Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 318
المشتركون
+324 ساعات
+207 أيام
+15030 أيام
أرشيف المشاركات
የክህሎት ዘርፉ አምባሳደሮቻችን!
በቻይና ሻንጋይ በተካሄደው 48ኛው የዓለም ክህሎት ውድድር፣ ኢትዮጵያ በ9 የሙያ ዘርፎች በ9 ወጣት ባለሙያዎች ተወክላ ተሳትፋለች። ይህ ተሳትፎ የኢትዮጵያ ወጣቶች በሙያ፣ በፈጠራ እና በዲጂታል ክህሎት በዓለም አቀፍ ደረጃ መወዳደር የሚችሉበትን አቅም ያሳያል።
በDigital Interactive Media Design የሙያ ዘርፍ ኢትዮጵያን ወክሎ የተወዳደረው ወጣት ሮቤል ለገሰ የBest of Nation እውቅና በማግኘቱ ታላቅ ኩራት ነው። ስኬቱ የአንድ ተወዳዳሪ ውጤት ብቻ ሳይሆን፣ የወጣት ባለሙያዎቻችን ችሎታ፣ ጥረት እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት መገለጫ ነው።
የዓለም ክህሎት ውድድር ለሽልማት እና ለአሸናፊነት ብቻ የሚደረግ ውድድር አይደለም። የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናችንን ከዓለም አቀፍ መስፈርቶች ጋር ለማጣጣም፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂና የምዘና ሥርዓቶችን ለመቅሰም፣ እንዲሁም ሥልጠናን ከኢንዱስትሪና ከሥራ ገበያ ፍላጎት ጋር ለማስተሳሰር የማይተካ ሚና ነው።
በሁሉም ዘርፎች ሀገራችንን ወክላችሁ የተሳተፋችሁ በሙሉ የክህሎት ዘርፉ አምባሳደሮች ናችሁ። ኢትዮጵያን በክብር ወክላችኋል፤ ለወጣቶችም በትጋት፣ በዲሲፕሊን እና በክህሎት ወደ ዓለም አቀፍ ስኬት መድረስ እንደሚቻል አሳይታችኋል።
ለቴክኒካል ኤክስፐርቶች፣ አስተባባሪዎች እና ለዚህ ውድድር ለደከሙ ሁሉ ምስጋናዬ የላቀ ነው።
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
#የምን ባለሙያ መሆን ይፈልጋሉ? 🔹
የቴክኖሎጂ 🖥፣ የውበት 💄፣ የአውቶሞቲቭ 🚗፣ የፈርኒቸር 🪑፣ የሆቴልና ቱሪዝም 🏨፣ የኮንስትራክሽን 🏗፣ የፋሽን ዲዛይን 👗 ወይስ ሌላ? 🔧
ፍላጎትዎን እውን ያደርጉ ዘንድ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክንክ ኮሌጅ ሙሉ ዝግጅታቸውን አጠናቀው እርስዎን ለመቀበል በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ✅
ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፍላጎትዎ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን ምርጫዎ ያድርጉ
ለኮሌጁ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
College website፡ https://ddptc.edu.et/
College telegram: https://t.me/diredawapolytechniccollege
ባሉበት ቦታ ሆነው ለመመዝገብ www.ddptcregistration.edu.et
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
የአካባቢው ወጣቶች ክህሎት ያላቸውና አመለካከታቸው የተለወጠ ሆነው ከራሳቸው አልፎ ሃገራቸውን እንዲለውጡ ኮሌጁ ተግቶ እንደሚሰራ ገለጸ፡፡
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በክረምቱ መርሃ ግብር አንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ በሚል ርእስ ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች በድምቀት በዛሬው እለት አስመረቀ፡፡
ኮሌጁ በክረምቱ መርሃ ግብር አንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ በሚል ርእስ የአካባቢውን ወጣቶች ገበያተኮር በሆነ የአጫጭር ኮርስ ስልጠና የወሰዱ 194 ወንድ 182 ሴት በአጠቃላይ 376 ሰልጣኞችን ያስመረቀ ሲሆን በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት በድሬዳዋ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የአሰልጣኝ ልማት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታሪኩ ለገሰ እንዳሉት የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከራሳቸው አልፎ ሃገራቸውን ለመለወጥ የሚተጉ ወጣቶች ክህሎትና እውቀት የሚያገኙበት ኮሌጅ ነው በዚህ ኮሌጅ ደግሞ በአጫጭር ስልጠና ብቻ ሳይሆን በመደበኛው ስልጠና በመውሰድ የኢኮኖሚው ተጠቃሚ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በምርቃቱ መርሃ ግብር ላይ የእንኳን ደስ አላችሁ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ም/ዲን የሆኑት አቶ ቢቂላ ታደሰ እንዳሉት የክረምት ጊዜያችሁን በኮሌጃችን እውቀትና ክህሎት ለመቅሰም መርጣችሁን ስልመጣችሁና ስልጠናችሁንም በስኬት ስላጠናቀቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉ ሲሆን የአካባቢውን ወጣቶች ክህሎት ያላቸውና አመለካከታቸው የተለወጠ ሆነው ከራሳቸው አልፎ ሃገራቸውን እንዲለውጡ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተግቶ ይሰራል ብለዋል፡፡አያይዘውም በክረምቱ ከተሰጡ ሰልጠናዎች በተጨማሪ በ13 ዲፓርትመንቶች ስልጠናዎች እየሰጠን እንገኛለን ኮሌጁን ተቀላቅላችሁ እውቀትና ክህሎታችሁን አዳብሩ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በዘንድሮ የክረምት ስልጠና በኮሌጁ በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ፣በአውቶ ሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ፣በኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ፣በውድዎርክ ቴክኖሎጂ እና በሌዘርና ፋሽን ዲዛይን እንዲሁም በሆቴል ቱሪዝምና ICT እና በኢፖክሲ ስልጠና ዘርፎች 376 ሰልጣኞች ስልጠናቸውን አጠናቀዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
መስከረም 16/2019 ዓ.ም ድሬዳዋ ለኮሌጁ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
College website፡ https://ddptc.edu.et/
College telegram: https://t.me/diredawapolytechniccollege
You tube: Dire Dawa Polytechnic College(DDPTC)
Facebook: https://web.facebook.com/Dire Dawa Polytechnic College Regional Flagship TVET Institute
TikTok: tiktok.com/@diredawapolytechnicollege ባሉበት ቦታ ሆነው ለመመዝገብ www.ddptcregistration.edu.et
የ“መስመር” የብድር አገልግሎት ለሴቶችና ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች የፋይናንስ ተደራሽነትን እያሰፋ ነው
የ“መስመር” የብድር አገልግሎት በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ በተለይም በሴቶችና በወጣት ሥራ ፈጣሪዎች የሚመሩ ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅማቸውን እንዲያጠናክሩና ሥራቸውን እንዲያስፋፉ የሚያግዝ የብድር አገልግሎት ነው።
አገልግሎቱ በአቢሲኒያ፣ በአዋሽ፣ በዳሽንና በህብረት ባንኮች በኩል የሚሰጥ ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች በመጠነኛ የዋስትና መስፈርትና በአነስተኛ የወለድ መጠን የብድር አገልግሎቱን እንዲያገኙ ያስችላል። በተጨማሪም የሸሪዓ መርህን የተከተለ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት አማራጭ ተካቷል።
በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በተገኙበት፣ በብድር አሰጣጥ፣ በአጠቃቀምና በአመላለስ ሂደት ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱም የ“መስመር” የብድር አገልግሎት አስተባባሪዎች፣ የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች እና የአጋር ባንኮች ተወካዮች ተገኝተው፣ የብድር አገልግሎቱ ተደራሽነት፣ የአሰጣጥ ሂደት፣ የብድር አመላለስ እና ተጠቃሚዎች በብድሩ በተገቢው መንገድ ተጠቅመው የንግድ ሥራቸውን እንዲያሳድጉ ስለሚያስፈልጉ ጉዳዮች በጋራ ተወያይተዋል።
የ“መስመር” የብድር አገልግሎት የሥራ ፈጠራን፣ የሴቶችንና የወጣቶችን የኢኮኖሚ ተሳትፎ በማጠናከር የኢንተርፕራይዞችን የእድገት አቅም ለማሳደግ የሚያግዝ የፋይናንስ ድጋፍ ማዕቀፍ ነው።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብግንኙነት ድሬዳዋ | መስከረም 15/2019 ዓ.ም
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
#ለዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ!!
በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የድሬደዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሳተላይት ካምፓስ በ2019 የትምህርት ዘመን በሚከተሉት ሙያዎች በመጀመርያ ዲግሪ በምሽት (NIGHT) ወይም በቅዳሜ እና እሁድ (weekend) መርሃግብር፤ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከ 14/1/2019 እስከ 25/1/2019 በድሬደዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤት በመገኘት እንድታመለክቱ እያስተወቅን የመግብያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን በውስጥ ማስታወቅያ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+5
ዘመናዊና ለአሰራር ምቹ የሆነ ተቋም ለመገንባት ሁሉም የኮሌጁ አካላት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ተባለ፡፡
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በኮሌጁ ውስጥ ለሚገኙ የአስተዳዳር ሰራተኞች በስራ ስነ ምግባ ላይ ያተኮረ ስልጠና በዛሬው እለት ተሰጠ፡፡
ተቋሙ የትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ እንደመሆኑ መጠን ሁሉም የኮሌጁ ሰራተኛ ከማኔጅምንተ አካላቱ ጋር በቅርበት ሊሰሩ ይገባል ያሉት በስልጠናው ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉትና ለተጠየቁ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ አያይዘውም ዜጎች እንዲሁም ሃገራችን ከኛ የሚጠብቁትን ውጤት ለማምጣት በትጋት ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የአስተዳደር ሰራተኛው በተቋሙ የአሰራር ለውጥ ላይ ትልቁን ድርሻ እንደሚወስድ ይታወቃል ስለዚህ ለዚህ ለውጥ ደግሞ ዝግጁ እንዲሆን የማብቃቱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በዛሬው እለት የተሰጠው ስልጠና በስራ ስነ ምግባር ላይ የኮሌጁ ሰራተኞች ግንዛቤ ለማጎልበትና ብልሹ አሰራርን እንዲቀንስና ለዜጎች ምቹ የሆነ ተቋም ለመገንባት ያለመ ነው፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
መስከረም 15/2019 ዓ.ም ድሬዳዋ
ሕገወጥ የሥራ ስምሪት አሠራሮችን በመቆጣጠር የሠራተኞችን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ትኩረት ተሰጥቷል
በድሬዳዋ አስተዳደር ያለ ሕጋዊ ፈቃድ በግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ኤጀንሲዎችን ለመቆጣጠርና ወደ ሕጋዊ አሠራር እንዲገቡ ለማድረግ ከፀጥታ አካላት ጋር በተቀናጀ መልኩ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለጸ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ እንዳስታወቀው፣ ያለ ሕጋዊ ፈቃድ ቢሮ ከፍተው የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ አገልግሎት የሚሰጡ ሕገወጥ ኤጀንሲዎች በአስተዳደሩ እየበረከቱ መምጣታቸው በአሠሪና በሠራተኛ መካከል ተገቢ ያልሆኑ አሠራሮችን ከማስፋፋት ባለፈ በዜጎች መብት፣ ደህንነትና ጥቅም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችል ሁኔታ ፈጥሯል።
በመሆኑም ቢሮው የሕገወጥ ኤጀንሲዎችን እንቅስቃሴ በመከታተል፣ በመቆጣጠርና አስፈላጊውን የሕግ ማስፈጸሚያ ርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል። ያለ ፈቃድ ቢሮ ከፍተው የሚሠሩ ኤጀንሲዎችም ሕጋዊ መስፈርቶችን አሟልተው ወደ ሕጋዊ አሠራር እንዲገቡ እድል ከመስጠት ባለፈ፣ ያለ ፈቃድ የሚቀጥሉ አካላት ቢሮዎቻቸው እንዲታሸጉ የማድረግ እርምጃም እየተወሰደ ነው።
ሕጋዊ አሠራርን ማጠናከር የቁጥጥሩ መሠረት ቢሮው እንደገለጸው፣ እርምጃው በድንገት የተጀመረ ሳይሆን ከሕጋዊ ማዕቀፍና ቀደም ሲል ከተካሄዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ጋር የተያያዘ ነው።
መንግሥት በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች አገልግሎት የሚሰጡበትን ሥርዓት ለመደንገግ መመሪያ ቁጥር 45/2013 አውጥቶ በሥራ ላይ እንዲውል አድርጓል።
የመመሪያውን ተግባራዊነት ለማጠናከርም የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ በኩል ለኤጀንሲዎችና ለተዛማጅ አካላት በተለያዩ መድረኮች የግንዛቤ ማስጨበጫና የሕግ ትውውቅ ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።
የሠራተኞች መብትና ደህንነት በቁጥጥሩ ማዕከል
በቀጣይም ቢሮው በአስተዳደሩ የሚንቀሳቀሱ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሚሰጡትን የሥራ ስምሪት አገልግሎት በተገቢው ደረጃ በመከታተል፣ በመቆጣጠርና በመደገፍ የሥራ ገበያው በሕጋዊ፣ ፍትሐዊና ኃላፊነት ባለው አሠራር እንዲመራ ትኩረት ይሰጣል።
በተለይም በኤጀንሲዎቹ በኩል በሥራ የሚሰማሩ ዜጎች መብት፣ ደህንነትና ጥቅም የሚጠበቅበትን ሁኔታ መፍጠር፣ በአሠሪና በሠራተኛ መካከል ፍትሐዊ የሥራ ግንኙነት ማስፈን እና የኢንዱስትሪ ሠላምን ማጠናከር የቀጣይ ሥራው ዋና ትኩረቶች መሆናቸው ተጠቁሟል።
የቢሮው አቋም እንደሚያመለክተው፣ ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው የሥራ ስምሪት አገልግሎት መስጠት የሥራ ዕድል ማመቻቸት ሳይሆን የዜጎችን መብትና የሥራ ገበያውን ደህንነት ሊያውክ የሚችል ሕገወጥ አሠራር ነው።
በመሆኑም ሕጋዊ መስፈርቱን የሚያሟሉ ኤጀንሲዎችን በመደገፍ፣ ሕጉን የሚጥሱትን ደግሞ በሕግ አግባብ በመቆጣጠር የተሻለ የሥራ ስምሪት ሥርዓት ለመገንባት ቢሮው እንደሚሠራ ገልጿል።
በዚህ ሂደትም ከፀጥታ አካላት፣ ከአሠሪዎች፣ ከሠራተኞችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረገው ትብብር እንደሚጠናከር ተገልጿል።
ዓላማውም ሕገወጥ የሥራ ስምሪትን መቆጣጠር ብቻ ሳይሆን፣ የሥራ ገበያውን ታማኝ፣ ግልጽ፣ ፍትሐዊና የዜጎችን መብት የሚያስጠብቅ ሥርዓት ማድረግ መሆኑ ተጠቁሟል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ – ሕዝብ ግንኙነት
መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም. | ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
በኮሌጁ የISO 9001:2015 QMS የመጀመርያው ሰርቪላስ ኦዲት (Surveillance Audit) ተካሄደ::
#EIPC መስከረም 12. 2019 ዓ.ም ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በምስራቅ ኢትዮጵያ የመጀመርያው የመንግስት ተቋም በመሆን የISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት መሆኑን ተከትሎ በየአመቱ በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ኮሌጁ ያለበትን ደረጃ ለመገምገምና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ በሚደረገው የሰርቪላስ ኦዲት (Surveillance Audit) ከመስከረም 11-12/2019 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ተካሂዶ በስኬት ተጠናቋል::
በሰርቪላስ ኦዲት (Surveillance Audit) ወቅት ኦዲተሮች በኮሌጁ የሚገኙ የስራ ሂደቶችን፣ ስልጠና ክፍሎችን እንዲሁም የማሰልጠኛ ወርክሾፖችን ጨምሮ አጠቃላይ የኮሌጁን ነባራዊ ሁኔታ የገመገሙ ሲሆን በዚህም ኮሌጁ በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የተሰጠውን የISO 9001:2015 QMS ስታንዳርድ ትግበራ በማስቀጠሉ ረገድ ጥሩ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ያለ በመሆኑ የተሰጠው ሰርተፍኬት ቀጣይነት እንዲኖረው ማረጋገጫ ማግኘትም ችሏል::
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr
በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001
በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1
በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/
Repost from E-LMIS - ብቁ
በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ አረቢያ የሥራ ስምምነት ዙሪያ የተሰጠ ማብራሪያ
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ አረቢያ መካከል ስላለው የሥራ ስምምነት እና የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ሂደት ዙሪያ የተለያዩ የተሳሳቱ እና መሠረተ ቢስ መረጃዎች ሲሰራጩ ተመልክቷል።
ዜጎችና እና ባለድርሻ አካላት ትክክለኛ መረጃ እንዲኖራቸው፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ “አንድም ሰው ወደ ሳዑዲ አረቢያ መሄድ አልቻለም”፤ “የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ የተዘጋጀው ለጥቂቶች ብቻ ነው” ፤ “የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (E-LMIS) ተዘግቷል”፤ “ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች በበቂ ሁኔታ መረጃ አልተሰጣቸውም ” ወዘተ የሚሉ ብዥታ ሊፈጥሩ የሚችሉ፣ መሠረተ-ቢስ አሉባልታዎችን ለማጥራት ይሻል።
የኢትዮጵያ የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ሥርዓት የቅጥር ሂደትን ለመቆጣጠር፣ መስፈርቱን የሚያሟሉ ኤጀንሲዎች ሕጋዊ የሥራ ስምሪት እንዲያከናውኑ ለማረጋገጥ እና ለመቆጣጠር ብሎም ሕጋዊ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ክብር ያለው የሥራ ስምሪት ተጠቃሚነትን ለኢትዮጵያውያን ለማረጋገጥ የተመሠረተ ነው። በዚህም ሳዑዲ አረቢያ ለኢትዮጵያውያን የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ዋና መዳረሻ ከሆኑ አገራት አንዷ ስትሆን፣ በኢትዮጵያ ቁጥጥር የሚደረግበት የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ማዕቀፍ ውስጥ ቁልፍ አጋር ሆና ትቀጥላለች። በሳዑዲ አረቢያ የሥራ ስምሪት ውስጥ የሚሠሩትን ጨምሮ በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ምኅዳር ውስጥ ፈቃድ ያላቸው የቅጥር ኤጀንሲዎች የዚህ ሂደት የማይነጠል አካል ሆነው ቀጥለዋል።
ይሁንና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በሥራ ስምሪት ሂደት ውስጥ ያሉ ልዩ ልዩ ተግዳሮቶችንና ክፍተቶችን ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በማጣራት የማስተካከያ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል። ነገር ግን፣ "የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ ተዘግቷል" ፣ "ዜጎች እየተሰማሩ አይደለም" ወዘተ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ሙሉ በሙሉ መሠረት የለሽ መሆናቸውን እያስገነዘብን ይልቁንም ሕጋዊ የሥራ ስምሪት ሂደቱ በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ እየተቀላጠፈ የቀጠለ መሆኑን ልንገልጽ እንወዳለን፡፡
በመሆኑም ዜጎች እነዚህን በመሰሉ ከእውነት የራቁ መረጃዎች እንዳይደናገሩ እያሳሰብን፤ መሠረት የለሽና አሳሳች መረጃዎችን በሚያሰራጩ አካላት ላይ ማጣራት በማድረግ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆናችንን እናስገነዝባለን። ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ጋር በተገናኘ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ይፋዊ ድረ-ገጾች ብቻ እንድትከታተሉም እናሳውቃለን፡፡
Clarifications Regarding the Ethiopia-Saudi Arabia Labor Agreement
The FDRE Ministry of Labor and Skills (MoLS) has noted with concern several unsubstantiated claims circulating about the Ethiopia–Saudi Arabia employment agreement and the overseas employment process. To ensure the public and all stakeholders have accurate information, the Ministry wishes to address the following allegations directly:
“Not one person has gone to Saudi Arabia through the agreement.”
“The system was made exclusively for a few.”
“The Ethiopian Labor Market Information System (E-LMIS) is closed.”
“Overseas Employment Agencies have not been informed.”
Here are the verified facts:
Saudi Arabia is one of Ethiopia’s main countries of destination for overseas employment and remains a key partner in Ethiopia’s regulated overseas employment framework.
Ethiopia’s overseas employment system is designed to regulate recruitment, verify complaint agencies, and facilitate the legal, safe and dignified deployment of Ethiopian workers.
Authorized recruitment agencies continue to be an integral part of this process, including those operating within the Saudi Arabia corridor.
While the Ministry acknowledges that operational challenges, delays, and individual cases require attention,and are being continuously addressed, they should not be misrepresented as evidence that the entire system is closed or that “nobody” has been able to proceed.
Citizens and stakeholders deserve accurate information—not baseless rumours or blanket statements.
The Ministry welcomes constructive feedback and remains committed to open communication. But above all, our priority is to ensure that Ethiopian workers receive clear and reliable information about their opportunities.
