es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
4 393
Suscriptores
+2924 horas
+2547 días
+1 45030 días
Archivo de publicaciones
አሳምነው ፅጌ አማራ ያላደረገው ሰው መቼውንም አማራ አይሆንም። መቼም! በታጋይ ማንችሎት እሱባለው ሰሞንን ያየነውም እንደዚያ ነው! እርምን የመብላት ትልቅና ልዩ የግርድና ምልክት ነው። ከብርጋዴል ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ውድ የህይወት መስዋዕትነት ጀርባ የነበሩ ፌዞች ሁሉ ህመም ቢበዛባቸውም በጊዜ ሂደት እንዲህ ቀስ እያሉ ይገለፃሉ። ፤ የ “አማራነት” መለኪያ መስፈርት እንስጥ ከተባለ አሳምነው ፅጌ የምሉዕነት መነሻ መስፈርት መሆን አለበት። !አሳምነውነት! ለአማራነት ርዕዮተ ዓለም “አቻ ፍቺ” መሆን ይችላል። ከወሬ በላይ መሆንን በሚጠይቁ ገቢራዊነት ላይ ብዙዎች የይሁዳን፣ እጅግ በጣም ጥቂቶች የጴጥሮስን መንገድ ሲከተሉ እስከ ህቅታ ድረስ ለቃል መታመንን እንደ በላይ ዘለቀ ያሳየን አሳምነው ፅጌ ብቻ ነው። አሳምነዉ የጀግንነት ጉልላት አናት ላይ ተቀምጦ፤ በትውልዱ የደም ህዋስ ውስጥ የሚመላለስ የፀፀት እሳት ነው። ፤ በውጊያ መሀከል ላይ… “ግባ የአሳምነው ልጅ፤ በለው የአሳምነው ልጅ፤ የአሳምነው ልጅ ያዘው፤ የአሳምነዉ ልጅ ይችላል፤ የአሳምነው ልጅ ልቡን ያመነው፤ የአሳምነው ልጅ የውድማው ዘንዶ፤ … በአደረጃጀት ስያሜ ላይ ደግሞ አሳምነው ሻለቃ፤ አሳምነው ብርጌድ፤ አሳምነው ክፍለ ጦር… ለልጃቸው የሚወጣን ስም ‘አሳምነው’ ብለው መጥራት…” ይህንን መሰል ብዙ ድምፀቶች ከብዙ አቅጣጫ የምንሰማው በምክንያት ነው። አሳምነውነት! ፤ አሳምነው ፅጌን መቼም መሆን አይቻልም፤ የእሱ መንገድ ግን ፈለጋችን ነው። ፅናቱንም ሆነ የመታመን ቁርጠኝነቱን እንዲሰጠን የዘወትር ምኞታችን ነው። የጠላት ፍላጎት በሚዲያ አጀንዳ ባደረገን ቁጥር ምላሽ የማንሰጠው አቋማችን ሁሉ “ቀበሮ የበግ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል ዋለች” ብለን ከጅምሩ ስለደመደምን ነው። ጀግና የሚለካው በመጨረሻ ተግባሩ ነው። ፤ ጀግንነት ሁሌም ወኔን ይጠይቃል። ጠሽ በምትል የመኪና ጎማ ፍንዳታ ሁሉ ልቡ ‘ጩርቅ ጪርቅ’ የምትል ሚዲያ ያገነነው ወለፈንዲ ሁሉ ወኔን አልታጠቀም። የትግሉን አቅጣጫና ሂደት በደም ንግድ አስልቶ፣ የቢያሸንፍና ቢሸነፍ ቢሆናል ትንተናን ሰርቶ፣ ነገር መሀላችን ላይ ሲያቦካ የሚውለው ብዙ ነው። ይህ መሰል ኃይል በሀቀኞች የትግል ሂደት ፌርማታው ላይ እየተራገፈ ጉዞው ይቀጥላል። ከዚህ ላይ “አሳምነውን ‘ጤና የሌለው እብድ’ ብለው የሰደቡት ሁሉ” አማራነትን የማያውቁ ሆድ አደር አድፋጭ ሀይሎች መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል። እነዚህን መሰል አካላት አሁንም መሀላችን ላይ አሉ።  {በአጋጣሚ የፋኖን ትግል ተቀላቅለው ‘ትግሉን በውስጠ መሰሪነት አሰራር እንዲንበረከክ’ የሚሰሩት ትላንት አሳምነውን አዋክበው በልተው፣ ወይንም ሲበላ ተባባሪ ሁነው፣ አልያም ደግሞ በኅልፈቱ የተደሰቱት ናቸው} ፤ ጀግንነት “አፄ ቴዎድሮስ ውሀ በተጠማ ጉረሮ መቅደላ አፋፍ ላይ እንደ ጠጣው ጥይት፤ በላይ ዘለቀ አዲስ አበባ ላይ እንደ ተሰቀለባት ገመድ፤ አቡኑ በ፰ ጥይት እንደተደበደበበት ባሩድ፤ ምኒሊክ ወረኢሉ ድረስ እንገናኝ ብለው እንዳወጁት ክተት፤  አሳምነው ፅጌ ‘ቀሪው ህይወቴን የምኖረው ለአማራ ህዝብ ነው’ እንዳለበት ድፍረት፤ ፊታችን ላይ ትግሉን አደራ እያሉን እንደወደቁት ወጣት፤…፤ ጀግነንት የሚለካው በመጨረሻው ሰዓት ነው። እንጅማ ሆድ ብዙ ስድብን ችሏል። ፤ ክብር ለማይበገረው የአማራ ህዝብ ይሁንና “የተሸነፈን ጠላት” ድልን ለማብሰር ጫፍ ላይ ነን። ፤ ህዝብ! በተለይ ደግሞ የአማራ ህዝብ ልበ ባህር ነው። አይደለም ትግልህን እያንዳንዷን እንቅስቃሴ በሚዛን ያስቀምጣል። “ምን እየተደረገ ነው?፣ ማን ምንድን ነው?፣ ምንስ እየተከፈለ ነው፣? ጉዞው ከየት ወደ የት ነው፣?” ሁላችንም ከፈጣሪ በታች በህዝብ ዓይን ክትትል ውስጥ ነን። “ህዝብ አየን አላየን” የሚል ይሉንታና ሀፍረት ህሊናችን ውስጥ መኖሩ ለብዙ ነገሮች መሻሻል ምክንያት ሁኖናል። ጥሩ አሳዳጊ ጥሩ ነው! ፤ አሁን ያለነውም ትግሉ ያስገኘውን ድል የመሸከፍ ሂደት ላይ እንጅ ጠላት የተሸነፈው ከሶስት ክረምት በፊት መዋቅሩን ያፈራረስንበት ዕለት ነው። ሚናን መለየት፣ የማይናወጥ አቋም መያዝ፣ የማይበገርን መንፈስ መላበስ፣ ከትርኪ ምርኪ ወሬና ሀሜት መራቅ፣ መደማመጥና መከባበር፣ ዋኖችን መጠበቅና በአይን ጥቅሻ መግባባት ለትግሉ መቋጨት የሚያስፈልጉ ግብኣቶች ናቸው። ከዚያ በመለስ ግን የጠላትን አጀንዳ ይዞ ወጥቶ በሽንፈት አምልጦ ለገባ ሁሉ የአጀንዳ ጊዜን ማባከን ተገቢ አይደለም። ፤ የአሳምነው መንገድ የህዝባችን ብቸኛ መዳኛ መንገድ ነው። መንገዱን ተከትለነው ጉዞ ከጀመርን ውለን አድረናል። ይህ መንገድ ፍፁም ነው። መንገድ መሀል ላይ ቅርብ አዳሪነትና ተሰባሪነትን አይፈቅድም። መዳረሻው መስዋዕትነት ወይም ድል ብቻ ነው። የሆነው ሁኖ ይህ ህዝብ “ፀሀይ በምዕራብ ወጣለች”በሚል The worst scenario ለዳግም ባርነትና ስቃይ ይዳረጋል የሚል መላምልት ቢኖር የሚፈፀመው በኛ መስዋዕትነት ላይ ብቻ ይሆናል። ፤ እናም አንዳንዴ እንዲህ እንናገራለን… ኮርኳሪ ሀሳቦቻችን እየጎፈነኑ ባይወደዱም እውነታው ግን አሳምነው ፅጌ አማራ ያላደረገው ሰው መቼም አማራ ሊሆን አይችልም። መቼም!… ግን ግን ደግሞ… ቃል ለምድር፣ ቃል ለሰማይ፤ አማራ በጥቂትና ቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ድል ላይ ቁሞ ይስቃል። አይዞን! ©ማንችሎት እሱባለው

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የመቄት ወረዳ ጊዚያዊ ሕዝብ አስተዳደር ሕዝብን ከማወያዬት ጎን ለጎን ንዑስ ወረዳዎችን እያደራጀ ይገኛል። ሕዝባችን የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ የገጠመዉን ሁለተናዊ የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በሚደረገው ብርቱ ጋድሎ ሕዝቡ ማድረግ ያለበትን አበርክቶ በእጅጉ ከፍ ለማድረግና አስተዳደራዊ ስራዎችን ፣ የፍትሕ አገልግሎትን ለማሳለጥ ለሕዝብ በሚመች መልኩ የሕዝብ አደረጃጀቶችን እየዘረጋ የሚገኝ ሲሆን ወረዳውን በንዑስ ወረዳ ፣ በቀበሌ ደረጃ እስከ ታች ደረስ የማደራጀት ስራዎች እየተሰራ ይገኛል። በመሆኑም በመቄት ወረዳ የሚገኙትን 36 ቀበሌዎችን በአራት (4) ንዑስ ወረዳ እየተደራጀ የሚገኝ ሲሆን የሰርኮ ንዑስ ወረዳ እና አንጀብ ደፈርጌ ንዑስ ወረዳ ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ ሲሆን ሌሎች ሁለት (2) ንዑስ ወረዳዎች ደግሞ በቅርቡ የሚጠናቀቁ ይሆናል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ) ህዳር 28/2018 ዓ.ም

የነበልባል ክፍለ ጦር ቃኚ ነብሮ ሻለቃ ቀንደኛውን ባንዳ ቀነደሹት። አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር። ህዳር 28/03/2018 ዓ ም በነበልባል ክፍለ ጦር ቃኚ
+1
የነበልባል ክፍለ ጦር ቃኚ ነብሮ ሻለቃ ቀንደኛውን ባንዳ ቀነደሹት።     አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር።    ህዳር 28/03/2018 ዓ ም  በነበልባል ክፍለ ጦር  ቃኚ /ተወርዋሪ/ ፋኖ አባሎች በተደረገ ከፍተኛ ክትትልና ጥናት  በዛሬው ዕለት  አቡሽ ደረጀ የተባለ ቀንደኛ የሚሊሻ አባል ላይ  የማያዳግም እርምጃ ወሰዱ።   ይህ ቀንደኛ ባንዳ በህዝብላይ ከፍተኛ የዘረፋና የማሸማቀቅ ስራ ላይ እንዳለ በነበልባሎቹ በተደረገበት የጥቃት ሙከራ ተደናግጦ ወደ ከተማ እንደሸሸ ከዚህ ቀደም ዘግበን ነበር።    ታዲያ መስረቅ የለመደ እናቱን ያስማማል እንደተባለው የለመደውን ዝርፊያ ለመቀጠል ተመልሶ በመምጣት ላይ እያለ በነበለባሎቹ ነብሮ ሻለቃ ፋኖዎች ብርቱ ክትትል ሳማ ሰንበት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከእጃቸው በማስገባት  4:45 ሰዓት ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን አሳውቀውናል።    ይህ የባንዳዎች ቁንጮ የሆነው ሚሊሻ በኦሮሚያ ክልል ደከቦራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከግብር አበሮቹ ጋር በመሆን የአማራን ህዝብ ሲያርድ እና ሲያፈናቅል ከነበረ ኦህዴድ መድረክ ላይ በመገኘት  እሱም አማራነቱን ክዶ አራጆቹ ለፈፀሙት ጀኖሳይድ ጭፍጨፋ በመደገፍ እወደድበታለሁ ያለውን ምንጃርኛ ዘፈን በማቅረ የአማራን ህዝብ አንገት ያስደፋ ድርጊቱ ብዙዎቹን እንዳስቆጣ ይታወቃል።        ነበልባሎቹ ከእኛ እጅ የሚያመልጥ ምንም ነገር የለም የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሲሉ ለተቀሩት የሚሊሻ አባሎች መማሪያ ይሁናችሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አድርሰውናል         ድል አ.ፋ. ብ. ኃ   ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት ድላችን በተባበረ ክንዳችን ህዳር 28/03/218  ነበልባል ክፍለ ጦር ሚዲያ ክፍል

ይቺን 4ደቂቃ የማትሞላ ንግግር አዳምጡና ፥ ለሁሉም አካፍሉ ። አማራ ለምን ፣ እንዴት ትግል እንደጀመረ እና የመዳኛ መፍትሄውን በአጭሩ ታገኙበታላችሁ። ... . "በሁሉም ቀጠና የአማራ ህዝብ ፥ ከጫፍ እስከ ጫፍ ያረጀ መሳሪያውን እየወለወለ ፥ ከጠላት ጋር ሲዋጋ የሚውለው ..   --ሰላም ስላጣ ነው ፣   --ሜዳ ላይ ስለወደቀ ነው ፣   --ፍትህ ስላጣ ነው ፣   --መኖር ስላልቻለ ነው ፣   --ሀገር አልባ ስለሆነ ነው ፣   --ማንነቱን ስለተነጠቀ ነው ፣   --እምነቱን ስላጣ ነው ።   ሌላ ታሪክ እኮ የለውም። እናም በራሳቸው ጊዜ ገፍተው ፥ ገፍተው ፥ ትናንት ከተውነው ፥ ትናንት ካስቀመጥነው ፥ የአባቶቻችን ነፍጥ ወስደው ከተቱን ። ይላል ሻለቃ  ዝናቡ በንዴት ..ጨምሮም .. አብይ አህመድ ሳይወድቅ ፣ እና የእኛን ወንድሞች በተገ*ደሉበት ጥይት ራሱም ሳይገደ*ል እረፍት የለንም ። " ይለናል ትግሉ በምስር ወጥ ሊሸጡ ከተደራደሩ ባንዳዎች እና ከሃዲዎች ውጪ ያላችሁ አማራውያን አድምጡት። ዱሩ ቤቴ

🔥#ከጎጃም (#ከአፋብኃ_ቴዎድሮስ_ዕዝ ) #የአፈነገጠ_ኃይል_የለም‼️ ትናት አዳሩን #ጠቅል_ሻለቃ በሻለቃ #ቃልኪዳን_ልቅናው እየተመራች ለወረራ በ3 አቅጣጫ የመጣውን ኃይል እንደ አመጣጡ በማስተናገድ ሸበል ዙሪያ ማንቆርቆይ ፣የትመንና ቢቸና ላይ አስደማሚ ስራ መስራቷንና ለወረራ የመጣውን የአገዛዙ ኃይል ንስር አማራ መዘገቧ ይታወሳል። ይሁን እንጂ በዚህ የተደናገጠው የአገዛዙ ኃይል ሆነ #እጅ_የሰጡ ሆድ አደሮች #ጎጃም_ላይ_አፈንጋጭ_ኃይል እንደተፈጠረ በማድረግ ከታች ባስቀመጥነው መልኩ ሲዘግቡ ተመልክተናል 👇👇👇👇👇👇👇👇 ሰበር በፋኖ በላይነህ ዋልተንጉስ በፋኖ አስጨንቅ ታደለ  በፋኖ ቃልየ ሊቁ እና በፋኖ ደምሰው ታመነ የሚመራ የፋኖ ቡድን  ከእነ ዘመነ ካሴ  አፈንግጦ በርኃ ገብቷል። ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ ይህ መረጃ መሰራጨቱን ተከትሎ በውስጥ መስመርም #ጠቅል_ሻለቃ አፈንጋጭ ናት እንዴ የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ በመጠየቃችን ይሁን እንጂ ተርፎን የምንጥለው ታጋይ ፣ የአፈነገጠ ቡድን የለንምና፣ እንኳን የአንድ ቀጠና የሁሉም ቀጠና በአንድነት እየመጣ ነው። ለማንኛውም አፈነገጡ የተባሉ ጀግኖች የአፋብኃን የስራ ስምሪት ከአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ መቶ አለቃ #አበበ_ሰውመሆንና አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ #ዳሞት_አለኸኝ የስራ ስምሪት ሲቀበሉ የሚያሳይ ምስል እንሆ አየይዛለች‼️ 28/ዐ3/2018 ዓ.ም

*የአብይ ሦስቱ ምርኩዞች፡-* አብይ አህመድ ሥልጣን የያዘው በአማራ ባንዳዎች እገዛ ነው።ወደ ሥልጣን ሲመጣ ሦስት ስልቶችን ነድፎ እና አመቻችቶ ነበር። - *አንደኛው* ምርጡ ስልት ምርጫ ቦርድን መጠቀም እና ሕጋዊ ወኪል መስሎ መቅረብ - *ሁለተኛው* ሰይጣናዊ ሥራው ክፉ ቀን ሲገጥመው ድሮን መጠቀም ነው ። - *ሦስተኛው* ስልት በተቃዋሚዎች ውስጥ ሰርጎ መግባት ነበር ። እነዚህን ወሳኝ ነጥቦች በሚገባ በመጠቀም ሕዝብ ሳይመርጠው ራሱን በራሱ ለሥልጣን ለማብቃት ምርጫ ቦርድን እንደ ማስመሠያ ተጠቅሞ መጥቷል። በምርጫው ቅሬታ ያቀረቡትን በሙሉ እያፈነ እየገደለ የፖለቲካውን መድረክ የኦሮሞ ብልጽግና ብቻ እንዲቆጣጠረው ብርቱ ጥረት አድርጓል ። አንደኛ እና ሁለተኛውን ሥራ ሰርቶ ከጨረሠ በኋላ በተቃዋሚዎች ውስጥ በሚቻለው መንገድ ሰርጎ በመግባት በታሪክ 5ኛ ረድፍ የሚባለውን አሻጥር ተጠቅሞ ፋኖን ለማጥፋት እየተንገዳገደ ይገኛል። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ይህን 5ኛ ረድፍ የሚባል አሻጥር እንደ ትግራይ ወንበዴዎች የተጠቀመበት ባይኖርም ይበልጡን ፤ኦነግ ሸኔ/ኦነግ አምስተኛ/በሚል የተጠቀሙበት የኦሮሞ ብልጽግና ናቸው። ለምሳሌ፡፣- አምስተኛ ረድፍ ተዋናዮች በባልና ሚስት ጸብ ውስጥ ሽማግሌዎች ጋር ተደባልቀው ገብተው መርዝ በመርጨት ፍች እንደሚፈጽሙ ሰዎች አይነት ናቸው። ይህን ዘዴ በመጠቀም አብይ አህመድ አምስተኛ ረድፈኞቹን ከኦሮሞ እና ከአማራ አስማርቶ በዘዴ የራሱን አጀንዳ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲቀበሉት ያደርጋል ፤ካልተሳካለትም ድርጅቶችን ይከፋፍላል። ከዚህም አንፃር እስክንድር ነጋ፥ ማስረሻ ሰጤ እና ሌሎችን የአማራ ባንዳዎችን ተቃዋሚ በማስመሰል የፖለቲካ ወሮበሎችን(political gangsters) አሰማርቶ የፋኖን ትግል ለመከፋፈል በጣም ደክሟል። የፖለቲካ ፓርቲ በማንፌስቶ የሚመራ መሆኑ ተወግዶ በገበያ ዋጋ የሚሸጥ ሸቀጥ የሆነውም በአብይ አህመድ ዘመን ነው ። በአሁኑም ወቅት የፋኖን ትግል ከድተናል፥ትግሉ አይረባም ፋኖ ይፍረስ እያሉን የሚገኙት ለሕዝብ መብትና ነጻነት ተቆርቁረው ሳይሆን የደለበ ቀለብ ከብልፅግና ለማግኘት የተቀጠሩ የመንፈስ ባሪያዎች ተግባር ነው ። ጅል አይሙት እንዲያጫውት ሆነና ነገሩ ፤አዳዲስ መንግሥት ሲመጣ በቀላሉ ለመክበር የሚሯሯጡ ገደል ሆድ የድሐ እና የለማኝ ልጆች አምስተኛ ረድፍ ሆነው የድሐን ልጅ ደም ቢዝነስ ፕሮፖዛል ይዘው ብቅ...ብቅ ይላሉ። በዚህ የመሐይም ፖለቲካ ትግበራ በአሁኑ ወቅት ከ135 በላይ በምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ እነ ሆድ አምላኩ መሐይም የፖለቲካ ቡድኖች ይገኛሉ። ዋና ሥራቸው ጠላት መስለው በመቆም የአማራ ሕዝብ እንዳይደራጅ እና ከጭቆና ነፃ እንዳይወጣ ተፅዕኖ መፍጠር፥አልፎ ተርፎም በማንነቱ እንዲጨፈጨፍ ከብልፅግና ወያኔ ሕገ አራዊት ጋር መስራት ነው ። ስለዚህ እስከንድር ነጋ እና ሌሎችም የተደበቁት የአፋሕድ አባላት በሙሉ ጸረ አማራ እና አገር አፍራሽ ተልዕኮ ያነገቡ መሰሪ እና መርዘኛ ግለሰቦች መሆናቸውን አውቆ መጠንቀቅ የመላው አማራ ሕዝብ ግዴታ ነው። በቀጣይ በእነ እስክንድር ነጋ ድል ለዲሞክራሲ የምትል ውሽት በርካታ የፖለቲካ መዘዞች እንደሚፈጠሩ እምነቴ ነው ።በትዕግሥት እንጠብቅ። በጊዜ ካልተገታ በስተቀር የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ብሎ አማራን አንድ አደርጋለሁ ማለት ፍጹም ደረቅ ውሸት ነው ። ሕዝባዊ ድርጅት የምትባለው የጨነገፈች ሕልም የብልፅግና ስውር ጨዋታ በመሆኗ የትም አያደርስም። በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይሎች ቀልድ የለም ብሎ የተነሳውን የአማራ ትውልድ በመግፋት ብልፅግናን ከመፍረስ ለማዳን አይቻልም። የሚይዙትን የሚጨብጡትን ያጡት የኦሮሞ አሸባሩዎች የጥርነፋ ፖለቲካ እና የ5ኛ ረድፍ ስውር ጠላትን በማስገባት የፋኖን የነፃነት ትግል ማቆም አይቻልም ። ድል ለአማራ ሕዝብ ድል ለአፋብሐ ጀግኖች 💪💪💪💪💪

የአማራ ተስፋዎች የአማራ ጠላቶች ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያሉ አደንዝዘውን ሲያበቁ ለይተው የጨፈጨፉን የድንዛዜ ዘመን አለፈ ይህ የድንዛዜ ዘመን አልፈን በተፈፀመብን ጭፍጨፋ ወደ ድንጋጤ ዘመን አደጋ ላይ መሆናችን ደነገጥን። የድንጋጤ ዘመን ይህንን ድንጋጤያችንን ወደ ስራ ለመለወጥ በጩኸት ተደራጅ ልትጠፋ ነው በሚል የአደጋ ጊዜ ጩኸት በመጮህ ህዝባችን እንዲደራጅ ተጠቀምንበት ድንጋጤያችንን ወደ ተግባር ስራ ተለወጠ። ህዝባችን መደራጀት ብቻ ስለማያድነው ታጠቅ አልነው የእርሻ በሬውን እየሸጠ ታጠቀ ከጠላት እየማረከ ታጠቀ ከመደራጀትም መታጠቅ ደረጃ ደርሶ ወደ ህዝባዊ ቁጣ ተቀየረ። እኛም ቀደም ብለን ተደራጅ ብለን የጀመርነው ጩኸት ወደ  ታጠቅ የሚል ሌላ ደረጃ አደገ ይህም ተፈፀመ ቀጥለን ታገል ለክብርህ ሙት ለማንነትህ ታገል የሚል ሌላ ጩኸት አሰማን ህዝባችንም ይህንን ተቀብሎን ጠላቶቹን ላይቶ ትግል ገባ እልልልል ያስብላል ይህ ሂደት እዚህ ላይ እየተፃፈው ቀላል የውሃ መንገድ አልነበረም ግንቦት ሰባትን የሚያህል ደንቃራ በዝረራ አሸንፈን ኦነግን ትህነግን ብአዴንን እረ ስንቱን እንቅፋት አሸንፈን ነው እዚህ የደረስነው አሁን ተደራጅተናል ታጥቀናል እየታገልን ነው ለዚህ ሁሉ መሰረቱ የአማራነት ብሔርተኝነት ነው በዚህ ዘመን ብሔርተኝነት ለልጆቻችንን ማስተላለፍ ሌላኛው ደረጃ ላይ ደርሰናል ይህ ብሔርተኝነት በብረት የታጀበ የምስራቅ አፍሪካ ኃያል ህዝብ ያደርገናል ብረትህን ጠብቅ ትጥቅህን አጥብቅ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ማዳኛህ ብረትህ ነው!!

የስልጠና ጥሪ ማስታወቂያ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክ/ጦር አዲስ  የፋኖ ሰልጣኝ አባላትን መልምሎ ማሰልጠን ይፈልጋል።   ማንኛውም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን  መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ሰልጣኞች መሠልጠን የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ። 1ኛ,ዕድሜ ከ18 አመት  በላይ የሆነ/የሆነች 2ኛ,ከደባል ሱስ ነፃ የሆነ/የሆነች 3ኛ,ከማንኛውም ወንጀል የፀዳ/ነፃ የሆነ/የሆነች 4ኛ,የሚሰጠውን  ማንኛውንም ግዳጅ በአግባቡ መወጣት የሚችል/የምትችል። 5ኛ,የጤና ችግር የሌለበት/የሌለባት 6ኛ ትግሉ እሥኪጠናቀቅ መክዳት መውጣት አይቻልም። 7ኛ የፋኖ ድርጂት የሚያወጣውን ህግ ማክበር ማሥከበር የሚችል/የምትችል። 8ኛ ፆታ አይለይም 9ኛ,የመመዝገቢያ  ቦታ ኃይለማሪያም ማሞ ክ/ጦር በሚንቀሳቀስበት በሁሉም ቦታዎች እንመዘገባለን ። 10ኛ,የመመዝገቢያ ቀን --01----4/2018 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም  አካባቢ የምትገኙ ወጣቶች ትግላችንን ለመቀላቀል መዋል ማደር ቅንጣት ሆኖበት በሰቆቃ ውሰጥ ለሚገኜው የአማራ ህዝብ በጋራ እንቁም።     ➔ የአፋብኃ ደ/አ/ቀ/አ/እ/አሳምነው እዝ ከሰም ኮር የኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር ሥልጠናና መምሪያ ኃላፊ።        "ህልውናችን በተባበረ  ክንዳችን"                              የአማራ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ከሰም ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል   ህዳር 28/2018 ዓ/ም

"የአፋር ሕዝብ በፌድራል መንግስት ተብዬው ስፖንሰርነት የተከፈተበተ ወረራ እንዲቀለበስ እየሰራን እንገኛለን" የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ከአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ! የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ባለፉት አንድ አመት አስደናቂና አመርቂ የመደራጀትና የማደራጀትን ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝና አሁን ላይ ወደ ሙሉ ማጥቃት ለመሸጋገር ሙሉ ዝግጅትችን ማጠናቀቃችን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው። ብልጽግና መሩ ጦረኛው የአብይ አህመድ አገዛዝ ያለጦርነት ውሎ ማደር አይችልምና አገሪቱን የጦርነት ሜዳ ከአደረጋት እነሆ ስምንት ዓመታት ተቆጠሩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብም በኑሮ ውድነት፣ በሰላም እጦት፣ በሙስና፣ ሌብነት : ከአቅም በላይ በሆነ የግብር ብዝበዛ፣ በእገታ እና ወ.ዘ.ተ. እየተሰቃዬ ይገኛል። የብልጽግና አገዛዝ ጦርነት እስትንፋሱ ነውና ውድ የኢትዮጵያ ልጆችን በካኪ ልብስ እየጠቀለለ ወደ ጦርሜዳ በመሸኘት እናት ያለጦሪ ቀባሪ እየወረች ትገኛለች፤ ወጣቶች አጽማቸው የት እንደወደቀ ሳይታወቅ የአሞራ ቀለብ ከሆነ አመታት ተቆጠሩ፤ በመሆኑም ይህ ጦረኛ አገዛዝ እንዲገረሰስ እኛ የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ሕዝባችን ከላላ አድርገን የአብይ አህመድ አገዛዝ ለመጣል ጠንካራ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን። ስለሆነም በዛሬው ዕለት ሕዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ለመስጠት ተገደናል። የሚከተሉት ነጥቦችንም መላው የአፋር ሕዝብ ብሎም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና የአብይ አህመድ ጦረኛ አገዛዝ ከሕዝብ ጫንቃ ላይ እንዲወርድ የሚፈልግ ኃይል ሁሉ ትኩረት እንዲሰጥበት ማሳሰብ እንፈልጋለን። 1ኛ. አሁን ላይ የአፋር ሕዝብንና የአፋር መሬትን ቁማር በማስያዝ የጦር ሜዳ ለማድረግ እየሰራ ያለው የአወል አርባ አገዛዝም ሆነ አለቃው አብይ አህመድ እያደረጋችሁት ያለው ነገር ትክክል አይደለም፤ የአፋር ሕዝብም ሆነ መሬት ነጻ ሊወጣ ይገባል እያልን በተለይ በአፋር መሬት ውስጥ ያላችሁ "ሀራ መሬት/ነጻ መሬት" በሚል የተደራችሁ የትግራይ የሰላም ኃይል ነን የምትሉ የአፋር ክልልን በአስቸኳይ ለቃችሁ እንድትወጡ እናሳስባለን። በዚህ ቀጥተኛ ተጎጅ የምትሆነው የአፋር ሕዝብም እነዚህ ኃይሎች ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ጫና እንድታደርግ እንጠይቃለን። 2ኛ. በሙስጠፌ መሐመድ የሚመራው የኢሳ ኃይል አሁንም የወሰንና የደንበር ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች በአፋር ሕዝብ ላይ ተከታታይ የሆኑ ኢ- ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በቀጣይ በምርመራ የምናጋልጠው ሁኖ ዛሬም በኢሳ ኃይሎች ልጃገረጆችን ጨምሮ እናቶች እየተፈሩና እየተገደሉ መሆኑን እየገለጽን የሚዲያ ኃይሎችና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና ተሟጋቾች የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ትኩረት እንድትሰጡ ማሳሳብ እንፈልጋለን። 3ኛ. የአወል አርባ አገዛዝ የአፋር ሕዝብን ጥቅምና መብት የሚከራከሩ ምሁራንን፣ ወጣቶችን፣ የፀጥታ ተቋማት አመራሮችን ዛሬም እያሳደደ፣ እያሰረ እና እየገደለ ይገኛል። ከዚህ ድርጊቱ እንዲታቀብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲታቀብ እያሳሰብን፤ ምሁራን፣ ወጣቶች፣ የፀጥታ ኃይሎች አጠቃላይ በአወል አርባ አገዛዝ እየተሳደዳችሁ ያላችሁ የአፋር ልጆች ወደ አፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን። 4ኛ. ጦረኛውን የአብይ አህመድ አገዛዝ እየታገላችሁ ያላችሁ ኃይሎች፦ አብይ መሩ የብልጽግና አገዛዝ አንድ ቀን በሰጠነው ቁጥር ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በዲፕሎማሲ እያንኮታኮታትና እየደፈቃት የሚገኝ ኃይል መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው። ይሄን ጉዳይ በአግባቡ በመረዳት የአብይ አህመድ አገዛዝን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ እንተባበር ስንል የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ጥሪውን በይፋ ያቀርባል። በመጨረሻም አንባገነን አገዛዞች እንደወደቁት፣ ጭፈራዎቻቸውም እንደተሳደዱት ሁሉ አንባገነኑ የብልጽግና አገዛዝ በቁርጠኛ ታጋዮች ይወገዳል፤ የአንባገነኑ መሪም ሆነ አገልጋዮቹ ለፍርድ አደባባይ እንደሚቀርቡ የአለም ታሪክ ምስክር ነውና ይህም በቅርቡ ይሆናል። አንባገነኑ ሕዝብ መጨፍጨፍ የስልጣኑ መሠረት ነውና ሎሌዎቹ ከሕዝብ ጎን እንድትቆሙ የመጨረሻ ጥሪ እናቀርባለን። ድልና ድምቀት ለአፋር ኡጉጉሞ! የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ህዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም

"የአፋር ሕዝብ በፌድራል መንግስት ተብዬው ስፖንሰርነት የተከፈተበተ ወረራ እንዲቀለበስ እየሰራን እንገኛለን" የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ከአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ! የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ባለፉት አንድ አመት አስደናቂና አመርቂ የመደራጀትና የማደራጀትን ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝና አሁን ላይ ወደ ሙሉ ማጥቃት ለመሸጋገር ሙሉ ዝግጅትችን ማጠናቀቃችን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው። ብልጽግና መሩ ጦረኛው የአብይ አህመድ አገዛዝ ያለጦርነት ውሎ ማደር አይችልምና አገሪቱን የጦርነት ሜዳ ከአደረጋት እነሆ ስምንት ዓመታት ተቆጠሩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብም በኑሮ ውድነት፣ በሰላም እጦት፣ በሙስና፣ ሌብነት :  ከአቅም በላይ በሆነ የግብር ብዝበዛ፣ በእገታ እና ወ.ዘ.ተ. እየተሰቃዬ ይገኛል። የብልጽግና አገዛዝ ጦርነት እስትንፋሱ ነውና ውድ የኢትዮጵያ ልጆችን በካኪ ልብስ እየጠቀለለ ወደ ጦርሜዳ በመሸኘት እናት ያለጦሪ ቀባሪ እየወረች ትገኛለች፤ ወጣቶች አጽማቸው የት እንደወደቀ ሳይታወቅ የአሞራ ቀለብ ከሆነ አመታት ተቆጠሩ፤ በመሆኑም ይህ ጦረኛ አገዛዝ እንዲገረሰስ እኛ የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ሕዝባችን ከላላ አድርገን የአብይ አህመድ አገዛዝ ለመጣል ጠንካራ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን። ስለሆነም በዛሬው ዕለት ሕዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ለመስጠት ተገደናል። የሚከተሉት ነጥቦችንም መላው የአፋር ሕዝብ ብሎም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና የአብይ አህመድ ጦረኛ አገዛዝ ከሕዝብ ጫንቃ ላይ እንዲወርድ የሚፈልግ ኃይል ሁሉ ትኩረት እንዲሰጥበት ማሳሰብ እንፈልጋለን። 1ኛ. አሁን ላይ የአፋር ሕዝብንና የአፋር መሬትን ቁማር በማስያዝ የጦር ሜዳ ለማድረግ እየሰራ ያለው የአወል አርባ አገዛዝም ሆነ አለቃው አብይ አህመድ እያደረጋችሁት ያለው ነገር ትክክል አይደለም፤ የአፋር ሕዝብም ሆነ መሬት ነጻ ሊወጣ ይገባል እያልን በተለይ በአፋር መሬት ውስጥ ያላችሁ "ሀራ መሬት/ነጻ መሬት" በሚል የተደራችሁ የትግራይ የሰላም ኃይል ነን የምትሉ የአፋር ክልልን በአስቸኳይ ለቃችሁ እንድትወጡ እናሳስባለን። በዚህ ቀጥተኛ ተጎጅ የምትሆነው የአፋር ሕዝብም እነዚህ ኃይሎች ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ጫና እንድታደርግ እንጠይቃለን። 2ኛ. በሙስጠፌ መሐመድ የሚመራው የኢሳ ኃይል አሁንም የወሰንና የደንበር ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች በአፋር ሕዝብ ላይ ተከታታይ የሆኑ ኢ- ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በቀጣይ በምርመራ የምናጋልጠው ሁኖ ዛሬም በኢሳ ኃይሎች ልጃገረጆችን ጨምሮ እናቶች እየተፈሩና እየተገደሉ መሆኑን እየገለጽን የሚዲያ ኃይሎችና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማትና ተሟጋቾች የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ትኩረት እንድትሰጡ ማሳሳብ እንፈልጋለን። 3ኛ. የአወል አርባ አገዛዝ የአፋር ሕዝብን ጥቅምና መብት የሚከራከሩ ምሁራንን፣ ወጣቶችን፣ የፀጥታ ተቋማት አመራሮችን ዛሬም እያሳደደ፣ እያሰረ እና እየገደለ ይገኛል። ከዚህ ድርጊቱ እንዲታቀብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲታቀብ እያሳሰብን፤ ምሁራን፣ ወጣቶች፣ የፀጥታ ኃይሎች አጠቃላይ በአወል አርባ አገዛዝ እየተሳደዳችሁ ያላችሁ የአፋር ልጆች ወደ አፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን። 4ኛ. ጦረኛውን የአብይ አህመድ አገዛዝ እየታገላችሁ ያላችሁ ኃይሎች፦ አብይ መሩ የብልጽግና አገዛዝ አንድ ቀን በሰጠነው ቁጥር ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በዲፕሎማሲ እያንኮታኮታትና እየደፈቃት የሚገኝ ኃይል መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው። ይሄን ጉዳይ በአግባቡ በመረዳት የአብይ አህመድ አገዛዝን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ እንተባበር ስንል የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ጥሪውን በይፋ ያቀርባል። በመጨረሻም አንባገነን አገዛዞች እንደወደቁት፣ ጭፈራዎቻቸውም እንደተሳደዱት ሁሉ አንባገነኑ የብልጽግና አገዛዝ በቁርጠኛ ታጋዮች ይወገዳል፤ የአንባገነኑ መሪም ሆነ አገልጋዮቹ ለፍርድ አደባባይ እንደሚቀርቡ የአለም ታሪክ ምስክር ነውና ይህም በቅርቡ ይሆናል። አንባገነኑ ሕዝብ መጨፍጨፍ የስልጣኑ መሠረት ነውና ሎሌዎቹ ከሕዝብ ጎን እንድትቆሙ የመጨረሻ ጥሪ እናቀርባለን። ድልና ድምቀት ለአፋር ኡጉጉሞ! የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ) ህዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም

#ሰርቶ_መብላት_እንጅ_ተንኮል_የማያውቀው_ሸበል_በረንታ_የሽፈራው_ሀገር_የወንዶች_ሀገር_ነው። የጀመርነው ትግል የዋዛ የመሰላቸው ብዙ ካድሪዎች በአማራ ፋኖ ቅንድባቸውን እየተላጩ እስከ ወዳኘው ተሸኝተዋል። ትግል በውጭ እንደምናየው ውስጡ በርግጥ እንዲህ እንደዋዛ አይደለም! በውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን በቀጠናችንም የሚገኙ ሆዳም/አሳማ ካድሪዎች ጭንቀት እየጨመረ መምጣቱን አረጋግጠናል። የአገዛዙ ቅጥረኛ ካድሪዎች አሁን ላይ 64ኛ ክፍለ ጦር እየወሰደ ባአለው እርምጃ ዘመኑን በአወጀ የድርጅቱን አደረጃጀት መሬት ላይ አውርዶ እየሰራ ያለው አደረጃጀት በስጋት እና በጭንቀት ውስጥ ከገቡ ውለው አድርዋል። በርግጥ ትላት በተለያየ ምክንያት ያልሰራናቸው ስራዎችን አሁን ላይ እየሰራናቸው እንገኛለን። በዚህ ሰዓት ይህንን አረመኔዊ ስረዓት አፈር ደሜ አብልቶ የሚማርክ፣ የሚደመስስ ሰራዊት እየገነባን እንገኛለን። ህዝባችን ከትላንቱ የበለጠ አጀረጃጀቱን በመዘርጋት፣ ወጣቱን ብአዴን ከዘረገው ከተለያዩ ሱሶች አውጥተን በማደራጀት የአማራ ህዝብ ወቅታዊ የፖለቲካ ሸፍጥ እያስተማርን ሀገር ወዳድ ለአማራነቱ የሚሞት የሰለጠነ ወታደራዊ ኃይል እየገነባን እንገኛለን። ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል የማንከፍለው መስዋትነት የለም! በአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነብንን የህልውና አዳጋ ለመመለስ የማናደርገው ነገር ሁሉ የለም? በትግሉ ላይ የምንገኝ ታጋይ የፋኖ አባላት እና አመራር በሙሉ ጠላቶቻችን የብአዴን አመራሮች መንገድ እየመሩ፣ ትዛዝ እየሰጡ በህዝባችን ላይ እየፈፀሙብን ያለውን ግፍ እና መከራ ተረድተን ሁላችንም ለህዝባችን አዛኝ ሆነን በጠላቶቻችን ሀብት ንብረት እንዲሁም በራሳቸው ላይ #ከባድ_እርምጃ የምንወስድ ይሆናል። የሽፈራው ገርባው የበላይ ዘለቀ የትውልድ ቦታ ሸበል በረንታ በታሪክ አጋጣሚ እንድንመራ ድርጅታችን እና ህዝባችን ታላቅ ኃላፊነት ሰጥቶናል። ይህ ቀጠና ባንዳ እና ሰላቶ፣ ከአማራነቱ ይልቅ ሆዱ የሚበልጥበት #አሳማ_ካድሪ እንደማይኖርበት እርግጠኞች ነን። ከታች የምትመለከቶችው የሽፈራው ገርባው ልጆች ከውስጣቸው የወጡ ባንዳዎችን የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አባላትን ለመፋለም  የተኩስ ልምምድ ወስደው ተመርቀው ወደ ትግል ተቀላቅለዋል። ሙሉ ቪዲዮውን ለማየት በመረጃ ቲቪ ይከታተሉ🙏🙏🙏 አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!             ህዳር 28/2018 ዓ.ም

"አማራ በፍርሃት አይለካም። አማራ በልፍስፍስነት አይለካም። በጀግንነት! በአሸናፊነት! በሀገር መሪነት! በሀገር መስራችነት ነው የሚለካው "መመዘኛው እሱ ነው ሆኖም የኖረው ያንን ነው! እንደጀመርነው
+2
"አማራ በፍርሃት አይለካም።   አማራ በልፍስፍስነት አይለካም።    በጀግንነት!      በአሸናፊነት!       በሀገር መሪነት!         በሀገር መስራችነት ነው የሚለካው "መመዘኛው እሱ ነው ሆኖም የኖረው ያንን ነው! እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን💪 አርበኛ ሳሙኤል ባለዕድል የአፋብኃ ሴንተራል ኮማንድ አባልና የበላይ ዘለቀ ዕዝ  ም/ሰብሳቢ ና ወታደራዊ አዛዥ።💪🔥

#ጠቅል_ሻለቃ_አዳሩን_የተለያዩ_ቦታዎችን_አጠቃ‼️ ህዳር 21/3/2018 ዓም ሌሊት ጠቅል ሻለቃ ቢቸና ከተማ ላይ ሰርጎ በመግባት በቦምብ ሲያጋየው ማደሩ ይታወሳል። አገዛዙ ይህንን ጥቃት ተከትሎ በር
#ጠቅል_ሻለቃ_አዳሩን_የተለያዩ_ቦታዎችን_አጠቃ‼️ ህዳር 21/3/2018 ዓም ሌሊት ጠቅል ሻለቃ ቢቸና ከተማ ላይ ሰርጎ በመግባት በቦምብ ሲያጋየው ማደሩ ይታወሳል። አገዛዙ ይህንን ጥቃት ተከትሎ በርካታ ኃይል ሲያስገባ የሰነበተ ሲሆኝ እንደ አመጣጡ አናብስቶች ሲያስተናግደው ቢቆይም ዛሬም አዳሩን በድጋሚ  ጠላት እንደለመደዉ ፋኖን በለሊት ለማፈንና ጥቃጥ ለመፈፀም በሶስት አቅጣጫ ከበባ አድርጎ ወደ ፋኖ ካምፕ ቢተምም #ጠቅል_ሻለቃ በጀግናው #ሻለቃ_ቃልኪዳን_ልቅናዉ  እየተመራች #ቀዶ_ጥገና አድርጋለች፣ በዚህም:- 👉 ሸበል ዙረያ ማንቆርቆይ፣ 👉የትመን እና ቢቸና ማረሚያ ቤቱ ላይ ጠላትን ሰርጎ በመግባት በውስን የሰው ኃይል ፣ በነፍስ ወከፍ መሳሪያና ቦምብ በተመሳሳይ ሰዓት ሲያናዝዙት አድረዋል💪 የቃልየ ቀኝ እጅ የሆነዉ ፋኖ ቦንቦኛዉ #ዮሐንስ ትዕዛዙን በመቀበል ቢቸና ከተማ ላይ ከጠላት ጋር ተፋጦ ሰርጎ በመግባት ማረሚያ ቤቱ ላይ ቦንብ በመጣል በጠላት ላይ ጉዳት በማድረስና የስነልቦና ጫና በመፍጠር ነፍሴ አውጭኝ በማለት ወደ ቢቸና ከተማ ፈርጥጦ እንዲመለስ ተደርጓል ሲሉ አናብስቶች ለንስር አማራ ገልፀዋል‼️    #ሳተናዉ_ጠቅል_ሻለቃ_ይችላል💪💪💪💪💪 28/ዐ3/2018 ዓ.ም