YD airdrop
الذهاب إلى القناة على Telegram
airdrops will be released on this Telegram channel 2nd channel
إظهار المزيد1 460
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-77 أيام
-3230 أيام
أرشيف المشاركات
1 460
አቤት ውሸት🙄
ጨረቃን በገሶ ቆፍሬ ቆፍሬ፣
ለጆሮ የሚጥም አግንቻለሁ ወሬ። 🤗
በዘይት የጣፈጠች እንደ በቆሎ እሸት፣😋
ልሰጥ ነው አድምጡኝ ጥሩ ጥሩ ወሸት። 😜
እንደሚታወቀው አሳ የረገጠው፣😳
ከሞትም በስተቀር መዳኒትም የለው። 🤷♀
አንዴ ለሽር ሽር ስሄድ ወደ ጫካ፣ 🕴
ሳር ሲግጥ ያየሁት አሳ ኖርዋል ለካ። 🙀
በረጅሙ እግሩ አንዴ ሲመታኝ፤ 🤕
ያለሁበት ቦታ ጨርሶ ጠፋኝ። 🙄
አንድ ፈረስ መጥቶ ከሞት የጠነባ፣ 🤧
እንደምንም ብሎ ቤቴ ይዞኝ ገባ። 🤦♀
ደሞ አህያን አየሁ👀 ሲወላገድ ሰክሮ፣😃
በገንዘቡ ይሆን? 🤔ወይስ ተበድሮ?🙄
ጠይቄው ነበረ.........
ለሽንቱ ሲወጣ
አህያ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣ፣
" እቁብ ደርሶኝ ነው"ብትፈልግ ና ጠጣ፤😄
ብሎኝ ስቆ 😊ገባ ኮካዉን ሊጠጣ።
ለሰው ልጅ ተስማሚ ነው ጥብስም ሆነ ቅቅል፣😆
በአይኔ አይቻለሁ 👀 በግ እንቁላል ሲጥል።
ብታምኑም ባታምኑም ካለዚያም ልተወው፣🤷♀
ማስረጃ አቀርባለሁ ይ ሁሉሉሉሉሉሉ ውሸት ነው። 🤗🤣🤣
.
1 460
// እቀፊኝ \\
----------------------------------------------
ሰማዩ ይጠቅለል
ምድር ትተጣጠፍ፣
የወደድኩሽ አንቺን
አቅፌሽ ልንሳፈፍ።
እንወድቃለን ብለሽ
ከቶ አትጨነቂ፣
ማንም ያላወቀው
መልአክ መሆንሽን ድንገት እንድታቂ።
ወደቅን ስንባል
ክንፎችሽ ይዘርጉ፣
ለኔ የሚታየኝ ብርሀንሽን አይተው
ጨለማና ፅልመት ድንገት ይሸሸጉ።
ከዚ አለም ውሰጂኝ
ካንቺ ገነት ልኑር፣
ከእቅፍሽ አልውጣ
ህይወቴ እንዲሰምር፣
ሲኦልሽ ውሰጂኝ
እኔ እንደሆን አልቀር።
አንቺ ካለሽበት
ገነት ነው የኔ አለም፣
ካንቺ ጋራ ሆኜ
እሳት ቢበላኝም።
እንጦሮጦስ ይሁን
ብወርድም ግድ የለኝ፣
ተራራን አክሎ
መብረቅ ቢዘንብብኝ፣
አውሎ ንፋስ መጥቶ
ወስዶ ቢያንገላታኝ፣
ለኔ ምንም ነው
አንቺ ካለሽልኝ፣
መከራው ቢበዛ
ለሰከንድ አትራቂኝ፣
በይ እቀፊኝ፣
ስታቅፊኝ፣
ችግር ምን እንደሆን
ስለምታስረሺኝ እቀፊኝ፣
ዘላለም እቀፊኝ።
ተፃፈ ምድራዊ መልአክ ለሆኑ ሴቶች::
💚https://t.me/yeyonii 💚
❤️ https://t.me/yeyonii
