ar
Feedback
𝙳𝚂𝙳 𝙲𝚘𝚗𝚜𝚝𝚛𝚞𝚌𝚝𝚒𝚘𝚗 - 𝚂𝚘𝚕𝚞𝚝𝚒𝚘𝚗𝚜

𝙳𝚂𝙳 𝙲𝚘𝚗𝚜𝚝𝚛𝚞𝚌𝚝𝚒𝚘𝚗 - 𝚂𝚘𝚕𝚞𝚝𝚒𝚘𝚗𝚜

الذهاب إلى القناة على Telegram

ይህ ስለሀገራችን የግንባታ ሕግ (construction law)፣ ስለግንባታ ቁጥጥርና ክትትል ሥራዎች፣ ስለውል አስተዳደር (contract administration) እንዲሁ ተያያዥ ክፍት የሥራ ማስታወቂያዎችን የሚያገኙበት የእርስዎ ትክክለኛ ቤት ነው።

إظهار المزيد
630
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-57 أيام
-930 أيام

جاري تحميل البيانات...

سحابة العلامات
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
الإشارات الواردة والصادرة
---
---
---
---
---
---
جذب المشتركين
ديسمبر '24
ديسمبر '24
+5
في 0 قنوات
نوفمبر '24
+3
في 0 قنوات
Get PRO
أكتوبر '24
+3
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '24
+8
في 0 قنوات
Get PRO
أغسطس '24
+14
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '24
+20
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '24
+9
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '24
+20
في 0 قنوات
Get PRO
أبريل '24
+68
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '24
+35
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '24
+78
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '24
+478
في 1 قنوات
التاريخ
نمو المشتركين
الإشارات
القنوات
21 ديسمبر+1
20 ديسمبر0
19 ديسمبر+1
18 ديسمبر+1
17 ديسمبر0
16 ديسمبر0
15 ديسمبر0
14 ديسمبر0
13 ديسمبر0
12 ديسمبر0
11 ديسمبر0
10 ديسمبر0
09 ديسمبر+1
08 ديسمبر+1
07 ديسمبر0
06 ديسمبر0
05 ديسمبر0
04 ديسمبر0
03 ديسمبر0
02 ديسمبر0
01 ديسمبر0
منشورات القناة
የሮቤ-ጋሰራ-ጊኒር መንገድ ድልድይ ፈርሷል የሮቤ-ጋሰራ-ጊኒር የመንገድ ክፍል በድልድይ መደርመስ የተነሳ ከትራፊክ እንቅስቃሴ ለጥቂት ቀናት ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያስታወ
የሮቤ-ጋሰራ-ጊኒር መንገድ ድልድይ ፈርሷል
የሮቤ-ጋሰራ-ጊኒር የመንገድ ክፍል በድልድይ መደርመስ የተነሳ ከትራፊክ እንቅስቃሴ ለጥቂት ቀናት ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያስታወቀ ሲሆን ከጋሰራ መገንጠያ 30 ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኘው የደንበል ወንዝ የብረት ድልድይ ከባድ ጭነት በጫነ ተሸከርካሪ ምክንያት ጉዳት እንደደረሰበት ጠቁሟል። በመሆኑም የጥገና ሥራው ተጠናቆ ድልድዩ ለትራፊክ ክፍት እስኪደረግ ድረስ አሽከርካሪዎች የሮቤ-ጎሮ-ጊኒር እና ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል፡፡ የቴግራም ቻናላችን: t.me/DSDConstruction ሊጽፉልን ካሰቡ t.me/DSDCon ቲክቶክ: www.tiktok.com/@dsdconstruction

2
ጥያቄ፦ የሀገራችን ህጎች (በተለይ FIDIC እና PPA) ላይ "መሐንዲስ (The engineer)" ብሎ የሚጠራው አካል ከሚከተሉት ውስጥ የትኛውን ነው።
387
3
የግንባታ ቦታን ማስረከብ የግንባታ ባለቤት (Client) ለግንባታ ሥራ መሰናክል ከሆኑ ነገሮች (ለምሳሌ፦ የካሳ ጥያቄ ከሚያነሱ ሰዎች ቁጥጥር፣ ከመብራት፣ ከውሃ፣ ከቴሌ ግንባታዎችና መሣሪያዎች) በማጽዳት ወይም ነጻ በማድረግ ዝግጁ የሆነ የግንባታ ቦታን ለሥራ ተቋራጩ (Contractor) የማስረከብ ሕጋዊ ኃላፊነት አለበት። ባለቤቱ የግንባታ ቦታውን ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ለሥራ ተቋራጩ ካላስረከበ የግንባታ ማስረከቢያ ጊዜ መራዘም/መዘግየት/ ላይ ለሚያስከትለው ኪሳራ ወይም ወጪ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ የሕንጻ ግንባታ ደንቦች (Standard Building Contract with quantities) በአንቀጽ 2.4 እና 2.24 ስር የሰፈረ ድንጋጌ ነው። የቴግራም ቻናላችን: t.me/DSDConstruction ሊጽፉልን ካሰቡ t.me/DSDCon ቲክቶክ: www.tiktok.com/@dsdconstruction
326
4
በሕንጻ አዋጅ ቁጥር 624/2001 እና በሚስቴሮች ም/ቤት ደንብ ቁ 243/2003 መሰረት፦ __________ ማለት አንድ ሕንጻ መገንባት ለሚፈልግ አካል ሕንጻውን ለመገንባት የሚያስችሉት ዝርዝር መሥፈርቶች እንደተሟሉ በከተማው ሹም ተረጋግጦ ፍቃድ መሰጠቱን የሚገልጽ ማስረጃ ማለት ነው።
360
5
የኢትዮጵያ የህንጻ ኮዶችን የሚያሻሽልና አዲሶችን የሚያካትት ፕሮጀክት ስምምነት ተካሄደ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን  ነባር የህንጻ ኮዶችና ስታንዳርዶችን የሚያሻሽልና አዳዲዲስ ኮዶችና ስታንዳርዶችን የሚያካትት ፕሮጀክት ስምምነት ከአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር ተፈራርሟል። ነሀሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው የስምምነት ፊርማ ስነስርአት ላይ እንደተመለከተው 20 ነባርና በስራ ላይ የሚገኙ የህንጻ ኮዶችና ስታንዳርዶችን የማሻሻልና የማዘመን እንዲሁም 10 አዳዲስና አስገዳጅ ኮድና ስታንዳርዶችን የማዘጋጀት ፕሮጀክት ነው። ለፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በኩል 57 ሚሊዮን ብር የተበጀተ ሲሆን የአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ11 ወር አገባዶ ያስረክባል። ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ  እና የኢንስቲትዩቱ ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር ልብሰወርቅ ነጋሽ ተፈራርመዋል። በስነስርአቱ ላይ የሁለቱ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች በሰነዶቹ ዝግጅት ላይ መካተት ያሉባቸውና ትኩረት በሚሰጣቸው ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። የኢትዮጵያ ህንጻ ኮዶች  ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ሶስት ጊዜ ክለሳና ማሻሻያ የተካሄደባቸው ሲሆን የኮንስትራክሽን ዘርፉ ፍላጎት ውስብስብ መሆን፣ እንደሀገርም በዘርፉ ከፍተኛ ለውጥ  በመኖሩ እና አዳዲስ ግብአቶችና አሰራሮች  እያደጉ በመምጣታቸው ምክንያት እነዚህን ነባራዊ ሁኔታዎች ያገናዘበ የኮድና ስታንዳርድ ማሻሻያና አዳዲስ ሰነዶች ዝግጅት እንደሚደረግ ተሰምሮበታል። በቀጣይም የዘርፉን ውጤታማነት ከፍ ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን  ለማከናወን ሁለቱ ተቋማት ግንኙነታቸውን እንደሚጠናከር በስምምነት ስነስርአቱ ላይ ተመልክቷል። የቴግራም ቻናላችን: t.me/DSDConstruction ሊጽፉልን ካሰቡ t.me/DSDCon ቲክቶክ: www.tiktok.com/@dsdconstruction
368
6
ጥያቄ፦ በፍትሐብሔር በተጠቀሰ የግንባታ ሕግ መሰረት አንድ ተቋራጩ የተከናወኑ ሥራዎች የደረሱበትን ሁኔታና እንዲሁም የሥራውን ዋጋ፣ ለሥራ የተጠቀማቸውን ነገሮች (ግብአቶችን የሰው ኃይል እና ማሽኖች/እቃዎች) ታሳቢ ያደረገውን ወጪ ላሠሪው አካል የማሳወቅ ግዴታ አለበት። በውሉ ላይ የተገለጸ ተቃራኒ ቃል የሌለ እንደሆነ ተቋራጩ በ___________ ጊዜ ውስጥ ለአሠሪው ሪፖርት ማቅረብ አለበት።
427
7
የአረንጓዴ ቦታ ሽፋን መመሪያ (Green Area Coverage Directive) አዲስ መመሪያ፦ በአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፍቃድ ለምታወጡ ባለይዞታዎች እና ዲዛይን ለምሠሩ ባለሙያዎችና አማካሪዎች
የአረንጓዴ ቦታ ሽፋን መመሪያ (Green Area Coverage Directive) አዲስ መመሪያ፦ በአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፍቃድ ለምታወጡ ባለይዞታዎች እና ዲዛይን ለምሠሩ ባለሙያዎችና አማካሪዎች የአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አንድ ሰው ሕንጻ ለመገንባት ፍቃድ ሲያወጣ 4% የሚሆነው ቦታውን የአረንጓዴ ቦታ እንዲያደርግ የሚያስገድድ መመሪያ አውጥቷል። ይህም ማለት፦ ለምሳሌ አንድ ሰው 100 ካሬ ሜትር የካርታ ቦታ ቢኖረው እና የግንባታ ፍቃድ ለማውጣት ቢፈልግ የሚያሠራው ዲዛይን ቢያንስ 2ሜትር በ2ሜትር (2m*2m = 4 square meter) ወይም አራት ካሬሜትር የሚሆነውን የግቢውን ቦታ የአረንጓዴ ቦታ አድርጎ ማሠራት ይጠበቅበታል። ይህ የአረንጓዴ ቦታ በመሬት ውስጥ፣ በመሬት ላይ እና በአየር ላይ የትኛውም የሕንጻው አካል የማይነካው ንጹሕ መሬት መሆን እንዳለበት ተደንግጓል። በአጭሩ፦ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገነቡ ሕንጻዎች በዲዛይን ሥራ ላይ የይዞታውን 4% ለአረንጓዴ ቦታ ታሳቢ የተደረጉ መሆን እንዳለባቸው ተመርቷል። እንደመመሪያ አገላለጽ ታሳቢ የሚደረገው ቦታ እኩል ርዝመትና ወርድ (Length and width) ያላቸው እንዲሆኑ ጠቋሚ ነው። የቴግራም ቻናላችን: t.me/DSDConstruction ሊጽፉልን ካሰቡ t.me/DSDCon ቲክቶክ: www.tiktok.com/@dsdconstruction
414
8
+5
https://t.me/ETCONp
574
9
ከመንገድ የህንጻ ርቀት ህግ (Set back rules) በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የቀረበው ከመንገድ የህንጻ ርቀት ህጎች። በነዚህ ህጎች መሰረት በርቀት ክልል ውስጥ ምዝውጥ (cantilever)+1
ከመንገድ የህንጻ ርቀት ህግ (Set back rules) በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የቀረበው ከመንገድ የህንጻ ርቀት ህጎች። በነዚህ ህጎች መሰረት በርቀት ክልል ውስጥ ምዝውጥ (cantilever) መገንባትም አይፈቀድም። @ethiopianarchitectureandurbanism
351
10
لا يوجد نص...
1
11
ጥያቄ፦ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ በመደበኛ የግንባታ ሥራ የውል ሰነድ (Contract document) ውስጥ ለብቻው ተነጥሎ እንደሥራ ተቆጥሮ (As separately described task) የማናገኘው የትኛውን ሥራ ነው?
458
12
የቁፋሮ ሥራ (Excavation works) ላይ መረጋገጥ ያለባቸው የቁጥጥር ነጥቦት የቁፋሮ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ቁፋሮዎች፣ አጎራባች ቦታዎች እና የመሬት መንሸራተት መከላከያ ዘዴዎች በባለሙያ ጥናት ሊደረግባቸው ይገባል። ይመረመራሉ። በመሆኑም በቁፋሮ ሥራ የግንባታ ቁጥጥር ባለሙያው የሚከተሉትን ነጥቦች ትኩረት አድርጎ ማረጋገጥ አለበት። 1. የአጎራባች ወሰንን ከመፍረስ መታደግ፦ በግንባታ ሥራ የመጀመሪያው ተግባር ቁፋሮ ሲሆን ማንኛውም ቦታ አጎራባች የሆነ የሕንጻ ቦታ ወይም መንገድ የሚኖረው ሲሆን ቁፋሮው ወደአጎራባች ወሰን ተጠግቶ የሚከናወን ከሆነ በቁፋሮው መጠጋት አልያም በንቅናቄ (Vibration) የተነሳ የአጎራባች መሬት በመውደቅ ወይም በመንከባለል ለሁለቱም ቦታዎች አደጋ እንዳይፈጥር የሚያስችል ቅድመ ጥንቃቄ መደረጉን ማረጋገጥ አለበት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ የጎረቤት ወሰን/አጥር/ ቢፈርስ ወይም ሕንጻ ቢወድቅ በመሐንዲሱ የክትትል ድክመት የተነሳ ካሳ እንዲከፍሉ ሊገደዱ ይችላሉ። 2. በሕግ የሚፈቀደውን የውጪ መስመር አለማለፉን ማረጋገጥ፦ ሕንጻው የሚሰራበት የካርታ ቦታ በአካባቢ ልማት (Local development plan) መሰረት ከፍተኛ የኢሌክትሪክ ኃይል (High Electric tension) የሚያልፍበት አልያም የመንገድ ማስፋፊያ ስፋት (Road Widening Area) የሚገባበት ሊሆን ስለሚችል በግንባታ ወቅት የተዘጋጀ አዲስ የፕላን ስምመትን በማመሳከር እንደዲዛይኑ በተፈቀደ ክልል ውስጥ ማረፉን እና በባለቤት ግፊት የተነሳ ያልተፈቀደ ቦታ ላይ አለማረፉን ማረጋገጥ አለበት። 3. በቁፋሮ ክልል ደህንነትን ማረጋገጥ፦ ከቁፋሮው በኋላ ከመሬት ውስጥ ያለው ሥራ (Sub Structure Works) ተጠናቆ የተቆፈረው ክፍል እስኪሞላ ድረስ የሰከረ፣ ወይም የአእምሮ እክል ያለበት፣ ወይም ሕጻናት፣ ወይም ሽማግሌዎች ወደጉድጓድ ገብተው አካላዊ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ከተፈቀደላቸው የግንባታ ሰራተኞች ውጪ ወደ ክልሉ እንዳይገቡ የታጠረ (Fenced) እና የውስጥ መሸጋገሪያ (Bridge Ladders) የተሰራላቸው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። 4. የመሬት ውስጥ ዝርጋታዎች (Underground installations)፦ በሰፋፊ ግቢዎች ውስጥ ለግቢው አግልግሎት የሚሰጡ አስቀድሞ የተዘረጉ የውኃ፣ የኢንተርኔት፣ የመረጃ እና የመብራት ዝርጋታዎች የሚኖሩ ከሆነ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር በጥንቃቄ እንዲነሱ አልያም ግንባታው ጉዳት ሳያደርስባቸው እንዲከናወን ማድረግ ይኖርበታል። 5. የቁፋሮውን ልኬት ማረጋገጥ፦ በተለይ በአርክቴክቸራል፣ ስትራክቸራል እና ሳኒታሪ ንድፎች ላይ የተመለከተው ተጓዳኝ የቁፋሮ ሥራ የሚጠይቁትን ልኬቶች ማሟላቱን (ወርዱን፣ ስፋቱን፣ ርዝመቱን፣ ዲያሜትሩን፣ ጥልቀቱን) ጠብቆ ቁፋሮ መንዲከናወን የመቆጠጠርና መከናወኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። 6. ውኃ እንዳይቋጥር ማስደረግ፦ በዝናባማ እና የመሬት ውኃ በሚፈልቅባቸው አካባቢዎች ቁፋሮ እንደተከናወነ ዝናብ ቢዘንብ ቢያንስ የጎርፍ ውሃ እንዳይገባ የመከላከያ ሥራዎች፣ እንዲሁም የመሬት ውስጥ ምንጭ ውሃን የመከላከያ (like: Permeable hardcore layer, geotextile material, channelization...) መንገዶች ተግባራዊ የሚደረጉበት መሆኑን ማረጋገጥና መከታተል አለበት። 7. የቁፋሮ ግብአቶችና ማሽኖችን ደህንነት ማረጋገጥ፦ በቁፋሮ ሥራ መወጣጫ የሚሆኑ የብረት፣ የእንጨት እና የፕላስቲክ ግብአቶችን ብልሽት የሌለባቸው መሆኑ እና ለቁፋሮ ሥራ የቀረቡ የእጅ መሳሪያዎች እና ማሽኖች የደህንነት ችግር የሌለባቸው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። 8. በቂ አየርና ብርሃን የሚገኝበት መሆኑን፦ በጣም ልዩ ሁኔታ የሚባልና በብዙዎቹ ግንባታዎች ላይ የማይገጥም ቢሆንም በውኃ ውስጥ፣ በመሬት ውስጥ ለሚከናወኑ ቁፋሮዎች የሚሳተፉ ሰራተኞች በቂ የሆነ የኦክስጅን አየር ማግኘት ስላለባቸው መሐንዲሱ የአየር ሁኔታውን የሚቆጠጠሩ ማሽኖች፣ አልባሳት እና ብርሃን መቅረባቸውን ማረጋገጥ ማድረግ አለበት። የቴግራም ቻናላችን: t.me/DSDConstruction ሊጽፉልን ካሰቡ፡ t.me/DSDCon ቲክቶክ: www.tiktok.com/@dsdconstruction
399
13
መልስ በኢትዮጵያ የሕንጻ ነክ ሕጎች መሰረት በአንድ የሕንጻ ተቋራጭ ሥር የሚሰሩ ምክትል /ንዑስ/ ሥራ ተቋራጮች (Sub contractors) ወይም ሠራተኞች (labours) ዋናው ተቋራጭ ለሠሩበት ሥራ ሳይከፍላቸው ከቀረ እና ለሠሩበት ሥራ ዋጋ እንዲከፈላቸው ክስ ካቀረቡ ክሳቸውን ባቀረቡበት ጊዜ አሠሪው ለሥራ ተቋራጩ ሊከፍል በሚገባው ገንዘብ መጠን በቀጥታ ገንዘባቸውን የመጠየቅ መብት ስላላቸው ያንን ክፍያ የማግኘት መብት አላቸው። ለምሳሌ፦ አንድ ተቋራጭ በውል ሰነዱ ውስጥ የአንድ ካሬሜትር የፎርምወርክ ሥራን በ500 ብር ሂሳብ ተዋውሎ ለምክትል ሥራ ተቋራጩች በ300 ብር ተነጋግሮ ካሠራቸው በኋላ ክፍያ ሳይከፍላቸው ቢቀር (ቢያዘገይባቸው) ክስ ማቅረብ ይችላሉ። ክስ ሲያቀርቡ ሥራውን ለመሥራታቸው ማረጋገጫ ካቀረቡ እና የሥራው ጥራት ታይቶ ተቀባይነት ካገኘ ዋናው ተቋራጭ የተዋዋለበትን 500ብር ሊከፈላቸው የሚችልበት አግባብ አለ ማለት ነው። ለማንኛውም አስተያየትዎ እና ሀሳብዎ ይጻፉልን! የቴግራም ቻናላችን: t.me/DSDConstruction ሊጽፉልን ካሰቡ t.me/DSDCon ቲክቶክ: www.tiktok.com/@dsdconstruction
336
14
ጥያቄ፦ በአንድ ተቋራጭ ሥር የሚሠሩ ምክትል ሥራ ተቋራጮች (Sub Contractors) የሠሩበትን የሥራ ክፍያ ዋናው ተቋራጭ አልከፍል ቢላቸው ክስ መስርተው በዋናው ተቋራጭ ውል ላይ የተመለከተውን የሥራ ዋጋ የማግኘት መብት አላቸው።
324
15
የጥገና ሥራ (Maintenance of defects) እና ጥገና የሚከናወንበት አስገዳጅ ጊዜ [ኢ/ር ዳንኤል ታጠቅ] አንድ ተቋራጭ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት ገንብቶ የማስረከብ ግዴታ ያለበት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከጊዜያዊ ርክክብ እስከ መጨረሻ ርክክብ ድረስ ያለው ጊዜ የብልሽት (እክል) መለያ ጊዜ (defect liability period) የሚባል ሆኖ አሠሪው ባለቤት ሥራዎቹን ለመጨረሻ ጊዜ ከመረከቡ በፊት አገልግሎት እየሰጠበት ሳለ ሁሉም ሥራዎች በአግባቡ መሠራታቸውን ለመመርመር የሚያስችለው ጊዜ ሲሆን ርዝማኔው በውላቸው ላይ የሚወሰን መሆኑን የፍ/ህ/ቁ 3276 እስከ 3277 ድንጋጌ አስቀምጧል። በድንጋጌው መሰረት ሥራ ተቋራጩ በጊዜያዊ ርክክብ ለባለቤቱ ሳያስረክብ ከፍተኛ በሆነ ኃይል ምክንያት መፈራረስ ወይም ጉዳት ቢደርስበት ኪሳራው የሥራ ተቋራጩ ስለሆነ ከርክክብ በፊት ጥገና ማከናወን አለበት። በፍ/ሕ/ቁጥር 3278 (2) መሰረት ሥራ ተቋራጩ ከአሠሪው መሥሪያ ቤት /ባለቤት/ እንዲያድሳት የሚያስፈልገው ሥራ ተመልክቶ እንዲያድስለት ትእዛዝ በደረሰው ጊዜ የማደስ ግዴታ አለበት (ሥራ ተቋራጩ የእክል መለያ ጊዜ ውስጥ ከሆነ ከአንድ ጊዜ በላይ የእድሳት ትእዛዝ ሊሰጠው የሚችል ሲሆን እየተመላለሰ ሊያድስ የሚችልበት አስገዳጅ ሁኔታ ነው)። ይህ የጥገና ጊዜ በፍ/ሕ/ቁ 3277 (2) መሰረተ በውል የሚወሰን እንዲሆን የተፈቀደ ሲሆን ብዙ የሀገራችን የግንባታ ውሎች ስድስት ወር (6 Months) እና አንድ ዓመት (1 year) የመጠቀም ልምድ አላቸው። ተቋራጩ ከእያንዳንዱ ክፍያው ላይ 5% የጥገና መያዣ እየተቀነሰ የሚከፈለው ሲሆን በጊዜያዊ ርክክብ ሰዓት ግማሹ (ማለትም 2.5%) ይመለስለታል። ነገር ግን 2.5% ክፍያው የብልሽት መለያ ጊዜ እስኪጠናቀቅ ድረስ አሠሪው ባለቤት የሚይዘው ሲሆን ጥገና በሚያስፈልግበት ሰዓት ጥገናውን ለማከናወኑ መያዣ ነው። ሥራ ተቋራጪ ጥገናውን የማያከናውን ከሆነ ለጥገና ማሠሪያ የሚውል ገንዘብ ሲሆን ለተቋራጩ ተመላሽ አይሆንም። ተቋራጩ የተጠየቀውን የጥገና ሥራ ካከናወነ ግን ቀሪ 2.5% በመጨረሻ ርክክብ ጊዜ የሚለቀቅለት ክፍያ ይሆናል። የቴግራም ቻናላችን: t.me/DSDConstruction ሊጽፉልን ካሰቡ t.me/DSDCon ቲክቶክ: www.tiktok.com/@dsdconstruction
350
16
የዲኤስዲ ኮንስትራክሽን (DSD Construction) ቤተሰቦች በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ በደረሰው የመሬት ናዳ ብዙ ወገኖቻችንን ማጣታችን ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል። መጽናናትን ለሀገራችን ያድላት! የተጎዱ+1
የዲኤስዲ ኮንስትራክሽን (DSD Construction) ቤተሰቦች በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ በደረሰው የመሬት ናዳ ብዙ ወገኖቻችንን ማጣታችን ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል። መጽናናትን ለሀገራችን ያድላት! የተጎዱትን ለማገዝ እንረባረብ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።
355
17
አንድ ግለሰብ ለረጅም ጊዜ መንግሥት ወይም ሌላ አካል የገነባውን ቤት ለረጅም ጊዜ መያዙ ባለቤት ሊያደርገው ይችላልን? አንድ ግለሰብ አንድን የመንግሥት የኪራይ ቤት ወይም በሌላ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተገንብቶ ለረጅም ዓመት እንዲኖርበት የተፈቀደለትን ቤት ለረጅም ግዜ ስለኖረበት ብቻውን የባለቤትነት መብት እንደማያሰጠው የሰበር ሰሚ መዝገብ ቁጥር 228002 (ሠ/መ/ቁጥር 228002) በውሳኔ አጽንቷል። ይህ መዝገብ "አንድን ቤት ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት የማያጎናጽፍ ነው" ብሏል። አያይዞም "ቤቱ የቀበሌ /የመንግስት/ ቤት መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌሉበት ሁኔታ በተቋሙ የመረጃ ስርአት ቅጽ 008 በቀበሌ ቤትነት መመዝገቡ ብቻ ቤቱ በመንግስት የተወረሰ የቀበሌ /የመንግስት ቤት ነው ሊያስብለው አይችልም" ብሎም አረጋግጧል። በተጨማሪም "በአዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሶ ለረጅም ግዜ በመንግስት እጅ የነበረ ቤትን በሚመለከት በስህተት አላግባብ ያለህጋዊ ምክንያት የተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የመከነና በመንግሰት ባለቤትነት የሚታወቅ መሆኑ በተገለጸበት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት መንግስት የወረሰው መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌለበት ቤቱን የመንግስት ንብረት አያሰኘውም" ብሏል። በዚህ አግባብ ለረጅም ጊዜ የኖረበት አካል ረጅም ዓመት ስለኖረ ብቻ የባለቤትነት መብት እንደማያገኘው ሁሉ መንግሥት ወይም የቤቱ ባለቤት የባለይዞታ ማረጋገጫ ለማግኘትም እንዲሁ ማሟላት ያለበት መስፈርት ተቀምጧል። የቴግራም ቻናላችን: t.me/DSDConstruction ሊጽፉልን ካሰቡ t.me/DSDCon ቲክቶክ: www.tiktok.com/@dsdconstruction
379
18
የከተማን ቤትን ንብረትነት ዝውውርን ለመፈጸም የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች ~ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት/ካርታ/ ~ ግንባታው በዋስትና ያልተያዘ እንዲሁም እዳ የሌለበት መሆኑ ማረጋገጫ ወይም እዳው በሚመለከተው አካል በደብዳቤ መነሳቱን ያረጋገጠበት ደብዳቤ ~ የቤትና ይዞታ ሽያጭ ወይም የስጦታ ውሉ በምስክሮች የተረጋገጠብት ሰነድ በፍትህ ወይም በመሪ ማዘጋጃ ቤት ፊት ቀርቦ የጸደቀበት ሰነድ ~ ግንባታው ጸድቆ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት 50 በመቶና በላይ የተሰራ መሆኑ በባለሙያ ተረጋግጦ ሲቀርብ ~ በይዞታው ላይ ውዝፍ የቦታ ኪራይ የሌለበት ስለመሆኑ ወይም ውዝፍ የቦታ ኪራይ ክፍያ አጠናቆ የከፈለ ስለመሆኑ የቀረበ ክፍያ ደረሰኝ ማስረጃ ~ የአገልግሎትና የገቢዎች ክፍያ በቤቱ ግምት መሰረት ስለመከፈሉ ማረጋገጫ ~ የቤት ሽያጭ ውል/ስምምነት/ ሰነድ የቴግራም ቻናላችን: t.me/DSDConstruction ሊጽፉልን ካሰቡ t.me/DSDCon ቲክቶክ: www.tiktok.com/@dsdconstruction
362
19
ዜና ዕረፍት! የዝነኛው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ባለቤት ሲሞን ፔትሮ ሳሊኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ በአገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ብሔራዊ እና ግዙፍ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ዝናን ያተረፈው ሳሊኒ
ዜና ዕረፍት! የዝነኛው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ባለቤት ሲሞን ፔትሮ ሳሊኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ በአገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ብሔራዊ እና ግዙፍ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ዝናን ያተረፈው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ባለቤት በ92 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። እኚህ ግለሰብ 1.5 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የፎርብስ መጽሔት መረጃ ያሳያል። Via-#Artstvworld #Artstv_world_news
393
20
📌 የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ካሣ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁ. 1161/2011
348