Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 319
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+127 أيام
+14830 أيام
أرشيف المشاركات
በአስተዳደሩ ገጠር ወረዳዎች ለሚገኙ የ2017 ዓ.ም ቅድመ ሞዴል የ2018 ዓ.ም ለሞዴል ኢንተርፕራይዞች በኢንተርፕርነርሽፕ እና በቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ላይ ሰልጠና ተሰጠ።
በዚህም ስልጠና የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾችን ባገኙት ዕውቀትና ክህሎት ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግና ያላቸውን ልምድ እርስ በእርሳቸው እንዲለዋወጡ ለቀጣይም የዕድገት ደረጃ ለማብቃት አቅማቸውን የሚገነባ ይሆናል።
በስልጠና መድረኩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በአስተዳደሩ ገጠር የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑን አስታውሰው መሰል ስልጠናዎች ከፍ ባለ ደረጃ አቅማቸውን እንዲጠቀሙ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 27/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ ምሩቅ ስራ ፈላጊዎች በድሬዳዋ ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል ለማሳየት ፍላጎትና ተነሳሽነታቸውን ከፍ የሚያደርግ ለዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጅ ምሩቃን ስራ ፈላጊዎች ሲሰጥ የነበረው የማይንድ ሴት ስልጠና ተጠናቀቀ።
በአስተዳደሩ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ስልጠናው የነገ ሃገር ተረካቢ የሆኑ ወጣት ምሩቃንን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል አስተሳሰብ እንዲይዙ የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።
ስልጠናው የአስተዳደሩን ወጣቶች የስራ ባህል በማዳበርና የወጣትነት አቅማቸውን በመጠቀም ውጤታማ ተግባራትን መስራት እንዲችሉ ያበረታታል ያሉት አቶ ሮቤል ወጣቱ በተሰጠው ዕድል ተጠቅሞ ሀገርን ለመገንባት የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት የሚጠይቅ መሆኑንም ገልጸዋል።
ኃላፊው አክለው ወጣትነት ሙሉ አቅምን፣ እውቀትንና ክህሎትን ተጠቅሞ ለመጪው ጊዜ መሰረት የሚሆን የህይወት መስመር የሚዘረጋበት አልባሌና አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ንቆ በመተው ጊዜን ሙሉ በሙሉ ለጠቃሚ ነገሮች በማዋል ተዓምር የሚመስሉ ነገሮችን ማሳካት የሚቻልበት የዕድሜ ክልል መሆኑን በማውሳት በስልጠና ያገኙትን እውቀት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም በህይወታቸው ተጨባጭ ለውጥና ስኬት ለማምጣት መትጋት እንደሚኖርባቸውም ተናግረዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 27/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ለሪፎርም አስተግባሪ ኮሚቴ አባላት የግንዛቤ መስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የሥራና ክህሎት ሚንስቴር ዕቅድን መነሻ በማድረግ የቢሮው ዕቅድ መዘጋጀቱንና ሪፎርም አስተግባሪ ኮሚቴዎችንም ከቢሮው እስከ ወረዳ አንድ ማዕከላት ድረስ እንዲሁም በፖሊቴክኒክ ኮሌጆች መዋቀር በቢሮው ማኔጅመንት እንዲጸድቅ ማድረግን ተከትሎ የተዘጋጀ ሆኗል፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት ቢሮው ይህን በአገር አቀፍና በአስተዳደር ደረጃ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን የሪፎርም ስራዎች እንቅስቃሴ ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመፈጸም የሚያስችለውን ስራዎች በአግባቡ መርቶ ከዳር ለማድረስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 27/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ለዩኒቨርስቲ እና ኮሌጅ ምሩቃን ስራ ፈላጊዎች የኢንተርፕርነርሺፕ እና የማይንድ ሴት ስልጠና በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።
ስልጠናው በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት ስራ ፈላጊዎች ተቀጥሮ መስራት ላይ ብቻ ሳይሆን በግልም ሆነ ተደራጅተው ስራ እንዲፈጥሩ በሚያነሳሳ መልኩ እየተሰጠ መሆኑን የዳይሬክቶሬቱ ተወካይ ወ/ሮ ቤተልሄም ድንበሩ ተናግረዋል።
በዚህም ተሳታፊ የሆኑ የዩኒቨርስቲ እና የኮሌጅ ምሩቃን ስራ ፈላጊዎች ከዚህ በፊት ተቀጥሮ ለመስራት ብቻ ይጠብቁ የነበሩ ከስልጠናው በሚያገኙት ግንዛቤ በግልም ሆነ ተደራጅቶ ለመስራት መነሳሳት እንዲፈጠርባቸው ታሳቢ ያደረገ ሆኗል።
ቢሮው በአስተዳደሩ ትኩረት የተሰጠውን የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ የተጀመሩ የተለያዩ ስራዎችን በተለይም ከኢንዱስትሪዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠርና ተመራቂዎች ተደራጅተው ወደ ሰራ እንዲሰማሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመስራት ላይ ይገኛል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 26/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር ወረዳ 2 ዋናው እና ወረዳ 4 አንድ ማዕከል ስር የሚገኙና በቢሮው ኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ድጋፎች የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞችን ወደ ሞዴል ኢንተርፕራይዝነት ለማሳደግ የሚያስችል የተደረገ የመስክ ምልከታና ልየታ በምስል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 26/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የማሰልጠን ስነ-ዘዴ/ Training Methodology/ ላይ ስልጠና ላልወሰዱ ከሁለቱ የመንግስት እና ከግል ኮሌጆች በተለያዩ ሙያዎች ለሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ለተከታታይ 8 ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀመረ፤
በስልጠናውን መጀመር በንግግር የከፈቱት የቢሮው ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን ውጤታማ ሊያደርግ የሚችል የስልጠና አሰጣጥ ሥርዓትን በመተግበር ሙያው የሚጠይቀውን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት በበቂ ሁኔታ ለሰልጣኞች በማስረጽ በክህሎት የዳበሩና ስኬታማ የሆኑ ሰልጣኞችን ለስራ ገበያው ለማቅረብ የሚችሉ በአስተዳደራችን የሚገኙ ብቁ አሰልጣኞችን ማፍራት የቢሮው፤ የኤጀንሲው ብሎም የዳይሬክቶሬቱ ቁልፍ ተግባር መሆኑን በመግለፅ ሰልጣኞች በስልጠናው በሚቆዩባቸው ቀናት የሚጠበቅባቸውን የተግባር ስራዎች በማሟላት በስልጠናው ማጠናቀቂያ የሚኖረውን ምዘና ብቁ ለመሆን በንቃት ተሳታፊ እንዲሆኑ አሳስበዋል፤
የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ በበኩላቸው አሰልጣኞች በሙያቸው የሚጠበቅባቸውን የእውቀት፣ የክህሎትና የሙያ ስነምግባር በመላበስና በሙያቸው ብቃታቸውን ከማረጋገጥ ባሻገር፣ የማሰልጠን ስነ ዘዴ ስልጠና/Training Methodology/ በመሰልጠን አሰልጣኞች ሊኖራቸው የሚገባውን የሙያ ብቃት ማዕቀፍ/ Training Qualification Frame Work/ ስታንዳርድ ማሟላት እንዳለባቸው የዘርፉ ስትራቴጂ ማስቀመጡን አውስተው፤ የዘርፉ ስልጠና አሰጣጥ ስርአትም ውጤትን መሰረት ያደረገ/Out Come Based Training / መሆኑ፤ ይህንንም የሚያስተገብሩት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና ጥራት ያለው ስልጠና በመስጠት ብቁ የሆነ የሰው ሀይል የማፍራት ተልዕኮን በመወጣት እረገድ ምንግዜም የማይተካ ሚና ያላቸው አሰልጣኝ መምህራን መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 25/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ ለሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ክፍሎችና ስራ ሂደቶች የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወር የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር ማካሄድ ጀመረ::
በኮሌጁ ዲን በሚመራው በዚህ የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር በድጋፍና ክትትል ቡድኑ በተዘጋጀው ቼክሊስት መሰረት ትምህርትና ስልጠና ክፍሎች፣ ዋና ስራ ሂደቶችና የስራ ክፍሎች በግማሽ አመቱ በእቅድ አፈፃፀም፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በስልጠና ጥራት፣ በመረጃ አደረጃጀት፣ በሀብት ማፍራትና ግብዓት አጠቃቀም ላይ ባተኮሩ ነጥቦች መነሻነት ሂደቶችና ክፍሎች ያሉበትን ቁመና የሚገመግም የድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብር መሆኑም ተገልጿል::
የዚህ ድጋፍና ክትትል ዋና አላማ በተቋሙ የሚገኙ ስራ ሂደቶችና ክፍሎች ከተሰጣቸው ተልዕኮ አንፃርና ካስቀመጡት ግብ አኳያ ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ክትትል ለማድረግና በአፈፃፀም ክፍተት የሚታይባቸውን ተግባራቶች ተለይተው ክፍተቶች እንዲሞሉ ድጋፍ የማድረግ ሲሆን በተጨማሪም የተሻለ አፈፃፀም ለታየባቸው ስራ ሂደቶችና ክፍሎች እውቅና በመስጠት ለሌሎች ሞዴል እንዲሆኑ ማስቻል እንደሆነው ተገልፇል::
በድጋፍና ክትትል መርሃ-ግብሩ እስካሁን የአውቶሞቲቭ፣ የማኑፋክቸሪንግ፣ የአይ.ሲ.ቲ፣ የውድ ዎርክ እና የኮስትራክሽ ትምህርትና ስልጠና ክፍሎችን ማካሄድ የተቻለ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም በተቀመጠው መርሃ-ግብር መሰረት የድጋፍና ክትትሉ የሚቀጥል መሆኑም ታውቋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የካቲት 25/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
