ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más3 279
Suscriptores
+3924 horas
+3057 días
+69830 días
Archivo de publicaciones
ከአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ የተሰጠ የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መግለጫ
ሚያዝያ 03 ቀን 2018 ዓ.ም
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እና በየግንባሩ ለምትገኙ የሰራዊታችን አባላት በሙሉ፤ በመጀመሪያ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለትና የትንሳኤ በዓል እንኳን በፅናት አደረሳችሁ።
የሰው ልጅ በኃጢአት ቀንበር ወድቆ ሲማቅቅ፣ ክርስቶስ ለአለሙ ሁሉ መዳን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ የሰውን ልጅ የሞት ደብዳቤ ደምስሶ ለሚያምኑት ሁሉ የዘላለም ልጅነትን ሰጥቷል። ይህ ዕለት ፍቅር ድል ያደረገበት፣ የሰው ልጅ በደል የተሰረዘበት፣ የትህትና እና የቤዛነት ታላቅ ምስጢር የታየበት ታላቅ ቀን ነው።
በአሁኑ ወቅት አንባገነኑ የብልፅግና አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ ግልጽ ጦርነት አውጆ፣ በየቀኑ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ይገኛል። ዛሬ ህዝባችን የልማትና የዲሞክራሲ ጥያቄ ቀርቶ "በህይወት የመኖር መብቱ" እንኳን ቅንጦት ሆኖበታል። በታሪካችን አይተነው በማናውቅ መልኩ፣ ከውጭ በሚሸመት የጦር መሳሪያ ድብደባ እንዲሁም በአገዛዙ ዘራፊ ጦር ግፍና መከራ እንደ ዶፍ እየወረደበት ይገኛል።
ይሁን እንጂ ህዝባችን ይህንን የመኖርና ያለመኖር የህልውና ትግል አምርሮ እየታገለ፣ የተደቀነበትን የሞት ደብዳቤ ቀዶ በመጣል በቅርብ ቀን ነፃ እንደሚወጣ አንጠራጠርም። ይህ አረመኔ አገዛዝ የአማራ ህዝብ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች እንዲቋረጡ፣ ሀብትና ንብረቱም እንዲወድም ሆን ብሎ የሚሰራ ጨካኝ ስብስብ መሆኑ ዛሬ ለዓለም ግልጽ ሆኗል።
በመሆኑም የዘንድሮው የፋሲካ በዓል ሲከበር እንደ ወትሮው ሁሉ አስፈላጊው ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ እንዲሆን እያሳሰብን፤ ሃይማኖታዊ በዓሉን ስናከብር ይህን የመከራ ጊዜ በመተሳሰብ እንድናሳልፈው ጥሪያችንን እናቀርባለን። በተለይም፦
• በዚህ የህልውና ትግል የተሰዉ ጀግኖችን ቤተሰቦች በመጠየቅ፤
• የቆሰሉ ጀግና ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን በመንከባከብ፤
• እንዲሁም ደጋፊና ረዳት የሌላቸውን ወገኖቻችንን በመርዳት እንዲሆን መላው ህዝባችንን በአክብሮት እንጠይቃለን።
በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የጸሎትና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ስለ እኛ መከራን የተቀበለና ፍቅሩን በመስቀል ላይ የገለጸልን አምላክ፣ ሰላሙንና በረከቱን በሁላችንም ላይ ያሳድርብን።
መልካም በዓል!
"ክብር ለተሰዉት ጀግኖቻችን!"
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!"
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ

ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን )የትግል ጎን ከቆሙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሞዐ ተዋሕዶ ሥራ አስፈጻሚ አባላት የቀረበ ጥያቄ !!!!!!!!
1ኛ. በፋኖ ስም ተደራጅታችሁ ድብቅ ማንፌስቶ እና ርእዮተ ዓለም የያዛችሁ መሆኑን በተመለከተ ።።
2ኛ .ሁሉም ፋኖ በእኛ አስተሳሰብ እና አደረጃጀት የተሠራ እና የተመሠረተ ነው ማለታችሁ ።።
3ኛ. በትግሉ መካከል ገብቶ ፋኖን ከፋኖ የመነጣጠል ሥራ ሲሰራ መቆየቱ። ማለትም አንዱን ክርስቲያን አንዱን ጴንጤ አንዱን የዓለም ብርሃን ሌላኛውን ሙስሊም ሲቀጥል አንዱን አክራሪ ጿሚ ፀሎተኛ ሌላኛውን በላተኛ በማለት ሲከፋፍል ቆይቷል ።።
4ኛ.የአማራ ፋኖ በተለያየ ድርጅት እና መሥመር ተከፋፍሎ እርስ በርሱ ሲመታታ በበነበረበት ሰዓት የእርቅ መድረክ ፈጥሮ አንድ በማድረግ ፈንታ ይባስ ብሎ እንዲያውም የሞዓ ተዋሕዶን ሐሳብ ያልተቀበለ ፋኖ ካለ ገደል መግባት ይችላል ተብሎ በሚዳያ መግለጫ ተሰጥቷል ።።።።
5ኛ. ሞዓ ተዋሕዶ በ2014 በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት በተፈጸመ ጊዜ 7 ጥያቄ ይዞ የተቋቋመ ግብረ ኃይል ሲሆን ፋኖ ሁኖ ወደ ፋኖነት የተቀየረው መቸ ነው?
6ኛ. የአማራ ፋኖ የትግል ጉዳይ የመኖር እና የአለመኖር ጉዳይ መሆኑ እየታወቀ የሃይማኖት ጦርነት ነው የተነሳ እያላችሁ ሙስሊሙ እና ሌላው አማኝ በአማራነቱ እንዳይታገል እንዳይደግፍ አድርጎታል ።።።
7ኛ. ከውስጥ እና ከውጭ ካለው ሕዝባችን ከተለያዩ ተቋማት በአማራ ፋኖ ስም ከፍተኛ ፋይናንስ እየተሰበሰበ ሞዐን ለሚደግፉ ግለሰቦች ብቻ ሲታደል የቆየ መሆኑ ።።።
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ እዝ
ም/ወታደራዊ አዛዥ እና ስራ አስፈጻሚ
አርበኛ ሸጋ ጌታቸው
ህልውናችን በተባበረ ክዳችን
ጎደር አማራ ኢትጵያ
ሚያዝያ 03 /08/2018 ዓ.ም
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ ለኦፕሬሽን የተላለፈ የጥንቃቄ መመሪያ!!
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ፣ ለመላው የአማራ ህዝብ እና በዱር በገደሉ የአማራን ህዝብ የህልውና ጥያቄ ለማስመለስ ለመትዋዱቁ የፋኖ ሰራዊት አባላት በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን!!
መራሹ የብልፅግናው አገዛዝ የአማራን ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት የከፈተውን መጠነ-ሰፊ ጥቃት በክንዳችን እየተመከተ ቢሆንም፣ ጠላት በበዓል ሰሞን ያለውን የህዝብ እንቅስቃሴ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የክህደት ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጅት ማድረጉን የውስጥ መረጃዎቻችን አረጋግጠዋል። በመሆኑም በዕዝ በኮር፥ በክፍለ ጦር የሻለቃ አመራሮችንና የሰራዊት አባሎች የሚከተለውን አስቸኳይ ጥንቃቄ እንዲደረግ መልክቴን እንደሚከተለው አስተላልፋለሁ።
1. ማንኛውም የሰራዊት አባልም ሆነ አመራር በበዓሉ ሰሞን የሚሰጥ የፈቃድ ዕረፍት የማይኖር ሲሆን ሰራዊቱ በሙሉ በያለበት ቀጠና በንቃትና በጥርነፋ እንዲቆይ
2. በበዓል ስም የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ለደፈጣ ጥቃቶችና ለንብረት ዝርፊያ ምቹ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ጥበቃ ማድርግ
3. የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ሰርጎ ገቦችን በማስገባት እና መረጃ በመሰብሰብ ስራዊታችን እና ህዝባችን ላይ ጥቃት ለማድረስ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን የውስጥ መረጃዎች ያመላክታሉ በመሆኑም ህዝባችን እና ሰራዊታችን ይህንን ጉዳይ በጥብቅ እንዲከታተል አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው እክል በአፋጣኝ እንዳታሳውቁ ይሁን
4. ተስፋ የቆረጠው መራሹ የብልግና አገዛዝ የሰራዊቱን ስብስብ በመረጃ አረጋግጦ የድሮን ጥቃት ለመሰንዘር እያደባ ስለሆነ የተለመደውን ጥንቃቄ እንዲደርግ።
5. ሰራዊታችን ከሲቪሉ ማህበረሰብ ጋር በሰፊው መቀላቀልና በግልጽ ስፍራዎች መሰባሰብ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
6. ጠላት የሰራዊቱን መዘናጋት ጠብቆ ድንገተኛ ወረራ ለማድረግ ያቀደ ስለሆነ ጥንቃቄ እንዲደረግ።
7. በሁሉም ቀጠናዎች የቀንና የሌሊት የደፈጣ ጥበቃ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
8. የጥንቃቄ መመሪያው ለመላው ሰራዊታችንን ተግባራዊ እንዲሆን እና አስቸኳይ የጠላትን እቅድ ቀድመን በመረዳት የህዝባችንን በዓልና የሰራዊታችንን ደህንነት እናስጠብቃለን።
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ
የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ምክትል ወታደራዊ አዛዠ ለኦፕሬሽን !!
የአምቡላንስ እርክክብ ተደረገ ።
መጋቢት 30/2018ዓ.ም አፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሰዴ ከተማ ላይ በተደረገ ውጊያ ጠላትን በመደምሰስ ከ09 በላይ ተሽከርካሪዎችን መማረካችን ይታወቃል ። ከዚህ መካከልም አምቡላንሱን ለ ከርኒ ቀበሌ ጤና ጣቢያ አስረክበናል።
ሞጣ ከተማ መሽጎ የሚገኘው የአብይ አሕመድ አሽከር የሆነው የብልፅግና ሴል ፋኖ በተቆጣጠራቸው አካባቢ ማህበረሰቡን በመፈረጅ የመድሃኒት አቅርቦት በመከልከል፣ ነፍሰጡር እናቶች ክትትል እንዳያደርጉ እና በሜዳ እንዲወልዱ አምቡላንስ ተከልክለው ለዓመታት እንደ 19ኛው ክፍለዘመን በሳንሳ ሲንቀሳቀሱ አድርገው ከርመዋል። ማህበረሰቡ ከዚህም በከፋ መልኩ ሸቀጣ ሸቀጥ እንዳያስገባ ፣ ነዳጅና የኢንዱስትሪ ግባት እንዳይጠቀም ለወራት በመዝጋት አንዳንዴ ደግሞ በመክፈት ሲያሰቃዩት ከርመዋል። ይህን የማህበረሰቡን እና የነፍሰጡር እናቶችን ችግር ለመቅረፍ በዛሬው ዕለት አንድ አምቡላንስ ለከርኒ ቀበሌ ጤና ጣቢያ ማስረከብ ተችሏል።
የ201ኛ ኮር አመራሮች ፣የ54ኛ ክፍለጦር አመራሮች እና የሰዴ ወረዳ ጊዜአዊ መንግስት አመራሮች የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች በተገኙበት የመኪና ቁልፍ የማስረከብ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል።
ተወካይ የማህበረሰብ አባላትም '' ሚስቶቻችንና ልጆቻችንን ጤና ጣቢያ ለማድረስ እና ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ በአህያ ፣በበቅሎ ፣በሳንሳ እና አንዳንዴም በባጃጅ እናደርስ ነበር። ይህን አንቡላስ ስላስረከባችሁን ከልብ እናመሰግናለን '' ሲሉ ያሳለፉትን መከራ እና ስቃይ በማስታወስ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ክፋት ለማንም ፣በጎነት ለሁሉም!
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 03/2018 ዓ.ም
ሚያዝያ 03 /08/2018 ዓ.ም
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ ለኦፕሬሽን የተላለፈ የጥንቃቄ መመሪያ!!
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ፣ ለመላው የአማራ ህዝብ እና በዱር በገደሉ የአማራን ህዝብ የህልውና ጥያቄ ለማስመለስ ለመትዋዱቁ የፋኖ ሰራዊት አባላት በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን!!
መራሹ የብልፅግናው አገዛዝ የአማራን ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት የከፈተውን መጠነ-ሰፊ ጥቃት በክንዳችን እየተመከተ ቢሆንም፣ ጠላት በበዓል ሰሞን ያለውን የህዝብ እንቅስቃሴ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የክህደት ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጅት ማድረጉን የውስጥ መረጃዎቻችን አረጋግጠዋል። በመሆኑም በዕዝ በኮር፥ በክፍለ ጦር የሻለቃ አመራሮችንና የሰራዊት አባሎች የሚከተለውን አስቸኳይ ጥንቃቄ እንዲደረግ መልክቴን እንደሚከተለው አስተላልፋለሁ።
1. ማንኛውም የሰራዊት አባልም ሆነ አመራር በበዓሉ ሰሞን የሚሰጥ የፈቃድ ዕረፍት የማይኖር ሲሆን ሰራዊቱ በሙሉ በያለበት ቀጠና በንቃትና በጥርነፋ እንዲቆይ
2. በበዓል ስም የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ለደፈጣ ጥቃቶችና ለንብረት ዝርፊያ ምቹ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ጥበቃ ማድርግ
3. የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ሰርጎ ገቦችን በማስገባት እና መረጃ በመሰብሰብ ስራዊታችን እና ህዝባችን ላይ ጥቃት ለማድረስ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን የውስጥ መረጃዎች ያመላክታሉ በመሆኑም ህዝባችን እና ሰራዊታችን ይህንን ጉዳይ በጥብቅ እንዲከታተል አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው እክል በአፋጣኝ እንዳታሳውቁ ይሁን
4. ተስፋ የቆረጠው መራሹ የብልግና አገዛዝ የሰራዊቱን ስብስብ በመረጃ አረጋግጦ የድሮን ጥቃት ለመሰንዘር እያደባ ስለሆነ የተለመደውን ጥንቃቄ እንዲደርግ።
5. ሰራዊታችን ከሲቪሉ ማህበረሰብ ጋር በሰፊው መቀላቀልና በግልጽ ስፍራዎች መሰባሰብ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
6. ጠላት የሰራዊቱን መዘናጋት ጠብቆ ድንገተኛ ወረራ ለማድረግ ያቀደ ስለሆነ ጥንቃቄ እንዲደረግ።
7. በሁሉም ቀጠናዎች የቀንና የሌሊት የደፈጣ ጥበቃ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
8. የጥንቃቄ መመሪያው ለመላው ሰራዊታችንን ተግባራዊ እንዲሆን እና አስቸኳይ የጠላትን እቅድ ቀድመን በመረዳት የህዝባችንን በዓልና የሰራዊታችንን ደህንነት እናስጠብቃለን።
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ
የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ምክትል ወታደራዊ አዛዠ ለኦፕሬሽን !!
ሚያዝያ 03 ቀን 2018 ዓ.ም
ለሰራዊቱ እና ለአመራሩ ከአፋብን የተሰጠ ማሳሰቢያ
በአስደናቂ ተጋድሏችን እየተሰባበረ ያለው የአገዛዙ ሰራዊት የወገን ኃይል ላይ የተደራጀ ማጥቃት እንዲፈፅም ተደጋጋሚ ስምሪት ቢሰጥም እግረኛው ስራዊት የተሰጠውን ስምሪት መፈፀም አልቻለም። አንድም የሚደርስበትን ምት በመፍራት ሁለትም የብልፅግና ጦርነት ዓላማ የሌለው መሆኑን በመረዳት።
በዚህ ምክንያት የወገን ሰራዊት ከበዓል ጋር የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴወች እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም አገዛዙ የጅምላ ጥቃት ለመፈፀም በሁሉም አካባቢወች የድሮን ስምሪቶች ሰጥቷል።
የዩናይትድ አረብ ኢምሬት አየር ኃይል አባላት የድሮን እና የጀት ጥቃት ለመፈፀም ከሌላው ጊዜ በተለዬ ሁኔታ የወትሮ ዝግጁነት ላይ ይገኛሉ።
በመሆኑም መላው ሰራዊታችን እና አመራሩ ይህንን የድሮን እና የአየር ኃይል ስምሪት ታሳቢ ያደረጉ እንቅስቃሴወች እንዲያደርጉ እና በተለይም በዓል ለማክበር የሚደረጉ ክንውኖች እጅጉን ጥንቃቄ የተሞላባቸው እንዲሆኑ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በጥብቅ ያሳስባል!
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ስር የሚንቀሳቀሰው የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር (ነጎድጓድ ክፍለ ጦር) በደብረ ብርሃን ዙሪያ በሚገኙ ስልታዊ ቦታዎች ላይ በከፈተው ጥቃት ከፍተኛ ወታደራዊ ድል ተቀናጀ!!
ሆኖም ውጊያው ሰሞኑን ለተካታታይ ለሶስት ቀን የቀጠለ ቢሆንም በዛሬ ዕለት ሌሊት 10፡30 ስዓት የተጀመረ ሲሆን ለተከታታይ አምስት ሰዓታት በከፍተኛ ግብግብ ቀጥሏል። ውጊያው በዋናነት መጥቆርያ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ልዩ ስሙ አራዳ በሚባለው ቀጠና ላይ ያተኮረ ነበር።
የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ነጎድጓድ ክፍለ ጦር አባላት የጠላትን ምሽግ በመስበር እስከ ግፍት ድረስ ያለውን ስፍራ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረው እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ ቆይተዋል።
በዚህ ብርቱ ውጊያ በአብይ አህመድ መከላከያ አራዊት ሰራዊት ኃይሎች ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ ኪሳራ የደረሰ ሲሆን፣ እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ከ30 እስከ 40 የሚደርሱ አስከሬኖች ተነስተዋል።
በስም ከተረጋገጡት 11 ሟቾችና 8 ቁስለኞች በተጨማሪ፣ በርካታ ቁጥር ያለው የሰው ኃይል መገደሉና መቁሰሉ ተረጋግጧል።
ሆኖም የአብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው በአሁኑ ወቅት በመከላከያ ሠራዊቱ አማካኝነት በአካባቢው የምርጫ ካርድ የማደልና ነዋሪው የተወሰኑ አካላትን እንዲመርጥ ጫና የማሳደር ተግባር እያከናወነ ይገኛል። ይህ አረመኔያዊ ሰራዊት ስንዴና ዘይት በማከፋፈል ነዋሪው ድምፁን እንዲሰጥ እየቀሰቀሰም ይገኛል።
የአብይ ወንበር አስጠባቂው ጥምር ጦር ኃይሎች በግፍት ቀበሌ የሕዝቡን ሃይማኖታዊ እሴትና የጾም ሥርዓት በጣሰ መልኩ በዕለተ ስቅለት (አርብ) የነዋሪዎችን ፍየል አርደው በመብላት ነዋሪውን ማማረራቸውን ገልጸዋል። ይህ በደብረ ብርሃን ዙሪያ የተመዘገበው ድል እጅግ አኩሪ ተግባር ነው።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ሚያዝያ 02/08/2018 ዓ.ም

+2
ሰበር ዜና
የአፋብን ጎ/ጠ/ግ በላይ ዘለቀ ዕዝ በሰሜናዊ ጎንደር ዞን የሚንቀሳቀሰው 208ኛ ኮር አጋች ላይ እርምጃ ወስዶ የታገቱ ዶክተሮችን ማስለቀቁን አስቀድመን የዘለገብን ሲሆን አሁንም ሌባን አሳዶ መቅጣቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
ዛሬ ቀን 2/8/2018ዓ.ም ምሽት 2:00 ገደማ አካባቢ አምባ ጊወርጊስ ወረዳ መረባ ቀበሌ የአቶ ብርሌው ቢራራን 5ከብቶችን ሰርቀው ሲሰወሩ ከማህበረሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ሰርቀው የተሰወሩ ዳኛው እጅጉ እና ወርቁ ጋፋር የተባሉ ሁለት ወንበዴ ሌቦችን በተሰራ አሳዶ የመያዝ ኦፕሬሽን ሌቦችን እስከ ከብቶች በቁጥጥር ስር በማዋል በሬዎቹን ለባለቤቱ መመለስ ተችሏል።
ከህዝብ የወጣ ታጋይ ከባህር እንደወጣ አሳ እንደማለት ሲሆን ህዝባዊነት የትግሉ መሰረት በመሆኑ አጠናክራቹህ መቀጠል እና የቀጠናውን ሰላም ከሰላም ጠል ወንበዴ ሌቦች መጠበቅ ይኖርባቹሃል በርቱ ጀግኖች✊
ድል ለአማራ ፋኖ
+1
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነው ኮር 21ኛ ክፍለ ጦር የአገዛዙን ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ድል ተጎናፀፈ።
ጠላት 21ኛ ጦርን አጠፋለሁ በሚል አጉል ምኞት በሶስት አቅጣጫ ማለትም አገዉየ ሰቀላ ፣ አጤሁዳድ እና ማዉሬ ኪዳህነ ምህረት በሚባሉ ቦታወች አስፍቶ ቢመጣም ንስሮቹ የዘላለም ሲሳይ ግርፎች እንደ ቃርያ ሲያረግፉት ዉለዋል።
ወጊያዉ ዛሬ ማለትም ሚያዚያ 2/2018 ዓ.ም የተደረገ ሲሆን በዚህም ከ30 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት እስከወዲያኛዉ ሲሸኝ ከ20 ያላነሰዉ ደግሞ ቁስለኛ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ጠላትም አስክሬኑን እስከ ምሽት 3:00 ድረስ በየአቅጣጫዉ እየፈለገ ሲቀብር አምሽቷል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 2/2018ዓ.ም
✝️ ቢዛሞ/ወለጋ የዘመኑ ጎልጎታ❗️፤የአማራ ፋኖ ደግሞ የማይቀረው የትንሳኤ መብረቅ❗️
==============================
በቢዛሞ/ወለጋ ምድር የፈሰሰው የአማራ ደም፣ ዝም ብሎ ፈሳሽ አይደለም፤ እንደ አቤል ደም ከምድር ወደ ሰማይ የሚጮህ፣ ፍትህን የሚጠይቅ የሰማዕታት ህያው ቃል ነው!
ልክ እንደ ቀራኒዮ፣ በቢዛሞ/ወለጋ ያለው ህዝባችን የማንነቱን "የሾህ አክሊል" ተጭኖበት፣ በግፈኞች "ለዋጠው" እና "ለአራጁ" ተላልፎ ተሰጥቷል። የስቅለተ ዓርብ ጨለማ በዛ ምድር ላይ ለዘመናት ነግሷል። ነገር ግን፣ መከራው እና ስቅለቱ የጭካኔያቸው ጥግ ቢሆንም፣ የእኛ ግን የፅናታችን እና የታሪካችን አዲስ ምዕራፍ ማብሰሪያ ነው።
ምክንያቱም እውነት ይሰቀላል እንጂ አይሞትም! መቃብርም እውነትን ለዘላለም ይዞ ማቆየት አይችልም!
ስቅለት ባለበት ትንሳኤ አይቀሬ ነው! ዛሬ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የዛ የታፈነች እውነት ትንሳኤ፣ የመቃብሩን ድንጋይ ፈንቅሎ የወጣው የህዝባችን የክብር ብርሃን ነው! ፋኖ በቢዛሞ/ወለጋ ለደረሰው ግፍ የተሰጠ የመለኮት ምላሽ፣ የሞትን ደጃፍ የሰበረ የነፃነት መዶሻ ነው።
እንደ አንድ የዚህ ቅዱስ ትግል አባል፣ በመከራው እቶን ውስጥ ላለፈው ህዝቤ ቃል እገባለሁ፦
የተሸከምነውን የመከራ መስቀል አስቀምጠን፣ የጠላቶቻችንን የጭቆና በትረ-መንግስት ሰብረን፣ የድሉን እና የነፃነቱን አክሊል በጋራ እንቀዳጃለን! የቢዛሞ/ወለጋ አማራ ከገባበት የመከራ መቃብር በክብር፣ በኃይል እና በግርማ መነሳቱ የማይታጠፍ የታሪክ ሀቅ ነው።
የአርብ ጨለማ በትንሳኤ እሁድ ብርሃን እንደሚገፈፍ፣ የቢዛሞ/ወለጋ ግፍም በፋኖ የድል መብረቅ ይበተናል!
ትንሳኤያችን በክንዳችን፣ ነፃነታችን በደማችን ይረጋገጣል!
ድል ለተገፋው፣ ነገር ግን ለማይሸነፈው የአማራ ህዝብ!
Nigusie Walelgn
©️ንጉሴ ዋለልኝ አማረ
በአፋብን የቢዛሞ ቀጠና አይሻ ሰይድ እዝ ሰብሳቢ
ለመላው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሰራዊት አባላትና ለጽኑ ደጋፊዎቻችን፦ እንኳን ለ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከሰማያት ሰማይ ወርዶ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ፣ በሞቱ ሞትን ድል አድርጎ ዓለምን ያዳነበት ፍቅሩ እጅግ ይደንቃል! ይላሉ አበው!!
ዛሬም እኛ አማራዎች፣ በመስቀል ላይ ካለው መከራ በኋላ የሚመጣውን ትንሳኤ በተስፋ የምንጠብቅ ሕዝቦች ነን።
ይህ ታላቅ ሕዝብ በገዛ ምድሩ ላይ የሰላም አየር እንዳይተነፍስ የአብይ አህመድ አምባገነን አገዛዝ ሌት ተቀን ክፉውን ይዶልታል። ሰማዩን በባዕድ ሀገር (ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ) ድሮኖች አጨልሞታል፤ ምድሩን ደግሞ በወንበር ጠባቂ መከላከያ ሰራዊትና "ዳይፐር" በታጠቁ የብአዴን ሚሊሻዎች፣ የአድማ መከላከልና የሕዝብ ፖሊስ ጋር በፈጠረው "የአላቻ ጋብቻ" ደም እንዲነባ አድርጓል።
ያ የዋህና ሰፊ ሕዝብ፣ አማርኛ በመናገሩ ብቻ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ሊጠፋ ከታደነ እነሆ ስምንት ክፉ ዓመታት አልፈዋል።
ነገር ግን ሞትን የማይፈራው የተራራዎች ንጉሥ የአማራ ልጅ ፋኖ ይህንን አረመኔያዊ ሥርዓት ከምድረ ገጽ ለማጥፋትና የሕዝቡን ክብር ለመመለስ በየሸንተረሩ እየተዋደቀ ይገኛል።
ውድ ሰራዊታችንና ጽኑ ሕዝባችን ሆይ! የፋሲካን በዓል ስታከብሩ፣ ይህ "ሰው በላ" ሥርዓት በጭንቀትና በሽንፈት ውስጥ ስላለ፣ በበዓል አጋጣሚ ጥቃት እንዳይሰነዝር ከወዲሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ፍኖተ አማራ ሚዲያ ከጦር ግንባር መልእክቱን ያስተላልፋል።
ድል ለአማራ ሕዝብ!
የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk