YD airdrop
الذهاب إلى القناة على Telegram
airdrops will be released on this Telegram channel 2nd channel
إظهار المزيد1 460
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-77 أيام
-3230 أيام
أرشيف المشاركات
1 460
Repost from ትምርት ሚንስትር
ቻይና 🇨🇳 አማርኛ ቋንቋ ማስተማር ጀመረች 🇪🇹
ሩሲያ 🇷🇺 የአማርኛ ቋንቋ ማስተማር መጀመሯን ካወጀች ሳምንታት በኋላ ቻይናም ለቻይና ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ መጽሃፍ ማከፋፈል ጀምራለች።
ቻይናውያን በግጥም በአማርኛ ማንበብ ጀምረዋል።
1 460
••●🍃ልረሳሽ አልቻልኩም••●🍃
አማራጭ አጥቼ የግድ ሲሆንብኝ፣
እምረሳሽ መስሎኝ መጠጥን ለመድኩኝ፣
ተዋት እንኳን ቢሉኝ እኔ መች ሰማሁኝ፣
አንቺን ረሳሁ ብዬ በሱስ ተጠመድኩኝ፣
በጫት በሲጋራ እራሴን ደበቅኩኝ።
፡
ምናልባት ሆኖ...
ልቤ ፍቅርን አምኖ..
የኔ ባትሆኝም፣
ፈጣሪ ባይፈቅድም፣
አንቺ የሌላ ሆነሽ በአይኔ እንኳን ባይሽም፣
ያፈቀረሽ ልቤ ፈፅሞ አልረሳሽም።
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢
ሼር 💚 t.me/yeyonii
1 460
ይህን ያዉቃሉ?🤔
አይበለዉና በስናይፐር ቢመቱ ድምጹን ሳይሰሙት ነዉ የሚሞቱት ምክንያቱም የስናይፐሩ ጥይት ከድምጹ ስለሚፈጥን ነዉ🔫
https://t.me/yeyonii
1 460
Repost from N/a
🌹🌹🌹በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!🌹🌹🌹
🌹🌹🌹ሥርዓተ ሕማማት!🌹🌹🌹
🌹እንበለ ደዌ ወሕማም፤
🌹እንበለ ጻማ ወድካም፤
🌹ዓመ ከመ ዮም፤
🌹ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤሁ በፍስሓ ወበሰላም አሜን!!!
🌹በስሙነ ሕማማት ማማተብ ፣ ማዕድ መባረክ ፣ መልክዐ መልክ ስለ መድገም
🌹ሰሙነ ሕማማት ከገባ ጊዜ ጀምሮ ማማተብ ፣ ማዕድም ሲቀርብ ባርኮ መቁረስና ስለ እነሱ ብሎ ቡራኬ መስጠት ስለ መከልከል!
🌹በሰሞነ ሕማማት መልክዐ መልኮች አይደገሙም ፣ የሃይማኖት ጸሎት ሲደገምም "ስለኛ ተሰቀለ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ ሞተ ተቀበረ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ..." እስከሚለው ድረስ ከሰኞ እስከ ሐሙስም አይደገምም!
🌹በሰሞነ ሕማማት እስከ አንድ ሰዓት እንድንጾምም ሥርዓት ተሰርቷል!
🌹ስንዱዋ እመቤት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሰሞነ ሕማማት በጉባዔ ፣ በአደባባይ ፣ በይፋ የሚደረገውን ነው፡፡ በብዙኃን ፊት ቡራኬ መስጠት ፣ የሞተ መፍታት ፣ መስቀል የማሳለምን ሥርዓት ትከለክላለች፡፡
🌹ይህም ፭ ሺህ ፭ መቶ ዘመን ዓለም በማእሠረ ሰይጣን እንዳለ ፣ በግዞት በመርገም ውስጥ እንደነበረ ለማስታወስ ነው እንጂ ማዕዳችሁን አትባርኩ የሚል ሥርዓት አልተደነገገም፡፡
🌹በግሉ አንድ ሰው ፊቱን በትእምርተ መስቀል አማትቦ መጸለይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰው ካላማተበ የአጋንንትን ውጊያ ድል መንሣት አይችልም፡፡ ስለዚህ በግል ጸሎት አታማትብ አይባልም፡፡ አይከለከልም፡፡
🌹የሃይማኖት ጸሎትም ሲደገም ፦ "ስለ እኛ ተሰቀለ ፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ ፣ ሞተ ፣ ተቀበረ ፣ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ" እስከሚለው ድረስ ከሰኞ እስከ ሐሙስ አይደገምም "ሐመ" ብለው ይተውታል፡፡ ይሄ ታሪኩን ለማስታወስ ነው፡፡ ጸሎቱ የሚከለከል ሆኖ እንዳይደለ ልብ ይሏል፡፡ ወቅቱን እየጠበቅን ድርጊቱን ለማስተማር ነው፡፡
🌹ይኸውም ሰኞ ፣ ማክሰኞ ፣ ረቡዕ ፤ ሐሙስ መከሩ ከሐሙስ እስከ ዓርብ ሌሊት መከራውን ተቀበለ ፤ ዓርብ ስድስት ሰዓት ላይ ተሰቀለ እንላለን ፤ ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ "ሞተ ተቀበረ" ይባላል፡፡ "ተነሣ" የምንለው ደግሞ ቅዳሜ በሌሊት ስድስት ሰዓት ነው፡፡ ያንን በየሰዓቱ የተደረገውን ታሪክ ለማስታወስ ፣ ለመግለጽ ፣ ለማስተማር ነው፡፡
🌹መልክዐ መልኮች አለመደገማቸው ደግሞ ወደ ነገረ መስቀሉ ለማድላት ነው፡፡ ነገረ መስቀሉ ከሁሉ በላይ ነውና፡፡
🌹ዓለም የዳነው በጌታችንና በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካሳነት ነው ፤ ይህንን የምናስታውስበት በስሙነ ሕማማት የእርሱን ካሳነት በፍጹም ተመስጦ እናስባለን እንጸልያለን፡፡
🌹በሰሞነ ሕማማት በቂ ጊዜ ስለማይኖር ወደ ቅዱሳን ገድል ትሩፋት ድጋም [ጸሎት ፣ ንባብ] አንሄድም፡፡
🌹ነገር ግን ጊዜ ከተገኘ በሕማማት ቢሆን የቅዱሳንን ገድሎች እናነባቸዋለን፡፡ የሰዓት ቁጠባ ነው እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት የለውም፡፡
🌹ግብረ ሕማማቱ እራሱ በየሰዓቱ የተዘጋጀ የራሱ ጸሎት አለው፡፡ በእረፍት ሰዓት ግን ገድሎችንም ሆነ ስንክሳርን እናነባለን፡፡ ከሰዓት አንጻር የሚታይ ነው፡፡
🌹ወደ ነገረ መስቀሉ ለማድላት ሕማሙን ሞቱን መከራውን ለእኛ ያደረገውን ካሳ በስሙነ ሕማማት በፍጹም ልቡና ለማሰብ ቅድሚያ ለእርሱ እንዲሰጥ ነው፡፡
ይቆየን!
ማንኛውንም ያለችሁን ጥያቄ በዚህ ማድረስ ትችላላችሁ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/orthodoxppp
https://t.me/orthodoxppp
1 460
አሁን እኔ ብሞት ፣ ከኔ ምን ይቀራል?
ስኖር "ክፉ" ያለኝ
"ደግ ሰው ነበረ " ፣ እያለ ያወራል።
።።።
"እሱ ሰው አይደለም" ፣ ሰይጣን ነው መሠሪ"
ሲለኝ የከረመ ፣
"መልካም ሰው ነበረ ፣ መልአክ መሥሎ ኗሪ
ብሎ ቀብሬ ላይ ፣ እንባውን ይዘራል
መቼም በዚህ ሀገር
ሲኖር የተናቀ ፣ ሲሞት ይከበራል ።
* * * *
የሚጠላኝ ሁላ
ተወዳጅነቴን ፣ ቀብሬ ላይ ያወሳል
መቼም በዚህ ሀገር
ሲኖር የሚነቀፍ ፣ ሲሞት ይወደሳል
ሲኖር የተረሳ ፣ ሲሞት ይታወሳል!!!
።።።
1 460
እኤአ በ 2015 በተደረገ ጥናት
😔በአለም ላይ አብዛኛው ፖሊሶች የሚሞቱት እራሳቸውን በማጥፋት ነው
ይህም የሆነው ከስራዉ ውጥረት የተነሳ ነው😥
https://t.me/yeyonii
1 460
👐#አስተማሪ የፍቅር ታሪክ💝
🚶♀አንድ ሴት መንገድ ላይ እየሄደች አንድ ልጅ ከኋላዋ ሲሮጥ ሰምታ ዞር አለች "ባንቺ ውስጥ ሴትነት ውበት አለ ወደድኩሽም" አላት 💔
😁ፈገግ ብላ "ከኔ በላይ ቆንጆ እና በሴትነቷም ከኔ የተሻለች ጓደኛዬ ከኋላክ አለች " ስትለው ዞሮ ፈለገ ግን ምንም ሴት አላየም" የታለች?" አላት እሷም #ፈገግ ብላ"ወደኸኝ ቢሆን ኖሮ ሌላ ባልፈለክ ነበር " ብላ መንገዷን ቀጠለች።
👌በአንድ ምክንያት የሚወድህ ሰው በሌላ ምክንያት ይለይሀል ለምን እንደሚወድህ የማያውቀው ግን ሁሌም ቢሆን ይወድሀል💔💓.....
መልካም አዳር 🙏
💛 💛https://t.me/yeyonii
https://t.me/yeyonii
#ሼር
