ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅 👈

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
3 954
订阅者
+22224 小时
+3937 天
+1 35930 天
帖子存档
አስማረ ፀጋ ከደብረ ማርቆስ ከተማ የጋንታ መሪውን ክላሽ ማርኮ 206ኛ ኮርን ተቀላቀለ። 206ኛ ኮር ጥር 30/2018 ዓ.ም ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, አስማረ ፀጋ በደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪ ሲሆን የትግሉን የእድገት ከፍታ የፋኖ ጠንካራ እንቅስቃሴ በፈጠረበት እልህና ወኔ ይህ 23 አመቱ ወጣት ከጠላት ክላሽ ማርኮ ትግሉን ለመቀላቀል ምቹ ሁኔታ ሲጠባበቅ ከቆየ በኋላ በዛሬው ዕለት የአድማ ብተና ጋንታ አዛዥ የነበረውን ደልዳላው ሞላን ማንጅራቱን መቶ ክላሹን ማርኮ 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦርን ሲቀላቀል ደማቅ የጀግና አቀባበል ተደርጎለታል። በአረመኔው ሰራዊት ንፁሃን ሲገደሉ ፣ ወጣቶች በጅምላ እየታፈሱ ሲታሰሩ ተመልክቻለው ያለው አስማረ ፀጋ የሴትነት ክብራቸው ተገፎ በአብይ አህመድ ሰራዊት የተደፈሩ እህቶቸን ህመም ለመበቀል ተዘጋጅቻለሁ ሲል ተናግሯል። በመልሶ ማደራጀት ትግበራው የአረመኔውን ሰራዊት በስቦ ማስከዳት ከ72 በላይ ክላሽ ያገኘው 206ኛ ኮር በደብረ ኤልያስ፣ ሉማሜ፣ ቁይ፣ ደብረ ማርቆስ ከተሞች በመሸገው የጠላት ኃይል ላይ ተናጥላዊ ጥቃት ፈፅመው ትግሉን የሚቀላቀሉ ወጣቶችን በማበረታታትና እውቅና በመስጠት ኮሩ በርካታ ወጣቶችን በጀግንነት እየተቀበለ በመሆኑ የጠላትን ትጥቅ ታጥቀው ትግሉን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑም ተገልጿል። አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ፀረ ዕምነቱ የብልፅግና ሥርዓት  ቄሱን በግፍ ገደላቸው !! ቀን 30/05/2018ዓ,ም የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለ ጦር ቀጠና ጨፍጫፊው ስርአት ካህኑን ቀጥቅጦ ገድሏቸዋል ። 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለ ጦር ባህርዳር ዙርያ ወረዳ አንዳሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ቄስ ሻረው አምበሉ የተባሉ ካህንን በቀን 29/05/2018ዓ,ም ከነ ልጃቸው  ግፍ ፈፅሞባቸዋል ። የአይን እማኞች እንደነገሩን                👇🏻 ከቀናት በፊት ልጃቸውን ምክንያቱ ባልታወቀ ጉዳይ ጠላት አስሮት የነበረ ሲሆን ካህኑ ልጃቸው ወደ ታሰረበት ቦታ ለመጠየቅ ሲሄዱ ልጃቸው በጠላት ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመበት ይደርሳሉ ። ወላጅ አባት ልጃቸው ወደ ታሠረበት ግቢ ዘልቀው ሲመለከቱ አረመኒ የስርአቱ ቅጥረኛ ሀይል ልጃቸውን በጩቤ ሲወጋው በአይናቸው ተመለከቱ ። ይሄን ስሜት መቋቋም ያልቻሉ ወላጅ አባት በቀጥታ በጩቤ ሲወጋው ሲመለከቱ  ኧረ ልጀን ብለው ወደ ልጃቸው ተወረወሩ ከጀርባቸው በኩል አንድ የስርአቱ ቅጥረኛ ጭንቅላታቸውን በፍልጥ እንጨት ደጋግሞ መታቸው ወደቁ ከወደቁበት ሳይነሱ እስከ ወዲያኛው አሸለቡ ። ካህኑ በዚህ መልኩ በግፍ ተገድለው በጩቤ የተወጋው ልጃቸው ሆስፒታል ገብቶ እየታከመ ይገኛል ። አንዳሳ ጊዮርጊስ ፀበል በብዙ አስር ሺወች የሚቆጠሩ ህሙማን የሚገኙበትና የሚፈወሱበት ፀበል ነው ። ካህኑ ላይ ያነፃፀረው ይህ ጥቃትም እምነት ተቋማትን እና  ህዝብንም አለኝታ ማሳጣትን አላማው ያደረገ ተግባር ነው ። ይህ ሥርዓት ከመንግስትነት ወደ ተራ ውርጋጥነት የመቀየሩ ማረጋገጫ ጭምር ነው ። ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም !! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ተመከረች እምቢ አለች ቀመሰች 😂 😂 ይቺን የፍኖተሰላም ሚሊሻ ፅ/ቤት ሀላፊ የነበረች ሰውዬ ቆንጆዎቹ ጎብኝተዋት ባህርዳር ሆስፒታል እየታከመች ነው። ሌሎቻችሁም ሳይረፍድ ለፋኖ እጅ ስጡ
ተመከረች እምቢ አለች ቀመሰች 😂 😂 ይቺን የፍኖተሰላም ሚሊሻ ፅ/ቤት ሀላፊ የነበረች ሰውዬ ቆንጆዎቹ ጎብኝተዋት ባህርዳር ሆስፒታል እየታከመች ነው። ሌሎቻችሁም ሳይረፍድ ለፋኖ እጅ ስጡ

በምዕራብ አማራ ቀጠና ምዕ/ጎጃም ዞን ወምበርማ ወረዳ ሽንዲ ከተማ ዙሪያ ቀበሌዎች የአገዛዙ ሠራዊት የአርሶ አደሮችን ንብረት ዘረፈ! *** ጥር 28 እና 29/2018 ዓ.ም ወምበርማ ወረዳ ሽንዲ ከተማ የመሸገው የአገዛዙ ዘራፊና ጨፍጫፊ ሠራዊት ወደ ዙሪያ ቀበሌዎች ቡራፈር እና ሻምብላ ከሌሊቱ 10 ሠዓት ጀምሮ እኩይ የጥፋት  አላማ አንግቦ ተንቀሳቅሷል። ይህ ዘራፊ የአገዛዙ ሠራዊት አማራን ዘር ከማጥፋት በዘለለ ሐብት ንብረት መዝረፍ፤ ለመዝረፍ ያልተመቸውን ማውደም በመላ አማራ የሚፈፅመው ነውር የሆነ የዘወትር ድርጊቱ ነው። ጥር 28/2018 ቡራፈር ቀበሌ አርባገል ጎጥ ከንጋቱ 11:30  አካባቢ የአቶ አለማየሁ አዳነ መለሰን ቤት ሰብሮ በመግባት ከአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በብድር የተገዛ ሶላር ባትሪ እና ከባለቤቱ አንገት ላይ አንድ ጠገራ ብር ቆርጦ የወሰደ ሲሆን የአቶ ጌታሰው ምንባለ አጉማስን ቤት እንዲሁ በመስበር የልጁን ስማርት ተች ስልክ ነጥቀዋል። ጥር 29/2018 ዓ.ም  ወደ ሻምብላ ቀበሌ ተንቀሳቅሶ የወ/ሪት እብስቴ ትጋረድ ዴሶን ቤት ሠብሮ 19,000 /አስራ ዘጠኝ ሽህ ጥሬ ብር እንዲሁ ዘርፏል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ጥር 30/2018ዓ.ም

👉አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች የሚደረጉ የአባት አርበኛ የውይይት መድረኮች ተጠናክረው ቀጥለዋል!!! ጥር 29/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች ውስጥ የጃቢጠህናን ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት ከአባት አርበኞች ጋር የሚያደርገው የውይይት መድረኮች ተጠናክረው ቀጥለዋል። በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እየተደረገ በሚገኘው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ውስጥ አባት አርበኛው ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። የጃቢጠህናን ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት ከሚያስተዳድራቸው( 38) ቀበሌወች መካከል ከ(5) ቀበሌ ማለትም ከቡጊ ጎሸፈጂ፣ከየራበር ግርግሪያ፣ከወንጌ በርቀኝ፣ከራዶስ አቅላትና ከበርቀኝ በረቨይ ቀበሌ የአባት አርበኞች ጋር ሰፊ የውይይትና የግምገማ መድረክ ተደረጓል፡፡ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስረታ፣የትግሉ ወቅታዊ ቁመና በተጨማሪም የፋኖ ትግል የደረሰበትን ደረጃና እያስመዘገባቸው የሚገኙትን እምርታዎች እንዲሁም ትግላችንን ከግቡ ለማድረስ ከአባት አርበኛው ምን ይጠበቃል በሚሉ መሠረታዊ ነጥቦች ዙሪያ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ተሰጧል፡፡ በተነሱ የግልጸኝነት አንዳንድ ጥያቄዎች ዙሪያ በክ/ጦሩ አመራሮችና በጃቢጠህናን ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በመጨረሻም የቀጣይ አቅጣጫወችን በማስቀመጥ የዕለቱ ፕሮግራም በሰላም ተጠናቋል። 👉መረጃው የአፋብን ቴውድሮስ ዕዝ፣ 109ኛ ኮር፣ 77ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ነው!! አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ጥር 30/2018ዓ.ም

የቆራጥነት ተምሳሌት፣ የቁርጥ ቀን ልጅ፤ ሜጀር ጀነራል ኪኒ ማሓይ። ለቃሉ የታመነ 'የምሬ' ወንድም፣ ለዓላማው የማይደራደር ሞት አይፈሬው ጀግና!" ​ ​ሞት የማይገታው ወኔ፣ ቃላት የማይገልጹት ታማኝ
የቆራጥነት ተምሳሌት፣ የቁርጥ ቀን ልጅ፤ ሜጀር ጀነራል ኪኒ ማሓይ። ለቃሉ የታመነ 'የምሬ' ወንድም፣ ለዓላማው የማይደራደር ሞት አይፈሬው ጀግና!" ​ ​ሞት የማይገታው ወኔ፣ ቃላት የማይገልጹት ታማኝነት! ሜጀር ጀነራል ኪኒ ማሓይ ማለት በሥራው ጀግና፣ በልቡ ወንድም፣ በወኔው ደግሞ የሞት ጥላ የማይበግረው የአማራው ጀግና ይህ የአማራ የነፃነት ትግል ከጀመረ ጀምሮ የአብይ አህመድ አረመኔዊ ሰራዊት አንድ የሻለቃ አናብስቶች ብቻውን ይዞ በጎጃም፥በወሎ፥በሽዋ፥በጎንደር ፥ አዋጊ ተዋጊ ባለውለታ

እኛ አማራዊያን አሸናፊዎች ነን ደግሞም እንሆናለን ፍኖተ አማራ ሚዲያ አሁን ላይ መሬት ላይ ያለውን የአገዛዙ መርጃዎች ከሔት ወደ ሔት የሚለውን እንቅስቃሴዎች ከትግል ጓዶቸ ጋር ሁኘ እየሰራሁ እገኛለሁ ከተወሰነ ስዓት በኃላ ጠቅለል ያለ መርጃዎች ይዠ እመለሳለሁ በሽዋ በጣም ብዙህ በወሎ በጣም ብዙህ እንዲሁም በጎንደርና በጎጃም እንዲሁ ኃይል አስገብቷል ምን ይመስላል የሚለውን ሙሉ መርጃዎች ይዠ እመለሳለሁ!! መረጃዎች እንዲደርሱ ሸርና ጆይን በማድርግ ይወዳጁን

ለተከታታይ አራት ቀናት በተደረገ ውጊያ 171 የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ተደረጉ! በቋራ ግንባር አባድግሱ ተብሎ የሚጠራው አከባቢን ጨምሮ ጋዝጌ እና ባርባስ እንዲሁም በአዳኝ አገር ጫቆ ደግሞ ነጋዴ ባህር ከተማ አከባቢ ነው ባለፉት አራት ተከታታይ ቀናት ከባድ ውጊያ የተደረገው። በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሰሜን አማራ ቀጠና ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዕዝ ስር የሚገኘው ግዙፉ መይሳው ካሳ ኮር ከጥር 26/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ትናንት ጥር 29/2018 ዓ/ም ረፋድ ድረስ ባደረገው ተጋድሎ የጠላት ብልፅግና ወታደሮችን አከርካሪ በመስበር አንፀባራቂ ድል ማስመዝገቡን መረብ ሚዲያ ከዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል። ጥር 28/2018 ምሽት ጀምሮ እስከ ትናንት ረፋድ ድረስ በቋራ ወረዳ አባድግሱ ተብሎ በሚጠራው ቀጠና የጠላት ብልፅግና ወታደሮች በፋኖ 360° ድግሪ ተከበው ከባድ የሆነ ሰብአዊና ቁሣዊ ካሳራን ተከናንበዋል። የፋኖ የማጥቃት አቅም በምን ያህል ደረጃ እንዳደገ በታየበት በዚህ የቆረጣና የከበባ ማጥቃት፡ 36 ወታደሮች ሲገደሉ 45 ወታደሮች ደግሞ ክፉኛ ቆስለው በሞትና በሕይወት መካከል እንደሚገኙ ታውቋል። በውጊያው ከተገደሉት የአገዛዙ ወታደሮች መካከል የሃምሳ አለቃ ማዕረግ ያለው መስመራዊ አዋጊና ሌሎች የሬጅመንት አመራሮች እንደሚገኙበት ዕዙ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል የገለፀው። በዚህ ተጋድሎ አንድ የዶሽቃ አፈሙዝን ጨምሮ 12 ክላሽንኮቭ መሣሪያ እና 650 የክላሽ ተተኳሽ በፋኖ ቁጥጥር ስር ውሏል። በቀጠናው በተመሣሣይ ጋዝጌ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ልዩ ስማቸው ሮቡዕ ገበያና ኤፈርት ተብለው በሚጠሩ አከባቢዎች በተደረገው ተጋድሎ 30 የፀረ አማራው ብልፅግና ወታደሮች ሲገደሉ ሌሎች 30 ወታደሮች ደግሞ ቆስለው በአከባቢው ወደሚገኝ ጤና ተቋም መወሰዳቸውን ነው መረብ ሚዲያ ከዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ የቻለው። በተጋድሎው 10 ክላሽንኮፍ መሣሪያን ጨምሮ ከ3 ሺ በላይ ተተኳሽና ሌሎች ወታደራዊ ግብአቶች በፋኖ ተማርከዋል። በተመሣሣይ በዚኸው ግንባር ከአባድግሱ ወደ ባርባስ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ በተከፈተ ጥቃት አምስቱ ወዲያውኑ ሲገደሉ 12ቱ ደግሞ መቁሰላቸው ተረጋግጧል። ከቋራ ወረዳ በተጨማሪ በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ በተደረገ ተጋድሎ፡ ፋኖ በጠላት ላይ ፈጣን የፀረ ማጥቃት እርምጃ በመውሰድ ይዞታዎችን አስከብሮ ድል ተቀዳጅቷል። በዚህ ቀጠና ለጠላት መንገድ መሪ በመሆንና የፋኖ ደጋፊ ናቸው በሚል ንፁኋንን በማስገደልና በማሳሰር እኩይ ድርጊት ላይ ተሰማርቶ የነበረ አንድ ባንዳን ጨምሮ አምስት የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ፡ ስምንቱ ደግሞ ቆስለዋል፡ አምስት ክላሽንኮፍ መሣሪያ ከነ ተተኳሹ በፋኖ ቁጥጥር ስር ውሏል። በበላይ ዘለቀ ዕዝ ስር የመይሣው ካሳ ኮር ሰራዊት ከጥር 26/2018 ዓ/ም ጀምሮ በቋራ እና በአዳኝ አገር ጫቆ ግንባር ላለፉት አራት ቀናት ባደረገው ተጋድሎ በድምሩ 76 የአገዛዙ ወታደሮችን ሲገድል፡ 95 ወታደሮችን ደግሞ ማቁሰሉን ነው ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ከዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ የቻለው። በተጋድሎው ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮኛ ከተደረጉ ወታደሮች በተጨማሪ አንድ የዶሽቃ አፈሙዝ እና 27 ክላሽንኮቭ መሣሪያ፣ 4ሺ የሚደርስ ተተኳሽና ሌሎች ለትግሉ ግብአት የሚሆኑ ወታደራዊ ቁሳቁሶች በፋኖ ቁጥጥር ስር ውለዋል። አገዛዙ በቀጠናው የኔትዎርክና የመብራት አገልግሎቶችን በማቋረጥ በበርካታ ከባባድ መሣሪያዎች ታግዞ ተኩስ የከፈተ ቢሆንም፡ ነገር ግን ከወደ ፋኖ የተወሰደበትን አፀፋዊ የፀረ ማጥቃት እርምጃን መቋቋም አቅቶት ቆሞ መዋጋት እስኪያቅተው ድረስ ተሽመድምዶ ቀጠናውን ለቆ ወጥቷል።

ከአዉደ ዉጊያ ጎን ለጎን የሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር በመቄት ጥልቅ ተሐድሶ አደረገ!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳ
+2
ከአዉደ ዉጊያ ጎን ለጎን የሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር በመቄት ጥልቅ ተሐድሶ አደረገ!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር የሚገኘው ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር በመቄት ከጥር:-26 ጥር:- 28/05/2018 ዓ/ም ለተከታታይ ሶሰት ቀናት በጥልቀት በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል ። በተሐድሶው ላይ የተገኙት የሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍለጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ አማን ጎበዜ ፣ምክትል አዛዥ አርበኛ ሸጋው ወርቄ ጉድለቶቻችን በማረም ቀጣይ ግዳጆችን በብቃት መፈፀም አለብን ብለዋል። የወረዳው ጊዚያዊ ህዝብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ፋኖ መምህር በሪሁን ደምሌ በበኩሉ ወታደሩ በየወቅቱ አቅሙን እያሳደገ አቅዶ ጠላትን መምታት እንዳለበት ገልፆ የህዝብ ጉዳይን የህዝብ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ቀጣይም አቅሙን አጠናክሮ ህዝብን በቅን ልቦና ያገለግላል ብሏል። በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

💚💛❤️አባቶች ከፖለቲ,ካ ውጡ ለሚሉ ሁሉ:- መጸሐፍ ቅዱስም ሆነ ሌሎች የቤተክርስቲያን ድርስናት እንደሚነግሩን የሰው ልጅ ከአዳም መውደቅ ጀምሮ ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ምድርን አርሶ እንስሳትንም አርብቶ ከመብላት ጀምሮ በምድር ሲበዛም የአኗኗር ዘይቤንና አስተዳደርን ህግና ስርዓት ዘርግቶ መኖር ጀምሯል:: በእግዚአብሔር የሚያምኑ ከህገ ልቦና እግዚአብሔርን ከማምለክ ጋር አያይዘው አስተዳደርን ዘርግተው እንደኖሩ ትውፊትም መጻፍትም ይናገራሉ:: በሗላም ህግ ከእግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት ከተሰጠ ጀምሮ እግዚአብሔርን ከማምለክ ጋር የተያያዘ ምድራዊ የአስተዳደር መዋቅር ነበር:: ከዚያም በተዋረድ የሰው ልጆች በምድር እየበዙ ሲሄድ በእግዚአብሔር በተመረጡና በእግዚአብሔር ህግ በሚመሩ ህዝብን ከባህል፣ ከመልካም እሴትና ከፈሪሃ እግዚአብሔር ሳያርቁ ለዘምናት መርተዋል:: በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን እንዳገኙ እንደ ዳዊትና ልጁ ሰለሞን የነበሩ እንዳሉ ሁሉ ከእግዚአብሔር መንገድ አርቀው ህዝብን የመሩ ከብሉይ እንደ ሳዖልና ናቡከደነጾር ሌሎቹም ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ በሗላም እንደ ሄሮድስና የመሳሰሉ መሪዎች ነበሩ አወዳደቃቸው የከፋ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል:: ከብሉይ ጀምሮ በሀድስ ኪዳን ኢትዮጵያ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በህገ እግዚአብሔር ህዝቦቿን እንዳስተዳደረች በታሪክ ይታወቃል:: ለዚህም አይነተኛው ምስክር ፍትሀ ነገስት ነው:: ይህም ደጋግ ነገስታት ህዝብን ሲያስተዳድሩበት የነበረ ነው:: ህዝብን ማስተዳደርና መጠበቅ በእግዚአብሔር ለተመረጠ ሰው ብቻና ብቻ ነው:: ከእግዚአብሔር ያልተመረጡ ሰዎች ህዝብን መምራት አይችሉም:: የህዝቡን መንገድ ጨለማና እልቂት ነው የሚያደርጉት:: ዓለም አሁን ያለችበት የምስቅልቅል ምስጢር ይህ ነው:: አሁን በተለይ የቤተክርስቲያን ሰዎች (አገልጋዮች) ምንም ህዝብን ማስተዳደር ላይ እንዳይሳተፉ ህዝብም ችግር ውስጥ ሲወድቅ እንዳይመለከቱ ለማድረግ የቄስ ፣ የመነኩሴ ፣ የጳጳስ ፣ የዲያቆን ወዘተርፈ ፖለቲከኛ እያሉ ያሳቅቃሉ:: እና ህዝብን ማስተዳደርና ለተበደለ ህዝብ መቆም የማን ስራ ነው? እንደ ቅዱስ ላሊበላ የመሳሰሉት ነገስታት ይችን ሀገር ጠብቀው ያቆዩልን እኮ እናንተ አሁን ፖለቲካ የምትሉት በአስተዳደር ነው! ቤተክርስቲያን እንድትደፈርና ምዕመናንም ጠበቃ አልባ ሆነው ያሉት በዚህ ምክንያት ነው:: እኛ አባቶች ህዝብን በምናድንበትና በምንጠብቅበት መንገድ ሁሉ መንቀሳቀስ ግድ ይለናል:: ወንጌልን ለተራበ ወንጌልን፣ የታመመን በመፈወስ፣ ያዘነን በማጽናናት፣ ሰላምን ያጣ ሰላምን በማጎናጸፍ ከሃይማኖት በዘለለ በማንኛውም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ሁሉ ህዝብን ማገልገል የአባቶች ስራ ነበር! ሐዋርያት፣ አበው መነኮሳትና ካህናት፣ ሰማዕታት፣ ቅዱሳን ነገስታት (ስልጣነ ክህነትና ስልጣነ መንግስትን አጣምረው ያገለገሉ) ሁላቸውም ለእውነት ኖረዋል እውነትን መስክረዋል ህዝብን በጽድቅ ጎዳና መርተዋል! በዚህ ዘመን ያሉ አብዛኛዎቹ አባቶች አይ እኔ ፖለቲካ ውስጥ አልገባም እያሉ ስንቶቹን አስበልተዋል? የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያን ሃይማኖት ተከታይ በመሆናቸው በስልጣን በማንኛውም ፖለቲካዊ ፓርቲ እዳይገቡ እንዳይንቀሳቀሱ ከገቡም ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ ይደረጋል:: ፖለቲ,ካ መር ግጭ,ት ሲነሳ እንኳን ሆን ተብሎ የሚጨፈጨ,ፈው ክርስቲያን እየተመረጠ ነው:: ስንቶቹ ተጨፉጨ,ፉ? ስንት ንዋዬ ቅዱሳት ተመዘበሩ? ስንት አብያተ ክርስቲያናት እንደ ጧፍ ነደ,ዱ? ስንቶቹስ ለስደት ተዳረጉ? ስንት መከ,ራ በቤተክርስቲያን ላይ መጣ? እኛ ግን አንቀላፍተናል:: ወዳጄ ንቃ አትሸወድ! አባቶች ሙሴን ፣ ዳዊትን ፣ አጼ ዘርዓ ያዕቆብን ፣ቅዱስ ላሊበላን ፣አራቱን ነገስታትና ሌሎች የቀድሞ መሰረቶቻችንን እንምሰል! ህዝብን እናድን ሀገርን እንጠብቅ! ይህ ሁሉ የታሪክ ክሕደት ሲፈጸም፣ ቤተክርስቲያን እና አማኝ እንዳይኖሩ ሲሰራ ዝም ብሎ የሚያይ አባት አባት አይደለም! አንዳንድ አባት ተብዬዎች ለህዝብ የቆሙትን በህዝብ ዘንድ እንዲጠሉ እያደረጉ ይህ ፖለቲካ ነው ኃጥአት ነው ወዘተ እያሉ መሰናከያም እያዘጋጁ ነው:: ሃይማኖትና ሀገር ሲጠፋ ክቡር የሆነውም የሰው ልጅ ሲጨፈጨፍና ሲሳደድ እየተመለከቱ ምንም ደንታ የሌላቸው አባቶች እግዚአብሔር ዋጋቸውን ይሰጣቸዋል ታሪክም ይፋረዳቸዋል:: የሚገርመኝ አዋቂ ነን የሚሉት የሀይማኖት አባቶች ሀገር በፖለቲካ ቁማር ተጨዋቾችና በሀገር አፍራሽ ወንበዶች ተወራ እየተበታተነች እያዩ ልባቸውን ያደነደኑ ፣እያወቁ የሚታለሉና ለከርስ ብለው ከሰይጣን ጋር የሚኖሩ ሆነዋል:: እነዚህ አባቶች ለራሳቸው ሲሉ ራሳቸውን ይፈትሹ ዘንድ እንመኛለን:: ለእውነት ቁሙ የዚህ ዓለምን ገዥ አትፍሩ! የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ መስቀል መሸከም አለብን! ለእውነት እንቁም! መታገል ያለብንን እንታገል፣ መገሰጽ ያለብንን እንገስጽ፣ ማጽናናት ያለብንን እናጽናና! "ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ እንገደ*ላለን፤ እንደሚታ,ረዱ በጎች ተቆጥረናል" እንደሚል መጽሐፍ አትፍሩ:: እኔ ሀገሬ ነጻ እስክትወጣ የሰው ልጅም ነጻነት እስኪረጋገጥ እታገላለሁ! አባቶች እንንቃ ህዝብን እንታደግ! ✍️ቆሞስ አባ ጳውሊ ከግንባር

ትልቁ ባንዳ በቆንጆዎች ተወገደ‼️‼️ ብልጽግና የሚሊሻዎች ዋና አዛዥ አይቸው ሙሉዓለም በአዳኝ ጀግኖቻችን ተወገደ ══════════🕊❁✿❁🕊══════════ (ጥር 30/2018 ዓ.ም፣ ዐፋብን 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት) ከውስጥ እና ከውጭ ያሉ አነፍናፊ ጦረኞቻችን ባደረጉት የተቀናጀ የምሽት ኦፕሬሽን በቋሪት ወረዳ የብልጽግና ሚሊሻዎችን በበላይነት በሚያስተባብረው ፶ አለቃ አይቸው ሙሉዓለም ላይ የማያዳግም እርምጃ ወሰዱ። ጥንቁቅና የታለመ ጥቃት /surgical strike/ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ኦፕሬሽን፣ ተቅበዝባዡን የብልጽግና ሥርዐት በመቅበር ሂደት ያሉ ውጤቶችን አመላካች ነዉ ተብሏል። በዚህ ፈጣንና ድንገተኛ ጥቃት #አይቸው ባልጠበቀበት ሁኔታ ጀግኖች ገበዘ-ማርያም ከተማ ከመኖሪያ ቤቱ ድረስ ዘልቀው በመግባት ነፍሱን ወደ coል ሸኝተው ወዲያውኑ ወጥተዋል። ሕይወቱን ለማትረፍ የተደረገው ርብርብ ሳይሳካ ቀርቶ እኩለ-ሌሊት አሸልቧል። #አይቸው_ሙሉዓለም የፋኖን ንብረት በመዝረፍ ለሚሊሻ ሲያከፋፍል የነበረ፣ የፋኖ ቤት እንዳይከራይ ሲያደርግ የነበር፣ የፋኖ ቤተስሰብ ሲያግትና ከፍተኛ ዝርፊያ ስሲፈፅም የነበረ ነው። ሚሊሻ አይቸው በንፁሃን ላይ ያለው የተዛባ አመለካከትና የሚወስደው ያልተገባ እርምጃ ይበልጥ ተተኳሪ እንዳደረገውም ተገልጿል። ይህ የብልጽግና ጠብ ደል መወገዱ ሌሎች ግለሰቡ ያስተባብራቸው የነበሩ አባላት ትክክለኛ ውሳኔ ለመወሰን ያስችላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። 🖊 የንፁሃን ደም ይፈርዳል‼

የጥንቃቄ መልዕክት! ​በአሁኑ ወቅት በመንግስት መከላከያ ሰራዊት በኩል እየታዩ ያሉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን የሚመለከት አስቸኳይ መረጃ፦ ​በምንጃር ሸንኮራ፣ በበረኸት፣ በአገረማርያም እና በአሳግርት
የጥንቃቄ መልዕክት! ​በአሁኑ ወቅት በመንግስት መከላከያ ሰራዊት በኩል እየታዩ ያሉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን የሚመለከት አስቸኳይ መረጃ፦ ​በምንጃር ሸንኮራ፣ በበረኸት፣ በአገረማርያም እና በአሳግርት ወረዳዎች የኔትወርክ አገልግሎት ተቋርጧል። ​ይህም የሆነው የአረመኔው ሰራዊቱ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ባለበት በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ በሄሊኮፕተር ጭምር የታገዘ ኃይል እየተከማቸ ይገኛል። ​ በአሁኑ ሰዓት ከአሳግርት በሁለት አቅጣጫዎች ወደ በረኸት ጉዞ ተጀምሯል። ​በሜጢ በኩል ​በፉራ፣ በምንታምር እና በማስፋት በኩል ​የፋኖ አመራሮች አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ፣ በፍጥነት እንድትናበቡና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ መልዕክቱ ይድረሳችሁ።

ባለሽርጡ ክፍለ ጦር የሃብሩ ወረዳ ካድሬዎችን ያጀበ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ጋር ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ:: የአገዛዙ ካድሬዎች ህዝብን በስብሰባ ለማደናገርና የሃሰት ቅስቀሳ ለማድረግ ብሎም ፀረ-ህዝብና አገር አፍራሽ ተልዕኳቸውን ለማስፈፀም ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ ልዩ ስሙ 032 ቀበሌ ኮሎቦ በብልፅግና መከላከያ ታጅበው ህዝብ ሊሰበስቡ ባሰቡበት ሁኔታ ከባለሽርጡ ክፍለ ጦር በደረሰባቸው ያላሰቡት ድንገተኛ ጥቃት ብትንትናቸው ወጥቶ ወደ መርሳ ከተማ ተመልሰዋል:: ባለሽርጡ ክፍለ ጦር ቀጠናውን በመቆጣጠር የህዝብ አስተዳደር መዋቅር ዘርግተው እያስተዳደሩት ያለ ሲሆን አገዛዙ ብልፅግና ምንም አይነት መፈናፈኛ እንዳያገኝ በማድረግና በተደጋጋሚ ጊዜ ክንዳቸውን በማቅመስ ዛሬም ድላቸውን አስቀጥለዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ትግላችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 29/ 2018 ዓ.ም

አፋብን በሁሉም አቅጣጫ ሰፊ ቀጠና ያካለለ አውደ ውጊያ እያደረገ ነው በዚህም እስካሁን ሰሜን ሸዋ, ምስራቅ ጎጃም, ምዕራብ ወሎ እና በጎንደር አንዳንድ አካባቢዎች የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት የ
አፋብን በሁሉም አቅጣጫ ሰፊ ቀጠና ያካለለ አውደ ውጊያ እያደረገ ነው በዚህም እስካሁን ሰሜን ሸዋ, ምስራቅ ጎጃም, ምዕራብ ወሎ እና በጎንደር አንዳንድ አካባቢዎች የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋርጠባቸው ቀጠናዎችም አሉ በመላው አማራ ግዛት 24 ስዓት ፍኖተ-አማራ መርጃዎችን ጎልልጉላ እየሰራች ትገኛለች ።