ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

الذهاب إلى القناة على Telegram
1 331
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+97 أيام
+8030 أيام
أرشيف المشاركات
photo content
+9

እንኳን ደስ አለን!!✊
እንኳን ደስ አለን!!✊

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እና የማኔጅምንት አባላት በቢሮውና በኮሌጆች ቅንጅት የሚሰሩ የአቅመ ደካሞችን ቤት በአዲስ የመስራት መርሐ-ግብር አስጀመሩ፡፡ **** በዚህም አቶ ሮቤል ጌታቸው እና ማኔጅመንታቸው በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 05 እና በወረዳ 08 የሚገኙ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ መርሐ-ግብር ዛሬ አስጀምረዋል። የቢሮ ኃላፊው የቤት እድሳት መርሐ-ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅቱ እንደገለጹት፣ በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሕይወትን ማሻሻል የመንግሥት ዋነኛው ትኩረት እንደሆነ ገልጸው የቢሮ ተልዕኮም ሰው ተኮር እንደመሆኑ መጠን በመሰል ተግባራት ላይ ቢሮው በመሳተፉ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። በመርሐ-ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም በአስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት ኮሌጆች የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች በዚህ ክረምት በወረዳ 02 እና በወረዳ 01 የሚገኙ ጨምሮ 7 ቤቶችን በአዲስ የሚሰሩ ሲሆን የቤት ዕድሳት የተጀመረላቸው ነዋሪዎችም የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

"የአድራ አይነት መሰል ፕሮጀክቶች እንደ አገር የተቀረጹ ፖሊሲዎችን ወደ ተግባር በማውረድ ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረጉ ረገድ የሚጫወቱት ሚና ላቅ ያለ ነው፡፡" አቶ ሮቤል ጌታቸው የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ =============================== በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኘውን ተፈጥሮ የለገሰችውን የጸሃይ ኃይል ያለ ምንም ጥቅም ለዘመናት ትርጉም ያለው ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል ምስጋና ለአድራ ኢትዮጵያ ከአድራ ጀርመኒ ጋር በመተባበር በጀርመን መንግስት ድጋፍ ለሶላር ፒቪ ዝርጋታ እና ጥገና የሚሆን የማሰልጠኛ ወርክሾፕ በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በማዘጋጀት በመጀመሪያ አመት ትግበራው ቀላል የማይባሉ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ በትላንትናው ዕለትም አድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በSolar PV Instalation ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ለሚገኙትን 48 ሰልጣኞች በተለያዩ Unit of Competency በማሰልጠን አስመርቋል ሰልጣኞቹ በንድፈ ሀሳብ ሲከተታተሉ የቆዩትን ስልጠና ስራ ቦታው ላይ በአካል ተገኝተው በተግባር የሰለጠኑ ሲሆን ይህም ሰልጣኞቹ በቀጣይ ወደስራ አለም ሲገቡ በእጅጉ የሚያግዛቸው ይሆናል:: አድራ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ላለፉት አመታት የተለያዩ የልማት ስራዎችን በተለይ የነብስ አድንና ዜጎችን ህይወት መለወጥ ላይ ትኩረት አድርጎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ሲሰራ የቆየና አሁንም እየሰራ ያለ ድርጅት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የአስተዳደሩ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በቀጣይ ፕሮጀክቱ ተደራሽነቱን በሚያሰፋበትና በአስተዳደሩ ላይ በተመዘገበው ውጤታማ አፈጻጸም ጥራትን አስጠብቆ በሚቀጥሉበት አግባብ ላይ ከፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ እና የጀርመን ዳይሬክተሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+4

"የአድራ አይነት መሰል ፕሮጀክቶች እንደ አገር የተቀረጹ ፖሊሲዎችን ወደ ተግባር በማውረድ ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረጉ ረገድ የሚጫወቱት ሚና ላቅ ያለ ነው፡፡" አቶ ሮቤል ጌታቸው የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ =============================== በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኘውን ተፈጥሮ የለገሰችውን የጸሃይ ኃይል ያለ ምንም ጥቅም ለዘመናት ትርጉም ያለው ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል ምስጋና ለአድራ ኢትዮጵያ ከአድራ ጀርመኒ ጋር በመተባበር በጀርመን መንግስት ድጋፍ ለሶላር ፒቪ ዝርጋታ እና ጥገና የሚሆን የማሰልጠኛ ወርክሾፕ በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በማዘጋጀት በመጀመሪያ አመት ትግበራው ቀላል የማይባሉ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ በትላንትናው ዕለትም አድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በSolar PV Instalation ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ለሚገኙትን 48 ሰልጣኞች በተለያዩ Unit of Competency በማሰልጠን አስመርቋል ሰልጣኞቹ በንድፈ ሀሳብ ሲከተታተሉ የቆዩትን ስልጠና ስራ ቦታው ላይ በአካል ተገኝተው በተግባር የሰለጠኑ ሲሆን ይህም ሰልጣኞቹ በቀጣይ ወደስራ አለም ሲገቡ በእጅጉ የሚያግዛቸው ይሆናል:: አድራ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ላለፉት አመታት የተለያዩ የልማት ስራዎችን በተለይ የነብስ አድንና ዜጎችን ህይወት መለወጥ ላይ ትኩረት አድርጎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ሲሰራ የቆየና አሁንም እየሰራ ያለ ድርጅት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የአስተዳደሩ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በቀጣይ ፕሮጀክቱ ተደራሽነቱን በሚያሰፋበትና በአስተዳደሩ ላይ በተመዘገበው ውጤታማ አፈጻጸም ጥራትን አስጠብቆ በሚቀጥሉበት አግባብ ላይ ከፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ እና የጀርመን ዳይሬክተሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

ዓመታዊ የአካባቢ እና ማህበራዊ ኦዲት ግኝት ሪፖርት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክንቺ ኮሌጅ ለEASTRIP ግንባታ ፕሮጀክት ቀረበ። በኦዲት ሪፖርቱ ላይ በመገኘት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ዲን አቶ ሳ
+3
ዓመታዊ የአካባቢ እና ማህበራዊ ኦዲት ግኝት ሪፖርት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክንቺ ኮሌጅ ለEASTRIP ግንባታ ፕሮጀክት ቀረበ። በኦዲት ሪፖርቱ ላይ በመገኘት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን ሲሆኑ አቶሳሊም በንግግራቸው ይህ የEASTRIP ፕጀክት በኮሌጁ ሲገነባ በአለም ባንክና በኢትዮጵያ በጸደቀው የአካባቢ እና ማህበራዊ ደረጃዎች ላይ መሰረት አድርጎ ስራዎችን እየሰራ እንዳለና በግንባታው ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችም ማህበረሰቡ ላይ ተጽእኖ ከማምጣጡ በፊት እየተከታተለ ለችግሮቹ መፍትሄ እየሰጠና ድጋፍና ክትትሎችን እያደረገ እንዳለ በሪፖርቱ ወቅት ገልጸዋል፡፡ ዓመታዊ የአካባቢ እና ማህበራዊ ኦዲት ግምገማው በድሬዳዋ አስተዳደር አካባቢ፣ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የተካሄደ ሲሆን በግምገማው መሰረት የግንባታ ፕሮጀክቱ በአለም ባንክ የአካባቢ እና ማህበራዊ ደረጃ እንዲሁም በኢትዮጵያ በጸደቀው አዋጅ እና በፀደቀው እየተተገበረ እንዳለ ተገልጿል። በኦሪት ሪፖርቱ ወቅት የተገኙ EFCC ባለስልጣን ተወካዮች አንዲሁም ተሳታፊ አካላት እንደ ተናገሩት ኮሌጁ እየተከተለ እንዳለው ስርአት መሰረት የመንግስት እና የግል ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በESIA መስፈርት እና አዋጅ መሰረት መተግበር አለበት ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ። የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ነሀሴ 2/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

አድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በSolar PV Installation Maintenance በመጀመርያ ዙር ያሰለጠናቸውን ሰልጣኝ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል። የዛሬ ተመራቂዎች በአድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) ከኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በአጫጭር ስልጠና በSolar PV Installation Maintenance ላለፉት 8 ወራት  ሲሰለጥኑ የቆዩ ሲሆን በዚህም 30 ወንድ እና 18 ሴት እንዲሁም 3 አካል ጉዳተኞች በድምሩ 48 ሰልጣኝ ተማሪዎች በዛሬው እለት ለምረቃ በቅተዋል:: ተመራቂ ተማሪዎቹ በሰለጠኑት ስልጠና የሶላር ሲስተም ጥገናን በሚፈለገው ልክ ተደራሽ ለማድረግ የብቃት ምዘና(COC) በብቃት በማጠናቀቅ ወደ ስራ አለም ለመግባት መዘጋጀታቸውም ተገልፇል:: በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ ለመገኝት  የአድራ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ የተለያዩ ሀላፊዎች ከአዲስ አበባ የተግኙ ሲሆን ከምረቃ ፕሮግራም መጠናቀቅ በኃላ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በኮሌጁ አካሂደዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ነሃሴ 2/2016 ዓ.ም

photo content
+9

Repost from N/a
photo content
+9

Repost from N/a
የአድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) ፕሮጀክት የ2016ዓ.ም የፕሮጀክቱን አመታዊ አፈፃፀም ሪፖርት ለኮሌጁ ማኔጅመት አቀረበ:: በዕለቱ በቀረበው ሪፖርት አድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ)ፕሮጀክት በአመቱ የተሰሩ ስራዎችንና የተመዘገቡ ውጤቶች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም በፕሮጀክቱ ትግበራ ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የተወሰዱ መፍትሄዎችም ጭምር በፕሮጀክቱ ሀላፊ አማካኝነት ለኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል:: የማኔጅመንት አባላቱ በመቀጠል በአመቱ የአድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) ፕርጀክት በሰልጣኝ ተማሪዎቹ የተሰሩ ፕሮጀክቶችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል:: በመጨረሻም አድራ ኢትዮጵያ(ድሬዳዋ) በዘንድሮ ዓመት በSolar PV Instalation ያሰለጠናቸውን 48 ሰልጣኝ ተማሪዎቹን ነሃሴ 2/2016 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ የሚያስመርቅ መሆኑም ተገልፇል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም

በድሬዳዋ አስተዳደር የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አባላት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመስክ የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡ በመስክ ጉብኝቱ ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኮሌ
+4
በድሬዳዋ አስተዳደር የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አባላት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመስክ የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡ በመስክ ጉብኝቱ ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ም/ዲና እና የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጣና ኃላፊ አቶ ሰልሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ በንግግራቸውም እንኳን ወደ ምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ወደ ሆነው የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በደህና መጣችሁ ኮሌጁ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ብዙ ሺህ ወጣቶች የሙያና የክህሎት ባለቤት ያደረገ ኮሌጅ ነው ኮሌጁ አሁን ለደረሰበት ስኬትም የከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም የኮሌጁ ማህበረሰቦችና ባለድርሻ አካላቶች የማይተካ ሚና አላቸው ያሉ ሲሆን ኮሌጁ በቀጣ የባቡር ምህንድስና እና የICT የልህቀት ማእከል እንደመሆኑ መጠን ከድሬዳዋ አስተዳደር ስር ከሚገኙ ተቋም ጋር በርከት ያሉ ስራዎችን በጋራ የምንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡ በመስክ ምልከታው ወቅት የተሳተፉ የፖሊስ አባላት እንዳሉት አጠቃላይ የኮሌጁ እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ጥሩ የሚባልና በኮሌጁ ውስጥ እየተገነባ የሚገኘውም የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት መአከል ግንባታ በከፍተኛ ፍጥነት ተከናውኖ ለሚፈለገው አላማ መዋል እንዲችል እየታየ ያለው ርብርብ በጣም አስደማሚ ነው በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ያላቸው አቅም ከሌሎች ኮሌጆች አንጻር ከድሬዳዋ አልፎ ለምስራቁ የሀገራችን ክፍሎች የሚበቃ ነው ያሉ ሲሆን ይህንን አቅም በተገቢው መንገድ በጋራ እየተጠቀምን ከተማችንን በጋራ የምናለማ ይሆናል ብለዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ነሀሴ 1/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስር መተግበር ላይ ያለው የEASTRIP እናየ SIFA ፕሮጀክቶችን በምስራቅ አፍሪካ የፕሮጀክቶች አስተባባሪ ከሆነው ከ IUCA እና ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር የተውጣጡ ኃላ
+8
በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስር መተግበር ላይ ያለው የEASTRIP እናየ SIFA ፕሮጀክቶችን በምስራቅ አፍሪካ የፕሮጀክቶች አስተባባሪ ከሆነው ከ IUCA እና ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር የተውጣጡ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች አመታዊ የስራ አፈጻጸም ግምገማ አከናወኑ፡፡ ለግምገማው የመጣውን ልኡክ ቡድን የተቀበሉትና የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር እንዲሁም የኮሌጁን ሁኔታ ለልኡክ ቡድኑ ያብራሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን ሲሆኑ በመቀጠልም ስለ ልህቀት ማእከሉ የህንጻ ግንባታ እና የSIFA ፕሮጀክቶች እንዲሁም አሁን ያሉበትን ሁኔታና በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች በአቶ መሳይ ጥላሁን የEASTRIP ፕሮጀክት M&E አማካኝነት ቀርቧል፡፡ ከ IUCA እና ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር የተውጣጡ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች በኮሌጁ ውስጥ እየተገነባ ያለው የልህቀት መአከሉን ግነባታ እንዲሁም ከኮሌጁ ጋር ትስስር ባላቸው ኢንዱስትሪዎች ውስጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ከሪፖርቶና ከመስክ ጉብኝቱ በኋላ በቀረበው አፈጻጸም ላይ ልኡክ ቡድኑ የተለያዩ ገንቢ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን በመጨረሻም በፕሮጀክቱ የስራ አፈጻጸም እጅግ እንዳስደመማቸው እና ለፕሮጀክቱ መሳካት እየተሰሩ ያሉ ድጋፎችን አድንቀዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ነሀሴ 1/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2016 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የኮሌጁ ሰራተኞች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት የእውቅና እና የምስጋና መርሃ ግብር አካሄደ፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት በስራ ክህሎት ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደገለጹት ኮሌጁ ባለፉት አመታት ያስመዘገባቸው ስኬቶች በሙሉ እንደ ሃገር ልምድ የሚቀሰምባቸውን ትልልቅ ተግባራትን ያከናወነና በነዚህም ተግባራት ደግሞ በሃገር ደረጃ ስኬትን ማምጣት የቻለ አንጋፋ ኮሌጅ ነው፡፡በኮሌጁ የተገኙ ስኬቶች ደግሞ የአመራሩ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የኮሌጁ ሰራተኞች ድርሻ ትልቁን ቦታ የሚወስድ ነው ብለዋል፡፡ በመጨረሻም በቀጣይ የEASTRIP እና SIFA ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደስራ ሲገባ ደግሞ አሁን ከተገኘው ስኬት በላይ የላቀ ስኬቶች ይገኛሉ ለዚህ ደግሞ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊዘጋጁ ይገባል ብለዋል፡፡ ኮሌጃችን በ2016 በጀት አመት ያስመዘገባቸው ስኬቶች በሙሉ የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላቶች ነው ለነዚህ ባለድርሻ አካለቶች ደግሞ ምስጋናና እውቅና መስጠት ያስፈልጋል ያሉት ደግሞ የኮሌጁ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን ናቸው፡፡ አቶ ሳሊም በማስቀጠልም በ2016 በጀት አመት የተመዘገቡ ስኬቶች በ2017 ተጠናክረው መቀጠልና እንደ ሃገር ለሚገኙ ስኬቶች የሚጠበቅብንን ድርሻ መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡በመጨረሻም ለዚህ መርሃ ግብር መሳካት ትልቁን ድርሻ ለወሰዱት ለኮሌጁ ማኔጅመንት፣ለኮሌጁ ሰራተኞች፣ባለድርሻ አካልት፣ የEASTRIP ፕሮጀክት አባላት እንዲሁም ለኮሚቴ አባላት በኮሌጁ ሰራተኞች ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡ በእለቱ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት ኢኮኖሚ እና የንግድ ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት አይናለም ተዘራ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት ኢኮኖሚ እና የንግድ ኢንዱስትሪ ጉዳዮች አማካሪ ክቡር አቶ ሽመልስ፣በስራ ክህሎት ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ፣የኮሌጁ ማኔጅመንትና እና ሰራተኞች እንዲሁም ባለድርሻ አካለት ተገኝተዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ሀምሌ 28/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ