያየት፤ "መንግስት ነኝ" የሚለው የብልፅግና ስርዓት በቴሌቪዥን የሚደሰኩረው ወሬና መሬት ላይ ያለው እውነታ ሰማይና ምድር መሆኑን ገልጸዋል።
"የውሸት ፖለቲካው ሰልችቶናል፤ ህዝቡም እውነታውን ጠንቅቆ ያውቃል" ያሉት ወጣቶቹ፣ "ፋኖ ለሀገር ብቸኛው ተስፋና ለብልፅግና አምባገነንነት ብቸኛው መድኃኒት ነው" በማለት አሞካሽተዋል።
አክለውም፣ ስርዓቱ በአሁኑ ወቅት የሚይዘውና የሚጨብጠው የጠፋበት፣ አቅጣጫ የሳተና የህልውና ቀውስ ውስጥ የገባ መሆኑን ጠቁመዋል። "ይህንን እውነት በስርዓቱ ውስጥ ያሉ አመራሮችም ሆኑ ታች ያለው ሚሊሻ ጠንቅቀው ያውቁታል" ሲሉ ንግግራቸውን ቋጭተዋል።
✔ ድል ለህዝባዊ ፋኖ!
➡መረጃው የ102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ነዉ
በላስታ ግንባር ይባር አከባቢ ፋኖ በወሰደው የስቦ መምታት እርምጃ አንድ አመራርን ጨምሮ ከ30 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ተደመሰሱ!
በምስራቅ አማራ ቀጠና ላስታ ግንባር ይባር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የጥራሪ ክፍለጦር አርበኞች በወሰዱት የተቀናጀ የስቦ መምታት እርምጃ የአገዛዙ 45ኛ ክፍለ ጦርን ክፉኛ በመምታት ድል አስመዝግበዋል።
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር ስር የሚገኙት የጥራሪ ክፍለ ጦር አርበኞች ትናንት ሚያዚያ 01/2018 ዓ/ም እስከ ምሽት ድረስ በወሰዱት እርምጃ አንፀባራቂ ድል ተቀዳጅተዋል።
ከግዳን ሙጃ ከተማ ተነስቶ ወደ ይባርና አምበሳው ከተሞች በፋኖ በተዘጋጀለት ወጥመድ ሰተት ብሎ የገባው የጠላት ኃይል፡ በ360 ዲግሪ ተከቦ ክፉኛ ተቀጥቅጦ ተሸመድምዶ ተብታትኗል።
በጥራሪ ክፍለ ጦር ስር ከሚገኙት ከተመስገን ሬጅመንት፣ ከአቡነ ዮሴፍ፣ ከኤፍሬም እና ከትዕግስቱ ሬጅመንቶች የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ናቸው የስቦ መምታት እርምጃውን በመውሰድ የጠላት አከርካሪን የሰበሩት።
በዚህ ተጋድሎ ማዕረጉና ስሙ ለጊዜው በውል ያልታወቀ አንድ ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ ከአሥር በላይ ወታደሮች ሲገደሉ፡ የአመራሩ አስከሬን ዛሬ ሚያዚያ 02/2018 ዓ/ም በከፍተኛ ወታደራዊ አጀብ በሙጃ ማርያም ቤተክርስቲያን ተቀብሯል።
በተጨማሪም ከ20 በላይ ወታደሮች ከቀላል እስከ ከባድ የቆሰሉ ሲሆን፡ የጦር መሣሪያዎችና ገዢ ወታደራዊ ስፍራዎች በጥራሪ ጀግኖች ቁጥጥር ስር ውለዋል።
ሽንፈትን የተከናነበው የአገዛዙ ሰራዊት፡ ቂሙን በንፁኋን ላይ ለመወጣት ሞርታር፣ ቢኤም እና ዙ-23 በመጠቀም በእንጃፋትና በመለየ አከባቢ ነዋሪዎች ላይ የሽብር ጥቃት ሲፈፅም ውሏል።
ይኸው የነውረኛው ብልፅግና አገዛዝ ተላላኪ ኃይል፡ በህዝቡ ላይ የኢኮኖሚና የስነልቦና ጫና ለማድረስ ከከተማ ወደ ገጠራማ አከባቢዎች ሸቀጦችና የቅባት እህሎች እንዲሁም የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦች እንዳይገቡ መንገዶችን መዝጋቱ ተነግሯል።
የጥራሪ ክፍለ ጦር አርበኞች ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎችን በመቆጣጠር በጠላት ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው ቀጥለዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
ሚያዚያ 02/2018 ዓ.ም
ነፃ በወጡ ቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይቶች እየተደረጉ ነው።
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ በተከታታይ በርካታ ቦታዎች ላይ ውጊያ በመክፈት ሰዴን ጨምሮ ከተሞችን ነፃ እያደረገ ይገኛል። በዚህም በርካታ ወታድራዊ ድሎችን ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን ወታደራዊ ድሉን ወደ ፖለቲካዊ ድል ለመቀየር የሕዝብ ግንኙነት ስራ አስፈላጊ በመሆኑ ከሰዴ ማህበረሰብ ጋር ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።
የቴዎድሮስ ዕዝ አመራሮች ፣ የ201ኛ ኮር አመራሮች ፣የ54ክፍለጦር አመራሮች እና ጊዜአዊ መንግስት አመራሮች በተገኙበት ሕዝባዊ ውይይቱ ተደርጓል።
በስብሰባውም የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች፣ ፋኖ የደረሰበት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ የእድገት ደረጃ ፣ አገዛዙ እየደረሰበት ያለውን ዲፖሎሲአዊ ውድቀት እና የማህበረሰባችን ሰላምና ደህንነት መጠበቅን በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰጧል።
ማህበረሰቡም አገዛዙ ሲያደርስበት የነበውን ጭቆና በመዘርዘር እንኳን መጣችሁልን የትንሳኤን በዓል በሰላም እንድንውል ልታደርጉን ነው በማለት ለፋኖ ምስጋና አቅርቧል።
ሴት ልጆቻችን በአብይ ሠራዊት ተደፍረውብናል ፣ሀብት ንብረታችን ተዘርፏል ፣ የምርጫ ካርድ ካላወጣችሁ እየተባልን ተደብድበናል፣ በየምክንያቱ የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ እየተባልን ተደብድበናል የተገደለም አለ በማለት አገዛዙ ያደረሰባቸውን በደል ተሰብሳቢዎቹ ገልፀዋል።
ወጣቱም እንሰለጥናለን ቤተሰባችንንና የአማራን ሕዝብ ለመታደግ መክፈል ያለብንን ለመክፈል አብረናችሁ እንቆማለን ሲል ድምፁን አሰምቷል።
የፋኖ ትግል የሕዝብ ትግል መሆኑን በተግባር ያሳየ መድረክ መሆኑን ያሳየ ነበር ሲሉ አስተያይት ሰጪዎች ገልፀዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ክፋት ለማንም ፣በጎነት ለሁሉም!
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 02/2018 ዓ.ም
✍️ እንኳን ለበዓለ ስቅለቱ በሰላም አደረሳችሁ
♦️ ከዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር የተሰጠ መግለጫ
እንኳን ለ2018 ዓ.ም የጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ሞት የማይገባው ጌታ የድንግል ማርያም ልጅ ለህዝበ ክርስቲያን ነፃነትን ለመስጠት፤ አዳምም የታሰረበትን የኃጢያት ሰንሰለት ለመበጣጠስ ሲል በመስቀል ላይ ዋለ። ይህ ቀን በክርስትና እምነት ልዩ የሆነ በዓል ነዉ። እኛ ፋኖዎችም የህዝባችን ደስታ ደስታችን፤ የህዝባችን መከራ መከራችን ነውና በድጋሚ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ።
♦️ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱን ዝቅ አድርጎ በሰዉ እጅ ተሰቃየ ፣ታሰረ፣ ተገረፈ፣ ተሰቀለ፣ ህይወቱን ለሰዉ ልጅ ሲል ሰጠ ። የአማራ ፋኖም እራሱን ዝቅ አድርጎ ድንጋይ ተንተርሶ፣ ውርጭ ልሶ ብዙ መከራ እያሰላፈ አንዲት ህይወቱን ሳይሳሳ ለሚወደዉ ለታላቁ የአማራ ህዝብ እየሰጠ ይገኛል።ለዓለም ሕዝብ መከራ መቀበልን አምላካችን አሳይቶናልና እኛም ከእሱ በመማር መከራ እየተቀበልን፣ ለምንወደዉ የአማራ ህዝብ ህይወታችንንም በደስታ እየሰጠን እንገኛለን።
♦️እየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተሰቀለው ህዝብን ከወደቀበት ለማንሳት ሲል ነበር ። የአማራ ፋኖም ህዝባችን ያለአበሳው ከገባው መከራ ለማዳን ሲል ነፍጥ አንግቦ ጫካ በመውጣት ለአማራ ህዝብ አለኝታ እና ጠበቃ በመሆን እየታገለ ይገኛል። እየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ እንዳልቀረው በትንሳዔ እንደተነሳው ሁሉ የአማራ ህዝብም ተሰቃይቶ የማይቀር፤ጌታ አምላካችን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳው ሁሉ ህዝባችንም ድል አድርጎ ትንሳኤችንን በቅርብ ቀን እንደሚሆን እናረጋግጣለን።
♦️የአማራ ፋኖ የአማራ ህዝብ እምነቶች፣ ባህሎች፣ ትውፊቶች ጠበቃ ነውና ብዙ መከራ ችሎ ግፉ ሲበዛ እምቢ ያለውን የአማራ ሕዝብን በመያዝ የአብይን ወንበር እየነቀነቅነዉ እንገኛለን። ለህዝባችን እስከ መጨረሻዋ ሰዓት ድረስ በኩራት ፣ በፍፁም ፍቅር ፣በፍፁም ትህትና እንደምናገለግል፤ አገዛዙንም እንደምናስወግድ ስንገልጽ በልበ ሙሉነት ነው።
♦️በተጨማሪም ሁሉም አማራ እንዲሁም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በዓሉን ስናከብር የክርስቶስን ምግባር ተላብሰን ፣በመደጋገፍና በመረዳዳት ፣በመደማመጥና በፍቅር ፣በደስታ አቅመ ደካሞችን በማገዝ እንዲሁም በአገዛዙ የተፈናቀሉ ወገኖችንም ጭምር በማሰብ፤ በዋናነትም ልጆቻቸው የተሰዋባቸውን የፋኖ ቤተሰቦችንም በመጠየቅና በማገዝ ለአማራ ሕዝብ ሲሉ በየጫካው የቀሩት ልጆቻቸው አለመኖር እንዳይሰማቸውም በዓሉንም አብሮ በማክበር እንዲሆን ስንል በትህትና እንጠይቃለን ።
መልካም በዓል ይሁንላችሁ ‼️
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ እዝ
ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር
ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም
ዛሬ ቀን 2/8/2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በላይ ዕዝ የሜ/ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር (፩ኛ ኮር)የጣና ገላውዲወስ ክፍለጦር ለብዙ ወራት ያሰለጠናቸውን ሰራዊት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።
ጣና ገላውዲወስ ክፍለጦር እጅግ ተዋጊ ሀይል የተሰባሰበበት፣ ብዛት ያለው የሰው ሀይል ያለበት፣ በርካታ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪወችን የታጠቀ ፣ በበሳል እና በአማራ ብሄርተኝነት በማይደራደሩ መሪወች የሚመራ ፣ ከውድቀት ወደ ከፍታ የገሰገሰ በኮራችንም ውስጥ የምንተማመንበት ክፍለጦር ነው።
ከዚህ በፊት በክፍለጦሩ ሰልጥነው የተመረቁት ሰራዊቶች በርካታ ጠላትም ደምሠዋል።
በተለይ የካቲት አንድ ቀን የተጀመረው መደበኛ ማጥቃት በደቡባዊ ጎንደር ክፍል ውስጥ የነበረውን ጠላትም ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ማርከው ታጥቀው እና አስታጥቀው ይገኛሉ።
ያልሰለጠነው ትውልድም ይህን በመረዳት መሰልጠን ፣ መደራጀት ፣ መሰባሰብ ፣ ፋኖ ሁኖ መገኘት እና በአማራ ሰማይ ስር ሁኖ መታገል አማራጭ የሌለው ግዴታ መሆኑንም ተገንዝበው ዛሬ በደማቅ ሁኔታ ስልጠናቸውን አጠናቀው መደበኛ ሰራዊት በመሆን ተመርቀዋል።
ዛሬ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት የግፍ፣ የመከራ፣ የስቃይ፣ የግርፋት ቀን መሆኑ ለዛሬው ተመራቂ ለየት ያደርገዋል
ምክንኛት ያለው የፋኖ ትግል ዛሬ ይህን ሰራዊት ስናስመርቅ ባርነቱን ፣ ድብደባውን፣ በደሉን በደንብ ተገንዝቦ የእውነት በአርብ ቀን ተመርቆ የእውነተኛ አርበኛ መሆኑ ነው።
ፋኖ አመኑ አለም አንተ!!!
#ፍቅሩ_ሙሉዬ የሚባል ወዶ ገብ #በቀቀን በሚዲያ ቀርበ ብልፅግና የፃፈለትን ተውኔት እየተወነ የአመራር ልጆች በወጭ አገር እየተሞላቀቁ እየኖሩ እያለ ሲቀደድ አየውት ሰማሁት። የየትኛው የአፋብን አመራር ቤተሰብ ነው ዉጭ ሀገር የሚኖር ❓ ከዚህ በታች ያሉትን አየወቃቸውም ልበል❓
የአፋ--ብን ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ ቤተሰቦች።
- አርበኛ ዘመነ ካሴ
- አርበኛ ንብረቱ ካሴ
- አርበኛ ገደፋው ካሴ
- አርበኛ ኪሩቤል ዘመነ ካሴ ሌሎች በርካታ ቤተሰቡ በትግል ሜዳ ተገኝተው ዋጋ እየከፈሉ ነው።
የአፋ----ብን ምክትል አዛዠ ለወታደራዊ አስተዳደር አርበኛ ዝናቡ ልንገረው ቤተሰቦች።
- አርበኛ ልንገረው ደለለ :- ወላጅ አባት
- ፋኖ ዝናቡ ልንገረው ደለለ
- ፋኖ ይታይህ ልንገረው ደለለ
- ፋኖ ለጌታ ልንገረው ደለለ
- ፋኖ ለሰሚ ልንገረው ደለለ
- ዋስይሁን ደረጄ በላይ ( ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም የተ--ሰዋ)
- አማኑኤል ደረጄ በላይ ( መስከረም 7/2017 ዓ.ም የተ---ሰዋ )
የአፋ---ብን ጎጠግ በላይ ዘለቀ ዕዝ የአባት አርበኞች ምክርቤት ፀሃፊ የሆነው ኮማንደር አረጋ አለባቸው ሶስት ወንድሞቹን ሁለት ልጆቹን እንዲሁም አንድ የወንድም ልጅ እና የእህቱን ልጅ ይዞ እየተ----ዋደቀ ይገኛል። እነሱም፦
- አርበኛ ማርየ አለባቸው
- አርበኛ ጌትነት አለባቸው
- አርበኛ ፍቅሬ አለባቸው
- አርበኛ ክንድየ አረጋ አለባቸው
- አርበኛ ጌታው አረጋ አለባቸው
- የኮማንደር አረጋ አለባቸው የወንድም ልጅ አርበኛ አለሙ ፍቅሬ አለባቸው ( መጋቢት 21/2018 ዓ.ም የ--ተሰዋ )
የአፋ---ብን ጎጠግ በላይ ዘለቀ ዕዝ የአባት አርበኞች ምክርቤት ሰብሳቢ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ቤተሰቦች!
- ፋኖ ገብሬ መሳፍንት ተስፉ ( በክብር የተ---ሰዋ)
- ፋኖ ጌትነት መሳፍንት ተስፉ ( ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም የተ---ሰዋ)
- ፋኖ ሰላም መሳፍንት ተስፉ
- ፋኖ መከተ ተስፉን ጨምሮ ከ30 በላይ ቤተሰቦቹ በነቂስ እየተሳተፉ ነው።
የፋኖው አባት የዋዋ ጎቤ መልኬ ቤተሰቦች።
- አርበኛ ፋሲል ጎቤ
- አርበኛ እሱባለው ጎቤ
- አርበኛ አንተነህ ጎቤ
- አርበኛ ስጦታው መልኬ ሌሎች ያልጠቀስኳቸው የአጎትና የአክስት ልጆች እንዳሉ ልብ ይሏል።
የዝምተኛው መብረቅ የሲሳይ አሸብር ወንድሞች!
- አርበኛ እሸቴ አሸብር
አርበኛ ደጀን አሸብር( በክብር ተሰው---ቷል)
የአፋ---ብን ምክትል ወታደራዊ አዛዠ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ልጅ ንጉሡ ምሬ ወዳጆ በትግል ሜዳ ነው።
ከአንድ ቤተሰብ ለህልውና ትግላችን በክብር የተ--ሰው ፣ የቆ---ሰለ ፣ አሁንም እየተጋሉ ያሉ ያልጠቀስኳቸው እጅግ እጅግ በርካታ ወንድሞች አለ። ከከፍተኛ አመራር እስከታች ድረስ ውድ ዋጋ እየተከፈለልን ነው።
ክብር ለሰማእታት!🙏🙏🙏
