ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

الذهاب إلى القناة على Telegram

# ቁልፍ እሴቶች 1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣ 2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣ 3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣ 4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

تُعد قناة FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት (@fdredefenseforc) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 43 071 مشتركاً، محتلاً المرتبة 6 124 في فئة الأخبار والوسائط والمرتبة 837 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 43 071 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 19 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 726، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -21، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 14.57‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 8.92‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 6 279 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 3 842 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 50.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“# ቁልፍ እሴቶች 1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣ 2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣ 3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣ 4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 20 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الأخبار والوسائط.

43 071
المشتركون
-2124 ساعات
+77 أيام
+72630 أيام
أرشيف المشاركات
በግጭት ወቅት የሚከሰቱ ፆታዊ ጥቃቶችን መከላከል የሚያስችል የፓናል ዉይይት ተካሄደ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል የአለም አቀፍ ሠላም ማሥከበር ኢንስቲትዩትና የፈረንሳይ መንግስት ያዘጋጁት በግጭት ወቅት የሚከሰቱ ፆታዊ ጥቃቶችን መከላከል የሚያስችል የፓናል ዉይይት ተካሂዷል። በማጠቃለያዉ የተገኙት በመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል የሎጀስቲክስ ዝግጅትና ስምሪት ድጋፍ መምሪያ ሀላፊ ብርጋዲየር ጄነራል ጠቅለዉ ክብረት በዚህ ወቅታዊና በግዳጅ ወቅት የሚከሰቱ ፆታዊ ጥቃቶች በማህበረሰቡ የሚያስከትሉትን ስነ-ልቦናዊ ጫና ለመቅረፍ መሰል የፓናል ዉይይቶች ለተጎጂዎች ላቅ ያለ ጠቀሜታ አላቸዉና አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል የአለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ገዛኸኝ ፍቃዱ በበኩላቸዉ ፆታዊ ጥቃት መከላከል የሚያስችል ዉይይት መካሄዱ መከላከያን ጨምሮ በዉይይቱ የተሳተፉ ባለ ድርሻ አካላት ለሁሉም ለማዳረስ መስራት ይጠበቅባችኋል ብለዋል። ሴቶች በዉሳኔ ሰጭነት ቦታዎች ላይ ሙሉ በሙሉና በእኩልነት ሲሳተፉ ብቻ ነዉ ፍትሃዊነትን ማረጋገጥና ፆታዊ ጥቃትን መከላከል የሚቻለዉ ያሉት ደግሞ የመካከያ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ብርጋዲየር ጄነራል ሁላገርሽ ድረስ ናቸዉ፡፡ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ዳሚያን ሳይፕሪክ ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ የሴቶች ተሳትፎን ከመቶ ሃያ አምስት ፐርሰንት ማድረሷ የፆታ እኩልነት በማረጋገጥ ረገድ ያላትን ቁርጠኝነት ያመላክታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ዘጋቢ ፍፁም ተካ ፎቶግራፍ አበረ አየነው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

የዞብል ክፍለ ጦር በጽንፈኛው ሃይል ላይ እርምጃ ወስዶ ድሽቃ ማርኳል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም የምስራቅ ዕዝ ዞብል ክፍለ ጦር ሬጅመንቶች በምዕራብ ጎጃም እና በአዊ ዞን ልዩ ልዩ ወረዳዎች ባደረጉት ስምሪት በጽንፈኛው ሃይል ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ እና የንብረት ኪሳራ ማድረሳቸው ተገልጿል። የክፍለ ጦሩ አንድ ሬጅመንት በሰከላ ወረዳ ሱርባ ቀበሌ ባደረገው የተጠና ኦፕሬሽን የጽንፈኛው ሃይል ከማህበረሰብ ቀምቶ ይጠቀምበት የነበረ አንድ የጭነት መኪናን ጨምሮ 01 ዲሽቃ እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ አመርቂ ድል መቀዳጀታቸውን የሬጅመንቱ አዛዥ ተወካይ ሻምበል ዳዊት ማቲዮስ ተናግረዋል። በሌላ በኩል በአዩ ጓጉሳ ወረዳ እሁዲት እና አርቢት ቀበሌ ባከናወነው ስምሪት የጽንፈኛውን ሀይል ሙት እና ቁስለኛ ከማድረግም በተጨማሪ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እና ልዩ ልዩ ንብረት መማረክ መቻሉን የገለፁት ደግሞ በአካባቢው የተሰማራው ሬጅመንት ምክትል አዛዥ መቶ አለቃ እዮብ ማሞ ናቸዉ። ሃምሳ አለቃ ኤሊያስ ዘለቀ በበኩላቸዉ ክፍሉ ከሰሞኑ በተንቀሳቀሰባቸው አጉት ፣አሽፍ ፣ማርታ፣ ሱርታ፣ ጉባላ፣ ፋግታ ፣አምቢሲ፣ ሲፋ ተራራ ፣ጓልሳ እና ሱርባ በተባሉ አካባቢዎች የጸረ ሰላሙን ቡድን ተከታትሎ መደምሰስ መቻሉን  አብራርተዋል። ዘገባው የክፍለጦሩ የሠራዊት ሰነ-ልቦና ግንባታ ነው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

ሴት የሠራዊት አባላት ተልዕኳቸውን በውጤት እየፈፀሙ መሆኑ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ​የምስራቅ ዕዝ ኮር ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ኮሎኔል ባህሩ ንጉሴ የኮሩ ሴት የሠራዊት አባላት ባዘጋጁት መድረክ ላይ ተገኝተዉ ባስተላለፋት መልዕክት፦ ሴቶች ለሀገር ሰላም፣ ደህንነት እና ለህዝቦች አብሮነት የሚከፍሉት መስዋዕትነት ለትውልድ የሚሻገር ትልቅ የጀግንነት ታሪክ መሆኑን ተናግረዋል። የኮሩ ሴት የሠራዊት አባላት በተሰጣቸው ማንኛውም ወታደራዊ እና ህዝባዊ ተልዕኮ ላይ ሴትነታቸው ሳይገድባቸው በሙሉ ቁርጠኝነት በመሰለፍ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል። ሴቶች በጦር ሜዳ ውሎ ብቻ ሳይሆን በቴክኒክ፣ በስታፍ፣ በስነ-ልቦና እና በሌሎችም መዋቅራዊ ዘርፎች የሚያሳዩትን የላቀ ብቃትና አመራር ሰጭነት አጠናክረው መቀጠላቸውን አስረድተዋል። ​በሠራዊቱ ውስጥ የሚገኙ ሴት አባላት አቅምና ክህሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የጠቆሙት ምክትል አዛዡ ፤ ይህም በየደረጃው የሚደረጉ ስልጠናዎች የተሰጣቸው እምነት እና የራሳቸው የጸና ፍላጎት ተደምሮበት ውጤት እያመጡ ነው ብለዋል ። የኮሩ ሴቶች ጉዳይ ኃላፊ ተወካይ መቶ አለቃ እየሩስ አባይ ሴቶች በግዳጅ አፈፃፀም የሚያሳዩት ብቃትና ታማኝነት ለሌሎች አባላትም ትልቅ የሞራል ጥንካሬ እና አርአያነት እየሆኑ መምጣቱን ጠቁመዋል። ​በኮሩ ሠራዊት ውስጥ የሴቶችን እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገው የአመራሮች ድጋፍ እና ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ሴት አባላትን ሁለንተናዊ አቅም በመገንባት የተጣለባቸውን ሀገራዊ አደራ እና ግዳጅ በላቀ ሁኔታ እንዲወጡ የሚያስችል ስራ በልዩ ትኩረት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። ዘጋቢ ሀብታሙ አወቀ ፎቶ ግራፍ አማኑኤል ግርማ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

የሠላምን ትርጉም የተረዱ ታጣቂዎች በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረደ እጅ ሰጥተዋል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም የሠላምን ትርጉም የተረዱ 18 የፅንፈኛው ፋኖ ታጣቂዎች በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረደ  ገደብዬና በጦሃ ቀበሌዎች ዙሪያ ለሠራዊታችን እጅ ሰጥተዋል። በ10ኛ ዕዝ አንድ ክፍለጦር በተሰማራበት ቀጠና ትጥቅ ታጥቀው ፀረ-ሰላም ተግባር ሲፈፅሙ የቆዩ የፅንፈኛው ታጣቂዎች የሠላም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሠላም እየመጡ መሆናቸውን የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ሸለመው ሙለታ ተናግረዋል። ምህረት ጠይቀው የገቡት ታጣቂዎች በበኩላቸው ፍላጎታችንና ጥቅማችን የሚረጋገጠው ሰላም ሲኖር በመሆኑ አስተማማኝ ሰላም እንዲኖር የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ወስነን መጥተናል ብለዋል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ በጡረታ ለተሰናበቱ አባላት ሽኝት አደረገ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ በተለያዩ ሙያዎች ሀገራቸውንና ተቋማቸውን በታማኝነትና በቁርጠኝነት ላገለገሉና የአገልግሎት ዘመናቸውን አጠናቀው በክብር ለተሰናበቱ የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች የምስጋናና የሽኝት መርሐ ግብር አካሂዷል። በዋና መምሪያው የፈውስና ክብካቤ መምሪያ ኃላፊ ብርጋዲየር ጀነራል እርጎ ሺበሺ፣ ከ30 ዓመታት በላይ ያለመታከት ተቋሙን በታማኝነት ያገለገሉ አባላት የሀገር ባለውለታ መሆናቸውን ገልፀው፣ አባላቱ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በሙሉ ቁርጠኝነት በመወጣት ያስመዘገቡት ስኬት ለእነርሱም ሆነ ለተቋሙ ትልቅ ክብር እንደሆነ አስረድተዋል። አባላቱ ከተቋሙ ያገኙትን ልምድና መልካም ሥነ ምግባር በሚሄዱበት አካባቢ ሁሉ በማንጸባረቅ የተቋሙ አምባሳደር ሆነው እንዲቀጥሉም አስገንዝበዋል። የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የፋይናንስ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል አበራ ድሪባ በበኩላቸው፣ ለአባላቱ የተደረገው ሽኝት ለአበረከቱት አገልግሎት እውቅና ከመስጠት ባለፈ፣ በተቋሙ እያገለገሉ ለሚገኙ አባላት ሞራልና የሥራ ተነሳሽነት ለመፍጠር ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። የዘገበው ደስታ ተረፈ ነው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

የሠራዊት ሥነ-ልቦና ግንባታ ለግዳጅ ስኬት ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም. የ6ኛ ዕዝ የሠራዊት ሥነ-ልቦና ግንባታ ክፍል ለዕዙ ከፍተኛ አመራሮችና መስመራዊ መኮንኖች የሞራልና የሥነ-ልቦና ዝግጁነትን የሚያጠናክር ሥልጠና ሰጥቷል። በስልጠናው ላይ የተገኙት የዕዙ የሠራዊት ሥነ-ልቦና ግንባታ ኃላፊ ብርጋዲየር ጀኔራል መለስ ይግዛው፣ ሀገራዊና ተቋማዊ እሴቶችን መሠረት ያደረገ ቀጣይነት ያለው የሥነ-ልቦና ግንባታ ለሠራዊቱ የድል ዝግጁነትና ለግዳጅ ስኬታማ አፈጻጸም ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። አመራሮች በሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀትና የሥነ-ልቦና ዝግጁነት በተግባር በመተርጎም፣ የሠራዊቱን እሴቶችና የድል መንፈስ በማጠናከር ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን በታማኝነት እንዲወጡም አሳስበዋል። ሥልጠናው የሠራዊቱን ሞራል፣ የዓላማ ጽናትና የጋራ አንድነት በማጠናከር፣ በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ መሰናክሎች ሳይበገር ግዳጁን በብቃት መፈጸም የሚችል ሠራዊት ለመገንባት ያለመ ነው። ዘጋቢ ውበቴ አማረ  ፎቶግራፍ የኔብቻ ቦጋለ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

የፅንፈኛውን ቡድን ዓላማ አንግበው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም የፅንፈኛውን ቡድን ዓላማ አንግበው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 110 ታጣቂዎች እጃቸውን ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ ክፍለጦር ሰጡ። በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች ለሠራዊቱ እጅ ሰጥተዋል። በተሳሳተ መንገድ ነፍጥ አንስተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 83 የፅንፈኛው አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃችው 27ቱ ደግሞ ጀሌ የቡድኑ አባላት ከጦርነት ይልቅ ሠላም የበጀናል ብለው እጅ መስጠታቸውን የክፍለጦሩ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል በንድር በደድ ተናግረዋል። በአካባቢው በተሰራው ጠንካራ የማግባባት ሥራ በርካታ የፅንፈኛው ታጣቂዎች መግባታቸውን አዛዡ  ጠቁመው በአካባቢው የነበረውን የፀጥታ ስጋት ለማሰወገድ ሠላማዊ መንገድን ለመከተል መምረጣቸው አዋጪ መንገድ ነው ብለዋል። የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አስማረ የኋላሽት  በበኩላቸው ለወረዳው ሠላምና መረጋጋት የአገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች ሚና የላቀ ድርሻ  እንደነበረው ገልፀው ይህም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። የሠላም አመራጩን ተቀብለው በሠላም የገቡ ታጣቂዎች በበኩላቸው በተሳሳተ መንገድ ሀገራችንን እና ህዝባችንን ስንበድል ቆይተናል አሁን ግን ከህዝባችን ጋር ሆነን በሠላምና ፀጥታ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል። የዘገበው ያዴታ ወዬሳ ነው። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

የሠራዊቱ የሀገር ወዳድነት መገለጫ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በማንኛውም ጊዜ የላቀ ግዳጅ መፈፀም የሠራዊታችን የሀገር ፍቅር፣ የጽናትና የተልዕኮ ቁርጠኝነት መገለጫ ነው። ይህ የሠራዊታችን ድንቅ አባባል የሀገር ፍቅርን፣ የተልዕኮ ቁርጠኝነትን፣ የወታደራዊ ጽናትንና ለሀገር ሉዓላዊነት የመቆም የማይናወጥ አቋምን የሚያንጸባርቅ የጀግንነት መርህ ነው። ለሠራዊታችን ኢትዮጵያ የተልዕኮው መነሻ፣ የቁርጠኝነቱ መዳረሻና የመስዋዕትነቱ ትርጉም ናት። ሠራዊታችን በታሪኩ የተሸከመው የሀገር አደራ በቃል የሚገለጽ ብቻ ሳይሆን በተግባር የሚረጋገጥ ነው። ይህ አደራ የሀገርን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ፣ የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት መጠበቅ፣ የሕገ መንግሥት ሥርዓትን ማክበርና ለሀገራዊ ጥቅም በተሟላ ዝግጁነት መቆምን ይጠይቃል። የሠራዊታችን ብቃት በስልጠና፣ በዲሲፕሊን፣ በተቀናጀ አመራር፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በተልዕኮ ታማኝነት የተገነባ ነው። ለሠራዊታችን መስዋዕትነት ማለት የግል ምቾትን ትቶ ለሀገር አደራ መቆም፣ በፈተና ወቅት ጽናትን ማሳየት፣ በችግር ፊት አለመንበርከክና የተሰጠውን ተልዕኮ በኃላፊነት መወጣት ነው። ወታደራዊ ጀግንነት የሚገለጸው በአካላዊ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን በአእምሮ ዝግጁነት፣ በሥነ ምግባር፣ በትክክለኛ ውሳኔና በተልዕኮ ላይ ባለው ቁርጠኝነት ጭምር ነው። የሠራዊታችን ጥንካሬ በግዳጅ ወቅት ብቻ ሳይሆን በሰላም ጊዜም የሙያ ሥነ ምግባሩን በመጠበቅ፣ ሕዝባችንን በማክበር፣ የሕዝብን ንብረት በመጠበቅና ለሰላም መጠናከር በሚያበረክተው አስተዋጽኦ የሀገር አለኝታነቱን ያረጋግጣል። የሠራዊታችን ክብር ከሕዝባችን እምነት ጋር የተሳሰረ በመሆኑ  የዘወትር ኃላፊነቱ በተግባር እያስመሰከረ ይገኛል ። ስለሆነም “ለአንድ ሀገር  መስዋዕት እንከፍላለን፤ እሷም ኢትዮጵያ ናት!” የሚለው አባባል የሠራዊታችን የቁርጠኝነት መግለጫ ብቻ አይደለም፤ የሀገር አደራን በታማኝነት ለመወጣት፣ በተሟላ ዝግጁነት ለመቆም፣ በዲሲፕሊንና በሥነ ምግባር ለመመራት እንዲሁም ለሕዝባችን ሰላምና ደኅንነት በተግባር ለመሥራት የገባነው የኃላፊነት ቃል ኪዳን ነው። በሃዱሽ ገብረህይወት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

የሠራዊቱ ክፍሎች በህዝባዊ ድጋፍ ላይ በስፋት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል የተሰማሩ የሠራዊት ክፍሎች ከተልዕኳቸው ጎን ለጎን በግዳጅ ቀጣናቸው የሚገኙ አርሶ አደሮችን ሰብል በመሰብሰብ ህዝባዊ ድጋፎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። በዕዙ ስር የሚገኝ የአንድ ሬጅመንት አዛዥ ሻምበል ሲሳይ ወጋየሁ እንዳሉት በእድሜ፣በጤና እና በሌሎች መሰል ምክንያቶች ሰብላቸውን መሰብሰብ ያቃታቸውንና ደጋፊ የሌላቸውን አርሶአደሮች ሰብል በመሰብሰብ የሬጅመንቱ የሠራዊት አባላት ከፍተኛ ህዝባዊ ድጋፎችን በማድረግ ላይ ናቸው። ሠራዊቱ የተሰጠውን ግዳጅ በፅናትና በጀግንነት እየፈፀመ ባገኘው ፋታ ሁሉ የአካባቢውን ማህበረሰብ ለመደገፍ የሚያሳየው ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ከተገነባበት ተቋማዊ እሴት የሚመነጭ መሆኑን የጠቆሙት አዛዡ የጥንካሬአችን ሁሉ መሰረት ለሆነው ህዝባችን የምናደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ድጋፍ ከተደረገላቸዉ አርሶ አደሮች መሀከል ወይዘሮ ሚዛን ብርሀኔ በሰጡት አስተያየት "ሠራዊቱ የህዝብ ልጅ  መሆኑን በተግባር አሳይቶናል"  ያሉ ሲሆን ለተደረገላቸው የጉልበት ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል። ዘገባዉ የመሀመድ ሠይድ ነዉ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

የሠራዊቱ ክፍሎች በህዝባዊ ድጋፍ ላይ በስፋት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል የተሰማሩ የሠራዊት ክፍሎች ከተልዕኳቸው ጎን ለጎን በግዳጅ ቀጣናቸው የሚገኙ አርሶ አደሮችን ሰብል በመሰብሰብ ህዝባዊ ድጋፎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። በዕዙ ስር የሚገኝ የአንድ ሬጅመንት አዛዥ ሻምበል ሲሳይ ወጋየሁ እንዳሉት በእድሜ፣በጤና እና በሌሎች መሰል ምክንያቶች ሰብላቸውን መሰብሰብ ያቃታቸውንና ደጋፊ የሌላቸውን አርሶአደሮች ሰብል በመሰብሰብ የሬጅመንቱ የሠራዊት አባላት ከፍተኛ ህዝባዊ ድጋፎችን በማድረግ ላይ ናቸው። ሠራዊቱ የተሰጠውን ግዳጅ በፅናትና በጀግንነት እየፈፀመ ባገኘው ፋታ ሁሉ የአካባቢውን ማህበረሰብ ለመደገፍ የሚያሳየው ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ከተገነባበት ተቋማዊ እሴት የሚመነጭ መሆኑን የጠቆሙት አዛዡ የጥንካሬአችን ሁሉ መሰረት ለሆነው ህዝባችን የምናደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ድጋፍ ከተደረገላቸዉ አርሶ አደሮች መሀከል ወይዘሮ ሚዛን ብርሀኔ በሰጡት አስተያየት "ሠራዊቱ የህዝብ ልጅ  መሆኑን በተግባር አሳይቶናል"  ያሉ ሲሆን ለተደረገላቸው የጉልበት ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል። ዘገባዉ የመሀመድ ሠይድ ነዉ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official

የፍትሕ ስርዓቱን ለማዘመን የሙያተኛውን አቅም  ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በመከላከያ ፍትሕ ዋና ዳይሬክቶሬት እና በኢፌዴሪ ፍትሕ ሚኒስቴር አዘጋጅነት ለፍትሕ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ተጀመረ። በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ስልጠናውን ያስጀመሩት የመከላከያ ፍትህ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል አሰፋ ደበሌ ዳይሬክቶሬቱ ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር ከስልጠና ባሻገር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ስለመሆኑ ተናግረዋል። ሰራዊታችን የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ በሕግ አግባብ በስኬት እንዲፈጽም ሰልጣኞች በየክፍላቸው ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ሊሰሩ እንደሚገባ የጠቆሙት ብርጋዲየር ጄኔራል አሰፋ ደበሌ የሠራዊቱንና የተቋሙን ጥቅም ለማስጠበቅ በሕግ አግባብ ከመስራት ባሻገር አመራሮችን ማማከር እንደሚገባም አመላክተዋል። ስልጠናው በፍትሃብሔር ጉዳይ ክስ መስማት ፣ማደራጀትና ፍትሀዊ ውሳኔ ማስወሰን ላይ ያተኮረ መሆኑን የገለጹት በኢፌዴሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ንቃተ ሕግና ስልጠና ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ወርቁ በቀጣይም ከመከላከያ ፍትሕ ዳይሬክቶሬት ጋር  በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል። በኢፌዴሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ረዳት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ተክለልብሰ ወርቅ ከበበው በአቤቱታ አቀራረበ ፣ የምስክር አቀራረብ ፣ የሕግ ባለሙያ ስነ ምግባሮች፣ ይግባኝና ፍርድ አፈፃፀም ላይ በስፋት ትምሕርቱን የሰጡ ሲሆን የሕግ ባለሙያው ተአማኒ ፣ በቂ ዕውቀት ፣ ጠንቃቃ፣ የማሳመን ብቃት ያለውና ጥሩ ስነ ምግባር ሊኖረው ይገባል ብለዋል። ስልጠናው ከዕዞች ኃይሎችና ዋና መምሪያዎች የተውጣጡ የፍትሕ ባለሙያዎችን ያካተተ መሆኑም ተጠቁሟል። ዘጋቢ ጀማነሽ ታደሰ ፎቶግራፍ ጌታሰው ጌትነት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት https://dfmc.mod.gov.et/ https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2 https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0 https://www.facebook.com/fdredefense.official