ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

الذهاب إلى القناة على Telegram
1 331
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+97 أيام
+8030 أيام
أرشيف المشاركات
ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር አንፃር በቀጣይ በጀት አመት በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ       የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ 2016 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም እና የ 2017 በጀት አመት እቅድ ዙሪያ የቢሮው አመራሮች እና በየደረጃው ያሉ ሰራተኞች ተሳታፊ የሆኑበት የውይይት እና የግምገማ መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል ።     በያዝነው በጀት አመት ከስራ እድል ፈጠራ አንፃር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረው በተለይም የስራ እድል ፈጠራዎቹ የዜጎችን ህይወት ከመቀየራቸውም በላይ ለሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት አይነተኛ አስተዋፆ እንዳላቸውም ነው አቶ ሮቤል ያስታወቁት ።     በገጠር የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በስራ እድል ፈጠራ ተጠቃሚ ከማድረግ ጋር ተያይዞ በቀጣይ በስፋት ከመሰራቱም በላይ ፋሚሊ ቢዝነስ ላይም በርካታ ስራዎችን ለመስራት መታቀዱን የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ወ\ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናግረው በተለይም ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የአርሶ እና አርብቶ አደሩን ኑሮ በቴክኖሎጂ የማሻሻል ስራዎች እንደሚሰራም ነው ወ\ሮ ፈጡም ያስታወቁት ።     በእለቱም በበጀት አመቱ የተሰሩ እንዲሁም ደግሞ በ 2017 በጀት አመት ለመስራት የታቀዱ ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይትም ተደርጓል ። ©️ የድሬዳዋ መንግስት ኮምኒኬሽን

photo content
+5

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በስሩ ከሚገኙ ኮሌጆች ጋር በ2016 ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸምን መነሻ በማድረግ የ2017 በጀት አመት ዕቅድን የማናበብ ስራ ተሰራ። ይህ የዕቅድ ማናበብ በኤጀንሲው የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ፤ የአሰልጣኝ ልማትና የተቋማት ጥራት ቁጥጥር እና የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬቶች ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ማለትም ከድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ እና ከኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ጋር የዘርፉን ተልዕኮ በቅንጅትና በመናበብ ለማሳካት የሚያስችል ይሆናል። የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+6

የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ "ብቃት" የወጣቶች ስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ለወጣቶች በተከታታይ ዙሮች የሚሰጠው መሠረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በመሰጠት ላይ ይገኛል፤ በአስተዳደሩ ቀላል የማይባሉ እድሜያቸው ከ18-25 የሆኑ ወጣቶችን ከስራ ጋር እያስተሳሰረ ሁለተኛ አመት በትግበራ ላይ የሚገኘው "ብቃት" የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ወጣቶች በህይወት ክህሎት እንዲበቁ በማድረግ የተግባቦት አቅማቸውን በማሳደግ ቴክኒካል ክህሎቶችንና የሥራ ባህልን በተግባር እንዲያዳብሩ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል። በተለይ የሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ሚና በዚህ እረገድ ወሳኝ ሆኖ የሚታይ ሲሆን ሰሞኑን በተከታታይ የሚሰጠውም መሠረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት ስልጠና ማሳያ መሆኑን በቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ የገለጹ ሲሆን አክለውም ብቃት የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ለአምስት ዓመት የሚተገበር መሆኑና ከ70 ሺ በላይ ወጣቶችን ቋሚ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን አስታውሰው እንደ አስተዳደር በመጀመሪያው ዓመት የፕሮግራሙ አፈጻጸም በተሰራው ስራ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተገኙ ውጤቶችን አስጠብቆና አስፍቶ በመስራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+7

photo content

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ "ብቃት" የወጣቶች ስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሁለተኛ ዙር ትግበራ ለወጣቶች  መሠረታዊ የኮምፕዩተር ስልጠና መስጠት ተጀመረ፤ እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር በ2016 ዓ.ም እየተተገበረ የሚገኘው ሁለተኛው ዙር "ብቃት" የወጣቶች ስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም የ10 ቀን የህይወት ክህሎት ሰልጠና ወስደው ተግባራዊ የሥራ ላይ ልምምድ በተለያዩ በአስተዳደሩ የሚገኙ ኢንደስትሪዎች ላይ ስድስት ወራት የሚፈጀውን ውጤታማ ቆይታ እያደረጉ ለሚገኙ ወጣቶች መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ ይህንንም ስልጠና በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እየተከታተሉ የሚገኙ ወጣቶች በአጠቃላይ በፕሮግራሙ ተጠቃሚነታቸው በአመለካከት፣ በክህሎት እንዲሁም በዕውቀት ከዚህ በፊት ከነበሩበት የተሻለ ነገሮችን የመረዳትና የማድረግ አቅም እያዳበሩ እንደሚገኙ የተናገሩ ሲሆን መሠረታዊ የኮምፒውተር ስልጠናው በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅም በተመሳሳይ ከነገ ጀምሮ የሚሰጥ ይሆናል። የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኑነት ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ "ብቃት" የወጣቶች ስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሁለተኛ ዙር ትግበራ ሦስተኛው ዙር የአቻ ለአቻ ውይይት ተደረገ፤      ወጣቶቹ  በየወሩ የአቻ ለአቻ  ውይይት  በማድረግ  በየጊዜው ያገኙትን እውቀት  የገጠማቸውን ችግሮች  ለይተው የተወያዩበት መድረክ  ሲሆን ይህ  ለሦስተኛ ጊዜ የተዘጋጀ  ውይይት የተደረገ ሲሆን የስራ ላይ ልምምዱን ሲያጠናቅቁ  በተቀጠሩበት ወይም በሚቀጠሩበት ድርጅቶች በሰለጠኑት ሞያ መሰረት ለማገልገል እራሳቸውን የሚያዘጋጁበትና እርስበርሳቸው የሚመካከሩበት ይሆናል፡፡      በዚህም ውይይት ላይ ተሳታፊ የሆኑ ወጣቶች በአጠቃላይ በፕሮግራሙ ተጠቃሚነታቸው በአመለካከት፣ በክህሎት እንዲሁም በዕውቀት ከዚህ በፊት ከነበሩበት የተሻለ ነገሮችን የመረዳትና የማድረግ አቅም እያዳበሩ እንደሚገኙ የተናገሩ ሲሆን በተለይ እርስ በዕርስ በመነጋገር ችግሮችን የፈቱበትና የተሻለ ዕውቀት የቀሰሙበት እንደነበር ተናግረዋል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ "ብቃት" የወጣቶች ስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ለወጣቶች በተከታታይ ሦስተኛው ዙር የአቻ ለአቻ ውይይት ተደረገ፤      ወጣቶቹ  በየወሩ የአቻ ለአቻ  ውይይት  በማድረግ  በየጊዜው ያገኙትን እውቀት  የገጠማቸውን ችግሮች  ለይተው የተወያዩበት መድረክ  ሲሆን ይህ  ለሦስተኛ ጊዜ የተዘጋጀ  ውይይት የተደረገ ሲሆን የስራ ላይ ልምምዱን ሲያጠናቅቁ  በተቀጠሩበት ወይም በሚቀጠሩበት ድርጅቶች በሰለጠኑት ሞያ መሰረት ለማገልገል እራሳቸውን የሚያዘጋጁበትና እርስበርሳቸው የሚመካከሩበት ይሆናል፡፡      በዚህም ውይይት ላይ ተሳታፊ የሆኑ ወጣቶች በአጠቃላይ በፕሮግራሙ ተጠቃሚነታቸው በአመለካከት፣ በክህሎት እንዲሁም በዕውቀት ከዚህ በፊት ከነበሩበት የተሻለ ነገሮችን የመረዳትና የማድረግ አቅም እያዳበሩ እንደሚገኙ የተናገሩ ሲሆን በተለይ እርስ በዕርስ በመነጋገር ችግሮችን የፈቱበትና የተሻለ ዕውቀት የቀሰሙበት እንደነበር ተናግረዋል፡፡ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+8

#ጥቆማ ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን #ኮደሮችን ለማሰልጠን ያለመ ፕሮጀክት አስጀምራለች። ለ3 ዓመታት ያህል የሚቆየው ይሄ ፕሮጀክት ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ (UAE) ጋር በመተባባር የሚተገበር ነው ተብሏል
#ጥቆማ ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን #ኮደሮችን ለማሰልጠን ያለመ ፕሮጀክት አስጀምራለች። ለ3 ዓመታት ያህል የሚቆየው ይሄ ፕሮጀክት ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ (UAE) ጋር በመተባባር የሚተገበር ነው ተብሏል። ምን መማር ይቻላል ? - Android Kotlin Development Fundamentals - Data Science Fundamentals - Programming Fundamentals ትምህርቱን እንዴት ማግኘት ይቻላል ? ስልጠናዎቹ በዩዳሲቲ (Udacity) በተሰኘው ኦላይን የትምህርት ፕላትፎርም ተዘጋጅተው የቀረቡ ናቸው። ሰልጣኞች ያለ አንዳች ክፍያ በነጻ ኮምፒውተራቸውን ወይም ስልካቸውን በመጠቀም መሰልጠን ይችላሉ። ስልጠናዎቹ 6-7 የሚሆኑ ሳምንታትን የሚፈጁ ሲሆን በማጠቃለያው ላይ ሞያዊ ሰርተፊኬት ይሰጣል። የስልጠናዎቹን ይዘት እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎች በተዘጋጀው ድረ-ገጽ ( https://ethiocoders.et/ ) ላይ መመልከት ይችላሉ።

የሐዘን መግለጫ --------------------- በቢሯችን የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሞያ አቶ ነጋሽ በላይነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶናል። የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎት
የሐዘን መግለጫ --------------------- በቢሯችን የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሞያ አቶ ነጋሽ በላይነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶናል። የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለቢሮው ማህበረሰብ መፅናናትን ይመኛል::

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በአስተዳደሩ ስር ከሚገኙ የከተማ እና የገጠር አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ማስተባበሪያ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር  የ2017 በጀት ዓመት ለወረዳዎቹ የተሸነሸነ ዕቅድ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡ በዚህም የውይይት መድረክ ላይ ማዕከላቱን የሚመለከቱ ሥራዎችን በመቁረስ በከተማና በገጠር ለሚገኙ አንድ ማዕከላት ማውረድ የተቻለ ሲሆን በቀጣይም በመናበብ የአስተዳደሩን ነዋሪ ተደራሽና ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን በተጨባጭ ለመስራት አስፈላጊውን ምችችት እንደሚደረግና የሚታይ ውጤትና ለውጥ ለማምጣት ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የቢሮው ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ገልጸዋል፡፡ ዕቅዱን ወደ ታች ሸንሽኖ ከማውረድ ስራው ጎንለጎን የሥራ ዕድል የማመቻቸት እና የመፍጠር አቅምማጎልበቻ ሰነድ ቀርቦ በቀጣይ በዋናነት በአገራዊና በዘርፉ አዲስ ዕሳቤዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ ይዞ የተናበበና የተቀናጀ ሥራ መስራት እንደሚገባ በማመላከት በማጠቃለያው በክረምት በንቅናቄ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች በወረዳዎች ቀርበው ተገምግመዋል፡፡ የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በአስተዳደሩ ቀበሌ አስተዳደር ስር ከሚገኙ የከተማ እና የገጠር አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ማስተባበሪያ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር  የ2017 በጀት ዓመት ለወረዳዎቹ የተሸነሸነ ዕቅድ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡ በዚህም የውይይት መድረክ ላይ ማዕከላቱን የሚመለከቱ ሥራዎችን በመቁረስ በከተማና በገጠር ለሚገኙ አንድ ማዕከላት ማውረድ የተቻለ ሲሆን በቀጣይም በመናበብ የአስተዳደሩን ነዋሪ ተደራሽና ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን በተጨባጭ ለመስራት አስፈላጊውን ምችችት እንደሚደረግና የሚታይ ውጤትና ለውጥ ለማምጣት ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የቢሮው ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ገልጸዋል፡፡ ዕቅዱን ወደ ታች ሸንሽኖ ከማውረድ ስራው ጎንለጎን የሥራ ዕድል የማመቻቸት እና የመፍጠር አቅምማጎልበቻ ሰነድ ቀርቦ በቀጣይ በዋናነት በአገራዊና በዘርፉ አዲስ ዕሳቤዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ ይዞ የተናበበና የተቀናጀ ሥራ መስራት እንደሚገባ በማመላከት በማጠቃለያው በክረምት በንቅናቄ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች በወረዳዎች ቀርበው ተገምግመዋል፡፡ የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

photo content

በሳዑዲዓረቢያ ተቀጥረው ለመሥራት የሠለጠኑ ሥራ ፈላጊዎች የቅድመ ጉዞ ስልጠና ተሰጣቸው!! በኢትዮጵያ እና ሳዑዲዓረቢያ መንግሥት ሥምምነት መሰረት ወደ ሳዑዲዓረቢያ ከሚሔዱ ሥራ ፈላጊ ዜጎች መካከል በድሬዳዋ  አስተዳደር በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ 52 ሰልጣኞች ጉዞ ከማድረጋቸው በፊት አስፈላጊ  የሆነ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ የሚያስቸላቸው ገለጻ በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የውጭ አገር ስራ ስምሪትና የሰራተኞች ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባሙያዎች ተደርጎላቸዋል። በዚህም ከሃገር ውጭ ለስራ ጉዞ ሲያደርጉ ቅድመ ጉዞ መደረግ እና ማሟላት የሚገባቸውን እንዲሁም በጉዞ ላይ እና ለስራ በሚሄዱበት አገር ሊገጥማቸው የሚችሉ ጉዳዮችን በተብራራ መልኩ ማግኘታቸው በቂ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ሰልጣኞች ተናግረዋል። የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ