ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 319
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+127 أيام
+14830 أيام
أرشيف المشاركات
አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል!!! በድሬዳዋ አስተዳደር 130ኛው የአድዋ ድል በዓል ከአኩሪ ታሪክ፤ ወደ ብሩህ አድማስ ! በሚል መሪ ቃል በለገሀር አደባባይ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች በድምቀት ተከበረ። በ
+6
አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል!!! በድሬዳዋ አስተዳደር 130ኛው የአድዋ ድል በዓል ከአኩሪ ታሪክ፤ ወደ ብሩህ አድማስ ! በሚል መሪ ቃል በለገሀር አደባባይ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች በድምቀት ተከበረ። በበዓሉ አከባበር መርሀ ግብር የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የካቢኔ አባላትና በአስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ የፀጥታ አመራርና አባላት፣  ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የድሬዳዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። ©️ DGC

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በአጫጭር ስልጠና ማዕቀፍ የአምራች ኢንዱስትሪውን ፍላጎት መለየት የሚያስችል የውይይት መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ:: ከተማችን ድሬደዋ የኢንዱስትሪ ማዕከል ከመሆኗ ጋር ተያይዞ አምራች ኢንዱስትሪው የሚጠይቀውን ብቁና የሰለጠን የሰው ሀይል በአጫጭር ስልጠና ማዕቀፍ አሰልጥኖ ለማቅረብ ታሳቢ ያደረግ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናትና የምክክር መድረክ ከኮልጁ የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪንግ ቦርድ አካላት ጋር ማካሄድ ተችሏል:: የምክክር መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸው "ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ወጣቶች ከረጅም ጊዜ ስልጠና ይልቅ ወቅቱ ሚጠይቀውን የአጫጭር ሙያ ስልጠናዎች ላይ ትኩረት በማድረጋቸው አምራች ኢንዱስትሪው በሚፈልገው ልክ የበቃ የሰው ሀይል የማቅረብ ውስነት እንዲስተዋል እድርጎታል ያሉ ሲሆን ይህን ክፍተት በዘላቂነት ለመቅረፍ የአምራች ኢንዱስትሪውን የሙያ ፍላጎት መሰረት ያደረገ የአጫጭር ስልጠና ፕሮግራም መቅረፅ አስፈላጊ በመሆኑ ከኢንዱስትሪ አድቫይዘሪግ ቦርድ አባላት ጋር ለመወያየት ይህ መድረክ መዘጋጀቱንም ገልፀዋል:: በEASE ፕሮጀክት ትኩረት ተደርጎባቸው ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል ለኢንዱስትሪው ግብዓት የሚሆኑ ብቁ ባለሙያዎችን የማፍራቱን ሂደት መደገፍ አንደኛው መሆኑን ያስታወሱት የፕሮጀክቱ ኮርዲኔተር ኢ/ር ፋሲል ማዘንጊያ ሲሆኑ የፕሮጀክቱ ባለሙያዎች ከትምህርትና ስልጠና ዘርፉ ጋር በመቀናጀት በሚያዘጋጁት የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት ያደርገ የአጫጭር ስልጠና ፕሮግራም ላይ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም ገልፀዋል:: የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት አስፈላጊነት ዝርዝር ዓላማ እንዲሁም የአጫጭር ስልጠና ሞጁሉን በማዘጋጀት ሂደት ውስጥ የሚያካተቱ ዝርዝር ተግባራትን በተመለከተ በኮሌጁ ም/ል ዲን እና የትምህርትና ስልጠው ዋና ሀላፊ በሆኑት አቶ ኤሊያስ አህመድ አማካኝነት ለባለ ድርሻ አካላት ግንዛቤ መስጠትም ተችሏል:: በመድረኩ በነበረው ውይይት ኢንዱስትሪውን ወክለው የተገኙ ተስታፊዎች አምራች ኢንዱስትሪዎች ከበቃ የሰው ሀይል አኳያ ያላቸው ፍላጎት ለጥናት ቡድኑ በዝርዝር አቅርበው ሰፊ ውይይት የተካሄደት ሲሆን ለፍላጎት ዳሰሳ ጥናቱ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችም የተገኙበት መድረክ ነበር:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የካቲት 21/6/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች ጋር በመተባበር የኩባንያ ውስጥ ስልጠና ለማጠናከር የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡ ይህም ስልጠና በ2018 ዓ.ም የኩባንያ ውስጥ ስልጠና ለመስጠት በአስተዳደሩ ከሚገኙ ለትብብር ስልጠና መስጫነት ከተመረጡ ኩባንያዎች በ4 የሙያ ዘርፎች ማለትም  በማኑፋክቸሪንግ፣ ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ፣ በሆቴልና ቱሪዝም እንዲሁም በአውቶሞቲቭ ሙያዎች  ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች  በተውጣጡ አሰልጣኞች የኩባንያዎቹን ሰራተኞች ያለባቸውን የክህሎት ክፍተት በመለየት ስልጠና ለመስጠት ያስችል ዘንድ ከ4ቱ ዘርፎች ለተውጣጡ አሰልጣኝ  መምህራንና ስልጠና አስተባባሪዎች የአሰልጣኞች ስልጠናው መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡ የስልጠናው ዋና አላማ የኩባንያ ሰራተኞችን በማብቃት፤ የቴክኖሎጂ ክፈተቶችን በመሙላት ምርትና ምረታማነትን ማሳደግ ሲሆን በተጨማሪም የአሰልጣኝ መምህራንን አቅም በማሳደግ  በትብብር ስልጠና ሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጥራት ችግሮችን ከወዲሁ ለመፍታት ማስቻል ነው ሲሉ የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ምንልክአለው ወርቅነህ ገልጸዋል ፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 21/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+8

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ዋና ስራ ሂደት በተቋሙ ከሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ:: በትምህርትና ስልጠና አካዳሚክ ካላንደሩ መሰረት
+4
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ዋና ስራ ሂደት በተቋሙ ከሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ:: በትምህርትና ስልጠና አካዳሚክ ካላንደሩ መሰረት የስልጠና ዘመኑ የአንደኛ ተርም መጠናቀቁን ተከትሎ በተርሙ የተከናወኑ የትግበራ አፈፃፀም እና የሁለተኛ ተርም ማስጀመሪያ የውይይት መድረክ ተካሂዷል:: የውይይት መድረኩ የመሩት የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ም/ዲን አቶ ኤሊያስ አህመድ በንግግራቸው እንደግለፁት በአካዳሚክ ካላንደሩ መሰረት የትምህርትና ስልጠናው የመጀመሪያ ተርም ተጠናቆ ሁለተኛውን ተርም ምንጀምርበት ወቅት ላይ እንደመሆናችን የነበሩ ክፍተቶችን በሚገባ ለይቶ መፍትሄ ለማበጀትና በሁለተኛው ተርም ላይ ማስተካከያ ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑንም ገልፀዋል:: በመድረኩ ተሳታፊ ከነበሩት አሰልጣኝ መምህራንም የመጀመርያውን ተርም የትምህርትና ስልጠና ሂደቱን አስመልክቶ የተስተዋሉ ጠንካራ ጎኖችና ያጋጠሙ ትግዳሮቶችን በዝርዝር ያስቀመጡ ሲሆን አያይዘውም የመፍትሄ ሀሳብ ይሆናሉ ያሏቸውንም በመድረኩ አቅርበዋል:: በመጨረሻም ከመድረኩ በተገኙ ግብዓቶችና አጠቃላይ በተነሱ ሀሳቦች ላይ በመወያየት ሰፊ ማብራርያና ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን በተጨማሪም በቀጣይ በተቋምና አገር አቀፍ ምዘና ሰልጣኝ ተማሪዎችን ማብቃት፣ፕሮጀክት መሰረት ያደረገ ስልጠና፣የትብብር ስልጠና፣ የዲጂታል ስልጠና አገልግሎት እና አሰልጣኝ መ/ራንን በረጅም ጊዜ የማሰልጠን ስነዘዴ ማብቃት ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የጋራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የካቲት 19/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የካይዘን ፍልስፍና ስራ ቦታን ምቹ ከማድረግ ባሻገር ምርትና ምርታማነትን በማሻሻሉ ረገድ ፋይዳው የላቀ በመሆኑ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ። የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ የካይዘን ማሻሻያ ትግበራ ንቅናቄ ማስጀመሪያ የሆነ የግንዛቤ መስጫ መድረክ ለኮሌጁ አጠቃላይ ሰራተኞች አካሄደ:: የካይዘን ፅንሰ-ሀሳብን ተረድቶ በትኩረት መተግበር ከተቻለ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን መፍቻ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን የገለፁት የኮሌጁ ም/ል ዲን እና የቴ/ሽ/ኢ/ኤ/አ ዋና ስራ ሂደት ሀላፊ የሆኑት አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ የካይዘን ትግበራ ምቹና ፅዱ የሥራ አካባቢን ከመፍጠር ባሻገር የሀብት ብክነትን ከማስወገዱም በተጨማሪ አሰራርን በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል:: ም/ል ዲኑ አክለውም በቀጣይ ቀናት በተቋሙ በሚተገበረው የካይዘን ማሻሻያ ትግበራ ወቅት ከትግበራው የሚጠበቀውን ውጤት ለማግኘት ሁሉም የኮሌጁ አመራርና ሰራተኞች ተገቢውን ትኩረትና ተሳትፎ ማድረግ ያስፈልጋልም ብለዋል:: በመድረኩ የካይዘን ትግበራ ማሻሻያ ንቅናቄውን አስመልክቶ ለኮሌጁ ሰራተኞች የተዘጋጀውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከአስተዳደሩ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመት ቢሮ በመጡ ባለሙያ አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን በዚህም በተቋም ደረጃ የካይዘን ትግበራ የሚፈጥራቸው ለውጦችና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን የዳሰሰ የግንዛቤ ስልጠና መስጠት ተችሏል:: በተጨማሪም በኮሌጁ በቀጣይ ቀናት የሚተገበረውን የካይዘን ማሻሻያ ትግበራ መነሻነት የተዘጋጀውን የካይዘን ማስተግበሪያ እና የአፈፃፀም መከታተያ መመሪያ ሠነድ በኮሌጁ የካይዘን ልማት ቡድን መሪ በሆኑት አሰልጣኝ መ/ር አቤል ዘገየ አማካኝነት ለሰራተኛው የቀረበ ሲሆን በዚህም የትግበራውን አካሄድ እና የትግበራ ሂደቱ የሚያካትታቸውን ዝርዝር ጉዳዮች አስመልክቶ በሰፊው ገለፃ ማድረግም ተችሏል:: "ዛሬን እናሻሽል፣ ብክነትን እናስወግድ ፣ ቅልጥፍናን እንጨምር፣ ነገን እንገንባ!" የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የካቲት 19/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በISO-17024 አተገባበር ላይ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ። ‎ ‎ስልጠናው ዓለም አቀፍ ስታንዳርድ የጠበቀ የሰነድ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችል ሲሆን  ለተቋሙ አመራሮች እና ባለሙያዎች እየተሰጠ እንደሚገኝም ተመላክቷል። ‎ በስልጠናው ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በቢሮው የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ አሚን አብዱላሂ ባደረጉት ንግግር ማዕከሉ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በገባው ውል መሠረት ISO-17024 ለመተግበርና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሰነድ በመዘጋጀት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን ያለመ ነው ብለዋል። ‎ ‎ISO-17024 የተቋማትን አገልግሎት ደረጃ በማሻሻል የሰው ኃይልን በማደራጀት እና የመረጃ ጥራትን በማጎልበት የተገልጋይ እርካታን ለመጨመር አጋዥ የሆነ ዓለም አቀፍ ስታንዳርድ ስለመሆኑም አቶ አሚን አብዱላሂ ተናግረዋል። ‎ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 18/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

በኮሌጁ የሚሰጡ ትምህርትና ስልጠናዎች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ አሰልጣኝ መምህራኖች ያላቸውን እምቅ አቅም አውጥተው ሊጠቀሙ ይገባል ተባለ፡፡ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስልጠና ጥራትን ለማጠበቅ ያለመ ውይይት ከኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን ጋር በዛሬው እለት አከናወነ፡፡ ኮሌጁ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ላይ የልህቀት ማእከል እንደመሆኑ መጠን በኮሌጁ የሚሰጡ የተለያዩ ስልጠናዎች ጥራታቸውን የጠበቁና ዘመኑን የዋጁ እንዲሆኑ ይገባል ያሉት በውይይቱ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ ዲኑ አክለውም ኮሌጁ በመደበኛነት ከሚሰጣቸው ስልጠናዎች በዘለለ በየጊዜው በአሰልጣኝ መምህራኖች የሚሰሩ ቴክኖሎጂዎች የአካባቢውን ማህበረሰብ እነዲሁም ኢንዱስትሪዎች ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች የሚፈልቁበት ተቋም እንዲሆን ሁሉም ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ አቶ ሰለሃዲን አያይዘውም በኮሌጁ የሚሰጡ ስልጠናዎች ተግባር ተኮር እንደመሆናቸው የግብአት አቅርቦቱ ወጥነት እንዲኖረው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በሙሉ በየትምህርት ክፍል ውስጥ የሚገኙ አሰልጣኝ መምህራኖች በሙሉ የተሳተፉበት እንዲሆን ለቀጣይ አመት ከወዲሁ ዝግጅት እንዲደረግ ያሳሰቡ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ በ5 የተለያዩ ዘርፎች ላይ የኢንተርፕራይዝ ፍቃድ ከአስተዳደሩ እንደማግኘቱ መጠን አሰልጣኝ መምህራኖች ያላቸውን ልምድ፣እውቀት እንዲሁም ክህሎት ወደ ገቢ ማስገኛነት ሊለውጡት ይገባል ብለዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ሂደትን በማሻሻል የስልጠና ጥራትን ማረጋገጥ እንዴት እንደሚቻል በጥናት የተደገፈ ሰነድ በዶ/ር ሲሳይ አበራ የቀረበ ሲሆን በኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራኖች ጋርም ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በአሰልጣኝ መምህራኖች የተነሱትን ጥያቄዎች የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ እንዲሁም የኮሌጁ ም/ዲን አቶ ቢቂላ ተሰማ በኩል ምልሽ ተሰጥቷል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን የካቲት 18/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በአስተዳደሩ የሚገኙ የግል እና የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ላይ ለሚሰለጥኑ ሰልጣኝ ተማሪዎች በትምህርትና ስልጠና ተቋማት ኤች አይ ቪ ኤድስን መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ። መድረኩ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣት በአንድ ቦታ የሚገናኙበት እንደመሆኑ መጠን ለኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭነቱን ለመቆጣጠር ቢሮዉ ከሚያዘጋጃቸው ተከታታይነት ያላቸው ስልጠናዎች አካል መሆኑ ታውቋል፡፡ ቢሮው ሰልጣኝ ተማሪ ዜጋውን ጤንነቱና ደህንነቱ የተጠበቀና የተረጋገጠ የነገይቱን ኢትዮጵያ ተረካቢ ባለሙያ አድርጎ ለማፍራት የሚያስችል ግንዛቤ እንዲፈጠር ማድረግ ችሏል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 17/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በአስተደዳደሩ የሚገኙ የግል እና የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ላይ ለሚሰለጥኑ ሰልጣኝ ተማሪዎች በትምህርትና ስልጠና ተቋማት ኤች አይ ቪ ኤድስን መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ። መድረኩ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣት በአንድ ቦታ የሚገናኙበት እንደመሆኑ መጠን ለኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭነቱን ለመቆጣጠር ቢሮዉ ከሚያዘጋጃቸው ተከታታይነት ያላቸው ስልጠናዎች አካል መሆኑ ታውቋል፡፡ ቢሮው ሰልጣኝ ተማሪ ዜጋውን ጤንነቱና ደህንነቱ የተጠበቀና የተረጋገጠ የነገይቱን ኢትዮጵያ ተረካቢ ባለሙያ አድርጎ ለማፍራት የሚያስችል ግንዛቤ እንዲፈጠር ማድረግ ችሏል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 17/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+7

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ወደ ሪፎርም የሚገቡ ተቋማት ለይቶ ወደ ስራ እንዲገቡ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠ
የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ወደ ሪፎርም የሚገቡ ተቋማት ለይቶ ወደ ስራ እንዲገቡ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የመንግስት አገልግሎት ዘርፉን የማሻሻል/ሪፎርም/ የማድረግ  ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ይገኛል፤ በድሬዳዋ አስተዳደርም በተተገበሩት የሪፎርም ስራዎች አበረታች ውጤት እንደተመዘገበና ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠልም  ወደ ሪፎርም ከገቡ ተቋማት መካከል የሥራና ክህሎት ቢሮ አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም የሥራና ክህሎት ሚንስቴር ዕቅድን መነሻ በማድረግ የቢሮው ዕቅድ መዘጋጀቱንና ሪፎርም አስተግባሪ ኮሚቴዎችንም ከቢሮው እስከ ወረዳ አንድ ማዕከላት ድረስ እንዲሁም በፖሊቴክኒክ ኮሌጆች በማዋቀር በቢሮው ማኔጅመንት እንዲጸድቅ ማድረግ ተችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች እየተዘጋጁ መሆኑንና ለአጠቃላይ ሰራተኛው በቀጣይ መድረክ ተዘጋጅቶ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እንደሚሰራ የቢሮው ም/ኃላፊና የቴክክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናግረዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 17/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር ወረዳ 2 ቅርንጫፍ 2 አንድ ማዕከል ስር የሚገኙና በቢሮው ኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ድጋፎች የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞችን ወደ ሞዴል ኢንተርፕራይዝነት ለማሳደ
+7
በድሬዳዋ አስተዳደር ወረዳ 2 ቅርንጫፍ 2 አንድ ማዕከል ስር የሚገኙና በቢሮው ኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ድጋፎች የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞችን ወደ ሞዴል ኢንተርፕራይዝነት ለማሳደግ የሚያስችል የተደረገ የመስክ ምልከታና ልየታ በምስል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 11/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በአስተዳደሩ ወረዳ 7 አንድ ማዕከል ስር የሚገኙና በቢሮው ኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ድጋፎች የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞችን ወደ ሞዴል ኢንተርፕራይዝነት ለማሳደግ የሚያስችል የመስክ
+9
በአስተዳደሩ ወረዳ 7 አንድ ማዕከል ስር የሚገኙና በቢሮው ኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ድጋፎች የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞችን ወደ ሞዴል ኢንተርፕራይዝነት ለማሳደግ የሚያስችል የመስክ ምልከታና ልየታ ተደረገ። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት የካቲት 11/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ