ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
4 389
المشتركون
+2924 ساعات
+2547 أيام
+1 45030 أيام
أرشيف المشاركات
"የአፋር ሕዝብ በፌድራል መንግስት ተብዬው ስፖንሰርነት የተከፈተበተ ወረራ እንዲቀለበስ እየሰራን እንገኛለን" የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ከአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ! የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ባለፉት አንድ አመት አስደናቂና አመርቂ የመደራጀትና የማደራጀትን ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝና አሁን ላይ ወደ ሙሉ ማጥቃት ለመሸጋገር ሙሉ ዝግጅትችን ማጠናቀቃችን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው። ብልጽግና መሩ ጦረኛው የአብይ አህመድ አገዛዝ ያለጦርነት ውሎ ማደር አይችልምና አገሪቱን የጦርነት ሜዳ ከአደረጋት እነሆ ስምንት ዓመታት ተቆጠሩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብም በኑሮ ውድነት፣ በሰላም እጦት፣ በሙስና፣ ሌብነት : ከአቅም በላይ በሆነ የግብር ብዝበዛ፣ በእገታ እና ወ.ዘ.ተ. እየተሰቃዬ ይገኛል። የብልጽግና አገዛዝ ጦርነት እስትንፋሱ ነውና ውድ የኢትዮጵያ ልጆችን በካኪ ልብስ እየጠቀለለ ወደ ጦርሜዳ በመሸኘት እናት ያለጦሪ ቀባሪ እየወረች ትገኛለች፤ ወጣቶች አጽማቸው የት እንደወደቀ ሳይታወቅ የአሞራ ቀለብ ከሆነ አመታት ተቆጠሩ፤ በመሆኑም ይህ ጦረኛ አገዛዝ እንዲገረሰስ እኛ የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ሕዝባችን ከላላ አድርገን የአብይ አህመድ አገዛዝ ለመጣል ጠንካራ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን። ስለሆነም በዛሬው ዕለት ሕዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ለመስጠት ተገደናል። የሚከተሉት ነጥቦችንም መላው የአፋር ሕዝብ ብሎም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና የአብይ አህመድ ጦረኛ አገዛዝ ከሕዝብ ጫንቃ ላይ እንዲወርድ የሚፈልግ ኃይል ሁሉ ትኩረት እንዲሰጥበት ማሳሰብ እንፈልጋለን። 1ኛ. አሁን ላይ የአፋር ሕዝብንና የአፋር መሬትን ቁማር በማስያዝ የጦር ሜዳ ለማድረግ እየሰራ ያለው የአወል አርባ አገዛዝም ሆነ አለቃው አብይ አህመድ እያደረጋችሁት ያለው ነገር ትክክል አይደለም፤ የአፋር ሕዝብም ሆነ መሬት ነጻ ሊወጣ ይገባል እያልን በተለይ በአፋር መሬት ውስጥ ያላችሁ "ሀራ መሬት/ነጻ መሬት" በሚል የተደራችሁ የትግራይ የሰላም ኃይል ነን የምትሉ የአፋር ክልልን በአስቸኳይ ለቃችሁ እንድትወጡ እናሳስባለን። በዚህ ቀጥተኛ ተጎጅ የምትሆነው የአፋር ሕዝብም እነዚህ ኃይሎች ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ጫና እንድታደርግ እንጠይቃለን። 2ኛ. በሙስጠፌ መሐመድ የሚመራው የኢሳ ኃይል አሁንም የወሰንና የደንበር ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች በአፋር ሕዝብ ላይ ተከታታይ የሆኑ ኢ- ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በቀጣይ በምርመራ የምናጋልጠው ሁኖ ዛሬም በኢሳ ኃይሎች ልጃገረጆችን ጨምሮ እናቶች እየተፈሩና እየተገደሉ መሆኑን እየገለጽን የሚዲያ ኃይሎችና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና ተሟጋቾች የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ትኩረት እንድትሰጡ ማሳሳብ እንፈልጋለን። 3ኛ. የአወል አርባ አገዛዝ የአፋር ሕዝብን ጥቅምና መብት የሚከራከሩ ምሁራንን፣ ወጣቶችን፣ የፀጥታ ተቋማት አመራሮችን ዛሬም እያሳደደ፣ እያሰረ እና እየገደለ ይገኛል። ከዚህ ድርጊቱ እንዲታቀብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲታቀብ እያሳሰብን፤ ምሁራን፣ ወጣቶች፣ የፀጥታ ኃይሎች አጠቃላይ በአወል አርባ አገዛዝ እየተሳደዳችሁ ያላችሁ የአፋር ልጆች ወደ አፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን። 4ኛ. ጦረኛውን የአብይ አህመድ አገዛዝ እየታገላችሁ ያላችሁ ኃይሎች፦ አብይ መሩ የብልጽግና አገዛዝ አንድ ቀን በሰጠነው ቁጥር ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በዲፕሎማሲ እያንኮታኮታትና እየደፈቃት የሚገኝ ኃይል መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው። ይሄን ጉዳይ በአግባቡ በመረዳት የአብይ አህመድ አገዛዝን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ እንተባበር ስንል የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ጥሪውን በይፋ ያቀርባል። በመጨረሻም አንባገነን አገዛዞች እንደወደቁት፣ ጭፈራዎቻቸውም እንደተሳደዱት ሁሉ አንባገነኑ የብልጽግና አገዛዝ በቁርጠኛ ታጋዮች ይወገዳል፤ የአንባገነኑ መሪም ሆነ አገልጋዮቹ ለፍርድ አደባባይ እንደሚቀርቡ የአለም ታሪክ ምስክር ነውና ይህም በቅርቡ ይሆናል። አንባገነኑ ሕዝብ መጨፍጨፍ የስልጣኑ መሠረት ነውና ሎሌዎቹ ከሕዝብ ጎን እንድትቆሙ የመጨረሻ ጥሪ እናቀርባለን። ድልና ድምቀት ለአፋር ኡጉጉሞ! የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ህዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም

"የአፋር ሕዝብ በፌድራል መንግስት ተብዬው ስፖንሰርነት የተከፈተበተ ወረራ እንዲቀለበስ እየሰራን እንገኛለን" የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ከአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ! የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ባለፉት አንድ አመት አስደናቂና አመርቂ የመደራጀትና የማደራጀትን ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝና አሁን ላይ ወደ ሙሉ ማጥቃት ለመሸጋገር ሙሉ ዝግጅትችን ማጠናቀቃችን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው። ብልጽግና መሩ ጦረኛው የአብይ አህመድ አገዛዝ ያለጦርነት ውሎ ማደር አይችልምና አገሪቱን የጦርነት ሜዳ ከአደረጋት እነሆ ስምንት ዓመታት ተቆጠሩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብም በኑሮ ውድነት፣ በሰላም እጦት፣ በሙስና፣ ሌብነት :  ከአቅም በላይ በሆነ የግብር ብዝበዛ፣ በእገታ እና ወ.ዘ.ተ. እየተሰቃዬ ይገኛል። የብልጽግና አገዛዝ ጦርነት እስትንፋሱ ነውና ውድ የኢትዮጵያ ልጆችን በካኪ ልብስ እየጠቀለለ ወደ ጦርሜዳ በመሸኘት እናት ያለጦሪ ቀባሪ እየወረች ትገኛለች፤ ወጣቶች አጽማቸው የት እንደወደቀ ሳይታወቅ የአሞራ ቀለብ ከሆነ አመታት ተቆጠሩ፤ በመሆኑም ይህ ጦረኛ አገዛዝ እንዲገረሰስ እኛ የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ሕዝባችን ከላላ አድርገን የአብይ አህመድ አገዛዝ ለመጣል ጠንካራ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን። ስለሆነም በዛሬው ዕለት ሕዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ለመስጠት ተገደናል። የሚከተሉት ነጥቦችንም መላው የአፋር ሕዝብ ብሎም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና የአብይ አህመድ ጦረኛ አገዛዝ ከሕዝብ ጫንቃ ላይ እንዲወርድ የሚፈልግ ኃይል ሁሉ ትኩረት እንዲሰጥበት ማሳሰብ እንፈልጋለን። 1ኛ. አሁን ላይ የአፋር ሕዝብንና የአፋር መሬትን ቁማር በማስያዝ የጦር ሜዳ ለማድረግ እየሰራ ያለው የአወል አርባ አገዛዝም ሆነ አለቃው አብይ አህመድ እያደረጋችሁት ያለው ነገር ትክክል አይደለም፤ የአፋር ሕዝብም ሆነ መሬት ነጻ ሊወጣ ይገባል እያልን በተለይ በአፋር መሬት ውስጥ ያላችሁ "ሀራ መሬት/ነጻ መሬት" በሚል የተደራችሁ የትግራይ የሰላም ኃይል ነን የምትሉ የአፋር ክልልን በአስቸኳይ ለቃችሁ እንድትወጡ እናሳስባለን። በዚህ ቀጥተኛ ተጎጅ የምትሆነው የአፋር ሕዝብም እነዚህ ኃይሎች ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ጫና እንድታደርግ እንጠይቃለን። 2ኛ. በሙስጠፌ መሐመድ የሚመራው የኢሳ ኃይል አሁንም የወሰንና የደንበር ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች በአፋር ሕዝብ ላይ ተከታታይ የሆኑ ኢ- ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በቀጣይ በምርመራ የምናጋልጠው ሁኖ ዛሬም በኢሳ ኃይሎች ልጃገረጆችን ጨምሮ እናቶች እየተፈሩና እየተገደሉ መሆኑን እየገለጽን የሚዲያ ኃይሎችና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና ተሟጋቾች የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ትኩረት እንድትሰጡ ማሳሳብ እንፈልጋለን። 3ኛ. የአወል አርባ አገዛዝ የአፋር ሕዝብን ጥቅምና መብት የሚከራከሩ ምሁራንን፣ ወጣቶችን፣ የፀጥታ ተቋማት አመራሮችን ዛሬም እያሳደደ፣ እያሰረ እና እየገደለ ይገኛል። ከዚህ ድርጊቱ እንዲታቀብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲታቀብ እያሳሰብን፤ ምሁራን፣ ወጣቶች፣ የፀጥታ ኃይሎች አጠቃላይ በአወል አርባ አገዛዝ እየተሳደዳችሁ ያላችሁ የአፋር ልጆች ወደ አፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን። 4ኛ. ጦረኛውን የአብይ አህመድ አገዛዝ እየታገላችሁ ያላችሁ ኃይሎች፦ አብይ መሩ የብልጽግና አገዛዝ አንድ ቀን በሰጠነው ቁጥር ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በዲፕሎማሲ እያንኮታኮታትና እየደፈቃት የሚገኝ ኃይል መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው። ይሄን ጉዳይ በአግባቡ በመረዳት የአብይ አህመድ አገዛዝን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ እንተባበር ስንል የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ጥሪውን በይፋ ያቀርባል። በመጨረሻም አንባገነን አገዛዞች እንደወደቁት፣ ጭፈራዎቻቸውም እንደተሳደዱት ሁሉ አንባገነኑ የብልጽግና አገዛዝ በቁርጠኛ ታጋዮች ይወገዳል፤ የአንባገነኑ መሪም ሆነ አገልጋዮቹ ለፍርድ አደባባይ እንደሚቀርቡ የአለም ታሪክ ምስክር ነውና ይህም በቅርቡ ይሆናል። አንባገነኑ ሕዝብ መጨፍጨፍ የስልጣኑ መሠረት ነውና ሎሌዎቹ ከሕዝብ ጎን እንድትቆሙ የመጨረሻ ጥሪ እናቀርባለን። ድልና ድምቀት ለአፋር ኡጉጉሞ! የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ህዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም

#ሰርቶ_መብላት_እንጅ_ተንኮል_የማያውቀው_ሸበል_በረንታ_የሽፈራው_ሀገር_የወንዶች_ሀገር_ነው። የጀመርነው ትግል የዋዛ የመሰላቸው ብዙ ካድሪዎች በአማራ ፋኖ ቅንድባቸውን እየተላጩ እስከ ወዳኘው ተሸኝተዋል። ትግል በውጭ እንደምናየው ውስጡ በርግጥ እንዲህ እንደዋዛ አይደለም! በውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን በቀጠናችንም የሚገኙ ሆዳም/አሳማ ካድሪዎች ጭንቀት እየጨመረ መምጣቱን አረጋግጠናል። የአገዛዙ ቅጥረኛ ካድሪዎች አሁን ላይ 64ኛ ክፍለ ጦር እየወሰደ ባአለው እርምጃ ዘመኑን በአወጀ የድርጅቱን አደረጃጀት መሬት ላይ አውርዶ እየሰራ ያለው አደረጃጀት በስጋት እና በጭንቀት ውስጥ ከገቡ ውለው አድርዋል። በርግጥ ትላት በተለያየ ምክንያት ያልሰራናቸው ስራዎችን አሁን ላይ እየሰራናቸው እንገኛለን። በዚህ ሰዓት ይህንን አረመኔዊ ስረዓት አፈር ደሜ አብልቶ የሚማርክ፣ የሚደመስስ ሰራዊት እየገነባን እንገኛለን። ህዝባችን ከትላንቱ የበለጠ አጀረጃጀቱን በመዘርጋት፣ ወጣቱን ብአዴን ከዘረገው ከተለያዩ ሱሶች አውጥተን በማደራጀት የአማራ ህዝብ ወቅታዊ የፖለቲካ ሸፍጥ እያስተማርን ሀገር ወዳድ ለአማራነቱ የሚሞት የሰለጠነ ወታደራዊ ኃይል እየገነባን እንገኛለን። ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል የማንከፍለው መስዋትነት የለም! በአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነብንን የህልውና አዳጋ ለመመለስ የማናደርገው ነገር ሁሉ የለም? በትግሉ ላይ የምንገኝ ታጋይ የፋኖ አባላት እና አመራር በሙሉ ጠላቶቻችን የብአዴን አመራሮች መንገድ እየመሩ፣ ትዛዝ እየሰጡ በህዝባችን ላይ እየፈፀሙብን ያለውን ግፍ እና መከራ ተረድተን ሁላችንም ለህዝባችን አዛኝ ሆነን በጠላቶቻችን ሀብት ንብረት እንዲሁም በራሳቸው ላይ #ከባድ_እርምጃ የምንወስድ ይሆናል። የሽፈራው ገርባው የበላይ ዘለቀ የትውልድ ቦታ ሸበል በረንታ በታሪክ አጋጣሚ እንድንመራ ድርጅታችን እና ህዝባችን ታላቅ ኃላፊነት ሰጥቶናል። ይህ ቀጠና ባንዳ እና ሰላቶ፣ ከአማራነቱ ይልቅ ሆዱ የሚበልጥበት #አሳማ_ካድሪ እንደማይኖርበት እርግጠኞች ነን። ከታች የምትመለከቶችው የሽፈራው ገርባው ልጆች ከውስጣቸው የወጡ ባንዳዎችን የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አባላትን ለመፋለም  የተኩስ ልምምድ ወስደው ተመርቀው ወደ ትግል ተቀላቅለዋል። ሙሉ ቪዲዮውን ለማየት በመረጃ ቲቪ ይከታተሉ🙏🙏🙏 አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!             ህዳር 28/2018 ዓ.ም

"አማራ በፍርሃት አይለካም። አማራ በልፍስፍስነት አይለካም። በጀግንነት! በአሸናፊነት! በሀገር መሪነት! በሀገር መስራችነት ነው የሚለካው "መመዘኛው እሱ ነው ሆኖም የኖረው ያንን ነው! እንደጀመርነው
+2
"አማራ በፍርሃት አይለካም።   አማራ በልፍስፍስነት አይለካም።    በጀግንነት!      በአሸናፊነት!       በሀገር መሪነት!         በሀገር መስራችነት ነው የሚለካው "መመዘኛው እሱ ነው ሆኖም የኖረው ያንን ነው! እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን💪 አርበኛ ሳሙኤል ባለዕድል የአፋብኃ ሴንተራል ኮማንድ አባልና የበላይ ዘለቀ ዕዝ  ም/ሰብሳቢ ና ወታደራዊ አዛዥ።💪🔥

#ጠቅል_ሻለቃ_አዳሩን_የተለያዩ_ቦታዎችን_አጠቃ‼️ ህዳር 21/3/2018 ዓም ሌሊት ጠቅል ሻለቃ ቢቸና ከተማ ላይ ሰርጎ በመግባት በቦምብ ሲያጋየው ማደሩ ይታወሳል። አገዛዙ ይህንን ጥቃት ተከትሎ በር
#ጠቅል_ሻለቃ_አዳሩን_የተለያዩ_ቦታዎችን_አጠቃ‼️ ህዳር 21/3/2018 ዓም ሌሊት ጠቅል ሻለቃ ቢቸና ከተማ ላይ ሰርጎ በመግባት በቦምብ ሲያጋየው ማደሩ ይታወሳል። አገዛዙ ይህንን ጥቃት ተከትሎ በርካታ ኃይል ሲያስገባ የሰነበተ ሲሆኝ እንደ አመጣጡ አናብስቶች ሲያስተናግደው ቢቆይም ዛሬም አዳሩን በድጋሚ  ጠላት እንደለመደዉ ፋኖን በለሊት ለማፈንና ጥቃጥ ለመፈፀም በሶስት አቅጣጫ ከበባ አድርጎ ወደ ፋኖ ካምፕ ቢተምም #ጠቅል_ሻለቃ በጀግናው #ሻለቃ_ቃልኪዳን_ልቅናዉ  እየተመራች #ቀዶ_ጥገና አድርጋለች፣ በዚህም:- 👉 ሸበል ዙረያ ማንቆርቆይ፣ 👉የትመን እና ቢቸና ማረሚያ ቤቱ ላይ ጠላትን ሰርጎ በመግባት በውስን የሰው ኃይል ፣ በነፍስ ወከፍ መሳሪያና ቦምብ በተመሳሳይ ሰዓት ሲያናዝዙት አድረዋል💪 የቃልየ ቀኝ እጅ የሆነዉ ፋኖ ቦንቦኛዉ #ዮሐንስ ትዕዛዙን በመቀበል ቢቸና ከተማ ላይ ከጠላት ጋር ተፋጦ ሰርጎ በመግባት ማረሚያ ቤቱ ላይ ቦንብ በመጣል በጠላት ላይ ጉዳት በማድረስና የስነልቦና ጫና በመፍጠር ነፍሴ አውጭኝ በማለት ወደ ቢቸና ከተማ ፈርጥጦ እንዲመለስ ተደርጓል ሲሉ አናብስቶች ለንስር አማራ ገልፀዋል‼️    #ሳተናዉ_ጠቅል_ሻለቃ_ይችላል💪💪💪💪💪 28/ዐ3/2018 ዓ.ም

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ 109ኮር 99ክ/ጦር በደጋ ዳሞት ሻለቃ ከባድ በትር የተናደደው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት በየሄደበት ቀጠና ያገኘውን ሀብት ንብረት እያወደመ እና እየዘረፈ ይገኛል ከ
+7
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ 109ኮር 99ክ/ጦር በደጋ ዳሞት ሻለቃ  ከባድ በትር የተናደደው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት በየሄደበት ቀጠና ያገኘውን ሀብት ንብረት እያወደመ እና እየዘረፈ ይገኛል ከነዚህም ውስጥ የሰቀላ እና የደልሙ ጤና ጣቢያወችን   ሀብት እና ንብረት የዘረፈ ሲሆን በተጨማሪም ፈንቴ ታረቀኝ  የተባለን ግለሰብን በአሰቃቂ ሁኔታ ገሏል።   እንስሳትን  ገሏል፤ የገበሬውን እህል አቃጥሏል፤ የልብስ፥የጫማ እና የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆችን ዘርፏል።

በነዚህ ላይ ተረማምዶ ከገዳያቸው፣ ከአሳዳጃቸው ጋር የሚደራደር... እሱ ......ሴት ልጅና እህቱን....እናቱንም ሳይቀር...የአልጋ መውረጃ አሲዞ ለገዳይ በስጦታ የሚልክ ወራዳ ብቻ ነው ፦፦፦፦ ከ
+2
በነዚህ ላይ ተረማምዶ ከገዳያቸው፣ ከአሳዳጃቸው ጋር የሚደራደር...   እሱ ......ሴት ልጅና እህቱን....እናቱንም ሳይቀር...የአልጋ መውረጃ አሲዞ ለገዳይ በስጦታ የሚልክ ወራዳ ብቻ ነው ፦፦፦፦ ከጠላት የባሰ ባንዳ ! .

ትግል በተላላኪ ባንዳዎች በኩል ይሸጣል ይለወጣል በእውነተኛ ሰዎች ዘንድ ግን። ✔ትግልን ታግለው ያሸንፉታል እንጂ ሸጠው አልያም በጥቅም ለውጠው መፍትሔ አይመጣበትምና ከዚህ የፀዳ ስራዊት መገንባት ግድ ይላል፡ ✔የትግልን ቅድመ ውጣ ውረድ የመጨረሻ ቋት መሰረታዊ ሁኔታ ጠንቅቆ ማወቅ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን መተንተን የአንድ አካል አልያም የሁለት ግለሰብ ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ አካል ግዴታ ነውና የፋኖነትን አላማ፣ራዕይ እና ተልዕኮ ጠንቅቆ ያወቀ ስራዊት ማደራጀት፣ማሰልጠን፣ማዋቀርና ማሰለፍ ሀቅነትን ያመነጫል፡ ✔የፋኖነትን፣የትግልን አላማ አለማወቅ ከጠላት አስተሳሰብ የተለየ አይሆንም ሀገር ለሰላም፣ህዝብ ለነፃነት መስመር የሚኖረው የወጡለትን አላማ ከዳር፣የያዙትን ተልዕኮ ከፍፃሜ፣ያሉበትን ራዕይ ከትርጓሜ ማድረስ ሲቻል ነውና ይህ የእያንዳንዱ አካል የስራ ድርሻ ሊሆን ግድ ይላል። ✔ከትጥቅ ትግል በፊት ስነ-ልቦናዊ የህዝብ የግንዛቤ አስተምህሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ አካሄድ ሀሳብ መለዋወጥ መማር መነጋገር ከጦር መሳሪያው ጎን ለጎን ደጋፊ ማህበረሰቡን ያበዘዋልና እንናበብ፡ ✔ሰይጣንን ተማክረው ተማምረው ተሳስበው አንድ ሆነው ሲታገሉት ይወድቃል፤አንዱ አብይ አንዱ ሽመልስ ሌላኛው ደግሞ አረጋ ከበደ ባንዳ ተላላኪ ከሆኑ ግን ትግሉን ማቆሸሻቸው አይቀርምና ትኩረት እንስጠው፡ ✔ተላላኪ ባንዳ ዛሬም አለ ድሮም ነበረ፤የዛሬው ለየት የሚያደርገው ከአስር ቁጥር በልጦ ሚሊዮኑ በተላላኪ ባንዳነት መቀጠሩ ነውና ሁሉም ራሱን ይፈትሽ። ✔ከፋኖ ጎን ቆሞ የፋኖነትና የትግሉን አላማ ጠንቅቆ አለማወቅ ሞትነት ነው፤ፋኖነትንና ትግሉን ግን ጠንቅቆ አውቆ በሁለት እጅ አጨብጭቦ መሰለፍ ግን ህያውነት ነውና እንገንዘብ። ✔ተላላኪ ባንዳ ዘርፈ ብዙ የልዩነት አጀንዳ ይቀይሳሉ፤በፋኖነት መርህ ግን ልዩነቶች ወደ አንድነት ይቀየራሉ ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያለውን ወደብም በሰላማዊነት አርማ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ✔ፋኖነት በተላላኪዎች እጅ ሲወድቅ ሀገር ያፈርሳል፣ህዝብ ያስኮበልላል፣መንግስት አልባ ድርጅት ፀረ ሰላም ሀይል ይፈጥራል፤ፋኖነት በእነ ዘመነ ካሴ፣በእነ ሀብቴ ወልዴ፣በእነ ዋርካው ምሬ ወዳጆ፣በእነ ደሳለኝ ሲያስብሸዋ እጅ ሲሆን ግን የሀገር ሰላም ይረጋገጣል፣ህዝብ ይደሰታል፣ጦርነት አልባ የሰላም አውታር ይዘረጋልና ሁላችንም ከሀሰተኛ ሰዎች ጉርብትና ተላቀን እውነተኞችን እንከተል፡ ✔ሚዲያ ላይ ለመውጣት እውነተኛ ፋኖ መሆን ግድ ይላል፣ከሚዲያው ዘንድ ለመንቦራቦር የእውነተኞችን ራዕይና አላማ መያዝ ግድ ይላል፤ከዚህ ውጭ ግን በስልጣን ጥምነትና በድንቁርና አስተሳሰብ"ሆ"ብሎ መጨፈር የንፁሃን ደም በራሱ እንቅፋት ሆኖ ሰደድ እሳት ውስጥ ይጥላልና ከሀሰተኞች ሳይሆን ከእውነተኞች ጋር እንመሳጠር፡ ማሳሰቢያ፦ዛሬን ከአገዛዙ ጎን ተሰልፎ የአማራን ህዝብ መውጋትና አማራን ማሳደድ ነገን ባልተፈጠርኩኝ አይነት ስሜት ያመነጫልና ተላላኪ ባንዳ የአገዛዙ ቅጥረኛ ይሰማል??? ✍️ህዳር 27/2018 ዓ.ም

"...ጥቆማ ‼#ሸርይደረግ👇👇 መረጃ(ለፋኖ የሚደርስ)❗️ "... በየአካባቢያቸው ለሚገኙ የፋኖ መሪዎች የዞን እና የወረዳ የብልፅግና አመራሮችና የሀይማኖት አባቶች ስልክ በመደወል ለሁሉም የፋኖ አባል በመደለል እና እንዲሁም እንደያግባቡ ለሁሉም የብልፅግና አመራሮች እና የሀይማኖት አባቶች ተልዕኮ የተሰጠ ሲሆን ከፋኖ መሪዎች ጋር የሚደረገውን የስልክ ልውውጥ ሪከርድ በማደረግ በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨት  እከሌ የሚባልው ፋኖ ከከሌ የዞን አመራር ጋር ድርድር እያደረገ ነው፡፡ እከሌ የሚባል የፋኖ መሪ እከሌ ከሚባል ወረዳ አመራር ጋር ድርድር አድርጎ ሊገባ ነው የሚሉ በሬ ወለድ መሰል ዜናዎች ሊሰሩ እና በፋኖ መሪዎች  መካከል ጥርጣሬ ለመፍጠር ተልዕኮ ተሰጥቷል። ስለሆነም በሁሉም አካባቢ የምትንቀሳቀሱ ፋኖዎች በተለይ የፋኖ መሪዎች ጥንቃቄ እንድታደረጉ እናሳስባለን፡፡ አንድነታችን ለዘላቂ ነፃነታችን፡❗️❗️ መረጃ አይናቅም አይደነቅም❗️❗️

ከሸዋ ሰማይ ስር የድሽቃው አለቃ የሴቷ አርበኛ አይ አነጣጠር አይ መሳሪያ አያያዝ ድሮስ የአስማረ ዳኜ ዘር ሆነሽ መጠርጠሩስ። የአሳምነው እዝ የከሰም ኮር የሀይለማሪያም ማሞ ክፍለጦ ሴቷ የድሻቃ ተኳ
ከሸዋ ሰማይ ስር የድሽቃው አለቃ የሴቷ አርበኛ አይ አነጣጠር  አይ መሳሪያ አያያዝ ድሮስ የአስማረ ዳኜ ዘር ሆነሽ መጠርጠሩስ። የአሳምነው እዝ  የከሰም ኮር የሀይለማሪያም ማሞ ክፍለጦ ሴቷ የድሻቃ ተኳሽ✊

#እንኳን ደህና መጣችሁ!! #አዲናስ!! የነቁት ወደ ትክክለኛዉ የትግል መስመር እየመጡ ነዉ 🙏 ሁለት ወንድሞቻችን አዲስ ቅዳም ከተማ  ከተከማቸዉ ጡት ቆራጭ አሸባሪ የብልፅግና ታጣቂ በመለየ
+1
#እንኳን ደህና መጣችሁ!! #አዲናስ!! የነቁት ወደ ትክክለኛዉ የትግል መስመር እየመጡ ነዉ 🙏 ሁለት ወንድሞቻችን አዲስ ቅዳም ከተማ  ከተከማቸዉ ጡት ቆራጭ አሸባሪ የብልፅግና ታጣቂ በመለየት ትክክለኛዉን  የትግል መስመር መርጠዉ   የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44 ክ/ጦር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ሻለቃን በሰላም ተቀላቅለዋል። አዲስ ቅዳም ከተማ ከሚገኘዉ የጠላት ካምፕ ዉስጥ <ጠላት ነበረበት> የሚለዉ ቃል እስኪቀር የብልፅግናን ታጣቂ የፋኖ ወታደር በማድረግ የጠላትን መዋቅር 100% እናፈራርሰዋለን ። አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ🙏 ህዳር 27/2018 ዓ/ም

ሁሉ ነገር የማይፃፍ እየሆነ ቸገረንኮ! ''የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል የኔም ትግል ነው!'' ብሎ የሚያስብና የሚጨነቅ ማንኛውም አካል ፣ በተለይ በማህበራዊም ሆነ በሜኒስትሪሚንግ ሚዲያው ለሚናገራቸው (ለሚፅፋቸው) ቃላት መጠንቀቅ ብሎም ከከፋፋይና ሴንሴቲቭ ጉዳዮች ራሱን ማራቅ የሚጠበቅበት እጅግ ወሳኝ ሰአት መሆኑን ይረዳል! ከግላዊ እይታና ስሜቱ ይልቅ የድርጅትን ውሳኔና አቅጣጫ ያከብራል። ከችኮላ ይልቅ መረጋጋትን ፣ ከስሜታዊነት ይልቅ አስተዋይነትን መገለጫው ያደርጋል። ከራሱ ስሜት ይልቅ የጋራ አላማን ያስቀድማል! አንዳንድ ተራ የመሰሉንና የናቅናቸው ጉዳዮች ፖለቲካሊ ብልጫ እያስወሰዱብንና ዋጋ እያስከፈሉን መሆናቸውን ልብ ልንልም ይገባል! ከተለምዷዊው መስመር ብንወጣና ህብረትና አንድነታችንን በሚገነባ እሳቤ ውስጥ ራሳችንን ብንገራው መልካም ነው! እኔ ፣ አንተ ፣ አንቺ ፣  በየፊናችን የምናደርገው ሀላፊነት የጎደለው እንቅስቃሴ እንደማህበረሰብ  ተያይዞ ለመውደቅ የሚያስችል እንቅፋት ሊፈጥር እንደሚችል መገንዘብ የእያንዳንዳችን ሀላፊነት መሆኑም ሊሰመርበት ይገባል! ©ዘር ይሁን ገሰሰ

#አሁናዊ_መረጃ_ወለጋ ‼️ ራሱን መከላከያ ብሎ የሚጠራው የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሰራዊት ስብስብ አማራ በብዛት ወደ ሚኖሩባቸዉ ቀበሌውች በስፋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል። በምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ገሊላ ወረዳ ዋጃ ስላሴ ቀበሌ ላይ በርካታ ንፁሃን የአማራ አርሶ አደሮች ወደ ጫካ ተሰደዋል። በደረሰበት ሁሉ አማራን መግደል፣ ማሳደድ ፣ ማፈናቀል እና መዝረፍ ግብሩ የሆነዉ  አራዊት ሰራዊት በዋጃ ስላሴ ቀበሌ በርካታ ቤቶችን አቃጥሎ የቀንድ ከቀቶችን መዝረፉን የአካባቢው ኗሪዎች ለቢዛሞ ሚዲያ ገልጸዋል ። ህዳር 27/2018 ዓ.ም #ቢዛሞ_ሚዲያ #የቢዛሞ_አማራ_ድምፅ

ስለዚህ ከጠላት ጎን ተሰልፋችሁ ወገናችሁን እየወጋችሁ ያላችሁ የሚሊሻ፣ አድማ ብተና እና ፓሊስ እንድሁም መከላከያ ሰራዊት አባላት ከዛሬ ህዳር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ የምህረት አዋጅ ይፋ ስላደረግን ይህን ወርቃማ እና ታሪካዊ እድል እንድትጠቀሙበት ስንል ከወዲሁ እያሳሰብን ጠላትን ከድታችሁ ስትመጡ እኛ በበኩላችን ለምታስረክቡን ትጥቅ ተገቢውን ካሳ በመስጠት ወደምትፈልጉበት ቦታ ለመላክ ዝግጁዎች መሆናችንን እንገልፃለን:: አብሮን ለመታገል ፈቃደኛ ለሚሆነውም ሁኔታዎችን የምናመቻችለት ይሆናል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 27 ቀን 2018 ዓ.ም

ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር አዛዥ አርበኛ አብነው ታደሰ የተላለፈ የትግል ጥሪ!! በመጀመሪያ ደረጃ ለሁሉም አማራ እና የህልውና ትግላችን ደጋፊዎች ለሆናችሁ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት የምሻው የአማራ ፋኖ የጄኔራል አሳምነው ፅጌን የኑዛዜ ቃል አክብሮ በቅንጅት እና በአንድነት እየታገለ መሆኑን በማብሰር ነው:: ቀሪው ስራችን አንድ እናት ድርጅት መመስረት ነው ይህም በቅርቡ እንደሚሳካ ጥርጥር የለኝም:: እንደምታውቁት እኛ አማሮች በፋሽስቱ አብይ አህመድ መንግስት የተከዳን እና ጥርስ የተነከሰብን ነን:: "አማራን ላጠፋ ነው" በማለት አብይ አህመድ ቃል በቃል ለኦሮሞ ተወላጅ የፌደራል እና ኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት መናገሩን የተከበሩ አቶ ታዬ ደንደአ ማጋለጣቸው ይታወሳል:: የማጥፋት ፕሮጀክቱ ትግበራ ከተጀመረ እነሆ ዓመታት ተቆጠሩ:: አብይ አህመድ እነ ጄኔራል አሳምነው ጽጌን ገድሎ ክልላችንንም አስወርሮ በክተት መክት ስትራቴጅ ህዝባችንን አስጭውፍጭፎ ሲያበቃ በድህረ ሰሜኑ ጦርነት ወቅት ፋኖን ትጥቅ አስፈትቶ አማራ ክልልን አባውራ የሌለው ቤት በማስመሰል ህዝባችንን ለማጥፋት እና የአማራን ጥንተ እርስት ለመቀማት አስቦ ብዙ እርቀት ሄዷል:: በዚህም መሰረት በህግ ማስከበር ስም አማራን ለመጨፍጨፍና ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት ዘመቻ መጀመሩና በርካታ ንፁሀንን መግደሉ ይታወቃል:: ይህን መንግስታዊ ክህደት በመቃወም አማራ አይጠፋም ትጥቁንም አይፈታም ብለን ወደ ጫካ በመግባት አፈሙዝ ወደ ህዝባችን ጠላት አዙረናል::  አማራ ሲፈናቀል፣ ሲገደል፣ ሲታሰር እና ሀብት ንብረቱ ሲዘረፍ ቆመን አናይም ይልቁንስ ባለጋራችንን እየገደልን እንሞታለን ብለን ፈንነናል::  ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖሩ አማሮችን ፀረ ህዝቦች በጅምላ ሲያቃጥሏቸው እና የአንድት ነፍሰ ጡር እናትን ሆድ በስለት ሰንጥቀው ሽሉን ሲያፈነዱት አማራ የሆነ ፅንስ ጭምር መኖር የለበትም ብለው ማወጃቸው መሆኑን ልብ ይሏል:: አዲስ አበባ አማራ እንዳይገባ ሸኖ እና ሰንዳፋ ላይ በኦሮሞ መንገድ ሲዘጋበት እና በየጊዜው ሀገር አቋራጭ አውቶቢስ እየታገተ መንገደኞች ታፍነው ተወስደው በሸኔ ሲገደሉ፣ መስጅድ እና ቤተክርስቲያን ሲቃጠል አማኞችም ሲረሸኑ እንድሁም አማራ በመሆናቸው ብቻ ወገኖቻችን በኦሮሚያ ክልል በየጊዜው በኦነግ ሸኔ ሲገደሉ እና ሲፈናቀሉ ይህም አልበቃ ብሎ እዚሁ ክልላችን ውስጥ የአብይ መንግስት ተላላኪው ካድሬ ለአርሶ አደራችን በቂ ማዳበሪያ ላለማረቅብ ወስኖ አማራን በርሀብ እንቀጣለን ብሎ ቆርጦ ሲነሳ አስተውለናል:: ገበሬው "የገመድ መሬቴ ጦም አደረ" ብሎ ሰልፍ ሲወጣ "የጅራፍ ፓለቲካ" የሚል ስላቅ ነበር የብልጽግና መልስ:: ክልላችን ውስጥ የማዳበሪያ እጥረት የገጠመን ተረኞች ሆን ብለው ማዳበሪያውን ኦሮሚያ ክልል ከዝነውት ነበር:: ለአማራ ያላቸው ጥላቻ ከልክ ያለፈ ነው:: ስለሚፈሩን እንደምንም ብለው ለርሀብ እና ስደት እንድሁም ሞት እንድንጋለጥ ይሰራሉ:: ይህ ሴራቸው የገባውና ቀድሞ የነቃው ፋኖ በአራቱም የአማራ ግዛት አገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀውን አኩሪ ገድል ፈጽሟል:: ወገኖቻችንን አትግደሉብን ብለን ሰልፍ ስንወጣ "ልቅሶ አይሰለቻቸውም ወይ?" በማለት ሰላማዊ ትግልን ብልጽግናዎች አጣጥለዋል:: ችግር አለ ችግሩ ይፈታ ስንልም ችግር ፍቱልን ያለውን አካል በማሰር ነው መልስ የሰጡን:: ሰላማዊ አማራጭ እንደማያዋጣ አውቀን እጅጉን ተገፍተን እና ግፍ ተፈጽሞብን ዘራችንም እየሳሳ ስለሆነ ነው የትጥቅ ትግል የጀመርነው:: ይህን የህልውና ትግል ለማደናቀፍ የሚጥር ባንዳ ወዮለት:: ባንዳ የሆንክ ሁሉ ዋ! ለራሴ በል:: እንግዲህ ባንዳን አንምርም:: አንድት ብርጭቆ ውሀ ውስጥ ጠብታ አንድ መርዝ ከተጨመረ ውሀው ይመረዛል:: ንፁህ ህዝብ ውስጥ አንድ ባንዳ ካለ ህዝቡ በየጊዜው ዋጋ ይከፍላል:: በአንዳንድ ባንዳ ምክንያት ህዝባችን ዋጋ መክፈል ስለሌለበት ተባብረን ባንዳን እናፀዳለን:: ለዚህ ተልእኮ ደግሞ ህዝባችን ሊተባበረን ይገባል:: የአማራን ህዝብ ክብር እና ጥቅም የሚያስከብር እንዲሁም አማራ የሚለውን ስም በበጎ የሚያስጠራ የአባቶቻችንን አትንኩኝ ባይነት የሚዘክር ድንቅ ስራ እየሰራ ያለው የአማራ ፋኖን ከድሉ አደባባይ ሳይደርስ ለመመለስ የሚታትር ባንዳ መጨረሻው ሞት ነው:: ከእንግዲህ በራሳችን ባንዳዎች ላይ የምንወስደው እርምጃ ከባድ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም:: ፋኖ የበረሃው ሙቀት እና የደጋው ብርድ፤ የስንቅ እጥረት ብሎም የጥቁር አማሮች እንቅፋትነት ሳይበግረው የክረምቱ ዶፍ ዝናብ ሳይገታው ለአማራ ህዝብ ዘብ ሆኖ ሌት ከቀን ትንቅንቅ ላይ ነው። መከላከያ ሰራዊት የኦሮሞ ወንበር አስጠባቂ ዝና የአብይ አህመድ ገረድ ነው:: ይህን ሰራዊት አጥፍቶ አብይን ለፍርድ ማቅረብና የአማራን ህዝብ እንባ ማበስ የፋኖ ግደታ ነው:: አማራውያን ሆይ ሚሊሻ፣ አድማ ብተና እና ፓሊስ እንድሁም መከላከያ ውስጥ ዘመድ ወዳጅ ያላችሁ መክራችሁ ወደ ቤቱ አስገቡ። በተለይ ሚሊሻ በአስቸኳይ ቢቻል አዳሩን ወደ ቤቱ እንድገባ ይነገረው:: ይህ ሳይሆን ቢቀር እኛ እንግዲህ ባንዳን ስለማንምር በገቡበት ገብተን እንደመስሳለን:: ይህ አዋጅ ታውጆ የሚተርፍ ባንዳ ላይኖር ይችላል:: አንዳንዶች ተደብቀው ውለው ቢያድሩም መጨረሻቸው አያምርም! መንግስትን አሽመድምደነዋል:: ክልላችንን ከ80 ፕርሰንት በላይ ተቆጣጥረናል:: ይህን ሀቅ ቢቢሲም ለዓለም አውጆታል:: በቅርቡ የማዕከላዊ መንግስት መቀመጫ የሆነችውን አዲስ አበባ ከተማን እንደምንቆጣጠር ተገማች ነው:: አዎ፤ ፋኖ በጎጃም እና ሸዋ እንድሁም በሸዋ እና ጎንደር ብሎም ወሎ ሰፊ ግዛት ተቆጣጥሮ እያስተዳደረ ሲሆን ወደፊት የሚያደርገው ግስጋሴም እንደቀጠለ ነው:: በምዕራብ ወሎ ግንባርም ከፋሽስቱ አብይ አህመድ መንግስት በርካታ ቀጠናዎችን ነፃ አውጥተን የጊዜያዊ መንግስት መዋቅር ዘርግተን ህዝባችንን እያስተዳደርን ነው:: የድል ባለቤት መሆናችን አይቀርም፤ እውነትን ስለያዝንና ግፍ አንገሽግሾን ስለተነሳን እናሸንፋለን ስለዚህ ባንዳ ሆይ ቶሎ ወደ ቤትህ ተመለስ:: በየእለቱ የወገኖቻችን ደም እየፈሰሰ ነው:: ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍም በአማራ ምድር እየተፈፀመ ነው:: በያዝነው ወርም የካህን ሚስትን ጨምሮ በድምሩ 3 እመጫት እናቶች መካነሰላም ከተማ የሚገኘው አድማ ብተና ካምፕ ውስጥ በአንድ የፋሽስቱ መንግስት የፀጥታ ኃይል አባል መደፈራቸው ይታወቃል:: ከለላ ወረዳ ዉስጥም ቲርቲራ ታዳጊ ከተማ አጠገብ የቀነሶ መንደር ነዋሪ የሆነው አቶ ሁሴን ከማል የተባለው አርሶ አደር አጨዳ ላይ ሳለ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም በአድማ ብተናዎች እንደተረሸነ ለማረጋገጥ ችለናል:: ሰኞ ማለትም ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጃማ ወረዳ ደጎሎ ከተማ ውስጥ አንድት ከአረብ ሀገር ተመላሽ እህታችንን መከላከያ ሰራዊት ተኩሶ ገድሏታል:: ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር በሚንቀሳቀስበት በምዕራብ ወሎ ግንባር ብቻ ሳይሆን በመላው አማራ ዘግናኝ ግፍ በህዝባችን ላይ እየተፈፀመ ነው:: ይህ የግፍ ግፍ አንገፍግፍ ሊቆም የሚችለው አንድ ሆነን መታገል ስንጀምር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል::