ar
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
3 931
المشتركون
+4524 ساعات
+1767 أيام
+1 15530 أيام
أرشيف المشاركات
ከአዉደ ዉጊያ ጎን ለጎን የሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር በመቄት ጥልቅ ተሐድሶ አደረገ!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳ
+2
ከአዉደ ዉጊያ ጎን ለጎን የሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር በመቄት ጥልቅ ተሐድሶ አደረገ!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር የሚገኘው ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር በመቄት ከጥር:-26 ጥር:- 28/05/2018 ዓ/ም ለተከታታይ ሶሰት ቀናት በጥልቀት በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል ። በተሐድሶው ላይ የተገኙት የሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍለጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ አማን ጎበዜ ፣ምክትል አዛዥ አርበኛ ሸጋው ወርቄ ጉድለቶቻችን በማረም ቀጣይ ግዳጆችን በብቃት መፈፀም አለብን ብለዋል። የወረዳው ጊዚያዊ ህዝብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ፋኖ መምህር በሪሁን ደምሌ በበኩሉ ወታደሩ በየወቅቱ አቅሙን እያሳደገ አቅዶ ጠላትን መምታት እንዳለበት ገልፆ የህዝብ ጉዳይን የህዝብ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ቀጣይም አቅሙን አጠናክሮ ህዝብን በቅን ልቦና ያገለግላል ብሏል። በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

💚💛❤️አባቶች ከፖለቲ,ካ ውጡ ለሚሉ ሁሉ:- መጸሐፍ ቅዱስም ሆነ ሌሎች የቤተክርስቲያን ድርስናት እንደሚነግሩን የሰው ልጅ ከአዳም መውደቅ ጀምሮ ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ምድርን አርሶ እንስሳትንም አርብቶ ከመብላት ጀምሮ በምድር ሲበዛም የአኗኗር ዘይቤንና አስተዳደርን ህግና ስርዓት ዘርግቶ መኖር ጀምሯል:: በእግዚአብሔር የሚያምኑ ከህገ ልቦና እግዚአብሔርን ከማምለክ ጋር አያይዘው አስተዳደርን ዘርግተው እንደኖሩ ትውፊትም መጻፍትም ይናገራሉ:: በሗላም ህግ ከእግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት ከተሰጠ ጀምሮ እግዚአብሔርን ከማምለክ ጋር የተያያዘ ምድራዊ የአስተዳደር መዋቅር ነበር:: ከዚያም በተዋረድ የሰው ልጆች በምድር እየበዙ ሲሄድ በእግዚአብሔር በተመረጡና በእግዚአብሔር ህግ በሚመሩ ህዝብን ከባህል፣ ከመልካም እሴትና ከፈሪሃ እግዚአብሔር ሳያርቁ ለዘምናት መርተዋል:: በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን እንዳገኙ እንደ ዳዊትና ልጁ ሰለሞን የነበሩ እንዳሉ ሁሉ ከእግዚአብሔር መንገድ አርቀው ህዝብን የመሩ ከብሉይ እንደ ሳዖልና ናቡከደነጾር ሌሎቹም ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ በሗላም እንደ ሄሮድስና የመሳሰሉ መሪዎች ነበሩ አወዳደቃቸው የከፋ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል:: ከብሉይ ጀምሮ በሀድስ ኪዳን ኢትዮጵያ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በህገ እግዚአብሔር ህዝቦቿን እንዳስተዳደረች በታሪክ ይታወቃል:: ለዚህም አይነተኛው ምስክር ፍትሀ ነገስት ነው:: ይህም ደጋግ ነገስታት ህዝብን ሲያስተዳድሩበት የነበረ ነው:: ህዝብን ማስተዳደርና መጠበቅ በእግዚአብሔር ለተመረጠ ሰው ብቻና ብቻ ነው:: ከእግዚአብሔር ያልተመረጡ ሰዎች ህዝብን መምራት አይችሉም:: የህዝቡን መንገድ ጨለማና እልቂት ነው የሚያደርጉት:: ዓለም አሁን ያለችበት የምስቅልቅል ምስጢር ይህ ነው:: አሁን በተለይ የቤተክርስቲያን ሰዎች (አገልጋዮች) ምንም ህዝብን ማስተዳደር ላይ እንዳይሳተፉ ህዝብም ችግር ውስጥ ሲወድቅ እንዳይመለከቱ ለማድረግ የቄስ ፣ የመነኩሴ ፣ የጳጳስ ፣ የዲያቆን ወዘተርፈ ፖለቲከኛ እያሉ ያሳቅቃሉ:: እና ህዝብን ማስተዳደርና ለተበደለ ህዝብ መቆም የማን ስራ ነው? እንደ ቅዱስ ላሊበላ የመሳሰሉት ነገስታት ይችን ሀገር ጠብቀው ያቆዩልን እኮ እናንተ አሁን ፖለቲካ የምትሉት በአስተዳደር ነው! ቤተክርስቲያን እንድትደፈርና ምዕመናንም ጠበቃ አልባ ሆነው ያሉት በዚህ ምክንያት ነው:: እኛ አባቶች ህዝብን በምናድንበትና በምንጠብቅበት መንገድ ሁሉ መንቀሳቀስ ግድ ይለናል:: ወንጌልን ለተራበ ወንጌልን፣ የታመመን በመፈወስ፣ ያዘነን በማጽናናት፣ ሰላምን ያጣ ሰላምን በማጎናጸፍ ከሃይማኖት በዘለለ በማንኛውም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ሁሉ ህዝብን ማገልገል የአባቶች ስራ ነበር! ሐዋርያት፣ አበው መነኮሳትና ካህናት፣ ሰማዕታት፣ ቅዱሳን ነገስታት (ስልጣነ ክህነትና ስልጣነ መንግስትን አጣምረው ያገለገሉ) ሁላቸውም ለእውነት ኖረዋል እውነትን መስክረዋል ህዝብን በጽድቅ ጎዳና መርተዋል! በዚህ ዘመን ያሉ አብዛኛዎቹ አባቶች አይ እኔ ፖለቲካ ውስጥ አልገባም እያሉ ስንቶቹን አስበልተዋል? የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያን ሃይማኖት ተከታይ በመሆናቸው በስልጣን በማንኛውም ፖለቲካዊ ፓርቲ እዳይገቡ እንዳይንቀሳቀሱ ከገቡም ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ ይደረጋል:: ፖለቲ,ካ መር ግጭ,ት ሲነሳ እንኳን ሆን ተብሎ የሚጨፈጨ,ፈው ክርስቲያን እየተመረጠ ነው:: ስንቶቹ ተጨፉጨ,ፉ? ስንት ንዋዬ ቅዱሳት ተመዘበሩ? ስንት አብያተ ክርስቲያናት እንደ ጧፍ ነደ,ዱ? ስንቶቹስ ለስደት ተዳረጉ? ስንት መከ,ራ በቤተክርስቲያን ላይ መጣ? እኛ ግን አንቀላፍተናል:: ወዳጄ ንቃ አትሸወድ! አባቶች ሙሴን ፣ ዳዊትን ፣ አጼ ዘርዓ ያዕቆብን ፣ቅዱስ ላሊበላን ፣አራቱን ነገስታትና ሌሎች የቀድሞ መሰረቶቻችንን እንምሰል! ህዝብን እናድን ሀገርን እንጠብቅ! ይህ ሁሉ የታሪክ ክሕደት ሲፈጸም፣ ቤተክርስቲያን እና አማኝ እንዳይኖሩ ሲሰራ ዝም ብሎ የሚያይ አባት አባት አይደለም! አንዳንድ አባት ተብዬዎች ለህዝብ የቆሙትን በህዝብ ዘንድ እንዲጠሉ እያደረጉ ይህ ፖለቲካ ነው ኃጥአት ነው ወዘተ እያሉ መሰናከያም እያዘጋጁ ነው:: ሃይማኖትና ሀገር ሲጠፋ ክቡር የሆነውም የሰው ልጅ ሲጨፈጨፍና ሲሳደድ እየተመለከቱ ምንም ደንታ የሌላቸው አባቶች እግዚአብሔር ዋጋቸውን ይሰጣቸዋል ታሪክም ይፋረዳቸዋል:: የሚገርመኝ አዋቂ ነን የሚሉት የሀይማኖት አባቶች ሀገር በፖለቲካ ቁማር ተጨዋቾችና በሀገር አፍራሽ ወንበዶች ተወራ እየተበታተነች እያዩ ልባቸውን ያደነደኑ ፣እያወቁ የሚታለሉና ለከርስ ብለው ከሰይጣን ጋር የሚኖሩ ሆነዋል:: እነዚህ አባቶች ለራሳቸው ሲሉ ራሳቸውን ይፈትሹ ዘንድ እንመኛለን:: ለእውነት ቁሙ የዚህ ዓለምን ገዥ አትፍሩ! የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ መስቀል መሸከም አለብን! ለእውነት እንቁም! መታገል ያለብንን እንታገል፣ መገሰጽ ያለብንን እንገስጽ፣ ማጽናናት ያለብንን እናጽናና! "ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ እንገደ*ላለን፤ እንደሚታ,ረዱ በጎች ተቆጥረናል" እንደሚል መጽሐፍ አትፍሩ:: እኔ ሀገሬ ነጻ እስክትወጣ የሰው ልጅም ነጻነት እስኪረጋገጥ እታገላለሁ! አባቶች እንንቃ ህዝብን እንታደግ! ✍️ቆሞስ አባ ጳውሊ ከግንባር

ትልቁ ባንዳ በቆንጆዎች ተወገደ‼️‼️ ብልጽግና የሚሊሻዎች ዋና አዛዥ አይቸው ሙሉዓለም በአዳኝ ጀግኖቻችን ተወገደ ══════════🕊❁✿❁🕊══════════ (ጥር 30/2018 ዓ.ም፣ ዐፋብን 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት) ከውስጥ እና ከውጭ ያሉ አነፍናፊ ጦረኞቻችን ባደረጉት የተቀናጀ የምሽት ኦፕሬሽን በቋሪት ወረዳ የብልጽግና ሚሊሻዎችን በበላይነት በሚያስተባብረው ፶ አለቃ አይቸው ሙሉዓለም ላይ የማያዳግም እርምጃ ወሰዱ። ጥንቁቅና የታለመ ጥቃት /surgical strike/ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ኦፕሬሽን፣ ተቅበዝባዡን የብልጽግና ሥርዐት በመቅበር ሂደት ያሉ ውጤቶችን አመላካች ነዉ ተብሏል። በዚህ ፈጣንና ድንገተኛ ጥቃት #አይቸው ባልጠበቀበት ሁኔታ ጀግኖች ገበዘ-ማርያም ከተማ ከመኖሪያ ቤቱ ድረስ ዘልቀው በመግባት ነፍሱን ወደ coል ሸኝተው ወዲያውኑ ወጥተዋል። ሕይወቱን ለማትረፍ የተደረገው ርብርብ ሳይሳካ ቀርቶ እኩለ-ሌሊት አሸልቧል። #አይቸው_ሙሉዓለም የፋኖን ንብረት በመዝረፍ ለሚሊሻ ሲያከፋፍል የነበረ፣ የፋኖ ቤት እንዳይከራይ ሲያደርግ የነበር፣ የፋኖ ቤተስሰብ ሲያግትና ከፍተኛ ዝርፊያ ስሲፈፅም የነበረ ነው። ሚሊሻ አይቸው በንፁሃን ላይ ያለው የተዛባ አመለካከትና የሚወስደው ያልተገባ እርምጃ ይበልጥ ተተኳሪ እንዳደረገውም ተገልጿል። ይህ የብልጽግና ጠብ ደል መወገዱ ሌሎች ግለሰቡ ያስተባብራቸው የነበሩ አባላት ትክክለኛ ውሳኔ ለመወሰን ያስችላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። 🖊 የንፁሃን ደም ይፈርዳል‼

የጥንቃቄ መልዕክት! ​በአሁኑ ወቅት በመንግስት መከላከያ ሰራዊት በኩል እየታዩ ያሉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን የሚመለከት አስቸኳይ መረጃ፦ ​በምንጃር ሸንኮራ፣ በበረኸት፣ በአገረማርያም እና በአሳግርት
የጥንቃቄ መልዕክት! ​በአሁኑ ወቅት በመንግስት መከላከያ ሰራዊት በኩል እየታዩ ያሉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን የሚመለከት አስቸኳይ መረጃ፦ ​በምንጃር ሸንኮራ፣ በበረኸት፣ በአገረማርያም እና በአሳግርት ወረዳዎች የኔትወርክ አገልግሎት ተቋርጧል። ​ይህም የሆነው የአረመኔው ሰራዊቱ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ባለበት በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ በሄሊኮፕተር ጭምር የታገዘ ኃይል እየተከማቸ ይገኛል። ​ በአሁኑ ሰዓት ከአሳግርት በሁለት አቅጣጫዎች ወደ በረኸት ጉዞ ተጀምሯል። ​በሜጢ በኩል ​በፉራ፣ በምንታምር እና በማስፋት በኩል ​የፋኖ አመራሮች አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ፣ በፍጥነት እንድትናበቡና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ መልዕክቱ ይድረሳችሁ።

ባለሽርጡ ክፍለ ጦር የሃብሩ ወረዳ ካድሬዎችን ያጀበ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ጋር ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ:: የአገዛዙ ካድሬዎች ህዝብን በስብሰባ ለማደናገርና የሃሰት ቅስቀሳ ለማድረግ ብሎም ፀረ-ህዝብና አገር አፍራሽ ተልዕኳቸውን ለማስፈፀም ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ ልዩ ስሙ 032 ቀበሌ ኮሎቦ በብልፅግና መከላከያ ታጅበው ህዝብ ሊሰበስቡ ባሰቡበት ሁኔታ ከባለሽርጡ ክፍለ ጦር በደረሰባቸው ያላሰቡት ድንገተኛ ጥቃት ብትንትናቸው ወጥቶ ወደ መርሳ ከተማ ተመልሰዋል:: ባለሽርጡ ክፍለ ጦር ቀጠናውን በመቆጣጠር የህዝብ አስተዳደር መዋቅር ዘርግተው እያስተዳደሩት ያለ ሲሆን አገዛዙ ብልፅግና ምንም አይነት መፈናፈኛ እንዳያገኝ በማድረግና በተደጋጋሚ ጊዜ ክንዳቸውን በማቅመስ ዛሬም ድላቸውን አስቀጥለዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ትግላችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 29/ 2018 ዓ.ም

አፋብን በሁሉም አቅጣጫ ሰፊ ቀጠና ያካለለ አውደ ውጊያ እያደረገ ነው በዚህም እስካሁን ሰሜን ሸዋ, ምስራቅ ጎጃም, ምዕራብ ወሎ እና በጎንደር አንዳንድ አካባቢዎች የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት የ
አፋብን በሁሉም አቅጣጫ ሰፊ ቀጠና ያካለለ አውደ ውጊያ እያደረገ ነው በዚህም እስካሁን ሰሜን ሸዋ, ምስራቅ ጎጃም, ምዕራብ ወሎ እና በጎንደር አንዳንድ አካባቢዎች የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋርጠባቸው ቀጠናዎችም አሉ በመላው አማራ ግዛት 24 ስዓት ፍኖተ-አማራ መርጃዎችን ጎልልጉላ እየሰራች ትገኛለች ።

መረጃ! በአማራ ግዛት ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ ጎጃምና ምዕራብ ወሎ አካባቢዎች የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል። በተለይም በይፋት፣ መንዝ፣ መርሐቤቴ፣ ወግዲ፣ ከላላ፣ ሸበል በረንታ፣ ደጀንና ባ
መረጃ! በአማራ ግዛት ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ ጎጃምና ምዕራብ ወሎ አካባቢዎች የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል። በተለይም በይፋት፣ መንዝ፣ መርሐቤቴ፣ ወግዲ፣ ከላላ፣ ሸበል በረንታ፣ ደጀንና ባሶ ሊበን ገጠራማ አካባቢዎች አገልግሎቱ መቋረጡ ታውቋል።

የጠላት እንቅስቃሴ መረጃ !! የጠላት ኃይል መነሻው ከአዲስ አበባ ጦር ሀይሎች በማድረግ 25 ተሳቢ ደጀን እየገቡ ሬሽን እና የህክምና ቁሳቁስ ፣የመድፍ እና የሞርተር ተተኳሽ የጫኑ 2 ኦራል ሀይል የ
የጠላት እንቅስቃሴ መረጃ !! የጠላት ኃይል መነሻው ከአዲስ አበባ ጦር ሀይሎች በማድረግ 25 ተሳቢ ደጀን እየገቡ ሬሽን እና የህክምና ቁሳቁስ ፣የመድፍ እና የሞርተር ተተኳሽ የጫኑ 2 ኦራል ሀይል የጫነ፣10 ባለስጣን የያዙ ኮብራዎች 5 ብሬን የጠመዱ ፓትሮሎች ፣እና 4መድፍ በመያዝ ደጀን ከተማ ገብቷል።

አሁን ከመሸ 1:00 ጀምሮ በመላው ሽዋ ድሮኖች አሰሳ እየተደረገ ነው። እንደሚታወቀው አረመኔው አብይ አህመድ ብዙህ ኃይል ሸዋ እንዳስገባ የሚታወቅ ሀቅ ነው የተወሰኑ የሽዋ ቦታዎች ኔትወርክ ሰለጠፋ
አሁን ከመሸ 1:00 ጀምሮ በመላው ሽዋ ድሮኖች አሰሳ እየተደረገ ነው። እንደሚታወቀው አረመኔው አብይ አህመድ ብዙህ ኃይል ሸዋ እንዳስገባ የሚታወቅ ሀቅ ነው የተወሰኑ የሽዋ ቦታዎች ኔትወርክ ሰለጠፋ ለመላው ፋኖ መረጃው እንዲደርስና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲደርግ። መረጃውን ለመላው ህዝባችን ሸር አድርጉ። አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ሰበር ሰበር ዜና !!! ነቀርሳ ነፍሰ በላ ተሸኘ !!! ሰዉየዉ #አሸናፊ ይባላል፣ በጃዊ እና ፓዊ ቀጠናዎች እየተንቀሳቀሰ #በብልፅግና ድጋፍ እና ሽፋን ሰጭነት በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ግፍ እና በደ
ሰበር ሰበር ዜና !!! ነቀርሳ ነፍሰ በላ ተሸኘ !!! ሰዉየዉ #አሸናፊ         ይባላል፣ በጃዊ እና ፓዊ ቀጠናዎች እየተንቀሳቀሰ #በብልፅግና ድጋፍ እና ሽፋን ሰጭነት በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ግፍ እና በደል ሲፈፅም የነበረ፣ ህዝቡን የደም እንባ ሲያስለቅስ የኖረ አረመኔ የመንግስት ተላላኪ ቅጥረኛ በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር በእሳት ነበልባሏ 3ኛ ሻለቃ እርምጃ ተወስዶበታል። በ2016 ዓ.ም ሚያዚያ ወር ላይ ወርቅ ሜዳ ከፋኖ ከድቶ ወደ ብልፅግና የገባ ሲሆን አንድ ሴት ገድሎ እንደገና ወጥቶ የመንግስት መረጃ በመሆን ከመከላከያ በቅርብ እርቀት ሆኖ ህዝቡን ሲዘርፍ የነበረዉ  ሌባ አሸናፊ በዛሬዉ እለት እስከ ወዲያኛው ተሸኝቷል። የያዘዉ #ስናይፐርም በፋኖ እጅ ገብቷል። ህዝቡም የደስታ ስሜቱን አንፀባርቆ ለጀግናው ፋኖ ያለዉን ክብር የበለጠ ያሳየበት እና ድጋፍ ያደረገበት ድንቅ ተዓምር ነበር። አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!! ©ያእቆብ ጌታሁን

የአረመኔው አራዊት - ሰራዊት አውዳሚ ሰራዊት የሲቪሊያንን ቤት አቃጠለ !!! 29/05/2018 ዓ.ም ➯አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለጦር ቀጠና የአረመኔው ሰራዊት በተደጋጋሚ ጊዜ ንፁሀንን ያነጣጠረ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል ። የፋኖ ደጋፊ በሚል ስበብ በህዝባችን ላይ ግድያ የጅምላ ግድያና ሀብት ንብረት የማውደም ተግባራትን ለተከታታይ እየፈፀመ ባለበት በዚህ ወቅትም በዛሬው ዕለት በቀን 29/05/2018 ዓ,ም በይልማና ዴንሳ ወረዳ ጎሸየ ቀበሌ ነዋሪ እና የጎሽዬ ሀና ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆቱት ቄስ ሀይማኖት ገበይን ቤት ከቀኑ 6:00 ሠዓት አቃጥሎታል ። በእሳት ቃጠሎው የወደመ ሀብት ንብረትም 1,ሙሉ የቤት እቃ 2,የቤተ ክርስቲያን ንዋየ ቅዱሳትና ከ100ሽ ብር በላይ የቤተክርስቲያኒቱን ጥሬ ገንዘብ ከተቀመጠበት ካዝና በመስበር 3,ከ100 ኩንታል በላይ እህል 4,ሁለት(2) ክበድ የሆኑ የፈረጅ ላምና አንድ የፈረንጅ በሬ በድምሩ 700,000ብር የሚያወጣ ንብረት ላይ ዘረፋ በመፈፀም በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ሽብር እየፈፀመ ይገኛል። ይህ አረመኒያዊ ሥርዓት በጅምላ በመግደል ያልቀለበሰው የህልውና ትግላችን ሀብት ንብረት በማውደም እንደማይገታ እራሱም ያቀዋል ። ስርዓቱ ከውልደቱ ይዞት የተፈጠረ ፀረ ሰው ተግባሩን ይዞ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከአማራ ህዝብ ብሎም ከኢትዮጵያ ህዝብ ትክሻ ወርዶ ይቀበር ዘንድ እንበርታ ። ክፋት ለማንም!በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

በአውደ ውጊያ በፋኖ የተሸነፈው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ወግዲ ወረዳ ከ35 በላይ ንፁሃኖችን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ:: በጀኔራል አድማሱ አለሙ እና በጀኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ የሚመራው 11ኛ ዕዝ እና ቀጠናው ላይ የተሰማራው ሪፐብሊካን ጋርድ ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ከንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ከባድ ተጋድሎ ገጥሟቸው ለጊዜው በስም ያልታወቁ ከፍተኛ የብልፅግና መከላከያ አመራሮችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠር ሰራዊቱ ያለቀበትና በመቶዎች የቆሰለበት ሲሆን አስከሬንና ቁስለኛውን በሄሊኮፕተር ወደ ኮምቦልቻ እና አዲስ አበባ ሲያመላልስ ከርሟል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም ዛሬ ጥር 29/2018 ዓ.ም አራተኛ ቀኑን በያዘው ከባድ ውጊያ የአገዛዙ ብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ከባድ መሳሪያ በማስወንጨፍ በርካታ ንፁሃን የጨፈጨፈ ሲሆን ወግዲ ወረዳ ጎረንጅ 016 ቀበሌ ብቻ ስድስት የአንድ ቤተሰብ አባላት በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ ሞተዋል:: በተመሳሳይ በዚሁ በጎረንጅ 014 ቀበሌ አንድ መኖሪያ ቤት ላይ ባረፈ ከባድ መሳሪያ አባት ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ እናትና ልጅ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል:: የምኒልክ ዕዝ ከፍተኛ አመራር የሆነው አርበኛ ሻለቃ ሃብታሙ ደምሴ ቤተሰቦች መኖሪያ የሆነች መንደር ላይ ብቻ ከ54 ጊዜ በላይ ከባድ መሳሪያ አስወንጭፎ ከባድ ውድመት አድርሷል:: ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ወግዲ ወረዳ በግፍ የጨፈጨፋቸው ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ አማራዎች ስም ዝርዝር፦ •የተሰው ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ አማራዎች 1.አለሙ ጌታሁን 2.አህመድ ደረሰ 3.አታላይ መንገሻ 4.አቡሽ አሸብር 5.አረቡ ሙህዬ 6.አየሉ ቡሽራ 7.አብርሃም አሸብር ናቸዉ። •ቀላልና ከባድ ቁስለኛ የሆኑ ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ አማራዎች 1.አህመድ ሻረዉ 2.ሰይድ አህመድ 3.አሊ ሻረዉ 4.ሙስጠፋ አህመድ 5.የሱፍ ብርቁ 6.ሁሴን ረምረም 7.ደሴ እንድሬ 8.አሸብር ጌታሁን 9.አስካል ፈለቀ 10.ሙሃመድ አህመድ 11.መካ ሙሃመድ 12.አረጋሽ ካሳዉ 13.ጦይባ አደም 14.ሙሃመድ ሰይድ 15.አህመድ አሸብር 16.አሚናት አለሙ 17.ተጓዴ ሃምዛ 18.እንድሪስ አለሙ 19.ሙሃመድ ደረሰ 20.ሙሃመድ አብዱ 21.አደም ሙህዬ 22.የሱፍ ጌታሁን 23.ኢዘድን የሱፍ 24.ከሪማ ሰይድ 25.ይማም አሸብር 26.ነኢማ አህመድ 27.አህመድ አረቡ 28.ፋኢዛ ሰይድ በግፍ ከተጨፈጨፉት ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ አማራዎች በተጨማሪ ከአርባ በላይ ቤቶች በፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ከባድ መሳሪያ ተቃጥለዋል:: *የተንቀሳቃሽ ምስል እና ምስል ማስረጃዎች እንደደረሰን የምናጋራ ይሆናል:: ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 29/2018 ዓ.ም

ሸዋ አካባቢ መረጃ❗️ ኦሄዴድ/ብልፅግና  ከዚህ ቀደም  በሸዋ ቀጠና :- 1: የሪፐብሊካን ጋርድ 2 ክፍለጦሮች 2: የአየር ወለድ እና ኮማንዶ  6 ክፍለጦሮች 3:- የባህር ኃይል ኮማንዶ 1 ክፍለጦር 4:- የ6ኛ ዕዝ አካል የሆኑ  እግረኛ ሁለት ክፍለጦሮች በለሚ እና በጅሩ በኩል። እንዲሁም ከአድማ ብተና እና ሚሊሻ አሰማርቶ የነበረ ቢሆንም ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ  በቀጠናው የስልክ ኔትወርክ በማጥፋት :- ~>  ናዝሬት ይገኝ የነበረውን የደቡብ ዕዝ አንድ ኮር ከ3ኛ መካናይዝድ ጋር በማቀናጀት በአፋር ዞሮ በከሚሴ በኩል ወደ ሸዋ ቆላማ ቦታዎች ~> የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ፅንፈኛ ታጣቂዎችን ጨምሮ የብሄረሰብ ዞኑን ሚሊሻዎች ወደ ራሳ፣ ቀወት፣ኤፍራታ ግድም እና ማጀቴ አካባቢ ሰምሪት ሰጥቶ እያንቀሳቀሰ ይገኛል።   ይሄ ተስፋ የቆረጠ ቡድን የአፋብን ከፍተኛ አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ፍላጎት ቢኖረውም፤ ፅንፈኛ የብሄረሰቡ ታጣቂዎችን በመጠቀም  ህዝብን ለማጎሳቆል ጨምሮ ድርብርብ ዓላማ ያለው በመሆኑ የአፋብን ሠራዊት እና ህዝቡ  ተገቢው ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል!

በ7ኛው ዙር ምርጫ ተሳትፎየን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ለተከበራችሁ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች፣ ለመላው የአማራ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በሙሉ፦ ባለፉት ዓመታት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ በኩሩው የባሕር ዳር ከተማ ሕዝብ ተመርጨ፣ እናንተን ወክዬ፣ ለሕዝባችን ሀቀኛ ድምፅ በመሆን ለማገልገል በመቻሌ ታላቅ ክብርና ኩራት ይሰማኛል። በዚህ ጉዞዬ ላሳያችሁኝ ያልተቆጠበ ድጋፍ፣ ፍቅር፣ አክብሮት እና ጽኑ እምነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በአሁኑ ወቅት ለ7ኛው ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ የእጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ እየተከናወነ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በመራጮቼ፣ ደጋፊዎቼ እና በሚዲያዎች ዘንድ በዕጩነት መመዝገብ አለመመዝገቤን በተደጋጋሚ ስጠየቅ ቆይቻለሁ። አንዳንድ ፓርቲዎችም ባሕር ዳርም ሆነ አዲስ አበባ በፈለግሁበት ቦታ በእጩነት እንድቀርብ እድሉን ሰጥተውኝ ነበር። በግልም የመወዳደርን አማራጭ በጥልቀት አስቤበታለሁ። ሆኖም ግን በመጪው 7ኛው ዙር ምርጫ ራሴን በዕጩነት ላለማቅረብ መወሰኔን ለሕዝቤ ይፋ ማድረግ እፈልጋለሁ። ለዚህ ውሳኔ ያበቃኝ ዋነኛው ምክንያት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ካለው ተጨባጭ ነባራዊ  ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው። ነፃ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ መደላድል አለመኖሩ እና በፖርላማ ውስጥ ተጨማሪ 5 ዓመታትን በመቆየቴ ለህዝቤ የሚያበረክተው የረባ ጥቅም የሌለው መሆኑንም ተረድቻለሁ። ስለዚህ የ6ኛው ዙር ፓርላማ እስኪጠናቀቅ ድረስ ባሉት ጥቂት ወራት የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደራሴነት ስራየን ቀጥየ ሰኔ መጨረሻ ላይ የዚህን ዙር የአገልግሎት ዘመኔን የማጠናቅቅ ሲሆን፤ ወደፊት ሀገሬን እና ህዝቤን እንዴት ለማገለግል እንደምፈልግ የማሳውቅ ይሆናል። እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ በጽናት አብራችሁኝ ለቆማችሁ ቤተሰቦቼ፣ ጓደኞቼ፣ ውድ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች፣ ለአማራ ሕዝብና ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ምስጋናዬ የላቀ ነው። እግዚአብሔር ይባርካችሁ፣ ህዝባችንን እና ሀገራችንም ይጠብቅልን! ደሳለኝ ጫኔ ዳኜው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል

አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ አሳምነዉ ኮር እሸት ክፍለ ጦር ከአዉደ ዉጊያ ጎን ለጎን ጥልቅ ተሐድሶ አደረገ!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)  ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር የሚገኘው እሸት ክፍለ ጦር ለተከታታይ ሶሰት ቀናት በጥልቀት ከገመገመ በኋላ ሁሉን አቀፍ ተሐድሶ ካደረገ በኃላ የአመራር ሪፎርም ስራ ሰርቷል ። በተሐድሶው ላይ የተገኙት የምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ  አርበኛ ወንድሙ ማሩ ፣የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስትራቴጅክ ጉዳዮች ኃላፊ አርበኛ ተመቸ ቢራራ እና ሌሎች የኮር አመራሮች ተገኝተዉ ለሰራዊቱ አቅም ግንባታና ማበረታቻ የሰጡ ሲሆን ሰራዊቱም የነበሩባቸውን ጥቃቅን ክፍተቶች እንደሞሉበት ታውቋል። እሸት ክፍለ ጦር ወቅቱን የዋጄ በግዳጅ አፈፃፀም የላቀ ሰራዊት እየገነባ ያለ ክፍለ ጦር ሲሆን ከተራ ተዋጊ አባል እስከ ክፍለ ጦር መሪ ቅልቅልና አዲስ አደረጃጀት በመስራት ለቀጣይ ግዳጅ በወትሮ ዝግጁነታቸው እንደሚገኙ አስታውቀዋል። በመጨረሻም የተመደቡት  አመራሮች  ይህን የተጣለብነን አደራ በአግባቡ ተወጥተን የአማራን ህዝብ የተደቀነበትን የህልዉና አደጋና ዘርፈ ቡዙ ችግሮች አላቀን አማራ በማንነቱ እማይሸማቀቅበት እና ሁሉን አካታች ይምትሆን ሀገረ መንግስት እንደምንገነባ ቃል እንገነባለን ሲሉ ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። በዚህ ጥልቅ ተሐድሶ የክፍለ ጦሩ አመራሮች እንደሚከተለዉ ተዘርዝረዋል። 1.የክ/ጦር አዛዥ..... መቶ አለቃ በሪሁን ደምሌ 2. የክ/ም/አዛዥ ..... አርበኛ ፍቃድ አበባዉ 3. የክ/ጦር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ.......አርበኛ ደሰላ ወንዴ 4. የክ/ጦር ወታደራዊ  አስተዳደር ኃላፊ.........10 አለቃ  አንደበት ወንድምነዉ 5. ዘመቻ ኃላፊ.............አርበኛ ኮስትር አሸነፍ 6 .  ሕ/ግንኙነት ኃላፊ......... መቶ አለቃ ደስታዉ አንባዉ 7. ፋይናስ አርበኛ ዮሐንስ አዱኛዉ (ጆን) 8.  የሰዉ ሃይል አርበኛ ቡግሳ ተስፋ 9.  ስልጠና ክፍል ኃላፊ ......አርበኛ ጌትነት አለምነዉ 10.  ሎጀስቲክ  ኃላፊ.......አርበኛ እያያዉ ደረሰ 11. ህግ ክፍል  ኃላፊ.........አርበኛ ጌታሁን ወዳይ 12.  ጤና መምሪያ ኃላፊ......አርበኛ አበበ ሞላ 13. መረጃና ደህንነት         .............. አርበኛ XXXX የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 29/2018 ዓ.ም