998
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
ለተማሪ ወላጆች በሙሉ
የ2019 አ.ም የማጠናከሪያ ትምህርት የጀመርን በመሆኑ ተማሪዎችን በማስመዝገብ ወደ ማጠናከሪያ ትምህርቱ እንድታስገቡ በማለት እናሳስባለን።
ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ወላጆች በሙሉ
የስብሰባ ቀን ማስተካከያን በተመለከተ
ጥቅምት 2 ቀን 2019 የተባለው ጥሪ እሁድ ጥቅምት 1 ቀን 2019 አ.ም በሚል ይስተካከል።
ለወላጆች በሙሉ
የ2019 አ.ም የትምህርት ዘመን የማጠናከሪያ ትምህርት ከጥቅምት 2 ቀን 2019 አ.ም ጀምሮ ከ1ኛ-8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የሚሰጥ ሲሆን ተማሪዎቹን እንድታስመዘግቡ በማለት እያዳሰብኩ በተለይም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች የብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ በመሆናቸው ሁሉም ተማሪቆች መሳተፍ ያለባቸው መሆኑን አውቃችሁ ወላጆች ምዝገባውን እንድታከናውኑ በማለት እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ ለተማሪዎችና ለወላጆች በሙሉ
ከመስከረም 26-ጥቅምት2ቀን 2019 አ.ም ድረስ የ1ኛው ተርም የመጀመሪያ ዙር ቴስት የሚሰጥ በመሆኑ ከዚህ በታች ባለው መርሃ ግብር መሰረት እንድትዘጋጁ በማለት እያሳሰብ ትምህርት ለሙሉ ቀን የሚሰጥ መሆኑን እናሳስባለን የት/ቤቱ አስተዳደር
ለተማሪዎችና ወላጆች በሙሉ
አርብ መስከረም 22 ቀን 2019 አ.ም ትምህርት የማይኖር ሲሆን ተማሪዎች ጥናታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ በማለት እናሳስባለን።
54ቱ የአፍሪካ ሀገራትና ዋና ከተሞቻቸው፦
1. አልጀሪያ — አልጀርስ (Algiers)
2. አንጎላ — ሉዋንዳ (Luanda)
3. ቤኒን — ፖርቶ-ኖቮ (Porto-Novo)
4. ቦትስዋና — ጋቦሮኔ (Gaborone)
5. ቡርኪና ፋሶ — ዋጋዱጉ (Ouagadougou)
6. ቡሩንዲ — ጊቴጋ (Gitega)
7. ኬፕ ቬርዴ — ፕራያ (Praia)
8. ካሜሩን — ያውንዴ (Yaoundé)
9. ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ — ባንጊ (Bangui)
10. ቻድ — ንጃሜና (N’Djamena)
11. ኮሞሮስ — ሞሮኒ (Moroni)
12. ኮንጎ ሪፐብሊክ — ብራዛቪል (Brazzaville)
13. ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ — ኪንሻሳ (Kinshasa)
14. ኮት ዲቯር — ያሙሱክሮ (Yamoussoukro)
15. ጅቡቲ — ጅቡቲ (Djibouti)
16. ግብፅ — ካይሮ (Cairo)
17. ኢኳቶሪያል ጊኒ — ሲዩዳድ ዴ ላ ፓዝ
18. ኤርትራ — አስመራ (Asmara)
19. ኢስዋቲኒ — ምባባኔ (Mbabane)
20. ኢትዮጵያ — አዲስ አበባ (Addis Ababa)
21. ጋቦን — ሊብሬቪል (Libreville)
22. ጋምቢያ — ባንጁል (Banjul)
23. ጋና — አክራ (Accra)
24. ጊኒ — ኮናክሪ (Conakry)
25. ጊኒ-ቢሳው — ቢሳው (Bissau)
26. ኬንያ — ናይሮቢ (Nairobi)
27. ሌሶቶ — ማሴሩ (Maseru)
28. ላይቤሪያ — ሞንሮቪያ (Monrovia)
29. ሊቢያ — ትሪፖሊ (Tripoli)
30. ማዳጋስካር — አንታናናሪቮ (Antananarivo)
31. ማላዊ — ሊሎንግዌ (Lilongwe)
32. ማሊ — ባማኮ (Bamako)
33. ሞሪታኒያ — ኑዋክሾት (Nouakchott)
34. ሞሪሺየስ — ፖርት ሉዊስ (Port Louis)
35. ሞሮኮ — ራባት (Rabat)
36. ሞዛምቢክ — ማፑቶ (Maputo)
37. ናሚቢያ — ዊንድሆክ (Windhoek)
38. ኒጀር — ኒያሜ (Niamey)
39. ናይጄሪያ — አቡጃ (Abuja)
40. ሩዋንዳ — ኪጋሊ (Kigali)
41. ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ — ሳኦ ቶሜ (São Tomé)
42. ሴኔጋል — ዳካር (Dakar)
43. ሲሸልስ — ቪክቶሪያ (Victoria)
44. ሴራሊዮን — ፍሪታውን (Freetown)
45. ሶማሊያ — ሞቃዲሾ (Mogadishu)
46. ደቡብ አፍሪካ — ፕሪቶሪያ (Pretoria)
47. ደቡብ ሱዳን — ጁባ (Juba)
48. ሱዳን — ካርቱም (Khartoum)
49. ታንዛኒያ — ዶዶማ (Dodoma)
50. ቶጎ — ሎሜ (Lomé)
51. ቱኒዚያ — ቱኒስ (Tunis)
52. ኡጋንዳ — ካምፓላ (Kampala)
53. ዛምቢያ — ሉሳካ (Lusaka)
54. ዚምባብዌ — ሐራሬ (Harare)
ማሳሰቢያ ለወላጆች
ተማሪዎች ጤ.ሰ.ማ ትምህርትን በተግባር ውጪ ወተው ስለሚሰሩ የስፖርት ትጥቅ እንድታሟሉ በማለት እናሳስባለን።
የት/ቤቱ አስተዳደር
እንኳን ለ2019 አ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያልን የ2019 አ.ም ትምህርት የሚከፈተው መስከረም 4 ቀን 2019 አ.ም ሲሆን
🍇 በእለቱ የክፍል ሃላፊ መ/ራን የት/ ቤቱን ህግና ደንብ ገለጻ ይሚያደርጉና ተማሪዎችም የተመደቡበትን የመማሪያ ክፍል የሚያዩበት ሲሆን
🍇መስከረም 5 ቀን 2019 አ.ም የመጀመሪያው ቀን የመጀመሪያ መደበኛ ትምህርት ለሙሉቀን የሚሰጥ ሲሆን ተማሪዎች አስፈላጊ የመማሪያ ቁሳቁሶችን አሟልተው መገኘት ይኖርባቸዋል።
ከ1ኛ-2ኛ ክፍል የሚያስፈልጋቸው ግበቶች
🍊 8 ደብተር ባለ 50 ሉክ
🍊2 እርሳስ
🍊1 መቅረጫ
ከ3ኛ-6ኛ ክፍል
🍏 9 ደብተር ባለ 50 ሉክ
🍏 1 እርሳስ
🍏 1 እስኪርብቶ
🍏1 መቅረጫ
7ኛ - 8ኛ ክፍል
🍉 12 ባለ 50/ 100 ሉክ ደብተር
🍉 1 እርሳሰ
🍉 1 እስኪርብቶ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን እንገልጻለን።
ለ2018 አ.ም የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ የሚኒስትሪ ውጤት ስለመጣ ነሃሴ 20 ቀን 2018 አ.ም ከጠዋቱ 2:00-6:00 ሰአት ብቻ የምንሰጥ ሲሆን በተጠቀሰው ቀንና ሰአት ተገኝቶ ያልወሰዱትን በሌላ ጊዜ የማናስየናግድ መሆኑን እንገልጻለን።
የመጨረሻ ማሳሰቢያ ለ2019 አ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ ላላካሄዳችሁ የተማሪ ወላጆች በሙሉ
ከላይ ለተጠቀሰው የትምህርት ዘመን የምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ ያሳወቅን መሆኑ ይታወቃል።ነገር ግን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ያልተመዘገቡ ወላጆች መተው በጠየቁት መሰረት ከሃምሌ 15-16 ቀን 2018 አ.ም ድረስ ተጨማሪ 2 የመመዝገቢያ ቀናት የሰጠን መሆኑን እየገለጽን በተጠቀሰው ቀን ውስጥ መታችሁ ያላስመዘገባችሁ የተማሪ ወላጆች በቦታችሁ አዳዲስ ተማሪዎችን መቀበላችንን የምንቀጥል መሆኑን እየገለጽን ሳታስመዘግቡ ቀርታችሁ ቦታው ቢሞላ ሃላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን እንገልጻለን።
የት/ቤቱ አስተዳደር
ለነባር ተማሪ ወላጆች በሙሉ
እንደሚታወቀው ለ2019 አ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዙር ምዝገባ ከሃምሌ 1-6 ቀን 2018 አ.ም ድረስ የነበረ ቢሆንም በአንዳንድ ወላጆች ጥያቄ ምክንያት እስከ ሃምሌ 10 ቀን 2018 አ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑ ይታወቃል።ነገር ግን በተራዘመው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ያልተመዘገባችሁ እንዳላችሁና አንዳንዶቻችሁም ሌላ ት/ቤት መሸኛ ሳትወስዱ ምዝገባ የፈጸማችሁ እንዳላችሁ የደረስንበት በመሆኑ ከሰኞ ሃምሌ 13 ቀን 2018 አ.ም ጀምሮ በቦታችሁ አዲስ ያመለከቱ ተማሪዎችን የምንቀበል መሆኑን እንገልጻለን
ማሳሰቢያ: ነባር የተማሪ ወላጆች ቦታው ከሞላ በኋላ መታችሁ ብታመለክቱም የማናስተናግድ መሆኑን በአክብሮት እንገገልጻለን።
Repost from አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
+1
የ2019 የትምህርት ዘመን የአዳሪ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ቅበላ ውድድር
ማስታወቂያ
(ሀምሌ 9 /2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ትምህርት ቢሮ የገላን የወንዶች እና የእቴጌ መነን የልጃገረዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በየዓመቱ 7ኛ እና 9ኛ ክፍልን በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል በከተማ አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በማወዳደር ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
በ2018 ትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተምረው ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ 7ኛ እና 9ኛ ክፍል የተዘዋወሩ ተማሪዎች ለወንድ ተማሪ በገላን የወንዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሁም ለሴት ተማሪ በእቴጌ መነን የልጃገረዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አወዳድሮ በ2019 ዓ.ም ቅበላ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች በአዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ለመግባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
1. በ2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በማስተማሪያ ቋንቋ በአማርኛ ወይም በአፋን ኦሮሞ በመማር ላይ የነበረ/ች፤
2. በ2018 ዓ.ም በ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አማካኝ /Average/ ውጤት 80% እና በላይ፤ እንዲሁም በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አማካኝ/Average/ ውጤት 80%ና በላይ ያስመዘገበ/ች
3. በ2018 ዓ.ም ከሚማሩበት ትምህርት ቤት ምንም ዓይነት የስነ-ምግባር ችግር እንደሌለባቸው ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፤
4. በትምህርት ቤቱ በልዩ ልዩ ተጓዳኝ ክበባት በንቃት ተሳታፊ የሆነ/ነች፤
5. 7ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች የ5ኛ ክፍል ውጤት አማካኝ ውጤት 80% እና በላይ ሆኖ በሒሳብ ትምህርት ዓይነት አማካ
1️⃣/የኮተቤ ሳይንስ ሸርድ የትምህርት እድል
⬇️⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76/5877?single
2️⃣/የገላን የወንዶች አዳሪ እና የእቴጌ መነን የልጅ አገረዶች አዳሪ ት/ቤት የት/ት እድል
⬇️⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76/5879?single
https://t.me/dam76/5880
🔠🔠🔠🔠
🔠🔠🔠
Our Channel
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76
